cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ዜና አበው ቅዱሳን

በዚህ ቻናል ላይ ያላችሁ አስተያየት @ Kiduse Solomon2324 ብሎ በተጨማሪም ስልክ ቁጥር 0989740239 የአብሥራ ብሎ ማገኘት ይችላል ስንክሳር ምስባክ የቅዱሳን ታሪክ መተረክ ነገረ ሃይማኖት ድርሳናት ወረብ እና ዚቅ ብሒል አበው ዜና አበው ምክር አበው መንፈሳዊ ግጥሞች የጉባኤ ቤት ስብከቶች መዝሙሮች የቤተክርስቲያን ታሪክ የተለያዩ ነገሮች በዚህ ቻናል ማገኘት ይችላል

Більше
Рекламні дописи
600
Підписники
-124 години
-37 днів
-930 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

"እውነተኛ ሐሴት ትፈልጋላችሁን? እንግዲያውስ ለድሆች መጽውቱ፤ ክርስቶስን ወደ ቤታችሁ ጥሩት፡፡ ይህን ስታደርጉ ማዕዱ ቢነሣም ሐሴቱ አይነሣም፤ ይቀጥላል እንጂ፡፡ በተለይ ደግሞ በዚህ በወርሐ ጦም ይህን አብዝታችሁ አድርጉት።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
✨✨✨🌿🌿🌿✨✨✨🌿🌿🌿✨✨✨🌿🌿🌿 “እምሥርወ እሴይ ሠሪጻ ወእምዘርዐ ዳዊት ተወሊዳ ታዐብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ፤ ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ ወከመ ሮማን መላትሒሃ፤ ኅብስተ ሕይወት በየማና ወጽዋዐ ወይን በፀጋማ ጸሎታ ወስእለታ ይኩነነ ወልታ” እመቤታችን ከእሴይ ባሕርይ ወጥታ፤ ከዳዊት ዘር ተወልዳ፤ ሰውነቴ እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ታደርገዋለችሥ አለች፤ ከንፈሮቿ እንደ ጽጌሬዳ አበባ ቀይ ናቸው፤ ጉንጮቿም እንደ ሮማን ናቸው፤ የሕይወት እንጀራ በቀኝዋ በጽዋ ውስጥ ያለ ወይንም በግራዋ አለ፤ ጸሎቷ ልመናዋ ጋሻ ይኹነን ✨🌿 መጽሐፈ ዝማሬ ቅዱስ ያሬድ ✨🌿 ✨✨✨🌿🌿🌿✨✨✨🌿🌿🌿✨✨✨🌿🌿🌿
Показати все...
++++ የገሊላዉ ጳጳስ፡፡++++ አንድ ክርስትያን ያልሆነ ሰዉ ባለቤቱ ልትወልድ ተጨንቃ ነበር ነገር ገን ለማሳከሚያ የሚሆን ገንዘብ የለውም ከዚያም <"የገሊላውን ጳጳስ"> አባ አብርሐን እጠይቀዋለሁ አለ ("<አባ አብርሐም የገሊላዉ ጳጳስ በመባል ይታወቃል>") ስለሆነም ወደ ቤቱ ሄዶ ገንዘብ እንዲሰጠዉ ለመነዉ አባ አብርሐምም """ጳጳሱ ለክርስትያን ብቻ መሰለህ እንዴ""" ብሎ በመቀለድ ከትራሱ አንድ ፖስታ እሽግ ብር ሰጠዉ፡፡ያ ሰዉ ሲከፍተዉ 1 ፓውንድ(የግብፅ በብር ፓውንድ ተብሎ ነዉ ሚጠራዉ)ነዉ በሚከፈፍትበት ጊዜ አንድ መነኩሴ አይቶት ነበር እና ያ ገንዘብ በወቅቱ ትልቅ ገንዘብ ነበረ መነኩሴዉ ለጳጳስ ወንድሙ በመቆርቆር እንዴት 1 ፓውንድ ሰጠህ ብሎ ሰውየዉ ላይ ያንን ገንዘብ ወስዶ በምትኩ 20 ፒያስትረስ ሰጠዉ ያ ሰዉ ተመልሶ አባ አብርሐም ተናገረ አባ አብርሐም መነኩሴዉን ጠርቶ ብሩን ተቀብሎ ሰውየው ሰጠዉ ያም ሰዉ አመስግኖ ባለቤቱን ይዞ ሄደ፡፡በመቀጠል አባ አብርሐም መነኩሴውን """ከጌታችን ምን ተማርን ምንቀበለዉ ልንሰጥ አይደለምን ከቀደሙት አባቶቻችንን የተማርነዉ ስስት ነዉ""" ብሎ ገሰፀዉ መነኩሴው አማላጅ ይዞ ይቅርታ ተባለ፡፡ ++++ አንካችሁ ቅበሩት፡++++ አንድ ጊዜ 3 ወጣቶች በዘዴ ከአባ አብርሐም ገንዘብ መቀበል ፈለጉ ስለሆነም ዘዴ ሲያስቡ ከሶስታቸዉ አንዱ እንደ ሞተ በማስመሰል ሁለቱ ሄደዉ ገንዘብ ሊቀበሉ ሄዱ ከዚያም የውሸት እያለቀሱ ገንዘብ ጠየቁት አባ አብርሐም በመንፈስ የሆነውን ተረድቶ ነበርና ጭንቅላቱን እየነቀነቀ """ <እንካችሁ ቅበሩት>""" አላቸዉ በደስታ ገንዘቡን ይዘዉ ሄዱ በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲደርሱ የያ ጓደኛቸዉ ሞቶ አገኙት በድንጋጤ እየሮጡ ያደረጉትን አባ አብርሐም እያለቀሱ ነግረውት ገንዘቡን ሊመልሱ ሲሉ አባ አብራም ግን ፈገግ ብሎ """ገንዘቡን ግን ቅበሩበት""" ብሎ ተወላቸዉ፡፡ ++++ድርሻዉ ነዉ ይውሰደዉ፡፡እግዚአብሔር ችግሩን ስለሚያውቅ ነዉ ይህን የላከለት፡፡++++ አንድ ሐብታም በፖስታ ገንዘብ ሰጥቶት ሄደ አባ አብርሐም በፖስታ የሚሰጠውንም ገንዘብ ከፍቶ አያየውም እንደታሸገ ከትራሱ ሥር ያስቀምጠዋል እንጂ ስለሆነም አንድ ደሐ መጣና ገንዘብ ሲጠይቀዉ ያንን የታሸገ ገንዘብ አውጥቶ ሰጠዉ፡፡ከዚያም ያ ደሐ ከቤቱ ባለዉ በረንዳ ጋር ቆሞ ፖስታውን ሲከፍተዉ 10 ፓውንድ ነዉ፡፡ይህንን ያየ አንድ ደቀ መዝሙሩ መጥቶ ነገረዉ 10 ፓውንድ እንደ ሰጠዉ አባ አብርሐምም <"""ድርሻዉ ነዉ ይውሰደዉ እግዚአብሔር ችግሩን ስለሚያውቅ ነዉ ይህን የላከለት""">አለዉ፡፡ +++ቤቱን ገንብቻለሁ+++ የተወሰኑ አባቶች ተሰብስበዉ የአባ አብርሐም ቤት ለማሳደስ ወሰኑ ለምን ቤቱ እንኳን ጳጳስ ተራ ሰዉ የማይኖርበት በመሆኑ ነዉ፡፡በሌላ አጋገር በጣም አርጅቷል፡፡ስለሆነም አስፈላጊውን ወረቀት እና ፈቃድ አውጥተዉ ከጨረሱ በኋላ ለቤቱ ግንባታ የያሰባሰቡትን ገንዘብ ለአባ አብርሐም ሰጥተዉ ሄዱ አርሱም ተቀብሎ ገንዘቡን ለነዳያን አከፋፈለ በሚቀጥለዉ ወር ሲመጡ ቤቱ ምን ለውጥ አልታየበትም ወደ ውስጥ ዘለቁ እና """አባታችን ለምንድነዉ ቤቱን ያላሳደስከዉ???!!!""" ሲሉት """እኔ እኮ <ቤቱን ገንብቻለሁ ቤቱን ገንብቻለሁ>""" አላቸዉ """ታዲያ ምንም ለውጥ አላየንበትም""" ሲሉት <"""እኔ እኮ ለዘላለማዊ የሚሆን ቤት ገንብቻለሁ""""> አላቸዉ፡፡ገርመዉ እና ተደንቀዉ ተመልሰዉ ሄዱ፡፡ *በእርሱ ዘመን ድሐ ፆሙን አያድርም ነበር፡፡ድሆቹም የእርሱ ቤት እንደ ሁለተኛ ቤታቸዉ ነበር፡፡ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከእርሱ ጋር ሲሆኑ ሰላም ይሰማቸዋል፡፡** +++ ዕለተ ዕረፍቱ +++ አባ አብርሐም አንድ ካህንና አንድ ዲያቆን ጠርቶ መዝሙረ ዳዊት እንዲደግሙ አዘዛቸዉ ከዚያም ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ በዓቱ እንዲገቡ አዘዛቸዉ ሲገቡም አርፎ አገኙት፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፡፡ እኛንም በድሆች ጳጳስ በቅዱስ አባ አብርሐም ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለም ጸንታ ትኑር፡፡አሜን አሜን አሜን፡፡ በዛሬዉ ዕለት አብረዉ ከሚዘከሩ ቅዱሳን ሰማዕቱ ቅዱስ ኢላዲዮስ ጳጳስ የሰማዕታት አለቃ የሚሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተክርስትያኑ በግብፅ ታነጸ ሰማዕቷ ቅድስት ማርታ ግብጻዊት ብፁዕ ወቅዱስ አባ ቀስማ የግብፅ 44ተኛዉ ፓትርያርክ አቡነ ያሳ ሚካኤል ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፡፡እኛንም በሰማዕቱ ኢላዲዮስ ጳጳስ፡፡ በሰማዕታት አለቃ የሚሆን በቅዱስ ጊዮርጊስ በሰማዕቷ ቅድስት መርታ ግብጻዊት፡፡ በብፁዕ ወቅዱስ አባ ቀስማ የግብፅ 44ተኛዉ ፓትርያርክ፡፡ በአቡነ ያሳ ሚካኤል ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ጸንታ ለዘላለም ትኑር፡፡አሜን አሜን አሜን፡፡ ለወንድማችን Dn. Michael Misrue ቃለ ሕይወት ያሰማልን። @hiwotemenekosat
Показати все...
#ዝክረ_መነኮሳት_ወመነኮሳይያት #ዝክረ_አበው_ጳጳሳት በ Dn. Michael Misrue('My Beloved') ++++ የድሆች ጳጳስ፡፡ ++++ በዛሬዉ እለት(ሰኔ 3) የፋዩም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ቅዱስ አባ አብራአም(አብርሐም)አረፈ፡፡ አባታችን ቅዱስ አባ አብራአም(አብርሐም)የተወለደዉ በግብፅ ውስጥ ጋላድ በሚባለዉ የማላዊ መንደር ከቅዱሳን ቤተሰብ ተወለደ፡፡የልደት ስሙ ጳውሎስ ይባላል፡፡ዕድሜዉ ለትምህርት ሲደርስ በአካባቢዉ በሚገኝዉ ቤተክርስትያን ገብቶ መማር ጀመረ መምህሩ አባ ሩፋኢል(ሩፋኤል) ይባላል፡፡ብሩህ አዕምሮ ስለነበረዉ ሁሉንም የቤተክርስትያን ትምህርቶች አጠና፡፡ ስምንት አመት በሞላዉ ጊዜ እናቱ ባደረባት ህመም በመሞት ተለየችዉ፡፡ነገር ግን ጳውሎስ በሕፃንነት ዕድሜዉ እግዚአብሔርን መጽናኛዉ አደረገ፡፡15 ሲሞላዉ ስሙ የተጠራ ጎበዝ ተማሪ ስለነበር የዲያቆናት ሐላፊ የነበረዉ ሊቀጳጳስ በዲቁና ሾመዉ፡፡ 19 አመት እስኪሞላዉ ደድረስ በመልካም አገልግሎት አገለገለ ልክ 19 አመት ሲሞላዉ አባ ጳውሎስ አል-ሞሐራቂ(የሞሐራቂዉ አባ ጳውሎስ እንደ ማለት ነዉ፡፡)ተብሎ ምንኩስናን በሞሐረቅ ገዳም ተቀበለ፡፡አባ ያኮቦስ የተባለ ሊቀጳጳስ ዝናውን ስለሰማ ከእርሱ ጋር እንዲኖር ጋበዘዉ፡፡አባ ጳውሎስም ከእርሱ ጋር መኖር ጀመረ ሊቀጳጳሱን ቀን ከሌሊት ማገልገል ጀመረ፡፡ቀስ በቀስ የሊቀጳጳሱን ቤት ወደ ድኃ መጠለያነት ለወጠዉ፡፡ለአራት አመታት የሊቀጳጳሱን ቤት አገለገለ በነዚያ አመታት ድሆች ጠግበዉ ያድሩ ነበር ማንም አይቸግረውም፡፡ከዚያም የሊቀጳጳሱን ቤት ለመልቀቅ ወሰነ ለምን ቢባል በከተማዉ ያሉ ሰዎች እያወደሱት ስለነበር ከንቱ ውዳሴን ለመሸሽ ሲል ነበር፡፡ሊቀጳጳሱም የቅስና መዓረግ ሰጥቶት እና መርቆት ባርኮት ሸኘዉ፡፡ ወደ ገዳሙ ሲመለስ ሁለት ሰዎች ተጣልተዉ ነበር የደረሰዉ ነገር ግን በሁለቱ መሐል መግባት አልፈለገም፡፡በገዳሙ በቅድስና እና በትህትና ሆኖ ማገልገል ጀመረ፡፡ከዚያም ከጥቂት አመታት በኋላ የገዳሙ አበምኔት ሆኖ እንዲሾም ተመረጠ ገን እርሱ አልፈለገም በግድ ተጎትቶ የገዳሙ አበምኔት(አለቃ) ሆነ፡፡ጊቢውንም የድሐ እና የነዳያን አደባባይ አደረገዉ፡፡ዝናውን የሰሙ ወጣቶች ከየቦታዉ መጥተዉ ወንጌል እየተማሩ በመመንኮስ የመነኮሳቱን ቁጥር እጥፍ አደረሱት አሳደጉት፡፡ከእነርሱም መካከል 1ኛ አሲዮት የተወለደዉ አባ ማርቆስ አል ሞሐራቂ ጳጳስ(በብፁዕ ወቅዱስ አባ ቄርሎስ 5ተኛ የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 113ተኛ ፓትርያርክ በጵጵስና ወደ ባራሙስ ገዳም ላከዉ በተላከባቸውም ቦታዎች ሁሉ ጸሎተኛነቱ ባሻገር አሮጌ አብያተክርስትያናትን በማሳደስ ስሙ የተጠራ አባት ነበር፡፡) 2ተኛ ቆሞስ አባ ሚካኤል አል ባሂሪ(ይህ አባት ትክክለኛ የመምህሩን የአባ ጳውሎስ ምግባር የወረሰ ሲሆን የቅድስና ማዕረግ ያለዉ ነዉ በሁለቱ አባቶች ያለዉ ፍቅር እና ወንድማማችነት በቃላት አይገለጽም ጸሎትም ለምግብም ለስራም አንድ ላይ ነበር የሚሄዱት፡፡ በሌላ ጊዜ የዚህን አባት ታሪክ ይዤ እመጣለሁ፡፡ታሪኩ አባ ሉቃስ በተባለ ሊቀጳጳስ ተጽፎ ይገኛል) 3ተኛ አባ ማቴዎስ ሊቀጳጳስ ወደ ኢትዮጵያ የተላከ፡፡የመልካም ነገር ጠላት የሆነዉ ሰይጣን በጥቂት ሰዎች አድሮ አባ ጳውሎስ ለ 5 ዓመት ካለበት ገዳም እንዲባረር አደረገዉ፡፡ እነዚያ ሰዎች ምክንያት አድርገዉ ያቀረቡት የገዳሙን ገንዘብ ጨረሰዉ በሚል ነዉ ገዳሙ ለድሆች ክፍት ነበር እንደዚሁም ብዙ ወጣት መነኮሳት እየመጡ ስለነበር ነዉ፡፡ለ5 አመታት ካገለገለበት ገዳም ማስተማር እና ማገልገል እንዲተዉ በመገደዱ ገዳሙን ለቆ ከአራት ደቀ መዝሙሮቹ ጋር ወደ ካይሮ ዋዲ አል ናትሮን ወደ ሚባለዉ በረሐ ወደ ታላቁ አባት ወደ ቅዱስ አባ ቢሾይ ገዳም ሄዱ ከዚያም ከቅዱስ አባ ቢሾይ ገዳም ጥቂት ቆይታ ካደረጉ በኋላ ወደ የባራሙስ ገዳም አመሩ ያኔ የባራሙስ ገዳም አበምኔት የነበሩት አባ ዮሐንስ(((( በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ቄርሎስ 5ተኛ የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 113ተኛ ፓትርያርክ የሆነዉ፡፡)))) በደስታ ተቀብሎ ለሁሉም በዓት ሰጥቶአቸዉ አስቀመጣቸዉ፡፡ ምንም እንኳን አባ ጳውሎስ በትምህርት እና በጸሎት የተጠመደ ቢሆንም ለአካባቢዉ ላሉት ድሆች ግን መራራቱን ፍቅሩን አልተሻማበትም በተለይም አካባቢዉ ለሰፈሩት አረቦች ልዬ ፍቅር ነበረዉ ልብሱን ምግቡን ሳይቀር ያለውን ነገር ሁሉ ከእነርሱ ጋር ይጋራ ነበር፡፡ኢትዮጵያዊዉ ንጉስ አጼ ዮሐንስ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ቄርሎስ 5ተኛን አራት ጳጳሳትን እንዲልክ በመጠየቁ ከእርሱ ጋር የተሰደዱት አራት አባቶች ለጵጵስና ተመረጡ እና ተሾሙ፡፡ 1ኛ አባ ዮክላዴዎስ አል-ሜሪ የተባለዉ አባት ብፁዕ አባ ጴጥሮስ ተብሎ ለአስመራ(ኤርትራ) የተመደበ፡፡ 2ተኛ አባ ዮክላዴዎስ አልካላዲ አል-ሞሐራቂ ብፁዕ አባ ማቴዎስ ተብሎ ለአዲስ አበባ የተመደበ እና ተዓምር የሚያደርግ እና አይን የሚያበራ ነበር፡፡(((((አጼ ዳግማዊ ምንሊክ ለአድዋ ጦርነት ሲሄድ አብሮ የነበረ እንዲሁም አንዲት የገጠር ሴት አይኗ ጠፍቶ ወደ ሐዋርያዉ ቅዱስ ማርቆስ ስትጸልይ ቅዱስ ማርቆስ በሕልም ተገልጦ"""ወደ ጳጳሱ ወደ አባ ማቴዎስ ሂጂ እሱ ቅብዐ ቅዱስ ሲቀባሽ እኔ እጄን አሳርፍብሻለሁ""" አላት እሷም እሺ ብላ ልክ ጳጳሱ ጋር ቀርባ በታላቅ ድምጽ አባቴ ቅዱስ ማርቆስ ልኮኛል ፈውሰኝ አለችዉ ሰዉ ሁሉ ፊት ግን አባ ማቴዎስ እኔ አልችልም አላት ውዳሴ ከንቱ ለመሸሽ ነገር ግን በመንፈስ ተረድቶ ነበርና በምስጢር ሰዉ ልኮ አስመጣት እና ቅብዓ ቅዱስ ቀባት ተፈወሰች፡፡)))))፡፡ 3ተኛ አባ ሰሎሞን አልደጋዊ አልሞሐራቂ ብፁዕ አባ ሉቃስ ተብሎ ለአክሱም የተመደበ፡፡ 4ተኛ አባ ሚካኤል አል መስሪ አልሞሐራቂ ብፁዕ አባ ማርቆስ ተብሎ (ኤክላድዮስ) ተብሎ የተሾሙት አባቶች ናቸዉ፡፡ እነዚህ አባቶች ይህን ማዕረግ ሲሰጣቸዉ እነርሱም መምህራቸዉ ሹመት እንዲያገኝ ለፓትርያርኩ ጠየቁ አባ ጳውሎስ ሹመት ባይፈልግም ነገር ግን ብፁዕ አባ አብራአም (አብርሐም) የፊዩም አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ተብሎ ተሾመ፡፡ወደ ነበረበት አካባቢም ተመለሰ ህዝቡም የዛፍ ዝንጣፊ ይዞ በታላቅ ደስታ ተቀበሉት፡፡ጳጳስ ከሆነ በኋላ እንኳን ብሕትውናውን አልተወም ነበር ልብሱ አልቀየረም የእጁ መስቀል ያዉ መነኩሴ እያለ የሚይዘዉ መስቀል ነበር፡፡በቤተ ክርስትያን ሥርዐት ለጳጳሳት የተለየ ወንበር ነዉ የሚዘጋጀዉ ልክ እንደ ንጉስ ነገር ግን አባ አብርሐም ምዕመናን ከሚቀመጡበት የተለየ ወንበር ከተጋጀለት ሌላ ተራ ወንበር ካላመጡለት አይቀመጠጥም ነበር፡፡ሌላዉ እንደ ቤተክርስትያን ሥርዓት በሥርዐተ ቅዳሴ ለላይ ለሊቃነ ጳጳሳት የሚፀለየዉ ጸሎት "ጸልዬ በእንተ ሊቃነ ጳጳሳት" ላይ የእርሱ ስም እንዲጠራ አይፈልግም ነበር፡፡ሌላዉ ካህናት ወደ እርሱ አካባቢ ማዕጠንት ይዘዉ እንዲያጥኑ አይፈቅድም ነበር(በግብፅ ቤተክርስትያን ስርዐት ካህናት ጳጳሳትን ያጥናሉ ቅዳሴ ላይ ይህም ትህትናን ያመለክታል እንደዚሁም በኢትዮጵያ ምዕመናን ይታጠናሉ፡፡)አባቶች ፊት ሰግዶ መስቀል እና እጃቸውን መሳም የተለመደ ሲሆን አባ አብርሐም ግን እንዲሰገድለትም ሆነ እጁን እንዲስሙ አይፈቅድም መስቀሉን ብቻ እና ብቻ፡፡ ምዕመናን አለቃችን ጌታችን((በግብፅ ቤተክርስትያን ሥርዐት ጳጳሳትን ""ሰይድና"" ተብለዉ ነዉ ምዕመናን የሚጠራዉ ትርጉሙ አለቃችን ጌታችን ማለት ነዉ))ብለዉ ከሚጠሩት ይልቅ አባታችን ሲሉት በጣም ደስ ይለወዋል፡፡ራሱን የመጨረሻ አድርጎ ነበር የሚቆጥረዉ፡፡ .... @hiwotemenekosat
Показати все...
... አንድ ጊዜ ካይሮ በሚገኘዉ የሴቶች ገዳም በሚያስተዳድርበት ጊዜ የነዳያኑን አመጋገብ ለማየት ሲሄድ ለእነርሱ ከቀረበዉ ምግብ ይልቅ ለእርሱ የቀረበዉ ምግብ የተለየ እና የተሻለ ሆኖ አገኘዉ ይህ ነገር ስላላስደተዉ መጋቢዋን መነኩሲት ከምድቧ አሰናበታት፡፡አንድ ቀን ደግሞ ሃና ናክላ የተበለ ሀብታም አባታችን ለአባ አብርሐም ዶሮ እና ሌሎች ልዬ ልዬ ጥሩ ጥሩ ምግቦችን አዘጋጅቶ እንዲላክ አደረገ ነገር ግን አባ አብርሐም የአካባቢውን ድሆች እንዲሰበሰቡ አደረገ ከዚያም ሁሉንም ጋበዛቸዉ እያንዳንዱ ደሐ መመገቡን ቆሞ አይቶ ካረጋገጠ በኋላ እርሱ ጥቂት አትክልት በልቶ ተኛ፡፡ሌላ አልተመገበም፡፡በገዳሙ የሚገኙት ሊቃነ ጳጳሳት በሚያዘጋጁት አጋቢ(አጋፔ የፍቅር ገበታ)ላይ ለሐብታሞቹ የተጠሰ ዓሣ ለድሆቹ ደግሞ የተቀቀለ ዓሣ ቀረበ ይህንን ያስተዋለዉ አባ አብርሐም በጣም ተቆጥቶ የተጠበሰዉ ዓሣ እና የተቀቀለዉ ዓሣ እንዲደባለቅ አዘዘ ቀጥሎም እንዲህ አለ"""የተደባቀውን ዓሣ ለመመገብ የሚመኝ ሁሉ ይመገብ እግዚአብሔር ሐብተታም ደሐ ትልቅ ትንሽ አይልም አይለይም ሁሉ በእርሱ ዘንድ እኩል የአዳም ልጆች ናቸዉ፡፡""" አለ ይህን የተመከቱት ነዳያን ወዳጆቹ በእውተኛ አባትነቱ ሲደሰቱ ሀብታሞቹ ደግሞ በመንፈሰ ጠንካራነቱ ለድሐ ባለዉ ፍቅር የተደባለቀውን ዓሣ ቅቅል እና ዓሣ ጥብስ በደስታ ተመገቡ፡፡ አንዲት ሴት ስለችግሯ ባጫወተችዉ ጊዜ ትራሱ ስር ገንዘብ ሲፈልግ አጣ ከዚያም አንድ ወዳጁ ያመጣለትን ያንገት ልብስ አዲስ ያንገት ልብስ አውጥቶ ሰጣት(አዲስ ልብስ ገዝተዉ ሲሰጡት አይለብስም፡፡አሮጌ ብቻ ነዉ የሚለብሰዉ፡፡) ያንን ልብስ ወስዳ ሸጠችዉ የገዛዉ ደግሞ ያ ወዳጁ ነበር ገዝቶ ወደ አባ አብርሐም ቤት መጣ እና """አባታችን የሰጠሁን ሻርፕ የት አደረክኸዉ""" አለዉ አባታችን መልሶ """ላይ ቤት አስቀምጨዋለሁ""" አለዉ ወዳጁም ይኸዉ እንደገና ከሌላ ሰዉ ለይ አግኝቼ ገዛሁት አለዉ አባ አብርሀምም መልሶ"""ሙሉ ዋጋውን ነዉ የሰጠሃት???""" አለዉ """"አዎ ሙሉ ዋጋውን ነወዉ የሰጠኃኋት አላስከፋኋትም፡፡"""አለዉ መልሶ የአንገት ልብሱን ሰጥቶት ሄደ፡፡ በሌላ ጊዜ አንድ ሐብታም እጅግ ውድ ለስላሳ የሆነ የአንገት ልብስ ገዝቶ ሰጠዉ እንደ ተለመደዉ አስቀመጠዉ እና ከዚያም አንድ ገበሬ በብርድ ሲንቀጠቀጠጥ አየዉ ጭንቅላቱን እየነቀነቀ """" ወይ ጉድ ይህህን ያንገት ልብስ እንደሚያስፈልግ ያወቀ እግዚአብሔር ነዉ ያዘጋጀልህ""""ብሎ አውጥቶ ሰጠዉ፡፡ያ ገበሬ በጠዋት ያንገት ልብሱን ሲያየዉ ሐብታሞች የሚለብሱት ነዉ ወዲያውኑ ሸጦ ለእርሱ ርካሽ ጀለቢያ ገዛ የያንን የገዛዉ ደግሞ ያ መጀመሪያ የገዛዉ ሐብታም ነበር፡፡እንደገና ይለብሰዋል በሚል ተስፋ እንደገና ገዝቶ ሰጠዉ፡፡ አባ አብርሐም ተቀብሎ እግዚአብሔር ያዘዘለት ተረኛ እስኪመጣ ድረስ በትራሱ ስር አኖረዉ ... @hiwotemenekosat
Показати все...
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 "የማርን ጥፍጥና ማርን ቀምሶ ለማያውቅ ሰው በመቅመስ እንጂ በቃላት ማስተማር እንደማይቻል ሁሉ የእግዚአብሔርን መልካምነት በቃላት በጠራ መልኩ ማስተማር አይቻልም። ራሣችን ወደ እግዚአብሔር መልካምነት ዘልቀን መግባት ይኖርብናል እንጂ።" ✨ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ✨ "የተባረከ ሰው ማለት የራሱን ድክመት የሚያውቅ ሰው ነው። ምክንያቱም ይሄ የእውቀቱ መሠረትና የሁሉም መልካም ነገሮች መጀመሪያ ይሆንለታልና፡፡" ✨ ማር ይስሐቅ✨ እስካልበደልን ኃጢአትም እስካልሠራን ድረስ የምንኖረው በእግዚአብሔር ነው፡፡ ✨ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ✨ የእግዚአብሔር ቃላት የነፍስን ሙቀት ያድሳሉ፡፡ እንድታድግ ከፈለግህ የእግዚአብሔርን ቃላት እንደ ህጻን ልጅ መጥባት አለብህ ✨ቅዱስ አትናቴዎስ✨ የሰው ልጅ በወደቀ ጊዜ እግዚአብሔርን መምሰል ተነጥቆ ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶሰ የመጣው ያጣነውን ክብር ሊመልስልን ነው፡፡ ✨ቅዱስ አትናቴዎስ✨ "እግዚአብሔርን በምልዓት ማወቅ ባይቻልም በአቅማችን የተገለጠልንን ያህል ከመመስከር እና ስለ እርሱ ከመናገር ከመጻፍ ራሳችንን ልናሳርፍ አይገባም! " ✨ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ✨ 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
Показати все...
#ገድለ_መነኮሳይያት #ተነሳሕያን_መነኮሳት ቅድስት ማርታ ግብጻዊት(ተጋዳላይት) ****** በግብጽ ምስር(ካይሮ) ከተማ ከሀብታም ክርስቲያን ቤተሰቦች ተወለደች፡፡በወጣትነቷ ዝሙትን እና ርኩሰትን ትወድ ነበር፤ ስራዋም የታወቀ ነበር፡፡ ነገር ግን ከላይ የሆነው የእግዚአብሔር ቸርነት ጠበቃት፣ ወደ ቤተክርስቲያን እንድትሄድ አነሳሳት፡፡ ቀኑም የጌታ ልደት ቀን(ገና) ነበር፡፡ ወደ በሩ ደርሳ ወደ ውስጥ ለመግባት ስትል ጠባቂው ሰው እንዲህ አላት :-" ወደ ተቀደሰው ቤተክርስቲያን እንድትገቢ ላንቺ የተገባ አይደለም፣ አንቺ ማን እንደሆንሽ አንቺም ታውቂዋለሽ" በሁለቱ መሃል ጭቅጭቅ ተፈጠረ፣ ይህን የሰሙት ጳጳስ የሆነውን ለማወቅ ወደ በሩ መጡ፡፡ ባዩአትም ጊዜ እንዲህ አሏት "የእግዚአብሔር ቤት ቅዱስ እና ወደርሱም የሚገቡት ለመነጻት ራሳቸውን ያዘጋጁ ብቻ እንደሆኑ አታውቂም?!"፡፡ ይህን ስትሰማ አምርራ አለቀሰች፤ እንዲህም አለች "አባ ሆይ ተቀበለኝ ከዚህች ሰዓት ጀምሮ ተነሳሒ(ተጸጻች) እሆናለሁ፣ ወደ ቀደመው ኃጢአቴም እንዳልመለስ ወስኛለሁ" ጳጳሱም መልሰው "የምትይው እውነት ከሆነ ጌጣጌጦችሽን እና ልብሶችሽን እዚህ አምጭ" አሏት፡፡ ፈጥና ሄዳም ሁሉንም ልብሶቿን እና ጌጣጌጦቿን አምጥታ ለጳጳሱ ሰጠች፡፡ ሁሉም እንዲቃጠል ካዘዙ በኃላ ጸጉሯን ላጯት፡፡ የምንኩስናን ልብስም አልብሰው ወደ አንዱ የእናቶች ገዳም ላኳት፡፡ በዚያም ታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎን ተጋደለች፤ ዘውትርም በጸሎቷ እንዲህ ትል ነበር:- "ኦ ክርስቶስ አምላኬ ከቤትህ አገልጋይ(ከጳጳሱ) ፊት ውርደትን መሸከም ያልቻልኩ እኔን እባክህን በመላዕክትህ እና ቅዱሳንህ ፊት አታሳፍረኝ"፡፡ በመንፈሳዊው ተጋድሎ ጸንታ ለ25 ዓመታት ቆየች፣ በነዚህም ጊዜያት ከገዳሙ በር አልወጣችም፤ ከዚያንም በሰላም አረፈች፡፡ ጸሎቷ ከኛ ጋር ይሁን፡፡ አሜን
Показати все...

Показати все...
ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፫

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን

Показати все...
ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፬

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን