cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

BDU FELLOWSHIP VLM

ይህ የBahir Dar University Fellowship VLM ይፍዊ የቴሌግራም ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ዉስጥ 👉 አዳዲስ እና የድሮ መዝሙሮች 👉 የእግዚአብሔር ቃል 👉 የተለያየ ይዘት ያላቸው ጽሁፎች 👉 ጥቅሶች 👉 የህይወት ምስክርነቶች 👉 ጥያቄና መልሶች 👉 ሌሎችም ብዙ ዝግጅቶችም አሉን:: Fb👉fb.me/BDU-Fellowship-VLM

Більше
Рекламні дописи
2 682
Підписники
+324 години
+127 днів
+3530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
መንፈስ ቅዱስ ➥ሰው ሁሉ መማር ያለበት ከመንፈስ ቅዱስ ነው፤ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራ እውነተኛ አስተማሪ እርሱ ስለሆነ። ከመንፈስ ቅዱስ የተማረ የምኖር ሰው ከሰው እና ከዓለም አይኮርጅም ፤ ከእግዚአብሔር ሕይወት እየቀዳምና እየሰማ ይናገራል፤ ይኖራልም እንጂ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ የማይቋረጥ ህብረት ስያደርግ በሁለንተናው በእግዚአብሔር ጥበብ እየተሞላ፤ የክርስቶስ መልክ እየገለጠ ማደግ ይጀምራል። ➥ስለ እግዚአብሔር ሳይሆን እግዚአብሔርን በማወቅ በመገለጥ ዕውቀት ያድጋል፤ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምስጢር ያስተምራል።  አዳዲስ መገለጥ ይሰጣል፤ ሰው ከመንፈስ ቅዱስ ካልተማረ ስለ እግዚአብሔር information እንጂ እግዚአብሔርን ማወቅ አይችልም። ከመንፈስ ቅዱስ ለመማር ደግሞ ከእርሱ ጋር የማይቋረጥ ህብረትና ወዳጅነት ማድረግ ይጠበቅብናል።
አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ_ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን_ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።"   - ዮሐንስ 14፥26
FAITHFUL SERVANTS OF THE KINGDOM      ታማኝ  የመንግሥቱ አገልጋዮች    እንለያለን | እንመለሳለን | እንጠብቃለን Follow Us On  INSTAGRAM  YOUTUBE
Показати все...
5
Blog Monday ➥መወደድ በሀና ኤልያስ #ክፍል_2 በሌላ ገጽ ደግሞ በቤት ውስጥ ብዙ የሚለፋና የሚደክመው የዚህ የጠፋው ልጅ ታላቅ ወንድም፥ በጣም ብዙ ስለሰራና አባቱን ስላገለገለ ከወንድሙ በተሻለ መልኩ የሚወደድ ይመስለው ነበር። ይሄንንም የሚያስረግጥልን በምእራፉ 29ነኛ ቁጥር ላይ፥ አባት የጠፋውን ልጁን አስመልክቶ ባደረገው የደስታ ዝግጅት ላይ በመናደድ የተናገረው ንግግር ነው። “እነሆ ይህን ያህል አመት እንደ ባሪያ ተገዝቼልሀለሁ፥ ከትእዛዝህም ከቶ አልተላለፍኩም፥ ለእኔም ከወዳጆቼ ጋር ደስ እንዲለኝ አንድ ጠቦትስ እንኳን አልሰጠሀኝም።” በማለት ለአባቱ ያለውን መገዛትና መታዘዝ ከወንድሙ በተሻለ መልኩ ሊወደድበት የሚገባ ምክኒያት አድርጎ ያስቀምጣል። ይሄ ልጅ መገዛቱ መልካም ነው። የአባቱን ትእዛዝ በትክክል አክብሮ ማገልገሉም እጅግ በጣም መልካም ነው። አንድ የሳተው ትልቅ ነገር ግን ምንድነው? ለአባቱ የሚሰጠው ይሄ ሁሉ አገልግሎት፥ አባቱ እርሱን የወደደባቸው ምክኒያቶች አለመሆናቸውን አለመረዳቱ ነው። አባታቸው እርሱንም ሆነ ወንድሙን የወደዳቸው፥ ስለሰሩና ስላገለገሉት አይደለም። የወደዳቸው ልጆቹ ስለሆኑ ነው። የወደዳቸው ስለወለዳቸው ነው። ሰው ልጁን የሚወደው፥ ስለሰራና ስላገለገለው አይደለም። ሰው ልጁን የሚወደው፥ ስለወለደው ነው።  እኔ ገና ልጅ ባለመውለዴ ስሜቱ በትክክል ባይገባኝም፥ አንድ ወዳጃችን የመጀመሪያ ልጇን ከወለደች በኋላ የነገረችን አንድ ነገር ልቤ ውስጥ ቀርቷል......... ➥  ሙሉ ለማንበብ  👉 ይጫኑ ➥ Offline ለማንበብ  ከስር ያለውን Instant View ይጫኑ ።
Показати все...
መወደድ || ክፍል -1

በልጅነቱ እንደ እኔ ጨዋታ የሚወድ ሰው ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ መጫወት በጣም ነበር የምወደው። ገና ከትምህርት ቤት ስንወጣ ልቤ የሚቸኩለው፥ ቶሎ ብዬ ቤት በመሄድ ልብሴን ቀይሬ ከሰፈር ጓደኞቼ ጋር አባሮሽ እስክንጫወትና ሩጫ እስክንወዳደር ነበር። ታዲያ ገና እኔና እህቴ ከትምህርት ቤት እንደገባን፥ እናታችን ከስራ ትመጣና ለእኔና ለእህቴ መስራት ያለብንን የቤት ስራ አከፋፍላን መሄድ ወዳለባት የማህበራዊ ህይወት ጉዳዮች ትሄዳለች። አብዛኛውን ጊዜ የእህቴ ስራ እቃ ማጠብ ሲሆን፥ የእኔ ስራ ደግሞ ቤቱን ማጽዳት ነው። “በቃ ቶሎ ቶሎ ሰርቼው ሄጄ ልጫወት” እልና ገና ቤቱን መጥረግ እንደጀመርኩ፥ የሰፈር ጓደኞቼ በአጥሩ በኩል ስሜን እየጠሩ ጊቢውን ይደባልቁታል። ድሮም ለመጫወት የቸኮለው ልቤ “በቃ ትንሽ ልጫወትና ቶሎ ተመልሼ እጨርሰዋለሁ” በማለት፥ ጓደኞቼን ለማግኘት ወደ ውጪ እሮጣለሁ። ከጓደኞቼ ጋር…

9
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#መቼ_ዘገየ? ➥እስራኤላውያን ቀይባህር ጋር ሲደርሱ የሚመራቸው ደመና ቆሞ ከዃላቸው እነሱን እየተከተለ እንደሆነ ሲገባቸው እግዚአብሔር እንደተዋቸው አስበው አለቀሱ ነገር ግን ደመናው ጠላቶቻቸው ከሆኑት የግብፃውያን ወታደሮች እየጠበቃቸው እንደሆነ አልገባቸውም! ከዛ እግዚአብሔር ለሙሴ ምን እንዳለው ታውቃላችሁ?
"........ ለምን ትጮኽብኛለህ? እንዲጓዙ ለእስራኤል ልጆች ንገር።"   - ዘጸአት 14፥15
➥እግዚአብሔር በጨነቀህ በፈተና ውስጥ ባለፍክ ጊዜ የተወህ እና የረሳህ የመሰለህ አንተ ነው ነገር ግን ይረሳ ዘንድ ሰው ያለሆነ እግዚአብሔር ከማታየው ነገር በማታየው ሁኔታ እየጠበቀህ ስለሆነ ነው ለመልሶችህ የዘገየው! ነገር ግን ኪዳኑን የሰጠህ ካንተ ጋር ስላለ ለሙሴ እንደተናገረው መጓዝህን በፍፁም ሳታቋርጥ ለ Destiny'ህ ወደፊት ሂድ! FAITHFUL SERVANTS OF THE KINGDOM      ታማኝ  የመንግሥቱ አገልጋዮች    እንለያለን | እንመለሳለን | እንጠብቃለን Follow Us On  INSTAGRAM  YOUTUBE
Показати все...
7👍 1
Blog Monday ➥መወደድ በሀና ኤልያስ #ክፍል_1 በልጅነቱ እንደ እኔ ጨዋታ የሚወድ ሰው ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ መጫወት በጣም ነበር የምወደው። ገና ከትምህርት ቤት ስንወጣ ልቤ የሚቸኩለው፥ ቶሎ ብዬ ቤት በመሄድ ልብሴን ቀይሬ ከሰፈር ጓደኞቼ ጋር አባሮሽ እስክንጫወትና ሩጫ እስክንወዳደር ነበር። ታዲያ ገና እኔና እህቴ ከትምህርት ቤት እንደገባን፥ እናታችን ከስራ ትመጣና ለእኔና ለእህቴ መስራት ያለብንን የቤት ስራ አከፋፍላን መሄድ ወዳለባት የማህበራዊ ህይወት ጉዳዮች ትሄዳለች። አብዛኛውን ጊዜ የእህቴ ስራ እቃ ማጠብ ሲሆን፥ የእኔ ስራ ደግሞ ቤቱን ማጽዳት ነው። “በቃ ቶሎ ቶሎ ሰርቼው ሄጄ ልጫወት” እልና ገና ቤቱን መጥረግ እንደጀመርኩ፥ የሰፈር ጓደኞቼ በአጥሩ በኩል ስሜን እየጠሩ ጊቢውን ይደባልቁታል። ድሮም ለመጫወት የቸኮለው ልቤ “በቃ ትንሽ ልጫወትና ቶሎ ተመልሼ እጨርሰዋለሁ” በማለት፥ ጓደኞቼን ለማግኘት ወደ ውጪ እሮጣለሁ። ከጓደኞቼ ጋር ስንሮጥ፣ ስንስቅ፣ ስንቀልድና ስንጫወት ቆይተን ቆይተን ልክ ቀኑ እየመሸ ሲመጣ፥ እናቴና የሰፈር ጎረቤቶቿ ነጭ ነጠላቸውን አንደለበሱ ሰፈር ውስጥ ከነበረ ለቅሶ ቤት ሲመለሱ ከሩቅ አያቸዋለሁ። “ወይኔ ስራዬን ሳልጨርስ እናቴ እየመጣች ነው” ብዬ በሩጫ ወደ ቤት በመመለስ የጀመርኩትን ቤት ጠርጌ ሳልጨርስ ውዷ እናቴ ትገባለች። “ቀጥ ብለሽ መኝታ ቤት ሄደሽ ጠብቂኝ” ማለት በእኛ ቤት አማርኛ፥ መኝታ ቤት ቁጭ ብለሽ እየመጣ ያለውን ዱላ ጠብቂ ማለት ነው። ዱላው ደግሞ እዛው መኝታ ቤት አልጋ ስር ስለሚቀመጥ፥ አንዳንድ ጊዜ ሰባብሬ ብጥለው እራሱ ደስ ይለኛል። በ4 አመት ከእኔ ታናሽ የሆነችው እህቴ ደግሞ በጣም በሚገርም ሁኔታ እንደ እኔ ጨዋታ የማያታልላትና የተሰጣትን ስራ ሳትሰራ የትም ቦታ ለመጫወት የማትሄድ ልጅ ነበረች። ኸረ አንዳንዴ እንዲያውም ስራውን እየሰራች ሳትጫወት ቀኑ ሊመሽባት ይችላል። አሁን ላይ ስለ ልጅነታችን ስናወራ ታዲያ፥ እህቴ የጨዋታ ጊዜዋን በአግባቡ ስላልተጠቀመችበትና መጫወት ባለባት ጊዜ ስላልተጫወተች ሲቆጫት እመለከታለሁ። “እንዴት ነው ታዲያ ጨዋታ ሊያታልልሽ በሚችልበት እድሜ ላይ ሆነሽ ስራን ልታስቀድሚ የቻልሽው?” ብዬ ስጠይቃት..... ➥  ሙሉ ለማንበብ  👉 ይጫኑ ➥ Offline ለማንበብ  ከስር ያለውን Instant View ይጫኑ ።
Показати все...
መወደድ || ክፍል -1

በልጅነቱ እንደ እኔ ጨዋታ የሚወድ ሰው ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ መጫወት በጣም ነበር የምወደው። ገና ከትምህርት ቤት ስንወጣ ልቤ የሚቸኩለው፥ ቶሎ ብዬ ቤት በመሄድ ልብሴን ቀይሬ ከሰፈር ጓደኞቼ ጋር አባሮሽ እስክንጫወትና ሩጫ እስክንወዳደር ነበር። ታዲያ ገና እኔና እህቴ ከትምህርት ቤት እንደገባን፥ እናታችን ከስራ ትመጣና ለእኔና ለእህቴ መስራት ያለብንን የቤት ስራ አከፋፍላን መሄድ ወዳለባት የማህበራዊ ህይወት ጉዳዮች ትሄዳለች። አብዛኛውን ጊዜ የእህቴ ስራ እቃ ማጠብ ሲሆን፥ የእኔ ስራ ደግሞ ቤቱን ማጽዳት ነው። “በቃ ቶሎ ቶሎ ሰርቼው ሄጄ ልጫወት” እልና ገና ቤቱን መጥረግ እንደጀመርኩ፥ የሰፈር ጓደኞቼ በአጥሩ በኩል ስሜን እየጠሩ ጊቢውን ይደባልቁታል። ድሮም ለመጫወት የቸኮለው ልቤ “በቃ ትንሽ ልጫወትና ቶሎ ተመልሼ እጨርሰዋለሁ” በማለት፥ ጓደኞቼን ለማግኘት ወደ ውጪ እሮጣለሁ። ከጓደኞቼ ጋር…

10🙏 2👍 1
00:31
Відео недоступнеДивитись в Telegram
8.94 MB
9
Фото недоступнеДивитись в Telegram
➥ ትልቅ ስጦታ ብሰጥህ ምናልባት በሰጠውህ ስጦታ ተመልካቹን ልታስደምም ትችል ይሆናል ነገር ግን በገዛ ስጦታዬ የሰጪዋን የኔን ልብ ግን መግዛት አትችልም! ይልቁኑ የልቦና አይኔን ሊይዝ የሚችለው ስጦታውን ያስተናገድክበት ስብዕናህ(Character)ብቻ ነው! ➥ ፀጋም እንደዚህ ነው! የፈለገው ሀይለኛ ነገር አንተ ለይ ቢገለጥ ካንተ አንዳችም አስተዋጾ ሳይኖር ምርኮን በማረከ ጊዜ የሰጠ የስጦታ ባለቤት ስላለ በራሱ ስጦታ ልታስገርመው አትችልም! ➥ ወዳጆቼ መንፈስቅዱስ ግን ልብን  ይመረምራል! Character'ን ይመዝናል! ስለዚህ የእግዚአብሔር አይነት ልብ ልኖረን ይገባል ማለት ነው
"ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን........   - 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥11-12
FAITHFUL SERVANTS OF THE KINGDOM      ታማኝ  የመንግሥቱ አገልጋዮች    እንለያለን | እንመለሳለን | እንጠብቃለን Follow Us On  INSTAGRAM  YOUTUBE
Показати все...
3👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
➥ሀኪሙ ጠዋት አንድ ማታ አንድ የሚወሰድ መድኃኒት ለ 5 ቀን ቢሰጠህ, አንተ ከቀኖቹ ውስጥ በአንደኛው ማታ ለይ ከታዘዘልህ ውጪ 2 ብትወስድ ለትዕዛዙ ስላልታመንክ መድሀኒቱን በመውሰድህ የምታገኘው ውጤት ለይ እምነትን አጓድለክ የራስህን መንገድ ጨምረህ ለመሙላት ጥረት እያረክ ነው! ➥ትክክለኛ እምነት(Faith) ግን የሚለካው እምነትህ ላለበት ለዛ ነገር እግዚአብሔር የሚያዘውን የትኛውንም ነገር ያለጥርጥር በመታመን(faithfulness)'ን በመፈፀም ውስጥ ነው!
"የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ፤" ዕብራውያን 10:23
➥ እግዚአብሔር በምታለፉበት በየትኛውም ነገር የእምነት እና የመታመን አቅማችሁን በኢየሱስ ስም ይጨምርልህ። FAITHFUL SERVANTS OF THE KINGDOM      ታማኝ  የመንግሥቱ አገልጋዮች    እንለያለን | እንመለሳለን | እንጠብቃለን Follow Us On  INSTAGRAM  YOUTUBE
Показати все...
🙏 9🔥 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
3👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
➥ ባርኮት መዝሙረኛው
"አምላክ ሆይ፤ የብሶት ቃሌን ስማ፤ ሕይወቴንም ከሚያስፈራ የጠላት ዛቻ ከልላት።" መዝሙር 64፥1
ብሎ እንደለመነ እግዚአብሔር ህይወታችሁን ከጠላቶቻችሁ ይጠብቅላቹ። በዘመናቹ ሁሉ ጠላቶቻችሁ ውድቀታቹሁን አይዩ። እልፍ ሁኑ። ዘራቹ ይብዛ። ባለ በገናው
"ጌታ ሆይ፤ ድምፄን ስማ፤ ጆሮዎችህ የልመናዬን ቃል፣ የሚያዳምጡ ይሁኑ።"   መዝሙር 130፥2
ብሎ እንደለመነ እግዚአብሔር  ጆሮውን ይስጣቹ። የልመናችሁን መልስ ያሰማቹ። በአምላክ ዘንድ ተደመጡ። ልዑል ሞገሳቹ ይሁን። እግዚአብሔር ድካማችሁን ይባርክላቹ። የልፋታችሁን ፍሬ በብዙ ያሳጭዳቹ። ሰዎች አይተዋቹ አባታቸው እግዚአብሔር ነው ይበሉ ። በፍቅር፣ በትህትና ታወቁ። ሰዎች ይስሟቹ። ለምናቹ አትጡ። የእግዜሩ እንደልቤ
"በድንኳንህ ለዘላለም ልኑር፤ በክንፎችህም ጥላ ልከለል። "    መዝሙር 61፥4
ብሎ እንደለመነ እና በዶፍ ዝናብ ውስጥ ሰው ላለመበስበስ ዣንጥላ እንደሚያጠላ ከዝናቡም እንደሚያመልጥ እግዚአብሔር በጭንቅ ዘመን ጥላ ሆኖ ያሳልፋቹ። እግዚአብሔር ንፁህ ልብን ይፍጠርላቹ። መንገዳችሁን ደልዳላ ሜዳ ያድርግላችሁ። FAITHFUL SERVANTS OF THE KINGDOM      ታማኝ  የመንግሥቱ አገልጋዮች    እንለያለን | እንመለሳለን | እንጠብቃለን Follow Us On  INSTAGRAM  YOUTUBE
Показати все...
6👍 3🙏 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"ለባሪያህ ተስፋ ያስደረግኸውን ቃልህን አስብ።"   - መዝሙር 119፥49 ያለንበት ወቅት ትንሽ ብለን በማናቃልለው የህይወት ጉዞ እንዳለን እርግጥ ነው። እየሄድንበት ያለው መንገድ ግን መሄድ ከምንፈልገው በጣም ያላሰብነው ነው ። እግዚአብሔር አደርሳችኋለሁ ካለን ስፍራ የሚያደርስ ነገር አይመስልም መንገዱ። እናም ተስፋ መቁረጥ ይታይብናል። በዚህ አያያዛችንማ አንደርስም ብለን ቁጭ ብለናል። እግዚአብሔር ምን አለን?ምን ጠብቁ አለን? እሱ አይዘገይም በጊዜያችን ሳይሆን በጊዜው ይመጣል። "..፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤" ዕብ 13፥5 ። ላይተወን ቃል ገብቶልናል። FAITHFUL SERVANTS OF THE KINGDOM      ታማኝ  የመንግሥቱ አገልጋዮች    እንለያለን | እንመለሳለን | እንጠብቃለን Follow Us On  INSTAGRAM  YOUTUBE
Показати все...
10👍 1
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.