cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

⛪️የተዋህዶ ልጆች⛪️

"እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር "

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
169
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

>>>>> የሰማዩ መንገደኛ <<<< የአመነ ሰው ከክርስቶስ ዙፋን የሰማያዊውን ደጅ በንሰሃ ለመምታት የምትሄድባቸው አምስቱ የንሰሃ መንገዶች፦ (1) ሀጢያትን ማሰብ የመጀመሪያው መንገድ የሰራነውን ሀጢያትን ማሰብ/ማሰላሰል/፡፡ ሀጥያተኛነትህን የምታስበው እና የምታሳስበው ከሆነ እግዚአብሔር ይቅር ሊልህ ታማኝ ነው። ሀጥያተኛነትህን ስታስበው ደግመህ አትበድልም። ህሊናህ ሲከስህ መንፈስ ቅዱስ ሲወቅስህ እንጂ በጌታ ዙፋን ፊት ሌላ አካል እስኪከስህ አትጠብቅ። "እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።" (መዝሙር 51:3) (2) የሌሎችን ጥፋት መርሳት ሁለተኛው መንገድ ንሰሃ ከመግባትህ በፊት የሌሎችን በደል ይቅር በላቸው። ይህም ስሜትን መቆጣጠር እና ሌሎች ሰዎች በአንተ ላይ ያደረጉትን ሀጢያት ይቅር ማለት አለብህ። ሌሎችን ይቅር ስትል ጌታ ይቅር ይልሃል። "ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅርብለናልና፤" (የሉቃስ ወንጌል 11:4  ) (3) ፀሎት ፀሎት ሶስተኛው መንገድ ሲሆን። ይቅር ይለኛል ብለህ አምነህ በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክከህ ስለሀጢያትህ ፀልይ እርሱንም እጠበኝ ቆሽሻለሁ፣ አንፃኝ ከበረዶ ይልቅ ነጭ እሆናለሁ በለው። መለወጥ እና በሰውና በአንተ ፊት ቅዱስ ሆኜ እንድኖር መንፈስህ ይቆጣጠረኝ በለው። ስትጨርስም ስለምህረቱ የምስጋናን ፀሎት አምጣ። "በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ። ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል። ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ። አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ!" (መዝሙር 51:7-10) (4) ደግነት መንገድ አራት ምህረትና ፍቅሩን ለመለመን በፊቱ ስትቆም ከሚሰጥና ደግ በሆነ ልብ ይሁን። ደግነትህ ብዙ እንድትቀበል ያደርግሃል። መካስ ባትችልም እንደ ካሳ ግን የተቀበልከውን ፍቅር ለብዙ ስጠው። (5) ትህትና አምስተኛው መንገድ ትህትና ። በማስመሰል ሳይሆን በእውነት ትህትና የአንተ ክብር ምንም መልካምነት እንደሌለው እና ትከሻህ በሀጥያት ሸክም እንደጎበጠ በእግዚአብሔር ፊት ሁን። እግዚአብሔርም በምህረት ከባዱ ሸክምህን ከላይህ ላይ አራግፎ ሀጢያትህን በደሙ እያነፃ ፍቅሩን በልብህ ያሳዝልሃል። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" (ማቴዎስ 11:2) # የሰማዩ መንገደኛ ሆይ በየእለት ኑሮህ ብትችል በሁሉም ካልቻልክ ከነዚህ በአንዱ መንገድ ላይ ተጓዝ! ነገር ግን እንዳልቆምክ እና በየእለቱ እየተጓዝክ መሆንህን እርግጠኛ ሁን!! እግዚአብሔር ይርዳህ!! መልካም መንገድ!!!
Показати все...
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ +"+ +ባለንበት ዘመን አሳዛኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የቅዱሳኑ ስማቸው ከነሥራቸው መዘንጋቱ ነው:: ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ደማቸው እንዳልፈሰሰ: አጥንታቸውም እንዳልተከሰከሰ ይሔው አስታዋሽ አጥተው ስማቸውም ተዘንግቶ ይኖራል:: +አንዳንድ ንፉቃን ደግሞ ከዚሁ ብሶ ጭራሹኑ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስለ ክርስቶስ ትታ ስለ ቅዱሳኑ ብቻ ትሰብካለች ይሉናል:: +በእጅጉ ከሚያሳዝኑኝ ነገሮች አንዱ የቅዱሳን ሐዋርያት (የ120ው ቤተሰብ) መዘንጋት ነው:: ከ120ው ቤተሰብ የአብዛኞቹ ስም በመዘንጋቱ: ሊቃውንቱም ዝምታን በመምረጣቸው "ያሶን: አርስጦስ: አፍሮዲጡ: ቆሮስ . . . እያልን የ72ቱን አርድእት ስም ስንጠራ ግር የሚለው ዓይነት ትውልድ ተፈጥሯል:: +እስኪ እንዲያው ቢያንስ ሐዋርያትንና ዐበይት ቅዱሳንን እናስባቸው:: አስበናቸው የሚጨመረልን እንጂ የሚጨመርላቸው የለምና:: +ዛሬ የምናስበው ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው:: ጌታችንን ከጥምቀቱ በኋላ ተከትሎ ለ3 ዓመታት ከእግሩ ሥር ቁጭ ብሎ ተምሯል:: ከጌታችን ዕርገት በኋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል:: +ለብዙ ጊዜ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ተመላልሶ ሰብኳል:: በመከራውም ተካፍሎታል:: ታላላቆቹ ሐዋርያት ሰማዕትነትን ከተቀበሉ በኋላ ለመጣው አዲስ ክርስቲያን ትውልድ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በቃል የሰማውን አስተላልፏል:: +ወንጌልን ስለ ሰበከላቸው አሕዛብ ብዙ ጊዜ አስረው ይደበድቡት: ያንገላቱት ነበር:: አንዳንድ ጊዜም እሳት እያነደዱ ያቃጥሉት ነበር:: ፈጣሪው ግን በተአምራት እያዳነው ከርሱ ጋር አልተለየም:: +ከከተማ ወጥቶ በዱርና በእስር ቤቶች ብዙ ነፍሳትን: ሽፍቶችንም ሳይቀር ወደ ክርስትና ማርኳል:: ቅዱስ ያሶን ለረዥም ዓመታት ሰብኮ በመልካም ሽምግልና አርፏል:: ❖ ንግሥት ወለተ ማርያም ❖ +ዳግመኛ በዚህ ቀን ኢትዮዽያዊቷ እናታችን ቡርክት ወለተ ማርያም ትታሰባለች:: +ወለተ ማርያም ማለት የደጉ አፄ ናኦድ ሚስት: የአፄ ልብነ ድንግልና የቅድስት ሮማነ ወርቅ እናት ናት:: በንግስትነት በቆየችባቸው ዘመናት (ከ1487-1500 ዓ/ም) የረሃብ ጊዜ በመሆኑ ብዙ ሕዝብ አልቆ ነበር:: +ቡርክት ወለተ ማርያም ከጾምና ከጸሎት ባሻገር የተራቡትን በማብላት ብዙዎችን ታድጋለች:: የንጉሡን ቤተሰብ ወደ መልካም ክርስትና በመምራትም የተመሰገነች ነበረች:: በዚህ ቀንም አርፋ ተቀብራለች:: ❖አምላካችን ከቅዱሳኑ በረከት አይለየን:: ❖ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት አንዱ) 2.አባ ብሶይ ሰማዕት 3.ቅዱስ አውሳብዮስ ቀሲስ 4.ቡርክት ወለተ ማርያም ንግሥት (የዐፄ ልብነ ድንግል እናት) ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም 2፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3፡ ካህናት ዘካርያስ ወስምዖን 4፡ አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ 5፡ አባ ዜና ማርቆስ 6፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ 7፡ ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት 8፡ ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ ++"+ ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው ጌታ ሆይ! አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት:: እንዲህም አላቸው . . . እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችሁአለሁ:: የሚጐዳችሁም ምንም የለም:: ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ:: ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ:: +"+ (ሉቃ.10:17) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Показати все...
​​#የቤተክርስቲያንንዋየተቅድሣት #ታቦት 🔹ታቦት ማለት እግዚአብሔር አስርቱ ትዕዛዛትን በእጁ ፅፎ ያስቀመጠበትና ለሙሴ የሰጠው ቅዱስ ንዋይ ነው፡፡ 🔸በቤተክርስቲያንም ፃህሉን እና ፅዋውን በዚህ ላይ በማስቀመጥ መስዋዕቱን እናከብርበታለን፡፡ 🔹ይህም ማለት ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ የሚዘጋጀው በዚህ ላይ ነው፡፡ 📖ዘጸ 31፥18 📖ዘዳ 20፥ #መስቀል 🔸ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶ በቀራንዩ የተሰቀለበት ሰይጣን ድል የተነሳበት የመዳናችን አርማ ነው፡፡ 🔹መስቀል ምዕመናንን እና ንዋየ ቅዱሣትን ለመባረክ ያገለግላል፤ የተለያዩ የመስቀል አይነቶች አሉ። ከእነዚህም መካከል #የእጅ #መስቀል 🔹ይህ የክህነት ማዕረግ ያላቸው አባቶች ብቻ የሚይዙት ሲሆን ምዕመናንን ለመባረክ ይጠቀሙበታል፡፡ #የመፆር #መስቀል 🔸ይህ ዲያቆናት በቅዳሴ ጊዜ የሚሠብኩበት ሲሆን በመጠኑም ከፍ ያለ ነው፡፡ #መብራት 🔹መቅረዝ የሻማ ማብሪያ ነው፤ ቀንዲል ደግሞ ሻማ ወይም የዘይት መብራት ነው፡፡ 🔸የመቅረዙ አገልግሎት ለሻማ ማብሪያነት ሲሆን ቀንዲሉ ደግሞ ቅዱሣት መፃህፍት፣ መልዕክታት፣ ወንጌል ሲነበቡ ይበራሉ። #አልባሳት 🔹በቤተክርስቲያን የአገልግሎት ልብስ እንደ ግለሠቡ የስልጣን ሁኔታ ይለያያል፤ የመነኮሣት ልብስ፣ ከካህናት ልብስ የካህናትና ዲያቆናት ይለያል። 👉የጳጳሳት ልብስ፣ 👉የመነኮሳት ልብስ፣ 👉የካህናት ልብስ፣ 👉የዲያቆናት ልብስ 🔺ቀሚስ 🔺ቀሚስ 🔺ካባ ላንቃ 🔺ለምድ 🔺ሞጣህት 🔺ድግድጋት 🔺ቆብ 🔺ስአክሊል #ማኅፈድ 🔹የጨርቅ መሸፈኛ ነው፤ ታቦቱን እና ጻህሉን ለመሸፈን ያገለግላል፡፡ 🔸ከምስራቅ ወደ ምዕራብ፤ ከሰሜን ወደ ደቡብ፤ ከመስዕ/ ከሰሜን ምሥራቅ /ወደ አዜብ /ደቡብ ምዕራብ/ ሆኖ ይለበሳል፡፡ #መንጦላዕት 🔹በሶስቱም የመቅደስ በር የሚጋረዱ መጋረጃዎች ናቸው፤ ቀለማቸውም ቀይ ነው፡፡ #መጎናፀፊያ 🔸ይህ በቅዳሴ ጊዜ መንበሩ (መሠዊያው) የሚለብሰው ሲሆን፤ ታቦት በሚወጣበት ጊዜ የሚጎናፀፈው ነው፡፡ #መንበር 🔹የጽላቱ (የታቦቱ) መቀመጫ ዙፋን ነው፤ ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙ የሚዘጋጀውም በዚህ ላይ ሆኖ ነው፡፡ 🔸ካህን ያልሆነ ሠው መንበሩን መንካት የማይችል ሲሆን መንበሩ እና ታቦቱ ወዳለበት ክፍል (መቅደስ) መግባት የሚችሉት ዲያቆናት፣ ካህናት፣ ኤጲስ ቆጳሳት ጳጳሳት ናቸው፡፡ #ጻህል 🔹የቅዱስ ሥጋው ማስቀመጫና ማክበሪያ ነው፤ ከወርቅና ከብር፣ ከነሀስና ከብረት የሚሠራ ሲሆን የተለየ ቅርፅና የተለየም ምልክት ያለው ነው፡፡ #ፅዋ 🔸የክርስቶስ ክቡር ደም የሚቀርብበት ነው፤ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከመዳብ፣ ከነሀስ፣ ከብረት የሚሠራ ነው፡፡ #ዕርፈ #መስቀል 🔹ማንኪያ ዓይነት ሆኖ ጫፉ ላይ መስቀል ያለው ነው፡፡ 🔸ፅዋው ከተሠራበት ቁስ የሚሠራ ሲሆን አገልግሎቱም የክርስቶስን አማናዊ ደም ለመቀበል የሚያገለግል ነው፡፡ #ዐውድ 🔸በድርገት ጊዜ ጻህል የሚቀመጥበት ሰፋ ያለ ጻህል ነው፤ ሥጋው እንዳይነጥብ መጠበቂያ ነው፤ የሚሠራው ከብረት፣ ከነሀስ፣ ከእንጨት ነው፡፡ #አጎበር 🔹በዐውድ ላይ የሚደፋ አራት ማዕዘን ሦስት እግር ያለው እንጨት ወይም ብረት ሊሆን ይችላል፤ ይህም ቅዱስ ሥጋውን ልብሱ እንዳይነካው ከፍ አድርጎ የሚይዝ ነው፡፡ #ጽንሃ 🔸የዕጣን ማሣረጊያ ነው፡፡ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከብረት፣ ይሠራል፤ ይህን ንዋይ ምዕመናን መጠቀም (መንካት) አይገባቸውም፡፡ 🔹ዲያቆናት ይይዙታል ይነኩታል ነገር ግን ካህናት የሚይዙበት ቦታ ላይ መያዝ አይችሉም (አያጥኑም)። #መሶበ #ወርቅ 🔹የአነስተኛ መሶብ ቅርፅ አለው፤ አገልግሎቱም ቅዱስ ቁርባኑን ከቤተልሄም ወደ ቤተ-መቅደስ ለማምጣት ነው፤ በሚመጣበት ጊዜም በመጎናፀፊያ ተሸፍኖ ነው፡፡ #ሙዳይ 🔸ለማዕጠንት አገልግሎት የሚያስፈልግ ዕጣን የሚቀመጥበት ነው፡፡ #ቃጭል 🔹በቅዳሴ ጊዜ የሚቃጨልና ድምፅ የሚሠጥ ነው፤ በቅዳሴ ጊዜ አራት ጊዜ ቃጭል ይደወላል፡፡ 👉ቅዳሴ ሲገባ 👉ፃኡ ንዑሰ ክርስቲያን ሲባል 👉በእግዚኦታ ጊዜ 👉ድርገት በሚወርድበት ጊዜ #ጥላ 🔸ይህ ከተለመደው ጥላ የሚለየው የተለያየ አንፀባራቂ ቀለም ባላቸው ጨርቆች መሠራቱ ነው፡፡ 🔹አገልግሎቱ በቅዳሴ ጊዜ ምስባክ ሲሰበክ እና ወንጌል ሲነበብ ይዘረጋል፡፡ 🔹ንግስ በሚሆንበት እለትም ከፊት እና ከኋላ በታቦቱ ዙሪያ ይዘረጋል፡፡ #ድባብ 🔹በመጠኑ ከጥላ ሠፋ ያለ ሲሆን በንግስ በዓላት ቀን በታቦቱ ላይ ይዘረጋል፤ ይዞ በታቦቱ አጠገብ መቆም የሚችለው ካህን ብቻ ነው፡፡ #ከበሮ 🔸ከበሮ ከእንጨት እና ከበሬ ቆዳ ተሠርቶ በጨርቅ የሚሸፈን ከፍተኛ ድምፅ የሚሠጥ መሣሪያ ነው፤ ይሁንና ከነሃስ እና ከብርም ተሠርቶ ቆዳው ሊወጠር ይችላል፡፡ 🔹ሁለት ጎኖች ሲኖሩት በእነዚህ ሁለት ጎኖች የሚወጣው ድምፅ የተለያየ ነው፤ አገልግሎቱም በማህሌት ጊዜ ለመዝሙር ማጀቢያነት ነው፡፡ #ፅናፅል 🔸ከነሃስ ወይም ከብር ሊሠራ ይችላል፤ ድምፅ የሚሠጡት በውስጡ ያሉት 5 ወይም 7 የሚሆኑ የነሀስ ወይም የብር ቁርጥራጮች ናቸው፡፡ 🔹አገልግሎቱም በእጅ ተይዞ ወደ ላይ እና ወደታች በማወዛወዝ መዝሙሩን ማጀብ ነው፡፡ #መቋሚያ 🔹ከእንጨት ከነሀስ ከብር ይሰራል። 🔸አገልግሎቱም በመዝሙር ጊዜ በትከሻ በመሸከም ወይም በእጅ በማወዛወዝ መዝሙሩን ይጅባል፤ ለመደገፊያነትም ያገለግላል፡፡ ሁሉም ቦታ ይዳረስ ዘንድ ለሌሎች #ማጋራታችሁን አትርሱ #share #share ⤵️
Показати все...
የእመቤታችን ማርያም የዘር ሐረግ
Показати все...
የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል_ማርያም_የዘር_ሐረግ360p.mp33.37 MB
የድንግል ማርያም ልደት የእግዚአብሔር ሰው ሰሎሞን ለአምላኩ ሕንፃ መቅደስን ሊያንጽ በተነሣ ጊዜ ፤ "በጥበብና በማስተዋል በብልሃትም የተሞላ" የናሱን ሠራተኛ ኪራምን ከጢሮስ አስመጥቶ ነበር። ከዚህም ጥበበኛ ጋር ሆኖ እጅግ አስደናቂ የሆነውን መቅደስ በታላቅ ጥንቃቄ አንጿል። በእውነት ይህን ሰሎሞን ያሳነጸውን ውብ መቅደስ ማየት ምንኛ ያጓጓ ይሆን? በእርግጥም መቅደሱንና የመሥዋዕቱን ሥርዓት የተመለከተች ንግሥተ አዜብ ማክዳ "ነፍስ አልቀረላትም" ነበር (1ኛ ነገ 10:5)። ሆኖም ግን እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ አድሮ "ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ?" ብሎ መጠየቁ አልቀረም (ኢሳ 66:48)። ለጊዜው በረድኤት የሚያድርበትን መቅደስ ንጉሥ ሰሎሞን ውብ አድርጎ ቢያንጽለትም ፤ በኋላ ግን የሰውን ልጆች ለመቤዠት በአካል የሚያድርበትን ሕያው መቅደስ ማንም ማዘጋጀት አልቻለም ነበር። ስለዚህም "ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም" ተብሎ ተጻፈ (ሐዋ 7:50)። በመሆኑም መቅደሱን ላነጹ ለሰሎሞን እና ለኪራም ጥበብን የሰጠው ጥበበኛ "ለራሱን ቤት ሊሠራ ፣ሰባት ምሰሶዎችንም ሊያቆም" ፈቃዱ ሆነ። የመቅደሱንም መሠረት እንቁ አደረገ። ቤቱንም እጅግ በከበሩ ድንጊያዎች አነጸ። ይህች በአምላክ እጅ የታነጸች ፣እግዚአብሔር በረድኤት ሳይሆን በአካል የሚያድርባት ሕያው መቅደሱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። የተመሠረተችባቸውም አዕናቁ (እንቁዎች) ቅዱሳን ቤተሰቦቿ ናቸው። የታነጸችበትም የከበሩ ድንጊያዎች ንጽሕና ፣ቅድስና ናቸው። "ይህች ዓለም አይቶ የማያውቃት በተስፋ ትጠበቅ የነበረችው ድንቅ አማናዊት መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህች ምድር ላይ የታየችው በዛሬው ቀን ነበር" ኪራም ያነጸው የሰሎሞንን መቅደስ መጎብኘት "ነፍስ የማያስቀር" ፣ልብን በሐሴት የሚሞላ ከሆነ ፤ በእግዚአብሔር እጅ የታነጸች ፣የአምላክ ጥበብ የፈሰሰባት እውነተኛ መቅደሱን የእመቤታችንን መወለድ የማየትና የመስማት የደስታ ጥጉ ምን ያህል ይሆን? እንኳን ደስታን ወደ ዓለም ይዞ ለመጣ ተናፋቂው ለድንግል ማርያም ልደት አደረሳችሁ!!! ዲያቆን አቤል ካሳሁን [email protected] 💚 @Kokuha_haymanot 💚 💛 @kokuha_haymanot 💛 ❤️ @kokuha_haymanot ❤️
Показати все...
✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✝✝✝ ❖ ሚያዝያ ፳፱ ❖ ✞✞ እንኩዋን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርሐዊ በዓለ ልደትና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ ✞✞ +"+ ተዝካረ በዓሎሙ ለቅዱሳን ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ ወአባ አካክዮስ ጻድቅ +"+ =>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዕለት ከምታስባቸው ቅዱሳን ሐዋርያው ቅዱስ አርስጦስና አባ አካክዮስ ቅድሚያውን ይይዛሉ:: +"+ አርስጦስ ሐዋርያ +"+ =>ቅዱስ አርስጦስ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን ከጌታችን እግር ለ3 ዓመታት ቁጭ ብሎ የተማረ: ፈጣሪው ከዋለበት ውሎ: ካደረበት አድሮ: የእጁን ተአምራት ያየ: የቃሉንም ትምሕርት ያደመጠ ሐዋርያ ነው:: +ከጌታችን ዕርገት በሁዋላም በጽርሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ወጥቷል:: መጀመሪያ ከዋኖቹ ሐዋርያት ጋር በረዳትነት አገልግሏል:: ከቆይታ በሁዋላ ግን ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ብዙ ነፍሳትን ማርኩዋል:: አሕዛብንም ካለማመን ወደ ማመን አምጥቷል:: +በነዚህ ጊዜያት ጭንቅ ጭንቅ መከራዎች ደርሰውበታል:: ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ በተሰጠው መክሊት አትርፎ ፈጣሪውንም ደስ አሰኝቶ በዚሕች ቀን አርፏል:: +"+ አባ አካክዮስ +"+ =>ዳግመኛ በዚህ ቀን አባ አካክዮስ አርፏል:: ቅዱሱ ከሕጻንነቱ ጀምሮ ንጽሕናን ያዘወተረ: በገዳማዊ የቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ነው:: ምሑርነቱንና ቅድስናውን የተመለከቱ ሰዎች በኢየሩሳሌም ላይ ዽዽስናን ሹመውታል:: +በመንበረ ዽዽስናውም ላይ እያለ ዕረፍት አልነበረውም:: ኢ-አማንያን ይገርፉት: ያስሩት: ያረሰቃዩትም ነበር:: ቤተ ክርስቲያን ስለ ተጋድሎው ጻድቅ: የዋሕና ንጹሕ ብላ ትጠራዋለች:: =>እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ረድኤት: ጸጋና በረከት ይክፈለን:: =>ሚያዝያ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) 2.አባ አካክዮስ ዘኢየሩሳሌም (ጻድቅና ንጹሕ) 3.አባ ገምሶ ሰማዕት =>ወርኀዊ በዓላት 1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት 2.ቅድስት አርሴማ ድንግል 3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት 4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ 5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት 6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት) =>+"+ ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው ጌታ ሆይ! አጋንንት ስንኩዋ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት:: እንዲህም አላቸው:- 'ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ:: እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችሁአለሁ:: የሚጐዳችሁም ምንም የለም:: ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ:: ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ:: +"+ (ሉቃ.10:17-20) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Показати все...
#ዳግም_ትንሣኤ ዳግም ትንሣኤ ሲባል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ሞቶ፣ ተቀብሮ፣ ተነሳ ሳይሆን በድጋሜ ቅዱስ ቶማስ ባለበት ልክ በመጀመሪያ እንደተገለጠላቸው ሆኖ ስለታያቸው ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአስሩ ሐዋርያት ሲገለጥላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልነበረምና መጥቶ በተገናኛቸው ጊዜ እነሱም ጌታችን እንደተነሳና ተገልጦ ሰላምታ እንደሰጣቸው ሲነግሩት የተቸነከረውን እጁን እና እግሩን በጦር የተወጋ ጎኑን ካላየሁ አላምንም በማለቱ (ዮሐ 20፥25) እንደገና ተገልጦላቸዋል። ቶማስ ይሄንን ሊል የቻለው የተጠራው ትንሣኤ ሙታን የለም ከሚሉት ከማያምኑት ከሰዱቃውያን ወገን ነበርና ነው። አንድም ሌሎች ሐዋርያት ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ አየነው እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብዬ ላስተምር ነው ብሎ ነው። ጌታም የቶማስን ጥርጣሬ ያስወግድለት ዘንድ በተነሳ በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ቶማስ ከሌሎች ሐዋርያት ጋር ሳለ እንደገና በትንሣኤ እንደታያቸው ሆኖ በዝግ ቤት ገብቶ ሰላምታ ከሰጣቸው በኋላ ሐዋርያው ቶማስን ለይቶ "ቶማስ ቶማስ ና በችንካር የተቸነከሩ እጆቼን እይ እንዲሁም እጅሀን አምጥተሀ በጦር ወደ ተወጋው ጎኔ አግብተሀ ዳሰኝ ያመንክ እንጅ ተጠራጣሪ አትሁን ባለው ጊዜ ቶማስም በችንካር የተቸነከሩ እጆቹን በጦር የተወጋ ጎኑን በእጆቹ በዳሰሰ ጊዜ ከእሳት እንደገባ ጅማት ኩምትርትር ሲል "ጌታዬ አምላኬ" አለ። መዳሰሱን ሲያይ “ጌታዬ”፤ ማቃጠሉን ሲያይ “አምላኬ” አለ አምላክነቱንም መሰከረ፡፡ ጌታም አንተ አይተኽ አምነሃል ነገር ግን" ሳያዩ የሚያምኑ ብፁአን ናቸው"ብሎ ፈውሶታል (ዮሐ. 20፥29)። (እስከ ዛሬም ይህቺ ጌታን የዳሰሰች የቅዱስ ቶማስ እጅ በሕንድ አገር ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ትገኛለች) በሌላ በኩል ዳግም ትንሣኤ የተባለበት በአከባበር፣ በሥርዓት የመጀመሪያውን ትንሣኤ ስለሚመስል ነው፡፡ የትንሣኤ ዕለት የሚባለው ቃለ እግዚአብሔር ሳይለወጥ፤ በሙሉ በዚህ ቀን ይባላል፡፡ ከዚህም ሌላ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት፡፡ እነዚህም “#ፈጸምነ እና #አግብዖተ_ግብር” ይባላል፡፡ "ፈጸምነ" የተባለበት የሰሙነ ትንሣኤን በዓል አክብረን ፈጸምን ማለት ነው፡፡ "አግብዖተ ግብር" የተባለበትም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "አባ ወአቡየ ግብር ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ" "እኔ ልሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርሁህ" ያለውን ከቅዳሴ በኋላ ሊቃውንት በዚህ ቀን ስለሚዘምሩት ነው፡፡ (ዮሐ.17፥4) 👇👇👇👇👇👇 @Yahiwenesei
Показати все...
✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✝✝✝ ❀ ሚያዝያ ፳፯ ❀ ✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ ፊቅጦር" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +*"+ ማር ፊቅጦር +"*+ =>ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በደማቸውና በገድላቸው ያስጌጡ ብዙ ሰማዕታት አሉ:: ነገር ግን ከኮከብም ኮከብ ይበልጣልና ማን እንደ ጊዮርጊስና እስጢፋኖስ! +ከእነርሱ ቀጥለው ከሚጠሩ ሰማዕታት ደግሞ አንዱና ዋነኛው ቤተ ክርስቲያን "ማር" የምትለው ቅዱስ ፊቅጦር ነው:: እስኪ ከበዛው መዓዛ-ገድሉ ጥቂት እንካፈል:: =>ቅዱስ ፊቅጦር አባቱ ኅርማኖስ ይባላል:: አረማዊና ጨካኝ ነው:: እናቱ ግን የተመሰገች ቅድስት ማርታ ትባላለች:: ልጇን እንደሚገባ አሳድጋው 20 ዓመት ሲሞላው የአንጾኪያ ንጉሥ የሠራዊት አለቃና በመንግሥቱ 3ኛ አድርጐ ሾመው:: +የድሮዋ አንጾኪያ (ሮም) እንደ ዛሬዋ አሜሪካ ዓለምን የተቆጣጠረች ሃገር ነበረች:: ቅዱስ ፊቅጦር ደም ግባቱ ያማረ: በጦርነትም ኃይለኛ ስለ ነበር ሁሉ ያከብሩት: ይወዱትም ነበር:: እርሱ ግን ቀን ቀን ሲጾም: ነዳያንን ሲያበላ ይውል ነበር:: +ሌሊት ደግሞ እኩሉን ሲጸልይና ሲሰግድ: እኩሉን የእስረኞችን እግር ሲያጥብ ያድር ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆንኮ እርሱ የንጉሡ 3ኛ: የሠራዊትም አለቃ ነው:: በዘመኑ የሚያገድፍ ምግብና የወይን ጠጅ በአፉ ዙሮ አያውቅም:: +ከነገር ሁሉ በሁዋላ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ካደ:: ዘመነ ሰማዕታትም ጀመረ:: አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ:: ከ47 ሚሊየን በላይ ክርስቲያኖች በመንኮራኩር ተፈጩ: በመጋዝ ተተረተሩ: ለአራዊት ተሰጡ: በግፍም ተጨፈጨፉ:: ቀባሪ አጥተውም ወደቁ:: +በዚሕ ጊዜ ማር ፊቅጦር እናቱን ቅድስት ማርታን በዕንባ ተሰናብቶ ወደ ንጉሡ ቀርቦ በክርስቶስ ስም ታመነ:: ክፉ አባትም በልጁ ላይ ሞትን መከረ:: +ከዚያም ቅዱሱን አፉን በብረት ለጉመው ወደ ምድረ ግብፅ አወረዱት:: መሪያቸው እንዳልነበረ ወታደሮቹ መኳንንቱ ሁሉ ተዘባበቱበት:: እርሱ ከምድራዊ ንግሥና ሰማያዊ መንግስትን: በሰዎች ፊት ከመክበር ስለ ክርስቶስ ሲል መናቅን መርጧልና:: +ለቀናት: ለወራትና ለዓመታት መኳንንቱ እየተፈራረቁ አሰቃዩት:: በርሱ ላይ ያልሞከሩት የስቃይ ዓይነት አልነበረም:: አካሉን ቆራርጠዋል: ዓይኖቹን አውጥተዋል: ምላሱንም ቆርጠዋል:: +በዚሕች ዕለት ግን በሰይፍ አንገቱን ቆርጠውታል:: ስለዚህም እናት ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ማክበር ታከብረዋለች:: እግዚአብሔርም ለቅዱስ ፊቅጦር እንዲህ አለው:- "እንደ አቅሙ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ: ስምህን ያከበረ: የብርሃን ልብስ አጐናጽፌ ወደ መንግስተ ሰማያት አስገባዋለሁ::" ❖ቸሩ አምላከ ፊቅጦር ሁላችንም ይማረን:: ከቃል ኪዳኑ አሳትፎ ለርስቱ ያብቃን:: ❖ሚያዝያ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ጽኑዕና ኃያል ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት 2.ቅድስት ማርታ (የፊቅጦር እናት) 3.ብጽዕት እስጢፋና (በክርስቶስ ስላመነች ከ2 ሰንጥቀው የገደሏት የ15 ዓመት ወጣት) 4.ቅዱሳን ሳሲማና አባ ኖባ (ሰማዕታት) =>ወርኀዊ በዓላት 1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት 2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ 3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ) 4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ 5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ) 6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት ++"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Показати все...
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ሚያዝያ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ሰማዕቱ ቅዱስ ዮሐንስ +"+ +ቅዱስ ዮሐንስ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ቅዱስ ሰው ነው:: ወላጅ አባቱ ጣኦት ጠራቢና አምላኪ: የጣኦቱ አጣኝም ነበረ:: እናቱ ግን በድብቅ ክርስቶስን ታመልክ ነበር:: +ልጇን ክርስትና ብታስተምረው አባቱ ጨካኝ በመሆኑ ይገድለዋልና ዘወትር ጧት ማታ ወደ ፈጣሪዋ በዕንባ ትለምን ነበር:: ጧት ጧት አባቱ ጣኦት መጥረብና ማምለክን ያስተምረው ነበር:: አንድ ቀን እግዚአብሔር ለሕጻኑ ዮሐንስ በራዕዩ ተገለጠለት:: ምስሥጢራትንም አስተማረው:: +ለተወሰነ ጊዜ በሚደነቅ የክርስትና ሕይወት ከኖረ በኋላ ምንም ገና እድሜው 12 ዓመት ቢሆንም አባቱን ጦኦትህን ተው ሲል መከረው:: አባት ግን ጨካኝ ነውና ትልቅ መጥረቢያ አንስቶ አንገቱን መታው:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ መሬት ላይ ስትወድቅ አካሉ ግን ለ1 ሰዓት ቆሞ በደሙ ተጠመቀ:: ይሕ ሁሉ ሲሆን የተባረከች እናቱ ቆማ ታይ ነበር:: +መንፈሳዊት እናት ናትና አላዘነችም:: ይልቁኑ ከልጇ ደም ለበረከት ተቀባች:: አለችም:- "ጌታ ሆይ! የምሰጥህ ምንም የለኝም:: ይህንን ንጹሕ መስዋዕት ግን ተቀበለኝ::" +ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ካለፈ በኋላ አባቱን ርኩሳን መናፍስት አሳበዱት:: እናት ግን አረማዊ ባለቤቷን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መቃብር ወስዳ ጸለየች:- "ልጄ ሆይ! አባትህን ይቅር ብለህ ከፈጣሪ ዘንድ አማልድ::" +ይሕንን ብላ ባሏን ከመቃብሩ አፈር ወስዳ ቀባችው:: አባትም በቅጽበት ድኖ ወደ ልቡ ተመለሰ:: ስለ ሰራው ሁሉ ተጸጽቶ አለቀሰ:: በእውነተኛ አምላክ በክርስቶስ አምኖ: ተጠምቆ: በመልካም ክርስትና ኑሮ ኑሮ: ከተባረከች ባለቤቱ ጋር ለገነት በቅቷል:: +"+ ቅዱስ ሱስንዮስ +"+ +ዳግመኛ በዚህ ቀን ቅዱስ ሱስንዮስ ተሰይፏል:: ቅዱሱ በዘመነ ሰማዕታት ቤተ ክርስቲያንን በገድላቸው ካስጌጧት ታላላቅ ሰማዕታት አንዱ ነው:: ❖እግዚአብሔር አምላክ ከሰማዕታቱ ጽናትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: ❖ሚያዝያ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕት (ወልደ ፀራቢ) 2.ቅዱስ ሱስንዮስ ሰማዕት (ሶርያዊ) 3.ሰማዕታት (የቅዱስ ሱስንዮስ ማሕበር) 4.አባ ሠርጋ 5.ቅዱስ ይድራስ ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ አቡነ ሐብተ ማርያም 2፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ 3፡ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን 4፡ ቅዱስ ቶማስ 5፡ ሰማዕታተ ናግራን ++"+ ሰውን ከአባቱ: ሴት ልጅንም ከእናቷ: ምራትንም ከአማቷ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና:: ለሰውም ቤተሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል:: ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: መስቀሉን የማይዝ በኋላየም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: +"+ (ማቴ. 10:35-39) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.