cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ማኅበረ ዮርዳኖስ የማኅበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማኅበር

✝️ማህበረ ዮርዳኖስ የማህበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማህበር 👉 የማህበሩ አላማ ጥንታዊት ሐዋርያዊት ይሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በመልዕልተ አድባራት በቀራንዮ መድኋኒዓለምና ቅዱስ ገብርኤል እንዲሁም በወይብላ ቅድስት ማርያም ቤተክርስያን ስር ወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር በማቋቋም ባላቸው እውቀት ጉልበት እና የገንዘብ አቅም ልክ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመደገፍ የተቋቋመ ማህበር ነው

Більше
Рекламні дописи
270
Підписники
+124 години
+27 днів
-330 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

                ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ የሮሜ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ፦ እርሱም ከቅዱስ ጴጥሮስ በኋላ በከሀዲው ንጉሥ በጠራብያኖስ ዘመን ሆነ። ይህም ንጉሥ ስለ አባት አግናጥዮስ የጣዖት አምልኮን እንደሚአቃልል ሕዝቡንም ሁሉ እንደሚያስተምር ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን እንደሚያስገባቸው በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ አስቀርቦ "ለአማልክት መሥዋዕት አቅርብ" አለው ቅዱሱም "እኔ ለረከሱ ጣዖታት አልሠዋም" ብሎ መለሰለት። 💚💛❤ ንጉሡም ብዙ ቃል ኪዳኖችን በመግባት አባበለው በአልተቀበለውም ጊዜ ለአንበሳ ሰጠው ያን ጊዜም ቅዱስ አግናጥዮስ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ሕዝቡን አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ አንዱ አንበሳ ቀርቦ አንገቱን ያዘው ያን ጊዜም ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ነፍሱን ሰጠ። ከዚህ በኋላ ያ አንበሳ ወደ ሥጋው አልቀረበም ምእመናንም መጥተው ሥጋውን ወሰዱ በመልካም ቦታም አኖሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአቡነ አግናጥዮስ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 7 ስንክሳር።                ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ "ሰላም ለአግናጥዮስ ለመንበረ_ጴጥሮስ ዘወረሳ። እምነ መናብርት ኵሉ ዘተለዓለ ሞገሳ። ለመሥዋዕተ ጣዖት ምንንት እንዘ ያረኵሳ። በፍጻሜ ስምዑ ቀተሎ አንበሳ። ወእምድኅረዝ ኢቀርበ ለሥጋሁ ይግሥሣ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 7።               ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ሣህሉ ለእግዚአብሔር መልአ ምድረ። ወበቃለ እግዚአብሔር ፀንዐ ሰማያት። ወእምእስትንፋሰ አፋሁ ኵሉ ኃይሎሙ"። መዝ 32፥5-6። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 1፥1-6                 ✝️ ✝️ ✝️ 💚💛❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወኀሠሥኩ ገጸከ። ገጸ ዚአከ አኀሥሥ እግዚኦ። ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ"። መዝ 26፥8-9። የሚነበበው መልዕክታት ሮሜ 9፥1-17፣ 1ኛ ዮሐ 4፥11-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 11፥11-19። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 8፥51-59። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአጋእዝተ ዓለም የቅድስት ሥላሴ በዓል ለሁላችን ይሁንልን። 🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹     🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹           🕊     🕊     🕊     🕊  🕊 💚💛❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑ።💚💛❤️        ✝️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✝️   👉በቴሌግራም https://t.me/mahebreyoredanose 👉በዪትዪብ https://youtu.be/XEiySPTob9A     🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹     🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹           🕊     🕊    🕊 🕊 🕊
Показати все...
ማኅበረ ዮርዳኖስ የማኅበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማኅበር

✝️ማህበረ ዮርዳኖስ የማህበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማህበር 👉 የማህበሩ አላማ ጥንታዊት ሐዋርያዊት ይሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በመልዕልተ አድባራት በቀራንዮ መድኋኒዓለምና ቅዱስ ገብርኤል እንዲሁም በወይብላ ቅድስት ማርያም ቤተክርስያን ስር ወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር በማቋቋም ባላቸው እውቀት ጉልበት እና የገንዘብ አቅም ልክ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመደገፍ የተቋቋመ ማህበር ነው

💚💛❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 💚💛❤ ✝ 🌿🌹 ሐምሌ ፯ (7) ቀን።🌹🌿✝️ 🌻🌹🌿🌹🌿🌹🌻                 ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ለቅድስት ሥላሴ ወደ አብርሃም ቤት ለገቡበት የይስሐቅን መወለድ ለአበሰሩበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ ለሮሜ ሊቀ ጳጳስ ለሐዋርያው ለቅዱስ አግናጥዮ ምጥው ለአንበሳ ለዕረፍት በዓልና ለባሕታውያን አለቃ ለሆነ ለመስተጋድል አባ ሲኖዳ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአባ መቃቢስ፣ ከአግራጥም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                           ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ በዚችም ቀን ልዩ የሆኑ ሦስቱ አካላት (አጋዝእተ ዓለም ሥላሴ) በኦሪት መጽሐፍ እንደተጻፈ ወደ አብርሃም ቤት ገብ ያቀረበላቸውን ተመገቡ የይስሐቅንም ልደት አሠሰሩት ባረኩት አከበሩትም። ለእግዚአብሔር ይስጋና ይሁን በአባታችን በቅዱስ አብርሃም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ታሪኩን በመጽሐፍ ቅዱስ ዘፍ 18 ላይ ያንብቡ።                                             ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ የባሕታውያን አለቃ የሆነ መስተጋድል አባ ሲኖዳ፦ ይህም ቅዱስ በግብጽና በአክሚም አውራጃ ስሟ ስንላል ከምትባል ሀገር ከላይኛው ግብጽ ነበር። ስለእርሱም የመላእክት አምሳል የሆነ አባ ሐርስዮስ ትንቢት ተናገረለት። እርሱም ስለ ገዳም አገልግሎት ከመነኰሳት ጋር ሲሔድ የዚህን የቅዱስ ሲኖዳን እናት ውኃ ለመቅዳት ወጥታ አገኛት። ወደርሷ ሒዶ ሦስት ጊዜ ራሷን ሳማትና እንዲህ አላት "ዜናው በዓለሙ ሁሉ የሚሰማ የስሙ መዓዛ ከሽቱ የሚጥም የሆነ የሆድሽን ፍሬ እግዚአብሔር ይባርክ"። 💚💛❤ እነዚያ መነኰሳትም በአዩት ጊዜ አድንቀው "አባታችን አንተ የሴት ፊት ማየት ከቶ አትሻም ነበር ዛሬ ግን ከሴት ጋራ ትነጋገራለህ" አሉት። "ልጆቼ ሆይ ሕያው እግዚአብሔርን የእግዚአብሔርን ምሕረት ተስፋ የሚያደርግ ዓለሙ ሁሉ የሚጣፍጥበት ከዚች ሴት የሚወጣ የጨው ቅንጣት አለ" አላቸው። 💚💛❤ አንድ በገድል የጸና ጻድቅ ሰው መነኰስ ነበረ እርሱም መልሶ አባ ሐርስዮስን እንዲህ አለው "እግዚአብሔር ሕያው ነው አንተ ራሷን ትስም ዘንድ ወደዚያች ሴት በቀረብክ ጊዜ በእጁ የእሳት ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ በዙሪያዋ አየሁት። ራሷንም በሳምካት ጊዜ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል ሲልህ ደግሞም ከዚች ሴት የሚወለደው የተመረጡ ቅዱሳንን ሁሉ ልባቸውን ደስ ያሰኛል ወልደ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋር ብዙ ጊዜ ይነጋገር ነበር ሲል ሰማሁት" አለ። 💚💛❤ በግንቦት ሰባት ቀን ይህ ቅዱስ አባ ሲኖዳ ተወለደ በአደገም ጊዜ አባቱ በጎች ስለነበሩት ለልጁ ለሲኖዳ እንዲጠብቃቸው ሰጠው ይህ ሲኖዳም ምሳውን ለእረኞች ሰጥቶ እስከ ማታ ድረስ ይጾም ነበር። በሌሊትም ከውኃ ዐዘቅት ውስጥ ወርዶ በዚያ ቁሞ እስቲነጋ ድረስ ሲጸልይ ያድር ነበር። በክረምትም ሆነ በቊር ሰዓት እንዲሁ ያደርግ ነበር። አባቱም የሲኖዳ እናት ወንድም ወደ ሆነው ወደ አባ አብጎል እጁን በላዩ ጭኖ ይባርከው ዘንድ ወሰደው። አባ አብጎልም በአየው ጊዜ የሕፃኑን እጅ አንሥቶ በራሱ ላይ አድርጎ "ሲኖዳ ሆይ ባርከኝ ለብዙ ሕዝብ ታላቅ አባት ትሆን ዘንድ የሚገባህ ሁነሃልና" አለው። አባቱም በአባ አብጎል ዘንድ ተወው። 💚💛❤ ከዕለታትም በአንዲቱ ቀን አባ አብጎል እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ ሰማ "እነሆ ሲኖዳ ለዓለሙ ሁሉ አርሲመትሪዳ የባሕታውያን አለቃ ሁኖ ተሾመ"። ይህም ሲኖዳ ለዓለሙ ሁሉ ብርሃን እስከሚሆን በበጎ አምልኮ ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት በስግደትና በመትጋት ታላቅ ተጋድሎ መጋደልን ጀመረ። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን ለአባ አብጎል የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና የኤልያስን አስኬማ የሠለስቱ ደቂቅን ቆብና የመጥምቁ ዮሐንስን ቅናት አመጣለት። እንዲህም አለው "እንድትጸልይና የምንኵስና ልብስ ለሲኖዳ እንድታለብሰው እግዚአብሔር አዝዞሃል"። ያን ጊዜም አባ አብጎል ተነሥቶ ጸለየ የምንኵስና ልብስንም አለበሰው። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ተጋድሎውን አበዛ። ለመነኰሳት፣ ለመኳንንት፣ ለሕዝባውያንና ለሴቶች ለሰዎች ሁሉ መመሪያ የሚሆን ሥራትን ሠራ። በኤፌሶንም የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ስለ ከሀዲው ንስጥሮስ በተደረገ ጊዜ ከማኅበሩ አባት ከሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስ ጋራ ወደ ጉባኤው ሔደ ንስጥሮስም ከክህደቱ ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ለይተው አሳደዱት። 💚💛❤ ከዚህ በኋላም ወደ ሀገራቸው በመመለሻቸው ጊዜ መርከበኞች ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋራ አትሳፈርም ብለው አባ ሲኖዳን ከለከሉት እርሱም ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ማለደ። ወዲያውኑም ደመና መጥታ ተሸከመችውና አባ ቄርሎስ በመርከቡ ውስጥ እያለ በበላዩ በአንጻሩ አደረሰችው። "አባቴ ሆይ ሰላም ለአንተ ከአንተ ጋራ ላሉትም ይሁን" ብሎ ሰላምታ አቀረበ። በመርከብ ያሉት ሁሉም "ላንተም ሰላም ይሁን በጸሎትህም አትርሳን" አሉት። እጅግም አደነቁ ለሚፈሩት ይህን ያህል ጸጋ የሚሰጥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። 💚💛❤ ወደ ገዳሙም ደርሶ ከልጆቹ መነኰሳት ጋራ የመንፈቀ ሌሊትን ጸሎት አደረገ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ብዙ ጊዜ ወደርሱ እየመጣ ያነጋግረው ነበር። እርሱም የመድኃኒታችንን እግሩን ያጥበው ነበር እጣቢውንም ይጠጣ ነበር ጌታችንም ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት ትንቢቶችንም ተናገረ። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ ሐምሌ ሰባት ቀን ተኛ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መጥቶ እያረጋጋው በእርሱ ዘንድ ተቀመጠ። ብፁዕ አባ ሲኖዳም ጌታችንን እንዲህ አለው "ጌታዬ ፈጣሪዬ ልዩ ሦስትነትህንና ጌትነትህን ስለሚነቅፉ ከሀድያን ወደ ጉባኤው እሔድ ዘንድ እንዲጠሩኝ ሊቀ ጳጳሳቱ ወደ እኔ ልኳልና እንደቀድሞው ታጸናኛለህን?"። ጌታችንም በጸጋና በጥዑም ቃል እንዲህ ብሎ መለሰለት "ወዳጄ ሲኖዳ ሆይ ሌላ ዕድሜ ትሻለህን?። እነሆ ዕድሜህ ሁሉ መቶ ሃያ ዓመት ከሁለት ወር ሁኖሃል ዕድሜህ ዘጠኝ ዓመት ሲሆን አስኬማን ለበስኽ ከዚያ በኋላ መቶ ዐሥራ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ኖርኽ አሁንስ ድካምህ ይብቃህ" ይህንንም ብሎ ጌታችን በክብር ዐረገ። 💚💛❤ በዚያንም ጊዜም የቅዱሳን አንድነት ማኅበር ወደርሱ መጡ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ዳግመኛ አየው ልጆቹንም ክብር ይግባውና "ለጌታዬ ለኢየሱስ ክርስቶስ እሰግድ ዘንድ አንሱኝ" አላቸው አንሥተውትም ሰገደለት። ከዚህም በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አላቸው "ወደ እግዚአብሔር አደራ አስጠብቅኋችሁ ነፍሴም ከዚህ ከደካማው ሥጋዬ የምትለይበት ጊዜ ደርሷል እኔም ለአባታችሁ ለዊዳ እንድትታዘዙ አዝዛችኋለሁ ከእኔ በኋላ ጠባቂያችሁ እርሱ ነውና" አላቸው። 💚💛❤ ለልጆቹም ይህን በተናገረ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "የመረጥሁህ ሲኖዳ ሆይ ብፁዕ ነህ ቸርነቴም ይደረግልሃል በሕይወትህ ዘመን ሁሉ አንተ የምወደውን ሥራ ሠርተሃልና እንግዲህ ወደ ዘለዓለም ተድላ ታርፍ ዘንድ ወደእኔ ና" አለው። ያን ጊዜም ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ ሲኖዳ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
Показати все...
ማኅበረ ዮርዳኖስ የማኅበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማኅበር

✝️ማህበረ ዮርዳኖስ የማህበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማህበር 👉 የማህበሩ አላማ ጥንታዊት ሐዋርያዊት ይሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በመልዕልተ አድባራት በቀራንዮ መድኋኒዓለምና ቅዱስ ገብርኤል እንዲሁም በወይብላ ቅድስት ማርያም ቤተክርስያን ስር ወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር በማቋቋም ባላቸው እውቀት ጉልበት እና የገንዘብ አቅም ልክ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመደገፍ የተቋቋመ ማህበር ነው

💚💛❤ ሳውልም "አቤቱ አንተ ማነህ" አለው "አንተ የምሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ በሾለው ብረት ላይ ብትረግጥ አንተን ይጎዳሃል" አለው። እየተንቀጠቀጠም አደነቀ "አቤቱ ምን እንዳደርግ ትሻለህ" አለው ጌታም "ተነሥና ወደ ከተማ ግባ ልታደርግ የሚገባህን ከዚያ ይነግሩሃል" አለው። ከርሱ ጋራ ቁመው የነበሩ ሰዎችም ንግግሩን ይሰሙ ነበር ነገር ግን የሚያዩት አልነበረም። 💚💛❤ ሳውልም ከምድር ተነሣ ዐይኖቹንም ተገልጠው ሳሉ አያይም ነበር እየመሩም ወደ ደማስቆ አስገቡት በዚያም ሳያይ ሳይበላና ሳይጠጣ ሦስት ቀን ሰነበተ። በዚያም በደማስቆ ከደቀ መዛሙርት ወገን ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ጌታም በራዕይ ተገለጠለትና ሐናንያ ብሎ ጠራው እርሱም "አቤቱ ጌታዬ እነሆኝ" አለ። ጌታም "ተነሥና ቀጥተኛ ወደምትባለው መንገድ ሒድ በይሁዳ ቤትም ጠርሴስ ከሚባል አገር የመጣ ሳውል የሚባል ሰው ፈልግ እርሱ አሁን ይጸልያልና" አለው። 💚💛❤ ሐናንያ ግን መልሶ እንዲህ አለ "አቤቱ ስለዚያ ሰው በኢየሩሳሌም በቅዱሳኖችህ ላይ የሚደርገውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰምቻለሁ ወደዚህም ከካህናቱ አለቃ አስፈቅዶ የመጣ ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ሊአሥር ነው"። ጌታችንም "ተነሥና ሒድ በአሕዛብና በነገሥታት በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ አድርጌዋለሁና። እኔም ስለ ስሜ መከራ ይቀበል ዘንድ እንዳለው አሳየዋለሁ"። 💚💛❤ ያን ጊዜም ሐናንያ ሔደ ወደ ቤትም ገባ "ወንድሜ ሳውል በመንገድ ስትመጣ የታየህ ጌታችን ኢየሱስ ታይ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ ይሞላብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል" አለው። ያን ጊዜም የሸረሪት ድር የመሰለ ከዐይኖቹም ተገለጡ። ወዲያውም አየ ተነሥቶም ተጠመቀ እህልም በልቶ በረታ። ከደቀ መዛሙርትም ጋር በደማስቆ ጥቂት ቀን ሰነበተ። በዚያው ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰበከ አስተማረም። የሰሙትም ሁሉ አደነቁ እንዲህም አሉ "በኢየሩሳሌም ይህም ስም የሚጠሩትን ሁሉ ያሳድድ የነበረ ይህ አልነበረምን ወደዚህስ የመጣው እያሠረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሊወስዳቸው አይደለምን"። 💚💛❤ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም አደረበት እውነተኛንም ሃይማኖት ግልጽ አድርጎ አስተማረ። ለኦሪት ሕግ የሚቀና እንደ ነበረ እንዲሁ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሠራት ሕግ ወንጌል ዕጽፍ ድርብ ቅንዓትን የሚቀና ሆነ። ከዚህም በኋላ በአገሮች ሁሉ ዞሮ ሰበከ በጌታችንም ስም ሰበከ። ድንቆችንና ተአምራትንም አደረገ። ቁጥር የሌላቸው ብዙዎች አሕዛብንም አሳመናቸው ነገር ግን ብዙ ጊዜ በመገረፍ በመደብደብና በመታሠር ብዙ መከራ ደረሰበት መከራውንም ሁሉ ታግሶ በሁሉ ቦታ አስተማረ። 💚💛❤ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደተጻፈ የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙና ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ "እኔ እነርሱን ለመረጥሁለት ሥራ ሳውልና በርናባስ ለዩልኝ" አላቸው። ከዚህም በኋላ ጾመውና ጸልየው እጃቸውንም በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሙአቸው ከመንፈስ ቅዱስም ተሹመው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ። 💚💛❤ በደሴቱም ሁሉ ሲዘዋወሩ ጳፋ ወደ ምትባል አገር ደረሱ። በዚያም ሐሰተኛ ነቢይ የሆነ ስሙ በርያሱስ የሚባል አንድ ሥራየኛ አይሁዳዊ ሰው አገኙ እርሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከሚባል ብልህ ሰው ከሆነ አገረ ገዥ ዘንድ የነበረ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ ወዶ በርናባስንና ሳውልን ጠራቸው። የስሙ ትርጓሜ እንዲህ ነበርና ኤልማስ የሚሉት ያ ሥራየኛ ሰው ይከራከራቸው ነበር ገዥውንም ማመንን ሊከለክለው ወዶ ነበር። 💚💛❤ ጳውሎስ በተባለው ሳውል ላይም መንፈስ ቅዱስ መላበት። አተኵሮም ተመለከተው "ኃጢአትንና ክፋትን ሁሉ የተመላህ የሰይጣን ልጅ የጽድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ የቀናውን የእግዚአብሔርን መንገድ እያመጣመምኽ ተው ብትባል እምቢ አልኽ እነሆ አሁን የእግዚአብሔር እጅ በአንተ ላይ ተቃጥታለች ትታወራለህ እስከ እድሜ ልክህም ፀሐይን አታይም" አለው። ወዲያውኑም ታወረ ጨለማም ዋጠው የሚመራውንም ፈለገ አገረ ገዥውም የሆነውን አይቶ ደነገጠ በጌታችንም አመነ። 💚💛❤ ከዚህ በኋላ ሒደው ወደ ሊቆኦንያ ከዚያም ወደ ልስጥራንና ደርቤን ከተማ ወደ አውራጃውም ሁሉ ገብተው አስተማሩ። በልስጥራን ከተማም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እግሩ ልምሾ የሆነ አንድ ሰው ነበረ ተቀምጦ ይኖር ነበረ እንጂ ልምሾ ከሆነ ጀምሮ ቁሞ አልሔደም። ቅዱስ ጳውሎስንም ሲያስተምር አደመጠው ጳውሎስ ተመልክቶ ሃይማኖት እንዳለው እንደሚድንም ተረዳ። ድምፁንም ከፍ አድርጎ "በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥና ቀጥ ብለህ ቁም እልሀለሁ" አለው ወዲያውኑ ተነሥቶ ሔደ። አሕዛብም ቅዱስ ጳውሎስ ያደረውን አይተው በጌታች አመኑ...። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ከሐዋርያ ፊሊጶስ ጋር ወደ ሁለት አገሮች በአንድነት ሔዱ ከዚያም በጌታችን ስም ሰበኩ የአገሩም አለቆች ያዟቸው እጆቻቸውንና እግሮቻቸው አሰሯቸው በአንገቶቻቸውም የብረት ሰንሰለቶችን አስገቡ እራሳቸውንም የሸፋን የብር ቆብን ሰሉላቸው ዳግመኛም በእጅና በሐል እጅ በጣቶችም ምሳሌ ሰሩ በእጆቻቸውና በክንዶቻቸው እያንዳንዱን የብረት እጅ ጨመሩ። ከብረቶችም ጋር ቸነከሯቸው። 💚💛❤ ሁለተኛም እስከ አንገት የሚደርስ በትከሻ አምሳል ሰሩ በፊትና በኋላም ቸነከሯቸው ደግሞም መላ አካላቸውን የሚከብና ከአካላቸው ምንም እንዳይታይ የሚሸፍን የብረት ሰሌዳ ሰሩ ከወገቦቻቸው ጋራ ቸነከሯቸው ችንካሮችም ተረከዛቸውን ነድለው ወደ ጭኖቻቸው እስከሚደርሱና እስከሚያቆስሏቸው ድረስ የብረት ጫማ ሰርተው እግሮቻቸውን ቸነከሩ። ደግሞ በመሸፈኛ አምሳል የብረት ሰናፊል ሠሩ ቀማሚዎችም መጡ አንድ መክሊት የሚመዝን እርሳስንም አመጡ ታላቅ የብረት ጋንንም ሰባት ልጥር የሰሊጥ ቅባት አመጡ። ስቡንና አደሮ ማሩን የእሳቱን ኃይል አብዝቶ የሚያነደውን ቅመሙን ከሙጫውና ከድኙ ጋር ቀላቀሉት ከዋርካና ከቁልቋል ከቅንጭብም ደም ሰባት ልጥር አንድ ወይን ሐረግንና ቅባት ያለቸውን እንጨቶች ሁሉ አመጡ። 💚💛❤ በጋን ውስጥ ያበሰሉትንና ያሟሙትን ልዩ ልዩ ቅመምን አምጥተው ከሥጋቸው እስሚጣበቅ በቅዱሳን ሐዋርያት ሥጋ ላይ ባሉት ሠሌዳዎች ውስጥ ጨመሩት። ከእግራቸው እስከ ራሳቸው ከፍ ከፍ እስከሚል ድረስ በእሳት ያቀለጡትን ያንን እርሳስ ጨመሩት። ርዝመቱ ዐሥራ አምስት ክንድ በሆነ ወፍራም የጥድ ምሰሶ ላይም አቆማቸውና ከበታቻቸው ፍሬ በሌለው በወይን ሐረግና በተልባ እሳቱን አቀጣጥለው አነደዱ። የእሳቱም ነበልባልም ከሥጋቸው በላይ ከፍ ከፍ አለ ሐዋርያትን ግን ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር። 💚💛❤ ከመኳንቱም በአንዱ ልብ ርኅራኄ አሳደረና እንዲፈቷቸው አዝዞ ፈቷቸው። በፈቷቸውና ሠሌዳው ከሥጋቸው ላይ ባስወገዱ ጊዜ ቆዳቸው ተገፈፈና ከብረቱ ሠሌዳዎች ጋር ወጣ። ብዙ ደምም ከሥጋቸው ፈሰሰ። 💚💛❤ ሰይጣንም በከተማው ሰዎች ልብ አደረና ሐዋርያትን ወደ እሳት ውስጥ መለሷቸው ያን ጊዜ ጌታች ወርዶ የእሳቱ ነበልባል አጠፋው። ዝናብን የተሞላች ብርሕት ደመና መጥታ ቅዱሳን ሐዋርያት ከበበቻቸው በዚያም አገር አንድ ጊዜ በደንጊያ በመወገር አንድ ጊዜም በፍላጻ በመንደፍ ብዙ ተሰቃዩ። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ሙታንን በአነሱ ጊዜ የከተማው ሰዎች ሁሉ አመኑ አጠመቋቸው። ቤተ ክርስቲያንንም ሠሩላቸው ካህናትንም ሾሙላቸው በቀናች ሃይማኖት እስኪጸኑ አስተማሯቸው። ከዚያም ወጥተው ጌታችን ወደ አዘዛቸው ወደ ሌላ አገር ሔዱ።
Показати все...
💚💛❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 💚💛❤ ✝ 🌿🌹 ሐምሌ ፭ (5) ቀን።🌹🌿✝️ 🌻🌹🌿🌹🌿🌹🌻                 ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ እንኳን ለብርሃናተ ዓለም ለቅዱስ ጴጥሮስ፣ ቅዱስ ጳውሎስ በጫካኙ ንጉሥ በኔሮን ቄሳር እጅ ሰማትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል፣ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሳቁኤል ለበዓሉ መታሰቢያ፣ ለሰባ ሁለቱ አርድእት ለመታሰቢያቸው በዓላቸው፣ ለአባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓላቸውና ለሐዋርያት (ለሰኔ) ፆም ፍቺ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ፡በዚች ከሚታሰቡ፦ በጋዛ ሰማዕት ከሆነ ከይስሐቅና ከደብረ ዓሣ ጻድቃንም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                            ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ፦ ይህም ጴጥሮስ ከቤተ ሳይዳ የነበረ ዓሣ አጥማጅም ነበረ ጌታችንም ከተጠመቀባት ዕለት ማግስት አግኝቶ መረጠው ከእርሱ አስቀድሞም ወንድሙ እንድርያስን አግኝቶ መረጠው። መድኀኒታችንንም እስከ መከራው ጊዜ ሲያገለግለው ኖሩ ፍጹም ሃይማኖት ለጌታውም ቅንዓትና ፍቅር ነበረው። ስለዚህም በሐዋርያት ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው። 💚💛❤ ጌታችን ም ሰዎች ማን እንደሆነ ማንም እንደሚሉት ስለ ራሱ በጠየቃቸው ጊዜ ሌሎች "ኤርምያስ ይሉሃል ወይም ኤልያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል" አሉት። ቅዱስ ጴጥሮስ ግን "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህ" አለ። ጌታችንም "የሃይማኖት አለት የቤተ ክርስቲያንም መሠረት ነህ" ብሎ ብፅዕና ሰጠው "የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻ ቁልፍ ሰጥቼሃለሁ" አለው። 💚💛❤ አጽናኝ የሆነ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ ከተበቀለ በኋላ ተናገሪዎች ከሆኑ በዚህ ዓለም ተኲላዎች መካከል ገባ በውስጣቸውም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች አሕዛብንም መልሶ የዋሆች ምእመናን አደረጋቸው። ጌታችንም የማይቈጠሩ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችን በእጆቹ አደረገ ጥቅም ያላቸው ሦስት መልእክቶችንም ጽፎ ለምእመናን ላከቸው። ለማርቆስም ወንጌሉን ተርጒሞ አጽፎታል። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ የከተማው መኳንንት ወደሚሰበሰቡበት ወደታላቁ የጨዋታ ቦታም ሔዶ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ብሎ ተናገረ "የሚራሩ ብፁዓን ናቸው ለርሳቸውም ይራሩላቸዋልና" የዚህንም ተከታታይ ቃሎች ተናገረ። በዚያም ከዚያ የነበሩ አራት የደንጊያ ምሰሶዎችም በሚያስፈራ ድምፅ "አሜን" አሉ የተሰበሰቡትም ይህን ቃል በሰሙ ጊዜ ደነገጡ። ከሰባ ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያደረበት አንድ ሰው ነበረ ከእነዚያ ድንጋዮች ቃልን ስለ ሰማ ያን ጊዜ ጋኔኑ ጣለው ከእርሱም ወጥቶ ሔደ። መኳንንቱም ፈርተዋልና ስለዚህ ነገር እያደነቁ ወደ ቤታቸው ገቡ። 💚💛❤ ከከተማ መኳንንቶችም ቀውስጦስ የሚባል አንዱ ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ ስሟ አክሮስያ የምትባል ሚስቱ ዓለምን ስለ መተው ለድኆችም ስመራራትና የመሳሰለውን ቃል ቅዱስ ጴጥሮስ እንዴት እንዳስተማረ ነገራት። እርሷም በሰማች ጊዜ በልቧ ነቃታ "ይህ ገገር መልካምና ድንቅ ነው" አለች። ቅዱስ ጴጥሮስ ያስተማረውንም ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በአንድነት ተስማሙ ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በአንድነት ተስማሙ ከዚህም በኋላ ገንዘባቸውን ሁሉ ለድኆች ሰጡ ከዕለት ራት በቀር ምንም አላስቀሩም። 💚💛❤ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ንጉሡ ስለ መንግሥት ሥራ ከርሱ ጋራ ለመማከር በቶሎ እንዲደርስ ወደርሱ መልክትን ላከ። ቀውስጦስም ይህ በሰማ ጊዜ ገንዘብ ስላልነበረው ፈርቶ ደነገጠ ተጨነቀም። ምክንያትም አመካኝቶ ይሰወር ዘንድ ከሚስቱ ጋራ ተማከረ። እርሷ ግን "ምክንያት አታድር ነገር ግን ወደ ንጉሥ ሒድ የቅዱስ ጴጥሮስ አምላክን ጎዳናህን ያቅናልህ" አለች። እርሱም ነገሯን ተቀብሎ ወደ ንጉሡ ሔደ በመንገድም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ብዙ በረከትን አገኘ ወደ ንጉሡም ደረሰ ንጉም በደስታና በክብር ተቀበለው። 💚💛❤ ከሦስት ዓመት በኋላም ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሁለቱ ልጆቹ የተመረዘ ውሃ ጠጥተው እነሆ ሞተው ነበር ሚስቱም ለእርሱ መንገርን ፈራች ብዙ ምሳሌዎችን ከመሰለችለት በኋላ ነገረችው። በሰማ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀሰ። ሚስቱም እንዲህ አለችው "ጌታዬ ሆይ ልባችን የሚጽናናበትን እርሱ ያደርግልናል የቅዱስ ጴጥሮስ ፈጣሪ እግዚአብሔርን እንለምነው"። ሊጸልዩም በጀመሩ ጊዜ ቀወስጦስና አክሮስያ "የደቀ መዝሙሬ የጴጥሮስ ቃል ስለሰማችሁና ስለተቀበላችሁት ስለዚህ ልጆቻችሁን በሕይወታቸው እሰጣቸዋለሁ" የሚል ቃልን ከሰማይ ሰሙ ያን ጊዜም ልጆቻቸው ድነው ተነሱ ቀውስጦስና ሚስቱም ደስ አላቸው የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። 💚💛❤ እሊህም ከሞት የተነሱ ልጆች ለቅዱስ ጴጥሮስ ቀደ መዝሙሮቹ ሆኑ የአንዱ ስሙ ቀሌምንጦስ ነው እርሱም ቅዱስ ጴጥሮስ ያየውንና ጌታች በሥጋ ወደ ሰማይ በሚያርግ ጊዜ የገለጠለትን ምስጢር ሁሉ የነገረው ነው ሰዎች ሊያዪአቸው የማይገባቸውን መጻሕፍትን አስረከበው። ይህንም ቀሌምጦስን ሊቀ ከጵጵስና ወንድሙንም ዲቁና ሾማቸው። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ቅዱስ ጴጥሮስ አምላክን የወለደች የንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ክብራን በምሳሌ አየ። በቀስት አምሳል ደመናን አይቷልና በላዪዋም የብርሃን ድንኳን ነበር በድንኳን ውስጥም አምላክን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያም ተቀምጣለች። በእጆቻቸው ውስጥ የነበልባል ጦሮችና ሰይፈችን ያያዙ መላክትና የመላእክት አለቆች በዙሪያዋ ነበር። እንዲህም እያሉ ያመሰግኗት ነበር። "ከእርሷ የደኅንነት ፍሬ የተገኘ የሰመረች የወይን ተክል አንቺ ነሽ ማኅፀንስሽም የእግዚአብሔር በግ የተሸከመ ንጽሕት አዳራሽ አንቺ ነሽ"። 💚💛❤ ሁለተኛም እንዲህ ይሏት ነበር " የብርሃን እናቱ ሆይ የምሕረት መገኛ ሆይ ደስ ይበልሽ የአማልክት አምላክ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሆነ የመድኅን ዙፋን ሆይ ደስ ይበልሽ ክብርና ምስጋናን የተመላሽ የፍጥረት ሁሉ እመቤት ደስ ይበልሽ"። መላእክት ምስጋናዋንና ሰላምታዋን ባደረሱ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእርስዋ ተገልጦ ከእርሷ በቀር ማንም ሊያውቀው የማይቻል ነገርን ነገራት ወዲያውኑም ምድር ተናገወች ሊነገር የማይቻል ምሥጢራትንም ገለጠላት። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ መድኀኒታችን ለአገሩ ሁሉ ቅዱስ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ቅዱስ ጴሮስን አዘዘው ቅዱስ ጴጥሮስም መጥቶ ሔደ ኢዮጴም ወደምትባል የባሕር ዳርቻና ልድያ ወደምትባል አገር ደረሰ። በአንዲት ዕለትም በኢዮጴ ሳለ ብርሕት ደመና ዞረችው። እነሆም ሰፊ መጋረጃ ወደርሱ ወረደች በውስጧም የእንስሳት የምድረ በዳ አውሬዎችና የሰማይ አዕዋፍ አምሳል ነበር። "ጴጥሮስ ሆይ ተነሥና አርደህ ብላ" የሚል ቃልም ከሰማይ ጠራው። ቅዱስ ጴጥሮስም "አቤቱ አይገባኝም እርኲስ ነገር አልበላም ወደ አፌም ከቶ አልገባም" አለ። ያም ቃል ዳግመኛ ጠራውና እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገው አንተ ርኲስ ነው አትበል" አለው ያም ቃል ሦስት ጊዜ መላልሶ እንዲህ ነገረው። በየንግግሩም ወደ እሪያዎች፣ ወደ አራዊትና ወደ አእዎፍ ሥዕሎች ጣት ያመለክተው ነበር።
Показати все...
ማኅበረ ዮርዳኖስ የማኅበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማኅበር

✝️ማህበረ ዮርዳኖስ የማህበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማህበር 👉 የማህበሩ አላማ ጥንታዊት ሐዋርያዊት ይሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በመልዕልተ አድባራት በቀራንዮ መድኋኒዓለምና ቅዱስ ገብርኤል እንዲሁም በወይብላ ቅድስት ማርያም ቤተክርስያን ስር ወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር በማቋቋም ባላቸው እውቀት ጉልበት እና የገንዘብ አቅም ልክ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመደገፍ የተቋቋመ ማህበር ነው

💚💛❤ ክብር ይግባውና ጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጳውሎስ ተገለጠለትና "የመረጥኩህ ጳውሎስ ሆይ ስላም ላንተ ይሁን። መታሰቢያህን የሚደርገውን፣ በስምህ ቤተ ክርስቲያን የሚሰራውንና የሚጸልየውን፣ ስለትንና መባንም የሚሰጠውን፣ በመታሰቢያህም ቀን ለድኆች የሚመጸውተውን ሁሉ ከአንተ ጋር በመንግሥተ ሰማያት አኖራቸዋለሁ" አለው። "በስምህ የታነጹትም አብያተ ቤተ ክርስቲያናት መላእክቶቼን እንዲጠብቋቸው አደርጋቸዋለሁ" ቡዙ ቃል ኪዳንም ሰጠው። በመለኮታዊ አፉ አፉን ሳመውና ከእርሱ ዘንድ ወደ ሰማያት በክብ ዐረገ። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ እልዋሪቆን ወደ ምትባል ታላቅ አገር እስከሚደርስ በብዙ አገሮች ውስጥ ተመላለሰ በዚያም የብርሃን እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻለት አረጋጋችው ረዳችውም በመጋቢት ሃያ ዘጠኝ እንደጻፍነው የአገሩን ሰዎች እንዲያጠምቃቸውና እንዲያስተምራቸው አዘዘችው። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሮሜ ከተማ ገብቶ በውስጧ ሰበከ በስብከቱም ብዙዎች ሰዎች አምነው የክርስትናን ጥምቀትን አጠመቃቸው። በመጻፍትነት የታወቁ ዐሥራ አራት መልክቶችን ጻፈ የመጀመሪያ መልክቱም ለሮሜ የተጻፈችው ናት። 💚💛❤ መልካም ሩጫውን ከፈጸመ በኋላ ንጉሥ ኔሮን ይዞ ጽኑ ሥቃይ አሰቃየው። ራሱንም በሠይፍ እንዲቆርጡት ለሠያፊ ሰጠው ከሠያፊውም ጋር አልፎ ሲሆድ ከንጉሥ ኔሮን ዘመዶች ወገን የሆች አንዲት ብቴና አገኘችው እርሷም ክብር ይግባውና በጌታችን ያመነች ነበረች ስለእርሱ አለቀሰች። እርሱ ግን "መጎናጸፍያሽ ስጭኝ እኔም ዛሬ እመልስልሻለሁ" አላት። እርሷም መጎናጸፍያዋን ሰጠችውና ራስ ወደሚቆርጡበት ቦታ ሔደ። ለሠያፊው ራሱ በዘነገበለለት ጊዜ በመጎናጸፍያዋ ፍቱን ሸፈነ ሠያፊው የቅዱስ ጳዌሎስ ራስ ሐምሌ 5 ቀን ቆርጦ በዚያች ብላቴና መጎናጸፍያ እንደተሸፈነ ጣለው። 💚💛❤ ሠያፊው ጳውሎስን እንደገደለው ለንጉሥ ሊነግረው በተመለሰ ጊዜ ያቺ ብላቴና አገኘችው "ያ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ አለ" አለችው። ራስ በሚቆርጥበት ቦታ ወድቋል ራሱም በመጎናጸፍያሽ ተሸፍኗል" አላት። እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችለት "ዋሽተሃል እነሆ ጴጥሮስና ጳውሎስ በእኔ ዘንድ አልፈው ሔዱ እነርሱም የመንግሥት ልስን ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ በእንቊ የተጌጡ አይንን የሚበዘብዙ አክሊላትን አድርገዋል። መጎናጸፍያየም ሰጡኝ። እርሷም እነኋት ተመልከታት" ብላ ለዛያ ሠያፊ አሳየችው። ከእርሱ ጋር ለነበሩትም አሳየቻቸው። አይተውም አደነቁ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። 💚💛❤ ለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ተአምራቶች ቁጥር የሌላቸው እጅግ የበዙ ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በቅዱስ ጳውሎስ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከርእሰ ሊቃ ጳጳሳት ከአባ መርቆሬዎና ከአባ ማትያስ ከሁሉ ሊቃነ ጳጳሳት እና የቅድስት የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያ ልጆች ጋር ይኑር ለዘለላሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 5 ሰንክሳር።                                               ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ "ሰላም ለከ ጴጥሮስ ተልሚድ። ዘኢያቅበጽከ ተስፋ ነገረ ኑፋቄ ወካህድ፡፡ እንዘ ትረውጽ ጥቡዕ ለመልእክተ ክርስቶስ ወልደ። አመ ለሊከ ወሬዛ ቀነትከ በእድ። ወአመ ልህቀ አቅነተከ ባዕድ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 5።                 ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። ወውስተ ፀሓይ ሤመ ጽላሎቶ"። መዝ 18፥4-5። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 15፥1-17።               ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወበኀቤየሰ ፈድፋደ ክቡራን አዕርክቲከ እግዚኦ። ወፈድፋደ ፀንዑ እምቀደምቶሙ። እኌልቆሙ እምኆፃ ይበዝኁ"። መዝ 138፥17-18። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ተሰ 1፥4፥-13-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 1፥1-12 እና የሐዋ ሥራ 23፥10-16። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 21፥15-20። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱሳን የጴጥሮሰና የጳውሎስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። 🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹     🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹           🕊     🕊     🕊     🕊  🕊 💚💛❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑ።💚💛❤️        ✝️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✝️   👉በቴሌግራም https://t.me/mahebreyoredanose 👉በዪትዪብ https://youtu.be/XEiySPTob9A     🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹     🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹           🕊     🕊    🕊 🕊 🕊
Показати все...
ማኅበረ ዮርዳኖስ የማኅበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማኅበር

✝️ማህበረ ዮርዳኖስ የማህበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማህበር 👉 የማህበሩ አላማ ጥንታዊት ሐዋርያዊት ይሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በመልዕልተ አድባራት በቀራንዮ መድኋኒዓለምና ቅዱስ ገብርኤል እንዲሁም በወይብላ ቅድስት ማርያም ቤተክርስያን ስር ወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር በማቋቋም ባላቸው እውቀት ጉልበት እና የገንዘብ አቅም ልክ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመደገፍ የተቋቋመ ማህበር ነው

💚💛❤ ከዚህም በኋላ ያቺ መጋረጃ ወደ ሰማይ ተመለሰች። ቅዱስ ጴጥሮስም ስለ አየው ራእይ አደነቀ ይህም ራእይ ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር የሚመለሱ አሕዛብን ስለመቀበል እንደሆነ አስተዋለ። ለወንድሞቹ ሐዋርያትም አሕዛብ የእግዚአብሔር ቃል እንደተቀበሉ የመቶ አለቃ ቆርኔሎስንም ከወገኖቹ ጋር እንዳጠመቀው ነገራቸው። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ከቅዱ ዮሐንስ ጋር ጌታችን እንደአዘዛቸው ወደ አንጾኪያ ከተማ ገቡ የአገሪቱንም ሁኔታ ይጠይቅ ዘንድ ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ዮሐንስን ላከው ሰዎችንም አግኝቶ ክፉ ነገርን ተናገሩት። ሊገድሉትም ፈለጉ እያለቀሰም ተመለሰ ሰውነቱም ተበሳጨች ጴጥሮስንም አለው "አባቴ ሆይ የእሊህ ጎስቋሎች ክፍታቸው እንዲህ ከሆነ ወደ ነገሥታቱና ወደ መኳንንቱ ገብተን በጌታችን ስም በሰበክን ጊዜ ምን እንሆ ይሆን እንዴትስ ሃይማኖትን እናስተምራለን"። ቅዱስ ጴጥሮስም "ወዳጄ ሆይ የሃያውን ቀን መንገድ በአንዲት ሌሊት ያመጣን እርሱ ሥራችንን መልካም ያደርግልናል አትፍራ አትዘን" አለው። 💚💛❤ከዚህም በኋላ ወደ ከተማ መካከል ክብር ይግባውና በጌታችን ስም ሰበኩ የከተማውም ሰዎችና የጣዖታቱ አገልጋዮችም በእነርሱ ላይ ተሰበሰቡ ታላቅ ድብደባንም ደበደቧቸው አጎሳቋሏቸውም ግማሽ የእራስ ጠጉራቸውን ላጭተው ተዘባበቱባቸው አሥረውም በግንብ ውስጥ ጣሏቸው። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ተነሥተው ይረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ወደያውን ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኪሩቤልና ሱራፊል እያጀቡት ተገለጠላቸውና እንዲህ አላቸው "የመረጥኳችሁ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሆይ በዘመኑ ሁሉ እኔ ከእናንተ ጋር እኖራለሁና አትፍሩ አትዘኑም"። ለመዘባባቻም በራሷችሁ መኳካከል ስለላጩአችሁ አታድንቁ ይህም መመኪያና ክብርን የክህነት ሥርአትና ምልክትንም ይሆናችኋል ካህን የሚሆን ሁሉ ያለዝህ ምክንያት ሥጋዬንና ደሜን ማቀበል አልችልም። ይህ መልእክት እያለው የሚሞት ካህምን ኃጢያቱም ይሰረይለታል" ይህን ካላቸው በኋላ ከእርሳቸው ዘንድ በክብር ዐረገ። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወጥቶ ቅዱስ ዮሐንስን ተገናኘው "የዚህ አገር ሰዎች ያደረጉብህ ምንድን ነው" አለው እርሱም "ስለ እኔ አታድንቅ የሐዋርያትን አለቃ በእኔ ላይ ባደረጉት አምሳል አድርገውበታልና" አለው። ቅዱስ ጳውሎስ አጽናናቸው እንዲህ አላቸው "እኔ በጌታችን ፍቃድ ወደ ከተማው ውስጥ ገብቼ እናንተንም አስገባቸዋለሁ"። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ሒዶ ምክንያትን ፈጠረ ጣዖታቸውንም እንደሚያመልክ መስሎ ሐዋርያትን እንዲያቀርቡለትና ስለ ሥራቸውም እንዲይቃቸው የከተማውን መኳንን አነጋገራቸው። መኳንንቱም ወደ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲያቀርቧቸው አዘዙ በቀረቡም ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ ስለሥራቸው ጠየቃቸው። እነርሱም "ድንቆችንና ተአምራቶችን የሚያደርግ ለክርስቶስ ወደ መዛሙርቶቹ እንደሆኑ ነገሩት። ዳግመኛም "እናንተ እንደርሱ ማድረግ ትችላላችሁ" አለቸው እነርሱም "አዋ በእርሱ ስም ሁሉን ሥራ መሥራት እንችላለን" አሉት። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ከእናቱ ማኅፀን እውር ሁኖ የተወለደውን አይኑን አበሩ። የንጉሡንም ልጅ ከሞተ በሦስት ወሩ ሥጋውን ከተባላሸ በኋላ ከመቃብር አሥነሱት። ንጉሡና የከተማ ሠዎች ሁሉ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ጴጥሮስም ምድሩን ረግጦ ውሃን አፈለቀ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አደረጓቸው። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ በሎዶቅያ ያሉ ምእመናን የቂሳሮስ ባሕር ከወሰኑ አልፎ ቡዙ ሰዎችን ከአትክልት ቦታዎቻቸውና ከከቡቶቻቸው እንዳሰጠማቸው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ላኩ ጴጥሮስም ተወዳጅ ቅዱስ ዮሐንስን ወደ እነርሱ ላከ ዮሐንስም ወደ እነርሱም ሲጓዝ በጎዳና በግ አገኘ በጉንም እንዲህ ብሎ ላከው "ወደ ቂሳሮስም ወንዝ ሒደ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ወደ አንተ ልኮኛል ወደ ቀድሞው ወሰንህ ተመልሰህ ትገባ ዘንድ አንተ በእግዚአብሔር ቃል የታሰርክ ነህ ብሎሀል በለው"። ያን ጊዜ በጉ ሒዶ እንደአዘዘው አደረገ ወንዙም ሸሽቶ ወደ ቦታው ተመለሰ ቁጥር የሌላቸው ቡዙዎች የከተማ ሰዎችም ይህን አይተው በጌታ አመኑ። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ አልፎ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በዚያም ሥራ መሠሪው ሲሞን ተቃወመው እርሱንም ከአየር አውርዶ ጥሎ አጠፍው ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ብዙዎች ሕዝቦች አመኑ። የከተማው ገዢ የአክሮጶስ ቊባቶችም የቅዱስ ጴጥሮስን ትምህርት ተቀበሉ ሌሎችም የከበሩ ቡዙዎች ሴቶች ትምህርቱን በመቀበል ከባሎቻቸው እርቀው ንጽሕናቸውን ጠበቁ። ስለዚህም ነገር ቅዱስ ጴጥሮስ ሊገድሉት የሮሜ መኳንንት ተማከሩ። የአልታብዮስ ሚስትም እንዳይገሉት ከሮሜ ከተማ ወጥቶ እንዲሆድ ወደ ቅዱ ጴጥሮስ ላከች ምእመናን ወንድሞችም ውጣ አሉት እርሱም ቃላቸውን ተቀበለ ትጥቁንም ለውጦ ከከተማ ወጣ። በሚወጣበትም ጊዜ መስቀል ተሸክሞ ወደ ከተማ ሲገባ ጌታችንን አገኘውና "አቤቱ ጌታዬ ወዲት ትሆዳለህ" አለው ጌታዬም "ልሰቀል ወደ ሮሜ ከተማ እህሔዳለሁ" ብሎ መለሰለት። ቅዱስ ጴጥሮስ "አቤቱ ዳግመኛ ትሰቀላለህን?" አለው። 💚💛❤ ያን ጊዜም "ጎልማሳ ሳለህ ወገብህ በገዛ እጅህ ታጥቀህ ወደ ወደድከው ትሔዳለህ በሸመገልክ ጊዜ ግን እጅህን ታነሳና ሌላ ያስታጥቅሃል ወደ ማትወደው ይወስድሃል" ያለውን የጌታችንን ቃል አሰበ አስተዋለውም። ያን ጊዜም ወደ ከተማው ተመልሶ ክብር ይግባውና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የሆነውን ለወንድሞች ነገራቸው እነርሱም እጅ አዘኑ። 💚💛❤ ንጉሥ ኔሮንም ቅዱስ ጴጥሮስን እንዲሰቅሉት አዘዘ ሊሰቅሉት በያዙት ጊዜ ወታደሮችን እንዲህ ብሎ ለመናቸው "የክብር ንጉሥ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ላይ ሁኖ ስለተሰቀለ እኔ ቊልቊል ልሰቀል ይገባኛል"። ወዲያውንም እንደነገራቸውም ሰቀሉት። ተሰቅሎም ሳለ ለምእመናን የሕይወትን ቃል አስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ከዚህም በኋላ ሐምሌ 5 ቀን ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታች በሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎት ይማረ በረከቱም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘለላለሙ አሜን።                ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ ይህም ቅዱስ በተለያዩ ስሞች ይጠራ ይኸውም ልሳነ ዕረፍት፣ የክርስቶስ አንደበት፤ የዕውቀት አዘቅት፤ የቤተ ክርስቲያን መብራት፤ እንደ ስሙም ትርጓሜ መሪ አመስጋኝ ወደብ ጸጥታ ነው። 💚💛❤ ይህም ጳውሎስ አስቀድሞ በክርስቶስ ያመኑትን የሚያሳድድ ነበር፤ እርሱም ከብንያም ወገን የፈሳሪሳዊ ልጅ ነው። ወላጆቹም ሳውል ብለው ስም አወጡለት ትርጓሜውም ስጦታ ማለት ነው። ቁመቱ ቀጥ ያለ መልኩ ያማረ ፊቱ ብሩህ ቅላቱ እንደ ሮማን ቅርፍት ደበብ ያለ ዐይኑም የተኳለ የሚመስል አፍንጫው ቀጥ ያለ ሸንጎበታም ጉንጩ እንደ ጽጌ ረዳ ነበር። 💚💛❤ እርሱም ሕገ ኦሪትን አዋቂ ነበረ። ለሕጉም ቀናተኛ ሆኖ ምእመናን አሳዳጅ ነበረ። ወደ ሊቀ ካህናቱም ሔዶ መንገድ የሚያገኘው ሰው ቢኖር ወንዶችንና ሴቶችን እንደ ታሠሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይመልሳቸው ዘንድ ለደማስቆ ከተማና ለምኵራቦች የፈቃድ ደብዳቤ ለመነ። ሲሔድም ወደ ደማስቆ ከተማ አቅራቢያ በደረሰ ጊዜ ድንገት ከሰማ መብረቅ ብልጭ አለበት በምድር ላይም ወደቀ ወዲያውም "ሳውል ሳውል ለምን" ታሳድደኛለህ የሚለውን ቃል ሰማ።
Показати все...
💚💛❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 💚💛❤ ✝ 🌿🌹 ሐምሌ_፫ (3) ቀን።🌹🌿✝️ 🌻🌹🌿🌹🌿🌹🌻                  ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ እንኳን ለእስክድርያ ሃያ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ ለአምደ ሃይማኖት መናፍቁ ንስጥሮስ በጉባኤ ኤፌሶን ተከራክሮ ረቶ ላወገዘው ለታላቁ ለአቡነ ቄርሎስ ለዕረፍት መታሰቢያ በዓልና ከእርሱ በፊት ለነበረው ሊቀ ጳጳሳት ዮናክንዲኖስ ደቀ መዝሙሩ ለነበረው ለሮሜ ሊቀ ጳሳት ለቅዱስ አባት #ለአባ_ክልስቲያኖስ_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።                 ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ አባ ቄርሎስ፦ ይህም አባት ለእስክንድርያ (ለግብጽ) ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ አራተኛ ነው። ይህም ቅዱስ የእናቱ ወንድም በሆነው በአባ ቴዎፍሎስ ዘንድ አደገ፤ ጥቂት ከፍ ባለ ጊዜም ወደ አስቄጥስ ወደ መቃርስ ገዳም ላከው በዚያም አምላካውያን የሆኑ መጻሕፍትን ተማረ እግዚአብሔርም መጽሐፍትን አንድ ጊዜ አንብቦ እስከሚአጸናው ድረስ ዕውቀትንና ማስተዋልን ሰጠው። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ ያስተምረው ዘንድ ለአባ ሰራብዮን ሰጠው ከእርሱም ዘንድ ያለውን ትምህርትን በፈጸመ ጊዜ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ መለሰው። እርሱም እጅግ ደስ ተሰኘበት እግዚአብሔርንም አመሰገነው። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ሁል ጊዜ መጻሕፍትን እንዲያነብና ሕዝቡን እንዲያስተምር ለሊቀ ጵጵስና ሥራ ውስጥ ሾመው። ከትምህርቱም ጣዕም የተነሣ ዝም ይል ዘንድ ማንም አይወድም ነበር። 💚💛❤ አባ ቴዎፍሎስ በዐረፈ በኋላ በእስክንድርያ ከተማ ላይ ይህን አባ ቄርሎስነ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም በትምህርቱ ቤተ ክርስቲያን በራች። ይኸው አባት ቄርሎስ የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት የነበረው ንስጥሮስ በካደ ጊዜ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ማኅበርን በኤፌሶን ከተማ ሰበሰበ። ይህ አባት ቄርሎስን መረጠው ሊቀ ጉባኤ አደረጉት ንስጥሮስንም ተከራከረው ስህተቱንም ገለጠለት ከስህተቱም ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ከመንበረ ሲመት አሳደዱት። 💚💛❤ ይህም አባት ቄርሎስ አሥራ ሁለት አንቀጾችን ደረሰ። በውስጣቸውም የቀናች ሃይማኖትን ገለጠ። ከዚህም በኋላ ግን ብዙዎች ድንሳናትን ተግሳጻትንና መልእክቶችን ደረሰ። እሊህም በሁሉ ቦታ በመምእመናን እጆች ይገኛሉ። 💚💛❤ ይህም አባት ቄርሎስ እግዚአብሔር ቃል ከትሥብእቱ ጋራ ከተዋሐደ በኋላ በሥራ ሁሉ በምንም በምን የማይለያይ አንድ አካል አንድ ባሕሪይ እንደሆነ አስረዳ። ይህኀኀዕዐዐዐዘፈዐጸዐሬፈጰም አባት ቄርሎስ ሃይማኖታቸው ከቀና ከሦስት መቶ አሥራ ስምንት አባቶ ሃይማኖት ወጥተው ክርስቶስ ወደ ሁለት የሚከፍሉት መናፍቃንን ሁሉንም አውግዞ ለያቸው። 💚💛❤ ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ መንበር ላይ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ መልካም የሆነኄዐጸዘጨዐዐዐው ሥራውም ፈጽሞ ሐምሌ 3 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቄርሎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላዓለሙ አሜን።                 ✝ ✝ ✝ 💚💛❤ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ክልስቲያኖስ፦ ይህ አባ ዮናክንዲዮስ በሚያርፍበት ጊዜ በእርሱ ፈንታ አባ ክልስቲያኖስን ሊቀ ጵጵስና እንዲሾሙት አዘዘ እርሱንም አባ ክልስቲያኖስን "በሮሜ አገር ነጣቂ ተኩላዎች አሉና ልጄ ሆይ ተጠበቅ" ብሎ አዘዘ። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ አባ ዮናክንዲዮስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት ክልስቲያኖስን በእርሱ ፈንታ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። በዚያ ወራት ደግ ንጉሥ አኖርዮስ ነበር ከእርሱም በኋላ አመጸኛ ሉልያኖስ ነገሠ እርሱም ክርስቲያኖስን ከመንበሩ አሳድዶ መናፍቁን ንስጥሮስን ሊቀ ጵጵስና ሾመው። የከተማ ሰዎች ግን አባረሩት እንጂ አልተቀበሉትም በከሀዲው ንጉሥም ልብ በክርስቲያስ ላይ ቂም ነበረ ሊገድለውም ይሻ ነበር። እርሱ አባ ክልስቲያኖስ ግን በሮሜ ከተማ የሚገኙ ገዳማት በንዱ ገብቶ ኖረ እግዚአብሔርም ብዙ ድንቆችንና ተአምራቶችን በእጆቹ ያደርግ ነበር። 💚💛❤ ከዚህም በኋላ ከሀዲው ንጉሥ ወደ ጦርነት ሆደ የእግዚአብሔር መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሩፋኤልን ለክልስቲያኖስ ተገለጠለት ወደ አንጾክያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ድምትርያኖስ ይሔድ ዘንድ አዘዘው "በዚያም ኑር" አለው። "ንጉሡ ከጦርነት እንደተመለሰ ይገድልህ ዘንድ በልቡ አስባልና"። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ከዚያ ገዳም ወጣ ከእርሱም ጋራም ሁለት መነኰሳት ነበሩ ወደ አንጾኪያ ከተማ ወደርሶ ቅዱስ ድምትርያኖስ አገኘው ከአመጸኛው ንጉሥም የደረሰበትን ሁሉ ነገረው እርሱም በአንጾኪያ ከተማ የሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም አኖረው። 💚💛❤ ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሊቃ ጳጳሳት አግናጥዮስና ዮናክንዲዮስ በሌሊት ዕራይ ለንጉሡ ተገለጡለት ከእርሳቸውም ጋራ የነበረው አንዱ እጅግ የሚያስፈራና ግሩም ነበር። እርሱም ንጉሡን እንዲህ አለው "ሊቀ ጳጳሳቱን ክልስቲያኖስን አገሩን ለምን አስተውከው እነሆ እግዚአብሔር ነፍስህን ከአንተ ይወስዳል በጠላቶችህም እጅ ትሞታለህ"። ንጉሥም ጌታዬ "ምን ላድርግ" አለው እነዚያም ሁለትም አባቶች "በእግዚአብሔር ልጅ ሕማም በመቀበሉ ታምናለህን" ብለው መለሱለት "እኔ አምናለሁ" አላቸው "ዳግመኛም መልእክትን ልከህ ልጃችን ክልስቲያኖስ ወደ መንበሩ መልሰው" አሉት። 💚💛❤ ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ መልክትን ጽፌ ወደ ድምትራያኖስ እንዲህ ብሎ ላከ "ስለ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ በእኔ ላይ አትዘን ወደ መንበረ ሲመቱ ይመልሱት ዘንድ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ ያለበትን በመላእክተኞቼ ታመላክታቸውና ታደርሳቸው ዘንድ እለምንሀለሁ"። መልአክተኞችም በሔዱ ጊዜ አገኙትና መለሱት ሕዝቡም በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ ተቀበሉት በዚያም ወራት ንጉሡ ከጦርነት በደና ተመለሰ ቤተ ክርስቲያንም በዕረፍትና በሰላም ኖረች። 💚💛❤ የንስጥሮስም ክህደቱ በተገለጠ ጊዜ በእርሱ ምንክያት አንድነት ያላቸው ማኅበር ተሰበሰቡ ይህ አባት ክልስቲያኖስ በደዌውና በእርጅናው ምክንያት ወደ ጉባኤው መምጣት አልተቻላቸውም ነገር ግን ንስጥሮስን ከሚያወግዝ ደብዳቤ ጋር ሁለት ቀሳውስትን ላከ። 💚💛❤ ክብር ይግባውና ጌታችንም ከዚህ ኃላፊ ዓለም ድካም ሊያሳርፈው በፈቀደ ጊዜ ዮናክንዲዮስና አትናስዮስ ተገለጡለት እንዲህም አሉት "ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕይወት ጠርተሀልና አንተ ወደ እኛ ስለምትመጣ አስጠንቅቃቸው" አሉት። ከእንቅልፉ ነቅቶ ወገኖቹን ጠራቸው እንዲህም አላቸው "ተኩላዎች ወደዚች ከተማ ይገቡ ዘንድ አላቸውና ተጠንቀቁ"። 💚💛❤ ይህንም ከተናገረ በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አለ "እንነሳና እንሂድ እነሆ ቅዱሳን ይሹኛልና ሁለቱ ሌሎች ናቸው በዚችም ሰዓት በዚች ዓለም በአንድነት እንወጣለን እነርሱም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስና የፃን አገር ኤጲስቆጶስ ሉቅያስ ናቸው" ይህንንም ብሎ ሐምሌ 3 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 3 ሰንክሳር።
Показати все...
ማኅበረ ዮርዳኖስ የማኅበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማኅበር

✝️ማህበረ ዮርዳኖስ የማህበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማህበር 👉 የማህበሩ አላማ ጥንታዊት ሐዋርያዊት ይሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በመልዕልተ አድባራት በቀራንዮ መድኋኒዓለምና ቅዱስ ገብርኤል እንዲሁም በወይብላ ቅድስት ማርያም ቤተክርስያን ስር ወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር በማቋቋም ባላቸው እውቀት ጉልበት እና የገንዘብ አቅም ልክ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመደገፍ የተቋቋመ ማህበር ነው

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.