cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Word of GRACE Believers

WGGMtelegram channel is created to spread Zword of GraceGospel to every part of the world.lf U learn U can Change Ur Self& ZRest of Z world. @IKNOWWHOIAMINCHRIST ✟👈BY Z Word of Grace👑MINFESTING THE SUPER ABOUNDAT GRACE OFGOD.🌍

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
189
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎 2015/2022/23 #The-Year-of #DOMINION,INFLUENCE,PROSPER Operating Supenaturaly by Anointing and Grace 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎 Word of Grace GM የፀጋ ቃል የወንጌል አገልግሎት መስከረም 1/1/2015 11/9/2022/23 https://t.me/gospelofgrace
Показати все...
Word of GRACE Believers

WGGMtelegram channel is created to spread Zword of GraceGospel to every part of the world.lf U learn U can Change Ur Self& ZRest of Z world. @IKNOWWHOIAMINCHRIST ✟👈BY Z Word of Grace👑MINFESTING THE SUPER ABOUNDAT GRACE OFGOD.🌍

Repost from Grace
📖📖📖📖📖📖📖📖 📖 እግዚአብሔር_ጽድቅ📖 📖📖📖📖📖📖📖📖 ክፍል=ሁለት ❤❤❤❤❤❤❤❤❤ ❤#በእምነት_የሚገኝ_ጽድቅ❤ ❤❤❤❤❤❤❤❤❤ ሮሜ 3 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²¹ አሁን ግን ሕግና ነቢያት የመሰከሩለት፣ ከሕግ ውጭ የሆነ፣ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጦአል። ²² ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የሚገኝ ጽድቅ ነው። በብሉይ ኪዳን ዘመን ይገለጣል የተባለው የእግዚአብሔር ጽድቅ በአሁኑ ሰአት ከሕግ ውጭ በሆነ መልኩ ተገልጧል። ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠው በሙሴ ሕግ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኝ ጽድቅ ነው። 📌 በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ለመቀበል እምነት ብቻ በቂ ነው። 📌 በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ በስራ እና በጥረት የሚገኝ ሳይሆን በእምነት የምትቀበለው ስጦታ ነው። 📌 ጽድቅ የእግዚአብሔር ማንነት ስለሆነ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ጽድቅ ወደ ሰዎች የመጣው በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ነው። 📌 በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘው ጽድቅ ሰዎች መቀበል የምችሉት በእምነት ብቻ ነው። 📌 “ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ፣ ሕግን በመጠበቅ እንደማይጸድቅ እናውቃለን። ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን እንጸድቅ ዘንድ እኛም ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፤ ሕግን በመጠበቅ ማንም አይጸድቅምና።” — ገላትያ 2፥16 (አዲሱ መ.ት) 📌 “እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤” — ሮሜ 9፥30 📌“ማንም ሰው ሕግን በመፈጸም ሳይሆን፣ በእምነት እንደሚጸድቅ እናረጋግጣለን።” — ሮሜ 3፥28 (አዲሱ መ.ት) የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠው በሙሴ ሕግ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የተገለጠ ጽድቅ ነው። ሙሴ እና ነቢያት የመሰከሩለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ከሕግ ውጭ ሲሆን ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠው በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ያገኘነው ጽድቅ በእምነት ተቀብለናል። ➡➡➡➡ይቀጥላል➡➡➡➡ የእግዚአብሔር ሰው ኤፍሬም ገ/ኢየሱስ Join and follow👇👇👇 https://t.me/+LUMYTeZz9lk2MzM8
Показати все...
የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌል\ The Gospel of the grace of God\

“For I am not ashamed of the gospel of Christ, for it is the power of God to salvation for everyone who believes, for the Jew first and also for the Greek.” -Rom.1:16 ተከታታይ የሮሜ ትምህርት @Grace_Century @Grace_Century Please Contact @Ephraim_Gebreyesus

🔶 አዋጅ 🔷 👉 እኔ በክርስቶስ ጻድቅ ተደርጌያለሁ! የጽድቅን_ዘር ተካፍያለሁ ስለዚህም የጽድቅን_ፍሬ እገልጣለሁ። 👉በክርስቶስ_ኢየሱስ በድህነት፣በሽታ፣በኃጢአት፣በጭንቀት፣ በእጦት ላይ #እነግሳለሁኝ!!! 👉በብርሃን 👉በክብር 👉በቅባት 👉በጸጋ 👉በበረከት 👉በበጎነት 👉በጤንነት 👉በስኬት እመላለሳለሁኝ ❗❗❗ #በኢየሱስ_ስም አሜን። ኢየሱስ_ክርስቶስ ጌታ ነው❗❗❗ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። Word of Grace GM የፀጋ ቃል የወንጌል አገልግሎት ✞ ተወዳጆች ሆይ ተባርካችኋል ✞ https://t.me/gospelofgrace
Показати все...
Word of GRACE Believers

WGGMtelegram channel is created to spread Zword of GraceGospel to every part of the world.lf U learn U can Change Ur Self& ZRest of Z world. @IKNOWWHOIAMINCHRIST ✟👈BY Z Word of Grace👑MINFESTING THE SUPER ABOUNDAT GRACE OFGOD.🌍

Repost from Grace
ምዕራፍ አንድ #የእግዚአብሔር_ጽድቅ #ክፍል=አንድ #ጽድቅ_ምንድነው? (መግቢያ) "ጽድቅ" የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ግሪክ "ዲካይሱኔ" የሚባል ሲሆን ቃሉ "ዲኬ" ከሚለው ስርወ-ቃል (Root Word) የመጣ ነው። "ዲኬ" ማለት "ትክክል" (Right) ማለት ነው። እንዲሁም በዕብራይስጥ "ጸዴቅ" የሚል ሲሆን ትርጉሙ "ትክክል፣ ንጹሕ" ማለት ነው። እንግዲህ በቃሉ ትርጉም መሰረት አንድ ሰው ጸደቀ ማለት "ትክክል" ወይም "በደል-የለሽ" ሆነ ማለት ነው። ሮሜ 3 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²¹ አሁን ግን ሕግና ነቢያት የመሰከሩለት፣ ከሕግ ውጭ የሆነ፣ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጦአል። ²² ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የሚገኝ ጽድቅ ነው። ልዩነት የለም፤ ጽድቅ ማለት በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ መሆን ማለት ነው። (Righteousness is right standing with God.) በሕግ እና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ የተገለጠ የእግዚአብሔር ማንነት ነው። ጽድቅ የእግዚአብሔር ብቸኛው ማንነት ሲሆን በሰው ስራ እና ጥረት የማይገኝ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ነው። 📌 የእግዚአብሔር ጽድቅ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኝ ጽድቅ ነው፤ ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ መቀበል የሚቻለው በእምነት ብቻ የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ነው። 📌 የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠው በሙሴ ሕግ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገለጥ እምነት ነው። 📌 የእግዚአብሔር ጽድቅ በሀይማኖታዊ ስርዓት ኖረን የምንቀበለው ሽልማት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ባለው እምነት የሚገኝ ነው። 📌 እውነተኛ የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኝ መሆኑን በግልጽ ይናገራል። ማርቲን ሉተር የሚታወቀው "Every week I preach justification by faith to my people because every week they forget it" ("በየሳምንቱ ለሕዝቤ በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ እሰብካለሁ፥ ምክንያቱም በየሳምንቱ ይረሱታል") በሚለው ንግግሩ ነው። እናም ማርቲን ሉተር በእምነት ስለሚገኘው ጽድቅ አበክሮ ያስተምር ነበር። ማርቲ ሉተር ዋንኛ ነጥቡ ጽድቅ የሚገኘው በሌላ በማንኛውም መንገድ ሳይሆን በእምነት ብቻ መሆኑን አረጋገጠ:: ➡➡➡➡ይቀጥላል➡➡➡➡ #Messager_Ephraim_Gebreyesus Join and follow👇👇👇 https://t.me/+LUMYTeZz9lk2MzM8
Показати все...
የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌል\ The Gospel of the grace of God\

“For I am not ashamed of the gospel of Christ, for it is the power of God to salvation for everyone who believes, for the Jew first and also for the Greek.” -Rom.1:16 ተከታታይ የሮሜ ትምህርት @Grace_Century @Grace_Century Please Contact @Ephraim_Gebreyesus

Repost from GOSPEL TV ETHIOPIA
Фото недоступнеДивитись в Telegram
... ጽድቅ በእምነት... ✍ በክርስትና ሕይወት ውስጥ ክርስቲያን ሊረዳቸው ከሚገቡ ቁልፍ ነገሮች አንዱ እምነት ነው። ክርስቲያን ስኬታማ የክርስትና ሕይወት እንዲኖር ስለ እምነት ትክክለኛ መረዳት ሊኖረው ይገባል። “ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።” — ሮሜ 1፥17 ከመንፈሳዊ ዓለምን መጠቀም ወይም መቀበል የምንችለው በአምስቱ የስሜት ሕዋሳቻን ሳይሆን በስድስተኛው የስሜት ሕዋሳችን ነው፤ እርሱም በእምነታችን ነው። “ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።” — ገላትያ 3፥11 #እንደ_ክርስቲያን_እምነትን_ችላ_ብለን_መኖር_አንችልም_ምክንያቱም_እምነት_የጻድቅ_መኖርያው_ነው! ጻድቅ መኖሪያው ገንዘቡ ወይም ደሞዙ ወይም ስራው ሳይሆን ጻድቅ መኖሪያው እምነት ነው! ጻድቅ ይህን መኖሪያውን የለቀቀ ቀን መኖር ያቆማል። “ዓለማት በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠሩ በእምነት እንረዳለን፤ ስለዚህ የሚታየው ነገር የተፈጠረው ከሚታየው እንዳልሆነ እንገነዘባለን።” — ዕብራውያን 11፥3 (አዲሱ መ.ት) ስለዚህ ከመንፈሳዊ ዓለም ያለውን መልካም ነገር ወደ ስጋዊ ዓለም የምንቀበለው በእጃችን ሳይሆን በእምነታችን ነው! መልካም ቀን ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ @GospelTvEthiopia @GospelTvEthiopia @GospelTvEthiopia
Показати все...
Repost from Grace
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በቅርብ ቀን በዚህ የቴሌግራም ቻናን ላይ አዲስ ትምህርት ይጀመራል። ምዕራፍ አንድ #የእግዚአብሔር_ጽድቅ በቅርብ ቀን #የእግዚአብሔር_ጽድቅ የሚል ትምህርት በቴሌግራም ቻናን ይተላለፋል። Join and follow👇👇👇 https://t.me/+LUMYTeZz9lk2MzM8
Показати все...
Repost from Grace
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌል ቴሌግራም ቻናን ላይ ቤተሰብ የሆናችሁ ወንድሞች እና እህቶች በአዲስ መልክ ለመጀመር እናስባለን። ከዚህ ቀደመ በነበረው አገልግሎት Order ጠብቀን ማስተማር እንጀምራለን። በዚህ የቴሌግራም ቻናን ላይ የሚተላለፉ ትምህርቶች፦ 📌 የእግዚአብሔር ጽድቅ 📌 ጸጋ 📌 አዲስ ፍጥረት 📌 እምነት 📌 በሕግ እና በጸጋ መካከል ያለው ልዩነት 📌 የእግዚአብሔር መልካምነት 📌 ትንሣኤ 📌 የክርስቶስ ደም እና ሌሎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልዕክቶች እንማራለን። Join and follow👇👇👇👇 https://t.me/+RadfKjJvYdaWhzed
Показати все...
Repost from Grace
Фото недоступнеДивитись в Telegram
❝በእምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል፤ እምነት ግን መጥቶአልና ከእንግዲህ ወዲህ ከሞግዚት በታች አይደለንም።❞ --ገላትያ 3:24-25 የፀጋ ተቃዋሚ ሰይጣን ሳይሆን ሐይማኖት ነው። የፀጋን ጉልበት የሚያዳፍኑ በአዲስ ኪዳን እየኖሩ በብሉይ ኪዳን ሕግ መገዛት ተገቢ እንደሆነ የሚቆጥሩ ሐይማኖተኞች እንጂ ሰይጣን ፀጋን የማዳፈን አቅም አልተሰጠውም። ጌታ ኢየሱስ በምድር ባገለገለበት ዘመን ዋነኛ ተቃዋሚዎቹ ፈሪሳዉያን(ሐይማኖተኞች)ነበሩ። ከአሮጌው ሥርዓት(ከብሉይ ኪዳን) ሕግ ሙሉ በሙሉ ያልተላቀቀ አዕምሮ በአዲሱ ሥርዓት(በአዲስ ኪዳን) የፍቅር ሕግ እንደሚገባ መመላለስ ስለማያስችል ፀጋን በሙላት ሊገለገልበትም ሆነ ሊያገለግልበት አይችልም። ፅድቅን በተመለከተ፤ሐይማኖተኞች እንደሚሉት በኢየሱስ ተጀምሮ በሰው ሥራ የሚቀጥልና ከፍፃሜ የሚደርስ ለሰው የቀረ ድርሻ የለም። የሰው አስተዋፅዖ ያልተጨመረበት እውነተኛው የእግዚአብሔር ፅድቅ ክርስቶስ ራሱ ነው። ያ ፅድቅ ደግሞ የሚገኘው ሕግን በመጠበቅ በሥራ ሳይሆን በእምነት ነው። ❝አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት #የእግዚአብሔር_ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው።❞ ሮሜ 3:21-22 የእግዚአብሔር ፅድቅ የሚገኘው ❝ለሚያምኑ ሁሉ እንጂ ለሚሰሩ(ሕግን ለሚጠብቁ ሁሉ)❞ አልተባለም። በፀጋ ሥር ሆኖ፤ሕግን በመፈፀም(በሥራ) ጽድቅን መፈለግ የክርስቶስን ሞት ከንቱ ማድረግ ነው። ❝ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።❞ —ገላትያ 2: 21 የመረጃ ምንጭ Milka Yonatan Facebook page የተወሰደ ነው። http://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD
Показати все...
Repost from Grace
00:16
Відео недоступнеДивитись в Telegram
የልጅነት ዘር ሃይል - Sneak peak videos ll Apostle Zelalem Getachew http://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD
Показати все...
2.66 MB
#ምን_ታስባለህ??? 👉 #ትኩረትህን_ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት #በክርስቶስ የሆነው ማንነትህ ላይ አድርግ። 👉 #ከሚያጉረመርሙና ስንፍናን ከሚናገሩ ሰዎች ጋር ከመዋል ይልቅ ራስህን #በእምነት በበረቱ እና እምነትን_በሚናገሩ_መልካምን_ነገር_በሚያውጁ እና #በክርስቶስ በሆኑት ነገር ላይ በሚያተኩሩ ሰዎች ክበብ። #እንግዲያስ_እምነት:ከመስማት ነው:መስማትም:በእግዚአብሔር _ቃል :ነው። ሮሜ 10፦17 LET THE REVOLUTION BEGIN 👑👑👑👑👑👑👑👑👑👑 የጸጋ አብዮት በክብርና በኃይል https://t.me/revolutionbygrace
Показати все...
GRACE REVOLUTION/የፀጋ አብዮትበክብርናበኃይል

LET THE REVOLUTION BEGIN 🗽✟🔥🌍

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.