uk
Feedback
Ethio music instruments

Ethio music instruments

Відкрити в Telegram

Hello 🤝,We are happy to have you here! አዲስና ያገለገሉ የሙዚቃ መሣሪያዎችን መሸጥና መግዛት ትችላላችሁ! For any Music Instrument supply 🎷 🥁 🎸🎙🎻🎺🎬🎹🎧 Call or text 0962157600

Показати більше
1 231
Підписники
-324 години
-57 днів
-730 день
Архів дописів
photo content

Roland
+2
Roland

Yamaha psr E263 Call 0962157600
Yamaha psr E263 Call 0962157600

One of my customer bought this vintage audio set up from me, and send it back with a set of furniture!
One of my customer bought this vintage audio set up from me, and send it back with a set of furniture!

Sony 3 way speaker system with player Frequency response =20-20k Hertz Have usb hub Best for studio Call 0962157600
Sony 3 way speaker system with player Frequency response =20-20k Hertz Have usb hub Best for studio Call 0962157600

ሰዉ ሆይ ሀይማኖትህ እና ሰዉነትህ የሚጠንክረዉ ስለሁሉ ታማኝ ስትሆን ነዉና ታማኝነት ላይ በርታ!!!
ሰዉ ሆይ ሀይማኖትህ እና ሰዉነትህ የሚጠንክረዉ ስለሁሉ ታማኝ ስትሆን ነዉና ታማኝነት ላይ በርታ!!!

#ሩብ ክፍለ ዘመን እንደ ፏፏቴ የማይደነፋ፣ እንደ ፈርሰኛ ውኃ የማይገለገል -ዝምታ:: በአኒሜሽን የተሰሩ እንደሚመስሉት እንደነዛ ውብ የሲውዝ ወንዞች በጸጥታ ውስጥ መፍሰስ:: ባለፉት 25 ዓመታት የ
#ሩብ ክፍለ ዘመን እንደ ፏፏቴ የማይደነፋ፣ እንደ ፈርሰኛ ውኃ የማይገለገል -ዝምታ:: በአኒሜሽን የተሰሩ እንደሚመስሉት እንደነዛ ውብ የሲውዝ ወንዞች በጸጥታ ውስጥ መፍሰስ:: ባለፉት 25 ዓመታት የሙዚቃ ታሪካችን ውስጥ 5 እንቁዎች ቢኖሩት አንዱ እሱ ነው:: በሩብ ክፍለ ዘመን መንገዳችን ውስጥ ከመጡት ሁለት ተፅዕኖ ፈጣሪ አቀናባሪዎችም ስሙ መኖሩ ግድ ይመስለኛል:: ብዙዎች ስለ ኤልያስ መልካ አውርተናል:: ኤልያስ ራሱ ግን ስለዚህ ሰው ብቃት ያወራ ነበር:: ልማዳችን ሆኖ ሁለት ያንድ ዘመን ሰዎችን በልክ ማወደስ አይሆንልንም:: በፖለቲካችን በኩል የገባ ጠንቅ ነው መሰል ጎራ እንወዳለን:: እንዲያም ሆኖ ኑ ብሎ የማይጣራ፣ ተረሳሁ ብሎ የማያላዝን ሰው ስናይ መልሰን ማፈራችን አይቀርም:: ዳግማዊ ዓሊ እንድዛ ነው:: በሙዚቃ ታሪካችን ውስጥ ቦታ ስጡኝ ብሎ አልተነጫነጨም:: ይህን ሰራሁ እያለ በየሚዲያው አለፈፈም:: ይህም ሆኖ የልጅነት ትዝታችን የእሱ ጣት አርፎበታል:: ከአብዱ ኪያር እስከ ሀይማኖት ግርማ፣ ከብስራት ጋርደው እስከ ታምራት ደስታና ጥበበ ወርቅዬ ድረስ አንድ ጣቶቹ ያልጠኑ መልከ መልካም ምትሀተኛ አለ ካሏችሁ እሱ ዳግማዊ አሊ ነው። #Maereg_Getachew

Jbl speaker Price 7000 0962157600
+2
Jbl speaker Price 7000 0962157600

photo content

photo content
+4

photo content

አሪፍ እቃ ነዉ 0962157600
+1
አሪፍ እቃ ነዉ 0962157600

Sony audio player 0962157600 Price 19,500
Sony audio player 0962157600 Price 19,500

ESP LEAD GUITAR CALL 0962157600 55K
+1
ESP LEAD GUITAR CALL 0962157600 55K

photo content
+1

photo content
+3

ክፍል 3 ቸል የተባለው የጓዳችን ምስጢር በተፈተሹ መደበኛ የቤት የሙዚቃ ማጫወቻዎች እና በርካሽ የድምጽ ማሰራጫ ምርቶች (በተለምዶ Geepas)  መካከል ያለው ቀዳሚ ልዩነቶች distortion level ፣ የሞገድ ትክክለኛነት እና የተረበሸ ድምጽ ማግለል ናቸው። ፍተሻን በማለፍ የተመረቱ ጥራት ያላቸው የቤት ውስጥ የሙዚቃ ሲስተሞች የጆሮ ድካምን የሚቀንስ ጥርት ያለ ትክክለኛ ድምጽ ያመነጫሉ ነገር ግን ርካሽ እና ቁጥጥር ያልተደረገባቸው ምርቶች ብዙውን ጊዜ የመስማት ችሎታን በጊዜ ሂደት የሚጎዳ ከባድ የሃርሞኒክ መዛባት ያስከትላሉ። ‎ ‎1. ሃርሞኒክ ማዛባት እና የጆሮ ድካም፡ ታዋቂ የኦዲዮ ብራንዶች ለዝቅተኛ ጠቅላላ የሃርሞኒክ መዛባት (THD) የተሰሩ ናቸው። የድምፅ ሞገድ በትክክልኛው ልኬት ሲሰራጭ፣ አእምሮዎ በቀላሉ ለመተርጎም ራሱን ያዘጋጃል፣ ይህም የማዳመጥ ድካም በፍጥነት እንዳይጀምር ይከላከላል። ነገር ግን በሀገራችን በስፋት እንደተሰራጩት አይነት በተለምዶ ስማቸው Geepas ተብለው እንደሚጠሩት አይነት ርካሽና የላብራቶሪ ፍተሻ ያልተደረገባቸው ምርቶች ደብዛዛነት ወይም ረባሽ ጩኸትን በከፍተኛ ደረጃ የድምፅ ሞገድ ስለሚለቁ ውስጣዊ ጆሮን እና አእምሮን ድምጹን ለመረዳት የበለጠ ጠንክረው እንዲሰሩ ያስገድዳቸዋል፣ ይህም አካላዊ ጫና (የጆሮ መዳከም)  እና ወዲያው ሙዚቃው በሚሰማበት ሰአት ላይ ራስ ምታት ያስከትላል።

Sony Hi-Fi model:- fh e-737 cd Call 0962157600 Almost new with the remot
Sony Hi-Fi model:- fh e-737 cd Call 0962157600 Almost new with the remot

‎ዊልሰን ኦዲዮ አሌክሲያ V፡ ዋጋው በአንድ ጥንድ (Left & Right) 67,500 ዶላር አካባቢ ነው። በድምፅ ፍፁምነት ላይ ያሉ ገምጋሚዎች እጅግ በጣም ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ሞዴሎቻቸው አፈጻጸም ጉልህ ክፍል እንደሚሰጠው ይናገራሉ። ‎ ‎Magico S7 M-Coat ‎ማጊኮ ኤስ7 ኤም-ኮት፡- ይህ ስፒከር በአንድ ጥንድ (Left & Right) 76,300 ዶላር ያህል ያስወጣል። በአልማዝ የተሸፈነ ቤሪሊየም ዲያፍራም እና ለማዳመጥ በሚሰጠው ከፍተኛ የምቾት ችሎታዎች ባለው አዲስ ስሪት ትዊተሩ ይታወቃል። ‎ ‎Sonus faber Lilium ‎ሶነስ ፋበር ሊሊዬም: በአንድ ጥንድ እስከ 75,000 ዶላር አካባቢ ይገኛል፣ የወርቅ ልብጥ ባለው አጨራረስ አማራጭ ደግሞ በ100,000 ዶላር ይገኛል። ገምጋሚዎች ብዙ ጊዜ የሚያምር መልኩን እና በሙዚቃ አቀራረቡ  ያወድሱታል። ‎ ‎MBL 101 E Mk II ‎እነዚህ በድምፃቸው ቦታን የሚሞሉ ተናጋሪ ስፒከሮች ዋጋቸው 84,500 ዶላር አካባቢ ነው፣ በጣም ትልቅ እና እውነተኛ ድምፅ የመፍጠር ብቃታቸውም ከፍተኛ ነው። ‎ ‎አምፕሊፋየር እና የምንጭ ተቀባዮች (Receivers) ‎ ‎Dan D'Agostino Master Audio Systems ‎ዳን ዲ አጎስቲኖ ማስተር ኦዲዮ ሲስተሞች፡ በተሰሩበት ጥራት በጣም የተከበሩ ናቸው፣ በአንድ ዴክ ከ$15,000 እስከ $50,000+ ባለው ክልል ውስጥ ያሉ አማራጮች አሏቸው (ለምሳሌ፣ preamplifiers፣ stereo amplifiers, CD players ...). ‎ ‎Vivaldi Apex DAC ‎ቪቫልዲ አፔክስ DAC: ከፍተኛ ደረጃ ያለው ዲጂታል ምንጭ አካል ተደርጎ ይቆጠራል፣ ዋጋውም እንደ ውቅር (የተለያዩ ዴኮች በአንድ ላይ)  በግምት $30,000+ ነው። ‎ ‎Antileon EVO Power Amplifier ‎አንቲሊዮን ኢቪኦ ፓወር አምፕሊፋየር፡ ከዴንማርክ ብራንድ ከፍተኛ ኃይል ያለው ማጉያ፣ ከ$30,000+ የመክፈል አቅም  ጋር የሚስማማ ጥሩ እቃ ነው። ‎ ‎Nagra Audio ‎ናግራ ኦዲዮ፡- በስዊዘርላንድ የተሰራ ኤሌክትሮኒክስ እጅግ በጣም ጥሩ የግንባታ ጥራት እና ዝርዝር ሰርስሮ ማውጣት (Detailed amplification) ፣ ከ10,000 እስከ $40,000+ ባለው ክልል ውስጥ የተለያዩ ፕሪአምፖች እና ዋና አምፖች ይገኛሉ። ‎ ‎ምንም እንኳን አሁን ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ተደምሮ ስለሙዚቃ ማጫወቻ ጥራት ማሰብ እንደሰማይ የራቀ ቢሆንም በተቻለ አቅም ሶኒ እና ኤልጂ ወይም ሌሎች ታዋቂ ሆነው ሻለ ያለ ብቃት ባላቸው በማስ ፕሮዳክሺን የገበያ መስመር ውስጥ ያሉ የቤት ውስጥ የሙዚቃ ማጫወቻዎችን እና ሆም ቴያትር ሲስተሞችን በመግዛት የማድመጥ ልምምዳችንን እና የጆሮ ጤንነታችንን መጠበቅ እንችላለን። ስለጆሮ ጤና እና ከሙዚቃ ማጫወቻ ስለሚወጡ የድምፅ ዌቮች ለማብራራት እንመለሳለን 🙌

የሙዚቃ አደማመጥ ባህላችን እና የጆሮ ጤና ‎ ‎ቀደም ባሉት ጊዜያት በተለይም ከ1950ዎቹ - 1980ዎቹ መጨረሻ (በሁሉም ቤት ባይሆንም) ጥራት ያላቸው የሙዚቃ ማጫወቻዎችን ኢትዮጵያዊያን ቤት ውስጥ
+6
የሙዚቃ አደማመጥ ባህላችን እና የጆሮ ጤና ‎ ‎ቀደም ባሉት ጊዜያት በተለይም ከ1950ዎቹ - 1980ዎቹ መጨረሻ (በሁሉም ቤት ባይሆንም) ጥራት ያላቸው የሙዚቃ ማጫወቻዎችን ኢትዮጵያዊያን ቤት ውስጥ መመልከት ብዙም ብርቅ አልነበረም። አሁን ግን በተለይ ከኢትዮጵያ ሚሊኒየም መግባት በኋላ በአብዛኛው ማህበረሰብ ቤት ውስጥ በተለምዶ አጠራሩ ጂፓስ (Geepas) የሚባል የቻይና ስራ ሀገሩን ሁሉ ወሮት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የድለቃ አድናቂ ከሆነ ሰነባብቷል። ሲገዛ በውስጡ ብሉቱዝ ፣ ራዲዮ ፣ ተጨማሪ መቀበያዎች ወይም እኛ ጃኮች የምንላቸው 😆 (Receivers) እናም ሶስት ወይም አራት ስፒከሮችን ያካተተ ነው። በአለም ገበያ ዋጋው ከ 10 - 20 ዶላር ድረስ ይሸጣል (ይህን ያህል እቃዎችን አካቶ 😆) ማለት ነው። ‎ ‎ኦሪጅናል የሙዚቃ ማጫወቻዎች (High end audiophiles) እነዚህን ሁሉ በአንድ ላይ አካተው አይሸጡም። የሸክላ ወይም ሲዲ ማጫወቻ ለብቻ ፤ የድምፅ ማጉያ (amplifier) ለብቻ ፤ ሬዲዮና የብሉቱዝ ሪሲቨር ለብቻ ... (እንደዴክ  አይነት የሚመስሉ የተለያዩ ናቸው) እና በተጨማሪም ስፒከሮችን ለብቻ ተገዝተው ሁሉንም በአንድ በማዋቀር የሚገነባ የሙዚቃ ማጫወቻ ሲስተሞች ናቸው። የሚያወጡት ድምፅም አርቲስቱ ሙዚቃውን ስቱዲዮ ውስጥ ሆኖ ከተጫወተው ጋር በጣም የቀረበ ወይም ምንም ሊለይ በማይችል ብቃት እና ከፍተኛ ጥራት ነው። ‎ ‎እስኪ እንደምሳሌ ስማቸው የሚጠቀስ አምራቾቹ በመካከለኛ የዋጋ ደረጃ ላይ የሚመድቧቸውን ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ማጫወቻዎችን እንመልከት (ከባለ 10 ዶላሩ ጂፓስ ጋር ልዩነቱን ለማወዳደር እንዲመች ከታች የተዘረዘሩት ዋጋዎችም በዶላር መሆናቸው ይሰመርበት):- => የተጠቀሱት እቃዎች ምስልም ከታች ተያይዟል ‎ ‎ስፒከሮች ‎ ‎Wilson Audio ... በክፍል 2🙏 ‎