cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ቁርዓንን በተጅዊድ እንቅራ📖📖📖

አላማችን ማስተማር ነው።

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
136
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

⚃የአምፖል ውበቱ ከውስጡ የሚወጣው ብርሃኑ ነው ! በሚቃጠልበት ጊዜ ለምንም የማይጠቅም፣ የማንንም አይን የማይስብ በቀላሉ የሚሰበር ተራ ብርጭቆ ነው የሚሆነው ። የሰውም ውበት ከውስጡ በሚፈልቀው #የደስታ_ፋናና #የተስፋ_ጨረር እንጂ በፊቱ ቅርጽና በሰውነቱ አሰካክ ብቻ አይደለም ። @islammstudent22
Показати все...
ኢስላማዊ ዲክሽነሪ ለጀማሪዎች ክፍል 5
Показати все...
ዲክሽነሪ ክፍል 5.mp33.27 MB
ኢስላማዊ ዲክሽነሪ ለጀማሪዎች ክፍል 4
Показати все...
ዲክሽነሪ ክፍል 4.mp32.56 MB
ኢስላማዊ ዲክሽነሪ ለጀማሪዎች ክፍል 3
Показати все...
ዲክሽነሪ ክፍል 3.mp32.64 MB
ኢስላማዊ ዲክሽነሪ ለጀማሪዎች ክፍል 5 https://t.me/islamawe99
Показати все...
#_ሙሳ_ዐለይሂ_ሰላም           ክፍል 2⃣ ሙሳ በከተማዋ መግቢያ ላይም ሲደርስ የመድየን ከተማ ነዋሪያን በሙሉ እንስሳዎቻቸውን ውሀ የሚያጠጡበትን አንድ ምንጭ ቦታ ደረሰ።ልክ እዛ ሲደርስ ህዝቡ በሙሉ ውሀ ሲያጠጣ ሁለት ሴቶች ግን በጎቻቸውን ወደ ውሀው እንዳይጠጉ ሲከለክሉ ተመለከተ። ሙሳም ወደ ሴቶቹ ጠጋ ብሎ፦"ለምን በጎቻችሁን ውሀ መጠጣት ትከለክላላች" ሲል ጠየቃቸው። ሴቶቹም፦"እኛ በጎቻችንን ይዘን ከወንዶች ጋር እዚህ ግፊያ ውስጥ መግባት ስለምናፍር ሁሉም እንስሳዎቻቸውን አጠጥተው ሲሄዱ ነው እኛ ምናጠጣው።ሚያግዘን ሰው የለም በዚያ ላይ አባታችን ትልቅ ሽማግሌ ነው" አሉት። ሙሳም የሴቶቹን በጎች ሊያጠጣላቸው በጎቹን እየነዳ ግፊያውን ሰንጥቆ መሀል አስገብቶ አጠጣላቸው።ሙሳ አቅማም ስለነበረም ማንም ገፍቶ አይችለውም...በጎቹን እስኪጠግቡ ካጠጣላቸው በኋላ ሰብስቦ ለሴቶቹ አስረከባቸው።ሴቶቹም ሙሳን በጣም አመስግነውት በጎቻቸውን እየነዱ ወደ አባታቸው ተመለሱ። ሁሉም እንስሳቶቹን ካጠጣ በኋላ የምንጩን ቦታ ለቆ ሲሄድ ሙሳ ብቻውን እዛው ቀረ።የትም መሄጃ የለውማ...ከዚያም ወደ አንድ ዛፍ ጥላ ጋ ሄደ'ና፦"ያ አላህ! እኔ ከመልካም ነገር (ምንም ይሁን ምን) ወደኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ" ሲል አላህን ተማፀነው። ብዙም ሳይቆይ ከቅድሞቹ ሴቶች አንዷ እያፈረች መጣች'ና መሬት መሬቱን እያየች፦" በጎችን ስላጠጣህልን አባቴ ውለታውን ሊመልስልህ ይፈልጋል። ስለዚህ ና እኛ ቤት እንሂድ" አለችው።(ያ ሰላም ደስ አይልም በአላህ!!!) ሙሳም ብድግ ብሎ ተነሳ'ና መሄድ ጀመሩ።እየሄዱ ሳለ ልጅቷ መንገዱን ለመጠቆም ፊት ፊት ስትራመድ ሙሳ ወጣትም ስለሆነ ከኋላ ሆኖ እሷን መመልከት ስላልፈለገ፤ ጠርቷት ከኋላ ኋላው እንድትራመድ'ና መታጠፊዎችንም ሲደርሱ ወደ ቀኝ ከሆነም ወደ ግራ ድንጋይ በመወርወር እንድታሳውቀው ነግሯት እሱ ከፊት ፊት መራመድ ጀመረ። አባታቸው(ነቢዩላህ ሹዐይብ) ዘንድም ደረሱ'ና አባታቸው ሙሳን አመስግነውት ከየት እንደመጣ ሲጠይቁት ሙሳም ሙሉ ታሪኩን ተርኮላቸው ወደ መድየን የመጣበትንም ምክንያት በግልፅ ነገራቸው። ሙሳ ከዚህ በኋላ የትም መሄጃ እንደሌለው የተመለከተውም የሴቶቹ አባት፦"ለ8 አመታት ያህል በጎቼን የምታግድልኝ እንደሆን እኔ ከሁለቱ ሴት ልጆቼ አንደኛዋን እድርልሀለሁ። ግን አንተን ደስ ካለህ ስምንቷን አመታት 10 ሙላት" አሉት። ሙሳም በሀሳባቸው ተስማምቶ ለ10 አመታት ያህል በታማኝነት አገለገላቸው።በመጨረሻም አስሩ አመት ሲሞላ ሙሳ ሹዐይብን የገባለትን ቃል እንዲያሟላ(ልጅቷን እንዲዘውጀው) ጠየቀው'ና ወደ ሌላ ሀገርም መሄድ እንደሚፈልግ ነገረው። ሹዐይብም ሴት ልጁን ሞሽሮ ከተለያዩ ስጦታዎች ጋር ለሙሳ ጀባ አለው። ሙሳም ሚስቱን እና ከሹዐይብ የተበረከተለትን እንስሳቶች ይዞ ጉዞ ጀመረ።በጉዞ ላይ ሳሉም ሰይናእ የተባለ ቦታ ላይ በሚገኝ የጡር ተራራ ላይ ሲደርሱ መሽቶ ጨለመባቸው።እዛው ጋ ሳሉ መንገዱም ተወዘጋገበባቸው ወዴት እንደሚሄዱ'ና ከየት በኩል እንደመጡ ሁላ ጠፋባቸው። በዚህ ጨለማ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ከተራራው በስተቀኝ በኩል የሚነድ እሳት ሚመስል ነገር ሙሳ አየ'ና ለሚስቱ፦"እዚሁ ጠብቂኝ ከተራራው ጫፍ የሚነድ እሳት ስላየሁ ለኩሼ እመጣለሁ። ወይም መንገድ ወዴት እንደሆነ እጠይቃለሁ" ብሏት ሄደ። ሙሳ እሳቱ ወደሚንቀለቀልበት ተራራ ላይ በጨለማው ከወጣ በኋላ ሲያይ ምንም እሳት የለም።ሙሳም ደነገጠ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ከወደኋላ በኩል፦"አንተ ሙሳ" የሚል ድምፅ ሰማ። ሙሳ ተደናግጦ ሲዞር፦"እኔ ጌታህ (አላህ) እኔ ነኝ መጫሚያዎችህንም አውልቅ፡፡ አንተ በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ ነህና፤ እኔም መረጥኩህ፤ የሚወረድልህንም ነገር አዳምጥ። እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት፡፡ ልደብቃት እቃረባለሁ፡፡ ነፍስ ሁሉ በምትሠራው ነገር ትመነዳ ዘንድ (መጭ ናት)። በእርሷ የማያምነውና ዝንባሌውን የተከተለውም ሰው ከእርሷ አያግድህ ትጠፋለህና" አለው። ሙሳ በድንጋጤ ዝምታ ወርሮታል።አላህም ቀጠል አድርጎ፦"ሙሳ ሆይ! ይህችም በቀኝ እጅህ ያለችው ምንድን ናት?" አለው። ሙሳም እየተርበተበተ፦"እርሷ በትሬ ናት፡፡ በእርሷ ላይ እደገፍባታለሁ፣ በእርሷም ለፍየሎቼ ቅጠልን አረግፍባታለሁ፣ ለእኔም በእርሷ ሌሎች ጉዳዮች(ጥቅሞች) አሉኝ" አለው። አላህም፦"ሙሳ ሆይ! በትርህን ጣላት" አለው። ሙሳም እሽ ብሎ በትሯን ሲጥላት፤ በትሯ የምትሯሯጥ እባብ ሆነች" ሙሳ እባቡን ሲያያ እግሬ አውጭኝ ብሎ ሲበረግግ አላህ፦"አንተ ሙሳ አትፍራ እባቧን ያዛት እንደነበረች ዱላ አደርጋታለሁ" አለው። ሙሳም እየተንቀጠቀጠ እባቧን ሲይዛት እንደነበረች ዱላ ሆነች። ከዚያም አላህ፦"ሙሳ ሆይ! እጅህን በብብትህ ውስጥ አስገባ" አለው። ሙሳም እሽ ብሎ እጁን በብብቱ ሲያስገባ እጁ እንደ መብራት መብራት ጀመረ።ሙሳ እጁን በዚህ መልኩ ሲያይ በሽታ መስሎት በጣም ተጨነቀ። ያን ግዜ አላህም፦"ሙሳ ሆይ! አትፍራ ይህ ከኛ የሆነ ተአምር ነው" አለው። አላህም ቀጠል አድርጎ፦"ሙሳ ሆይ! ወደ ግብፅ ተመለስ። ፊርዐውንም ወሰን አልፏል" አለው። ሙሳም፦" ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ፡፡ ነገሬንም ለእኔ አግራልኝ፡፡ ከምላሴም መኮላተፍን ፍታልኝ። ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ፡፡ ሃሩንን ወንድሜን፡፡ ኅይሌን በእርሱ አበርታልኝ፡፡ በነገሬም አጋራው፡፡ በብዙ እናጠራህ ዘንድ፡፡ በብዙም እንድናወሳህ፡፡ አንተ በእኛ ነገር ዐዋቂ ነህና" አለው። አላህም የሙሳን ፍላጎት እንዲሚያሳካለት ቃል ገባለት'ና ሙሳም ወደ ሚስቱ በመሄድ ወደ ግብፅ መሄድ እንዳለባቸው ነግሯት ከሚስቱ ጋር ጉዞ ወደ ግብፅ ጀመሩ። ግብፅ እንደገቡም ሙሳ የወንድሙን የሀሩን ቤት በመግባት ለሀሩን ሁሉንም ነገር ነገረው።ሀሩንም እጅጉን በመደሰት በሀሳቡ ተስማሙ። በነጋታው ሙሳ እና ሀሩን ያለ ምንም ፍራቻ ወደ ፊርዐውን ቤተ መንግስት ዘልቀው ገቡ።ከዚያም ፊርዐውንን እንደተገናኙም ወደ አላህ እንዲመለስ'ና በኒ ኢስራኢሎችንም እንዳይበድል፤ ሙሳ እና ወንድሙ ሀሩንም የአላህ መልዕክተኞች መሆናቸውንም አክለው ነገሩት። ፊርዐውንም ከ10 አመት በፊት እቤቱ ይኖር የነበረውን ሙሳን በትኩረት ሲመለከት አወቀው'ና፦"አንተ ህፃን ሆነህ እቤቴ አላሳደግኩህም እንዴ!!! ያችንም የሠራሃትን ሥራህን አልሠራህምን? አንተም ከውለታ ቢሶቹ ነህ"አለው ሙሳም፦"ያን ግዜ ተሳስቼ ነው። ከዚያም እናንተ ትገድሉኛላችሁ ብዬ ሩቅ ሀገር ሸሸሁ። እዚያው ጌታዬም ጥበብን ሰጠኝ።ይህችም የእስራኤልን ልጆች ባሪያ በማድረግህ በእኔ ላይ የምትመጻደቅባት ጸጋ ናት" አለው። ፊርዐውንም፦" (ላከኝ የምትለው) የዓለማትም ጌታ ምንድነው" አለው። ሙሳም፦" የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምታረጋግጡ ብትኾኑ (ነገሩ ይህ ነው)" አለው። ፊርዐውን ትንሽ ሳቀ'ና ወደ ዙሪያው ያሉትን ሰዎች እየተመለከተ፦"ሚለውን አትሰሙትም እንዴ!" አላቸው። ሙሳም፦"......... ክፍል 3⃣ ኢንሻአላህ ይቀጥላል join 👉 @islamawe99 @islamawe99
Показати все...
#መልስ 1. #ነቢዩላህ ዩኑስ ( ዓለይሂ ሰላም ) ናቸው ነቢዩላህ ዩኑስ( ዓለይሂ ሰላም )በአሳ ሆድ ውስጥ ሆነው በጣም ሲጨንቃቸው ወደአላህ ይህን ዱኣ አደረጉ👇 ሱረቱል አል አንቢያዕ ቁጥር 87 ላይ ይህ ዱኣ ይገኛል لَّا إِلَهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ (21:87) “ላኢላሀ ኢልላ አንተ ሱብሃነከ ኢንኒ ኩንቱ ሚን አዝዛሊሚይን” “ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም:: ጥራት ይገባህ::እኔ ከበደለኞች አንዱ ነኝ ::” ( አል አንቢያ 21: 87) አላህም የባሪያውን የዩኑስን( ዓለይሂ ሰላም ) በጭንቅ ጊዜ ተማፅኖ፣ልመና፣ዱኣ ሰምቶ ከዛ ከአሳ ሆድ ውስጥ ነፃ አውጥቶታል። ለበለጠ መረጃ ሱረቱል አል አንቢያዕ ሙሉ አንቀፁን እንድታነቡት እጋብዛቹሃለው join 👇 @islamawe99 @islamawe99
Показати все...
#_ሙሳ_ዐለይሂ_ሰላም ክፍል 1⃣ #_ግዜው_ዩሱፍ_ዐ_ሰ ከሞተ 97 አመታትን አስቆጥሯል።በዩሱፍ አማካኝነት የግብፅን ምድር ገብተው በመንፊስ ከተማ መኖር የጀመሩት የያዕቁብ ልጆች ሁሉ ሞተው አልቀው የልጅ ልጆቹ ግን በመተካካት ግብፅን እጅጉን እየሞሏት ነው። ምንም እንኳን ያኔ በዩሱፍ (ዐ ሰ) ዘመን እነዚህ በኒ ኢስራኢሎች (የያዕቁብ ልጆች) በግብፅ ምድር የተከበሩ ሰዎች ቢሆኑም አሁን ላይ ያለው ንጉስ ግን እጅጉን ይበድላቸው ጀምሯል። ይሄን ግዜ ነበር እንግዲ አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ነፃ እንዲያወጣ ሙሳን የላከው። የሙሳ የዘር ሀረግ፦ ሙሳ ኢብን...ዒምራን ኢብን...የስሀር ኢብን...ቃሂስ ኢብን...ላዊ ኢብን...ያዕቁብ ኢብን...ኢስሀቅ ኢብን...ኢብራሂም ኢብን....አዛር......ምናምን እያለ ይቀጥላል። ሙሳ ከመወለዱ በፊት ፊርዐውን አንድ ቀን በህልሙ የሆነች እሳት ከእየሩሳሌም ወደ ግብፅ መጥታ የግብፃውያንን ቤት እየዞረች ታቃጥል'ና የበኒ ኢስራኢሎችን ቤት ስትተው ተመለከተ። እና ይህ ህልም እረፍት የነሳው ንጉስ በነጋታው ጠንቋዮችን እና ኮከብ ቆጣሪዎችን ሰብስቦ የህልሙን ፍች ሲጠይቃቸው፦"ከነዚህ የያዕቁብ ልጆች(ከበኒ ኢስራኢሎች) አንድ ንግስናህን የሚሽር ልጅ ሊወለድ ነው" አሉት። ፊርዐውን ይህን ሲሰማ በጣም በመደንገጥ የበኒ ኢስራኢል ወንድ ልጆችን እንዳለ እንዲገደሉ አዘዘ...ምንም አይነት ወንድ ልጅም ቢረገዝ እንደሚገድልም ትዕዛዝ አስተላለፈ። የፊርዐውን ትዕዛዝ መተግበር ተጀመረ...በጣም ለቁጥር የሚያዳግቱ የበኒ ኢስራኢል ወንድ ልጆች እንደ ገፍ ተገደሉ። በመጨረሻም ይህ ህግ ማሻሻያ መደረግ እንዳለበት የግብፅ ህዝብ አቤቱታ ሲያቀርብ ፊርዐውንም ዘወትር የሚተገበረውን የግድያ ተግባር አንድ አመት ግድያ እንዲቆም እና አንድ አመት እንዲገደል አደረገ..... በዚህ ሁኔታ ነበር የማይገደልበት አመት ላይ ሀሩን የተባለው የሙሳ ወንድም ተወልዶ፤ በሚገደልበት አመት ደሞ ሙሳ የተወለደው። ሙሳ ልክ እንደተወለደ የሙሳ እናት ህፃኗን አይኗ እያየ እንዳይገድሉባት በጣም ተጨነከች።ምታደርገው ጠፍቷት በመዋለል ላይ ሳለች አላህም እናትየውን ከእንጨት የሆነ ሳጥን ሰርታ፤በዚያ ሳጥን ውስጥ ህፃኑን እንድታስገባው'ና ሳጥኑንም ከነ ህፃኑ ወንዝ ላይ እንድትጥለው አዟት፤ ይህንንም ህፃን ነቢይ አድርጎ እንደሚመልስላት ቃል ገባላት። በዚህ መሰረት የሙሳ እናት ህፃን ልጇን በጨርቅ ጠቅልላ በሳጥን አሽጋ ሆዷ እየባባ በናይል ወንዝ አሻግራ ሸኘችው። ውሀውም ሳጥኑን ከነ ህፃኑ እያንሳፈፈ የልጆችን ግድያ ትዕዛዝ ወደሰጠው ፊርዐን ግቢ ይዞት ገባ።በሰዐቱ የፊርዐውን የሚስቱ አገልጋዮች እዚያ ወንዝ ዳር እየታጠቡ ነበር'ና ይህን ሳጥን ሲመለከቱ በውስጡ ወርቅ ያለ መስሏቸው ለእመቤታቸው ሳጥኑን ሳይከፍቱ በስጦታ መልክ ወስደው አስረከቧት። የሙሳ እህት እዚያ ቤተ መንግስት ውስጥ ተቀጥራ ትሰራ ነበር'ና እናቷ የጣለችው ሳጥን በገዳዮች እጅ መግባቱን ስታረጋግጥ ወደ እናቷ ስትከንፍ ሄዳ ነገረቻት።እናትም ልጇን ተመልሳ ሄዳ ሁኔታውን እንድታጣራላት ላከቻት። ልጅቷም ሁኔታውን ለማጣራት ቤተመንግስት ተመልሳ መጣች። ንግስቲቱም አገልጋዮቿ እና ባለቤቷ ባሉበት ቦታ ሳጥኑ እንዲከፈት አዘዘች፤ሳጥኑ ሲከፈትም ልብን የሚያማልል ውብ እና ማራኪ ልጅ በሳጥኑ አገኙ።የፊርዐውን ሚስት ልጅ መውለድ አትችልም ነበር'ና፦"ልጅ ስለሌለን እባክህ ይሄን ህፃን አትግደለው።ወደ ፊትም ልጃችን አድርገን እንይዘዋለን " አለችው። እሱ ህፃኑን መግደል ቢፈልግም የሚስቱን ሀሳብ መቃረን አልፈለገም'ና በሀሳቧ ተስማማ። አሁን አስቸጋሪው ነገር መጣ....ይህን ምግብ ያልጀመረ ህፃን ማን ያጥባው?????? የተለያዩ አጥቢ እናቶች ይህን ህፃን ሊያጠቡ ቢሞክሩም ህፃኑ ግን የማንንም ጡት ከአፉ ሊያስጠጋ ፍቃደኛ አልሆነም።ይልቁኑ አጥቢዎቹ ሲመጡ ይባስ ያለቅስ ነበር። የፊርዐውንም ሚስት እጅጉን ተጨነቀች አላህ በልቧ የሙሳን ፍቅር ስለከተበባትም በህፃኑ ለቅሶ ጭንቀት ምትገባበት ጠፋት። ይሁ ሁሉ ሲሆን ሁኔታዎችን ትከታተል የነበረችው የሙሳ እህት ምንም እንደማያውቅ ሆና፦"ይህን ህፃን ለናንተ የሚያሳድግላችሁን ቤተሰብ ለመላክታችሁ!! ታማኝም ናቸው" አለቻት። የህን ስትሰማ የፊርዐውን ሚስት ደስታዋ ወደር አጣ።የፈለጉትን ክፍያም ለአጥቢዋ እንደሚከፍሉም ቃሉ ገቡላት'ና የሙሳ ትክክለኛዋ እናት እንድትመጣ አደረጉ። የሙሳ እናት ቤተ መንግስት ገብታ ልክ ልጇን ስትመለከት ልቧ ተንሰፈሰፈ...፣እንባዋ ከአይኗ ሊሾልክ ተቃረበ።እንደምንም ራሷን ተቋቁማ ህፃኑን ልታጠባ ስታቅፈው ህፃኑ ለቅሶውን ትቶ ጡቷን ይሞጥሙጥ ጀመር።ፊርዐውን እና ኣሲያ(የፊርዐውን ሚስት) ይህን ሲመለከቱ በጣም ተደሰቱ። በዚህ ሁኔታ የሙሳ እናት እየተከፈላት ልጇን ለ2 አመታት ያህል አጠባችው። ግዜ ግዜን እየተካ ሙሳም ትልቅ ልጅ ሆነ።ምንም እንኳን ሙሳ የፊርዐውን ያብራኩ ክፋይ ባይሆንም በህዝቡ ዘንድ ግን የፊርዐውን ልጅ በመባል ነው ሚታወቀው። ከእለታት አንድ ቀን ሙሳ በጠራራ ፀሀይ ከተማ ውስጥ እየተራመደ ሳለ አንድ ግብፃዊ እና አንድ በኒ ኢስራኢላዊ ሲደባደቡ ተመለከተ። በኒ ኢስራኢላዊውም ሙሳን አድነኝ በማለት ተጣራ። ሙሳም ይህን ግዜ ግብፃዊው ላይ ገራሚ ቦክስ ሰነዘረበት'ና ሳያስበው የግብፃዊው ህይወት በሙሳ እጅ አለፈች።ይሁን እንጂ ማንም አላወቀበትም ነበር። ይሄን ግዜ ሙሳ በጣም በመፀፀት አላህን ምህረት ለመነው። አላህም ተውበቱን ተቀብሎት፦"ሙሳ ሆይ! በልቅናዬ እምላለሁ ይህች የገደልካት ነፍስ ለቅፅበት እንኳን በኔ ጌትነት ያመነች ብትሆን ከባድ ቅጣትን አቀምስህ ነበር" አለው። ሙሳም ከዚያ ቀን አንስቶ የግብፃዊው ሟች ወገን መጥተው እንዳይበቀሉት በጣም ስለሰጋ እንቅስቃሴውን በጥንቃቄ ማድረግ ጀመረ። በማግስቱም ሙሳ ከተማ ላይ ሳለ ይህ ትናንት ሲደባደብ የነበረው (በኒ ኢስራኢላዊው) የሙሳ ዘመድ ዛሬም ከሌላ ግብፃዊ ጋር ሲደባደብ ተመለከተው። የሙሳ ዘመድ ሙሳን ሲመለከት ዛሬም የእርዳታ ጥሪውን ለሙሳ አሰማ። ሙሳም ወገኑን(በኒ ኢስራኢሉን) ሲመለከት፦"አንተ በእርግጥ ግልጽ ጠማማ ነህ" አለው። ወገኑም፦"በትናንትናው ቀን ነፍስን እንደ ገደልክ ልትገድለኝ ትፈልጋለህን በምድር ለይ ጨካኝ መሆንን እንጅ ሌላ አትፈልግም፡፡ ከመልካም ሠሪዎችም መሆንን አትፈልግም" አለው። በዚያ አካባቢ የነበሩ የግብፅ ነዋሪያንም ወገናቸውን የገደለው ሙሳ መሆኑን ሲያውቁ እሱን ሊገድሉት መመካከር ጀመሩ። ይህን የሰማ ሂዝቂል የተባለ ግብፃዊ ሙእሚን ለሙሳ፦"ግብፃውያን አንተን ሊገድሉ እየተመካከሩ ስለሆነ የግብፅን ምድር ለቅቀህ እንድትወጣ እመክርሀለሁ" ብሎ መከረው። ሙሳም የግብፅን ምድር ትቶ በረሀውን እያቆራረጠ እግሩ ወደ መራው ቦታ መጓዝ ጀመረ።ብዙ ተጉዞ ረሀብ፣ጥማት እና ድካም ድንበር አልፈው ካዳከሙት በኋላ መድየን የምትባል ሀገር ደረሰ። ሙሳ በከተማዋ መግቢያ ላይም ሲደርስ የመድየን ከተማ ነዋሪያን በሙሉ እንስሳዎቻቸውን ውሀ የሚያጠጡበትን አንድ ምንጭ ቦታ ደረሰ።ልክ እዛ ሲደርስ...... ክፍል 2⃣ ኢንሽዓሏህ ይቀጥላል join 👉 @islamawe99 @islamawe99
Показати все...
 #የሰው ልጅ ከምን ተፈጠረ? ክፍል ሁለት 3፡- የወንዱ የዘር ፈሳሽ “ውሃ” ተብሎ የተጠራ ሲሆን ከሴቷ ፈሳሽ ጋር ሲቀላቀል “አምሻጅ” (ውሁድ) ይሆናል፡፡ አላህ ሱ.ወ በቅዱስ ቁርአን ይህኑ ሲገልጽ፡- “እኛ ሰውን (በሕግ ግዳጅ) የምንሞከረው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው፡፡” (ሱረቱ አል-ኢንሳን 76፡2)   4፡- የዘር ፈሳሽ “ደካማ ውሃ” ተብሎ የተጠራው የስፐርም ሴል በባህሪው “ደካማ” በመሆኑ ነው፡፡ተከታዩ የቁርአን አንቀጽ ይህንኑ ይገልጻል፡-“ ያ ሁሉንም ነገር አሳምሮ የፈጠረው፤ የሰውንም ልጅ አፈጣጠር ሂደት ከጭቃ የወጠነ (አምላክ) ነው፡፡ (7) ከዚያም ዘሮቹን ከተንጣለለ፣ ከደካማ ውሃ ያደረገ ነው፡፡ ” (ሱረቱ አል-ሰጅዳህ 32፡7-8)   5፡- የወንድ የዘር ፈሳሽም በተራክቦ ወቅት ተስፈንጥሮ ስለሚወጣ “ተስፈንጣሪ” ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ይህንም አላህ ሱ.ወ በተከበረው ቅዱስ ቁርአን እንዲህ ተጠቅሳል፡- “ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡ (5) ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡ (6) ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡” (ሱረቱ አል-ጧሪቅ 86፡8-7)   በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል!!!!! @islamawe99 @islamawe99
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.