cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ማራናታ Maranata

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሊመጣ በደጅ ነው!አሜን ምጣልን እንጂ አትምጣብን!

Більше
Ефіопія7 924Амхарська6 962Категорія не вказана
Рекламні дописи
460
Підписники
Немає даних24 години
+137 днів
+4230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

1 ዜና 16 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³³ በምድር ሊፈርድ ይመጣልና፥ የዱር ዛፎች በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል። ³⁴ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ። ³⁵ የመዳናችን አምላክ ሆይ፥ አድነን፤ ቅዱስ ስምህን እናመሰግን ዘንድ፥ በምስጋናህም እንመካ ዘንድ፥ ከአሕዛብ ሰብስበህ ታደገን በሉ። ³⁶ ከዘላለም እስከ ዘላለም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበሉ፤ እግዚአብሔርንም ያመስግኑ። መልካም አዲስ አመት 2016💟💝💝💘💘💗🔆🔆🔆🔆
Показати все...
“እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።” — ዕብራውያን 6፥10
Показати все...
አስር የልማድ እውነታዎች - ክፍል ሰባት ልማድና ሕይወት “ቀኖቻችንን የምናሳልፍበት ሁኔታ ሕይወታችንን የምናሳልፍበት ሁኔታ ነው” - Charlie Gilkey ደቂቃ የሰኮንዶች ጥርቅም ነው፤ ሰዓት የደቂቃዎች ጥርቅም ነው፤ ቀን የሰዓታት ጥርቅም ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ሳምንት የቀናት፣ ወር የሳምንታት፣ ዓመት ደግሞ የወራት ጥርቅም ነው፡፡ ሕይወትም ከዚህ ተለይቶ አይታይም፡፡ የየቀኑ ድግግሞሻችን ተጠራቅሞና ተደምሮ ሕይወታችንን ይሰራዋል፡፡ በየቀኑ ስፖርት የሚሰራ ስፖርተኛ ከመሆን ሌላ፣ በየቀኑ የሚያጠና ሰው አዋቂ ከመሆን ሌላ፣ በየቀኑ የሚለምን ሰው ለማኝ ከመሆን ሌላ ምን ምርጫ አለው? ቀኖቻችንን የምናሳልፍባቸው ሁኔታዎች ሕይወታችን ከሆነ፣ የየቀናችን ልማድ ሕይወታችን ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህም፣ ለልማድ መጠንቀቅ ለሕይወት መጠንቀቅ ማለት ነው፡፡ ይህንን ሂሳብ ለማስላትና ለመገንዘብ የጠፈር ተመራማሪ መሆንን አይጠይቅም፡፡ መፍትሄው ደግሞ አጭርና ግልጽ ነው፡፡ ሕይወትህን በምን ላይ ማሳለፍ እንደምትፈልግ በሚገባ አስበህ እቅድህን ከነደፍክ በኋላ የየቀን ልማድህን ከዚያ ከቀረጽከው እቅድና አላማ አንጻር ቃኘው፡፡ ካለማቋረጥ የምትከታተለው ነገር ላይ መድረስህ አይቀርም፤ ደግመህ ደጋግመህ የምታደርገውን ነገር ደግሞ ሆነህ መገኘትህም አይቀርም፡፡ @kibirenaw
Показати все...
ቅደም ተከተልን የማወቅ ጥበብ “የሚያጣድፍ ነገር ሁሉ አስፈላጊ ነገር አይደለም” - Stephen Covey አንድ ቀን አንድ የማኔጅመንት ሳይንስ ሊቅ ለተማሪዎቹ ንግግር በማድረግ ላይ ነበር፡፡ ይህ ሰው ለእነዚህ በጣም ለተነሳሱና ብሩህ አእምሮ ላላቸው ተማሪዎች በመናገር ላይ እያለ አንድን ነገር አደረገ፡፡ አንድ ባሊ አመጣና ጠረጴዛው ላይ ካስቀመጠ በኋላ ድንጋዮችን በማምጣት ባሊውን አፉ ድረስ ጢም አድርጎ በድንጋይ ሞላው፡፡ ይህንን ካደረገ በኋላ፣ “ይህ ባሊ ሙሉ ነው የሚል እጁን ያውጣ” አለ፡፡ በክፍሉ ያሉ ተማሪዎች በሙሉ እጃቸውን አወጡ፡፡ “እርግጠኛ ናችሁ?” አላቸው፡፡ “አዎን” በማለት እርግጠኝነታቸውን አረጋገጡለት፡፡ ከዚያም ከጠረጴዛው ስር አስቀምጦት ወደነበረው ሌላ ባሊ አጁን ዘርግቶ አነሳውና በውስጡ ያለውን ጠጠር ወደዚያ ድንጋይ ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰው፡፡ ጠጠሮቹ ሹልክልክ እያሉ ባገኙት ቀዳዳ ሁሉ ገቡ፡፡ “አሁንስ ባሊው ሙሉ ነው የምትሉ ስንት ናችሁ?” አለ መልሶ፡፡ አሁን አሰልጣኙ ምን ሊል እንደፈለገ በመጠኑ እየገባቸው ስለመጣ በማንገራገር የተደባለቀ ምላሽ ሰጡት፡፡ አንዳንዶቹ፣ “አሁን ሙሉ ነው” ሲሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ፣ “አሁንም አልሞላም” አሉ፡፡ አሁንም በመቀጠል እጁን ወደ ጠረጴዛው ስር ሰደድ በማድረግ ሌላ ባሊ አነሳ፡፡ ይህኛው ባሊ በአሸዋ የተሞላ ነው፡፡ ወዲያውኑ አሸዋውን ወደዚያ ድንጋይና ጠጠር ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰው፡፡ አሸዋዎቹ ሹልክልክ እያሉ ባገኙት ቀዳዳ ሁሉ ገቡ፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ፣ “አሁንስ ባሊው ሙሉ ነው የምትሉ ስንት ናችሁ?” አሁን ተማሪዎቹ በሙሉ በአንድ ቃል፣ “ባሊው አሁንም አልሞላም” ብለው መለሱለት፣ አካሄዱ ገብቷቸው፡፡ አሰልጣኙ እንደገና ሌላ ውኃ የሞላበት ባሊ ከጠረጴዛው ስር በማንሳት ድንጋይ፣ ጠጠርና አሸዋ ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰውና በባሊው ውስጥ ሌላ ምንም ነገር መጨመር እስከማይቻል ድረስ ሞላው፡፡ የመጨረሻው ትምህርታዊ ጥያቄ እንዲህ የሚል ነበር፡፡ “ከዚህ ምሳሌ የምናገኘው ዋና ቁምነገር ምንድን ነው?” አላቸው፡፡ አንዱ ሰልጣኝ አጁን አውጥቶ፣ “ምንም እንኳ ጊዜህ በብዙ ነገር ቢጨናነቅ፣ አሁንም ሌላ ነገርን አጨናንቀህ ማድረግ እንደምትች ነው” አለው፡፡ አሰልጣኙም፣ “ተሳስተሃል! የዚህ ምሳሌ ዋነኛ ትምህርት በመጀመሪያ ትልልቆቹን ድንጋዮች ባሊው ውስጥ ባትጨምር ኖሮ ትንንሾቹን ጠጠሮች፣ አሸዋውንና ውሃውን መጨመር አትችልም ነበር፡፡ ትልልቆቹ ድንጋዮች የሚወክሉት በሕይወትህ ያሉትን ዋና ዋና የሕይወት አላማዎችና ግቦች ነው፡፡ ቤተሰብህ፣ ጤንነትህ፣ የትምህርትህ አቅጣጫ፣ ዋነኛ ሕልሞችህና የመሳሰሉት … ዋና ዋና ከሚባሉት “ድንጋዮች” መካከል ይገኛሉ፡፡ በመጀመሪያ በእነዚህ ነገር ካልተደላደልክና የሕይወትህን አቅጣጫ ካልሞላኸው፣ በጥቃቅን ነገሮች ተጨናንቀህ ሕይወትህን ታባክናለህ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ጊዜን በአግባቡ የመጠቀምን ጥበብ ማዳበር በራሱ እጅግ አድካሚ ስራ ነው  ብለው  ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ሁኔታው የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ ዛሬ የሕይወቴን ዋና ዓላማ በመለየትና ቅድሚያን ለእርሱ በመስጠት መልክ የያዘ ሕይወት ለመኖር ማቀድ ካልቻልኩ ነገ በዚህና በዚያ የባከነውን ጊዜዬን መለስ ብዬ ከማየትና ከመቆጨት ውጪ ምንም ነገር ለማድረግ ያስቸግረኛል፡፡ “የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተቀነጨበ፡፡ @kibirenaw
Показати все...
#ጓደኝነት(ወዳጅነት)_በዛፍ_ይመሰላል ያለው ማን ነበር? ይህንን የወዳጅነትን መግለጫ ማን እንዳለው ባላስታውስም እውነቱ ግን ይህው ነው። ወዳጅነት በዛፍ ይመሰላል፦ 1) #ቅጠል፤ በቅጠል የተመሰሉት ሲያጅቡ ብዙ ውበት ይሆናሉ። ቶሎ ለሁሉ ይታያሉ። ለሁሉ ሳቢ ናቸው። ግን ምን ያደርጋል በመጀመሪያው ንፋስ ይረግፋሉ። የመከራን ሰአት ወዳጅ መሆን አይችሉም። ጓደኝነታቸው እስከ ንፋሱ መንፈስ ድረስ ብቻ ነው። 2) #ቅርንጫፍ፤ እነዚህ ከቅጠሉ ይልቅ የተቀራረቡ ናቸው። ቅጠሎቹን የተሸከሙ ለመስፋፋት ምክንያት የሆኑ ናቸው። ግን ቢንጠለጠሉባቸው ወይም ልደገፋችሁ ሲባሉ ይዘው ይወድቃሉ። ማስደገፍ የሚችሉበት የወዳጅነት ጥንካሬ የላቸውም። ወዳጅነት የሚያስከፍለውን ዋጋ ስለማይገነዘቡ መነካካትን አይፈልጉም። ለእነሱ መንካት እንጂ መነካት ነውር ነው። ስለዚህ... 3) #ግንድ፤ እነዚህኛዎቹ ወዳጆች (ጓደኞች) አብሮነትን በመከራም በምቾትም ቀን ማስቀጠል የሚችሉ ናቸው። በሁሉ ሁኔታ ውስጥ አብሮ መጽናትን የተማሩ ወይም የቻሉ ናቸው። ደክመሃል ብለው በምድረበዳ ለአውሬ ጥለው የማይሄዱ ጠንካሮች ናቸው። ይጠብቁሃል እንጂ በአደባባይ አያሰጡህም። እንደ ዮናታን ከእነሱ መብት የሚያስቀድሙህ ናቸው። 4) #ስር፤ እነዚህ ደግሞ ታዋቂና በየቅያሱ አብረው የሚታዩ አይደሉም። ቅን ለአንተና ለጓደኝነትህ ሕይወትን ሲመግቡ ይኖራሉ። በጎደኝነት ጉዞ ውስጥ ሁሌም ደግሞ ደግሞ የሕይወት ሽታና ኃይል እንዲኖር የሚተጉ ናቸው። "ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወዳል፤" ምሳ 17:17 እንደ ግንድም እንደ ስርም የሆነ ጓደኛ እንሁን። ቅጠልና ቅርንጫፍ ለሆኑትም ልብ በመስጠት ጉዳትን አናብዛ። የእውነት ጓደኛ ነህ? የእውነት የሆኑስ ጓደኞች ዛሬ ላይ አሉህ? @kibirenaw
Показати все...
* እንደገና የመጀመር ዕድል! * ውድቀት አንድን ነገር ቀደም ሲል በሄድንበት መንገድ ሳይሆን እንደገና በጥበብ የመጀመር እድል ነው። ሄንሪ ፎርድ ብዙዎቻችን ውድቀትን እንፈራለን። ይሁንና ውድቀት ወይም አለመሳካት በየቀኑ በትምህርት ቤት፣ በስራ ቦታ፣ በቤተሰብ ውስጥ ወዘተ. የሚከሰት፤ የሚያበሳጭ፤ ነገር ግን ልናስወግደው የማንችለው ነገር ነው። እናም ውድቀትን ብንፈራው ከዓላማችን የሚያደናፈን፤ ከደፈርን ደግሞ ትምህርት ወስደን በአዲስ መንገድና በአዲስ ስልት እንደገና ለመጀመር እድል የሚሰጠን ነው፤ @kibirenaw
Показати все...
የማቆም ውሳኔ አንድ የጀመራችሁት ነገር በፍጹም እንደማያስቀጥላችሁ እያወቃችሁ ለውጥ ማምጣት ካቃታችሁ . . . እንዲሁም ከአንድ ሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት ፍጹም ጤና ቢስ እንደሆነና እንደማያዛልቃችሁ እያወቃችሁት ደንዝዛችሁ እንደቀራችሁ ከተሰማችሁ፣ ችግራችሁ ነገሩን የማቆም ከመሆኑ ይልቅ አዲስ ነገር የመጀመር ጉዳይ እንደሆነ አትዘንጉ፡፡ 1.  እንደገና የመጀመር ፍርሃት አንድን ነገር እንደገና የመጀመር ፍርሃት ካለብን አሁን ያለውና አላስኬድ ያለውን ነገር ማቆም እንዳለብን እያወቅነው እንኳን ያንን ማድረግ ያስቸግረናል፡፡ ሆኖም፣ የተበላሸ ነገር ይዞ የመቀጠል ሁኔታ ረጅም ርቀት የሚሄድን ችግር ይዞ እንደሚጠብቀን እናስታውስ፡፡ 2.  ግራ መጋባት አንድን ነገር ማቆም እንዳለብን ብቻ አውቀን ያንን ካቆምን በኋላ ምን እንደምንጀምር ካላወቅነውና ግራ ከገባን ሁኔታው አስፈሪ ያደርገዋል፡፡ እዚህ ጋር ማስታወስ ያለብን ነገር ቢኖር አንድን ነገር ስናቆም በቶሎ ሌላ ነገር መጀመር እንደሌለብን ነው፡፡ በተለይም ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት እንዳቆምን ወዲያው ሌላ መጀመር እንዳለብን ማሰብ ወደሌላ አስቸጋሪ ግንኙነት ውስጥ እንድንገባ ሊያሳስተን ይችላል፡፡ 3.  ጊዜ እንዳባከንን መሰማት አንድ ነገር አላስኬድ ሲለንና ማቆም ስንፈልግ፣ አንዳንድ ጊዜ የሚቆጨን በዚያ ነገር ላይ እስካሁን ያሳለፍነው (ያባከንነው) ጊዜ ነው፡፡ “ይህንን ያህል አመት ቆይቼ” እንላለን፣ ልክ በቁጭት ከተነሳን አሁን ያለው ነገር ይለወጥ ይመስል፡፡ አንድ ነገር ፈጽሞ እንደማያስኬደን ካወቅን በኋላ ብዙ ጊዜ አቃጥያለሁ ብሎ ማሰብ በማይሰራ ነገር ላይ ሌላ ተጨማሪ ጊዜ በመቃጠል ወደፊት ለሚቆየን የከፋ ጸጸት ራስን ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡ አስታውሱ . . . •  አዲስ የሚተክለውን ነገር በሚገባ ያወቀ ሰው አሮጌውን መንቀል አያስቸግረውም፡፡ •  አዲስ የሚገነባው ነገር የገባው ሰው አሮጌውን ማፍረስ አይከብደውም፡፡ •  አዲስ የሚጀምረውን ነገር የተረዳ ሰው አሮጌውን ማቋረጥ አያዳግተውም፡፡ ችግራችን አቅጣጫን ያለማወቅ እንደሆነ ተገንዝበን ስለነገው ጉዟችን ግልጽ የሆነ እይታን ስናዳብር በፊት ያስቸገረን ነገር ምን ያህል ቀላል እንደሆነ እንደርስበታለን፡፡ @kibirenaw
Показати все...
* ከፍ ብለህ ብረር! * ከፍ ብለህ ለመብረር ከፈለግህ ወደ ላይ ከፍ ከፍ እንዳል የሚጎትቱህን ማናቸውንም ክብደት ያላቸው ነገሮች አወግድ የሚል ጥቅስ አንብቤያለሁ። የምትሸከመው ነገር በበዛ ቁጥር ወደ ላይ ለመውጣት ከባድ ይሆናል። ስለዚህ መውጣትህ የግድ ከሆነ እና በፍጥነት ከፍ ከፍ ለማለት የምትፈልግ ከሆነ ክብደት ያላቸውን ነገሮች በሙሉ ከላይህ ላይ ማራገፍ ያስፈልግሃል። በሌላ አገላለጽ ወደ ስኬት በምናደርገው የለውጥ ጉዞ ከዓላማችን በፍጥነት እንዳንደርስ የሚያደናቀፉ ሰዎችን እንዲሁም አጉል የሆኑ አስተሳሰቦችና ልማዶቻችንን መተው ግድ ይለናል። @kibirenaw
Показати все...
ንስርን የሚገዳደር ብቸኛው የወፍ ዝርያ ቁራ ነው። ቁራ በንስሩ ጀርባ ላይ ይቀመጥና አንገቱን ይነክሰዋል። ንስሩ ምላሽ አይሰጥም ፣ ከቁራ ጋር አይጣላም ፣ ከቁራ ጋር አይታገልም ፣ በቁራ ላይ ጊዜና ጉልበቱን አያጠፋም ይልቁንም ክንፉን ዘርግቶ ወደ ሰማይ ከፍ በማለት መብረር ይጀምራል። በረራው ከፍ ባለ መጠን ቁራው ለመተንፈስ ይቸገራል። በመጨረሻም ቁራው በኦክሲጅን እጥረት ምክንያት ይወድቃል። 🎯.ዛሬ በህይወታችሁ የሚገዳደራችሁን ምንም አይነት ነገር አትታገሉት ፣ ጉልበታችሁን እና ጊዜአችሁን በእርሱ ላይ አታጥፉ ይልቁንም ከፍ ባለ አስተሳሰብ በልጣችሁ ውጡ ፣ በእውቀት ጠንክሩ ፣ መልካም ሥራችሁን ጨምሩ። ንስሩ በጀርባው ላይ የተንጠለጠለውን ቁራ ትቶ ከፍታው ላይ እንደሚያተኩር የሌሎችን አሉባልታ ፣ ሀሜት ፣ ማስፈራሪያ ወደታች ትታችሁ ከፍታችሁ ላይ አተኩሩ። ቁራው ከፍታውን መቋቋም እንዳቃተው እናንተም ከነገሮች በላይ ከፍ ስትሉ የእናንተም ተግዳሮት ከፍታውን መቋቋም አቅቶት ቁልቁል ይፈጠፈጣል ። መልካም ቀን @kibirenaw
Показати все...
ንስርን የሚገዳደር ብቸኛው የወፍ ዝርያ ቁራ ነው። ቁራ በንስሩ ጀርባ ላይ ይቀመጥና አንገቱን ይነክሰዋል። ንስሩ ምላሽ አይሰጥም ፣ ከቁራ ጋር አይጣላም ፣ ከቁራ ጋር አይታገልም ፣ በቁራ ላይ ጊዜና ጉልበቱን አያጠፋም ይልቁንም ክንፉን ዘርግቶ ወደ ሰማይ ከፍ በማለት መብረር ይጀምራል። በረራው ከፍ ባለ መጠን ቁራው ለመተንፈስ ይቸገራል። በመጨረሻም ቁራው በኦክሲጅን እጥረት ምክንያት ይወድቃል። 🎯.ዛሬ በህይወታችሁ የሚገዳደራችሁን ምንም አይነት ነገር አትታገሉት ፣ ጉልበታችሁን እና ጊዜአችሁን በእርሱ ላይ አታጥፉ ይልቁንም ከፍ ባለ አስተሳሰብ በልጣችሁ ውጡ ፣ በእውቀት ጠንክሩ ፣ መልካም ሥራችሁን ጨምሩ። ንስሩ በጀርባው ላይ የተንጠለጠለውን ቁራ ትቶ ከፍታው ላይ እንደሚያተኩር የሌሎችን አሉባልታ ፣ ሀሜት ፣ ማስፈራሪያ ወደታች ትታችሁ ከፍታችሁ ላይ አተኩሩ። ቁራው ከፍታውን መቋቋም እንዳቃተው እናንተም ከነገሮች በላይ ከፍ ስትሉ የእናንተም ተግዳሮት ከፍታውን መቋቋም አቅቶት ቁልቁል ይፈጠፈጣል ። መልካም ቀን
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.