cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ማለዳ

ካነበብኳቸው መጣጥፎች እነሆ Join us https://t.me/aaabbbeeelllaaa

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
459
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Share 'በሳንፍራንሲኮ የሚገኘዉ.txt'
Показати все...
በሳንፍራንሲኮ የሚገኘዉ.txt0.02 KB
ሕሊና እንጂ መልክ አያስብም፡፡ አንደበት እንጂ መልክ አይናገርም፡፡ መልካምነት እንጂ መልክ ከሰው አያኖርም፡፡ ስነ ምግባር እንጂ መልክ አያስከብርም፡፡ እምነትና ፍቅር እንጂ መልክ ሞትን አያሻግርም፡፡ መልክ የላይ ማንነትን እንጂ የውስጥ ሰብእናን አይገልጥም ፡፡ ፊት ቀልቶ ውስጥ ሊጠቁር፣ ውጪ አጊጦ ልብ ሊቆሽሽ ይችላል፡፡ እውነተኛ ፍቅር በአይን ሳይሆን በልብ ነው
Показати все...
☯ናስሩዲን ከተከታዮቹ ጋር በአጀብ ሆኖ በአንድ የገበያ ስፍራ ያልፋል። ምንም ነገር ቢያደርግ ተከታዮቹ የሚያደርገውን ይደግማሉ። ጥቂት ራመድ ይልና እጆቹን ሰቅሎ ይወዘውዛል፣ ዝቅ ብሎ እግሮቹን ይነካል፣ ወደላይ እየዘለለም ይጮሃል። ተከታዮቹም እያንዳንዷን እንቅስቃሴ ሳያዛቡ ይደግማሉ። 🔆ታዲያ አንድ ነጋዴ ወዳጁ " ምን እያደረክ ነው የዱሮ ጓዴ? እነዚህ ሰዎችስ ለምንድነው የምታደርገውን የሚያስመስሉት? " በሚል ይጠይቀዋል ⚜"የሱፊ ሼክ ሆንኩ እኮ! እነዚህ ደግሞ መንፈሳዊነትን ለመለማመድ የተከተሉኝ ተማሪዎቼ ናቸው ። ወደ መንፈሳዊ አብርሆት ይሸጋገሩ ዘንድ እየረዳኋቸው ነው። " ናስሩዲን መለሰ። ወዳጁ ግራ ተጋብቶ ጠየቀ። "አሃ! አብርሆት ላይ መድረሳቸውን በምን ታውቃለህ? 🔆ናስሩዲንም " ያ ቀላል ነው። በየማለዳው ተከታዮቼን እቆጥራቸዋለሁ። ከሰልፉ የጎደሉት በርቶላቸዋል ማለት ነው!" P.S: የናስሩዲን አይነት አሰላፊዎች ሞልተውናል። አሰላፊዎቹ የስሜት ህዋስህን በገዛ አንጎላቸው ያዙታል። ምናለፋህ your conformist being is a humble robot for them. 📍ባላበጀኸውና ባልፈተሽከው ሃሳብ ላይ ተለጥፎ ሰልፍ ውስጥ ራስህን ካገኘኸው "ዘናጭ በግ" ሆነህ ሰዎችን ተከትለህ አትትመም!
Показати все...
💡በጎ ሃሳቦች የስኬታማ ሕይወት ማስፈንጠሪያ ናቸው። ልበ ሙሉነትና ጉልበትን እየሰጡ በራስ የመተማመን ስሜትን ከፍ የማድረግ ሀይል አላቸው። በጎ አስተሳሰብ የማነቃቂያ ሃሳቦች ማለት አይደሉም። ከማንነትህና ፣ ከስብዕናህ ጋር ተሰናስለውና በልክ ተሰፍተው ከሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎችህና ተግባራቶችህ ጋር ተመጣጥነው በልኬት የሚመዘኑ ናቸው። ይበልጥ በጎና ቀና አሳቢ በሆንክ ቁጥር ፣ በሁለንተናዊ ሕይወትህ ይበልጥ ደስተኛና ስኬታማ እንድትሆን ማስቻል አለባቸው። 💎 አሉታዊ አስተሳሰቦችን ደግሞ በተቃራኒው መልኩ ልንረዳቸው እንችላለን። ደካማ ፣ እርባናቢስና ፈሪ እንድትሆን በማድረግ በራስ መተማመንህ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መጥቶ ዜሮ እንዲገባ ያደርጉሃል። አሉታዊ ሃሳብን ባሰብክ ቁጥር በውስጥህ ያለውን የመለወጥና የቀናነት መንፈስ ከእጅህ እንዲወጣ ታደርጋለህ። 💡 በዚህም ተናዳጅና የተከላካይነት ስሜት ይጋባብሃል። በአሉታዊ አስተሳሰብ ውስጥህ መቃኘት ሲጀምር ፍርሀት፣ ተጠራጣሪነትና ሀዘን ውስጥህን እየተፈራረቁ መጎብኘት ይጀምራሉ። ከጊዜ በኋላ ደግሞ ይህ አሉታዊ አስተሳሰብህ ሙሉ በሙሉ ሰውነትህን ይቆጣጠረውና ራስህን ከመጉዳት አልፎ ከሌሎች ጋር ያለህም የርስ በርስ ግንኙነት እስከማበላሸት ይደርሳል። 💎 ከአሉታዊ አስተሳሰብ በተቃራኒው በጎ(አወንታዊ) አስተሳሰብ በአንጻሩ ለአእምሮ ጤናና ለተሻለ የስራና የመንፈስ አፈጻጸም በርን ይከፍታል። 💡ስትኖር ደስተኛና ጤናማ ሕይወት እንዲኖርህ ከፈለግክ በጎ አስተሳሰብህን እያዳበርክ አሉታዊ አስተሳሰብህን ተጠራጣሪ ስሜትህን ከአእምሮህ ጠርገህ ማውጣት እንዳለብህ ይመከራል። መልካም ቀን❤️
Показати все...
🔷የጠቢቡ ሉቅማን ምክር ለልጁ… ልጄ ሆይ፣ በዝምታዬ ተፀፅቼ አላውቅም… ልጄ ሆይ፣ ከጠጣህበት የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ድንጋይ አትጨምር ልጄ ሆይ፣ ምላስህን 'ፈጣሪ ሆይ ማረኝ' ማለትን አለማምድ፡፡ ለፈጣሪ ጠያቂን የማይመልስበት ሰዓታት አሉትና፡፡ ልጄ ሆይ፣ ጥበብ(እውቀት) ምስኪኖችን የነገሥታት ደረጃ አድርሳለች፡፡ 🔶ልጄ ሆይ፣ ከሌላ ሰው እጅ ካለ በሬ በእጅህ ያለች ወፍ ትበልጣለች፡፡ ልጄ ሆይ፣ ከመገረም ጋር አትሳቅ፣ ከማይመለከትህም ነገር አትጠይቅ፡፡ ልጄ ሆይ፣ ሁለት ነገሮችን አታውሳ፤ ሰዎች ወዳንተ ያደረጉትን በደልና፣ ለሰዎች ያደረግከውን መልካም ነገር፡፡ 🔶ልጄ ሆይ፣ በጣም ጣፋጭ አትሁን እንዳትዋጥ፤ መራራ አትሁን እንዳትተፋ፡፡ ልጄ ሆይ፣ ከጥጋብ ላይ ጥጋብ ሆነህ አትመገብ፤ ከምትመገበው ለውሻ ብትጥለው የተሻለ ነው፡፡ ልጄ ሆይ፣ የፈጣሪን ፈራቻ ንግድ አድርገህ ያዘው፤ ትንሽ የማይባል ትርፋማ ሆኖ ይመጣልሀል፡፡ 🔷ልጄ ሆይ፣ አደራህን በብድር ላይ፤ ብድር የቀን ውርደት የማታ ጭንቀት ነው፡፡ ልጄ ሆይ፣ የማይረዳን ከማስረዳት ቋጥኝን ከቦታው ማንሳት ይቀላል፡፡ ልጄ ሆይ፣ ባወከው ነገር እስከምትሰራ ያላወከውን አትማር፡፡ 🔶ልጄ ሆይ፣ መጥፎ ጎረቤት ከከባድ ብረት በላይ ይከብዳል ልጄ ሆይ፣ መራራ ነገሮችን ሁሉ ቀምሻለሁ ከድህነት በላይ መራራ ነገር አልቀመስኩም፡፡ ልጄ ሆይ፣ አንድን ሰው ወንድም ለማድረግ ከፈለክ መጀመሪያ አስቆጣው በቁጣው ጊዜ ካለፍክ... ካልሆነ ተጠንቀቀው፡፡ 📍ልጄ ሆይ፣ በሰው ቤት ውስጥ ከሆንክ ዓይንህን ጠብቅ፤ በስብስብ መካከል ከሆንክ ምላስህን ጠብቅ፤ በጸሎት/ሰላት ውስጥ ስትሆን ልብህን ጠብቅ፡፡
Показати все...
01) ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ! 02) ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ! 03) ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ! 04) አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ! 05) ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ! 06) ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ! 07) ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ! 08) ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ! 09) ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ! 10) ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ሰትሳራ አትሙት ማለት እንጂ! 11) ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ! 12) እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነት ተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት እንጂ! 13) አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትጋጭም ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ! 14) ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ! 15) ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሸልክ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ! 16) አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ ❤ መልካም ቀን😊
Показати все...
ይሄን ያውቃሉ ? በኢትዮጵያ ውስጥ ለ፮(6) ሰዓታት ብቻ የነገሠ ንጉስ አለ ። ንጉስ #አይዙር ይባላል ። ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት በኋላ በሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከ ፯፻፶፱-፯፻፯፪ (759-772) ዓ.ም ሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ የነገሰው ንጉስ #ኦደጎሽ ለ ፲፫ (13) ዓመታት ያክል ሲሆን ከ ፯፻፯፪-፯፻፯፯ (772-777) ድረስ ደግሞ ለ፭ (5) ዓመታት የነገሰው ንጉስ #ድድም ይባላል ። እንግዲህ በነዚህ ንጉሶች መካከል ፯፻፯፪ ላይ የተፈጠረ ክስተት ነው ንጉስ ኦደጎሽ ከንግስናው ወርዶ የተተካው ንጉስ አይዙር ነበር ከ 6 ሰዓት በኋላ ግን ንጉስ ድድም መንበረ ንግስናውን ያዘ ። ያው ዘመኑ ዘመነ መሣፍንት ስለነበር ንጉስ ድድም የንግስናውን ዙፋን እንዴት እንደያዘ ማስረዳት አይጠበቅብኝም ። ለጦማሩ ምንጭ የሆነኝ :- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በክብር በጥራዝ መልክ የተቀመጠው የነገስታት ዜና መዋዕል ነው ። ከፌስቡክ መንደር
Показати все...
አንዱ ከ 12 አመት በኋላ ፍርድ ቤት ይሄድና ጎረቤቱን ይከሰዋል። የክስህ ምክኒያት ምንድነው? ሲባል ''ከዛሬ 12 አመት በፊት አዉራሪስ ብሎ ሰደሰቦኛል!'' ዳኛዉ ፈገግ ብሎ''ጎበዝ ከ 12 አመት በኋላ ስድቡ እንዴት ትዝ አለህ''ሲባል ''ዛሬ አይደል እንዴ አዉራሪስ ምን እንደሚመስል ያየሁት'' ተስፋሁን ከበደ/ፍራሽ አዳሽ መልካም ቀን😊
Показати все...
#ቀኖች በየእለቱ እጅግ የሚያስደንቁን ነገሮች ይፈጠራሉ።በሁሉም ነገር የምንደሰትባቸው ከት ብለን የምንስቅባቸው ዳግም መወለዳችንን የምንናፍቅባቸው ቀኖች አሉ። በጣምም የሚያሳዝኑን እንባ እንባ ሚለንም ቀን አለ እምባ እምባ ማለት ብቻ አደለም ደም እንባ የሚያስነቡ አቁሳይ ማንነት ጋ የተቆራቸኙ በክፉ ማንነት ክፍ ቀን የምንላቸው እለታት የትየለሌ ናቸው። አንዳን ቀኖች ደሞ አሉ በሚገርም ሁኔታ የማናውቃቸውን ነገሮች የምናውቅባቸው በሕይወታችን አዲስ ምን አልባትም አዲስ ምዕራፍ ሊከፍቱልን ምን አልባትም በጎርባጣ መንገድ የዛሉ እግሮቻችንን የሚያሳርፉ ሕይወታች የሚቆጠቁጡ ብሩህ ቀናቶች አሉ። ደግሞ በጣም የሚያናድዱን ነገሮች ሁሉ ባልጠበቅንበት ሁኔታ የሚመሩብን እራሳችንን መቆጣጠር እስከማንችልባቸው ደረጃዎች እምንደስባቸው ቀናቶች አሉ። ከሁሉም ደግሞ ሁሉ ነገር የሚታክተን ኑሮ ሕይወት ትርጉማቸው እስኪጠፋን ሞታችንን የምንመርጥባቸው ቀኖች አሉ። በዚህ ሁሉ ግን ሀቅን ከታጠቅን የማንሻገራቸው ቀኖች አይኖሩንም። መልካም አዳር
Показати все...
ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች በቅድሚያ እንኳን ለኢድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ እያልን እስኪ ከበአል ጋ ያላችሁን ገጠመኝ በዉስጥ መስመር ጀባ በሉን። በድጋሚ መልካም በአል @Enatu16
Показати все...