cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

TIKVAH-SPORT

Більше
Ефіопія22Амхарська21Спорт123
Рекламні дописи
211 673
Підписники
+10724 години
+1 1287 днів
+7 46230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

“ ካሴሚሮ ወደ ሳውዲ ወይም አሜሪካ ሊግ መሄድ አለበት “ በስካይ ስፖርት ቴሌቪዥን በተንታኝነት እየሰራ የሚገኘው የቀድሞ ተጫዋች ጄሚ ካራገር በካሴሚሮ ብቃት ደስተኛ አለመሆኑን ገልጿል። “ ካሴሚሮ በትልቅ ሊግ መጫወት የቀረው ሶስት ጨዋታዎች ብቻ ነው “ የሚለው ካራጋር “ እንደማስበው በቀጣይ ወደ ሳውዲ አልያም አሜሪካ ሊግ ማቅናት ይኖርበታል “ ሲል ተደምጧል። ካራገር አያይዞም “ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ከሀላፊነት የሚነሳ ከሆነ ምንም ምክንያት የሚያቀርብ አይመስለኝም “ በማለት ተናግሯል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Показати все...
👍 155😁 81👎 16 15
#PremierLeague በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ የሚመራው የማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ በዘንድሮው የውድድር ዓመት " አስከፊ " የሚባል ጉዞን እያደረጉ ይገኛሉ። ትላንት ምሽት ቡድኑ በክሪስታል ፓላስ መሸነፉን ተከትሎም :- - ከ 87ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ የውድድር ዓመት 8⃣1⃣ ጎሎች ተቆጥሮባቸዋል። - በአንድ የውድድር ዘመን 1⃣3⃣ ጨዋታ በሊጉ በመሸነፍ ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል። - በ 2024 የውድድር ዘመን በተጋጣሚ ቡድን ብዙ ሙከራዎች የተደረገባቸው ሲሆን 20ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ሼፍልድ ዩናይትድ #ያልተሻለ ነው። - ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች 2⃣1⃣ ጎሎች ተቆጥረውባቸዋል። ቀያይ ሴጣኖቹ በ 3⃣ የግብ እዳ 5⃣4⃣ ነጥቦችን ሰብስበው #ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Показати все...
😁 151👍 60😢 27👌 6👎 5 5
Repost from HEY Online Market
•PlayStation 5 •Playstaion 5 Slim •PlayStation 4 Slim •PlayStation 4 Pro •Playstaion portal •PlayStation VR Contact 0953964175 @heymobile @heyonlinemarket
Показати все...
👍 6 2👎 1
"ባሸነፉት ውርርድ ላይ እስከ 300% ACCA ጉርሻ ያግኙ! ቤቲካ ላይ ይወራረዱ! ያሸንፉ! የዛሬውን ዕለታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - (betika.et/dailyjackpot) የዛሬው የተመረጡ ዕለታዊ ጨዋታዎች ላይ ለመወራረድ - (betika.et) የሳምንታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - (betika.et/weeklyjackpot)"
Показати все...
👍 7🤔 2
" ስለ ቀጣይ ቆይታዬ አያሳስበኝም " - ቴንሀግ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ስለ ቀጣይ ቆይታቸው ምን እንደሚያስቡ ከጋዜጠኞች ተጠይቀው ፥ " ስለዚህ ጉዳይ አላስብም " ሲሉ መልሰዋል። " ቡድኑን በምችለው መንገድ አዘጋጃለሁ። ብዙ ችግሮች አሉብን። ትኩረት የማድረገው ከቡድኔ ጋር የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው። ቡድኔን የተሻለ ለማድረግ ብቻ ነው የማስበው " ብለዋል። አሰልጣኙ በፓላሱ ጨዋታ ላይ ካሴሜሮ ያሳየውን ብቃት ተጠይቀው ፤ በተፈጠረው ነገር በአንድ ተጨዋች ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ እንደማያስፈልግና አጠቃላይ የቡድኑን ብቃት ማየት እንደሚገባ ተናግረዋል። አሰልጣኙ ቡድናቸው በቀጣይ እሁድ ከአርሴናል ጋር ላለበት ጨዋታ ተሻሽሎ መቅረብ እንዳለበት ገልጸዋል። " የዛሬው ትክክል አልነበረም እሁድ ትክክለኛውን ነገር ማሳየት አለብን። ከዛሬው ጨዋታ ተምረን ማሻሻል ይጠበቅብናል " ብለዋል። " ልክ ደጋፊዎች ለቡድናቸው እንደተፋለሙት እኛም እንደዛው መፋለም አለብን " ያሉት ቴንሀግ ፥ " አሁንም ባሉኝ ተጫዋቾች መፋለሜም እቀጥላለሁ " ሲሉ ተናግረዋል። @tikvahethsport
Показати все...
😁 240👍 116👎 27 18🤬 5
" ለዩናይትድ ትክክለኛው ሰው ነኝ " ቴንሀግ የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከምሽቱ ሽንፈት በኋላ በሰጡት አስተያየት ለዩናይትድ ትክክለኛው አሰልጣኝ ነኝ ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል። " ዛሬ ያደረግነው ነገር በቂ አይደለም " ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ደጋፊዎች እስከመጨረሻው ድጋፍ አድርገውልናል እኛ እንደነሱ መፋለም አለብን ብለዋል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከጨዋታው በኋላ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ለማንችስተር ዩናይትድ ትክክለኛው ሰው ነኝ ብለው ያምኑ እንደሆነ ተጠይቀው " ያለጥርጥር " ሲሉ መልሰዋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Показати все...
😁 498👍 62👎 38🤬 29 7😱 4💯 4
" በዩናይትድ ደረጃ ያልሆነ ተጨዋቾች አሉ " ያንግ የቀድሞ የቀያይ ሴጣኖቹ ተጨዋች አሽሊ ያንግ ማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ በክለቡ ደረጃ ላይ ያልሆኑ ተጨዋቾች መኖራቸውን ተናግሯል። ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ አስተያየቱን የሰጠው አሽሊ ያንግ " በክለቡ ውስጥ በማንችስተር ዩናይትድ ደረጃ ያልሆኑ በርካታ ተጨዋቾች ይገኛሉ " ሲል ተደምጧል። አሺሊ ያንግ አያይዞም ማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ ምሽት እንዳሳየው አይነት እንቅስቃሴ በሚቀጥሉት ጨዋታዎች ካደረገ በአውሮፓ መድረክ መሳተፍ እንደማይችል ገልጿል ፈ። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Показати все...
👍 157😁 64 12🤔 3😱 3👏 1👌 1
" ቴንሀግ መቆየት አይችልም " የቀድሞ እንግሊዛዊ ተጨዋች ሚይክል ኦውን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድን ለማሰልጠን የሚበቁ አሰልጣኝ አለመሆናቸውን ገልጿል። " አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድን ለማሰልጠን በቂ አይደለም " ያለው የቀድሞ ተጨዋቹ እሱ ቀጣይ አመት ክለቡን መምራት አይችልም በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Показати все...
👍 269😁 72👎 24 13👏 8🔥 3👌 1
ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል ! ማንችስተር ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፈዋል። የክሪስታል ፓላስን የማሸነፊያ ግቦች ሚካኤል ኦሊሴ 2x ፣ ማቴታ እና ታይሪክ ሚቼል ማስቆጠር ችለዋል። ቀያዮቹ ሴጣኖች ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ሀያ አንድ ግቦች ተቆጥረውባቸዋል። ማንችስተር ዩናይትድ በአንድ የውድድር ዘመን አስራ ሶስት የሊግ ጨዋታዎችን ሲሸነፍ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል። ክሪስታል ፓላስ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንችስተር ዩናይትድ ላይ አራት የሊግ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 8️⃣ ማንችስተር ዩናይትድ :- 54 ነጥብ 1️⃣4️⃣ ክሪስታል ፓላስ :- 43 ነጥብ ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ? እሁድ - ማንችስተር ዩናይትድ ከ አርሰናል ቅዳሜ - ዎልቭስ ከ ክሪስታል ፓላስ @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Показати все...
😁 272👍 82👎 23 15🔥 5👏 2
90' ክሪስታል ፓላስ 4 - 0 ማንችስተር ዩናይትድ           ⚽⚽ ኦሊሴ           ⚽ ማቴታ           ⚽ ሚቼል @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Показати все...
😁 87👏 14👍 11👎 9😢 4🥰 3🤔 2 1