uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ETHIO CRYPTO ™

ETHIO CRYPTO ™

Відкрити в Telegram

Join us✨ for insightful analysis, expert tips, and exclusive strategies to maximize your returns in the dynamic world of digital assets. we launch projects on how to make money online🌟

Показати більше
3 571
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
-8230 днів
Архів дописів
+6
Amharic for Grade 1.pdf23.35 MB

New Curriculum 📚 Textbooks

New cariculem Grade 1 Text Books

#ብሔራዊ_ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ኮማንድ ፖስት በፈተናው ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ፦ • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ • የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ • የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣ • የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ • የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ • የፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ሀላፊዎች እና የክ/ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናውን ፦ - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ - ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ - ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ - አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ - ፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተገልጻል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የተፈታኞችን መብትና ግዴታዎች አቅርበዋል። #የተፈታኞች_መብቶች_የሆኑት፡-  ➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው። ➭ በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው። ➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው። ➭ የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው። ➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው። ➭ ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው። #የተፈታኞች_ግዴታ_የሆኑት፡- ➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት #ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት። ➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ  ሲመጣ  አንሶላ፣  ብርድልብስና  የትራስ  ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት። ➤ #ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት አለበት። #ለተፈታኞች_የተፈቀዱ_ነገሮች ፦ ➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ  ደብተር ፣ የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት ➣ ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንዱች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….) ➣ ገንዘብ (ብር) ➣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ ➣ የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት) #ለተፈታኞች_የተከለከሉ_ነገሮች ፦ ⮕ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው። ⮕ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና  ሌሎች  ማንኛቸውም  ፎቶ፣  ምስል  እና  ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ  ዙሪያ  ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት  ወይም  መጠቀም  የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣  ሲጋራ፣  በሓኪም  ማዘዣ  የሌለው  መድኃኒት  (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ) ⮕ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ  45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡ ⮕ በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ የተመዘገቡ ሲሆን ፈተናው ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው ይፈተናሉ ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ ያገኛሉ። @sTUdeNT_TExT

[In reply to TIKVAH-ETHIOPIA] [ Album ] #ብሔራዊ_ፈተና ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ከ50 ኪሎ ሜትር በላይ ለሆኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪን ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚሸፍኑ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል። ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አገልግሎቱ ገልጿል። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍ ቢ ሲ) የሰጡት ቃል ፦ - ፈተና ማተም ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ከወዲሁ ተጠናቀዋል። - ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በ50 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ተፈታኝ ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪን በራሳቸው ይሸፍናሉ፤ ከ50 ኪሎ ሜትር ርቀት #በላይ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች ወጪያቸውን ይሸፍናሉ። - ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ #የሚፈቀዱላቸው ፦ • መጽሐፍት፣ • ሲያጠኗቸው የነበሩ ማስታወሻወች፣ • የንጽህና መጠበቂያዎች • የሌሊት ልብስ ከተፈቀዱት ቁሳቁስ መካከል ናቸው። ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ ፣ የመፈተኛ ካርድ ወይም አድሚሽን ካርድ መያዝ ይኖርባቸዋል። - ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ #የሚከለከሏቸው ቁሳቁስ፦ • ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ • ከጋብቻ ቀለበት ውጪ የተለየ ፈርጥ ያላቸው ቀለበቶች፣ • ሀብሎች ፣ • የጸጉር ጌጦች • ድምጽ የሚያወጡ ጃኬቶች መያዝ አይቻልም። - የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የመኝታና የምግብ አገልግሎት ያመቻቻሉ። @STuDEnt_TeXT

[ Album ] " የምንሄድበት የለም፤ መፍትሄ ይፈለግልን " - ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርታቸውን ለመከታተል ከተለያዩ የፀጥታ ችግር ካለባቸው የሀገራችን ክፍሎች የመጡ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ተከትሎ ጭንቀት ውስጥ እንዳሉ ገልፀዋል። የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መሰጠቱን ተከትሎ ፈተና የሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ማንኛውም ተማሪ እንዳይገኝ ተብሏል። ይህ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኙ የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን ጭንቀት ውስጥ የከተተ ሲሆን ተማሪዎቹ መፍትሄ ይፈለግላቸው ዘንድ ጠይቀዋል። አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባልና ቤተሰቦቹ በሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ፤ "ወደ መጡበት ቦታ መመለስ የማይችሉ ተማሪዎች ምን ሊደረጉ ነው ? ጦርነት ካለበት ቦታ የመጣን ተማሪዎች አለን ድምፃችን ተሰምቶ መፍትሄ ይፈለግልን፤ ወደ ቤታችን መሄድ አንችልም፤ መሄጃም የለንም" ብሏል። ሌሎችም ተማሪዎች በተመሳሳይ መሄጃቸው እንደጨነቃቸው ገልፀዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብቻ 50 የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች መኖራቸው ለማወቅ የቻለ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለእነዚህ መሄጃ ለጠፋቸው ተማሪዎች ምን አሰቧል በሚል ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የቅርብ ሰው ጥያቄ አቅርቦ ነበር። እኚሁ ሰው ዩኒቨርሲቲው ለትምርህት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቦ ከግቢ ይውጡ እንደተባለና ምናልባት ከፈተና መለስ እንደሚመለሱ አስረድተዋል። መሄጃ የሌላቸው ተማሪዎች እስከዛ የት እንዲያርፉ ታስቧል ለሚለው ጥያቄ፤ ከግቢ ወጥተው ወደየ መጡበት/ቤተሰብ ጋር ይሂዱ መባሉን ገልፀዋል። በዚህ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አቅጣጫ ቢያስቀምጥ ጥሩ እንደሆነ ጠቁመዋል። ት/ት ሚኒስቴር ሚሰጠን ምላሽ ካለ እናሳውቃለን። @studenT_tEXT

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች  በሙሉ የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ:- 2014/15 የኢትዮ ዩኒቨርሲቲ መግቢያና የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ካምፖስ ጉዞ ሲያደርጉ መያዝ የተፈቀደላቸው፣ መያዝ የተከለከሉ እና የጊዜ ሠሌዳ እንደሚከተለው ያለው ሲሆን ተማሪዎች ከወዲሁ ራሣችሁን እንድታዘጋጁ ይሁን።       ❶ መያዝ የተፈቀደላቸው 👉አንሶላ፣ 👉ትራስ ጨርቅ፣ 👉የማታ ልብስ፣ 👉ደረቅ ምግብ፣ 👉ልብስ፣ቦርሳ፣ 👉የመፈተኛ ካርድ፣እርሳስ፣ላጲስ፣የማስታወሻ ደብተር፣ባዶ ወረቀት፤መጽሐፍ      ❷ መያዝ የተከለከሉ 👉ማንኛውም ድምፅ የሚቀዳ፤ቪዲዮ የሚቀዳ  ወይም ፎቶግራፍ የሚያነሳ፤ 👉ካሜራ 👉ማንኛውም ከቴሌ መስመርም ይሁን ከቴሌ ውጭ መልዕክት በድጂታል ቴክኖሎጂ መቀበያ ወይም ማስተላለፊያ ውጤቶች(ታብሌት፣ኮሚፕዩተር፣ላብቶፕ፣ ስልክ፣አይፓድ፥ሃርድ ዲስክ፣ፍላሽ)         ❸ የጊዜ ሠሌዳ ማህበራዊ ሳይንስ social science dep't ➤26_28/1/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ ➤29/01/2015 ኦሬንተሽን ➤30/01/2015_02/02/2015 ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል። የተፈጥሮ ሳይንስ Natural Science dep't ➤05_06/2/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ ➤07/02/2015 ኦሬንተሽን ➤08/02/2015_11/02/2015 ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል። ትምህርት ሚኒስቴር @student_tEXt

[In reply to TIKVAH-ETHIOPIA] [ Album ] #NationalExam ለ12ኛ ክፍል የብሄራዊ ፈተና አስፈፃሚዎች ስልጠና ተሰጣቸው። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ማጠናቀቂያ ፈተና አስፈጻሚዎች ሥልጠና እንደተሰጣቸው ገልጿል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ የፈተና አስፈፃሚዎች ትልቅ ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን በመገንዝብ በትጋትና በታማኝነት እንዲወጡ በማሳሰብ ዝርዝር የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው ፤ የፈተና አስፈፃሚዎች በቂ ትኩረት በመስጠት ያለ ምንም አድልዎ ሙያዊ በሆነ አግባብ እንዲሁም በቁርጠኝነት የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አስገንዝበዋል። ዝርዝር ስልጠና በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አመራርና በዘርፉ ባለሙያዎች ተሰጥቷል። የ2014 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከመጪው መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በሁለት ዙር ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል። @student_text

የትምህርት ሚኒስቴር በአብዛኛው የሀገሪቷ አካባቢዎች የ2015 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በዛሬው እለት መጀመሩን አሳውቋል። በዛሬው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ በይፋ በተጀመረው የ2015 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ት/ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ተቀብለው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክትና መመሪያ ማስተላለፋቸውን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ፤ የትምህርት ዘመኑ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርቧል። የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ስራ የሚከናወነው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውሷል። @student_text

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ከተዘጋጀው ፤ የ4ኛ ክፍል የሒሳብ መፅሀፍ ጋር በተያያዘ አንድ በመፅሀፉ ስራ ላይ የተሳተፈና ስሙን መግለፅ ያልፈለገ የቤተሰባችን አባል በመፅሀፉ ውስጥ መነጋገሪያ የሆነው " የግዕዝ ቁጥሮች ምልክቶች በቀጥታ ከግሪክ ነው የተወሰዱ ናቸው። " የሚለው ሀሳብ በእርግጥም በሶፍት ኮፒ ላይ እንደነበር አረጋግጠዋል። ነገር ግን ይሄ ሶፍት ኮፒ መፅሀፉ ከመታተሙ በፊት ኤዲት ሳይደረግ መምህራን ለዝግጅት እንዲሆናቸው ተብሎ በችኮላ የተላከ እንደነበር ፤ በኃላም ይሄንን ጨምሮ ሌሎች ያልታረሙ ሀሳቦች፣ ስሌቶች፣ የቃላት ግድፈቶች ታርመው አሁን ላይ የተስተካከለው መፅሀፍ መታትሙን አስረድተዋል። አዘጋጆችና ገምጋሚዎች በመፅሀፉ ውስጥ የነበሩ ክፍተቶችንና ስህተቶችን የማስተካከል ስራ የተሰሩት ቀደም ብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከመውጣቱ በፊት ነው ብለዋል። በዚህም አሁን ላይ የተስተካከል መፅሀፍ መታተሙን ገልፀዋል። ሙሉ ቃላቸው ፦ " በመጀመሪያ ደረጃ መፅሀፉ አልታተመም (ከግሪክ በቀጥታ የተወሰደ ነው የሚለውን ሀሳብ የያዘው) ፤ የታተመው መፅሀፍ ይህ የለበትም። ትምህርት እንዲጀምርና ስኬጁል እንዲያወጡ ተብሎ ይመስለኛል (ሁሉም ነገር ላይ ስለማልገባ ነው ይህን ያልኩት) ሶስት ቻፕተር ተቆርጦ እንዲላክ ጠይቀውን  እኛም ቆርጠን ልከናል። በአጋጣሚ ተቆርጦ የተላከው ኤዲት ያልተደረገው ነው። በኃላ ኤዲቶሪያሉ / ገምጋሚዎቹ ይሄ ይውጣ፣ ይሄ ይግባ ብለው ሚቀነሰውን ቀንሰው መስተካከል እና መታረም ያለበትን አስተካክለዋል። መጃመሪያ ኤዲት ያልተደረገው ተቆርጦ በመውጣቱ ነው ነገሩ የተጋጋለው ነገር ግን ታትሞ የወጣው የታረመው እና በገምጋሚዎችም የተስተካከለ ነው። መንግስትም ይሄን ግልፅ ቢያደርገው ኖሮ ጥሩ ነበር። በአጭሩ ግን መጀመሪያ ላይ ተቆርጦ የተላከው፣ መምህራንም የደረሳቸው ያልተስተከከለው ነው። ይሄ ነገር በዚህ ደረጃ ከመሆኑ በፊት ሶፍት ኮፒው የደረሳቸው ሰዎች እራሳቸው ት/ት ቢሮውን ቢጠይቁ ጥሩ ነበር ፤ እንዴት ሊሆን ቻለ ብለው ከዛ ያልተስተካከለው እንደሆነ ግልፅ ይሆን ነበር። በነገራችን ላይ ይሄ ብቻ ሳይሆን ብዙ የተስተከከሉ አሉ። ከዛ በኃላ እራሱ ብዙ ኤዲት ተደርጓል። በአጋጣሚ ይሄኛው ታየ እንጂ በዝግጅት ወቅት ብዙ ታርሟል። አሁን መናጋገሪያ የሆነው ሀሳብ ከአዘጋጆቹ አንዱ መረጃውን በሚያሰፍርበት ጊዜ የተሳሳተው ነው። ከዛም ስህተቶች ሲገኙ ታርሟል። በአጋጣሚ መምህራን እንዲዘጋጁበት በፍጥነት ላኩ ስለተባለ ያልተስተካከለው ተቆርጦ ተላከ እንጂ ይህ ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሳሆን ቀደም ብሎ ነው የተስተካከለው። በዛም ነው አሁን የተስተካከለው የታተመው። እኔ እስከማውቀው ግለሰቡም፤ ሌሎችም አዘጋጆች ምንም ሌላ አጀንዳ የላቸውም። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከሃይማኖት እና ከብሄር ጋር እያገናኙ እንደሚያወሩትም አይደለም፤ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙ ሲባል ስላየሁ ነው ገምጋሚዎቹም አዘጋጆቹም በሃይማኖት ሆነ በብሄር ምንም ችግር የሌለባቸው አንድ ላይ በጋራ በሀገራዊ መንፈስ በትብብር ያዘጋጁት ነው። በዝግጅት ወቅትም እንዲህ አድርጉ፣ እንዲህ አታድርጉ የሚል የመንግስት ጣልቃ ገብነት አልነበረም። እንደዛ አይነት ነገር ቢኖር እኔም በግል አልሰራም ነበር። መፅሀፉ በጣም ተደጋግሞ ነው የተገመገመው ፣ ከህትመት በፊትም ኤዲት የተደረገው። ይሄ የሀገር ጉዳይ እና የትውልድም መቅረጫ ስለሆነ በጣም በተደጋጋሚ ነው ያዩት አዘጋጆች እና ገምጋሚዎች። እንዳጋጣሚ ኤዲት ያልተደረገው በመውጣቱ ነው እንጂ ሌሎች የቃላት ስህተቶች፣ የስሌት ስህተቶችም ነበሩ እነሱም ታርመዋል። የታረመው ደግሞ ቀደም ብሎ ነው፤ ለዛም ነው ተስተካክሎ የታተመው መፅሀፉ። የመንግስትን መግለጫ በተመለከተ ግን ትክክለኛውን ነገር በግልፅ ማስረዳት ነበረበት ለሌላ ጊዜ እንደዛ መሆን የለበትም፤ መታረም አለበት። " @student_text

Civics SBK12.pdf6.03 MB

በመላው አዲስ አበባ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ! በዛሬው እለት በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት የ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመንን ማስጀመሪያ መርሀ ግብር እየተካሄደ እንደሚገኝ የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል፡፡ የትምህርት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የተገኙት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በ2014 በጀት አመት የተማሪ ውጤት ከማሻሻል አንፃር ከፍተኛ ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር አስታውሰዋል። @student_text

#ETHIOPIA በነገው ዕለት የ2015 የትምህርት ዘመን ይጀምራል። በዚሁ ዕለት ትምህርት ሚኒስቴር 5 ዓመታት ሲያዘጋጅ የቆየው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መተግበር ይጀምራል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው የአዲሱ የትምህርት ስርዓት ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ በሚገኙ 80 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሙከራ ደረጃ ይሰጣል። #ለማስታወሻ - የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ፦ - ከኢንተርናሽናል እና የማህበረሰብ  ትምህርት ቤቶች ውጭ ስርዓተ ትምህርቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ባሉ የግል እና  የመንግስት ትምህርት ቤቶች ይተገበራል። - ግብረ ገብ ፣ አገር በቀል ዕውቀት ፣ ሙያና የቀለም ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ምርትና ተግባር፣ ጥናት እና ምርምር ትኩረት ተደርጎባቸው ይሰጣሉ። - ከ1ኛ - 6ኛ ክፍል የግብረ ገብ ትምህርት ይሰጣል። - ለ7ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ራሳቸውን የቻሉ የትምህርት ዓይነቶች ሆነው ይሰጡ የነበሩት ኬሚስትሪ ፣ ባዮሎጂ እና ፊዚክስ " ጄኔራል ሳይንስ " ተብለው ይሰጣሉ። ጆግራፊና ሂስትሪም ተቀናጅተው የሚሰጡ ይሆናል። - ከ1ኛ - 6ኛ ክፍል ላሉ የክፍል ደረጃዎች ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ይሰጣል፤ ከ7ኛ ክፍል -12ኛ ክፍል ያሉት ደግሞ ሁሉም ተማሪ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ይማራል። - ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ያሉት ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይወስዳሉ። - 3ኛ ክፍል ላይ ተጨማሪ ቋንቋዎችን መስጠት ይጀመራል፤ በክልሎቹ ውስጥ በስፋት የሚነገረውን #ተጨማሪ_ቋንቋ በመምረጥ ተማሪዎቹ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲወስዱት ይደረጋል። -  አጠቃላይ ፈተና በክልል ደረጃ 6ኛ ክፍል ላይ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ላይ ይሰጣል። - የ7ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች " ኬሪየር ኤንድ ቴክኒካል ኤጁኬሽን " የተባለ ትምህርት ይሰጣቸዋል። የእርሻ ትምህርት፣ አካውንቲንግ፣ ቢዝነስና ጀነራል የሆነውን የሥራና ክህሎት ትምህርት በሙያ ትምህርት ተካቶላቸው ይሰጣቸዋል። - 11ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ጤና ፣ ግብርና፣ የእርሻ ትምህርት፣ ማኒፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን ፣ ቢዝነስ ፣ አካውንቲንግ የመሳሰሉት የሙያ ትምህርትነቶችን እንዲማሩ ይደረጋል። 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከእነዚህ የሙያ ትምህርቶች ውስጥ የመረጡትን ይወስዳሉ። 👉 የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍልን እንዲሁም ከ1ኛ 👉 8ኛ ክፍል ያሉ የተመረጡ 5 የትምህርት አይነቶችን መጸሐፍት ዝግጅት ትምህርት ሚኒስቴር ያከናውነዋል ፤ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያለውን የትምህርት መፀሐፍት ክልሎች በራሳቸው ባህልና አካባቢያዊ ሁኔታ ቃኝተው ያዘጋጁታል። መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ / ኢፕድ የተወሰደ ነው። @student_text

መነጋገሪያ የሆነው የ4ኛ ክፍል መፅሀፍ ምንድነው ? በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጀው የ4ኛ ክፍል የሒሳብ መፅሀፍ መነጋገሪያ ሆኗል። ይህ መፅሐፍ መነጋገሪያ ሊሆን የቻለው በውስጡ #ገፅ_18 ላይ " የግዕዝ ቁጥሮች ምልክቶች #በቀጥታ ከግሪክ ቁጥሮች የተወሰዱ ናቸው" የሚል ሀሳብ ይዟል በመባሉ ነው። ይህም ጉዳይ በርካታ ዜጎችን አስቆጥቷል። መፅሀፉ ውስጥ ገብቷል የተባለው ሀሳብ የታየው በሶፍት ኮፒ በተሰራጨው የመፅሀፉ ቅጂ ላይ መሆኑን በርካታ ወላጆች ልከውልን ተመልክተነዋል። መምህራንም በተመሳሳይ ደርሷቸው እንደነበር ገልፀውልናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ት/ት ቢሮ የተገለፀው ሃሳብ "በመጽሐፉ ውስጥ የማይገኝና ሆነ ተብሎ የተሰራጨ የሀሰት መረጃ" ነው ብሎታል። ይህም የተደረገው ሆን ብለው ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ውዥንበር ለመፍጠር በሚፈልጉ አካላት ነው ሲል ገልጿል። አዲሱ መፅሀፍ ህትመቱ ተጠናቆ በሁሉም ት/ቤቶች እየተሰራጨ መሆኑን አሳውቋል። ቢሮው በPDF ስለተሰራጨው መፅሀፍ ያለው ነገር/የሰጠው ማብራሪያ የለም። በዚህ ጉዳይ ላይ ግልፅ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጉዳዮች፦ 1ኛ. የሶፍት ኮፒ መፅሀፉ በማን፣ እንዴት፣ መቼ ተዘጋጀ ? ስህተት መሆኑ ከታወቀ እንዴት ተሰራጨ ? 2ኛ. ለት/ቤቶች #ታትሞ የተሰራጨው መፅሀፍ ዝግጅቱ መቼ ተጀመረ፣ መቼ ታተመ፣ መቼ ተጠናቀቀ ? ሶፍት ኮፒው በትክክል ከሚመለከተው አካላት ተልኮ ከሆነ እና ስህተት ካለው "ሀሰተኛ / ህዝብ ውዥንብር ውስጥ ለመክተት የፈለጉ አካላት" ከማለት ስህተት መሆኑን በመግለፅ ማረም አይቻልም ነበር ወይ ? ይህ ጉዳይ በዚህ ደረጃ መነጋገሪያ የሆነው ሀገር የሚረከቡ ትንንሽ ልጆች ስለሚማሩበትና ነገ ስለ ሀገራቸው ምን እያወቁ ነው የሚያድጉት የሚለው ስለሚያሳስብ ነው። @student_text

መነጋገሪያ የሆነው የ4ኛ ክፍል መፅሀፍ ምንድነው ? በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጀው የ4ኛ ክፍል የሒሳብ መፅሀፍ መነጋገሪያ ሆኗል። ይህ መፅሐፍ መነጋገሪያ ሊሆን የቻለው በውስጡ #ገፅ_18 ላይ " የግዕዝ ቁጥሮች ምልክቶች #በቀጥታ ከግሪክ ቁጥሮች የተወሰዱ ናቸው" የሚል ሀሳብ ይዟል በመባሉ ነው። ይህም ጉዳይ በርካታ ዜጎችን አስቆጥቷል። መፅሀፉ ውስጥ ገብቷል የተባለው ሀሳብ የታየው በሶፍት ኮፒ በተሰራጨው የመፅሀፉ ቅጂ ላይ መሆኑን በርካታ ወላጆች ልከውልን ተመልክተነዋል። መምህራንም በተመሳሳይ ደርሷቸው እንደነበር ገልፀውልናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ት/ት ቢሮ የተገለፀው ሃሳብ "በመጽሐፉ ውስጥ የማይገኝና ሆነ ተብሎ የተሰራጨ የሀሰት መረጃ" ነው ብሎታል። ይህም የተደረገው ሆን ብለው ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ውዥንበር ለመፍጠር በሚፈልጉ አካላት ነው ሲል ገልጿል። አዲሱ መፅሀፍ ህትመቱ ተጠናቆ በሁሉም ት/ቤቶች እየተሰራጨ መሆኑን አሳውቋል። ቢሮው በPDF ስለተሰራጨው መፅሀፍ ያለው ነገር/የሰጠው ማብራሪያ የለም። በዚህ ጉዳይ ላይ ግልፅ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጉዳዮች፦ 1ኛ. የሶፍት ኮፒ መፅሀፉ በማን፣ እንዴት፣ መቼ ተዘጋጀ ? ስህተት መሆኑ ከታወቀ እንዴት ተሰራጨ ? 2ኛ. ለት/ቤቶች #ታትሞ የተሰራጨው መፅሀፍ ዝግጅቱ መቼ ተጀመረ፣ መቼ ታተመ፣ መቼ ተጠናቀቀ ? ሶፍት ኮፒው በትክክል ከሚመለከተው አካላት ተልኮ ከሆነ እና ስህተት ካለው "ሀሰተኛ / ህዝብ ውዥንብር ውስጥ ለመክተት የፈለጉ አካላት" ከማለት ስህተት መሆኑን በመግለፅ ማረም አይቻልም ነበር ወይ ? ይህ ጉዳይ በዚህ ደረጃ መነጋገሪያ የሆነው ሀገር የሚረከቡ ትንንሽ ልጆች ስለሚማሩበትና ነገ ስለ ሀገራቸው ምን እያወቁ ነው የሚያድጉት የሚለው ስለሚያሳስብ ነው። @student_text

አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ምን ይመስላል ? አምስት ዓመታትን በፈጀውና ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ስርዓተ ትምህርት ክለሳ የያዛቸው አዳዲስ ነገሮች ፦ 👉 ስርዓተ ትምህርቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ባሉ የግል እና  የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚተገበር ቢሆንም፤ ኢንተርናሽናልና የማህበረሰብ አቀፍ ትምህርትቤቶችን አያካትትም፤ 👉 በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ግብረ ገብ፣ አገር በቀል ዕውቀት፣ ሙያና የቀለም ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ምርትና ተግባር፣ ጥናትና ምርምር ትኩረት ተደርጎባቸው እንዲሰጡ ይሆናሉ፤ 👉 ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ላሉ የክፍል ደረጃዎች ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ  ይሰጣል፤ 👉 ከሰባተኛ ክፍል እስከ12ኛ ክፍል ያሉት ደግሞ ሁሉም ተማሪ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ይማራል፤ 👉 ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ12ኛ ክፍል ድረስ ያሉት ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይወስዳሉ፤ 👉 ሦስተኛ ክፍል ላይ ተጨማሪ ቋንቋዎችን መስጠት ይጀመራል፤  በክልሎቹ ውስጥ በስፋት የሚነገረውን ተጨማሪ ቋንቋ በመምረጥ ተማሪዎቹ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲወስዱት ይደረጋል፤  👉 በቀድመው የትምህርት ሥርዓት 10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው አገራዊ የመልቀቂያ ፈተና ይቀርና በምትኩ አጠቃላይ ፈተናው በክልል ደረጃ ስድስተኛ ክፍል እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ስምንተኛ እና 12ኛ ክፍል ላይ ይሰጣል፤ 👉 ከዚህ ቀደም ሦስት ዓመት የነበረው የተማሪዎች የዩኒሸርስቲ ቆይታ ደግሞ ዝቅተኛዉ አራት ዓመት ይደረጋል፤ ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች በመጀመሪያ ዓመት ከሚሠጡ ትምህርቶች ውስጥ እንደ ጂኦግራፊ፣ አንትሮፖሎጂ፣ ሶሺዮሎጂና ሥነ-ምግባር የመሳሰሉት ይካተታሉ፤ 👉 ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል የግብረገብ ትምህርት ይሰጣል፤  በተጨማሪም የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ውህድ የሆነ ትምህርት ይሰጣል፤  👉 ሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል በተናጠል ይሰጡ የነበሩት ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪና ባይሎጂ  አጠቃላይ ትምህርት ወይም ጀነራል ሳይንስ ተብለው እንዲሁም ጆግራፊና ሂስትሪም ተቀናጅተው የሚሰጡ ይሆናል፤ 👉 የሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች የእርሻ ትምህርት፣ አካውንቲንግ፣ ቢዝነስና ጀነራል የሆነውን የሥራና ክህሎት ትምህርት በሙያ ትምህርት ተካቶላቸው የሚሰጣቸው ይሆናል፤ 👉 11ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ደግሞ ጤና ፣ ግብርና፣ የእርሻ ትምህርት፣ ማኒፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን፣ ቢዝነስ፣ አካውንቲንግ የመሳሰሉት የሙያ ትምህርትነቶችን እንዲማሩ ይደረጋል፤ 👉 የዘጠነኛና የአስረኛ ክፍልን እንዲሁም  ከአንድ እስከስምንተኛ ክፍል ያሉ የተመረጡ አምስት የትምህርት አይነቶችን መጸሐፍት ዝግጅት ትምህርት ሚኒስቴር ያከናውነዋል፤   👉ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ያለውን የትምህርት መፀሐፍት ክልሎች በራሳቸው ባህልና አካባቢያዊ ሁኔታ ቃኝተው ያዘጋጁታል https://t.me/student_text

Wolaita soddo University ‼️ ትምህርት ሚኒስቴር የ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ 30 ሺህ 255 ተማሪዎችን ለዩኒቨርሲቲው መድቧል። በዚህም በሦሥቱም ካምፓሶች አጠቃላይ በመጀመሪያ ዙር 18 ሺህ 512 እንዲሁም በሁለተኛ ዙር 11 ሺህ 743 ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሏል። የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ብሔራዊ ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አሳውቋል። ለተጨማሪ የ 12ኛ ክፍል መረጃዎች🙏 https://t.me/student_TeXt

* ጥንቃቄ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቃረብን ተከትሎ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ በመሆኑ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል። " የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ
+1
* ጥንቃቄ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቃረብን ተከትሎ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ በመሆኑ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል። " የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሸጋገረ " እየተባለ በአንዳንድ የማህበራዊ ገፆች ላይ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ የማይታወቅ በትምህርት ሚኒስቴር ሆነ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያልተገለፀ ነው። ተማሪዎች ከፈተና ጋር በተያያዘ ማንኛውም አዲስ መረጃ ሲኖር በትምህርት ሚኒስቴር / በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እንዲሁም በህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚገለፅ መሆኑን በማወቅ በሀሰተኛ መረጃ ሳትረበሹ ተረጋግታችሁ ዝግጅታችሁን ልታደርጉ ይገባል። የተማሪ ወላጆችም ትክክለኛና የተረጋገጡ መረጃዎች በትክክለኛ የመስሪያ ቤቶቹ አድራሻ እንዲሁም በህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚነገሩት መሆናቸውን በማስገንዘብ ልጆቻችሁ እንዳይረበሹ ልታድርጉ ይገባል። ተፈታኝ ተማሪዎች እንዲረበሹ እና ብዙ የለፉበት ዝግጅታቸው እንዲደናቀፍባቸው የሚያደርጉ ሀሰተኛ የፈጠራ ወሬዎችን የምታሰራጩ አካላት ድርጊታችሁ ፍፁም ተገቢ ያልሆነ ፤ በትውልድ ላይም አሉታዊ ተፅእኖ ያለው መሆኑን በማወቅ ከድርጊታችሁ ልትታቀቡ ይገባል። ተማሪዎች ምንጩ የማይታወቅ እና የተለያዩ አካላት ተከታይ ለማፍራት እንዲሁም ሆን ብለው ተማሪ እንዲረበሽ ለማድረግ ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩትን መረጃ ወደ ጓደኞቻችሁ ባለመላክ ሀሰተኛ መረጃዎችን ተከላከሉ።

* ጥንቃቄ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቃረብን ተከትሎ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ በመሆኑ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል። " የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ
+1
* ጥንቃቄ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቃረብን ተከትሎ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ በመሆኑ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል። " የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሸጋገረ " እየተባለ በአንዳንድ የማህበራዊ ገፆች ላይ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ የማይታወቅ በትምህርት ሚኒስቴር ሆነ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያልተገለፀ ነው። ተማሪዎች ከፈተና ጋር በተያያዘ ማንኛውም አዲስ መረጃ ሲኖር በትምህርት ሚኒስቴር / በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እንዲሁም በህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚገለፅ መሆኑን በማወቅ በሀሰተኛ መረጃ ሳትረበሹ ተረጋግታችሁ ዝግጅታችሁን ልታደርጉ ይገባል። የተማሪ ወላጆችም ትክክለኛና የተረጋገጡ መረጃዎች በትክክለኛ የመስሪያ ቤቶቹ አድራሻ እንዲሁም በህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚነገሩት መሆናቸውን በማስገንዘብ ልጆቻችሁ እንዳይረበሹ ልታድርጉ ይገባል። ተፈታኝ ተማሪዎች እንዲረበሹ እና ብዙ የለፉበት ዝግጅታቸው እንዲደናቀፍባቸው የሚያደርጉ ሀሰተኛ የፈጠራ ወሬዎችን የምታሰራጩ አካላት ድርጊታችሁ ፍፁም ተገቢ ያልሆነ ፤ በትውልድ ላይም አሉታዊ ተፅእኖ ያለው መሆኑን በማወቅ ከድርጊታችሁ ልትታቀቡ ይገባል። ተማሪዎች ምንጩ የማይታወቅ እና የተለያዩ አካላት ተከታይ ለማፍራት እንዲሁም ሆን ብለው ተማሪ እንዲረበሽ ለማድረግ ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩትን መረጃ ወደ ጓደኞቻችሁ ባለመላክ ሀሰተኛ መረጃዎችን ተከላከሉ። @student_text @tikvahethiopia

የ 12ኛ ክፍል ፈተና እንደበፊቱ በ #4_ኮድ እንደሆነ ከተለያዩ መረጃዎች አግኝተናል። ብርሃኑ ነጋ ዘንድሮ 12 Code ለማድረግ እየሰሩ እንደነበር ተናግሮ ነበር። ነገር ግን አልተረጋገጠም። አሁን ደግሞ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የኮዱን መጠን ከፍ ማድረግ እንዳልተቻለ እየተወራ ይገኛል። መረጃውን እርግጠኛ ስንሆን እናሳውቃለን grade 12 students @student_text