cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የእግዚአብሔር ወንጌል

Рекламні дописи
2 695
Підписники
Немає даних24 години
+27 днів
+3230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

እርሱን ከማወቃችን በፊት ተወደናል። ፍቅሩንም ለኃጢአታችን ማስተሰረያ ለመሆን በማቆም፣ ከሳሾቻችንን በመቅጣት፣ [በትንሳኤ በኩር ሆኖ መነሳት] ወደ ሰማይ በማረግ፣ ቅዱስን መንፈስ በመላክ፣ ጠበቃችንና አማላጃችን በመሆን፣ ሀዘናችንን በመካፈል ገልጧል። ደግሞም ከእኛ ጋር ባደረገው ግንኙነት ፍቅሩን አሳይቷል። ኃጢአተኞች ብንሆንም እኛን በማዳኑ ደስታውን አይቷል። በሞቱ ለእግዚአብሔር ጠላቶች የነበርነውን ልጆቹ አድርጎናል። በጸጋው በኃጢአታችንና በስንፍናችን ሁሉ ይደግፈናል።    አለን በምንላቸው ነገሮች ሁሉ ለአፍታ እንኳ መጽናት የማንችለውን እስከመጨረሻ አጽንቶ ያቆመናል። ከቅብዝብዝነታችን ሁሉ ያድነናል። በመግቦቱም የሚያስፈልገንን ሁሉ እንደ ባለጠግነቱ ይሞላልናል።     __James Smith @Gospel_of_God @Gospel_of_God @Gospel_of_God
Показати все...
4🔥 1
የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት የክርስትና ማዕከል ነው። በክርስትና አለን የምንለው ሁሉ፣ ደግሞም በክርስቶስ ያገኘነው ሁሉ፣ ተስፋችን፣ ደስታችን፣ ሰላማችን፣ መጽናታችን ብሆን መተማመኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት የታሰረ ነው።     _ጆን ማክአርተር @Gospel_of_God @Gospel_of_God @Gospel_of_God
Показати все...
13👍 2
በምን ወደድከኝ (ስለወደድከኝ እወድኻለሁ!!) በምን ወደድከኝ አልልህም በእርግጥ ወደኸኛል የፍቅርህ መግለጫ ይሄ ነው ለኔ ተወግተሃል አንተ ለኔ የሆንከውን ያህል እኔ ላንተ አልሆንኩም ምን ያህል እንደሆን አላውቅም ለክቼ አላየሁም ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ስለወደድከኝ ወድሃለሁ ከእርግማን ስለዋጀኸኝ ሞተህ ሸክሜን ስለወሰድክ በመንፈስ ቅዱስ ስለሞላኸኝ ነፍሴን ስለባረክ ፀጋን አብዝተህ ስለሰጠኸኝ ከቶም ስላልተውከኝ ምን ያህል እንደሆን አላውቅም ለክቼ አላየሁም ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ስለወደድከኝ ወድሃለሁ ደስ ላሰኝህ እቀናለሁ በሕይውቴ ላከብርህ ሆኖም ከቶ አልጠቀምኩህም ሁል’ጊዜ ሳሳዝንህ ይልቅ ብዙ አድክሜሃለሁ የትም እየቀረሁኝ ብዙ ስላላፈራሁ ኢየሱስ ከፍቶኝ አለቅሳለሁኝ ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ስለወደድከኝ ወድሃለሁ ዘማሪ፡ ተስፋዬ ጋቢሶ @Gospel_of_God @Gospel_of_God @Gospel_of_God
Показати все...
በምን_ወደድከኝ_ስለወደድከኝ_ወድሀለሁ_Bemin_wededkegn_Pastor_Tesfaye_luLMUngVxXM.mp35.79 MB
8👍 1🤔 1
ስለ እግዚአብሔርን ሉዓላዊነት ይበልጥ በተረዳን ቁጥር፣ ጸሎታችን ይበልጥ በምስጋና ይሞላሉ። __Robert Charles Sproul @Gospel_of_God @Gospel_of_God @Gospel_of_God
Показати все...
16👍 2👏 1
ያለ ኢየሱስ ገነት ስዖል ነው። ገነትን ገነት ሚያደርግልን የእርሱ መኖር ብቻ ነው። __ሰለሞን አበበ ገብረመድህን @Gospel_of_God @Gospel_of_God @Gospel_of_God
Показати все...
13👍 4
እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር የማይሻር መሆኑ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በተደጋጋሚ የተረጋገጠ እውነት ነው። ብናምንም ባናምንም ይሄ እውነታ ነው። የእኛ ጥርጣሬ የእርሱን ፍቅር አያጠፋውም፤ እምነታችንም አይፈጥረውም። ይህ ፍቅር የመነጨው ፍቅር ከሆነው ከእግዚአብሔር ማንነት ነው። እናም ከተወደደው ልጁ ጋር ባለን አንድነት በኩል ወደ እኛ ያለማቋረጥ ይፈሳል።     __Jerry Bridges @Gospel_of_God @Gospel_of_God @Gospel_of_God
Показати все...
11👍 3
የእግዚአብሔር ጸጋ ከኃጢአታችን ከፍ ያለ፣ ከርኩሰታችንም የጠለቀ፣ ከመቅበዝበዛችን የሰፋ፣ ከዘላለምም የረዘመ ነው። __Steven Lawson @Gospel_of_God @Gospel_of_God @Gospel_of_God
Показати все...
6🔥 1
ከሁሉ በላይ ታላቁ አስተምህሮ ይህ ነው። የሰው ልጆች በኃጢአታቸው ስጠፉ አይቶ ምትካቸው ይሆን ዘንድ አንድያ ልጁን ላከ፤ በዚህም በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ሆነዋል የሚለው ነው። “እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።” (2ኛ ቆሮ 5፥21) ይህ አስተምህሮ ለጥፋተኛው ሰው የሆነ የኢየሱስ ክርስቶስ ምትክነት።    __Charles Spurgeon @Gospel_of_God @Gospel_of_God @Gospel_of_God
Показати все...
👍 6 3
ክርስቶስ አልባ መስቀል ለእኔ መጠጊያ የሌለው ነው። ያልተሰቀለው ክርስቶስም አዳኜ ልሆን አይችልም። ኦኦ! በተሰቀለው ክርስቶስ በእርሱ አርፋለሁ።     __B.B. Warfield @Gospel_of_God @Gospel_of_God @Gospel_of_God
Показати все...
👍 6 4
የዓለም ሰላም አንጻራዊ እና ጊዜያዊ ነው፤ ምክንያቱም በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ነው። የእግዚአብሔር ሰላም ግን ፍፁም እና ዘላለማዊ ነው ምክንያቱም የተመሰረተው በጸጋው ላይ ነው።       _ጆን ማክአርተር #መልካም_ሠንበት! @Gospel_of_God @Gospel_of_God @Gospel_of_God
Показати все...
12🔥 1
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.