cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት (Kebena special woreda)

እጅ ለእጅ ተያይዘን የልዩ ወረዳችንን ልማት እናፋጥን!!

Більше
Рекламні дописи
358
Підписники
Немає даних24 години
+57 днів
+1830 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

01:23
Відео недоступнеДивитись в Telegram
ግብር ለሀገር ክብር የሚከፈል እንጂ እዳ አይደለም ! 👉ለፈጣንና አዳዲስ መመሪያዎችን ለማግኘት 🌼Telegram channel 👉https://t.me/kebenearevenujoinch 🌼Facebook https://www.facebook.com/kebenarevenu5634
Показати все...
1.25 MB
የገቢ ስራ የጋራ ተግባር በመሆኑ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር በልዩ ትኩረት መስራት ይገባል:- አቶ ሞሳ ኢዶሳ ሰኔ 22/2016፣ወልቂጤ፣የቀ/ል/ወ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የ2015 የግብር ገቢ አፈጻጸም ግምገማ፣ የ2016 ግብር ዓመት ገቢ አሰባሰብ የንግድ ፈቃድ እድሳትና የ2017 የገቢ እቅድ የንቅናቄ መድረክ ባለድርሻ አካላቱ በተገኙበት አካሂዷል። በመድረኩም የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ እንደተናገሩት የገቢ ስራ የጋራ ተግባር በመሆኑ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቁመው ተቋማት፣የገቢ ጽ/ቤቶች፣የየቀበሌው መዋቅሮች በመቀናጀት መስራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ገቢ ሲሰበሰብ የሚነሱ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚያገኙ አቶ ሞሳ ኢዶሳ ጠቁመው በቁርጠኝነት መስራትና ችግሮችን እየፈቱ ወደ ፊት መሄድና የገቢ አቅምን አሟጦ በመጠቀም መስራትና መፈጸም ይገባል ብለዋል። የቀቤና ልዩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ የህያ ሃምዛ እንደተናገሩት ስራዎችን ለመስራትና የገቢ አቅምን አጠናክሮ ለመፈጸም ሁሉም ሰው ቁርጠኛ መሆን ይገባዋል ብለዋል። በ2017 በጀት ዓመት በልዩ ወረዳ የታቀደውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራሮችንና የገቢ አቅምን በማጠናከር፣ተቋማቶች ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር በባለቤትነት መንፈስ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል። የልዩ ወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ዲጋ በበኩላቸው እንደተናገሩት በልዩ ወረዳው ውስጥ የሚሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ቅንጅታዊ አሰራሩን በማጠናከር ሁሉም አካል ባለቤት ሆኖ ከጽ/ቤቱ ጋር በመቀናጀት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። የ2015 የግብር ዓመት የገቢ አፈጻጸምና የ2016 ግብር ዓመት ገቢ አሰባሰብ አጠቃላይ ሁኔታ የዳሰሰ ሰነድ የቀረበ ሲሆን የግብር አሰባሰብና የንግድ ስራ ፍቃድ ዋና ዋና ተግባራት፣የ2015 ግብር ዓመት የታክስ አፈጻጸም ስራዎች በተመሳሳይም በገቢ አሰባሰቡ ላይ በጥንካሬና በጉለት የተለዩ ስራዎች በዝርዝር ቀርበዋል። የ2016 ግብር ዓመት የግብር አሰባሰብ የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት ማስፈጸሚያ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በውስጡም ዋና ዋና ተግባራት፣ግቦች፣በገቢ አሰባሰብ ላይ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና የባለድርሻ አካላቱ ሚና ተዳሷል። በተጨማሪሞ የ2017 ዓ/ም የበጀት እቅድ የቀረበ ሲሆን የልዩ ወረዳው መንግስት ከህብረተሰቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በተቋሙ የታቀደውን እቅድ ወደ ተግባር ለመቀየርና የሚታይ ለውጥ እንዲመጣ እንደሚያስችል በሰነዱ ተመላክቷል። ታክስን በፍቃደኝነት የመክፈል ባህሉን የማሳደግ፣ዲጂታል የገቢ አስተዳደር ስርዓትን መገንባት፣ፍትሃዊነትን ማረጋገጥና የባለ ድርሻ አካላት ስትራቴጂ አጋርነትንና ትብብርን ማሻሻል እንዲገባ በተቋሙ ስትራቴጂክ አቅጣጫ በማስቀመጥ ለመፈጸም የሚያስችል ዕቅድ ቀርቧል። በቀረበው የውይይት ሰነድና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ላይ ሃሳብና አስተያየቶች ተነስተዋል ቅንጅታዊ አሰራሮችን ከማጠናከር፣ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከመስራት፣ተገቢ ቁጥጥርና ክትትል ከማድረግ፣የገቢ አቅምን በማጥናት በትኩረት እንደሚሰሩ የተቋማት ኃላፊዎች ገልጸዋል። ከባለሙያ አቅም ግንባታ ጋር በልዩ ትኩረት በመስራት በጊዜ፣በሰዓትና በወቅቱ የሚጠበቀውን ገቢ ለመሰብሰብ ዝግጁ መሆናቸውን የተቋማት ኃላፊዎች ገልጸው፣ በቀበሌ ደረጃ ያሉትን የገቢ አማራጮች በመጠቀም ከልዩ ወረዳው መንግስትና ተቋማት ጋር በትኩረት እንደሚሰሩ የቀበሌ ሊቀመናብርቶች ተናግረዋል። ህዝቡ ለሚጠይቃቸው ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት የሚቻለው በትኩረት በመስራት ፣አሰራርን ተከትሎ በመፈጸም፣ የስራ መመሪያን በመጠበቅ፣ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከርና ማንኛውንም የገቢ አቅም ተጠቅሞ በመሰብሰብ በትኩረት እንደሚሰራ የቀቤና ልዩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብድረሂም ሙዴ ጠቁመዋል። በቀረቡት ሃሳብና አስተያየቶች ላይ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ባህሩ ዲጋ ጠቁመው የጀርባ አጥንት በሆነው የገቢ ስራ ላይ ከወትሮው በተለየ ትርጉም ሰጥቶ በጋራ ተቀናጅቶ መስራት ይገባል ብለዋል። በመጨረሻም የቀቤና ልዩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ የህያ ሃምዛ ባስተላለፋት መልዕክት ውይይቱን ወደ ውጤት በመቀየር መስራት እንደሚገባ ጠቁመው የተጀመሩ ስራዎችን በማስቀጠል ቅንጅታዊ አሰራሩን በማጠናከር ችግሮችን እየቀረፉ በመሄድ፣ያሉንን እድሎች በመጠቀም በዘርፉ አርበኛ መሆን ይገባል ብለው የሚታቀዱ እቅዶችን ማሳካት እንደሚቻልም ተናግረዋል። 👉ለፈጣንና አዳዲስ መመሪያዎችን ለማግኘት 🌼Telegram channel 👉https://t.me/kebenearevenujoinch 🌼Facebook https://www.facebook.com/kebenarevenu5634 እጅ ለእጅ ተያይዘን የልዩ ወረዳችንን ልማት እናፋጥን።
Показати все...
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት (Kebena special woreda)

እጅ ለእጅ ተያይዘን የልዩ ወረዳችንን ልማት እናፋጥን!!

በልዩ ወረዳችን ለምትገኙ በየደረጃው ላላችሁ ግብር ከፋዮች በሙሉ የ2016 ዓ/ም ግብር መክፈያ ወቅት እየደረሠ በመሆኑ ከወዲሁ ለክፍያዉ በመዘጋጀት እራሳችሁን ካላስፈላጊ መቀጫ እና ወለድ አንድታድኑ የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ጥሪ ያስተላልፋል። ግብርን በወቅቱ መክፈል የአዋቂነት መገለጫ ነው !!
Показати все...
02:58
Відео недоступнеДивитись в Telegram
የኢ-ታክስ ምንነትና ጠቀሜታው... *** የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ +251 046 145 78 15 /+251 046 145 72 82 +251 046 145 49 93 / +251 046145 72 29
Показати все...
448510683_860579699226039_5646732987305751111_n.mp43.24 MB
#ማስታወቂያ የገቢዎች ሚኒስቴር በፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 115(4) በተሰጠው ሥልጣን የታክስ አሰተዳደራዊ ቅጣት አነሳስ መመሪያ ለማውጣት ረቂቅ መመሪያ ያዘጋጀ ሲሆን በረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያያት ያለው ስው አስተያየቱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣውበት ግንቦት 08/2016 ዓ/ም ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ለገቢዎች ሚኒስቴር የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ማቅረብ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ረቂቅ መመሪያውን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ፡- https://rb.gy/jtq27l
Показати все...
የገጠር መሬት መጠቀሚያ እና የእርሻ ሥራ ገቢ ግብር ጥናት እና ረቂቅ አዋጅ ላይ አብይ ኮሚቴው ውይይት አደረገ *** የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የገጠር መሬት መጠቀሚያ እና የእርሻ ሥራ ገቢ ግብር ጥናት እና ረቂቅ አዋጅ ላይ ከዚህ በፊት በቴክኒክ ኮሚቴው ከተገመገመ በኋላ በቀጣይም ከሚመለከታቸው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን፣ የወረዳ እና የልዩ ወረዳ የገቢ እና የመሬት አስተዳደር መስሪያቤት ኃላፊዎች በተገኙበት የግብዓት ማሰባሰብ ውይይት መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በዛሬው እለትም የቴክኒክ ኮሜቴው ሰብሳቢ አቶ ኡስማን ሱሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ውይይቱን የመሩ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይ ጥልቅ ውይይት ተካሄዶበታል፡፡ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘይኔ በሰጡት አስተያየት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሚገኘውን የገጠር መሬት ኪራይ እና የግብርና ሥራ ገቢ ወቅታዊና ተመጣጣኝ የክፍያ መጣኔ ተመን ጥናት የክልሉን አቅም ያገናዘበ እና የክልሉን ወጪን በክልሉ ገቢ ለመሸፈን ከሚያስችሉ የገቢ አማራጮች አንዱ የገጠር መሬት ኪራይ እና የግብርና ሥራ የገቢ ግብር በመሆኑ ከዚህ ዘርፍ የሚገኘውን ገቢ በፍትሃዊነትና በግልጸኝነት ገቢ ማሰባሰብ እንዲቻል በሕግ ማዕቀፍ የመጣኔ ተመን ለመደንገግ ታስቦ የተሰራ ጥናት መሆኑን አስታውሰው ለዚህ ጥናት ግብዕት የሚሆኑ ሀሳቦችን ማፍለቅ የሁሉም ኃለፊነት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የጥናት ሰነዱ በአምስት ክፍሎች የተደራጀ ሲሆን በክፍል አንድ አጠቃላይ መግለጫ (መግቢያ፣ የጥናቱ ዓላማ፣የጥናቱ ተዳሳሽ ችግሮች፣የጥናቱ አስፈላጊነት፣የጥናቱ ውስንነት፣ የጥናቱ ወሰን፣ የጥናቱ ስልት እና የመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎች)፣ በክፍል ሁለት የህግ ማዕቀፍ ትንተና ፣ በክፍል ሶስት የገጠር መሬት ኪራይ እና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር የመረጃ ትንተና፣ በክፍል አራት የህግ ማዕቀፍ እና የመረጃ ግኝት፣ በክፍል አምስት አማራጭ የውሳኔ ሐሳብ በሚል የተዘጋጀ ሲሆን ሰነዶቹ አቶ አበራ ወ/ጊዮርጊስ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የገቢ ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና በአቶ ደረጀ ደስታ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ አቃቤ-ህግ ቀርቧል፡፡ የቴክኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ኡስማን ሱሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ በሰነዱ ላይ የተደረገውን ውይይት የመሩ ሲሆን የሰጡ አስተያየት እና ተጨማሪ ግብአቶች ተካቶ እንዲቀርብ ማለታቸውን የዘገበው የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ነው፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ +251 046 145 78 15 /+251 046 145 72 82 +251 046 145 49 93 / +251 046145 72 29
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.