cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

THE REASON WHY I AM HERE ( اسبب وجودي )

Bio እዚህ ቻናል ላይ የሚለቀቁትን እያንዳንዱን post መረዳት አይጠበቅባችሁም ነገር ግን ለናንተ ተመርጦና ለናንተ ተብሎ የተዘጋጀውን መርጣችሁ ታነሱት ዘንድ አላህ ይህንን መንገድ አመላከታችሁ። እዚህ የተገኛችሁበት ምክንያት አላችሁ። : : : :ለማንኛውም አስተያየት @thereasonwhyiamherebot

Більше
Ефіопія10 974Мова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
245
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

🌸 በኸይር አመላካቹ የሰሪው ያህል ነው 🌸 አንድ ሰው በስራ መዝገቡ ላይ ያልደከመባቸው መልካም ስራዎች ምንዳ ተፅፈው ማግኘቱ ምንኛ ያስደስተዋል?! ሌሎች በሰሩት በጎ ስራ ሚዛኑ ተሞልቶ ማግኘቱ ምንኛ ያስደምመው?! ከሙታን ተርታ ተሰልፎ አፈር ከለበሰ በኃላ የጀነት ውስጥ ደረጃው መጨመሩ ምንኛ ልቡን ይሞላው?! ይህ ሁሉ የሚሆነው መንገድ የሳቱትን አመላካች ሆኖ በአላህ (ሱ.ወ ) የተቀጠረ ከሆነ ነው። ደመወዙ የሚከፈለው በአኼራ ይሆናል። የፊርደውስ ነዋሪነት ከነብይ ወይም ከሶሀብይ አሊያም ከሸሂድ ጉርብትና ጋር ። @thereasonwhyiamhere
Показати все...
👆👆👆 If u wanna know more go n subscribe now
Показати все...
✍ ኢብኑል ቀይም አል ጀውዚ እኝዲህ ይላሉ፦ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያን (አላህ ይዘንላቸውና) በአንድ ወቅት እንዲህ ስል ጠየኳቸው፦ ለአንድ ባራያ ይበልጥ የሚጠቅመው ተስቢህ አላህን (ማወደስና ማጥራት ) ነው ወይስ ኢስቲግፋር (አላህን ይቅርታ መጠየቅ)? እርሳቸው እንዲህ አሉ፦ ልብስ ንፁህ ከሆነ ሽቶ መቀባቱ ጠቃሚ ነው፣ ልብሱ ቆሻሻ ከሆነ ግን የሚጠቀመው ትኩስ ውሀና ሳሙና ነው። ከዚያ እንዲህ ሲሉ ጨመሩ፦ ልብስ መቼም ቢሆን ከቆሻሻ ይፀዳል እንዴ?! @thereasonwhyiamhere
Показати все...
ሀብት ማለት የገንዘብ ሀብት ብቻ አይደለም። ይልቁንስ አንተ ያለህና ሌሎች ያጡት ነገር ሁሉ ላይ ሀብታም ነህ። ጤንነት፤ እውቀት ጥበብና ሌሎችም ኒዕማዎች ሁሉ ሀብት ናቸው። ጤነኛ ሰው ከጤናው ሰደቃ ይስጥ እንደዚሁም አዋቂ ከዕውቀቱ ፣ ጥበበኛ ከጥበቡ ይመፅውት። ባለትሩፋት ሁሉ ከትሩፋቱ ሊሰጥ የተገባ ነው ። በዚህ መልኩ ስንመዘገብ ካለው ሀብት የማያካፍል ሁሉ ስስታም ይሰኛል። ካለው ኒዕማ ያካፈለ ሁሉ እጅግ ቸር ማለት እርሱ ነው። በደጋጎቹ ገበያ ላይ የሚዘዋወረው ገንዘብ መልካም ስራ ነው። የእነርሱ ዋና ካፒታልም ይኸው ነው። መከላከያ ጋሻቸው፣ መጠጊያና መሸሸጊያቸውም እሱው ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፦ ወንድምህ ፊት ፈገግ ማለትህ ሰደቃ ነው፣ በጥሩ ነገር ማዘዝህና ከክፉ ነገር መከልከልህ ሰደቃ ነው፣ መንገድ የጠፉውን ሰው መምራትህ ሰደቃ ነው። ድንጋይ፣ እሾህና አጥንት ከመንገድ ማስወገድህ ሰደቃ ነው፣ ከአንተ ባልዲ ወደ ወንድምህ ባልዲ ውሀ መገልበጥ ሰደቃ ነው። (ቡኻሪና ቲርሚዚ) @thereasonwhyiamhere
Показати все...