cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ስለ አለም በግጥም

በዚህ ቻናል የማይነሳ ሀሳብ የለም በግጥም መልክ።።።።።።። ስለ ፍቅር ናፍቆት ስለሀገር እማይፃፍ የለም ቅሬታ ወይም አስተያየት ካላችሁ @abrshi12on ቴሌ ግራም ላይ ይስጡን

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
279
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

menaw kerfede.m4a2.36 MB
menaw mewashatek.m4a6.51 KB
Repost from N/a
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ያሉበት ድረስ እናመጣለን ዋጋ 1600ብር የሚፈልግ ካለ 0967318035 ደዉሉ t.me/gech23onto
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
።።።።።።።።።።።ትርታዬ።።።።።።።።።።። ።።።።።።።።።።ክፍል 17።።።።።።።።።። ከዛም በተቤሉበት ሰአት ወክ ብላ ይዛት ወጣች ሰአቱ መሽቷል የወይንሸት ሳቅ የውሸት ቢሆንም እየተሳሳቁ መንገድ ጀመሩ.....መድረስ አይቀርምና ዮናስ ያላት ቦታ ደረሱ ከዛም ከየት መጡ ሳይባል በጥቁር ጨርቅ የተሸፈኑ አራት ጎረምሶች አፋፍሰው ሁለቱ ወይንሸትን ሁለቱ መቅደስን ተሸክመው በግራና በቀኝ ወሰዷቸው ሁለቱ ጓደኛሞች እየተወራጩ ተለያዩ በርግጥ ለማስመሰል እንጂ ወይንሸት ውሸቷን ነበር..... ........ከዛም ቀጥታ በጣም አስፈሪና ጨለማ የሆነ ቦታ ወሰዷት ማን ይያዛት ማን ይልቁቃት ምንም አታውቅም ወዲያው አንዱ በደንብ ያዛትና አንዱ አደንዛዥ እፅ ወጋት ከዛም ከቆይታ ቡሀላ ሁለቱ ወንዶች ጥለዋት ወጡ ከመውጣታቸውም ሶስተኛው ዮናስ ዋሻ የመሰለውን አስፈሪ ቤት መብራት አበራው........ ......በሰአቱ ሌላ ሰው ሆና ነበር ምንም አታስታውስም ዮናስንም እንዳየችው ዋው ምን አይነት ውበት ነው አለችው እየተቅበጠበጠች እሱም ታዲያ ስንቱ ያረገደለትን ውበት እንዴት እረግጠሽው ሄድሽ አላት እሷም ግራ በመጋባት እኔ አለችው ...አዎ አንቺ አላት ቀጥላም አረ ይሄን የመሰለ ገላ እንቢ ብል እራሱ ሀጢያት ይሆንብኛል ስትለው የወጓት እፅ መስራቱን ተረዳ........ .........ሊበቀላት ያሰበው በህዝብ መሀል ነበር ዛሬ ደግሞ የቀወጠ ፓርቲ አለ ለዛም ነው ይህንን ቀን የመረጠው.... ......መጨፈር ትፈልጊያለሽ አላት እሷም አዎ በደንብ አለችው እየተሻሸችው እሺ እንደዛ ከሆነ ዛሬ ፓርቲ ስላለ አብረን ሄደን እንቀውጠዋለን አላት በደስታ ዘለለች አቀፈችውም እሱ ግን ከዛ በፊት ባንድ ነገር እንስሜ አላት እሷም ምንድነው አለችው ቀጠለ ማንም ሰው ዮናስ ምንሽ ነው ቢልሽ ፍቅረኛዬ ነው ትያለሽ አሁንም መቅደስ ግራ በመጋባት ዮናስ ማነው አለችው እሱም እየውልሽ ዮናስ ማለት እኔ ነኝ ለዛሬ ማለትም ለፓርቲው ፍቅረኛሞች ሆነን ነው የምንታየው ገባሽ አላት እሷም በደስታ ተስማማች..... .....ገና ተቃቅፈውም ሲገቡ ብዙ የሚያውቋት ተማሪዎች ስለነበሩ ሰላም ሊሏት ተጠጉ እሷ ግን ማንንም ልታውቅ አልቻለችም ግራ ተጋቡ መቅደስ መንታ እህት አላት እንዴ እስከማለት ደረሱ እውነትም ታስብላለች ቅብጥብጥ ብላ ዮናስ ላይ እንደማስቲሽ ተለጥፋ ለመጣው ለሄደው ትስቃለች ምንም አላሳፈረችውም አንዴ ካንገቱ አንዴ ከወገቡ እየተጠመጠመች ትስመዋለች ለማያውቃቸው አዲስ ፍቅረኛሞች ነው የሚመስሉትግን አብዛኛዎቹ የጌዲዮ ፍቅረኛ መሆኗን ስለሚያውቁ ግራ በመጋባት ጭፈራቸውን አቁመው እነሱን ያያሉ.... .......ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ግን ዮናስ እንዳሰበው ሳይሆን ተቃራኒ ሆኖ በቀሉን ከግብ ሳያደርስ ጌዲዮ ፊቱ በርበሬ መስሎ እሳት ለብሶና ጎርሶ ከፊትለፊቱ ቆመ ዮናስ የታወቀ ተደባዳቢ ስለሆነ አልፈራውም...ከዛም ጌዲዮ መቅደስን ከቅፉ ጎትቶ አስወጣት እሷም ምንድነው ብላ ጮኸችበት ዮናስም ፈልጋ እንጂ አስገድጃት እኮ አይደለም ምን ያበሳጭሀል አለው ጌዲም የመቅደስን ጉንጮች በሁለት እጆቹ ይዞ አይናይኗን እያየ መቅዲ ምንድነው የተፈጠረው አላት እሷም ማናት መቅደስ ምንድነው የምታወራው ብላ መልሳ ከጠየቀችው ቡሀላ ወደ ዮናስ ዞራ ፍቅር ምን ፈልጎ ነው አለችው...ዮናስም መልስ ለመመለስ ሲቃጣ ሁኔታዋ ግራ ያጋባው ጌዲዮ ምን አርገሀት ነው ብሎ ከመቅፅበት በቦቅስ አፍንጫውን ሲለው ዮናስ ደም በደም ሆነ የፓርቲው ሙዚቃ ባንዴ በጩኸት ተቀየረ......... .........ዮናስ ደሙን ጠራርጎ ሊመታው ሲል እንዳልነበር አርጎ ቀጠቀጠው ከዛም የዮናስ ጓደኞችም ተጨመሩ ቢሆንም ከጌዲዮ ቦቅስ ተቋደሱ እንጂ አላስጣሉትም ምናልባት አንድ ሁለቴ እንጂ ከዛ በላይ አልተመታም ጌዲዮ በቃ ከዚያን ቡሀላ ቆሞ የሚቀርፅና የሚጮህ እንጂ አገላጋይ ጠፋ ብዙ ተደባደቡ...... ......ጌዲዮ በበሽታው ይፈራል እንጂ ከማንም ጋር ተደባባድቦም ሆነ ተሰዳድቦ አያውቅም ነበር ዛሬ ግን በዝምታው ውስጥ ወንድነት ባንገት ደፊነቱ ውስጥ ጀግንነት መያዙን አስመሰከረ ወዲያው ነበር በሼር እየተቀባበለ ያየው............ ......ብርሀንና ሰአዳም ወዲያው እንዳዩት እየበረሩ ቦታው ላይ ደረሱ ሲደርሱ ግን አካባቢው በፖሊስ ተከቦ ነበረ ወዲያውም መቅደስን ጌዲዮንና ዮናስን ጥያቄ እየጠየቁዋቸው ተመለከቱ......ፓሊሶቹም የማን እንደሆነች ሲጠይቋቸው ሁለቱም የኔ የኔ ማለትና መከራከር ጀመሩ ሁኔታው ግራ ያጋባቸው ፓሊሶች ወደ መቅደስ አፍጥጠው የማን ነሽ አሏት እሷም ዮናስ እንዳላት የዮናስ ፍቅረኛ ነኝ አለች ጌዲዮ በሰላሟ እንደልሆነ ቢገባውም እንዲህ ስትል ደነገጠ ጓደኞቿም በድንጋጤ አፋቸውን ይዘው ደርቀው ቀሩ... ወዲያውም ፓሊሶቹ ጌዲዮን እስር ቤት ዮናስን ደግሞ በጣም ደም እየፈሰሰው ስለነበር ሆስፒታል ይዘዋቸው ሄዱ። መቅደስን ደግሞ እንደምንም ብለው በጌዲ መታሰር በሀዘን ተኮራምተው ግን ምንም ማድረግ ስላልቻሉ ወደ ዶርም ይዘዋት ሄዱ........ #ክፍል 18 ይቀጥላል ከወደዱት ሼር ማድረግም አይረሳ @abrshi12onto
Показати все...
።።።።።።።።።።።ትርታዬ።።።።።።።።።።።። ።።።።።።።።።።ክፍል 16።።።።።።።።።።። ጌዲና መቅዲ ባሁን ሰአት ለደቂቃ እንኳን መለያየት ይከብዳቸዋል በቀን ቀን ፍቅራቸው እየጨመረ አማላይ ጥንዶች ሆነዋል ጌዲም በብዙ ነገር ተቀይሯል አሁን ከሰው ጋር ይውላል ከክፍል ጓደኞቹም ጋር ይጮታል አብሮ ይበላል አብሮ ይጠጣል በመዘነጥም ቢሆን የግቢውን ቆንጆዎች አስንቋል ግን ለዚህ ሁሉ መሆን መቅደስ በፍቅሯ ቃል አስገብታው ነው አረ አሁንማ ከማድነቅ አልፈው ብዙ ሴቶች ለፍቅር እየተመኙት ነው ጌዲ ግን በፊቱ ፋሽን ሾ ሲሰሩ ቢውሉም ዘወር ብሎም አያያቸውም በርግጥም ትክክል ነው የፍቅር ጀግና የሚባለው መቶ ያሰለፈ ሳይሆ ከመቶዎቹ ላንዷ ብቻ መኖር ሲችል ነው መቅደስም ብትሆን ለማንም ቦታ የላትም ግን አንዳንድ ሰዎች 7ግርም ይሉኛል ወድቆ እያዩት አይጠቅምም ብለው ያላነሱት ነገር ሌላ ሰው አንስቶ ሲያዩ ለምን ቅጥል እርር እንደሚሉ አይገባኝም...... ጌዲዮ ካፌ ቁጭ ብሎ ሻይ እየጠጣ መቅደስ ከክፍል እስክትወጣ እየጠበቃት ነው አንዲትም ልጅ መጥታ አጠገቡ ተቀመጠች ጌዲዮም ይቅርታ የኔ እህት ወንበሩ ተይዟል አላት እሷም በተሞላቀቀ አፏ እኔ ሰው አይደለሁ ስትለው እንደዛ ማለቴ ሳይሆን ፍቅረኛዬን እየጠበኳት ነው ስለዚህ ቦታ ቀይሪ ብሎ ሳይጨርስ ምን መቅደስን አይደል ሶ እኔ ከሷ በላይ ፍቅርን ልሰጥህ ዝግጁ ነኝ ብላ ጠረንቤዛው ላይ ያረፉትን እጆቹን ጭብጥ አርጋ ያዘችው መቅደስም እየመጣች ስለነበረ ፊትለፊት እያየቻት ነበር ጌዲዮ እጇን ከጁ አመናጭቆ አስለቀቃት በጥፊ ሳልልሽ ተነስተሽ ከፊቴ ጥፊ ብሎ ሲጮህባት ደንግጣ እየበረረች ሄደች መቅደስ ፊቷ በደስታ ተሞልቶ በፈገግታ ታጀበ እንደደረሰችም አቅፋ ሳመችውና ተቀመጠች ........ .........ጌዲዬ ዛሬ ላይብረሪ እናጥና ድብርብር ብሎኛል አለች መቅዲ ከደበረሽ ለምን ቤተ ክርስቲያን ደርሰን አንመጣም አላት መቅደስም ደስ ይለኛል ነጠላዬን ላምጣና እኔዳለን አለችው። ከግቢም ሲወጡ ዮናስ አያቸው ወዲያው ወይንሸት ጋር ደውሎ ጠራት ከዛም ይዟት ወጣ እሷም ዮኒ ምን ፈልገክ ነው እዚሁ ንገረኝ ካንድ ሰአት ቡሀላ መቅደስ አስጠናችኋለሁ ብላናለች ስትለው ዮናስ ዶማ አጠና አላጠና ያው ዶማ እኮ ነው አላት ወይንሸት ንቀቱ አናደዳት ውስጧ ገብቶ ነዘራት መልሳ ዶማ እያልከኝ ነው አለች እሱም ገብቶሻል አታድርቂኝ ሲላት አሁን ትርፍ ማውራትህን አቁመህ ምን እንደፈለክ ንገረኝ አለችው እሱም ቀለል አርጎ ወደማታ መቅደስን እኔ ጋር እንድታመጪያት ነው አላት ወይናም ዮናስ ውላችንን የጨረስን መሰለኝ የተሰጠኝን ግዳጅ ባግባቡ ተወጥቻለሁ ውርርዱን የተሸነፍከው በራስህ ድክመት ነው ታዲያ ምን ችግር አለው አዲስ ውል እንዋዋል ገንዘብም ቢሆን ከባለፈው በላይ እከፍልሻለሁ ሲላት ወይና ፊቷን አኮሳትራ ......በቃኝ ዮናስ በቃኝ አልፈልግም አለችው እሱም ምኑ ነው የበቃሽ አላት በቃ ከዚህ ቡሀላ ካንተ ጋር መስራት አልፈልግም አለችው እሱም እየቀለድሽ መሆን አለበት ዮናስ እየቀለድኩ አይደለም በሀጢያት መጨማለቅ መሮኛል አይገርምህም መቅደስን እስከዛሬ የበደልኳት እየቆጨኝ ነው ደግሜ ሌላ ስተት መስራት አልፈልግም አለችው ወይንሸት የተቀየረችበትም ምክንያት ትላንትና ተደውሎላት አባቷ በጣም እንደታመመ ሲነግሯት ስታለቅስ መቅደስ አየቻት ምን እንደሆነችም ስጠይቃት አባቷ መታመሙን ነገረቻት መቅደስም በየዋህ ልቧ አብራት እያለቀሰች እግዚአብሔር ይረዳቸዋል ደግሞ አንቺን የመሰለ መልካም ልጅ አላቸው አይደል አይዞሽ ፀልዪ እኔም እፀልይልሻለሁ ብላ ስታፅናናት በደሏ ተሰማት ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ውስጧ ሲረበሽ ነበር ለዚያም ነው ዛሬ ለዮናስ ገንዘብ አልፈልግም ያለችው ዮናስ ግን............ መቼም ጨክነሽ ባባትሽ ነብስ አትፈርጂም ሲላት ስማኝ ይኸው ካይስኩል ጀምሮ በነውር በሀጢያት በምሰበስበው ገንዘብ አሳከምኩት ግን ዳነ አልዳነም አየህ እግዚአብሔር ካላለ እኔ ስላልኩ ወይም ማንም ስላለ አባቴ አይሞትም ደግሞ ቆሽሼ ከማገኘው ገንዘብ ንፁ ፀሎቴ ይሻለኛል መቼም ከዚህ ቡሀላ ወደኋላ አትመልሰኝም መቅደስ ጥሩና ደስ የሚል ስሜት ውስጥ ነው ያለችው ደግሜ ልበጠብጣት አልፈልግም ደግሞ የማላቅ አይምሰልህ ሆን ብለክ አንድ ዩኒቨርሲቲ እንዲደርሰን የጣ ድልድሉ ውስጥ እጅህን ያስገባኸው እኔ ካንተ ከማገኘው ጥቅም በላይ አንተ ከኔ የምታገኘው ጥቅም ስለሚበልጥ ነው ለፍቅር ብቀርብህም አንተ ግን ከየትም እንደተገኘ ገላ ተጫወትክብኝ መጫወትክም ሳያንስ አሳልፈህ ለሹገር ዳዲዎች ሸጥከኝ እኔ ከማገኘው መቶ ፕርሰንት ዘጠናውን አንተ እንደምትወስድ አውቃለሁ ግን አስሯ ፕርሰንት ላባቴ መኖር ምክንያት ስለመሰለችኝ የከተትከኝ ሀጢያት ውስጥ እንደተስማማኝ ሆኜ ኖርኩኝ በርግጥ የኔን ትክክለኛ ማንነት ማንም አያውቅም ግን ይሁን እስከዛሬ ያልሆንኩትን ሆኜ ብኖርም የኖርኩትም ላባቴ ቢሆንም ባርቴፊሻል ማንነቴ አባቴ ድኖ ከሚያዝንብኝ በትክክለኛው ማንነቴ የሆነውን ቢሆንም ወይና አባቷን እጅግ ከሚባለው በላይ ስለምትወደው እንባዋ እንደጎርፍ ወረደ ዮናስም እንዳመረረች ሲረዳ ኦኬ እንደዛ ከሆነ መቅደስ ላይ ያረግሽውን ሁሉ አንድም ሳይቀረኝ እነግራታለሁ ይህ ወሬ ተማሪዎች አወቁ ማለት ሳምንት እንኳን እዚህ ግቢ አትማሪም እኔን እንደሆነ አንዴ ጠልታኛለች የሆነው ቢሆን ማንም ከቁብ አይቆጥረኝም አንቺን ግን ሲላት ሰውነቷን ድንጋጤ ወረረው ዮናስ አታደርገውም አለችው ከት ብሎ ሳቀባት ዮናስ እኮ ነኝ ጭካኔዬን ያኔ ካይስኩል ጀምሮ ከማንም በላይ ታውቂዋለሽ አላት ወይንሸት ከመስማማት ውጪ አማራጭ አልነበራትም እሺ ግን እንዴት ብዬ ለፍቅር ከመጠየቅክ በላይ ደጋግመክ ጌዲዮን እንድትጠላው ለማድረግ በመሞከርክ ላይኗ እንኳን ጠልታሀለች ታዲያ የት ምን ብዬ ነው የማመጣት አለችው ለሱ አታስቢ ወክ እናርግ ብለሽ ውስጥ ውስጡን ትወስጂያታለሽ ከዛም እላይኛው ጫካ ጋር ስትደርሱ ሁለታችሁም የታፈናችሁ አስመስለን አንቺን በጎን ይወስዱሻል እሷ እጄ ትገባለች #ክፍል 17 ይቀጥላል!👍ከወደዱት ሼር!👍👍👍👍 @abrshi12onto
Показати все...
።።።።፡።፡።።።።።ትርታዬ።።።።።።።።።።። ።።።።።።።።።።ክፍል 15።።።።።።።።።። ጌዲዮ እንደምንም እንባውን ጠራርጎ ታሪኩን ቀጠለላት አየሽ እኔን ማንም ከሰው ተራ ቆጥሮኝ ስላላደኩ ዛሬም ሰው እፈራለሁ ብቸኝነቴን እመርጣለሁ ዝምታዬን እወደዋለሁ ለኔ የመኖር ምክንያቴ እናቴ ናት እሷ ናት ታሪኬ እንዳባት ሞፈር ተሸክማ እንደህት መክራ እንደወንድም ጋሻ ሆናኝ ከናት በላይ ብዙ ሆና ያኖረችኝ ታሪኬ እናቴ ብቻናት አየሽ መቅደስ አንቺ እኔን ከመደገፍሽ በፊት ከናቴ በቀር ማንም ጎንበስ ብሎ አንስትትምኝ አያውቅም ለዚም ነው አንቺን እንደናቴ ያየሁሽ አላት ሳያውቀው ለሷ ያለውን ስሜት ነገራት መቅደስ እጆቿን ከጉንጩ ሰዳ እንባዉን ጠረገችለት ለብዙ ጊዜ ፍቅራቸውን እንዴት መግለፅ እንዳለባቸው ሲጨነቁ የነበሩት ጥንዶች ዛሬ ያለማንም ጣልቃ ገብነት አንድ ሜዳ ላይ ተገናኙ በርግጥም እውነተኛ ፍቅር የቃላት ድርደራ አይፈልግም ለካ እውነተኛ ፍቅር ባይን ጥቅሻ ብቻ ያግባባል በቃ በዝምታ ተያዩ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌዲዮ ከንፈሩን ከሴት ከንፈር አገናኘው መቅደስ ለብዙ ጊዜ የናፈቀችውን ጌዲን በቅፎቿ አስገባችው በቃ ያለምንም አፈቅርሀለሁ አፈቅርሻለሁ ያለማንም አጃቢ በከንፈራቸው ቃልኪዳን አሰሩ የፍቅር ድግሳቸው ትተጠነሰሰ ማንም ባይገምትም የጌዲዮና የመቅደስ ፍቅር እውን ሆነ የዛኑ ቀን ነበር ግቢው ይህን እውነት የሰማው ዮናስ ጌሙን ባደባባይ ተሸነፈ መቅደስ ከሱ ቁንጅና ይልቅ የጌዲዮ መልካምነት አሸነፋት ከዮናስ ማስመሰል የጌዲዮ ፍቅር በለጠባት የውጭ ማንነቱን ሳይሆን በውስጥ መልካም ስብእናው ባደባባይ የጌዲዮ ነኝ አለች ዮናስ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ አይነት ጌም ሲሸነፍ ከፍተኛ ገንዘብና እሱ የሚያምንበትን ክብሩን አጣ የመጨረሻ እርምጃ ያለውን በቀል በውስጡ አበቀለ በክፋትም ሊጥላት አሰበ ጌዲና መቅዲ ግን ግቢውን ያስቀና ፍቅር ጀመሩ አይቶ ካይን ያውጣችሁ የማይል ምቀኛ ብቻ ነው በፍቅራቸው አልተደነኩም የሚል ካለ ውሸታም ነው.......... ክፍል 16 ይቀጥላል @abrshi12onto
Показати все...
።።።።።።።።።።።ትርታዬ።።።።።።።።።።። ።።።።።።።።።፡ክፍል 14።።።።።።።።።።፡ .......መቅደስም የመሄጃዋ ሰአት ደረሰ ወይንሸትም እንዴ መቅዲ አትቀባቢም እንዴ ዮናስ ጋር እኮ ነው የምትሄጂው ያውም እራት አለቻት ባክሽ ብዙም ደስተኛ አይደለሁ እንደውም እሱ ሆኖብኝ ነው እንጂ አልሄድም ነበረ አለቻት ወይንሸትም ቢሆንም አንዴ ተስማምተሻል ዝንጥ ብለሽ ነው መሄድ ያለብሽ ስለዚ አሁን ይሄንን ልበሺ ይሄንን ተቀቢ እያለች ያለውድ በግዷ ውበቷ ጎልቶ እንዲታይ አረገቻት ከዛም ተሰናብታቸው ስትሄድ ወይንሸት ወዲያው ተከትላት ወጥታ ጌዲዮን በሌላ ተማሪ አስጠራችውና ደብዳቤ ሰጠችው። ........እሱም ከፍቶ ሲያነበው ስማ አንተ በሽተኛ ነግሬህ ነበረ መቅደስ የኔ ናት ለማንኛውም እንድታምነኝ ስል ዛሬ ምሽት የፍቅር ጥያቄ አቀርብላታለሁ ከቻልክ መጥተክ መታደም ትችላለህ ዮናስ ይላል እሱም ወሬኛ ብሎ ደብዳቤውን ቀደደና ወደዶርም ሊመለስ ሲል መቅደስን በዛ በጨለማ ንግስት መስላ ከግቢ ስትወጣ ከሩቅ አያት ጌዲዮ ማመን አቃተው ባይፈልግም ፍቅር ነውና ተከትሎ መጨረሻቸውን ሊያይ ከኋላዋ ተከተላት......... .........መቅደስ ባላት ሰአት ሆቴሉ ገባች ባይኗም ብዙ ወንበሮች ላይ ፈለገችው የለም ከዛም አንድ ወንበር ይዛ ተቀመጠች አስተናጋጅ ፊትለፊቷ መጥቶ ምን ልታዘዝ አላት እሷም ሰው እጠብቃለሁ የሚል መልስ ሰጠችው ከቆይታዎች ቡሀላ ሌላ አስተናጋጅ መጣችና መቅደስ አለቻት እሷም አዎ ነኝ ኦኬ ተከተይኝ አለቻት መቅደስም ግራ በመጋባት ወዴት ስትላት ዮናስ የተባለ ደንበኛችን ነው ይዘሻት ነይ ያለኝ አለቻት እሺ ብላ ተከተለቻት ሁለተኛ ፎቅም እንደደረሱ ስለደረስን አይንሽን ላስርሽ ነው አለቻት መቅደስ ይበልጥ ግራ በመጋባት እኮ ለምን ስትል አርጊ የተባልኩትን ነው ብላ አይኖቿን አስራ ግን ግለጭ ሳትባይ ምንም እንዳታዪ አደራ ብላት የፎቁ በረንዳ ላይ አድርሳት ተመለሰች ዮናስም ከጥቂት ደቂቃ ቡሀላ ግለጪ አላት መቅደስ የታሰረችበትን ጨርቅ ካይኖቿ ስታነሳ የምታየው ነገር ህልም መሰላት አበባ ተጎዝጉዞ ምሽቱ በሻማዎች ደምቆ አለ የተባለ መጠጥ ቀርቦ ዮናስ አንዲት ቀይ ፅጌሬዳ ይዞ ፊቷ ተንበርክኳል .......በዛ ሰአት ጌዲዮ ዝብርቅርቅ ባለ ስሜት ውስጥ ህኖም እያያቸው ነበር..... መቅደስ ግራ ገባት ላንድም ቀን ዮናስን በዚህ መልኩ አስባው አታውቅም ዮናስ ምን እየሆንክ ነው አለችው እሱም ክሽን አድርጎ በሚያወራት አስመሳይ ግን ጣፋጭ በሆነ አንደበቱ መቅዲ ካየሁሽ ቀን ጀምሮ አፍቅሬሻለሁ የልቤ እመቤት አድርጌ ሾሜሻለሁ መቅዲ አንቺ ከማንም በላይ ለኔ ልዩ ነሽ እስከ ሂወቴ ፍፃሜ ያንቺ ብቻ ልሁን ፍቀጂልኝና የፍቅርሽ ባሪያ ልሁን አያለለ ዜማ ቢጨመርበት አንድ ክሊፕ የሚሰራውን ዜማውን አፈሰሰባት ከዛም መቅደስ ምን እንደምትል እንኳን ግራ ገብቷት እየውልክ ዮናስ ይሄን ላረግ አልችልም ብላ ከተንበረከከበት እጆቹን ይዛ አስነሳችው ዮናስ ደሙ ፈላ ግን ለምን አላት እየውልክ እኔ የኔ የምለው የማፈቅረው ሰው አለኝ አንተን ወንድሜ እንጂ ፍቅረኛዬ ላደርግህ አልችልም ዮኒ የእውነት በጣም አዝናለሁ እኔ ያንተ ልሆን አልችልም በቃ ውለታውን በዚ መልኩ ልትከፍለው እንደማትችል ነግራ በጣም አስተዛዝናው ተመልሳ ሄደች ልክ እሷ እንደተመለሰች ጌዲዮ ፊትለፊቱ ሄደና ስማ መቅደስን እንኳን በውንህ በህልምህም የግልክ አታደርጋትም የእውነት ግን በራሴ አፈርኩ አንተን አምኜ እዚህ ድረስ መልፋት አልነበረብኝም ይህንን ትርኪ ሚርኪህን በለመድካቸው ላይ ግን ለዚህ ሁሉ ወጪ ስንት ብር ፈጀብህ እያለ የዮናስን ንዴት በእጥፍ ጨምሮ ሄደ ዮናስ መጠጡን እየገለበጠ በፍቅር እንቢ ካልሽ የበቀል ልቡን አሳበጠው........ ...........ከዛም በንጋታው ጌዲዮና መቅደስ ተያይዘው ለጥናት ወደጫካው ሄዱ አጥንተውም እንደጨረሱ ታሪኩ እንዲነግራት አስገደደችው እሱም .....እኔ ምንም ሌላ ታሪክ የለኝም ታሪኬ አንድ ግን ብዙዋ እናቴ ናት ተወልጄ ያደኩት በደቡብ ወሎ ወረኢሉ ጃማ የሚባለው ገጠራማ ስፍራ ነው አባቴን አላውቀውም በልጅነቴ ነው የሞተው ከኔ በፊት እናቴ ሶስት ልጆች ሞተውባታል እኔንም ስለት ተስላ ነው ያደኩላት ግን ባድግም የአራት አመት ልጅ እያለሁ በየቦታው ይጥለኝ ጀመር እማ በሀዘን ላይ ሀዘን ተጨመረባት አስበሽዋል ሶስት ልጆቿን ባሏን ያጣች ሴት መከራ በዛላይ እኔም በሽተኛ መሆኔ አላፊው አግዳሚው አላስቀምጥ አላት ያባቴ ዘመዶችማ ለነገሩ እሷ ስላለችኝ እንጂ እንኳን ያባቴን የራሷንም ዘመዶች አላቃቸውም ምክንያቱም የሷ ቤተሰቦች እንድታገባ ሲለምኗት አሻፈረኝ ካገባሁ ልጄ ይጎዳብኛል ስላለች እስከዛሬ ድረስ ማንም የሚፈልጋት የሚጠይቃት የለም አየሽ እናቴ ለኔ ስትል ስንት ነገር እንዳጣች አባ ሲሞት ቆንጆ ወጣት ነበረች ብታገባ ኖሮ እንደ ወንድ ሞፈርና ቀንበር አንዴ ከጓሮ አንዴ ከጓዳ ባልተንከራተተች ነበር ግን ለኔ ስትል ሁለት መልክ አወጣች መከራ ትንሽ ነው ብዙ ብዙ ነገር አየች እኔ እናቴ የማስደስታት ቀንበር ይዤ ስከተላት አልነበረም ጓሮ ሄጄ ስቆፍር እንጨት ስሰብርላት አይደለም እውነተኛው የናቴ ደስታ ደብተር እስኪቢርቶዬን አንግቤ ለትምርት ስወጣ ነው ብዙ ጊዜ ትምርት አልማርም እላታለሁ እሷ ግን ምክንያቴን ስለምታውቅ ሰምቶ እንዳልሰማ አይቶም እንዳላየ ሁን ትለኛለች እዚህ ለመድረሴ የናቴ ትልቁ ምክሯ ይህ ነበር የልጆች ጨዋታን እየተጫወትኩ ሳይሆን እያየሁ እየዘመርኩ ሳይሆን እየሰማሁ ነው ያደኩት ማንም ልጅ ከኔ መጫወት ቢፈልግ እንኳን አይችልም ምክንያቱም የትኛውም እናት አባት አይፈቅድም መቅዲ እኔኮ ከሰው ጋር ስሆን አይደለም የሚያመኝ ግን ማንም አይረዳኝም ብሎ ለብዙ ግዜ ያመቀው ቁስል ስለሆነ ዛሬ ግን ፈነዳና አመመው ሳይጨርስላት እንባው ቀደመው አስተዳደጉ በሙላ አይኑ ላይ ተስሎ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ መቅደስም አንጀቷን በልቶት አብራው አለቀሰች.......... ️ ይቀጥላል......👍 Share ማድረግ አይረሳ t.me/abrshi12onto
Показати все...
ስለ አለም በግጥም

በዚህ ቻናል የማይነሳ ሀሳብ የለም በግጥም መልክ።።።።።።። ስለ ፍቅር ናፍቆት ስለሀገር እማይፃፍ የለም ቅሬታ ወይም አስተያየት ካላችሁ @abrshi12on ቴሌ ግራም ላይ ይስጡን

።።።።።።።።።።።ትርታዬ።።።።።።።።።።። ።።።።።።።።።።ክፍል 13።።።።።።።።።። .......ብርሀን መቅደስን እንኳን አንቺ ጌዲዮ ቢያስጠናትም አይገባትም ስትል መቅደስ አይምሮዋ ላይ አንድ ሀሳብ መጣላት ብርሀንና ወይንሸት ሲጣሉም መልስ አልሰጠቻቸውም እስካሁን ከጌዲዮ ጋር አብሮ ለመሆን ብዙ ተጨንቃለች ከዛም በውስጧ አዎ አስጠናኝ ብለው መቼም ጨክኖ እንቢ አይለኝም አው እለዋለሁ እያለች ሳታስበው ፊቷ በፈገግታ ተሞላ ለምን ብሎ የጠየቃትም የለም ምክንያቱም በሁለቱ ፀብ እየተገረመች መሰላቸው። ...............በንጋታውም ልጠይቀው ከክፍል እስኪወጣ ምንገድ ላይ ጠበቀችው ከዛም ሁሉም ተማሪ ወቶ ሲያልቅ መጨረሻ ላይ አቀርቅሮ መጣ መቅደስ ምን እንደምትለው እየተለማመደች ነበር ግን እሱን ስታየው ሁሉም ጠፋባት እንደደረሰም አያትና ሰላም ሊላት ተጠጋ እሷ ግን ደንግጣ ስለነበረ አንደበቷ ተያይዞ እጇ እየተንቀጠቀጠ ለሰላምታ መዘርጋት አቃተው ጌዲዮም ምን ሆነሽ ነው አላት እሷም በመጠየቅና ባለመጠየቅ መሀል ሆና አይ ምንም ስትለው የሆንሽውማ ነገር አለ ለምን አትነግሪኝም አላት እሷም እእእ ጎበዝ ተማሪ አይደለክ አለችው እሱም ማለት አላት ማለትማ የፈተና ዝግጅት ስለከበደኝ እንድታስጠናኝ ነው አለችው ቁና እየተነፈሰች ጌዲዮም እንዴ እኔ አንቺን ቀለሜ አይደለሽ እንዴ አላት መቅደስም ካልተመቸህ ችግር የለውም ስትለው አረ ለዛ አይደለም ማንም አስጠናኝ ብሎኝ ስለማያቅ ገርመሽኝ ነው እንጂ ማስጠናቱን አለመፈለግ አይደለም ደስ ካለሽ ከትምህርት ሰአቴ ውጪ ማጥናት ስትፈልጊ ሁሌም ጥሪኝ ይመቸኛል አላት ጥያቄዋን በፍጥነት ስለተቀበላት መቅደስ ደስ አላት።............... .........ይሄኔ ዮናስ ካፌ ቁጭ ብሎ እያያቸው ነበር በሚያየው ነገር ተበሳጨ የውርርዱ የመጨረሻ ወር ላይ ነው ያለው ግን ይበልጥ ያሳሰበው የውርርዱን ብር ማጣቱ ሳይሆን በማንም ተሸንፎ የማያውቀው ዮናስ ባንድ ሴት ክብሩ ሲነካ መሸነፉን ግቢው ሲያወራ ገና ካሁኑ ታይቶት ነው ከዛም የፍቅር ጥያቄ ሊያቀርብላት አሰበ። ................ጌዲም መቅደስን ይዟት ላይብረሪ ገቡና መፃህፍትን ይዘው ወጡ ከዛም ቀጥታ ወደጫካ ሄዱ እዛም አጥንተው ለነገሩ ምን አጥንተው እሱ ለፈለፈ እንጂ መቅደስ አንዱንም አልሰማችውን ከዛም እንደጨረሱ እንሂድ ሲላት አይ ለምን ትንሽ አንጫወትም ቦታው ደስ ይላል አለችው ደስ ካለሽ እሺ አላት ጌዲዮ ከማንም ጋር አፍ ለአፍ ገጥሞ አውርቶ ስለማያውቅ በመሀከላቸው ዝምታ ሰፈነ ከዛም መቅደስ እኔ እምለው እስኪ ታሪክህን አጫውተኝ ብላ ጠየቀችው እሱም መጀመሪያ አንቺ ንገሪኝና እነግርሻለሁ አላት ትንሽ አንገራግራ ቀጠለች....... ......ተወልጄ ያደኩት አ.አ ለገሀር የሚባለው ሰፈር ነው የልጅነት ጊዜዬ እንደማንኛውም ህፃን ደስ የሚል ነበረ ሁለት ወንድምና አንድ እህት አሉኝ የቤታችን የመጨረሻ ልጅ እኔ ነኝ ሁሉም ታላቆቼ ናቸው አባቴ የአ.አ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነው እናቴ ደግሞ ከፍተኛ የመንግስት ቢሮ ነው የምትሰራው ሁለቱም የተዋወቁት አባዬ መምህር እማዬ ተማሪ ሆነው ነበር አሁን ላይ ጥሩና ስኬታማ ቤተሰብ አለን ሁሉም ወንድምና እህቴ የማዕረግ ተመራቂ ናቸው እኔም ጠንካራ እንድሆን ዘውትር ያበረታቱኛል እንደውም የውጪ እድል መቶልኝ አልፈልግም ብዬ ነው ዛሬ ላይ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ትምህርቴን የምማረው ምክንያቱም ሳይማር ያስተማረኝን ህብረተሰብ እኔም ወግ ደርሶኝ ማገልገል እፈልጋለሁ ይህንን ሳደርግ ከቤት አንድም ተቃዋሚ አልገጠመኝም በቃ ይኸው አሁንም እየተማርኩ ነው እልሀለሁ አለችው ጌዲዮም ዋዉ የሚያስቀና ቤተሰብ ውስጥ ነው የበቀልሽው አላት መቅደስም አመሰግናለሁ ስትለው አረ ምንም አይደል ደግሞ ተምረሽ አንቺም ጥሩ ቦታ እንደምትደርሺ አልጠራጠርም አላት ................ . .........ከዛም የሱን እንዲነግራት ስጠይቀው ነገ ዲያሪውን አገላብጦ መጥቶ እንደሚነግራት ቃል ገብቶላት ተነስተው ወደግቢ ተመለሱ ......... ልክ እንደተለያዩም ዮናስ አስቆማት እሷም ሰላም ካለችው ቡሀላ በጣም ለጥብቅ ጉዳይ እፈልግሻለሁ አላት እሷም ምን እንደሆነ ስጠይቀው ማታ እራት እየበላን እነግርሻለሁ ብሎ ትልቅ ሆቴል ከምሽቱ ሁለት ሰአት እንድትመጣ ጋበዛት በፍፁም እንዳትቀርም አስጠነቀቃት እሷም የማትረሳው ውለታው አስገድዷት ውስጧ ቢደነግጥም ፍቃደኛ ሆነች ክፊል 14 ይቀጥላል..... t.me/abrshi12onto
Показати все...
ስለ አለም በግጥም

በዚህ ቻናል የማይነሳ ሀሳብ የለም በግጥም መልክ።።።።።።። ስለ ፍቅር ናፍቆት ስለሀገር እማይፃፍ የለም ቅሬታ ወይም አስተያየት ካላችሁ @abrshi12on ቴሌ ግራም ላይ ይስጡን

👍 3
ውስጤ የታመቁት መግለፅ ያልቻልኩት ቃላት አሉ፤ የደበኩት ስሜት፣ ያላነበብሻቸው መስመሮች …. አንዳንዴ ቅርበትሽ የስትንፋሴን ያህል ቅርብ ሊሆን ይችላል፡፡ ልናገር የምፈልገው ሁሉም ነገር ድምጽ አልባ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ሲሆን በጸጥታ አይኔ የልቤን እንዲናገርልኝ እመኛለሁ ታውቂያለሽ... እያልክ ማውራቱ አይደለም ለሷ ትርጉም የሚሠጣት። እራስህን መለወጥህ እና ማሻሻልህ እንጂ። የአይምሮህ ከፍታ እና የህይወትህ ደረጃ ነው የሚገዛት። ንግግር መቻልህ ሳይሆን እራስን ማሻሻልህ ነው የሚማርካት። ዋናው ምላስ ነው ለሚሉት መታሰቢያ ይሁንልኝ🙏🙏🙏
Показати все...
።።።።።።።።።።።ትርታዬ።።።።።።።።።።። ።።።።።።።።።።ክፍል 12።።።።።።።።።። መቅደስ ምንም እንኳ ከጌዲዮ ፍቅር ባትጀምርም አሁን ካይኗ ስር በመሆኑ ደስታዋ ተመልሷል ጌዲዮም እንደዛው...... .......አሁን ወሩ የፈተና ነው ጎበዝ ተማሪዎች በጥናት ተጠምደዋል እንደወይንሸት ያሉት ደግሞ እንዴት አስተማሪዎቻቸውን ማማለል እንዳለባቸው ብቻ ሁሉም በየፊናው እየተዘጋጁ ነው። ...............ጌዲዮም እንደለመደው ጫካ በመሄድ ማጥናቱን ተያይዞታል በነገራችን ላይ መቅደስ አሁንም ሳያያት ትከተለዋለች እናም ዛሬም ሳያያት ከኋላ ኋላው ሄዳ ከቅርብ እርቀት ሆና እያየችው ነው ግን ይህን የምታደርገው አንድ ቀን በህልሟ ጫካ ውስጥ ወድቆ አውሬዎች ሊበሉት ሲሉ በላብ ተጠምቃ ከንቅልፏ ባና ከዛ ወዲ እውን እንዳይሆን እየፈራች ከግቢ ሲወጣ አብራው ትወጣለች............ ........እናም ብዙ ቆየ በተስፋ ስትጠባበቀው ቆይታ የሆነ ሰአት ላይ በጫካው የጦጣዎች ትርኢት ተመለከተች ከዛም ቀልቧን ሳቡት ከዛፍ ዛፍ ሲዘሉ ሲቦርቁ ስታይ ለግዜው ጌዲን ለጥናቱ ተወችው ከዛም ስልኳን አውጥታ መቅረፅ ጀመረች ጌዲዮ በዛን ሰአት ጥናቱን ጨርሶ መፅሀፎቹን ሰብስቦ ተነሳ ተነስቶ እንደዞረም መቅደስን አያት ብታየው በተደበቀች ነበር ግን አላየችውም በጦጣዎቹ ሁኔታ እየሳቀች ካሜራዋን ደቅና እየቀረፀች ነው ጌዲዮ የልቡን ጀግና በተመስጦ እያደነቀ ለደቂቃዎች ሲያያት ቆይቶ ፊትለፊቷ ሄደ ከዛም እረጋ ባለ ድምፅ መቅዲ አላት መቅደስ በድንጋጤ ጮሀ አውቃ ፌንት እንደነቀለ ሰው እጁ ላይ ወደቀች እሱም እውነቷን መስሎት ሊያነቃት ብዙ ጣረ ከዛም የያዘውን ሀይላንድ ውሀ እላይዋ ላይ ደፋው ሆን ብላ እያለከለከች ነቃች ................እሱም ምነው ምን ሆንሽ አላት እሷም እንዴ አስደነገጥከኝ እኮ አለችው በርግጥ ከሚባለው በላይ ደንግጣለች ከዛም እንደማያቅ ሆና ቆይ እዚህ ምን ታደርጋለህ አለችው ጌዲም እኔማ በብዛት እዚህ ነው የማጠናው ይልቅ አንቺ እዚህ አስፈሪ ጫካ ብቻሽን ምን ታደርጊያለሽ አላት መቅደስም አምጣ አምጣ ምን መሰለህ የሆነ የፎቶ ኤግዚቢሽን አለብኝ እናም ለዛ ነው ስትለው ተቆጣት እንዴ ቢሆንስ ቢያንስ ከጓደኞችሽ ጋር አትመጪም ቆይ እኔ እንዳገኘሁሽ አውሬ ቢያጋጥምሽስ በሁኔታው ደስ አላት በርግጥ ማንም ቢሆን የሚያፈቅረው ሰው ሲጨነቅለት ያስደስተዋል መቅደስም ያ ደስታ ነው የተሰማት ቀጥላም እሱን ጠየቀችው እሱም ከልጅነቱ ጀምሮ የለመደው እንደሆነ ነግሯት መንገድ ጀመሩ መቅደስም ልክ እንዳዲስ ሰው መወለጋገድ ጀመረች ጭራሽ መሄድ ያቃታትም መሰለች ጌዲዮ በጆቹ ደገፋት እሷም ይህንን ስለነበር የፈለገችው ፈገግ አለች ግቢም ሲገቡ እንደደገፋት ነበር ነገሩ ብዙውን ተማሪ አስገርሟል። .......ዶርም ስትገባ እነ ሰአዳ ቆይ አብረን እናጠናለን ተባብለን የለም እንዴ ምነው ቆየሽ አሏት እሷም ከነሱ ምንም ስለማትደብቅ ነገረቻቸው ከዛም ጥናት ጀመሩ ወይንሸት ግን ማጥናት አልፈለገችም ቢሆንም መቅደስ በግድ ያዘቻት ከዛም በጋራ የሚያጠኑትን ሲጨርሱ በግል እንዲሰሩ ጥያቄ ሰጠቻቸውና ወይንሸትን ብቻዋን ማስጠናት ጀመረች ግን ምንም ሊገባት አልቻለም ሀሳቧ ሁሉ አብሯት የለም መቅደስ ተበሳጨች ብርሀን በሁኔታቸው እየሳቀች መቅዲ አትልፊ ወይንሸትን እኮ እንኳን አንቺ ጌዲዮ ቢያስጠናትም አይገባትም ስትል ወይንሸት በንዴት ትራስ ወረወረችባት። .......መቅደስ ብርሀን እንደዛ ስትል አንድ ሀሳብ መጣላት........... #ክፍል 13 ይቀጥላል👍 t.me/abrshi12onto
Показати все...
ስለ አለም በግጥም

በዚህ ቻናል የማይነሳ ሀሳብ የለም በግጥም መልክ።።።።።።። ስለ ፍቅር ናፍቆት ስለሀገር እማይፃፍ የለም ቅሬታ ወይም አስተያየት ካላችሁ @abrshi12on ቴሌ ግራም ላይ ይስጡን

👍 5
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.