cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Faaruu Ortodoksii tawahido

Nagenyi Waaqayyoo isiniif haata'u koottaa wajjin faarfanna matti Waaqayyoo

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
562
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Ineho bot ye felegachutini tiyake teyiku inimelisaleni hulachumi start inditilu be igzabiri sim inasasibaleni @mezmur_orthodoxbot @mezmur_orthodoxbot @mezmur_orthodoxbot
Показати все...
Ye tewahido Niku ke betekirstani goni inihin
Показати все...
#ጀሃድ_አወጁ!!☝️☝️☝️ ሁላችሁም ኦርቶዶክሳዊያን ይሄነን ቮይስ ስሙ!☝️ እኛ እራሳችሁን እንድትጠብቁ እና እንድትጠነቀቁ እንጅ ግደሉ ሚል አምላክ ስለሌለን እንደ እነሱ ገጀራ አናነሳም! የክርስቲያን ዝርያት በሙሉ የተዋሕዶ ልጅ ሆነ ፕሮቴስታንት የሆነ ሁሉ ይዳረስ ይስማ በክርስቲያን ላይ በሙሉ ነው እያወጁ ያሉት! ማንኛውም ሰው በቴሌግራም አካውንት ላለው ኦርቶዶክስ በሙሉ ሸር ያድርግ!!! ለበለጠ መሰል መረጃዎች በቴሌግራም ሊንኩን በመጫን ተ #ዲ ን እሱባለው✍(ሥሙር) ¶¶¶ ልዩ ልዩ የሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርቶች ፣መዝሙሮችን ፣ ግጥሞችን የሚፈልጉትን የመፅሐፍ ቅዱስን ቃል ያገኛሉ • • • • ለመቀላቀል ለሌላም ሰው ለማጋራት👇👇👇 🇪🇹ኢትዮጵ🇪🇹 @KIDUS017
Показати все...
3.80 KB
ሕማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ። በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦ 📖ሰኞ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፦ በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል። አንጽሖተ ቤተመቅደስ ይባላል፡- ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና። 📖ማክሰኞ የጥያቄ ቀን ይባላል፦ ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል። የትምህርት ቀን ይባላል፡- በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪። 📖ረቡዕ ምክረ አይሁድ ይባላል፦ ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል። የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፡- ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል። የእንባ ቀን ይባላል፡- ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። 📖ሐሙስ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። የምስጢር ቀን ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድህነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። 📖ዓርብ የስቅለት ዓርብ ይባላል፦ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል። መልካሙ ዓርብ ይባላል፡- ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል። 📖ቅዳሜ ቀዳም ስዑር ትባላለች ፦ ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል። ለምለም ቅዳሜ ይባላል፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡- ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል። አምላካችን በረድኤት ጠብቆ ለብርሐነ ትንሳኤው ያድርሰን! አሜን https://t.me/dnhayilemikael
Показати все...
አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

#መሰረታዊ_የቤተክርስቲያን_ክርስቲያን_ትምህርት / #የተለያዩ_ተከታታይ_ትምህርት ' #ስንክሳር_የቅዱሳን_ገድል_በየዕለቱ ! #ስዕለ_አድህኖ ! #ምስባክ #የየበአላቱ_ዋዜማና_ሥርተ_ማህሌት #መዝሙር #ግጥም #ለመናፍቃን_ጥያቄ_መልስ እና የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሁፎች ይለቀቁበታል Administration @DnIsraelYeArsemaLije

08:47
Відео недоступнеДивитись в Telegram
Faaruu Gaabbii Ortodoksii Tawaahidoo Afaan Oromoo «Yoomuu hin dagatamu» F/taa D/n Mirkanaa Biraanuutiin Channel keenya Telegram join taasifadhaa 👉 @Ortodoksii12
Показати все...
17.66 MB
#ቅድስት፤ #ሁለተኛው_የዐቢይ_ጾም_ሳምንት እንኳን አደረሳችሁ ሁለተኛው ሰንበት፦ቅድስት ይባላል፡፡ ✥"""""""""'''''''"'''''''''''''''''''''''""''''''''''"""''''''''''''"""""""""✥ #ቅድስት ማለት፦የተቀደሰች የተለየች » ማለት ነው፡፡ ይህ ሳምንት ‹‹ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ፠ ✥በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት ለ40 ቀን ጌታችን ጾም የጀመረበት ሳምንት ስለኾነም፤ ቅድስት ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡ ፠ ✥‹‹የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፡፡›› /#ዘዳ፣ 20÷8/ ይህን ቃል እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት ሙሴ ላይ አድሮ ተናግሮታል፡፡ ‹‹ዕረፍባት›› ያለው እግዚአብሔር የፍጥረቱን አቅም ስለሚያውቅ ነው፡፡ ስናከብር ለነፍስ ዕረፍትና ፍስሐን፤ ለሥጋ በረከት ሊያሰጡ የሚችሉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም የሚከበር ነው፡፡ በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት /በመማር/፣ ንሰሐ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል፣ የተጣላ በማስታረቅ፣ ያዘነ የተከዘ በማረጋጋት በማጽናናት የታሰረን በመጠየቅ፣ በችግር የወደቁትን በመጎብኘት በአጠቃላይ #በማቴ 25፥35-37 ላይ የተጠቀሱትን ምግባራት በመፈጸም ከተከበረ ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያልቅ ዘላለማዊ በረከትን ያስገኛል፡፡ #ኢሳ 56÷4-8 ይህችን ዕለት የናቁ ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል፡፡ ( #ዘኁ ፣15÷32-36)፡፡ ፠ ሰንበትን እንደምናከብረው ኹሉ በየ49 ዓመታት ደግሞ እንኳን ሰው መሬትም ከሚያርሱባት እንድታርፍ ኢዮቤልዩ አድርጎ ሰጥቶናል፤ መሬትን ያለ እረፍት ከዘራንባት ፍሬ አትሰጥምና፡፡ ፠በተጨማሪም በዚህ ሳምንት ቅዱስ ኾኖ ቅዱሳን ኹኑ ብሎ ያስተማረው የጌታችን ትምህርት የሚታሰብበት ሳምንትም ነው፡፡ #የዕለተ_ሰንበት_ክብር ፤ 1. ✥በብሉይ ኪዳን፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከስራው ኹሉ አርፎበታል፡፡ ( #ዘፍ 2፥3፣ ዘጸ. 20፥8) 2. ✥በሐዲስ ኪዳን፤ ጌታችን የተጸነሰባት፣ ትንሣኤውን የገለጠባት፣ ለሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅድስ የሰጠባት፣ ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣባት....ወዘተ ናት፡፡ በአጠቃላይ ታላላቅ ሥራዎችን የሰራበት በመሆኗ ከሌሎች ቀናት ለይተን እናከብራታለን፡፡ 3. ✥ከምጽአት በኋላ ሌሎች ቀናት ሲያልፉ ዕለተ ሰንበት ባለማለፏ ለዘለዓለም ጸንታ በመኖሯ ነው፡፡ /#ድርሳነ ሰንበት/ ምዕ 18፥3-7 በዕለተ ምጽዓት ከማያልፉ ነገሮች መካከል ቃሉ፣ ዕለተ ሰንበት፣ የሰው ልጅ ናቸው፡፡ ዛሬ ዛሬ የኀጢአት ሥራ ኹሉ ቀን ተለይቶ የሚፈጸመው (ዝሙት፣ ሴሰኝነቱ፣ መዳራቱ፣ ዘፈኑ) ወዘተ በዚች ቅድስት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ይህን ኀጢአት ቅድስት በምትኾን በእለተ ሰንበት፣ በሰሞነ ሕማማት፣ የሚፈታም ወዮለት›› ይላል፡፡ /መጽሐፈ ፍትሐ ነገሥት/፤ የባልና ሚስት ሩካቤ ኃጢአት ባይሆንም በማይገባ ወቅት ይልቁንም በዕለተ ስንበት በሰሞነ ሕማማት በረቡዕና ዐርብ ከተፈጸመ ኃጢአት ነው፡፡ #ኢሳ ፣ 58÷13-14 ‹‹ፈቃድህን በተቀደሰው ቀን ከማድረግ እግርህን በሰንበት ብትመልስ፣ የሰንበትንም ደስታ እግዚአብሔር የቀደሰው ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህን ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፣ በዚህ ጊዜ በእግዚአብሔር አፍ ተናግሯልና›› #ሮሜ፣ 14÷16 ‹‹ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል›› በማክበራችን ከእግዚአብሔር የምንቀበለው ዘላለማዊ ዋጋ ክብር አለና፡፡ ባለ ማክበራችን ደግሞ ቅጣት ጉዳት አለና ነው፡፡ ሰንበትን በሚገባ ለማክበር ቸሩ አምላክ ይርዳን፡፡ ጾም ፀሎታችንን እግዚአብሔር አምላክ ይቀበልልን ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን! የበርከት ሰንበት ያድርግልን አሜን ፫ Join @mezmur_orthodox
Показати все...
#ሰንበተ_ክርስትያን በኩር ናት የበዓላት ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት በእሷ ደስ ይበለን በሰንበተ ክርስቲያን በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና መልካም ስራ የሚሰራባት ሰንበት ቅድስት ናት እና ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት እግዚአብሔር ይህን ሰጠን ደስ ይበለን በሰንበት #አዝ ለአብርሃም ተገልጣለች ለሙሴም በደብረ ሲና በነቢያት የታወቀች ሰንበት ዳራዊት ናት እና በሳምንቱ ሰለጠነች ተሰበከች በሐዋርያት ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት ተሰጠችን ልናርፍባት #አዝ በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ ውዳሴያችን ይሰማልን ከምድር እስከ እዮር እራማ #አዝ እግዚአብሔር አብ የባረካት እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት ከእለታት ሁሉ መርጦ መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት በእርሷ ሀሴት እናድርግ እናክብራት እንድንከብር የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ @mezmur_orthodox
Показати все...
#ቅድስት.mp32.45 MB
08:33
Відео недоступнеДивитись в Telegram
🔴 #አዲስ_ዝማሬ "ምናል ብታስተምረን" ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ @mezmur_orthodox @mezmur_orthodox
Показати все...
_አዲስ_ዝማሬ_ምናል_ብታስተምረን_ዘማሪት_ሲስተር_ሕይወት_ተፈሪ_pVYAPWiy6qE_134.mp48.21 MB
​​🕯 ዜና እረፍት 🕯 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አራተኛ ፓትርያሪክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ። ​​➫ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ - በፊት ስማቸው አባ ዘሊባኖስ ፈንታ የሚባሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በጎንደር ክፍለ ሀገር በደብረ ታቦር አውራጃ በአለታ ወረዳ አረጊት ኪዳነ ምሕረት በተባለችው ገዳም ሰበካ፣ ልዩ ስሙ ማር ምድር በ1930 ዓ.ም.፣ ከብላታ ፈንታ ተሰማና ከወ/ሮ ለምለም ገሰሰ ተወለዱ፡፡ - ማዕርገ ምንኵስናን በጣና ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ በመግባትከመምህር ኃይለ ማርያም(በኋላ የባሕር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ መልአከ ገነት) በ1961 ዓ.ም. የተቀበሉ ሲሆን፣ በዚሁ ዓመት ማዕርገ ቅስናን፣ ከጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል፡፡ - ባላቸው በቂ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀትና ባሳዩትም የመንፈሳዊ አገልግሎትና የሥራ ወዳድነት፣ ቤተ ክርስቲያኗ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም. ባደረገችው የ13 ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ፣ በካህናትና በምእመናን በከፍተኛ ድምፅ ተመርጠው የኦጋዴን አውራጃ ኤጲስ ቆጶስ ኾነው ተሾመዋል፡፡ - ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በ1971 ዓ.ም. ወደ ጎንደር ሀገረ ስብከት ተዛውረዋል፡፡ - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ 4ኛ ፓትርያርክ ኾነው የተሾሙት፣ ነሐሴ 29 ቀን 1980 ዓ.ም. ሲኾን፣ በፖሊቲካዊ ግፊትና ጫና መንበራቸውን ለቀው ከሀገር ከመውጣታቸው በፊት እስከ ነሐሴ 28 ቀን 1983 ዓ.ም. ድረስ ለቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ አመራር ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ - ከ26 ዓመታት ስደት በኋላ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ በስሙ በተሠየሙበት በሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብረ በዓል ወደ ቅድስት ሀገራቸው ኢትዮጵያ መመለሳቸውን፣ ይታወቃል፡፡ - አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከቀናት በፊት ህመም አጋጥሟቸው በሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን ዛሬ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተነግሯል። በረከታቸው ይደርብን 🙏
Показати все...
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን ✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11     ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥ ውብ መልእክት ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥ ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አረፈዳችሁ፤ የተዋህድ ልጆች 🕹 አንድ ሀብታም ሰው መስኮቱን ተመለከተና አንድ ድሃ ሰው አንድ ነገር ከቆሻሻ መጣያው ውስጥ ሲመርጥ አየ ... እርሱም እንዲህ አለ ✍"ተመስገን አምላኬ ድሀ እንኳ አልሆንኩ አለ"። 🕹 ድሃው ሰው ዘወር ብሎ ተመለከተና ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ ሰው አየ ... እርሱም እንዲህ አለ ✍"ተመስገን አምላኬ እብድ እንኳ አልሆንኩ አለ"። 🕹 እብዱ ሰውየ ወደ ፊት ተመለከተ እና አንድ አምቡላንስ አየ አምቡላሱን ላይ በሕመም ምክንያት የሚሰቃይና የሚያለቅስ በሽተኛ አየ... እርሱም እንዲህ አለ ✍" ተመስገን አምላኬ በሽተኛ እንኳ አልሆንኩ አለ"። 🕹 ከዚያም የታመመው ሰውየ በሆስፒታል ውስጥ የሞተውን ሰው ሬሳ ተመለከተ ... እርሱም እንዲህ አለ " ✍ተመስገን አምላኬ እንኳን አልሞትኩኝ ምክንያቱም የሞተ ሰው እግዚአብሔር አያመሰግንምና አለ"። 🕹 ዛሬ ስለ ሁሉም የእግዚአብሔር በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም ❓ሕይወት ምንድን ነው 🕹 ህይወት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ 1. ሆስፒታል 2. እስር ቤት 3. መቃበር ቦታ 🕹 በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ። 🕹 በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ። 🕹 በመቃብር ውስጥ ሕይወት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ትገነዘባለህ። 🕹 የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው። 🕹ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ ሁን፤ ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን። #መልካም #ቀን #ቸር #ያውለን ✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝                ወስብሐት ለእግዚአብሔር                     ይቆየን @mezmur_orthodox
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.