cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ዘማሪ የአብስራ ጎራድ ቲዩብ

ይህ የዘማሪ የአብስራ ጎራድ ቴሌግራም ቻናል ነው ።በቻናላችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን መዝሙሮች ስነፅሁፎች ስብከትና ትምህርቶች እንድሁም ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች ይሰጡበታል።ሊንኩን በመጫን ጆይን እያደረጉ ይቀላቀሉን

Більше
Рекламні дописи
276
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

⛪️ አንዲት ናት ⛪️ አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት(፪) ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት ⛪️ አዲስ አይደለንም ለመከራው ጉዞ የወደቀ አናውቅም መስቀል ተመርኩዞ አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋር ነውና በርቱ ክርስቲያኖች በእውነት ጎዳና(፪) አዝ= = = = = የአበውን እምነት በአላውያን ፊት ሰምተን ስላደግን ከገድላት አንደበት መስዋዕትም ቀርቧል ከፊታችን እውነት ስትገፋ አይችልም ልባችን(፪) አዝ= = = = = አልጠፋችምና በእሳት ተፈትና ይህን እናውቃለን በገሀድ ነውና መሰደድ መቃጠል ሁሉም ከጊዜው ነው ለእውነት ከሆነ ሞትም ክብራችን ነው(፪) አዝ= = = = = ከተዋሕዶ ጋር ስላለ መንፈሱ እውነትን ለማጥፋት መቅደስ አታፍርሱ በግፍ ቢገደሉም ክርስቲያኖች ሁሉ ኦርቶዶክስ አትጠፋም ተነግሯል በቃሉ(፪) አዝ= = = = = ታሪክን ያኖረች ፊደላትን ቀርጻ ቅርስን ያወረሰች ገዳማት አንጻ እንግዳ ተቀባይ መንፈሳዊት እናት ይህንን አትዘንጉ ኦርቶዶስ አገር ናት ይህንን አትዘንጉ ተዋሕዶ አገር ናት
Показати все...
በቃ ከተደወለ ተደወለ የአድዋው ታሪክ ይደገማል ሰማእትነትም ይቀጥላል ሰለ ተዋህዶ ዝም ያልኩኝ እለትስ ማህተሜ ሳይሆን አንገቴ ይበጠስ ።።።።።።።።የአብ ነኝ እዮስያስ የተዋህዶ ልጅ
Показати все...
ቃና ዘገሊላ ምንድን ነው ? ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው ። እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አስተምሮ በጥምቀት በአል ማግስት ጥር12 ቀን የቃና ዘገሊላ በአል ይከበራል ።ይህ በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መፀሀፍ ቅዱሳዊ በዓል ነው ።በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስየገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆንቃና በተባለች ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው ። ቃና ዘገሊላ ምን ተፈፀመ ? ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና በዶኪማስ ቤት ሠርግ ላይ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋርተገኝቶ ነበር ። "ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዙእ ኢየሱስ" የጌታ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች "እዳለ ቅዱስ ዮሐንስ 2፥1 ። እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጃ ከወዳጃ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በሠርጉ ላይ ታድማ ነበር ። እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ሥርአት ሥላልሆነ፤በተጨማሪም ደግሞደቀመዛሙርቱን ከጌታ ጋር ታድመዋል ። ይህም መምህርን ጠርቶ ደቀ መዛሙርቱን መተው ሥርአት ሥላልሆነ ነው ። የሠርጉ ስነ ስርአት በሰመረ ባማረ ሁኔታ እየተከናወነ ሳለ ድንገት የወይን ጠጅ አለቀ ። አስተናባሪዎቹ በጭንቀት ባህር ስጥመው ምን እንደሚያደርጉ ግራ በገባቸው በጠበባቸው ጊዜ የችግር ጊዜ ደራሽ የሀዘን ጊዜ አፅናኝ የሆነችው የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅድስ ገብርኤል እንደተናገረ በፀጋ የተሞላች ናትና ሉቃ 1፥28 ማንም ሳይነግራት የልቦናቸውን ጭንቀት አይታ ጎዶላቸውን ተመልክታ ወደ ልጃ ወዳጃ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ "ወይንኬ አልቦሙ " "ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል" አለችው ። እርሱም መልሶ "አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም "አላት ።እመቤታችንም ለአገልጋዮቹ "የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ " አለቻቸው ። ጌታም በቦታው የነበሩትን ስድስት ጋኖች ውሀ ሞልተው እዲያመጡ አዘዛቸው ። ውሀውንም ወደ ወይን ለውጦ ለሊቀ ምርፋቃት( ለአሳዳሪው) እዲሰጡት አዘዘ ። አሳዳሪውም ወደ ወይን የተለወጠውን ውሀ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ ። ከወዴት እደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን " ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኅላ መናኛውን ያቀርባል አንተ ግን መልካሙን እሰከ አሁን አቆይተሀል"አለው ። ወይኑም በስው እጅ ያይደል በሰማያዊው አባት የተዝዘጋጀ ሰለነበር ጣፋጭ እና ልብን የሚያስደስት ነበር ። "አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ?" ይህንን የጌታችንን ንግግር ብዙዎች በዘመናችን ሣሣቱበት ይታያንል ። ክብር ይግባውና አምላካችን ይህንን የተናገረው እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም ። ስለሆነም ከመፀሐፍ ቅዱስ አንፃር ይህንን አረፍተ ነገር መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው ። በተናጥል ስንመለከት "አንቺ ሴት " ሴት የሚል ቃልየፆታ መጠሪያ ነውና በፆታዋ አክብሮ ሲጠራት ነው ። በሌላ በኩል ደግሞ ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር "ይህቺ አጥንት ከአጥንቴ ናት ስጋዋም ከስጋዬ ናት እርሳም ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል "ዘፍ.2፥23 በመሆኑም ጌታችን አንቺ ሴት ማለቱ ከስጋዋ ስጋ ከነፍሳ ነፍስ መንሳቱን ለማጠየቅ ነው ። " ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ?"የሚለውን አረፍተ ነገር የንቀት ሰለመስለን ብቻ የዳቦ መልክ የያዘ ድንጋይ ፤ ዳቦ ነው እደማይባል የንቀት ንግግር ነው ልንል አይገባም ። ጌታም እዲህ ሲል ውሀውን ወይን እድርግላቸው ብትይኝ አላደርግም እልሽ ዘንድ ከአንቺ ጋር ምን ፀብ አለኝ ማለቱ ነው። ድንግል ማርያም አማላጅነት በገሊላ ቃና ጌታችን መድሀኒታችን ኢየ�ሱስ ክርስቶስ በሠርግ ቤት ሳለ የወይኑን ማለቅ የማይመለከት ሆኖ አይደለም ። ነገር ግን የእናቱን የድንግል ምርይምን አማላጅነት ሊገልጥ ስለ ወይኑ ማለቅ እስክትነግረው ድረ�ስ አንዳች ነገር አላደረገም ። ኅላ ግን የጭንቅ አማላጅ ድንግል ማርይም ስለ ወይኑ አስብች ልጃ ወዳጃን ለመነች ። እር�ሱም የእናቱን ልመና ተቀብሎተአምራቱን ፈፀመ ። እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሳይነግራት በልብ ያለውን የምታቅ የምትመረምር እናት ናትና የሰርጉ አስተባባሪዎች ይህ ጎደለ ሳይላት የልቦናቸውን ሀዘን ተመልክታ ከልጃ ከወዳጃ አማልዳ የጎደላቸውን ሞልታለች ። ያሰጨነቃቸውንም አርቃለች በችግራቸውም ደርሳላቸዋለች ። ታዲያ ሳይነግራት የልቦናን አይታ ከማለደች ስሟን ጠርተው ለሚለምኗትማ እንዴት አብልጣ አታማልድ ? ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤቷን በረከቷንያሳድርብን አሜን !!! join @ortodoxslijoch
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሥላሴ ትትረመም🌹 ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር (፪) ይገባል ምስጋና ይገባል ውዳሴ ሁሉን ለፈጠረ ለቅድስት ሥላሴ ከዘመናት በፊት ቀድሞ የነበረ ፍጥረትን በሙሉ ለክብሩ ፈጠረ አዝ ልበል ሃሌ ሉያ ኪሩቤልን ልምሰል በእግረ ምስጋና ያሬድን ልከተል ላቅርብ ምስጋናውን ዘምስለ ሱራፌል ውዳሴ ምስጋና ነውና ለልዑል አዝ በስም ሦስት ሲሆን እንዲሁም በአካል በግብርም ሦስት ነው ያለመቀላቀል ፍጥረትን በመፍጠር በአምላክነት በባሕሪይ እና ደግሞም በመንግሥት አንድ አምላክ ነው እንጂ አይባልም ሦስት አዝ በኪሩቤል ጀርባ ዙፋኑን ዘርግቶ ክብሩን ጌትነቱን ከፍጥረት ለይቶ ይኖራል ዘለዓለም በመንግሥቱ ጸንቶ(፪) አዝ ይመስክር ዮርዳኖስ ይናገር ታቦር የአምላክ ጌትነት የሥላሴን ክብር ይኸው በዮርዳኖስ ወልድ ተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ታየ አብም ቃሉን ሰጠ
Показати все...
ጥር 1 ቀን የቀዳሚ ሰማዕት የሊቀ ዲያቆናት የ"ቅዱስ እስጢፋኖስ" የእረፍት ቀኑ ነው፤ የዚህ ሰማዕት ልደቱም በዚሁ ቀን ነው። በስሙ በታነጹለት አብያተ ክርስቲያናት ታቦተ ህጉ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፤ ዝነኛው ገዳሙ ሃይቅ እስጢፋኖስ በመዲናችን አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚገኘው ደብሩ ከቀደምቶቹ አንዱ ነው። እስጢፋኖስ ማለት ወደብ ጸጥታ ማለት ሲሆን ቁጥሩ ከ 72ቱ አርድዕት ነው፤ ለምን ቀዳሚ ሰማዕት ተባለ ከሱ በፊት ሰማዕታት የሉም ነበርን ? ቢሉ መኖርስ አሉ የእርሱ ግን ቀዳሚ መባሉ ከጌታችን እርገት በኃላ ስለ ጌታችን መውረድ መወለድ መስክሮ የሞተ የመጀመሪያው እርሱ ስለሆነ ነው፤ እሺ ለምንስ ሊቀ ዲያቆናት ተባለ ቢሉ በሐዋርያት እጅ ከተሾሙት ሰባቱ ዲያቆናት ውስጥ የሁሉም አለቃ እርሱ ስለሆነ ነው ሐዋ 6 ፤ 5። መጽሐፍ ቅዱስ ስለእስጢፋኖስ እንዲህ ሲል በእውነት መሰከረ "እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበረ...ፊቱም የመልአክ ፊት ይመስል ነበር ፤ ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም ሐዋ 6፤ 8 ። እህሳ አይሀድ አማጽያን መልስ መስጠት ቢያቅታቸው ድንጋይ አነሱ ልብ አናቱን እያሉ ወገሩት፤ ቀና ብሎ ቢመለከት ቅድስት ስላሴን አየ፤ አቤቱ ይህን ኃጢያት አትቁጠርባቸው ይቅር በላቸው እያለ ነፍሱን ሰጠ። ሐዋ 7፤ 60፤ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወለደው በኢየሩሳሌም በምትገኝ ሐኖስ በተባለች ቦታ ነው:: አባቱ ስምዖን ሲባል እናቱ ደግሞ ሐና ትባላለች ነገዱ ከነገደ ብንያም ነው :: የኦሪትን ሕግና ሥርዓት ከኦሪቱ ምሁር ከገማልያል ተምሯል::በሐዋርያት ሥራ ምዕ. 6 እንደምናነበው ሕዝቡን በማዕድ ያገለግሉ ዘንድ ሰባት ዲያቆናት ተመርጠዋል ከእነዚህ መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ሲሆን ለስድስቱ ዲያቆናት ደግሞ አለቃ( ሊቀ ዲያቆን) ሆኖ ተሹሟል ይህም የሆነው በጥቅምት 17 ነው :: ቅዱስ እስጢፋኖስ በማዕድ አገልግሎት ሕዝቡን ከማገልገሉ በተጨማሪ ወንጌልን ይሰብክ ነበር ተአምራትን የማድረግ ጸጋም ተሰጥቶት ነበር በዚህም አገልግሎቱ ብዙዎችን ወደክርስትና መልሷል:: በዚህም አይሁድ በቅናት ተነሳስተው በሐሰት ከሰሱት ከከተማውም ወደ ውጭ አውጥተው ቄዳር በተባለ ቦታ በድንጋይ ወገሩት በሚወግሩትም ጊዜ ሰማያት ተከፍተው ምሥጢረ ሥላሴን (እግዚአብሔርን በሦስትነቱ ) ተመለከተ ኢየሱስ ክርስቶስንም በአብ ቀኝ ተቀምጦ አየ ለሚወግሩትም ሰዎች ከአምላኩ እንዲህ በማለት ምሕረትን ለመነ "ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው "በመጨረሻም "ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል" ብሎ ነፍሱን ሰጠ ::የሐዋርያት ሥራ ምዕ 7 በተወለደ በ 30 ዓመቱ በ35 ዓ.ም በሰማዕትነት ዐረፈ:: ከሰማዕቱ በረከት ያሳትፈን።
Показати все...
ትምክህተ ዘመድነ(3) ማርያም የአባ ህርያቆስ ድርሳነ ቅዳሴው የያሬድ ውብዜማ የኤፍሬም ውዳሴው የሩሁባን ቀለብ የመንገደኞች ስንቅ ብርታት ሁኝን ድንግል ዝለን እንዳንወድቅ በድቅድቁ አለም በጨለማ ሳለን በአንቺ በእናታችን ብርሀን ወጣልን በኃጢአት በሽታ ለታመመው አለም መድኃኒት የሰጥን ከአንቺ በቀር የለም በጨነቀን ጊዜ አንቺን ስንጠራ አማላጅቱ ሆይ ነይልን አደራ ርህርተ ህሊና አዛኝቷ እመቤት ግቢ ከቤታችን ነይ በረድኤት የመመኪያችን ዘውድ የቤታችን ፋና በፈተና ጊዜ እርጅን እንድንፀና ድንግል ሆይ በምልጃሽ ከቤታችን ግቢ ምህረት አንድናገኝ ለልጅሽ አሳስቢ ትውልድ ሁሉ አንቺን ያመሰግኑሻል አምባ መጠጊያችን ፅዮን ሆይ ይሉሻል እውነተኛ ፀሐይ ካንቺ ሲወጣልን በአንቺ በእናታችን ጨላማው ጠፋልን
Показати все...
ሼር ላይክ ሰብስክራይብ ኮሜንት ያድርጉ ያስደርጉም በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው አድሱ ዝማሬ ተለቀቀ ትምክህተ ዘመድነ በዘማሪ የአብስራ ጎራድ https://youtube.com/watch?v=U1NdABJf77A&feature=share
Показати все...
በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው አድሱ ዝማሬ ተለቀቀ ትምክህተ ዘመድነ በዘማሪ የአብስራ ጎራድ

በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው አድሱ ዝማሬ ተለቀቀ ትምክህተ ዘመድነ በዘማሪ የአብስራ ጎራድ። ይህ ህጋዊው የዘማሪ የአብስራ ጎራድ የYouTube ቻናል ሲሆን በቻናላችን መዝሙራት፣ ስብከቶች፣ እንዲሁም በርካታ መንፈሳዊ ዝግጅቶች ይለቀቁበታል ቻናላችን Subscribe Like Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

አለቀብኝ ብዬ እጄ ባዶ ሆነ ብዬ ሳዝን የሚሞላው አለ ባዶ ጎተራዬን በፍሬ የሞላው እግዚአብሔር ከአባትም በላይ ነው እግዚአብሔር ከአባትም በላይ ነው       አዝ = = = = = የማይጥል የማይከዳ የሚያዝን የሚረዳ ፍቅር ነው የማይጠላ እግዚአብሔር ነው ከሌላ/2/ አዝ = = = = ጉልበታም ነው ክንዱ ጽኑ ድንቅ የሚያደርግ በየቀኑ ይሸከማል ነጋ ጠባ አይቆረቁር የእርሱ ጀርባ/2/        አዝ = = = = = በእፈፍት ውሃ እየመራኝ በለምለም መስክ አሰማራኝ አልጨነቅ ለሚመጣው የኔ ጉዳይ ከሰማይ ነው /2/       አዝ = = == = = በእርሱ ሞልቷል ማስሮዬ አንዳች አይጎድል ማድጋዬ የእርሱ ቁጥር ቀኑ ሲደርስ ያደርገዋል ሁሉን አዲስ/2/        አዝ = = = = = በእርሱ ሞልቷል ማሰሮዬ አንዳችን አይጎድል ማድጋዬ የእርሱ ቁጥር ቀኑ ሲደርስ ያደርገዋል ሁሉን አዲስ/2/ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE 💚 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💚 💛 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💛 💖 •✥• @Z_TEWODROS •✥• 💖 ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
Показати все...
አዲስ_ዝማሬ_አለቀብኝ_ብዬ_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ_mahtot_ማኅቶት_ቲዩብ_Mahtot_T.m4a5.73 MB
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.