uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ETHIO CRYPTO ™

ETHIO CRYPTO ™

Відкрити в Telegram

Join us✨ for insightful analysis, expert tips, and exclusive strategies to maximize your returns in the dynamic world of digital assets. we launch projects on how to make money online🌟

Показати більше
3 571
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
-8230 днів
Архів дописів
በትግራይ ክልል ላለፉት ሦስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ተጠናቋል። ፈተናው በክልሉ በ75 ወረዳዎች በሚገኙ 1,007 ትምህርት ቤቶች ተሰጥቷል። 60 ሺህ የሚጠጉ የስምንተኛ ክፍል ተ
በትግራይ ክልል ላለፉት ሦስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ተጠናቋል። ፈተናው በክልሉ በ75 ወረዳዎች በሚገኙ 1,007 ትምህርት ቤቶች ተሰጥቷል። 60 ሺህ የሚጠጉ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን እንደወሰዱ ተገልጿል። ፈተናውን በ518 ትምህርት ቤቶች ለመስጠት አለመቻሉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል። @StudenT_Text

የመውጫ ፈተና ተጀመረ። የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ያደረገው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን የመውጫ ፈተና በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀምሯል። በመንግሥት ከፍተኛ
+1
የመውጫ ፈተና ተጀመረ። የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ያደረገው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን የመውጫ ፈተና በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀምሯል። በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የመንግሥት እንዲሁም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ፈተናቸውን በ " ኦንላይን " መውሰድ ጀምረዋል። ዛሬ የመውጫ ፈተናቸውን መውሰድ የጀመሩት የጤና ተማሪዎች ናቸው። በቀጣይ ሳምንት ሰኞ ደግሞ ከጤና ተማሪዎች ውጭ የሆኑ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል። @Student_Text

photo content

የሀዋሳ ከተማ የሞዴል ፈተና ጊዜ ሰሌዳ
የሀዋሳ ከተማ የሞዴል ፈተና ጊዜ ሰሌዳ

Repost from ETHIO CRYPTO ™
የትምህርት ጥቆማ ለዘንድሮው የ8 - 12 ላላችሁ ተማሪዎች ያጠናቹት ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ የሚረዳ አሪፍ ቦት @neagovetbot አጠቃቀሙ 1. Start 2. practice exam 3. select grade 4. select subject 5. Select time and start @student_text For comment @text_book_1 ለሁላችንም መልካም የጥናት ጊዜ

ብሔራዊ ፈተና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ምክክር መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። በመድረኩ፦ - የትምህርት ሚኒስቴር፣ - የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች፣ - የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣  የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች እና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፤ ከሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በ102 የፈተና ጣቢያዎች የሚካሄደው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታውንና የክረምቱን የአየር ሁኔታ ያገናዘበ በርካታ የሰው ኃይል መመደቡን አሳውቋል። ፈተናው ከሥርቆት በፀዳ መልኩ እንዲካሄድ ሁሉም ኃላፊነቱን ወስዶ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባም ኮሚሽኑ አሳስቧል። በአማራና በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች በፈተና ጣቢያዎች የፀጥታ ችግሮች እንዳይከሰቱ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቂ ዝግጅት ማድረጉንም ኮሚሽኑ አሳውቋል። ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ፦ - የሀኪም ማዘዣ የሌለው መድሃኒት በሽሮፕም ሆነ በታብሌት፣ - የህክምና መስጫ መርፌ፣ - የአንገት ሀብል፣ - የፀጉርና የጆሮ ጌጥ፣ - ከጋብቻ ቀለበት ውጭ ፈርጥ ያለው የጣት ቀለበት እና የእጅ አንባር አድርገው መምጣት እንደማይችሉ ፖሊስ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። በተጨማሪም ፦ - ተንቀሳቃሽ  ስልክ፣  - አይ-ፓድ፣ - ታብሌት፣ - ላፕቶፕ፣ - ስማርት ሰዓት፣ - ሲዲ፣ - ሚሞሪ ሪደርና ኦ-ቲጂ ኮንቨርተር እንዲሁም ፎቶ የሚያነሱ እና ድምፅ የሚቀርፁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል። የተከለከሉ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲዎቹ ግቢ ውስጥም ሆነ በዙሪያው ይዞ መገኘት፣ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት እንዲሁም በዩኒቨርሲቲ ግቢ ወስጥ በግልም ሆነ በቡድን ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው። ይህንን ተላልፎ በተገኘ ተማሪ ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል። የትምህርት ሚኒስቴር ፤ አንዳንድ የትራንስፖርት ችግሮችን ለመቅረፍ፣ ለተማሪዎች ከትምህርት ቤት ጀምሮ በወረዳና በዞን ትምህርት ቢሮ አማካኝነት የፈተና መመሪያ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ መሆኑን አሳውቋል። መረጃ ከፌዴራል ፖሊስ

ከከበዳችው ተጠቀሙበት 😂
ከከበዳችው ተጠቀሙበት 😂

#EXIT _EXAM" አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አልተገኙም " የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
#EXIT _EXAM" አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አልተገኙም " የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ አስጠንቅቋል። የግል እና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞዴል የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ከዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም መሰጠት ተጀምሯል፡፡ ይሁን እንጂ ባለሥልጣኑ ዛሬ ባደረገው ክትትል፤ አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዳልተገኙ ገልጿል። የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ተማሪዎቻቸው ሞዴል ፈተናውን እንዲወስዱ አለማድረጋቸውንም ባለሥልጣኑ ጠቁሟል፡፡ በመሆኑም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በአቅራቢያቸው በሚገኙ ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ   የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን በመላክ ሞዴል ፈተና እንዲወስዱ ማድረግ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አሳስቧል። @student_text

የሪሚዲያል ተማሪዎች ዛሬ ፈተና መሰጠት ይጀምራል፡፡ በ2014 ዓ.ም የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የነበሩና በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተ
የሪሚዲያል ተማሪዎች ዛሬ ፈተና መሰጠት ይጀምራል፡፡ በ2014 ዓ.ም የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የነበሩና በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማጠናከሪያ ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የሪሚዲያል ፈተና ከዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል። ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን ለሚሰጡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የላከው የጊዜ ሰሌዳ እንደሚያሳየው ፈተናው ዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 መሰጠት ይጀምራል፡፡ የፈተና የፍተሻና የክፍል ቅድመ ዝግጅት በየዕለቱ ከቀኑ 8:00 የሚጀምር ሲሆን ፈተናው ደግሞ ከቀኑ 9:00 መሰጠት ይጀምራል። ተፈታኝ ተማሪዎች ለፍተሻ እና የክፍል ቅድመ ዝግጅት ሥራ 8:00 ላይ በመፈተኛ ክፍላቸው  በር ላይ እንዲገኙ ተብሏል፡፡ @Student_TexT

የ8ኛ ክፍል ፈተና የ8ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ሰኞ መሰጠት ተጀምሯል። ፈተናው ለሁለት ቀናት ይሰጣል። በከተሞች እንዲሁም በክልሎች በሚሰጠው በዘንድሮው ዓመት የ8ኛ ክፍል ፈተና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ይፈተናሉ። @Student_Text

የመውጫ ፈተና ላይ የሚፈፀሙ የደንብ ጥሰቶች እንደ ችግሩ ስፋት እና ጥልቀት የትምህርት ማስረጃ መከልከል ፣ ጥሰት የፈፀመው ተማሪ ድጋሚ ለፈተና እንዳይቀመጥ የማድረግን እርምጃ ሊያካትት እንደሚችል ተጠቁሟል። ባለፍው ሰኞ ሰኔ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በበየነ መረብ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከመንግስት ዩኒቨርስቲ አመራሮችና ባለቤቶች ጋር ዉይይት አደርጎ ነበር። በዚህ ውይይት ማጠቃለያ ላይ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2015 ዓ/ም ከሚሰጠው የመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ የጋራ ሊደረጉ የሚገባቸው ጉዳዮችን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል። - ለመዉጫ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎችን በተመለከተ በ2015 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር የትምህርት ዘመን ትምህርታቸዉን ያጠናቀቁ ወይም ተመዝግበው በመማር ላይ ያሉ እና ከዚህ በፊት ለህግና ጤና መዉጫ ፈተና ቀርበዉ ያላለፉ ተማሪዎች ይሆናሉ፡፡ ይህም ሆኖ ከዚህ በፊት ዝርዝራቸዉ ከተላከውና መለያ ኮድ ከተሰጣቸዉ ውጭ አንደ አዲስ የሚላክና የሚካተት ተማሪ አይኖርም ተብሏል። - በመዉጫ ፈተና ያለፉ ተማሪዎች በትምህርት ማስረጃቸው ማለትም በትራንስክሪፕት ላይ የመዉጫ ፈተና የወሰዱበት ወር፣ ዓመትና ከ100 ያስመዘገቡት በግልጽ የሚጻፍ ይሆናል። - በመዉጫ ፈተና ወቅት ለሚያጋጥሙ ፈተና ደንብ ጥሰቶች ሊወሰዱ የሚገቡ የዲሲፕሊን እርምጃዎችን በተመለከተ በዩኒቨርስቲዎች የዲሲፕሊን እርምጃ አወሳሰድ አሰራር የሚታይ ሆኖ የዲሲፕሊን እርምጃዉ እንደ ችግሩ ስፋትና ጥልቀት የትምህርት ማስረጃ መከልከል፣ ድጋሚ ለፈተና እንዳይቀመጥ ማድረግ እና ሌሎች እርምጃዎችን ሊያካትት እንደሚችል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። - በመዉጫ ፈተና አንድ ላይ የተጠቃለሉ ፕሮግራሞችን በተመለከተ በጋራ (በወል) የተዘጋጁ በአንድ ወይም የተለያዩ ሁለትና ከዚያ በላይ ስያሜ የሚጠሩ ፈተናዎች ያሉ ሲሆን ሌሎች ፕሮግራሞችን በተመለከተ በተቋማት የተሰጣቸዉ ስያሜ አጠራርን ይዘዉ የተዘጋጁ መሆናቸዉን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ለግል እንዲሁም ለመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ  ፤ ተመሳሳይ ፈተና እንዲኖራቸው የሆኑ ፕሮግራሞች እንዲሁም በስያሜያቸው ፈተና የተዘጋጀላቸው ፕሮግራሞችን በአባሪ አድርጎ በዝርዝር አሳውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለግል እና ለመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከውን ደብዳቤ የተመለከተና ትክክለኝነቱንም ከሚመለከተው የትምህርት ሚኒስቴር አካል ያረጋገጠ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለማሳወቅ ይወዳል።

Exit Exam " የሚሰጠው ሞዴል ፈተና በጥያቄ ክብደቱም ሆነ በብዛቱ ከዋናው የመውጫ ፈተና ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የግል እና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞዴ
+3
Exit Exam " የሚሰጠው ሞዴል ፈተና በጥያቄ ክብደቱም ሆነ በብዛቱ ከዋናው የመውጫ ፈተና ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የግል እና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞዴል የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 29 - 2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ የሙከራ ፈተናው ከ168 ሺህ ለሚበልጡ ዕጩ ምሩቃን እንደሚሰጥ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና ለኢዜአ ተናግረዋል። አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና በመስጠት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡ የሙከራ ፈተናው ተማሪዎች የራሳቸውን መለያ ቁጥር እና የይለፍ ቃል ተጠቅመው በቀላሉ መፈተን እንዲችሉና ከፈተና ስርዓቱ ጋር እንዲተዋወቁ የሚያስችል መሆኑን አመልክተዋል። ለሁሉም የግልና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጥያቄ ክብደቱም ሆነ በብዛቱ ከዋናው የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሞዴል ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 29/2015 ዓ.ም በተመሳሳይ ጊዜ እንደሚሰጥም ኃላፊው ገልጸዋል። የ2015 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል። @student_Text

ሰላም ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች እንዲለቀቁ የምትፈልጉትን ማንኛውም ነገር ወይም እንዲስተካከል የምትፈልጉትን #ኮመንት /#comment / ላይ አስቀምጡልን። @StUDenT_TExT

የ2015ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የፈተና አስተዳደር ማስፈጸሚያ ሰነድ ሰኔ/2015 ዓ.ም የሚኒስትሪ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች 1.የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡ 2.በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን ክብ ብቻ መጠቆር አለበት፡፡ 3.ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው ክብ ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡ 4.ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን ክብ በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡ 5. በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ ክብ ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡ 6) ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ 7.ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ 8.መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ 9. ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡

8.61 KB

#ስኩል ላይፍ አበቃ 😭😭😭😭

8.61 KB

ትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅን አጠናቋል ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዝግጅት መጠናቀቁን አስታወቀ። ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል
ትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅን አጠናቋል ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዝግጅት መጠናቀቁን አስታወቀ። ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል። በሚኒስቴሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ ዶ/ር እዮብ አየነው ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል ፤  " የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎችን እውቀትና ብቃት ለመለካት የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅት ተጠናቋል " ብለዋል። ዶ/ር እዮብ ፤ " ገበያው የሚፈልገውን ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የመውጫ ፈተናው ከ2015 ጀምሮ በሁሉም የትምህርት መስኮችና መርሐ ግብሮች መስጠት እንዲቻል ስራዎች ከአንድ ዓመት በላይ ሲሰሩ ቆይቷል " ሲሉ አስታውሰዋል።

በ 2015, የ 12ኛ ክፈተናን የሚወስዱ ተማሪዎች 869,765 ናቸው። ከዚህ ውስጥ       Natural Science 365,954 ተማሪዎች       Social Science 503,812 ተማሪዎች ናቸው ። በመጀመሪያ ዙር ፈተና የ Social Science ተማሪዎች     ሐምሌ 16 -17/2015 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።     ሐምሌ 18, የፈተና ኦረንቴሽን ይሰጣል።     ከሐምሌ ከ 19 - 21/2015 ፈተናው ለ 3'ት ቀናት ይሰጣል ።      ሐምሌ 22-23/2015 ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ። በሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች        ሐምሌ 22 -23/2015 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።         ሐምሌ 24/2015 የፈተና ኦረንቴሽን ይሰጣል።          ከሐምሌ 25 -28/2015 ፈተናው ለአራት ቀናት ይሰጣል።           ሐምሌ 29-30/2015 ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ። @student_text

ብሔራዊ ፈተና የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡ ለ2ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠውን አገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ 869 ሺህ 765 ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን በአገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወንደወሰን ኢየሱስወርቅ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡ ከተመዘገቡት ውስጥ 503,812 ተማሪዎች የሶሻል ሳይንስ እና 365,954 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል። የፈተና አስፈጻሚዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ምልመላ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30/2015 ዓ.ም በሁለት ዙር እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ @student_texf