cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

𝕪ᴏu㋛︎

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
381
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

እንዲህ እያወሩ ሰውየው ቤት ደረሱ። ፨ ዶክተሩ ውይ እነ አስሚም መጡ በቃ እንግዲህ ጋሼ እንገነኛለን አሁን ወደ ቤት እንመለስ። ሰውየውን ሁሉም ተሰናብተዋቸው ወደ እነ ዕዝራ ቤት ተመለሱ። ዕዝራ በጣም ደከመኝ በቃ ልተኛ ብሎ ክፍሉ ገባ። ዕዝራ ልክ ክፍሉ ከገባ ከደቂቃዎች በኋላ። ስሙኝ አሁን ይህንን ወረቀት ከፈቼ ለሁላችሁም አነብላችኋለው። የዕዝራ እናት "ልጆት ከተኛ ሄደው ከማንበቤ በፊት ይዩት" ሲላቸው ተነስተው ሄደው በሩን በቀስታ ከፈተው አዩት ዕዝራ ተኝቶል። ወደ ሳፈው ሄደው እየተቀመጡ "ተኝቷል" አሉ። ዶክተሩ ጥሩ ብሎ ወረቀቱን ኋላ ኪሱ አውጥቶ ዘረጋግቶ ማንበብ ጀመረ። ፨፨፨፨፨፨፨፨ ችምችም ካለው ጫካ ችምችም ካለው ጫካ እኔናአንቺ ሆነን ፍቅር ስንሻማ ፍቅርን ተከናንበን የሆነ አይነት ደስታ ደስ የሚል ስሜት ዛፎች አሸብሽበው ሲዘምሩ አዋፋት ትዝ ይልሻል ይታወስሻል እኔ እንደኔ አረሳውም ያንን ጊዜ ያንን እለት ትዝ ይለኛል ቀን ከለሊት ኡፍፍፍ ኡፍ ኡፍፍፍ ቃል ጠፋብኝ ሁሉ አቃተኝ ዛሬ የለሽም ካፈሩ ላይ ተኝተሻል አልፈልግም ይህን ማስተዋል ለምን ተኛሽ ለምንስ ሞትሽ ለምን መጣሽ ለምንስ ሄድሽ ይጨንቀኛል የት ናት የሚል ሰው ሲመጣ ብነግራቸው አንዳች ለውጥ ላያመጣ ስተነፍስ አተነፍስ እኔ ስስቅ እሷ አትስቅ እኔ ሳለቅስ እሷ አታቅስ ኧረ በስማም ኧረ በውልድ ይህ ፍቅር ውስጥ ሲያነድ ሞትሽ አልልም ካፌ አይወጣም ይከብደኛል ያስፈራኛል ግን ይህሞት ቅኔ ካለው ፍቺው የእሱ ነው እሱ ይፍታው በስማም ሲባል የማይጠፈ በወልድ ሲባል የማይጠፈ አንቺ ግን ለምንስ ሄድሽ አንቺ ግን ለምንስ ሞችሽ ሞች ስለሆንኩ እንዳትይኝ እንደ ልማድሽ ዝም በይኝ" ፨ ዶክተሩ ይህንን ካነበበ በኋላ በሀሳብ ነጎደ ክፍል 19 (አስራ ዘጠኝ) ይቀጥላል........
Показати все...
መጣው" ብሎ ክፍሉ ገባ። ፨ ዕዝራ ጆኬቱን ደረቦ ከክፍሉ ወጣ። እናቱ "እኔም እመጣለው" አሉ። ዕዝራም "አዎ እማማ ነይ አንቺም አለ። ሁሉም ተሰብስበው ወደ ሰውየው ሄዱ። የሰውየው መኖሪያ ቦታ ሲደረሱ ዕዝራ "ጋሼ ጋሼ " አለ። "አቤት ማነው" ብለው ወጡ። ዕዝራም " ጋሼ እንዴት ኖት ይሄው ቤተሰቦቼን በሙሉ ይዤያቸው መጥቻለው" አላቸው። ሰውየው ከቤታቸው ወተው "ሰላም ለእናንተ ይሁን ስጠብቃቹ ነበር እንደምትመጡ እረግጠኛ ነበረኩ" አሉ። የዕዝራ አባት ግራ ተጋብተው "እንዴት ሆኖ ነው እረግጠኛ ሊሆኑ የሚችሉት" ሲሏቸው ዶክተሩ በቀስታ ወደ አስሚ ጆሮ ጠጋ ብሎ "አስሚ አንቺ እና ዕዝራ ትንሽ ዞር ዞር ብላቹ አየር ተቀበሉ ዕዝራን አዝናኚው ስንጨረስ እንደውላለን ዕዝራ ስናወራ መስማት የለበትም ላንቺ ሁኒታውን እኔ እነግርሻለሁ እናት እና አባቱ ማወቅ ያለባቸው ነገር አለ " አላት። አስሚ ወደ ዕዝራ ሄዳ " ዕዝራ ና እስቲ ትንሽ ዞር ዞር ብለን እንምጣ ትንሽ ዘና ብትል ላንተም ጥሩ ነው ከሁሉም ጋር ዞር ዞር ብል ያስደብሩኛል ና" ብላ እጁን ያዛ ሄደች። ትንሽ እንደሄዱ ዕዝራ የአስሚን እጅ ጥብቅ አረጎ ያዛት። እረምጃውን እያፈጠነ መጣ የሆነ ሰው ሊፈለም የሚሄድ ይመስል ነበር የአስሚን እጅ በጣም በይበልጥ ጥብቅ አረጎ ያዛት አስሚ ደነገጠች ፣እጆን አመማት፣ ግራ ገባት። ክፍል 18 (አስራ ስምንት) ይቀጥላል...
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ክፍል18
Показати все...
Biz Gitar: ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)biz gitar የቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲ ሳልሳዊ ክፍል 17 (አስራ ሰባት) ፨ ዕዝራ ከብዙ ዝምታ በኋላ መናገር ጀመረ። " ሲማይን እየፈለኳት ነበር። መንገድ ላይ ከቤት የወጣው ቀን እሷን የሚያቃት ሰው ካለ ብዬ እየጠየኩኝ ነበር። በመጠየቄ በዛን ሰአት አንድ አዛውንት ሰውዬ "ና ልጄ" ብለው እጄን እየጎተቱ መሄድ ጀመሩ። እኔም በጥያቄ አጣደፈኮቸው "አባ ሲማይን ያውቋታል? ሲማይ ጋር እየወሰዱኝ ነው? ብዬ ጠየኳቸው እሳቸው ግን አንድም ቃል አልተነፈሱም እጄን ይዘው የሆነ የላስቲክ ቤት ውስጥ አስገብኝ ፀጥ ብዬ ተቀመጥኩ የላስቲኩ ቤት ውስጥ አንድ ልክ እንደ ቆጥ የተራች ፍራሽ አለች። ከአጠገብ ሳጥን አለ። እኔ የቤቱ ጠረዝ ጥቅግ ላይ ያለው ዱካ ጋር ተቀመጥኩ። ሰውየው ምንም አላወሩም። እኔ ግን ሲማይን እየጠበቁ እንደሆነ አስቤ ተቀሙጥኩኝ። በጣም ስጨቀጭቃቸው ችግሬ ምን እንደሆነ ጠየቁኝ። ስለ ሲማይ፤ ስላሳያችሁኝ የሲማይ ቦታ ፤ ሲማይ በሊት ላይ መጥታ እኔን እዳዋራችኝ ግን ማንም እንዳላመነኝ ብቻ ሁሉንም ነገር አስረዳዋቸው። እሳቸውም በእጄ የያዝኩት ምን እንደሆነ ጠየቁኝ የሲማይ ስጣታ እንደሆነ ነገረኳቸው ሲማይ የት ናት ብለው ጠየቁኝ ታቃላቹ ይንን ጥያቄ በጭራሽ አልወደውም አለች! እላለው እና የት ናት ስባል ይጨንቀኛል ከዛ ይልቅ ምን አሳለፋቹ ብባል ጥሩ መልስ ከልቤ እሰጣለሁ ደስ ብሎኝ።" አለ። ፨ዶክተሩ "እኒን ሰውዬ ማግኘት አብን" ሲለው "ዕዝራ አዎ ብትተዋወቁ እኔም ደስ ይለኛል እንደውም ጋሼ እራሳቸው ቤተሰቦችህን ታስተዋውቀኛለህ እያሉኝ ነበር" አለው። አባቱ "እሺ ቆይ ከዛስ" አሉ በጉጉት ዕዝራን እያዩ። ዕዝራ ካቀረቀረቀበት ቀና ብሎ አያቸው አይኖቹ እንባ ላለማውጣት የሚታገሉ ይመስላሉ ደሞም ያስታውቃሉ ግን እንባውን መቆጣጠር ጭራሽ ባለመቻሉ ዘረገፈው። እና "ጋሼ ነገ ወደ ገዳም እሄዳለሁ እዛ አብረን እንሂድና የተወሰነ ጊዜ እራስህን ታረጋጋለህ ፈጣሪ ለጥያቄዎቹ ሁሉ ከሰዎች በበለጠ መልስ ይሰጥሃል አሉኝ። ተስማማው ከእሳቸው ጋር ሰአታትን ካሳለፍኩኝ በኋላ ለሊት ተነስተን ጉዞ ጀመረን። ፨ በቅጥቅጥ መኪና ተጭነን ሄደን። ገዳም ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ቢጨንቁም እየቆየው ስሄድ ግን አለማዊ ህይወቱ አስጠላኝ እራሴን እና ማንነቴን እዛው ገዳሙ ውስጥ ያገኘው ያክል ተሰማኝ አግቺያለውም ከጋሼ ጋር ገዳም ውስጥ ለገዳሙ ገዳምተኞች ከምግብ ሰሪዎች ጋር ማዘጋጀት ጀመረኩ። የሲማይን ስጦታ ሁሌም ከአጠገቤ አለየውም በልብሴ ላይ እንደ ኪስ ሰረቼ በሄድኩበት ይዤው እዞራለው። ብዙ ወራትን አስቆጥሬ ሰላም የሆንኩኝ ያህል ሲሰማኝ ወደ እዝህ ተመለስኩ" አለ። ዶክተሩ "ስለዚህ ሰውየውም አብረው ነው የመጡት?" አለው። "አዎ አብረውኝ ነው የመጡት ኑ እና ቤተሰቦቼን ላስተዋውቆት ስላቸው ቤተሰቦችህን ያለሁበት አምጣቸውና አስተዋውቀኝ ብለውኛል" ሲል ዶክተሩ "ስለዚህ አሁኑኑ ሄደን ለምን አንተዋወቃችሁም" አለ አስሚ " እንዴ ሀኪሜ ይህ ነገር ያን ያክል አስፈላጊ ነው? አጣዳፊስ ነው?" አሉት። ዶክተሩ "ቆይ አንዴ ውጪ እናውራ" አላቸው። "እሺ" ብለው ብድግ አሉ። ዶክተሩ እና የዕዝራ አባት ተከታትለው ወጡ። ፨ የዕዝራ አባት "ዶክተር ምንድነው ችግር አለ እንዴ?" ሲሉት። "ይመስለኛል ዕዝራ አሁንም ድረስ አልተሻለውም ደና ቢመስልም አደለም" አላቸው። "ማለት ዶክተር ምን እያልከኝ ነው ቆይ" ሲሉት። እሱን በዝረዝረ ለማስረዳት እነዛን ሰውዬ ስናገኝ ነው።" አላቸው። የዕዝራ አባትም "እመነኝ ዶክተር ልጄ ወደ እራሱ ተመልሷል ከትናት ወዲያ ከሆነች ሴት ጋር ሲያወራ ነበር" አሉት። ፨ዶክተሩ "በምን ስልክ ስልክ መጠቀም ጀመረ እንዴ" ሲላቸው። "አዎ የመጣ እለት ነው እኔ እራሴ አጋጣሚ አዲስ ሲም አውጥቼ ስለበር ቀፎም ስለነበረኝ የሰጠውት " አሉት። ዶክተሩ ግራ ተጋብቶ " ቆይ ምን እያለ ነው እሺ ምንድነው ሲያወራ የሰማችውት" አላቸው እንዲያስረዱት በጉጉት እያያቸው ። "አባትየው የመጀመሪያ ቀን ልጄ ሲመጣ ከእናቱ ጋር ቤተ ክረስቲያን ሄዶ መጣና ብና ከጠጣን በኋላ ልተኛ ብሎ ገባ። ሊተኛ ሲል ሄጄ ልጄ ድንገት ይህ ካስፈለገክ ብዬ ስልኩን ሰጠውት እና ወጣው እኔም ወደ ስራ ሄድኩኝ እናቱም ተኛች። ፨ከስራ ስመለስ ልጄ ከክፍሉ አልወጣም ነበር። ሰራተኛዋ ቡና እያፈላች እራት ቀረቦ ልንበላ ስንል እናቱ እሱን ለመጥራት ሄደች። እና ወዲያው ተመልሳ 'ናና ልጃችን ሴት እያወራ ነው ና ስማው' አለችኝ እኔም ልክ እንዳንተ ነበር ያላመንኩት በቀስታ ወደ ክፍሉ በር ጠጋ ብለን ማዳመጥ ጀመረን ልጄ "ይገረምሻል ዛሬ በጣም ነው ደስ ያለኝ.... ደሞ አባባ እኮ ስልክ ሰጠኝ.... ሀሀሀሀሀ እና እንዴት አልደሰትም ስታስቢው በጣም ነው እንጂ ደስ ያለኝ.... በቃ አሁን ወደ ሳሎን ልሄድ ነው አታስቢ ስመጣ ከመተኛቴ በፊት አወራሻለሁ ቻው አፈቅርሻለሁ" ብሎ ነበር ያወራው እኛም ቶሎ ከበሩ ገለል አልን ትንሽ ቆይቶ ደስ በሚል ፊት ተመለሰ እራት እየበላን በመሀል ፊቱ በጣም ያበራ ነበር በጣም አልፎ አልፎ ግን ልክ ሲማይን ካጉኘ በኋላ ወደነበረው ድረጊት ይመለሳል ወዲያው ደሞ ይተወዋል። ፨ዛሬ እራሱ ጠዋት ላይ ሳቁን ሰምቼ ወደ መኝታ ቤቱ በረ ጠጋ ስል "አንቺ ደሞ ገዳሙ ውስጥ ያለውን ሰውዬ ነግሬሽ የለ እያወቅሽው...... ያኔ በደብ አልሰማሽኝም ማለት ነው ማለት ነው?.... በጣም ያስቅ ነበር.... ኧረ ጉደኛ ነው እሱ ሰውዬማ በቃ ሻውር ልግባ እና ቤተ ክረስቲያን መሄድ አብኝ ኦ ሳልነግረሽ ትናት ሳሻል ሚዲያ እያየው በጣም ያሳቀኝን ልንገረሽ! የሆነ በጣም ወፋራም ሰውዬ እየሄደ ቀጭኑ ሰውዬ መጥቶ በጥፊ ሲመታው እንዴት እንደተሽከከረ ብታይ...ሀሀሀ ኧረ አለም በጣም ቀልደኛ ሆናለች... ኧረ በቃ ቻው ሰአት ሄደብኝ ቻው አፈቅርሀለው ሁሌም' ብሎ ዘጋው።" እኔም እንዳልሰማው ሆኒ ሳሎን ቁጭ አልኩኝ ቆይቶ ወጥቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደ።" አሉት። ዶክተሩ የዕዝራ አባትም ያበዱ መሰለው ማመን ሁሉ አልቻለም። ፨ ዶክተሩ "በቃ የዕዝራ አባት ነገሩን የግድ ማወቅ አለብን ዕዝራ ከእኛ ተለይቶ በነበረበት ጊዜ ምን እንዳሳለፈ ትክክለኛውን ነገር ማወቅ ከፈለግን ዕዝራ ጋሼ የሚላቸውን ሰውዬ የግድ ማግኘት አብን እረሶም እንደዛው እንደውም አብረን እንሄዳለን ዕዝራ ከፔሸንትነቱ ባለፈ ልክ እንደ ወንድሜ ነው የማየው" ብሎ ቤት ሲገባ ዕዝራ እና አስሚ ሳሎን የሉም ሳሎን ሰራተኛዋ እና የዕዝራ እናት ብቻ ነበሩ። ዶክተሩ "አስሚ እና ዕዝራስ?" አላቸው እናቱን "አስሚ ሽንት ቤት ናት ልጄ ደሞ መጣው ብሎ ክፍሉ ገብቶል" አሉ። ዶክተሩ የዕዝራ መኝታ ቤት ከሳሎኑ አጠገብ ስለነበር ወደ ዕዝራ መኝታ ቤት ጠጋ ብሎ ዕዝራ የሚለውን መስማት ጀመረ። ዕዝራ እያወራ ነው "በጣም ስትናፍቂኝ እኮ ነው ላወራሽ ብዬ ክፍሌ የመጣውት የእውነት በጣም ነው እኮ የምትናፈቂኝ" አለ ዕዝራ። ዶክተሩ ደነገጠ የዕዝራን የቃላት ድረደራ ሲስማ ያልተዋጠላት ነገር አለ። ዶክተሩ "ዕዝራ ዕዝራ" አለው። ዕዝራም "መጣው ዶክተር ብሎ ከክፍሉ ወጣ። ዶክተሩ "በሉ ኑ ዛሬውኑ ሰውየውን ማግኘት አለብን።" አለ። አስሚም መጥታ "ምነው የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ?" ስትል ዕዝራ "ኧረ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ቆይ በቃ
Показати все...
Biz Gitar: ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)biz gitar የቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲ ሳልሳዊ ክፍል 18(አስራ ስምንት) ፨ዕዝራ በፈጥነት መራመዱን ገታውና ቆመ። አስሚ የዕዝራን ፊት አየችው የሆነ የጭንቀት ፊት ይታይበታል የፍጥነት እረምጃውን ቢገታውም የአስሚን እጅ ግን ድብን አረጎ አጥብቆ እንደየያዘው ነው። አስሚ ፈራች በጣም ለብዙ ደቂቃ የአስሚን እጅ አጥብቆ ይዞ ሊለቃት አልቻለም አስሚ እንባዋ ይፈስ ጀመረ። ግን ምንም ነበር ማለት ፈረታለች። ፨ሁሉም የሰውየው ቤት በረዳ ላይ ተሰብስበተው በእየ ድንጋዩ ተቀምጠዋል የዕዝራ አባት ሰውየውን "በሉ አሁን ንገሩን የእስካሁኑ ዝምታ ይበቃል" አሉ። ዶክተሩ ለዕዝራ አባት ዝም እንዲሉ ምልክት ሰጣቸው። ሰውየው "ልክ እንደ ልጆት ኖት ልጆትም ትግስት የለውም" ሲሉት። የዕዝራ አባት ተናደዱና "ቆይ ምንም አልገባኝም እሺ የፈለጉትን ይበሉ ችግር የለውም ግን ንገሩን እየጠበቀን ነው" አሉዋቸው። ሰውየው መናገር ጀመሩ "ከየት ልጀምረላቹ? " ሲሉ የዕዝራ አባት የሆነ ነገር በንዴት ሊናገሩ ሲሉ ዶክተሩ በድጋሜ አስቆማቸው። የዕዝራ አናትም "ልጄ ግልፅ ባልሆነ መንገድ የተወሰ ነገር ነግሮናል እረሶ ግን ከመጀመሪያው ጀምረው ቢገግሩን ደስስስ ይለናል ሁሉንም ነገር እንድናውቅ" አሉዋቸው። ሰውየው "ጥሩ! መልካም" ብለው ጀመሩ። " ጠዋት ከቤተ ክረስቲያን ስመለስ ልጃቹ መንገድ ላይ የሚያልፈውን ሰው ሁሉ ስለ አንዲት ልጅ እየጠየቃቸው ነበር ሁኒታውን ሳየው ልክ አደለም የሆነ አይነት ችግር ያለበት ይመስል ነበር። ሰው ሁሉ መጠቋቆሚያ እና መሳለቂያ አረጎትም ነበር። ጠጋ ብዬ ሳየው እኔንም ስለ ልጅትዋ ጠየቀኝ "ና" ብዬ እጁን ይዤ ወደ እዝህ አመጣውት ስንመጣ መንገዱን ሙሉ ስለ እሷ ሲያወራ እና ሲጠይቀኝ ነበር ምን እንደሆነ ጠየኩት። መጀመሪያ ዝም ብሎ ነበር ከዛ ግን ማውራት ጀመረ። ሲያወራ እጁን ጭብጥ አረጎ ይዞ በእጁ የያዘውን ጊጥ እየሳመ ነበር። ጭንቅ ብሎት አንገቱን ድፍት አረጎ "ሲማይ ስለምትባል ሴት ነገረኝ በፍቅር ታሪኩ በጣም ተገረሜ ነበር ምክያቱም እኔ ከአንድም አምስት ሚስት አግብቼያለሁ ግን ላንዳቸውም ይህ ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም ፍቅሩ ጥልቅ ነበር። በጣም የሚገረም እና የሚደንቅ ፍቅር ያው ስለ ሲማይ ያላብራራውት ለቤተስቦቹ ሁሉ ስለ እስዋ እንደተናገረ ስለተረደው ነው አሉ" የዕዝራ እናት "አዎ ልክ ነው" አሉ። ፨ ዕዝራ የአስሚን እጅ ለቆታል አሁን የሆነ ዞፍ ስር ቁጭ ብለዋል ዕዝራ እያለቀሰ ነው። አስሚ ጭንቀት ላይ ናት ልታባብለው ትልና ከዛ ግን ትተወዋለች። ምንም ቃል አልተናገረም ግን ለቅሶ ውስጥ ብዙ ቃላቶች አሉ። ዕዝራን ማፅናናት በጣም ይከብዳል። እሱን ስለምታውቅ ዝምታን መረጣለች አልቅሶ እስኪወጣለት ድረስ ዝምም አለችው። ወደ አስሚ ዞሮ አስሚን አቅፎ ማለቀስ ጀመረ። አቅፎትም ሲያለቅስ አቀፈችው አስተቃቀፋ ጠንካራ ነበር። አስሚ ሰውነቷ እስኪንቃቃ ድረስ ጥብቅ አረጎ አቀፋት። ዝም አለችው እሷም በስሱ አቀፈችው። ቆይቶ ዝም አለ አስሚንም ለቀቃት። ፨ የስውየው ንግግር ትግስት አስጨራሽ ነበረ። በየመሀሉ ዝም የሚሉት ነገር አለ። ዝምታቸው እዥም ነው። የዕዝራ አባት ሊናገሩዋቸው ሲሉ የዕዝራ እናትና ዶክተሩ ሲያስቆሞቸው ቆዩ። ሰውየው አሁን መናገረ ጀመሩ። "ያው ገዳም ቢሄድ ወደ እረሱ ይመለሳል ብዬ አስብኩኝ ምክንያቱም ሰውነቱም ሆነ ውስጡ በጣም ይንቀዠቀዥ ነበር። ከተገናኘን በኋላ ያሉትን ሰአቶች እሱን ሳዳምጠው ቆየው እንቅልፍ በመሀል አሸነፈን እና ሁለታችንም በየአለንበት ተኛን ብዙ መተኛት አልቻልንም ምክንያቱም ደሞ ወደ ገዳም የመሄጃ ሰአታችን ስለደረሰ። ተነስተን ሄድን ገዳም ከገባን ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ዕዝራ ላይ ያሉ የሰውነት አለመረጋጋቶች ተወገዱ ሰውነቱም ተመለሰ። ገዳም ውስጥ ስራ አለ ዶቤ የሚጋገረበት እንጨት እናመጣለን ክረምት ሲሆን ደሞ በገዳሙ ማሳ ላይ እናረሳለን እንዘራን እንኮተኮታለን ልጃቹ በሚገረም ሁኔታ ጥሩ ለውጥ አመጣ። በሄድን በአንድ አመት ውስጥ ዕዝራ ገዳም ውስጥ የሚገኑ የዘፍ ቀለሞች ምስላድኖች እና ቅረፃ ቅረፆችን ሰራ ሁሉም በጥበብ በጣም ተደነቀ እኔንም ጨምሮ። ከዛ ግን በተለያዩ ክልልሎች ባሉ ገዳማት እየዞረ እናንተ ጋር ከመምጣቱ በፊት ያሉትን ወራት እና መቶች ሁሉ ለገዳማት እየዞረ በመሳል ጊዜውን አሳለፈ ከእኔ ጋር መጀመሪያ በሄደበት ገዳም ውስጥ ለአመት ከሁለት ወራት ከቆየ በኋላ ነው በየ ገዳማት መዞር እና ጥበብን ተጠቅሞ ገዳማትን ማስዋብ የጀመረው። ከአስራ አምሰት ቀን በፊት ወደ እኔ ያለውበት ገዳም ተመልሶ መጥቶ ነበር ከዛ ወዲያው ነው የመጣውት ምክያቱም እሱ እናንተ ጋር እንዳደረሰው ስለፈለገ በገዳሙ ውስጥ አምሰት ቀን አስልፈን ወደ እዝህ ተመለስን እኔ እሱን እየጠበኩት ነበር ለእናንተ የምነገራቹ ነገር ስላለ ነው ቤተሰቦችህን እና የነገረከኝ የራስህ ታሪክ ውስጥ ያሉ ሰዎችን አምጣቸው ያልኩት" አሉ። ዶክተሩ "ይሄው ጠረጥሬ ነበር በሉ ንገሩኝ" አላቸው ለመስማት ጥድፍ ብሎ። ፨ እሳቸውም "ልጆቹ በጣምም የጨነቀው እና የማይፈታ ህመም ይዞታል ውስጡ ያለውን ጥያቄዎች ሁሉ ለመመለስ ደሞ ልክ በእሱ መንገድ ከሚጓዙ ሰዎች ጋር መቀላቀል አለበት" አሉ። ዶክተሩ "ማለት ጋሼ እሱን መስል ሲሉ የሀይምሮ ህመምተኞች ጋር ማለት ነው?" አላቸው። ሰውየው "በትክክል ገብቶሀል እያልኩኝ ያውት እሱን ነው እዛ ብታስገብት መልካም ነው" አሉ። የዕዝራ እናት "አይይ ልጄ አሁን በጣም ጤነኛ ነው እዛ ማስገባት በይበልጥ ልጄን ጨረቁን ጥሎ እንዲያብድ ነው የሚያረገው" አሉ። አባቱም "አዎ ልክ ናት እሱ በጭራሽ አይሆንም ልጃችን እዝህ የሚያደረስ ህመም ላይ አደለም ያለው" አሉ። ዶክተሩ "እኔ ግን ከሁለታችሁም የተለየ ሀሳብ ነው ያለኝ ጋሼ ልክ ናቸው ዕዝራን ትንሽ ቀን እንየው እና ካልሆነ እንወስናለን" አላቸው። ሰውየው "ምረጫው የእናንተ ነው"ብለው ዝም አሉ። ፨ ዶክተሩ አሁን የምፈልገው ነገር ተመልሶልኛል ሁሉንም ነገር ቀስ በቀስ አስረዳችኋለው አለ። ሰውየውም "ጥሩ ባለፈው እናንተ ጋር ሊመጣ ሲጣደፈ ይህ ወረቀት ከእቃው ላይ ወደቀ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ላስቀረው ፈለኩ እና አስቀረውት አነበብኩት የሚገረም ነገር አግኝቼበታለሁ ሊላው ሲሄድ በመንገድ አልፎ አልፎ የሚሰውረው ነገር አለ ሳታሰሰብት ወደ ድሮው ይመለሳል" አሉና ወረቀቱን ለመቀበል እጁን ለዘረጋው ዶክተር ሰጡት። ፨ አስሚ ዕዝራን እያየችው ዕዝራ ነው ዕዝራ ደሞ ጭብጥ ብሎ ተቀምጦ ቆይቶ ተነሳና ወደ አስሚ እጁን ልኮ "ነይ ተነሽ በቃ" አላት። አስሚም እጁን ይዛ ተነሳች። "ወደእነ አባባ እንመለስ አደል" አላት። አስሚ "አዎ እንመለስ"አለችው ፈገግ ብላለት። ዞረው እየተመለሱ ዕዝራ "አስሚ ከዶክተር አኪም ጋር አብራቹ ናቹ" አላት። አስሚ "አዎ ያንተን መምጣት ማለቴ መገኘት እየጠበቅን ነበር እንጂ ልንጋባም ወስነናል" አለችው። ዕዝራ "ጥሩ ነው አንድ ላይ በጣም ታምራላቹ እና መቼ ነው ሰረጉ" ሲላት። "አሁን እንወስናለን" አለችው። አስሚ በጣም ፈረታለች። በድጋሜ ዕዝራ ያንን ማንነቱን እንዳያመጣ ብላ። እጃን ለቆ አቀፋት እና "ታቂያለሽ በጣም ጥሩ እህቴ እንደሆንሽ ይሰማኛል የእውነት ልክ ከአንድ አባት እና እናት እንደተፈጥርን ነው የሚሰማኝ" አላት።
Показати все...
በጣም ደንግጠዋል። ፨የዕዝራ እናት እና አባት ፣ዶክተር ፣ አስሚ ሰብሰብ ብለው ሳሎን ተቀምጠዋ ል። ዕዝራ "እእ በቃ እንዲህ ሰብሰብ ካላቹ አይቀር ከእናንተ ውጪ የነበረኝን ህይወት ልንገራቹ አደል" አላቸው ሁሉም አዎንታቸን ገለፁ። ዕዝራ አንገቱን ደፈቶ እረዥም ሰአት ቆየ። ሁሉም ከዕዝራ በቀር እረስ በእረስ እየተያዩ ነው። ምክንያቱም ለማወቅ በጣም ጓጉተዋል። ሁሉም ልብ ውስጥ ዕዝራ እንዴት ከእዚህ ቀደም የነበረበትን ሁኒታ ትቶ ወደ ቀድሞ ማንነቱ ተመለሰ የሚለው ጥያቄ ጭንቅላታቸው ውስጥ አለ ዶክተሩም ይህ ጥያቄ ውስጡ አለ እሱ ግን የፈራ ይመስላል ግራም ጉብቶታል። ምክንያቱም ዕዝራ ልክ ከሲማይ ከተለየ በኋላ የሚያረጋቸው እንደ ልብስ መብላት፤ የሲማይን ስጣታ ይዟ በስሱ መሳም እና ደጋግሞ ማየት እጆቹን ማፋተግ የሆነ ሀይል እንደተቆጣው ኩምሽሽ ማለት ሁሉ የሉም። ፨እንደ ዕዝራ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያሉ የሀይምሮ ህሙማን በሙያው ብዙ ያውቃል ግን በእዚህ ፍጥነት ሲቀየሩ ችግር እንዳለ ያውቃል ህመሙ ወይም ትንሽ ፕረሰቱ ህሙማን የምረም ተሽሎቸው ሊሆን ይችላል። ሁሉም ግራ የገባቸው እንዴት እንዲህ ደና ሆነ የሚለው ጥያቄ ነው። ለዛም ነው ዕዝራ ስላሳለፋቸው ነገሮች ሁሉ ማወቅ የፈለጉት። ዕዝራ እንዴት በምን ተአምር ነው ወደ ቀድሞ ዕዝራ የተመለሰው በእረግጥ ፊቱ ላይ የተጎዳ ስሜት ይታያል ግን ለውጡም ይገረማል። ሁሉም በጉጉት እያዩት ነው አይናቸውን እረስ በእረስ መተያየታቸውን ትተው ዕዝራ ላይ አፋጥጠዋል። ክፍል 17(አስራ ሰባት)ይቀጥላል.....
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Biz Gitar: ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) biz gitar የቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲ ሳልሳዊ ክፍል 16 (አስራ ስድስት) ፨ የዕዝራ አባት ወደታች ውረደው እናቱን ሲያዩዋት ስልክ ጆሮቸው ላይ አረገዋል። ስልኩን ከጆሮዋቸው ወስደው። "ሄሎ" አሉ። የዕዝራን እናት እያዩ እናቱ እያለቀሱም እየሳቁም ነው። ስልኩ ተዘጋ። የዕዝራ አባት "ምን ሆነሽ ነው? ምን ተፈጥሮ ነው? ልጄ ስትይ ሰማው ልበል?" አሉ። የዕዝራ እናት "አዎ ልጄን ድምፁን ሰምቼዋለው እማማ ብሎ ጠረቶኛል" ሲሉ አባቱ "ተይ ባክሽን አትቀልጂ"ብለው ጥለዋቸው ሄደው ደረጃውን ሊወጡ ሲሉ ስልኩ በድጋሜ ጠራ ተመልሰው መተው አነሱት እናት መሬቱ ላይ ተደፈተው እያለቀሱ ነበር። "ሄሎ" አሉ። "አባባ" አለ የዕዝራ አባት ማመን ሁሉ አቃታቸው። "ልጄ?" አሉት። ዕዝራ "አዎ አባባ ልጅህ ነኝ" አላቸው። አባቱ እንባ እየተናነቃቸው "ልጄ ልጄ ደና ነህ? የኔ አንበሳ የት ነበርክ የት ነህ" አሉት። ፨ዕዝራም " አለው አባባ አለው አባባ ጠዋት አንድ ሰአት ላይ ድሮ ኢለመንተሪ ስማር የነበረበትን ትምህት ቤት እማማ ስለምታቀው እዛ መታቹ ተቀበሉኝ" አላቸው። አባቱ "አምላኬ ተመስገን ተመስገን እሺ ልጄ መጥተን እንቀበልሀለን" አሉት። ስልኩ ተዘጋ ስልኩን እንደዘጉት "የልጄ እናት ነይ እቀፊኝ ደስ ብሎኛል አሉ" የዕዝራ እናትም ተነስተው አቀፏቸው ተቃቅፈው ተላቀሱ የደስታ እንባ የፌሽታ እንባ ተራጩ። ለሊቱ እንደምንም አልፎ 12:25 ላይ ሄደው ዕዝራ ያላቸው ቦታ ተሰይመዋል። መኪና ውስጥ ሆነው ዕዝራን በጉጉት እየጠበቁት ነው። ልክ አስር ጉዳይ ለአንድ ሲሆን ከመኪናቸው ፊት ለፊት ዕዝራ ሲመጣ አዩት። ሰውነቱ ተመልሷል ጥሩ አቋም ያለው ዕዝራ ሆኖል በፊስታል እቃ ይዞል። እንደ ከእዚህ ቀደሙ አይቀጠቀጥም ልብሱንም አይበላም ጉዳቱ ግን እንዳለ ነው ፂሙ ችምችም ብሏል ተጉድቷል። እናትየው በደስታ ዘለው ከመኪናው ወጡና " ልጄጄጄ ልጄጄጄ" ብለው። ተጠመጠሙበት ዕዝራ እቅፍ አረጋቸው። "እማማ" አለ። አቅፎቸው ወደ እሱ በቀስታ እየመጡ ያሉትን አባቱን እያየ። እናቱ አለቀሱ ከእቅፋቸው አስወጥተው አገላብጠው ሳሙት እሱም ሳማቸው። አባቱ እሱ ጋር ልክ ሲደረሱ ዕዝራ "አባባ" ብሎ አባቱን እቅፈ አረጋቸው። አባቱ የዕዝራን ጀረባ መታ መታ እያረጉ እንኳን ደህና መጣህ ልጄ" አሉት። ዕዝራም "እንኳን ደና ቆያችሁኝ አባባ" አለ። ፨ መኪና ውስጥ ገብ እና ወደ ቤታቸው ሄዱ። ቤት እስኪደረሱ ድረስ ዕዝራ እና እናቱ ከኋላ እቅፍቅፍ ብለው ተቀምጠው ነበር። ቤት ደረሰው ወደ ሳሎን ሲገብ ሳሎን ማንም የለም ጠዋት ስለሆነ ሰራተኛዋም እንደተኛች ናት። የዕዝራ አባት ዕዝራን "ልጄ ክፍልክን እናትህ እስክታዘጋጅልህ ለምን እኛ ክፍል እረፍት አትወስድም ሲሉት። "አይ አባባ መጀመሪያ ቤተ ክረስቲያን ልሂድ ስመለስ እታጠባለሁ" ሲል። እናትየው "ልጄ አብሬህ ልምጣ " ሲሉት። "ይቻላል እማማ ነይ ነጠላ ለብሰሽ እጠብቅሻለው" አላቸው። እናትየው ነጠላቸውን ለብሰው መጡ። ቤተ ክረስቲያን ሲሄዱ ዕዝራ ልክ ድሮ እናቱን በመንገድ ሲሄዱ እንደሚያቅፋቸው አቅፎቸው ነበር ከቤቱ በር ጀምሮ የሄዱት። እናቱ ደስ ብሏቸዋል ቤተ ክርስቲያን ሲደረሱ ስርአቱን ጠብቀው ገብ። ገና በጣም ጠዋት ስለነበር ብዙ ሰው አልነበረም። ገብተው አጠገብ ላጠገብ ቆመው ፀሎት አረጉ አስቀደሱ ። ልክ ሲመጡ እንደነበሩት አልነበሩም ምእመናኑ ቤተ ክረስቲያኑዋን ሞልተዋታል። ሰላም ግብ ተብሎ ዕዝራ እና እናቱም ተቃቅፈው ወደ ቤት ተመለሱ። ፨ ቤት ሲደረሱ ቡና ቀራረቦ ቤቱ ሞቅ ሞቅ ብሎ ነው የጠበቃቸው። ቤት ገና ሲገብ ሰራተኛዋን ሰላም ብሏት። "እማማ በቃ ሻውር ልግባ እና እመጣለሁ" ብሎ ወደ መኝታ ቤቱ ገብቶ ቁም ሳጥኑን ከፈቶ ሊበቃው የሚችለው ልብስ ካለ ማየት ጀመረ። የበፊት ልብሶቹ ማለትም ሳይከሳ ሲያረጋቸው የነበሩት ሁሉ ልኩ ነበሩ። ሰማያዊ ቲሸረት እና ቢጫ ቱታ መረጦ አልጋው ላይ አረገ ነጭ ፎጣም አውጥቶ መኝታ ቤቱ ወዳለው ሻውር ቤት ገብቶ መታጠብ ጀመረ። ፨ አስሚ እና ዶክተሩ ከዶክተሩ ቤተሰቦች ጋር የቤታቸው በረንዳ ላይ ብና ተፈልቶ ወጥ ተሰረቶ ሞቅ ሞቅ እያረጉት ነው። ጨዋታቸው ደምቋል ደስተኞችም ናቸው። የዶክተሩ እናት አስሚን በጣም ወደዋታል። ሁሉም ቢወዶትም የእሶቸው ግን በጣም ይለያል። ከጨዋታው መሀል የዶክተሩ እናት ወደ ልጆቸው እያዩ "ልጄ ታዲያ ሰረጉ መቼ ነው ቸኮልሽ አትበለኝና በአንተ በኩል ደሞ የልጅ ልጄን ባይ ደስ ይለኛል አላህ ፈቅዶ አንድ ላይ እንዳረጋቹ እሱ በጥበብ ዘላለም ያኑራቹ" አሉ። አስሚ እና ዶክተሩ "አሜን አሜን" አሉ። የአባትም "እና ልጆቼ ሰረጋችሁን መቼ እንጠብቅ" ሲሉ።ዶክተሩ "አይ አባቴ እሱን አላህ ነው የሚያውቀው አንድ እኔንም እሷንም የሚያሳስበን ነገር አለ እሱ ሲሳካ ሰከንድ አንቆይም" አላቸው። አስሚም "ልክ ነው" አለች። ፨ ዕዝራ ገላውን ታጥቦ ፅድት ብሎ ከእናት እና ከአባቱ ጋር ሰራተኛዋ ያፈላችላቸውን ብና እየጠጣ ነው። በሰሀን ዳቦ ቆሎ እየበላ ነው። የዕዝራ አባትም "ልጄ እስቲ አሁን ተረጋግተሀል የት እንደነበረክ ንገረን" ሲሉት። "እሺ አባባ ግን አስሚ እና ዶክተር የት ናቸው?" አለ። እናቱም "ዶክተር እና አስሚ ትናት ነው እኮ አዳራቸውን እዚህ አረገው ተያይዘው የወጡት" አሉት። ዕዝራ "እና አይመጡም እንደውልላቸዋ" ብሎ ወደ ስልኩ ሄዶ "እእ አባባ የአስሚን ወይም የዶክተረን ስልክ ቁጥር ልትነግረኝ ትችላለህ?" ብሎ የስልኩን እጀታ ጆሮው ላይ አረጎ የአባቱን ቃል መጠበቅ ጀመረ። አባቱም "ስልክ ዝረዝሩ እሱ ጋር ያለ ትንሽዬ ደብተር ላይ አለልህ" አሉት። "ኣ አገኘውት አባባ" ብሎ ከስልክ ዝረዝሮች ውስጥ ስም መፈለግ ጀመረ። አገኘው ዶክተር የሚለውን መጀመሪያ ስላገኘ እሱ ጋር ደወለ አይሰራም ደግሞ ደጋግሞ ቢደውልም ሲሰራ አልቻለም ከስር አስሚ የሚል አለ። በእሷ ቁጥርም ላይ ደወለ ልክ እንደ ዶክተር የእሷም ስልክ የደወሉላቸ ውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም ይላል። ስልኩን ዘግቶ ወደ ነበረበት ቦታ ተመልሶ ተቀመጠ። የዕዝራ እናት "ምንነው ልጄ አያነሱም?" ሲሉት። "አይ እማማ ስልካቸው ጭራሽ አይሰራም በቃ እኔ ልተኛ ዶክተር እና አስሚ ሲመጡ ሁሉንም ነገር እነግራቸዋለው" ብሏቸው ሲነሳ እናቱ "ልጄ ሶስተኛውን አጠጣም" ሲሉት። "ይቅረብኝ እማማ በቃ ሰላም ሁኑ" ብሎ ወደ መኝታ ቤቱ ገባ። "ተመስገን " አሉ። ፨ አስሚ እና ዶክተሩ ጉብኝት ላይ ናቸው። የደሴ ከተማን የዶክተሩ የመጨረሻ ታናሽ ወንድም ነው እያስጎበኛቸው ያለው። በጣም ጥሩ ጊዜ እያሳለፉ ነው። አስሚ ከዶክተሩ እናት ጋር በደብ ተግባብታለች። ደሴን በረገጡ በሳምታቸው የዶክተሩን ቤተሰቦች ተሰናብተው ጉዞቸንውን ወደ አዲስ አበባ አቀኑ። በመንገዳቸው በመሀል በመሀል ዘፈን እየከፈቱ የተቋጠረላቸውን ምግብ እየበሉ ልክ ከቀኑ 7:51 ላይ አዲስ አበባን እረገጡ። ወዴትም አልሄዱም ቀጥታ የሄዱት ወደእነ ዕዝራ ቤት ነበር። የእነ ዕዝራን ቤት አንኳኩት ዕዝራ በረንዳ ላይ ተቀምጧ ነበር። ተነስቶ ከፈተው ልክ አስሚ ዕዝራን ስታየው "እእእ" አለች። ዕዝራ ፈገግ ብሎ አያት ዶክተሩ "ዕዝራ?" አለ። ዕዝራ "እንዲህ እንደምደነግጡ አውቄ ነበር እኮ አስቀድሜ ላሳውቃቹ የደወልኩት አለ። ሁለቱም ግን ዕዝራን የእውነት በአካል በጭራሽ ያዩት አልመሰላቸውም
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.