cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

😅😅 Dj ሳቅ በሳቅ 😅😁

🧨ቀልዶች😁🤣 🧨ቁም ነገሮች 😣🤔 🧨 ትኩስ እና አዳዲስ መረጃዎች 🧨 አስቂኝ ፎቶዎች 🧨 የድሮ ፎቶዎች 🧨ለእርሶ ጠቃሚ ነገሮች የሚያገኙበት ቦታ ነው 🧨አዳዲስ እና ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና vocal cross &admin ex @keymax_bot @keymax2_bot

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
346
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

#በዓለ_አስተርእዮ (ጥር 21 የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት) ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በስድሳ አራት አመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ” ትርጉሙ ሞት ለማናኛቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡ በማለት አደነቀ፡፡ በመሆኑም በዓሉ የወላዲተ አምላክ በዓለ ዕረፍት ከመሆኑ የተነሳ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ በየዓመቱ ይከበራል የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉ ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 እሁድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላዕክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት፡፡ ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁ አለችው፡፡ በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት፡፡ እኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፡፡ ቅድስት ሥጋዋን ከቅድስት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀ መዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው ሐዋርያት ክብርት ስጋዋን ይዘወት ወደ ጌሰማኒ ሲወስዷት አይሁዳውያን አይተው "ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖረዋል አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለም ብሎ ኑ እናቃጥላት" ተባባሉ፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ታውፋንያ ዘሎ ያልጋውን ሸንኮር ያዘ፡፡ የታዘዘው መላእክት መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት ድኖለታል፡፡ ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ ከመካከላቸው ነጥቆ በገነት እጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል በኋላ ሐዋርያቱ ዮሐንስን ሲያገኙት፡- “እመቤታችን እንደምን ሆነች?” አሉት፡፡ እርሱም “በገነት በዕጸ ሕይወት ሥር ዐርፋለች” አላቸው፡፡ የቀሩት ሐዋርያት “ዮሐንስ ያን ድንቅ የእግዚአብሔርን ሥራ አይቶ እኛስ ሳናይ እንዴት እንቀራለን?! አቤቱ ለእኛም ቸርነትህን አድርግልን” ብለው በነሐሴ መባቻ በአንድነት ሆነው ወደ ፈጣሪያቸው የሚቀርብ የአንድ ሳምንት ጾምና ጸሎት ጀመሩ፡፡ በሁለተኛው ሱባዔ ማብቂያ ዕለት ነሐሴ 14 ቀን እሑድ የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ መልአኩ ከገነት አምጥቶ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም ልመናቸው ስለ ተፈጸመላቸው ፈጣሪያቸውን በጸሎት አመስግነው በዚያችው ዕለተ እሑድ ቅዱስ ሥጋዋን ወስደው ቀብረውታል፡፡ እርሷም በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ማክሰኞ ተነሥታለች፡፡ ትንሣኤዋ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ (እንደ ልጇ ትንሣኤ)” ያሰኘው ይህ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይታ የመነሣቷ እውነታ ነው በዓሉ እግዚአብሔር ወልድ በሰውነት ተወልዶና ማንነቱ በይፋ ታውቆ በተገለጠበት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር የ“አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል፡፡ የአዛኚቱ እናታችን አማለጅነትና በረከት አይለየን፡፡ Via @kokuha_haymanot
Показати все...
"…ለወንድሜ ምህረተአብ አሰፋ ‼ "…በአሁን ሰዓት በምሥራቅ ወለጋ በአኖ ወረዳ፣ በስሬ ወረዳ፣ በባኮ ወረዳ ከአርባ በላይ የወሎ ሙስሊም ዐማሮች መታረዳቸው፣ በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለው በመጠለያ እንደሚገኙ፣ ወደ ወለጋ የሚሄደው ዋና መንገድም በኦነግ ተቆርጦ በጭንቅ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ሰቆቃ እየሰማን ድንገት አንተን ለምን አጀንዳ ሊያደርጉህ እንደፈለጉ ይገባናል። ጃዋርንና እስክንድርን አዋክበው ወደ ዘብጥያ ያወረዱ የአንተን ቤት ከበው የሚቆሙት ማንን ፈርተው ነው? አንተ በቤትህ የለህ፣ እና ቤትህ ለምን ይከበባል? "…የፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት ዐቢይ አሕመድ በባህርዳር፣ ብልጽግና ደግሞ በሸገር ሙግት ላይ ናቸው። ይሄን ዜና ለማፈን ለምን የአንተ የተከበብኩ ዜና አስፈለገ? "…በእነ ደረጄ ሃብተወልድ፣ ስዩም ተሾመ የሚመራው በሸገር ብልጽግና የሴቶች ሊግ ላይክና ኮሜንት ሰጪነት የሚታጀበው የአቦይ ስብሃት ታመመ፣ ሆስፒታል ገባ ምንትስዬ፣ ቅብጥርስዬ የማደናገሪያ ወሬ ላይ የአንተ እንደ ጃዋር ተከብቤያለሁ ድረሱልኝ ዜና ምን ይጠቅማል? "…እንበልና የነገው የቦሌ መድኃኔዓለም ጉባኤ ህዝቡ ግልብጥ ብሎ ሄደ እንበል፣ አንተ "ተዋሕዶ ሃይማኖቴ፣ የጥንት ነሽ የእናትና አባቴ፣ ማዕተቤን አልበጥስም፣ ትኖራለች ለዘላለም፣ የሉም ሞተናል ሲሉን በዝተን አለን በእግዚአብሔር ሁሉን አልፈን፣ የሚለውን፣ ቸርነት ሰናይ ደግሞ ነይ ነይ እምዬ ማርያም ብሎ ይዘምራል፣ የተለመደው ጧፍ ይበራል፣ ይሰበካል፣ ይፎከራል። በቃ አለቀ ሲደክማችሁ ወደየቤታችሁ ትሄዳላችሁ። አሁን ይሄ አይደለም የሚያስፈልገው። ኳስ በመሬት፣ በስሜት ሳይሆን በስሌት፣ በመዋቅር ነው መንቀሳቀስ። እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ምህረት ውጣ ይሰሩህ። አትሟሟ። ይልቅ በሴራው ውስጥ እጅህ ከሌለ በቀር ውጣ። እንዲያውም በአንተ መታሰር ቤተክርስቲያን ታተርፋለች።
Показати все...
"…ለመምህር ምህረተ አብ የጻፍኩትን ጦማር በድምጽ አድርጌው ነው። ስሙት።
Показати все...
➕➕ የእርግዝና ምርመራ ➕➕ 🖲 ገብስ እና ስንዴ ላይ በመሽናት ነበር በድሮ ግዜ እርግዝና የሚታወቀው በሽንት ውስጥ የተነከረው የስንዴ ወይም የገብስ ፍሬ እድገት ካሳየ እርግዝናን ያመላክታል 🖲ከዚህ ውጪም የወር አበባዋን ያሳለፈች ሴት ከ እንቅልፍ በፊት በውሀ የተበጠበጠ ማር ከጠጣች በኋላ የሆድ መነፋት እና የሆድ ቁርጠት ካጋጠማት እርግዝና ተፈጥረዋል ተብሎ ይተነበይም ነበር 🖲በ ፈረንጆች በ 1928 አካባቢ ለመጀመሪያ ግዜ የተገኘው HCG በመባል የሚታወቀው የእርግዝና ሆርሞን አሁን ላይ ላለው የእርግዝና ምርመራ መሰረት ነው 🖲ይህ የእርግዝና ሆርሞን ከፅንስ ህዋሶች የሚመነጭ ሲሆን፣ ጥቅሙም ፣መሀፀን ለእርግዝና እንዲዘጋጅ የእንቁላል እጢን ለማነቃቃት ነው 🚩ይህ ሆርሞን ከእርግዝናም ውጪ የሚፈጠርበት የበሽታ አጋጣሚም አለ🚩 🖲እስካሁን ባለው ጥናት በእርግዝና ወቅት ይህ ሆርሞን ከለት ወደለት የሚያሳየው የመጠን መጨመር ፣ብቁ የእርግዝና መመርመሪያ እንዲሆን አድርጎታል 🖲ጥሩው ነገር ደሞ በሽንት የሚደረግ የእርግዝና ምርመራን በቤት ውስጥ ማረግ የሚቻል ሲሆን የወር አበባ ከቀረ በ አንድ ሳምንት ውስጥ እርግዝና መፈጠሩን ማሳወቅ ያስችላል 🖲በደም ምርመራ ሲሆን ደሞ፣ የወር አበባ ይመጣል ተብሎ ከታሰበበት ቀንም አስቀድሞ እርግዝና መኖሩን ለማወቅ ያስችላል 🖲የሽንት እርግዝና ምርመራ ውጤት ሊሳሳት የሚችለው 👉የወር አበባ መዛባት ከነበረ 👉እርግዝና መኖሩ ሳይታወቅ ተፈጥሮአዊ ውርጃ ካጋጠመ 👉የእርግዝና መመርመሪያው ግዜው ያለፈ እና አነስተኛ አቅም ካለው 👉እንዲሁም አንዳንድ የእንቁላል እጢ እና በመህፀን ውስጥ በሚፈጠሩ እጢዎች ምክኒያት ምርመራው ያልተጠበቀ ውጤት ሊሰጥ ይችላል 🖲በዚህም ምክኒያት፣ ማንኛውም በቤት ውስጥ የሚሰራ የእርግዝና ምርመራ ውጤት፣ በጤና ተቋም መረጋገጥ ያስፈልገዋል።
Показати все...
የቴዲ አፍሮ 'አርማሽ' የተሰኘ ሙዚቃው ኦባማ በአመቱ ከወደዷለው ምርጥ ስራዎች ውስጥ ነው ሲሉ ጠቅሰውታል❗️ ⚡️ባራክ ኦባማ የ2021 ምርጥ ዘፈን በማለት በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ዘርዝረዋል። ባራክ ኦባማ አመታዊ ምርጥ ሙዚቃ ምርጫቸውን ቀደም ባሉ አመታትም ያደርጉት የነበረ ተግባር ነው። በሳቸው ምርጥ ውስጥ የሚካተቱ ዘፈኖች እጅግ የበዛ ተመልካች ገቢ ሲጎርፍላቸው እንደነበር ይታወሳል። ⚡️የቢልቦርድ ድረገፅ ዘገባ በ2019 የኦባማ ምርጥ ውስጥ የተካተቱ ሙዚቃዎች ያገኙት ጭማሪ ማሳያ የሚሆን ነው።ባራክ በወቅቱ የዘረዘሯቸው 44 ስራዎች ከሳምንት ወደ ሳምንት የተመልካችና ገቢ መጠናቸው በሺዎች እጥፍ ነው ያደገው። ViaThinkAbyssinia
Показати все...
ደንበኞች እንዴት የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በአግባቡ ማወቅ ይችላሉ? ********************* የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአሁን ወቅት ከ3 ሚሊዮን በላይ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች አሉት፡፡ ከእነዚህ ደንበኞቹ መካከል በርካቶቹ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ እንዴት እንደሚሰላ ባለማወቃቸው የተጋነነ የፍጆታ ሂሳብ ተጠየቅን የሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርቡ ይስተዋላል፡፡ ይሁን እንጂ ቅሬታው የሚነሳው ደንበኞች የተጋነነ ሂሳብ እንዲከፍሉ በመደረጉ ሳይሆን የኤሌክትሪክ ኃይል በአግባቡና በቁጠባ ባለመጠቀም የሚመጣ እንዲሁም የፍጆታ ሂሳብ እንዴት መሰላት እንዳለበት በቂ ግንዛቤ ባለመያዝ የመነጨ ነው፡፡ ስለሆነም የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች በመኖሪያ ቤታቸው የሚጠቀሙባቸውን የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶችን የኃይል መጠን መነሻ በማድረግ ምንያህል ኪ.ዋ.ሰ እንደተጠቀሙና ምን ያህል ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ እንደሚከፍሉ መረዳት ይችላሉ፡፡ ይህንንም በቀላሉ ለመረዳት እንዲያስችል የአንድ የመኖሪያ ቤት ድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛ የሆነ ሰው ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ስሌቱ በሚቀጠለው ምሳሌ እናስቀምጠው፡- • አንድ ደንበኛ በመኖሪያ ቤቱ 4 ባለ 60 ዋት አምፖሎች በቀን ለ6 ሰዓት በወር ለ30 ቀናት ቢያበራ፣ • 3000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም የእንጀራ ምጣድ በቀን ለ2 ሰዓት በወር ለ10 ቀናት ቢጠቀም • 1000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም ምድጃ በቀን ለ5 ሰዓት በወር ለ30 ቀናት ቢጠቀም • እና ይህ ግለሰብ ሌሎች የኤሌክትሪክ መገልገያ ቁሳቁሶች ሳይጨምር በወር ውስጥ ምን ያህል ኪ.ዋ.ሰ እንደተጠቀመና ምን ያህል የፍጆታ ሂሳብ እንደሚከፍል ለማወቅ የተጠቀመበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በመደመር ወደ ኪ.ዋ.ሰ መቀየር ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም መሰረት  4 አምፑል X 60 ዋት x 6 ሰዓት x 30 ቀናት = 43,200 ዋት.ሰ፣  3000 ዋት ኤሌክትሪክ የኃይል የሚጠቀም ምጣድ x 2 ሰዓት x 10 ቀናት = 60,000 ዋት.ሰ፣  1000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም ምድጃ x 5 ሰዓት x ለ30 ቀናት = 150,000 ዋት.ሰ፣ ሶስቱም ሲጠቃለሉ 43,200 ዋት.ሰ + 60,000 ዋት.ሰ + 150,000 ዋት.ሰ = 253,200 ዋት.ሰ ይሆናል፡፡ ይህም ወደ ኪሎ ዋት ሰዓት መቀየር አለበት፡፡ 1 ኪሎ ዋት ሰዓት = 1000 ዋት ሰዓት በመሆኑ፤ 253,200 ዋት ሰዓት = 253.2 ኪሎ ዋት ሰዓት ይሆናል፡፡ የመኖሪያ ቤት የታሪፍ ስሌት 7 ደረጃዎች ያሉት ሲሆን፤ አንድ የመኖሪያ ቤት ደንበኛ በወር የተጠቀመበት የኤሌክትሪክ ኃይል በሚያርፍበት የታሪፍ እርክን ተባዝቶ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ከላይ በምሳሌው የጠቀስነው ደንበኛ በወር 253.2 ኪ.ዋ.ሰ የኤሌክትሪክ ኃይል ቢጠቀም በቀጥታ 4ኛው እርከን ላይ የሚያርፍ በመሆኑ በ1.6375 ብር ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት 253.2 ኪ.ዋ.ሰ x 1.6375 ብር= 414.615 ብር ይመጣል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ ብር 42 ሲደመርበት በአጠቃላይ የደንበኛው ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ 456 ብር 615 ሳንቲም ይሆናል ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ደንበኞች የምትጠቀሙባቸው የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች የሚጠቀሙትን የኃይል መጠናቸው በመለየትና በቀን ውስጥ የምትገለገሉበት ጊዜ በማወቅ ወርሃዊ ፍጆታችሁን በቀላሉ መረዳት ትችላላችሁ፡፡ ገንዘባችሁ ይበልጥ ለመቆጠብ ደግሞ ቁሳቁሶቹ ኃይል ቆጣቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ Viaየኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Показати все...