cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

🐒ጥበብ ዕርቃኗን🐒

የከፍታ እና የዝቅታ ስሜቶች..... በተሰነጣጠቀ መስታወት ምልከታ..... (አንድ ምስል የለም...) እናም የማየው ምስል ሌላው ከሚያየው ይለያል፡ ለዛም ነው ከፍታዬ ዝቅታ ዝቅታዬም ከፍታ የማይሆንበት መንገድ የማይታየኝ... @Booooom01

Більше
Рекламні дописи
202
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

በችግር ጊዜ የሚተባበርን ወዳጅ እንደማግኘት ምን ያስደስታል? በደስታ ጊዜማ መንገደኛስ ቢሆን አንዴ ቆም ብሎ አብሮ ደስታችሁን ይካፈላል፡፡ እናም ይኸው አዳም አለሁ ፡ በእግዜር ፊት ራቁቱን የሆነው አዳም፡፡ በእግዜር ፊት ባዶ የሆንኩት አዳም ይኸው፡፡ ግን ደሞ በናንተ ፊት እራቁቴን ፡ ባዶዬን እንዳልሆንኩ አውቃለሁና ፡ አላፍርም ፡ አልሸማቀቅም ፡ አልሸሸግም፡፡ እናንተም በፊቴ እራቁታችሁን ፡ ባዷችሁን አይደላችሁምና ፡ በፊቴ አትሸሸጉ፡፡ በሰውኛ ፡ ..... የሰው ልጅ በከፋው ወቅት ላይ ፡ በሰው ፊትም እራቁቱን እንደሆነ ይሰማዋል፡፡ እኔ ግን እላችሁዋለው በኔ ፊት ባለግርማ ፡ ሞገሳም ፡ ሙሉ ናችሁ!...... ምንም ያህል ፡ ከፋ የተባለ ነገር አድርጓችሁዋል ተብላችሁ ብትከሰሱም ፡ በሰው ፊት አንገት የምደፉበት ምክንያት የለም፡፡ ስለዚህ በከሳሾቻችሁ ፊት አንገታችሁን ቀና አድርጋችሁ ተጓዙ!!! እኔም እከተላችሁዋለው!! #ምህረት
Показати все...
🥰 2
“Have you ever been in love? Horrible isn't it? It makes you so vulnerable. It opens your chest and it opens up your heart and it means that someone can get inside you and mess you up.” ― Neil Gaiman, The Sandman,
Показати все...
ልጅ እያሁ በጣም እረስ ወዳድ ከመሆኔ የተነሳ ሁሌም የተሻለውን ሁሉ ላራሴ ብቻ እል ነበር ። ከዚያም በዚሁ ባህሪ የተነሳ ባልንጀሮቼ ሁሉ ገፉኝ እኔም ብቻዬን ቀረው ከዛም እኔ ትክክልእንደነበርኩና እነሱ መሳሳታቸውን ነበር እማምነው። አባቴ በህይወት ውስጥ ሶስት ጠቃሚ ነገሮችን አስተምሮኛል አባቴ አንድ ቀን በሁለት ጎድጓዳ ሳህን የተቀቀለ ሩዝ አደረገና መመገቢያ ጠረጴዛ ላይ አደረገ አንደኛው ሳህን ከረዙ ላይ የተቀቀለ እንቁላል ነበረበት ሁለተኛው ደሞ ከላይ እንቁላል የለውም ነበር ከዚያ አባቴ አንዲ አለ ልጄ የፈለከውን ሳህን ምረጥና ብላ አለኝ ያንጊዜ እንቁላል እንዲ እንደዛሬው አልነበረም ብርቅ ምግብም ነበር ለአመትባልና ድግስ ካልሆነ አላገኝም ነበርና እንቁላም ከላዩ ያለብን ወስጄ በምርጫዬ እና በብልጠቴ እየተደሰትኩ መብላት ጀመርኩ እንቁላሉንም ፈርክሼ እየበላው ሳለ አባቴ የቀረውን ሰሀን ለራሱ ወስዶ ሲበላ ከሩዙ ስር ሁለት የተቀቀሉ እንቁላሎች ነበሩ ። ከዚያም ይህን ሳይ በምርጫዬ ተበሳጨው መቸኮሌ አናደደኝ አባቴ እንዲህ አለኝ ልጄ በምታየው ነገር አትሸወድ የምታየው ሁሉ እንዳየኸው አደለም በሰዎች ላይ ብልጥ ሁነህ አትውሰድ አለኝ ። በሌላ ቀንም እንዲሁ አደረገና ምረጥ አለኝ አንዱ ከላይ እንቁላል ነበረው ሌላኛው አልነበረውም እኔም ፈጠን ብዬ ከላዩ ላይ እንቁላል የሌለውን ወሰድኩና መመገብ ቸኩዬ ስገልጠው ከስሩ ምንም አንቁላል አልነበረውም ።በመሸወዴ በጣም ተናድጄ ሳለሁ አባቴ እንዲህ አለኝ ልጄ ሁሌም ካሳለፍከው ተሞክሮ ላይ ተስፋ አትጣል ህይወት ትሸውድሀለች ትላንት ከስር ስለነበር ዛሬ ይኖራል ማለት አደለም አለኝ ።ነገር ግን አትበሳጭ ከዚህ ነገር ትምህርት ውሰድ እንዲህ አይነቱን እውቀት በትምህርት ቤት መፅሀፍት ወስጥ አታገኘውም ከህይወት እንጁ አለኝ ። በሶስተኛ ቀን አንዲሁ አዘጋጀና የፈለከውን ወስደህ ብላ አለኝ ። አንዱ ሰሀን ከላይ እንቁላል ነበረው ሌላኛው ሩዙ ላይ እንቁላሉ አልነበረውም ። እኔም ፈርጠም ብዬ አባዬ አንተ የቤቱ አባወራ ነህ አንተ መጀመሪያ ምረጥ የቀረውን እበላለው አልኩት ። አባቴ አላቅማማም ወዲያው እንቁላል ከላይ ያለውን ወሰደ አኔም የቀረውን ለራሴ ወስጄ እንቁላል እንደሌለው በማሰብ መብላት ጀመርኩ በሚገርም ሁኔታ ከስሩ ሁለት እንቁላሎች ነበሩት ።በጣም ገርሞኝ ደስታዬ ወሰን አልነበረውም አባቴ ፈገግ እያለ እንዲህ አለኝ ልጄ ሁሌም እንዳትረሳ ለሌሎች መልካም ነገርን ባሰብክና ባረክ ቁጥር ላንተ መልካም ነገሮች ይሆኑልሀል አለኝ ። የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂን ፒንግ
Показати все...
👍 1
📜በኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ ታሪክ በጣም አጭሩ ልብወለድ• • • . ርዕስ፦ #የማይሞተው_ፍቅር ✍• • • ተገዳ ስትዳር የዘጠኝ ዓመት ጨቅላ ነበረች። አስራ ሰባት ሲሞላት ነው ፍቅር ልቧን የዳሰሰው። አፈቀረችው፤ አፈቀራት። አወቀችው፤ አወቃት። አንድ ቀን ውኃ ልትቀዳ ወንዝ ወርዳ ከፍቅረኛዋ ጋር ጣሻው ውስጥ ወደቀች። "ባልየው" ወሬ ሰማ፤ ሽጉጡን ታጥቆ ተንደረደረ። ተዋህደው እንደተኙ ደረሰባቸው። ተኮሰ፥ እሷን ገደላት። ተኮሰ፥ ፍቅረኛዋን ገደለ። ተኮሰ፥ ራሱንም ገደለ። የማይሞተው ፍቅር ግን ከሦስቱም ልብ ውስጥ ወጥቶ ሌላ ጉብል ፍለጋ፣ ሌላ ጎልማሳ ፍለጋ እያዘነ ገሰገሰ። ደራሲ - ደምሴ ጽጌ ምትሃት - መጽሐፍ (1995 ዓ.ም.)
Показати все...
🥰 2
ምስጋና ይግባውና እንዴት ያል መታደል ነው ሁልጊዜም አዲስ ቀን አለ አዲስ ተስፋ አዲስ ሳቅ ብዙ አዲስ ሰዎች ........
Показати все...
Zemas_Addis_ken_New_music_Video_2019__tgx2jBA78K4_140.mp36.91 MB
“You're on Earth. There's no cure for that.” ~Samuel Beckett
Показати все...
[ክፍል ሁለት] ናፍቆትና መልሱ አልዋሽሽም ናፍቆትሽ በርትቶብኝ ነበር፡፡ ገላሽም ናፍቆኝ ነበር፡፡ የፀጉርሽ ጠረኑ ፡ የጡቶችሽ ወበቁ ፡ የድምሽ ሜሎዲው ፡ የከናፍሮችሽ ግርማቸው... ጠቅልለው ናፍቀውኝ ነበረ፡፡ (ተዐምር ብዬ የጠበኩት ፡ አይጣም ብዬ የቆመርኩበት ) ቀኑ ደረሰ፡፡ ከበራፌ ደጃፍ ላይ ቆመሽ ፡ ማንኳኳትሽ ደረሰኝ(ዛሬም ድረስ የአንቺን የማንከቯት ድምጽ እለየዋለሁ ፡ ደሞ ምንም አይነት በር ብታንኳኪም እለየዋለሁ)... ተንደፍድፌ ሔጄ በሩን ከፈትኩት፡፡ "እራስሽ ነሽ?" እቅፍ(እቅፎቿ እንዴት ናፍቀውኝ ነበር? ፡ የእናቷን እቅፍ እንተራበች ጫጩት ተርቤ ነበር፡፡ ለዛም ዘልዬ የተወሸኩበት)! ከደቂቃዎች በኀላ ነበር ሆዷ ሲገፋኝ የተሰማኝ(በእግር የመረገጥ አይነት ስሜት)፡፡ ከሰውነቷ ፈንጠር ብዬ(ግን እጇን ሳለቅ ፡ የእጆቿ ልስላሴ ናፍቀውኝ ነበርና) ሆዷን ተመለከትኩት፡፡ አብጧል... ስደነግጥ ታውቆኛል ፡ መተንፈስ አቃተኝ... ድምፄ ተዘጋ "ም ም ም ምነው ጸጊ? ምንድነው ይሄ?" "በጣም ይቅርታ ሞሄ፡ ወደቤት አታስገባኝም?" አለቺኝ በሀዘን በተሰበረ ድምፅ ፡ በመከዳት ስሜት በበሸቀ አንደበት ፡ በከዳ ስሜት በተንቀጠቀጠ ድምጽ ነበር ሰው በሚወደው ላይ እንዴት ይጨክናል፡ እንዴትስ ቤቱን ይነፍጋል 'ና አስገባኀት፡፡ በ #ምህረት ይለጥቃል
Показати все...
ባለውለታችን በዓላችንን ልታከብርልን ነው❗️ 😆🤣😉🇺🇲 የአሜሪካ ኤምባሲ "ደርግ የወደቀበትን የግንቦት 20 በዓል በደማቅ ሁኔታ እንደሚያከብር፣ እና ይሄንንም በማስመልከት ለሁለት ቀናት የአዲስ አበባ ኤምባሲው ተዘግቶ እንደሚውል፣ አገልግሎትም እንደማይሰጥ አስታወቀ" ይላል የዛሬው ዜና ደሞ🤣🤓። ("The US Embassy in Addis Ababa announced that it's going to celebrate "Ginbot 20" for us, by shutting down its embassy for two days.") In Wollo there are two localities by the name Gorarba and Berebiyu. So goes the following local proverb that exactly explains the embassy's mood, "ጎራርቦች ሊዳሩ፣ በረብዮች ደሩ". በወሎ የሚገኙ ሁለት ኩታገጠም ወረዳዎች አሉ። ጎራርባ እና በረብዩ የሚባሉ። እና ወሎዎች ሲተርቱ ምን ይላሉ? - "ጎራርቦች ሊዳሩ፣ በረብዮች ደሩ"🤣🤣😆🙏 "ጎራርቦች ሊዳሩ፣ በረብዮች ደሩ"😀 ማለት ትርጉሙ፦ "ቅቤ አንጣሪዋ እያለች፣ ጎመን ቀንጣሿን ምች መታት" ማለት ነው😀። ወይም "እመይቴ ለተ*ዱት፣ ገረዶቹ ተንጫጩ" እንደማለት🤪!) አይ አሜሪካ😄 አታመጣው የለ መቼም🤣🤪 (Assaf Hailu Facebook)
Показати все...
😁 1
✍      የአንተ ወንጀል……… ለጠላትህ መሳሪያ እንደማቀበል ነው። ወንጀል ላይ በዘወተርክ ልክ………    ጠላትህ በአንተ ላይ የበላይ ይሆናል።
Показати все...
መልክአ ሕይወት (በእውቀቱ ስዩም) ቧልትን ከፈገግታ ሳቅን ከፌዝ ጋራ ባንድ ላይ ቀይጠን፥ አቅልመን በጥብጠን በሐዘን ባሕር ላይ ፥ ብናንቆረቁርም ባሕሩ ሰፊ ነው፤ መልኩን አይቀይርም:: (ኗሪ አልባ ጎጆዎች)
Показати все...