cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Adebabay Media

በወገንተኝነት፣ በጊዜአዊ ጥቅም እና አጋርነት ብቻ የሚደረግ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ጋዜጠኝነት ጥቅም እንደሌለው በመረዳት ዕውቀትና መረጃ ላይ የተመረኮዘ፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ፣ ሀገርንና ወገንን በመጥቀም ላይ የተመሠረተ ሁሉን አቀፍ ባለ ብዙ ቋንቋዎች ሚዲያ፤ ቤተሰባችን ስለሆኑ እናመሰግናለን። በFacebook/YouTube (@adebabaymedia) ይመልከቱን። www.adebabay.com

Більше
Рекламні дописи
4 254
Підписники
-324 години
-67 днів
-830 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ በዓል:- እንኳን አደረሳችሁ!!! +++++ ** ሥዕላት በኢትዮጵያ ይትበሐል እንዲሁም በምሥራቅ ኦርቶዶክሶች የአሣሣል ሥርዓት ለአብነት።
Показати все...
38👍 5
👍 6 2🤔 1
ቫቲካን "ግ*ብ*ረ ሰ*ዶ*ማዊነትን" የሚቃወሙትን ሊቀ ጳጳስ አወገዘች ++++ (ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ) የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያ፤ ፖፕ ፍራንሲስ ግ*ብ*ረ ሰ*ዶ#ም ላይ ባላቸው አቋም የሚቃወሟቸውን፤ ከፍተኛ የቫቲካን ባለሥልጣን ሊቀ ጳጳስ አወገዘች። ካርሎ ማሪያ ቪጋኖ የተባሉት የ82 ዓመት አረጋዊ ሊቀ ጳጳስ የተወገዙት "በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክፍፍል በመፍጠራቸው" እንዲሁም " የፖፕ ፍራንሲስን ሥልጣን ባለመቀበላቸው እና በመቃወማቸው ("the “crime of schism” and “denial of the legitimacy of Pope Francis") መሆኑ ተዘግቧል። ካርሎ ማሪያ ቪጋኖ በቫቲካን ውስጥ አለ ያሉትን ሙስና በዝርዝር በማሳወቅ እንዲሁም የሮም ጳጳሳትና ካርዲናሎች በሕጻናትና ልጆች ላይ ሲፈጽሙ የኖሩት አስጠያፊ ወንጀል እንዲድበሰበስና እንዲቀር በማድረግ በኩል ፓፓውን ጨምሮ የቫቲካን ባለሥልጣኖች እጃቸው አለበት ብለው በግልጽ ደብዳቤ በማጋለጥ ይታወቃሉ። የሮም ካቶሊክ በተለይም "መሻሻል አድርጌአለሁ" ካለችበት "ቫቲካን 2" በመባል ከሚጠራው ከ1960ዎቹ ወዲህ ብዙ ነገር እንደተበላሽ ካርሎ ማሪያ ቪጋኖ ይናገራሉ። በላቲን ቋንቋ መቀደስን ከመከልከል ጀምሮ የተፈጸሙ ጥፋቶች ቫቲካንን ከመንገዷ አስወጥቷታል ሲሉ ይከስሳሉ። ፖፕ ፍራንሲስ ይባስ ብለው በቅርቡ ባሳለፉት ውሳኔ የካቶሊክ ቄሶች "ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ መባረክ" እንደሚችሉ መግለጻቸው ነገሩን የበለጠ አክርሮታል። ካርሎ ማሪያ ቪጋኖ ፓፓውን በግልጽ "የሰይጣን መልእክተኛ" በማለት ገልጸዋቸዋል። እናም ይህንን ሁሉ ያጣራው የሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ካርሎ ማሪያ ቪጋኖ እንዲወገዙ ያደረገ ሲሆን "በንስሐ የሚመለሱ ከሆነ ለማየት" ለጊዜው ያላቸውን ማንኛውንም ጥቅማ ጥቅም (defrocking ይሉታል) አልቀማቸውም። በውግዘቱ መሠረት "Viganò cannot officially accept Catholic sacraments including Communion, ordain priests or officiate Mass" ማለትም "ከካቶሊክ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን መሳተፍ አይችሉም (ለምሳሌ መቁረብ)፤ ቅስናም ሆነ ዲቁና መሾም አይችሉም፣ መቀደስም አይችሉም"። ++++ ማጠቃለያ፦ ከዚህ የምንወስደው ዋና ሐሳብ ምንድነው? ** ግ*ብ*ረ ሰ*ዶ*ምን መቃወም እንኳን በዓለማዊ ሥፍራ፣ በቤተ እምነቶችም ውስጥ ዋጋ የሚያስከፍልበት ዘመን ላይ እንገኛለን። ** ይህንን ኃጢአት በሕዝባችን ላይ አንጭንም፣ ሕዝባችንን ለዚህ አሳልፈን አንሰጥም ያሉ መሠረታቸው ኦርቶዶክስ የሆኑ ሀገራት ላይ ብዙ መከራ እየደረሰ መሆኑን መመልከት እንችላለን። ** በሀገራችንም ይህ ነገር በተለያዩ NGOዎች አማካይነት፣ በመብትና በሊበራሊዝም ስም፣ በተለይ ለወጣቱ በስፋት እየተሰጠ የሚገኝ ነገር ነው። ** ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦቱ የርክበ ካህናት ጉባዔው ይህንን አጀንዳ አድርጎ መወያየቱ በሀገራችን የነገሩአሳሳቢነት ከፍ ማለቱን ያሳያል። ** በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሕጻናት ልጆቻችን በግድ ስለዚህ ነገር እንዲማሩ በመገደድ ላይ ናቸው። +++++ ** ጆሮ ያለው መስማቱን ይስማ!!!!!
Показати все...
👍 17 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ቅዳሴ እና ሌሎች ጸሎቶች ዜማ +++++++ ፩/ iPhone እና iPad ለምትጠቀሙ፣ https://apps.apple.com/us/app/kidase-bet/id6478123184 ++++ ፪/ ስልካችሁ Android ለሆነ (ለምሳሌ Samsung) https://play.google.com/store/apps/details?id=apps.kaleb.qalesebehate2&hl=en_US&gl=US&pli=1 +++ ** ከተጠቀማችሁ በኋላ አስተያየታችሁን አጋሩን! ጠንካራ እና ደካማ ጎን የምትሉትን!!! ** እነዚህን አፖች የሠሯቸውን ባለሙያዎች ባለውቃቸውም ስለ አገልግሎታቸው ግን ምሥጋና ይገባቸዋል። ** እጃችሁ ይባረክ !!!
Показати все...
14👍 6
ቅዳሴ እና ሌሎች ጸሎቶች ዜማ +++++++ ፩/ iPhone እና iPad ለምትጠቀሙ፣ https://apps.apple.com/us/app/kidase-bet/id6478123184 ++++ ፪/ ስልካችሁ Android ለሆነ (ለምሳሌ Samsung) https://play.google.com/store/apps/details?id=apps.kaleb.qalesebehate2&hl=en_US&gl=US&pli=1 +++ ** ከተጠቀማችሁ በኋላ አስተያየታችሁን አጋሩን! ጠንካራ እና ደካማ ጎን የምትሉትን!!! ** እነዚህን አፖች የሠሯቸውን ባለሙያዎች ባለውቃቸውም ስለ አገልግሎታቸው ግን ምሥጋና ይገባቸዋል። ** እጃችሁ ይባረክ !!!
Показати все...
‎Kidase Bet

‎Welcome to Kidase Bet, your ultimate companion for Ethiopian Orthodox Tewahedo liturgical prayers and hymns. Discover the Divine Rhythm: Experience the rich traditions of Ethiopian Orthodox Tewahedo liturgy wherever you are. Kidase Bet brings the sacred melodies and prayers of the Church directly t…

03:22
Відео недоступнеДивитись в Telegram
እንኳን አደረሳችሁ!!!! ++++++ ሰኔ 30፣ የነቢይ፣ ሐዋርያና ሰማዕት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ልደት!!!! ======= ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል /፪×/ 0ርኩ ለመርዓዊ ትሰመይ/፪×/ ነቢይ ልዑል /፪×/ ትርጉም:- አንተ ሕጻን [ሆይ]!!! የልዑል ነቢይ ትባላለህ፣ የሙሽራው የክርስቶስ ሚዜ (ወዳጅ፤ ባለሟል) ትባላለህ (ትሰኛለህ)።
Показати все...
21.10 MB
29👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 18 4
ቴክኖሎጂ መጠቀም ጥሩ ነው። ነገር ግን ሃይማኖታችንን፣ ሥርዓታችንን፣ ታሪካችንን፣ ማንነታችንን እና እውነታውን ባገናዘበ መልክ መሆን አለበት። ፩/ ምሥለ ፍቁር ወልዳ፣ ፪/ ሙሴ ጸሊም እና ፫/ "ማሕሌት" ተብለው የተለቀቁ ምናልባትም በአርተፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI) ርዳታ የተሠሩ ሥዕሎች ናቸው። እየታረመ ጎበዝ።
Показати все...
11👍 5
፫ኛ. የምዕመናን አንድነት (ሕብረት) ቤተክርስቲያን ይባላል:- “ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እመ ኲሉ ሕዝብ፤ የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ (ቦታ) የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ይገባል" (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ) በማለት እንደገለጸው:: ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን እንዲል ጸሎተ ሃይማኖት። የመዠመሪያዎቹ ምዕመናን:-የሚባሉትም:- ፩ኛ. አስራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ፪ኛ. 36ቱ ቅዱሳት አንዕስት፣ ፫ኛ. 72 አርድእት (ሐዋ.14፥27፣ ሐዋ.16÷5፣ ኤፌ.2÷20፣ 1ጴጥ.2÷5 ፣1ኛቆሮ.3÷16) “በሐኪ በሐኪ ቤተ ክርስቲያን እምነ፣ ግበሪ ሰላመ ማእከሌነ፤ እምኀይለ ጸላኢ ወፀር ዕቀቢ ኪያነ፤ ትንብልናኪ የሀሉ ምስሌነ፤ ሰላም ለኪ፣ ሰላምታ የተገባሽ እናታችን ቤተ ክርስቲያን ሰላም ሰላም እንልሻለን። በመኻከላችን ሰላምን አድርጊ። ከፍጹም ጠላት እኛን ጠብቂ። ልመናሽም ከእኛ ጋራ ይኹን" እንዳለ ሊቁ ለእኛም የእመቤታችን የወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም  ልመናዋ ክብሯ፣ ጣዕመ ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን:: ሀገራችንን ከጥፋት ሕዝባችንን ከስደት ከመለያየት፤ ቤተ ክርስቲያናችን ከፈተና ይጠብቅልን። አሜን
Показати все...
31👍 6🕊 6
እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!!! ++++++ "ለዛቲ ቤት ሣረራ አብ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት ሀነጻ ወልድ ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ" (ሊቁ ቅዱስ ያሬድ) +++++ (መ/ር ዮሐንስ ለማ፤ ረቡዕ ሰኔ 21/2015 ዓ/ም ከጻፉት ላይ የተወሰደ) በሰኔ 20 ቀን በሐዲስ ኪዳን ለመዠመሪያ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባረገች በአራተኛው ዓመት (በ54ዓ/ም) በፊልጵስዩስ ቂሳሪያ ከሦስት አዕባን (ዓለቶች) መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በስሟ የተሠራችው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በሰኔ 21 ቀን ቅዳሴ ቤቷ የከበረበት ታላቅ ዕለት ነው። ዕለቱም ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው። “በሠላስ አእባን ገጸ ሥላሴሁ ለአምሮ፣ ሐኒጸ ቤትኪ ድንግል ድኅረ ፈጸመ ሣርሮ፣ አመ ወረደ ለበዓል ምስሌኪ በአማኅብሮ፣ እንዘ ይብላ ቃለ ለዘምሮ፣ ልዑል ቀደሰ ማኅደሮ፣ ደናግል ለጽጌኪ ዘበጣ ከበሮ።" ትርጉም፦ "ድንግል በአካል ሦስት መኾኑን ለመግለጽ በሦስት ድንጋዮች ቤትሽን መሥራትን ከፈጸመ በኋላ ከአንቺ ጋር ለበዓል በተገለጸ ጊዜ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ እያሉ ልጅሽን ለማመስገን ደናግል በከበሮ ምስጋናን አቀረቡ" እንዲል ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል። 👉 ምሳሌነቱም፦ ፩ኛ. ሦስቱ ደንጊያዎች የሥላሴ አምሳል ምሳሌዎች። ፪ኛ. ከታች አቀማመጣቸው 3 ከላይ ሕንፃቸው 1 ነው። ፫ኛ. የአንድነታቸው እና የሦስትነተኛው ምሳሌ። 👉 ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በብሉይ ኪዳን፦ በብሉይ ኪዳን የመጀመዠሪያዋ ቤተክርስቲያን ደብተራ ወይም ድንኳን ነበረች። ከዚያም ቤተ መቅደስ በዘሩባቤል ዘመን 46 ዘመን ፈጅቶ ተሠርቷል። ** "በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ" (ዘጸ.25÷8)። 👉 ሕንጻ ቤተክርስቲያን በሐዲስ ኪዳን፦ በሐዲስ ኪዳንም ሰኔ 20 ቀን ጌታችን ከሦስት ድንጋዮች ቤተ መቅደስ አንጾ ሰኔ 21 ቀን ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት ዕለት ነው። (ማቴ.16÷13-19) 👉 ቤተ ክርስቲያን ስለምን ቅድስት ትባላለች?:- ፩ኛ. የቅድስት ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ይነገርባታልና፣ ፪ኛ. ክርስቶስ በደሙ አክብሯታልና፡፣ ፫ኛ. ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ይሰጥባታልና፡፣ ፬ኛ. በኀጢአት የረከሰ ሰው በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቆባት ይቀደስባታልና፡፡ “ሰላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን እምየ፣ ዘትጼንዊ መጽርየ፣ ብኪ ጸናዕኩ እምከርሠ እምየ፣ ቤተ ክርስቲያን አክሊለ ርእስየ ሰላም ለኪ፤ እንደ ቀጋ የምትሸቺ ቤተ ክርስቲያን እናቴ ሰላምታ ለአንቺ ይገባል፤ ከእናቴ ማሕፀን ዠምሮ በአንቺ ጸናኁ፤ የራሴ አክሊል የምትኾኚ ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል" (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ) 👉 ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ስለ3 ነገር ይነገራል። ፩ኛ. እያንዳንዱ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ይባላል:- ** በጥንተ ፍጥረት ከምድር አፈር አበጅቶ የሕይወትን እስትንፋስ እፍ ብሎ የራሱ ቤተ መቅደስ ያደረገን እሱ ነው። ** (ዘፍ.1÷27) "እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው" ** (ኢሳ.28÷16) እነሆ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ የተፈተነውን የከበረውን መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምንም አያፍርም። ከጽዮን ከድንግል ማርያም የተወለደው የጸናው ዓለት ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ፈጣሪ እንደሆነ የሚያምን ሁሉ በዚህ ዓለት ላይ ታንጿል። መሠረቱም የጸና ነው። ቤተ አይሁድ ተሰናከሉበት። ብዙዎችም ዛሬ የባሕርይ ክብሩን አቃለሉ። ኃይሉን ካዱ። አስቀድሞ በዳዊት የተነገረው ትንቢት ይደርስ ዘንድ። ** (መዝ.118÷22) "ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆነች ለዓይናችንም ድንቅ ናት"። ፪ኛ. የተቀደሰው ህንጻ ቤተክርስቲያን ይባላል፦ ** “እንተ ተሐንጸት በስሙ፣ ወተቀደሰት በደሙ፣ ወተዐትበት በዕፀ መስቀሉ ጌሡ ኀቤሃ እስመ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ፣ በስሙ ታነጸች በደሙም ከበረች በዕፀ መስቀሉም ተባረከች ወደ ርሷ (ቤተ ክርስቲያን) ኺዱ። የእግዚአብሔር ኀይል በርሷ ላይ ነውና" (ሊቁ ቅዱስ ያሬድ) ** (መዝ.118÷20) "ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት ወደ እርስዋ ጻድቃን ይገባሉ" ** (1ጢሞ.3÷15) "ብዘገይ ግን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው" ሕንጻውም:- ፩ኛ. ለእግዚአብሔር ክብር የምንዘምርበት፤ ፪ኛ. ስለተደረገልን ነገር ሁሉ ምስጋና የምናቀርብበት፤ ፫ኛ. ማሕሌቱ፣ ሰዓታቱ፣ ኪዳኑና ቅዳሴው የሚከናወንበት፤ ፬ኛ. የተሰበረው ልባችንና እንባችን የሚታበስበት፤ ፭ኛ. ታሪካችን የሚቀየርበት የጸጋው ግምጃ ቤት፤ ፮ኛ. ሐዘናችን ወደ ደስታ ለቅሶአችን ወደሳቅ የሚቀየርበት፤ ፯ኛ. እንቆቅልሻችን የሚፈታበት ነው። ፰ኛ. የጸጋ ግምጃ ቤት የበረከት ማዕድ ናት። (መዝ.65÷4) ፱ኛ.የእውነት ዓምድና መሠረት ጻድቃን የሚገቡባት ናት ------- (ይቀጥላል)
Показати все...
👍 9 4👎 2
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.