cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ድምፀ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት- የብቸና መ/ሕ/የቀ/አ/ገ/መ/ቅዱስ ካቴድራል

ይህ በብቸና ከተማ የየቀፈት መካነ ህይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካቴድራል ድምጸ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት የአባላት የመወያያና ትምህርቶች የሚተላለፉበት ቻናል ነው

Більше
Рекламні дописи
217
Підписники
Немає даних24 години
-17 днів
-530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

https://youtu.be/fmHG8Us-13I ለቤተ ክርስቲያን ብለህ ዘበእንቲአሃ ለቤተ ክርስቲያን ተጻፋእከ በውስተ ዓውድ ከመ ትቀድሳ በደምከ ክቡር  ዘበእንቲአሃ ዝግሃታት መዋቅሕት ፆረ ወተአገሠ ምራቀ ርኵሰ እንዘ አልቦ ዘአበሰ አምላክ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሰቅለ ለቤተ ክርስቲያን ብለህ ልትቀድሳት በደምህ በአደባባይ በጥፊ ተመታህ ንጹሕ ክርስቶስ በአዳም ጥፋት ልትወቀስ በከንቱ ልትከሰስ አመላለሱህ ከጲላጦስ ወደ ሄሮድስ ሁሉን ቻይ ሳለህ ምንም ማድረግ ሳይሳንህ በአይሁድ እጅ ተገረፍክ ወዮ ወሰን የሌላት ትዕግሥትህ ስለ እኛ ብለህ መከራን ተቀበልክ ምንም በደል ሳይኖርብህ አምላክ በእንጨት መስቀል ላይ ሰቀሉህ
Показати все...
"ለቤተ ክርስቲያን ብለህ የንስሐ መዝሙር" ZwT || ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video)

"ለቤተ ክርስቲያን ብለህ የንስሐ መዝሙር" ZwT || ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video) #MKZwT#ዜማወጥበብዘማኅበረቅዱሳን#Mahiberekidusan Subscribe:

https://www.youtube.com/channel/UC2U2...

Telegram:

https://t.me/+5e0PniMWKnsyMWFh

   ሰባቱ አጽርሐ መስቀል የሚባሉትም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም በቀራኒዮ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የተናገራቸው ቃላት ናቸው፡፡ እነዚህም፦ - ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ)…ማቴ 27፥40 - አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው…ሉቃ 23፥39 - ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ…ሉቃ 23፥39 - አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ…ሉቃ 23፥46 - እነሆ ልጅሽ እነሆ እናትህ…ዮሐ 19፥26 - ተጠማሁ…ዮሐ ፥28 - ተፈፀመ…ዮሐ ፥19፥30 ከዚያም በኋላ በሲዖል ለነበሩ ነፍሳት ቀኝ እጁን፣ የተወጋ ጎኑን አሳያቸው፤ እንደ ጥምቀትም ሆኗቸው ገነት አግብቷቸዋል፡፡ ዓርብ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከጲላጦስ አስፈቅደው ከመስቀል አውርደው በንጹሕ በፍታ ገንዘው ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር እያሉ ማንም ገና ባልተቀበረበት አዲስ መቃብር ቀበሩት፤ (ዮሐ 19፥41)፡፡ ጥንተ ስቅለት የበዓሉ መታሰቢያ መጋቢት 27 ቀን ነው፡፡ (ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ሙሉውን የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 18 እና 19ን ያንብቡ)፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ከሁላችን ጋር ሁን አሜን!         ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!   ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ መድበለ ታሪክ        • ┈┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈┈ •
Показати все...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ በዓለ ስቅለት በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ 🌺🌻🌺🌻🌺🌻🌺🌻🌺🌻🌺🌻🌺🌻🌺        🕯መጋቢት ፳፯(27) ተዝካረ ስቅለቱ ለመድኃኔዓለም    ጥንተ ስቅለቱ የመታሰቢያ በዓል በሚከበርበት መጋቢት 27 ቀን አምላክ ስለሰው ልጆች ፍቅር ሲል ጸዋትወ መከራዎችን የተቀበለበትና በሞቱ ሞትን ሽሮ የአዳምን ዘር ሁሉ ከሞት ሞት ያዳነበት፣ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅሩን የገለጠበት፣ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙም ዓለምን ነፃ ያወጣበት፣ ሕማማተ መስቀልን በትዕግሥት ተቀብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በገዛ ፈቃዱ የለየበት የስቅለቱና የሞቱ መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ጥንተ ስቅለት ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ በቀራንዮ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሕይወቱን ለዓለም ቤዛ አድርጎ የሰጠው መጋቢት 27 ቀን በ33 ዓ.ም ነው፡፡ ይህም ሐሙስ የሐዋርያቱን እግር አጥቦ ራት ከበሉ በኋላ በአምስት ሰዓት ስለራሱ በጌቴሴማኒ ጸለየ፤ ከዚህም በኋላ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት በአይሁድ እጅ ተያዘ፡፡ አይሁድም ልብሱን ገፈው አስረው እያዳፉና እየገፉ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሐና ወሰዱት፡፡ ሊቀ ካህናቱ ሐና ምን እያልክ ታስተምራለህ ብሎ ኢየሱስ ክርስቶስን ሲጠይቀው በስውር የተናገርኩት የለም የሰሙትን ጠይቅ አለው፡፡ አንዱ ጭፍራ (በወንጌል አንደምታ መጻጉዕ ተብሎ ተጠቅሷል)) ‹‹ሊቀ ካህናቱን እንዲህ ትመልስለታለህ?›› ብሎ የጌታን ፊት በጥፊ መታው፤ ጌታም ‹‹ክፉ ከተናገርኩ መስክርብኝ እንጂ እንዴት በዳኛ ፊት ትመታኛለህ?›› አለው፤ (ዮሐ 18፥19-23)።    ከዚያ በኋላ ደግሞ ከሌሊቱ በስምንት ሰዓት ከሐና ወደ ቀያፋ ወሰዱት፡፡ ከዮሐንስ ወንጌላዊው በቀር ሐዋርያት ጥለውት ተበተኑ፤ ጴጥሮስም ከሩቅ እየተከተለ ገብቶ እሳት ከሚሞቁት ጋር ተቀምጦ ነበር፡፡ ከካህናቱ አለቆች ገረዶች አንዲቱ ጴጥሮስን እሳት ሲሞቅ አየችው፤ ‹‹አንተም ከገሊላዊው ከኢየሱስ ጋር ነበርክ›› አለችው፡፡ ጴጥሮስም ደንግጦ አንቺ የምትይውን አላውቀውም ብሎ ካደ፤ ከቅጥሩም ወደ ውጭ ወጣ ዶሮም ጮኸ፡፡ ዳግመኛ ሌላይቱ ገረድ አየችው፤ ከዚያ ቁመው ላሉት ‹‹ይህም ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበር›› አለቻቸው፤ ሁለተኛ ካደ፡፡ ጥቂትም ቆይቶ ቆመው ያሉት ጴጥሮስን ‹‹አንተም በእውነት ከእነርሱ ወገን ገሊላዊ ነህ፤ አነጋገርህም ያስታውቃል›› አሉት፡፡ የምትሉትን ሰው አላውቀውም እያለ ይምል ይገዘት ጀመር፡፡ ያን ጊዜም ዶሮ ጮኸ፤ ጌታ ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ብሎት ነበርና ዘወር ብሎ አየው፡፡ ጴጥሮስም ወደ ውጭ ወጥቶ አለቀሰ፤ (ማር 14፥66-72 ፣ ሉቃ 22፥54-61 ፣ ማቴ 26፥69-75 ፣ ዮሐ 18፥25-27)።    አይሁድም በጥዋት ወደ ጲላጦስ ወስደው ሊያሰቅሉት መከሩ፤ ይሁዳም ሲወስዱት አይቶ ተጸጸተ፡፡ እርሱ በተአምራት ይድናል እኔ ገንዘቤን ይዤ እቀራለሁ ብሎ ነበርና እንደማይለቁት ተረድቶ ሔዶ ገንዘባችሁን እንኩ አላቸው፡፡ እነርሱም የምንሻውን ሰጥተኸናል የምትሻውን ወስደሃል አሉት፡፡ ብሩን በቤተ መቅደስ በትኖ ሊታነቅ ሔዶ ከዛፍ ተሰቀለ፤ ዘፏም ‹‹እንደ ወንድምህ ጴጥሮስ ንስሐ ግባ›› ብትለው ከሌላ ዛፍ ተሰቀለና ገመዱ ተበጥሶ በመውደቁ ሰውነቱ ቆስሎ ከዐርባ ቀን በኋላ ሞተ፡፡   ጌታ ተይዞ ወደ ጲላጦስ ሲገባ ከበር ቁመው የነበሩ ጦሮቹ ሰገዱለት፤ በሌሎች ኃያላን ቢያስይዟቸውም አሸንፈው ሰገዱለት፡፡ ጲላጦስ ይህን ሲያይ ፈራና በውኑ የአይሁድ ንጉሥ ነህን? አለው፤ ጌታም ‹‹አንተ አልክ›› አለው፤ (ዮሐ 18፥37)፡፡ አይሁድ ግን ሰንበትን የሻረ፣ ኦሪትን ያቃለለ፣ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ያደረገና ለቄሳር ግብር የከለከለ ዐላዊ ነው እንጂ ንጉሥ አይደለም አሉ፡፡ ጌታ ዝም ሲል ጲላጦስ ይህን ያህል ሲያሳጡህ  አትመልስም ልገድልህም ላድንህም ሥልጣን አለኝ አለው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስም ‹‹ከሰማይ ካልተሰጠህ በቀር ምንም ምን በእኔ ላይ ሥልጣን የለህም›› (ዮሐ19፥11) ይህን ተናግሮ ዝም አለ፡፡ ይህን በተናገርክበት እስኪ ንገረኝ አለው፤ መንግሥቴስ በዚህ ምድር ብትሆን ኖሮ ለአንተ ተላልፌ ባልተሰጠሁ ነበር፤ አዳምን ከነልጅ ልጆቹ ወደ ገነት ልመልሰው ከሰማይ ወርጄ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልጄ በዚህ ምድር ወንጌልን እያስተማርኩ ሳለሁ አይሁድ ይዘው ለአንተ አቅርበውኛል ብሎ ሁሉን ነገረው፡፡ ጲላጦስም ይህን ሰው በደል አላገኘሁበትም ብሎ ልልቀቀው? አላቸው፡፡ እነርሱም  ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ ሲያውክ የነበረ ነው አሉ፡፡ ጲላጦስም ከገሊላ ሲሉ ሰምቶ ወደ ገሊላው ገዥ ወደ ሄሮድስ ላከው፡፡ ሄሮድስም ዝናውን እየሰማ ሊያየው ይወድ ነበርና ሲያየው ደስ አለው፡፡ ነገር ግን ቢጠይቀው የማይመልስለት ሆነ፡፡ ሄሮድስም ይህስ ቢቻል ሁለት ሞት ይገባዋል ብሎ አስገርፎ ቀይ ግምጃ አልብሶ ወደ ጲላጦስ ሰደደው፡፡ ጲላጦስ ግን ብዙ እንዳስገረፈው አውቆ አዘነ፡፡ አይሁድንም ሦሰት ጊዜ አመጣችሁት በደሉ ምንድን ነው? አላቸው፡፡ ገርፌ ልልቀቀው በርባንን ልስቀለው አላቸው፡፡ አይሁድ ግን ሕዝቡን አስተባብረው ስቀለው ስቀለው እያሉ ጮሁ፡፡   ያን ጊዜ የጲላጦስ ሚስት አብሮቅላ ደብዳቤ ላከችበት፤ ዲዳ የነበሩ ልጆቹ መካራና ዶርታ አንደበታቸው ተፈቶ የሆነውን ነግረዋት ነበርና ይህን አይቶ ሊፈታው ፈለገ፡፡ ‹‹ይህን ብትፈታው የቄሳር ወዳጅ አይደለህም›› አሉት፤ (ዮሐ 19፥12)፡፡ ስለዚህ ውኃ በኩስኩስት አስመጥቶ ‹‹እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ›› ብሎ እጁን ታጠበ፤ እነርሱ ግን ደሙ በእኛና በልጅ ልጆቻችን ይሁን ብለው ተቀብለው 6666 ጊዜ ዐጥንቱ እንደ በረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ገርፈውታል፡፡ የሾክ አክሊል ጎንጉነው በራሱ ደፉበት፤ ራሱንም በዘንግ መቱት፡፡ ቁመቱ ሰባት ክንድ ከስንዝር ወርዱ ሦስት ክንድ ከስንዝር አድርገው መስቀል ሠርተው አሸክመው ከሊጦስጥራ ወደ ቀራንዮ ወሰዱት፤ ዓርብ ስድስት ሰዓት ላይም ሰቀሉት፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ግራ ዳክርስን በቀኙ ደግሞ ጥጦስን አብረው ሰቅለዋል።   ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ ሰባት ተአምራት ተደርገዋል፡፡ እነዚህም፦ - ሦስቱ በሰማይ፦ ፀሐይ ጨለመ፣ ጨረቃ ደም ሆነ፣ ከዋክብት ረገፉ (ሚልክያስ 4፥2 ፣ ዘካ 14፥7 ፣ ኢዮ 3፥15 ፣ ኢሳ 13፥10 ያለው ትንቢት ተፈጸመ)፡፡ ‹‹ፀሐይን አጨለመ፤ ገዳዮቹን ግን አልተቀየመም›› እንዲል (ግብረ ሕማማት ዘዓርብ 6 ሰዓት) - አራቱ በምድር፦ መቃብራት ተከፈቱ፣ ሙታን ተነሡ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተከፈለ፣ ዓለታት ተሰነጣጠቁ (ኢዮ 2፥10 ያለው ትንቢት ተፈጸመ)፡፡   ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ መከራን የተቀበለ ሲሆን በጥቅሉ ዐሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል ተብለው ይጠራሉ፡፡ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰባቱን አጽርሐ መስቀል ተናግሮ ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ፡፡
Показати все...
እንኳን ለዐብይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት ለምኩራብ አደረሰን #መዝሙር ዘምኩራብ ሃሌ ሉያ /5/ ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሀይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚአ ውእቱ ለሠንበት ወልደ እጓለ እምህያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሰጾሙ ያርምሙ አንከሩ ምሕሮቶ ሞገሰ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ። *ትርጉም*:- ኢየሱስ ከአይሁድ ምኩራብ ገብቶ ከመስዕዋት ይልቅ ምህረትን እወዳለሁ የሰንበት ጌታዋ የምህረት መገኛዋ እኔ ነኝ የአብ አንድያ ልጅ የሰንበት ጌታ ነው የአባቴን ቤት የሽፍታ መጠጊያ አታድርጉት ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል እያለ የሃይማኖት ቃል አስተማራቸው በምኩራባቸውም ገብቶ ፀጥ ይሉ ዘንድ ገሰጻቸው ከቃሉ ግርማ ካነጋገሩ ጣዕም ካንደበቱ ቅልጥፍና የተነሳ በትምህርቱ ተገረሙ ።
Показати все...
ቅድስት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት የቅድስና ባለቤት የሆነው እርሱ እግዚአብሔር አምላክ ነው። እቀደስ አይል ቅዱስ፣ እባረክ አይል ቡሩክ ነው። በእርሱ የባሕርይ ቅድስና እኛን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ቡሩክ ሆኖ ባረከን፣ ቅዱስ ሆኖ ቀደሰን፣ሕያው ሆኖ ሕያዋን አደረገን። የጸጋ ቅድስናንም ከእርሱ አገኘን። ቅድስናው የተለየ፣ የከበረ፣ የሚመሰገን፣ የሚሰጥ/የሚያድል፣ የሚያነጻ፣ የሚባርክ እናም የሚያስተሰርይ ስለሆነ እንከን፣ ጉድለት የሌለበት ምሉዕ ነው። ለባለሟሎቹ ቢሰጠው የማይጎድል፣ ተከፍሎ የሌለበት ቅድስና ሆኖ እኛም የቅድስና በጸጋ ተካፋይ ሆነናል። የተሰጠንን ቅድስና ገንዘብ እንድናደርግ እና እንድንጠቀምበት ደግሞ በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በምጽዋትና በሌሎች በጎ ምግባራት መትጋት ይገባናል። ‹‹እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ›› እንዲል፡፡ (ዘፍ.፪፥፫፣ ዘሌ.፲፱፥፪) የት መሄድ እንዳለብንም በግልጽ ልበ አምላክ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለ ትምህርትህና ስለ እውነትህ ስምህን አመሰግናለሁ፤ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና›› ይላል። (መዝ.፻፴፯÷፪) የተቀደሰን መሥዋዕት በተቀደሰ ቦታ እንፈጽማለን። መቼ ቢሉ፣ በሰንበት፣ በበዓላት በማኅበረ ዐቢይ/ክርስቲያኖች በሚሰበሰቡበት፣ ስመ እግዚአብሔር በሚጠራበት፣ ታቦት ባለበት፣ እግረ እግዚአብሔር በቆመበት ቅዱስ ስሙን ከፍ ከፍ በማድረግ ቅድስናን ገንዘብ እናደርጋለን። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ለዐቢይ ጾም ሁለተኛው እሑድ በአዘጋጀው ምስጋና አማካኝነት ዕለቱ ‹‹ቅድስት›› የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ትርጉሙም ‹‹የተለየች፣ የተመረጠች፣ የከበረች›› ማለት ነው። (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ገጽ ፯፻፹፬) ቅድስት የሚለው ቃል ዕለቱ ‹‹ቅድስት›› ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት እንዲሁም ስለ እግዚአብሔር አምላክ ፍጹም ቅድስና የሚያወሳ በመሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ፍጥረታቱ የእርሱን ስም በማመስገን ይኖሩ ዘንድ ለቅድስና ሕይወት ፈጥሯቸዋልና በሰንበት እሑድ ክርስቲያኖች የቅድስና ተግባራትን ከሌላው ቀን አብዝተው ይፈጽማሉ፡፡ ዕለት ከተግባር፣ ስም ከክብር የተባበረባት ክብርት ሰንበት ቅድስት ስለሆነች ቅዱስ ያሬድ “ቅድስት” ብሎ ጠራት። ይኸውም የምትቀድስ፣ ከብራ የምታከብረን፣ አክብረናት የምንከብርባት በመሆኗ ነው። ለዚህም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓ “ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ፤ ሀቡ ስብሐተ ለስሙ፤ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ፤ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት ኀበ ፃፄ ኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሰራቂ፤ ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ጸልዩ ኀበ ሀሎ ክርስቶስ” ትርጉም፦ “ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ሥራውንም ለአሕዛብ ንገሯቸው፤ ለስሙም ምስጋናን አቅርቡ ሰንበትን አክብሩ፤ እውነትንም አድርጉ፤ ብል የማያበላሸው ሌባም የማያገኘው በሰማያት ያለ መዝገብን ለእናንተ ሰብስቡ፤ ተዘጋጅታችሁም ተቀመጡ፤ ክርስቶስ ወዳለበት ወደ ላይ አስቡ፡፡“ ስለዚህ ሰው ሰንበትን አክብሮ ጾሞ ጸልዮ፣ ቅድስናን ጠብቆ መኖር እንዲችል እግዚአብሔር የፍቅሩ መገለጫ የሆኑ ትእዛዛቱ ይነግሩናል። ቅዱስ ያሬድም ወቅቱን “ቅድስት” ብሎ ሲሰይም፦ ፩. የአርባ ቀን ጾም መጀመሪያ በመሆኑ፦ ዕለቱ ከዐቢይ ጾም ቀናት ውስጥ አርባው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም መጀመሪያ ስለሆነች፣ ፪. ቅድስት ሰንበት ላይ በመዋሉ፣ እንግዲህ “የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ” ተብሏል፡፡ (ዘፀ.፳፥፰) የሰንበትን ቀን አስቀድሞ የቀደሰ የባረከ ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና፡፡” (ዘፍ.፪፥፫) “ከምእመናን ወገን አንድስ እንኳን በእሑድ ቀን ለገንዘብ መትጋት፣ ገንዘቤን አምጣ ብሎ መጣላት እና ዋስ መያዝ አይገባውም። ሁሉም ምእመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን በንጽሕና በትሕትና ሆነው። ዳኛ ግብሬን፣ አበዳሪ ብድሬን፣ ኤጲስ ቆጶስ ዐሥራት በኵራት፣ ነጋ ድራስ ቀረጥ አምጡ ይሉናል ብለው ሳይፈሩ ይምጡ። ፫. ወቅቱ ወርኃ ጾም በመሆኑ፦ ምእመናን ይህንን ወቅት በጾም፣ በጸሎት፣ በእንባ፣ በስግደት፣ በአርምሞ፣ በመልካም ሥራ ቅድስናን የምናገኝበት፣ ጊዜው ሰው ወደ እግዚአብሔር አብዝቶ የሚተጋበት ወቅት በመሆኑ፣ ለእግዚአብሔር የሚገባ ነገር ለማድረግ የነገር ሁሉ መጀመሪያ፣ ለመልካም ነገር መነሻው በቅድስና በንጹሕ ልቡና መቅረብ ስለሆነ ቅድስት ብሏታል። “እስመ ጾም እማ ለጸሎት ወእኅታ ለአርምሞ ወነቅዓ ለአንብዕ መቅድመ ኩሉ ግብር ሠናይት፤ ጾም ማለት የጸሎት እናት፣ የትሕትና እኅት፣ የእንባ ምንጭ፣የመልካም ሥራ ሁሉ መጀመሪያ ናት” እንዳለው ቅዱስ ያሬድ። ”ጾምን ቀድሱ፤ ጉባኤውንም ዐውጁ” የተባልን የተሰጠንን የጸጋ ቅድስና በእጃችን ላይ መኖሩን አመላካች ቃል ነው። (ኢዩ.፩፥፲፬) ፬. የወንጌል ትእዛዝ በመሆኑ ዕለቱን ተጠቅሞ ዓለምን አስተምሮበታል። “ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ” ትርጉም፡- “ይህች ዕለት እግዚአብሔር የሠራት ቀን ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።” (መዝ.፻፲፯፥፳፬) ቅዱስ ዮሐንስም በራእዩ ሰንበት የጌታ ቀን ስለመሆኗ እንዲህ ይላል፤ “በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፡፡” (ራእ. ፩፥፲) ሊቃውንቱ በፍትሐ ነገሥት “ተጋብኡ ኵሎ ዕለት ኀበ ቤተ ክርስቲያን ወፈድፋደሰ በዕለተ ሰንበት ወበበዓላት ወበዕለተ ትንሣኤ ዘውእቱ ዕለተ እሑድ” ትርጉም፦ “ሁልጊዜ በቤተ ክርስቲያን ተሰብሰቡ፤ ይልቁንም በዕለተ እሑድ፣ በዕለተ ቀዳሚት፣ በጌታ በዓላት ወደ ቤተ ክርስቲያን ተሰብሰቡ” በማለት አዘውናል፡፡ (ፍትሐ ነገሥት፣ ገጽ ፪፶፬) በትጋት ጾመን፣ ጸልየን ርስቱን እንድንወርስ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ፤ የቅዱሳን በረከት ይጠብቀን። የዕለቱ መዝሙር (ከጾመ ድጓ)፦ግነዩ ለእግዚአብሔር ምንባባት፡ (፩ኛ.ተሰ.፬÷፩-፲፫)፣ (፩ኛጴጥ.፩÷፲፫-ፍጻ.፣ሐዋ.፲÷፲፯-፴ ምስባክ “እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ:: አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ፣ ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ፈጠረ፡፡ እምነትና በጎነት በፊቱ፣ ቅድስናና የክብር ገናናነት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው፡፡” (መዝ.፺፭÷፭) ወንጌል (ማቴ.፮÷፲፮-፳፭) ቅዳሴ: ዘኤጲፋንዮስ ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
Показати все...
የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ከደጃቸው እየከፋኝ ብቀርም ሀገራችን ሰላም ሲሆን እናከብረዋለን ነገር ግን በሃሳብ ከእናንተ ጋር ነበርኩኝ።በደ3ጋሜ እንኳን አደረሳችሁ
Показати все...
ኦ ገብረሕይወት አኮ ዘተሴሰይከ ኅብስተ ምድራዊ ኅብስተ ፣ አላ ኅብስተ ሰማያዊ እመሰማየ ሰማያት። እንኳን ለአባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ።
Показати все...
Показати все...
የመዝሙር ምርቃት ማስታወቂያ

"መዝሙር ምርቃት ማስታወቂያ" ZwT||ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video)