cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ። #የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል #FTM

Більше
Рекламні дописи
986
Підписники
Немає даних24 години
+77 днів
+130 днів
Час активного постингу

Триває завантаження даних...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Аналітика публікацій
ДописиПерегляди
Поширення
Динаміка переглядів
01
Media files
940Loading...
02
††† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሳሙኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል ††† ††† እሥራኤል ከግብጽ ባርነት ወጥተው ከነዓንን ከወረሱበት ዘመን ጀምረው መሳፍንትና ካህናት ያስተዳድሯቸው ነበር:: በወቅቱ ታዲያ ክህነት ከምስፍና ተስማምቶለት ኤሊ የተባለ ሊቀ ካህናትና ልጆቹ (አፍኒና ፊንሐስ) ያስተዳድሩ ጀመር:: በዘመኑ ደግሞ ማኅጸኗ ተዘግቶባት ዘወትር የምታለቅስ ሐና የሚሏት ደግ ሴት ነበረች:: እግዚአብሔር የእርሷን ጸሎትና የሊቀ ካህናቱን ምርቃት ሰምቷልና ቅዱስ ልጅን ሰጣት:: "ሳሙኤል" አለችው:: "ልመናየን አምላክ ሰማኝ" ማለት ነውና:: ሐና ስዕለቷን ትፈጽም ዘንድ ሳሙኤልን በሦስት ዓመቱ ለቤተ እግዚአብሔር ሰጠችው:: በዚያም ስብሐተ እግዚአብሔርን እየሰማ : ማዕጠንቱን እያሸተተ : ከደብተራ ኦሪቱ ሳይለይ በሞገስ አደገ:: የኤሊ ልጆች (አፍኒና ፊንሐስ) ግን በበደል ላይ በደልን አበዙ:: ወቅቱ የአሁኑን ዘመን ይመስል ነበር:: ሁሉም ሰው ክፋተኛ የሆነበት በመሆኑ : እግዚአብሔር ርቆ ስለ ነበር ትንቢትና ራዕይ ብርቅ ነበር:: አምላክ ተቆጥቷልና ሳሙኤልን በሌሊት ሦስት ጊዜ ጠራው:: ነቢዩም ታጥቆ የፈጣሪውን ቃል ሰማ:: በዚሕም የተነሳ ታቦተ ጽዮን ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ ተማረከች:: ከሰላሳ አራት ሺ በላይ ሕዝብ በኢሎፍላውያን አለቀ:: አፍኒና ፊንሐስም ተገደሉ:: ኤሊም ወድቆ ሞተ:: ከዚህች ቀን በኋላ ቅዱስ ሳሙኤል በእሥራኤል ላይ ነቢይና መስፍን ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ ሁሉ እንደሚገባው እየኖረ : የእግዚአብሔርን ለእሥራኤል : የእሥራኤልን ለእግዚአብሔር ሲያደርስ ኑሯል:: ሕዝቡ ንጉሥ በፈለጉ ጊዜ ሳዖልን ቀብቶ አነገሠላቸው:: እርሱ (ሳዖል) እንደ ሕጉ አልሔደምና ፈጣሪ ናቀው:: ሳሙኤል ግን ደግ አባት ነውና ክፋተኛውን (ሳዖልን) ከጌታው ጋር ያስታርቅ ዘንድ ብዙ ደከመ:: አለቀሰም:: እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን:- "አትዘን! እንደ ልቤ የሆነ : ፈቃዴን የሚፈጽም ዳዊትን አግኝቸዋለሁና እርሱን በእሥራኤል ላይ አንግሠው" አለው:: ቅዱስ ሳሙኤልም ወደ ቤተ ልሔም ሔዶ : ከእሴይ ልጆችም መርጦ ልበ አምላክ ዳዊትን ቀባው : አነገሠውም:: ቅዱስ ሳሙኤል በተረፈው ዘመኑ ለፈጣሪው እየተገዛ ኑሯል:: ነቢዩ ዘወትር ከእጁ የሽቱ ሙዳይና የቅብዐት እቃ (ቀንድ) አይለይም ነበረ:: እነዚህም የድንግል ማርያም ምሳሌዎች ናቸውና አባ ሕርያቆስ :- "ሙዳየ ዕፍረት ወቀርነ ቅብዕ ዘሳሙኤል" ብሎ አመስግኗታል:: ነቢዩም በወገኖቹ መካከል በዚሕች ቀን አርፏል:: እሥራኤልም አልቅሰውለታል:: ††† ቅዱስ ሉክያኖስ ††† ††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ቅዱስ ሉክያኖስ ይታሠባል:: በቀደመ ሕይወቱ ጣዖት አምላኪና አጣኝ የነበረው ቅዱሱ ማንም ሳያስተምረው ክርስቲያኖቹን በመመልከት ብቻ አምኗል:: የወቅቱ ክርስቲያኖች አኗኗራቸው : ትጋታቸው : ጽናታቸውና ፍቅራቸው እንዲሁ ይስብ ነበር:: ከእነርሱ እምነት መውጣቱን የተመለከቱ ኢ-አማንያን አታልለው ሊመልሱት ሞከሩ:: እንቢ ቢላቸው በድንጋይ ጥርሱን አረገፉት:: ደሙን አፈሰሱ:: አሁንም በሃይማኖተ ክርስቶስ በመጽናቱ በዚሕ ቀን (ሰኔ 9) ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ በመስቀል ላይ ሰቅለው ገድለውታል:: ††† የቅዱሳኑን በረከት አምላካቸው ያድለን:: ††† ሰኔ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ 2.ቅዱስ ሉክያኖስ ሰማዕት 3.ቅዱስ ዮሐንስ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ) 3. ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮጵያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) ††† "እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅንም አደረጉ . . . " ††† (ዕብ. ፲፩፥፴፪) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
930Loading...
03
Media files
740Loading...
04
††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† በዓሉ ከሰላሳ ሦስቱ ዓበይት የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚሕች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እናቱ እግር ሥር ጠበል አፍልቋል:: ††† ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን አዝላ ስደት ወጥታ ምድረ ግብጽ ትደርሳለች:: በወቅቱ ከደረሱባት ችግሮች አንዱ ደግሞ ረሃብና ጽሙ ነበር:: እንኳን ለስደተኛ በቤቱ ላለም ረሃብና ጥም እንዴት እንደሚከብድ የደረሰበት ያውቀዋል:: ††† ለዛም ነው ሊቁ በቅዳሴው:- "አዘክሪ ድንግል ረሃበ ወጽምዐ : ምንዳቤ ወኀዘነ : ወኩሎ ዐጸባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ" ያለው:: ታዲያ አንድ ቀን የበርሃው ፀሐይ አቃጥሏቸው ባረፉበት ድንግል እመቤታችን ውኃ ልመና ወጣች:: ብዙ ለመነች : ግን ጥርኝ እንኳ የሚሠጣት አጥታ በሐዘን ተመለሰች:: ስትመለስ ግን ይባስ ብሎ የልጇን ጫማ ሽፍቶች ወስደውት ደረሰች:: ያን ጊዜ ልጇን ታቅፋ "ውኃ ሳላገኝልሕ : ጫማሕንም አሰረቅኩብህ" ብላ ምርር ብላ አልቅሳለች:: "በከየት ወትቤ ማርያም ማዕነቅ:: እምሰብአ ሃገር አልቦ ዘየአምራ ለጽድቅ:: ሰአልክዎሙ ማየ ኢወሀሐቡኒ በሕቅ:: ወአሕጎልኩ ለወልድየ አሳእኖ ዘወርቅ::" እንዳለ ደራሲ:: ይሕንን የተመለከተ ልጇ የቆመችበትን መሬት ቢባርከው ሕይወትነት ያለው ማይ (ጠበል) ፈለቀ:: ጌታችን : እመቤታችን: ዮሴፍና ሰሎሜ ከውኃው ጠጥተዋል:: ሲሔዱ ግን ለእንግዶች ጣፋጭ (መድኃኒት) : ለአካባቢው ሰዎች ግን መራራ ሁኗል:: "ከመ ኢይስተይዋ ሰብአ ሐገር ለይእቲ ማይ አምረራ:: ወለርኁቃንሰ ፈውሰ ወጥዕምተ ገብራ::" እንዳለ መጽሐፍ:: (ሰቆቃወ ድንግል) ከመቶዎች ዓመታት በኋላም ጌታ ጠበል ያፈለቀበት : ድንግል እመቤታችን የቆመችበት ቦታ ላይ በእመ ብርሃን ስም ቤተ ክርስቲያን ታንጿል:: ቅዳሴ ቤቱም ተከብሯል:: ጠበሉም ሲባርክና ሲፈውስ ይኖራል:: ††† የጠበል በዓል ††† †††ዳግመኛ ዕለቱ የጠበል በዓል ተብሎም ይታሠባል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጠበል ፈዋሽነት ሁሌ ብታስተምርም በዚህ ቀን ግን ልዩ ትኩረቷ ታደርገዋለች:: እግዚአብሔር በምክንያትም አለምክንያትም መፈወስ ይችላል:: ያለ ምክንያት በቃሉና በወዳጆቹ ቃል አድሮ "ዳን" ይላል:: ወይም ደግሞ በምክንያት በእመት (እምነት) : በጠበል : ቅዱስ ቃሉን በመስማት : በመስቀሉና በመጻሕፍት በመባረክ (በመታሸት) : በቅዱሳን አካል (በልብሳቸው : በበትራቸው : በጥላቸው በአጽማቸው . . .) ይፈውሳል:: እርሱ እግዚአብሔር ነውና በወደደውና በመረጠው አድሮ ያድናል ( ይፈውሳል):: (2ነገ. 5:10, ሐዋ. 3:6, 5:15, 19:11) ††† ዛሬ ግን የጠበል ፈዋሽነት በጉልህ ይነገራል:: (ዮሐ. 5:1, 9:7) ††† አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን:: ††† ሰኔ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅዳሴ ቤት 2.የቅዱስ ውኃ (ጠበል) መታሠቢያ 3.ቅድስት ትምዳ እናታችን 4.ቅዱስ አውሎጊስ 5.አባ አትካሮን ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት 2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ) 3.አባ ብሶይ (ቢሾይ) 4.አቡነ ኪሮስ 5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን 6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት) ††† "ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ:: ግርማው በእሥራኤል ላይ: ኃይሉም በደመናት ላይ ነው:: እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው:: የእሥራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን: ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል:: እግዚአብሔርም ይመስገን:::" ††† (መዝ. ፷፯፥፴፬) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
970Loading...
05
Media files
2931Loading...
06
Media files
30Loading...
07
Media files
20Loading...
08
Media files
1920Loading...
09
††† እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ††† ††† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው : በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው:: ሊቁ የተወለደው መጋቢት 27 ቀን በ433 ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር:: አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት : ገና በ3 ዓመቱ : እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው:: ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ:: ሊቀ ዻዻሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው:: የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "አንሰ እፈርሕ ሠለስተ ግብራተ - እኔስ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ:: ††† ዻዻሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት:: እርሱም:- 1.ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ:: 2.ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ:: 3.ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው:: ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ዻዻሳቱ "እግዚአብሔር በዚሕ ሕጻን አድሮ ዘለፈን" እያሉ ለንስሃ በቅተዋል:: ቅዱስ ያዕቆብ 7 ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት:: በ5 ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ12 ዓመቱ ሊቅ ሆኗል:: በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን:: አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት:: እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው:: "እንግዲያውስ ትንቢተ ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል:: ፈጣሪንም አመስግነዋል:: ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በኋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን : ዕጸበ ገዳምን : ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል:: በድንግልናው ጸንቶ : ጾምና ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል:: በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ (በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት) ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል:: ††† በዘመኑም:- 1.የ451ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል:: 2.ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል:: 3.በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል:: 4.ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል:: በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በኋላ በተወለደ በ72 ዓመቱ በ505 ዓ/ም በዚሕች ቀን አርፏል:: አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ 27 ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ:: ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች:: ††† አምላከ ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ይክፈለን:: ††† ሰኔ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ 2.ቅዱስ : ቡሩክና አሸናፊ አባ አበስኪሮን (ታላቅ ሰማዕትና ባለ ብዙ ተአምራት ነው) 3."16,000" ሰማዕታት (በአንድ ቀን የተገደሉ) 4.የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን የተከፈተበት በዓል (ከ1ሺ ዓመታት በፊት ምስር (CAIRO) ውስጥ) ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) 2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ) 4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 5.አባ ባውላ ገዳማዊ 6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ) ††† "ይሕንን እዘዝና አስተምር :: በቃልና በኑሮ : በፍቅርም : በእምነትም : በንጽህናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው:: እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር : ለማስተማርም ተጠንቀቅ::" ††† (1ጢሞ. 4:11) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/felegetibebmedia
1721Loading...
10
Media files
1721Loading...
11
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ከሰኔ 10 -12/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በደብረዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት ። ላልሰሙት በማሰማት ከጉባኤው ተሳታፊ ያደርጉ ዘንድ ተጋብዘዋል። #FTM
2513Loading...
12
ለመቅረት የሚያሳሳ በአይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ ኦርቶዶክሳዊት መንፈሳዊ ጉባኤ በቢሾፍቱ መስቀል አደባባይ ከሰኔ 07-09/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ። ለወዳጅ ዘመዶ ሼር እያደረጉ ጉባኤውን በጋራ እናስፋው ። የፈለገ ጥበብ መረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል #FTM
1802Loading...
13
†††✝✝✝ እንኳን ለጻድቅና ሰማዕት አባ ቴዎድሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† †††✝✝✝ አባ ቴዎድሮስ †††✝✝✝ †††አባ ቴዎድሮስ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ግብፃዊ አባት ነው:: ተወልዶ ባደገባት የእስክንድርያ ከተማ ብሉያትንና ሐዲሳት በወቅቱ ከነበሩ አበው ሊቃውንት ተምሯል:: ጊዜው ምንም መናፍቃን የበዙበት ቢሆን በዛው ልክ እነ ቅዱስ እለ እስክንድሮስና ቅዱስ አትናቴዎስን የመሰሉ ቅዱሳን ሊቃውንት ነበሩና ከነሱ የሚገባውን ወስዷል:: አባ ቴዎድሮስ "አባ" ያሰኘው ሥራው:- ሲጀመር ገና በወጣትነቱ ድንግልናንና ምንኩስናን በመምረጡ ነበር:: ምንም እንኳ ሐብት ከእውቀት ጋር ቢስማማለትም ይሕ እርሱን ከምናኔ ሊያስቀረው አልቻለም:: ከከተማ ወጥቶ: በዓት ወስኖ በጾምና በጸሎት ተወሰነ:: በ340ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ግን በምዕመናን ላይ ከባድ ችግር ደረሰ:: የወቅቱ ነገሥታት በስመ ክርስቲያን አርዮሳውያን ነበሩና ሕዝቡን ማስገደድ: አንዳንዴም የአርዮስን እምነት ያልተቀበለውን ማስገደል ጀመሩ:: በዚህ ምክንያትም ታላቁ የኦርቶዶክስ ጠበቃ ቅዱስ አትናቴዎስን ከመንበሩ አሳደዱት:: በምትኩም አርዮሳዊ ሰው ዻዻስ ተብሎ ተሾመ:: ይህን ጊዜ ነው እንግዲህ እውነተኛ እረኛ ያስፈለገው:: በበዓቱ የነበረው አባ ቴዎድሮስ አላቅማማም:: ቤተ ክርስቲያን ትፈልገዋለችና መጻሕፍትን ገልጾ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ምዕመናንን ያጸናቸው ጀመር:: መናፍቃኑን ተከራክሮ ምላሽ በማሳጣት ሕዝቡን ከኑፋቄ በመጠበቅ የሠራው ሥራ ሐዋርያዊ ቢያሰኘውም ለአርዮሳዊው ዻዻስ (ጊዮርጊስ ይባላል) ሊዋጥለት አልቻለም:: በቁጣ ወታደሮችን ልኮ አባ ቴዎድሮስን ተቆጣው:: እንዳያስተምርም ገሰጸው:: አባ ቴዎድሮስ ግን እሺ ባለማለቱ ግርፋት ታዘዘበት:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲገርፉት ረድኤተ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና ከዛ ሁሉ ግርፋት አንዲቷም አካሉ ላይ አላረፈችም:: በዚህ የተበሳጨው አርዮሳዊ ዻዻስ የአባ ቴዎድሮስን እጅና እግር ከፈረስ ጋሪ በኋላ አስረው በኮረኮንች መንገድ ላይ በፍጥነት እንዲያሮጧቸው አዘዘ:: ፈረሶቹ መሮጥ ሲጀምሩ የአባ ቴዎድሮስ አካሉ ይላላጥ ጀመር:: ትንሽ ቆይቶ ግን እጆቹ ተቆረጡ:: በኋላም ራሱ ከአንገቱ ተለይታ መንገድ ላይ ወደቀች:: አካሉ በሙሉ መሬት ላይ ተበታተነ:: እግዚአብሔር ቅድስት ነፍሱን ተቀብሎ አሳረጋት:: ††† ለቅዱሱም 3 አክሊል ከሰማይ ወርዶለታል:- 1.ስለ ፍጹም ምናኔውና ድንግልናው 2.ስለ ሐዋርያዊ የወንጌል አገልግሎቱ 3.ስለ ሃይማኖቱ ደሙን አፍስሷልና "እምአባልከ ተመቲራ ለእንተ ሠረረት ርዕስ: እግዚአብሔር አስተቄጸላ በአክሊል ሠላስ" እንዳለ መጽሐፍ:: ምዕመናን ሥጋውን ሰብስበው በዝማሬና በማኅሌት በክብር ቀብረውታል:: ††† አምላካችን ከቅዱሱ በረከት ይክፈለን:: ††† ሰኔ 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ቴዎድሮስ ሰማዕት 2.አባ ገብረ ክርስቶስ 3."40" ሰማዕታት ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅድስት ደብረ ቁስቋም 2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን 3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል 4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ 5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ 6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ 7.ቅድስት ሰሎሜ 8.አባ አርከ ሥሉስ 9.አባ ጽጌ ድንግል 10.ቅድስት አርሴማ ድንግል ††† "መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ:: ሩጫውን ጨርሻለሁ:: ሃይማኖቴን ጠብቄአለሁ:: ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል:: ይህንም ጻድቅ: ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያሰረክባል:: ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም::" ††† (2ጢሞ. 4:7) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††✝✝✝ " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/felegetibebmedia
1950Loading...
14
Media files
1790Loading...
15
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ከሰኔ 10 -12/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በደብረዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት ። ላልሰሙት በማሰማት ከጉባኤው ተሳታፍ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል። #FTM
1972Loading...
16
ለመቅረት የሚያሳሳ በአይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ ኦርቶዶክሳዊት ተ?መንፈሳዊ ጉባኤ በመስቀል አደባባይ ከሰኔ 07-09/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ። ለወዳጅ ዘመዶ ሼር እያደረጉ ጉባኤውን በጋራ እናስፋው ። የፈለገ ጥበብ መረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል #FTM
85830Loading...
17
Media files
1970Loading...
18
††† እንኳን ለኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ ብሶይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ አባ ብሶይ ሰማዕት ††† ††† ቅዱሱ አባታችን ከዘመነ ሰማዕታት ጣፋጭ ፍሬዎች አንዱና ግንባር ቀደሙ ነው:: ††† ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ማጠናቀቂያ አካባቢ ታግሕስጦስና ክሪስ የሚባሉ ክርስቲያኖች ነበሩ:: በቀናው የጽድቅ ጐዳና ቢኖሩም ከጋብቻ በኋላ ለአሥራ ሰባት ዓመታት መውለድ አልቻሉም:: የአሥራ ሰባት ዓመት ልመናቸውን የተመለከተ እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ አበሰራቸው:: "ሕፃኑ ለሰማዕትነት ተመርጧልና ብሶይ በሉት" አላቸው:: ብሶይ በተወለደ በሰባት ዓመቱ ወላጆቹ ይማር ብለው ወደ ገዳም ወሰዱት:: በገዳም ውስጥ መጻሕፍትን አጥንቶ ዲቁናን ተሾመ:: ወደ ዓለም ተመለስ ቢሉትም እንቢ አለ:: ከባልንጀራው ቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ለሃያ አንድ ዓመታት በድንግልና : በተጋድሎ : ጾምና ጸሎትን እያዘወተሩ ኖሩ:: ቅዱስ ብሶይ ሃያ ስምንት ዓመት በሞላው ጊዜ መልአኩ የተናገረው የትንቢት ዘመን ደረሰ:: በርካታ ምዕመናን ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ታረዱ:: ወደ እሳትም ተጣሉ:: ሞትን የፈሩ ደግሞ በየዱር ገደሉ ተሰደዱ:: ቅዱስ ብሶይም በሚያውቁት ሰዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ:: ድንገት ከሰማይ ፍጡነ ረድኤት ወሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ደረሰለት:: "አይዞሕ! እኔ እስከ መጨረሻው ከአንተ ጋር ነኝ" አለው:: የጦር መኮንኑ ክርስቶስን እንዲክድ አባበለው:: ቅዱሱ ግን ጣዖታቱ የአጋንንት ማደሪያ መሆናቸውን በገሃድ ነገረው:: መኮንኑ ቢበሳጭ ወታደሮቹ እንዲጨምቁት አዘዘ:: ደሙ እየወረደ ገረፉት:: በፊትና በኋላ ብረት አድርገው ሥጋውን ጨፍልቀው እሥር ቤት ውስጥ ጣሉት:: ሊቀ መላእክት መጥቶ ዳስሶ አዳነው:: መኮንኑ እርሱን ማሰቃየት ደከመው:: የቅዱሳን ሕይወት ግርም ይላል:: ተገራፊው እያለ ገራፊው : ስቃዩን የሚቀበለው እያለ አሰቃዩ ይደክመዋል:: ††† ይሕንን መሰለኝ አባ ጽጌ ድንግል:- "እመዐዛ ጽጌኪ ድንግል ውስተ ዐውደ ስምዕ ዘሰክረ:: ውግረተ አዕባንኒ ይመስሎ ሐሰረ:: እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ" ያለው:: ቅዱስ ብሶይን ከአንዱ መኮንን ወደ ሌላው እያመላለሱ አሰቃዩት:: አካሉን ቆራረጡት:: ዓይኑን በጋለ ብረት አወጡት:: በምጣድ ቆሉት:: በጋን ውስጥ ቀቀሉት:: እርሱ ግን በፈጣሪው ፍቅር የጸና ነውና ሁሉን ታገሰ:: በነዚሕ ሁሉ የስቃይ ዓመታት ቁራሽ ዳቦ እንኳ አላቀመሱትም:: በረሃብ ቀጡት እንጂ:: ለእርሱ ግን ምግቡ የክርስቶስ ስም ነበር:: በመጨረሻ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ አንገቱን በሰይፍ አስመታው:: ሥጋውንና የተቆረጠ አንገቱን ገንቦ (ጋን) ውስጥ ከቶ ጣለው:: የቅዱሱን አካል የያዘችው ጋን ግን በእግዚአብሔር ቸርነት : ማንም ሳይሸከማት ከመሬት ከፍ አለች:: ለሃያ ቀናት ተጉዛ ከሶርያ ግብጽ (ቦሃ) ደረሰች:: ክርስቲያኖች ተቀብለው ሲከፍቷት የቅዱስ ብሶይ ራሱና አንገቱ ተጣብቆ ተገኝቷል:: በክብርም አሳርፈውታል:: ††† ቅዱስ ያዕቆብ ††† ††† ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጻድቅና ተአማኒ (ታማኝ) የተባለ የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል:: ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር የነበረ አባት ነው:: ከቅድሰና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ (ጥብዐቱ) ይታወቃል:: በ340ዎቹ ዓ/ም ታናሹ ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ ገስጾታል:: በዚህም ምክንያት መከራን ተቀብሏል:: ታስሯል:: ተገርፏል:: እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት ቀስፎታል:: ቅዱሱ በዚህች ቀን ዐርፎ ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔዷል:: ††† ቸር አምላክ ከሰማዕቱ ቅዱስ ብሶይ እና ከቅዱስ ያዕቆብ በረከት ያሳትፈን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን:: ††† ሰኔ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ብሶይ (ኃያል ሰማዕት) 2.ቅድስት ማርታ ለባሲተ ክርስቶስ (በቅድስናዋ የተወደሰች : በስደት ያረፈች እናት ናት::) 3.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ 4.ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት 5.ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት 6.ቅዱስ መርቆሬዎስና ማኅበሩ (ሰማዕታት) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት 2.ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ 3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ 5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ 6.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ) ††† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ : ወይስ ጭንቀት : ወይስ ስደት : ወይስ ራብ : ወይስ ራቁትነት : ወይስ ፍርሃት : ወይስ ሰይፍ ነውን? "ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን" ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" ††† (ሮሜ. ፰፥፴፭-፴፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
2061Loading...
19
Media files
10Loading...
20
የማይቀርበት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በመስቀል አደባባይ
1 10438Loading...
21
Media files
2300Loading...
22
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ሰኔ ፬ ❖ ✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁዋ ሰማዕት "ቅድስት ሶፍያ" እና ለቅዱስ "ዮሐንስ ዘሐራቅሊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +*" #ሶፍያ (SOPHIA) "*+ =>ሶፍያ ("ያ" የሚለው ላልቶ ይነበብ) በቀደመው ዘመን በነበሩ ክርስቲያኖች ዘንድ ተወዳጅ ስም ነበር:: ዛሬ ብዙ አሕዛብ ሲጠሩበት ብንሰማም ትርጉሙ "ጥበበ ክርስቶስ" የሚል ነው:: በዚህ ስም የሚጠሩ አያሌ ቅዱሳት አንስት ሲኖሩ አንዷ ዛሬ ትከበራለች:: +*" ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት "*+ =>ቅድስቷ የተወለደችው በምሥራቅ ሮም ግዛት ውስጥ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ዘመኑ የጭንቅ : የመከራ በመሆኑ ሕዝቡ በስደት ይኖር ነበር:: +የቅድስት ሶፍያ ወላጆች ክርስቲያኖች ናቸውና በመልካሙ መንገድ በንጽሕና አሳድገዋታል:: ባለጠጐች በመሆናቸው አገልጋይ ቀጥረውላት : ያማረ ቤት ሰርተውላት በዚያ ትኖር ነበር:: ሁሉ ያላት ብትሆንም ሁሉን ንቃ በጾምና በጸሎት ትኖር ነበር:: +ለዐቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ ወላጆቿ ለከተማው መኮንን (ገዢ) ሊድሯት መሆኑን አወቀች:: ወደ ቤቷ ገብታ 100 ጊዜ ሰገደች:: ወደ ፈጣሪዋም ጸለየች:- "ጌታየ ሆይ! የዚህን ዓለም ቀንበር አታሸክመኝ:: አልችለውምና:: ያንተው ቀንበር ግን የፍቅር ነውና እችለዋለሁ" አለች:: +አገልጋዩዋን ጠርታ ብዙ ወይን አጠጥታት ልብስ ተቀያየሩ:: በሌሊትም ወጥታ ወደ በርሃ ሔደች:: ዓላማዋ ምናኔ ቢሆንም የእግዚአብሔር ፈቃዱ ግን ሌላ ነበር:: በመንገድ ብዙ ክርስቲያኖች በመከራ ብዛት ሲሰደዱ አገኘቻቸው:: እርሷ ስደትን አልመረጠችም:: +እያጠያየቀች "ሰው በላ" ከተባለው አረመኔ ንጉሥ ዲዮቅልጢያኖስ ደረሰች:: በንጉሡ ፊት ቀርባ "እኔ ክርስቲያን ነኝ" አለችው:: ንጉሡ ከመልኩዋ ማማርና ከድፍረቷ የተነሳ አደነቀ:: +ሊያባብላት: ሊያስፈራራትም ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው ጦር ባለው የብረት ዘንግ ደብድበዋታልና ደም አካባቢውን አለበሰው:: መሬት ለመሬት እየጐተቱ እሥር ቤት ውስጥ ጣሏት:: ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ፈውሷት ሔደ:: +አንዴ በእሳት: አንዴም በስለት: ሌላ ጊዜም በግርፋት አሰቃዩዋት:: ከሃይማኖቷ ግን ሊያነቃንቁዋት አልቻሉም:: በመጨረሻ አንገቷን እንድትሰየፍ ንጉሡ አዘዘ:: ወታደሮቹም ፈጸሙት:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቅድስት ሶፍያን በክብር አሳረጋት:: "ስምሽን የጠራ: መታሰቢያሽን ያደረገ ምሕረትን ያገኛል" አላት:: +"+ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ +"+ =>ቅዱሱ የነበረው በተመሳሳይ በዘመነ ሰማዕታት ነው:: አባቱ ዘካርያስ: እናቱ ኤልሳቤጥ: እርሱ ደግሞ ዮሐንስ ይባላል:: የሚገርም መንፈሳዊ ግጥጥሞሽ ነው:: የቅዱሱ ወላጆች የሃገረ ሐራቅሊ አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ የተመሰከረላቸው ደጐች ነበሩ:: +ዘካርያስ አርፎ ዮሐንስ በመንበሩ የተቀመጠው ገና በ20 ዓመቱ ነበር:: በወቅቱ ከ2 አንዱን መምረጥ ነበረበት:: 1.ለጣኦት ሰግዶ በምድራዊ ክብሩ መቀጠል 2.ወይ ደግሞ በክርስትናው መሞት +ቅዱስ ዮሐንስ ግን ልቡ በክርስቶስ ፍቅር የተሞላ ነውና 2 ከባባድ ነገሮችን ፈጸመ:: በመጀመሪያ በአካባቢው ያሉ ጣዖት ቤቶችን አወደመ:: ቀጥሎ ወደ ንጉሡ ሔዶ በመኩዋንንቱ ፊት "ክርስቶስን የተውክ ሰነፍ" ብሎ ገሠጸው:: +ከዚህ በኋላ በቅዱሱ ላይ የተፈጸመው መከራ የሚነገር አይደለም:: ያላደረጉት ነገር አልነበረም:: እሳቱ: ስለቱ: ሰይፉ: መንኮራኩሩ . . . ከሁሉ የከፋው ግን ቆዳውን ገፈው በእሳት ጠብሰውታል:: እርሱ ግን ስለ ሃይማኖቱ ይሕንን ሁሉ ታግሶ በዚህች ቅን አንገቱን ተሰይፏል:: =>አምላካችን እግዚአብሔር ግፍዐ ሰማዕታትን አስቦ እኛን ከሚመጣው መከራ ሁሉ ይሰውረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: =>ሰኔ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት ወሰማዕት 2.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት) 3.ቅዱስ ሳኑሲ ሰማዕት 4.ቅድስት ማርያ ሰማዕት 5.ቅዱስ አርቃድዮስና ባልንጀሮቹ (ሰማዕታት) 6.ቅዱስ አሞን ሰማዕት ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ 2፡ ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ =>+"+ እንግዲሕ አትፍሯቸው:: የማይገለጥ የተከደነ: የማይታወቅም የተሠወረ ምንም የለምና:: በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ:: በጀሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ:: ሥጋንም የሚገድሉትን: ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ:: ይልቅስ ነፍስንም: ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ:: +"+ (ማቴ. 10:26) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/felegetibebmedia
2310Loading...
23
Media files
2270Loading...
24
††† ✝እንኳን ለኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን እና ለእናታችን ቅድስት ማርታ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን። †††✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† አቡነ ተጠምቀ መድኅን ††† ††† ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ1610 ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው #ወልደ_ክርስቶስና #ወለተ_ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ 2 ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር 11 ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ #ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ #ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ #ጸጋ_እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ:: ሕጻን እያሉ #ቃለ_እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም:: ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን: ነብሩን: ተኩላውን ሰብስበው:- "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ: ከፍየሉ: ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን: ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ:: ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: 23 ዓመት ሲሞላቸው ወደ #መርጡለ_ማርያም ሔደው መንኩሰዋል:: ከዚሕ ጊዜ በሁዋላ ለ37 ዓመታት:- 1.በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል 2.ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል 3.ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል (ካህን ናቸውና) 4."7" ገዳማትንና "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል:: ††† ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ60 ዓመታቸው በ1670 ዓ/ም (በአፄ #ዮሐንስ_ጻድቁ ዘመን) ዐርፈዋል:: እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ #በጋሾላ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል:: ††† ቅድስት ማርታ ††† ††† እናታችን ቅድስት ማርታ በቀደመ ሕይወቷ እጅግ ኃጢአቷ የበዛ ሴት ነበረች:: እጅግ ቆንጆ መሆኗን ሰይጣን ለኃጢአት እንድትጠቀምበት አባበላት:: እርሷም ተቀበለችው:: በወጣትነት ዘመኗ በመልኩዋና በገላዋ በርካቶችን ወደ ኃጢአት ሳበች:: መጽሐፍ እንደሚል ለሁሉም ሰው የመዳን ቀን ጥሪ አለውና አንድ ቀን (በበዓለ ልደት) ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች:: ዘበኛው ግን ሲያያት ተጸይፏልና አትገቢም አላት:: ተከራከረችው: ለመነችው:: ግን አልተሳካላትም:: ሰዓቱ የቅዳሴ ቢሆንም እርሷ እሪ አለች:: ለቅዳሴ የቆሙ ሁሉ በመታወካቸው ዻዻሱ ወጥቶ ገሰጻት:: ያን ጊዜ ነበር ወደ ልቧ የተመለሰችው:: በጉልበቷ ተንበርክካ መራራ ለቅሶን አለቀሰች:: ዻዻሱንም ተማጸነችው:- "እጠፋ ዘንድ አትተወኝ:: ወደ ጌታየ አድርሰኝ" አለችው:: ወዲያውም ወደ ቤቷ ሔዳ የዝሙት እቃዋን አቃጠለች:: ጸጉሯን ተላጨች:: ንብረቷን ሁሉ ለነዳያን አካፈለች:: ዻዻሱም ንስሃ ሰጥቶ ወደ ገዳም አሰናበታት:: ወደ ገዳም ገብታ: በዓት ተቀብላ: ጾምና ጸሎትን ከእንባ ጋር አዘወተረች:: ለ25 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ከበዓቷ ሳትወጣ: አንድም ሰው ሳታይ ኖረች:: ከማረፏ በፊትም ብዙ ተአምራትን አድርጋለች:: ††† የቅዱሳን አምላክ ለእኛም እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሐ አይንሳን:: ከበረከታቸውም ያድለን:: ††† ††† ሰኔ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ማርታ ተሐራሚት 2.አቡነ ተጠምቀ መድኅን ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) 3.ቅዱስ ኢላርዮን ሰማዕት 4.ቅዱስ ኮርዮን ሰማዕት †††ወርኀዊ በዓላት 1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን) 4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ 5.አቡነ ዜና ማርቆስ 6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል ††† "አልሞትም: በሕይወት እኖራለሁ እንጂ:: የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ:: መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ:: ለሞት ግን አልሠጠኝም:: የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ:: ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ:: ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት:: ጻድቃን ወደ እርስዋ ይገባሉ:: ሰምተኸኛልና: መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ::" †††  (መዝ. 117:17-22) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
2270Loading...
25
††† እንኳን ለቅዱሳን ነቢያት ዮሐንስና ኤልሳዕ ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ††† †††የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ:- ¤በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ ¤በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ¤በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ ¤እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ ¤የጌታችንን መንገድ የጠረገ ¤ጌታውን ያጠመቀና ¤ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው:: ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን:- ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች:: ††† ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ ††† ††† ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ ኤልሳዕ:- ¤ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ ¤መናኔ ጥሪት የተባለ ¤በድንግልና ሕይወት የኖረ ¤የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት ¤እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ ¤አንዴ በሕይወቱ : አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው:: ቅዱሳት መጻሕፍት ሁለቱን ቅዱሳን በመልካቸውም ይገልጿቸዋል:: ቅዱስ ዮሐንስ ¤ቁመቱ ልከኛ ¤አካሉ በጸጉር የተሸፈነ ¤የራሱ ጸጉር በወገቡ ¤ጽሕሙ እስከ መታጠቃያው የወረደ ¤ግርማው የሚያስፈራ የ31 ዓመት ጎልማሳ ነበር:: ቅዱስ ኤልሳዕ ¤በጣም ረዥም ¤ራሱ ገባ ያለ (ራሰ በራ) ¤ቀጠን ያለ ¤ፊቱ ቅጭም ያለ (የማይስቅ) ሽማግሌ ነበር:: በዚሕች ቀን በ350 ዓ/ም አካባቢ የሁለቱም ቅዱሳን አጽም ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ ፈልሷል:: በወቅቱ ክፋተኛ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር:: ለዚሕ እንዲረዳው በ70 ዓ/ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም 3 ጊዜ ፈረሰበት:: ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ እሱን አውጥተህ አቃጥል" አሉት:: ሲቆፈር በመጀመሪያ የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው : ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል:: እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል:: በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል:: በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል:: ††† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅር ያድለን:: †††ሰኔ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ፍልሠቱ) 2.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ፍልሠቱ) 3.አባ ቀውስጦስ ኢትዮዽያዊ †††ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ 3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ 4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ) 5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ 6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ †††"ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ::" ††† (ማቴ. 11:7-15) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/felegetibebmedia
2130Loading...
26
Media files
2240Loading...
27
ይህንን ያውቃሉ??
2111Loading...
28
Media files
2410Loading...
29
✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✝✞✞✞ ❖ ✝እንኳን አደረሳችሁ ✝❖ ❖ ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ_ዮሴፍ_ጻድቅ +"+ =>ቤተ_ክርስቲያን በዚህ ስም ብዙ ቅዱሳን አሏት:: በተለይ ደግሞ እስራኤል የተባለ የቅዱስ_ያዕቆብ ልጅ ቅዱስ ዮሴፍ ከሁሉም ቅድሚያውን ይይዛል:: ታላቁ ቅዱስ_መጽሐፍ ላይ በስፋት ታሪካቸው ከተጻፈላቸው ቅዱሳን አንዱ ነው:: +ስለዚህ ቅዱስ ዝርዝር መረጃን ለማግኘት ኦሪት_ዘፍጥረትን ከምዕራፍ 39 እስከ 50 ድረስ ማንበብ ይኖርብናል:: ከዚህ በተረፈም በዜና ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሱ ብዙ ተብሏል:: +መጽሐፍ ቅዱስ ሲጀምር ስለ ቅዱስ ሰው አዳም ይነግረናል:: ቀጥሎም ስለ ቅዱሳኑ ሴት ሔኖክ ኖኅ ሴም አብርሃም ይስሐቅና ያዕቆብ ነግሮን ቅዱስ_ዮሴፍ ላይ ይደርሳል:: +ቅዱስ ዮሴፍ ያዕቆብ (እስራኤል) ከሚወዳት ሚስቱ ራሔል ከወለዳቸው 2 የስስት ልጆቹ አንዱ ነው:: ቅዱሱ ምንም እናቱ ብትሞተበትም በአባቱና በፈጣሪው ፊት ሞገስ ነበረው:: ምክንያቱም ቅን: ታዛዥና የፍቅር ሰው ነበርና:: +እንዲያ አምርረው ለሚጠሉት ወንድሞቹ እንኳን ክፋትን አያስብም ነበር:: ይልቁኑ ለእነሱ ምሳ (ስንቅ) ይዞ ሊፈልጋቸው በበርሃ ይንከራተት ነበር እንጂ:: +መንገድ ላይ ቢርበው አለቀሰ እንጂ ስንቃቸውን አልበላባቸውም:: የአባቶቹ አምላክ ግን ድንጋዩን ዳቦ አድርጐ መግቦታል:: 10ሩ ወንድሞቹ ግን ስለ በጐነቱ ፈንታ ሊገድሉት ተማከሩ:: ከፈጣሪው አግኝቶ በነገራቸው ሕልም "ሊነግሥብን ነው" ብለው ቀንተውበታልና:: +በፍጻሜው ግን በይሁዳ መካሪነት ለዐረብ ነጋድያን ሸጠውታል:: በዚህም ለምስጢረ ሥጋዌ (ለጌታ መሸጥና ሕማማት) ምሳሌ ለመሆን በቅቷል:: ወንድሞቹ ለክፋት ቢሸጡትም ቅሉ ውስጡ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበትና በባርነት በተሸጠበት በዺጥፋራ ቤት ፈጣሪው ሞገስ ሆነው:: +ወጣትነቱን በፍቅረ እግዚአብሔር ሸብ አድርጐ አስሮ ነበርና የዺጥፋራ ሚስት የዝሙት ጥያቄ አላንበረከከውም:: "ማንም አያየንም" ስትለውም "እፎ እገብር ኃጢአተ በቅድመ እግዚአብሔር" (ማንም ባያይስ እንዴት በፈጣሪየ ፊት ኃጢአትን አሠራለሁ?) በማለት ከበደል አምልጧል:: ስለዚህ ፈንታም የእሥር ቅጣት አግኝቶታል:: +ጌታ ከእርሱ ጋር ቢሆን በእሥር ቤትም ሞገስን አገኘና አለቅነትን ተሾመ:: "ኢኀደረ ዮሴፍ ዘእንበለ ሲመት" እንዲል መጽሐፍ:: ከዚያም የንጉሡን (የፈርዖንን) ባለሟሎች ሕልም ተረጐመ:: ቀጥሎም ንጉሡን በሕልም ትርጓሜ አስደመመ:: ፈርዖንም ቅዱሱን በግዛቱ (ግብጽ) ላይ ሾመው:: +ቅዱስ ዮሴፍ በምድረ ግብጽ ነግሦ ሕዝቡን ከረሃብ ታደገ:: ለቅዱስ አባቱ ለእሥራኤልና ክፉ ለዋሉበት ወንድሞቹም መጋቢ ሆናቸው:: አስኔት (አሰኔት) የምትባል ሴት አግብቶም ኤፍሬምና ምናሴ የተባሉ ልጆችን አፍርቷል:: +በመንገዱ ሁሉ እግዚአብሔርን አስደስቶ: ከአባቱ ዘንድም ምርቃትና በረከትን ተቀብሎ በ110 ዓመቱ በዚህች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፏል:: ወገኖቹም በክብርና በእንባ ቀብረውታል:: "አጽሜን አፍልሱ" ብሎ በተናገረው ትንቢት መሠረትም ልጆቹ (እነ ቅዱስ ሙሴ) ከግብጽ ባርነት ሲወጡ አጽሙን ወደ ከነዓን አፍልሠዋል:: +" ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት "+ =>ቅዱሱ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት ነገሥታቱን ያገለግል ነበር:: ድንግል: ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው:: +እርሱ ግን ምን ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ ይጸልየው: ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የታሸ ነውና ብዙ ጉዋደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት: ከክፋት ወደ ደግነት መልሷል:: +የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ ጊዜም አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት: ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር:: +በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገቱን ተሰይፏል:: ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና በእምነት እንጥራው:: ቤተ ክርስቲያንም ዛሬ የቅዱሱን ተአምራት ታስባለች:: ቅዳሴ ቤቱም የተከበረው በዚሁ ዕለት ነው:: =>አምላከ ቅዱሳን ወርኀ ሰኔን የፍሬ: የበረከት: የንስሃና የጽድቅ አድርጐ ይስጠን:: ከሰማዕቱ ጽናትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: =>ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (የያዕቆብ ልጅ) 2.እናታችን አስኔት (የቅ/ ዮሴፍ ሚስት) 3.ቅዱስ ለውንትዮስ ክቡር ሰማዕት 4.ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት 5.ቅዱስ ቆዝሞስ ሰማዕት ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ልደታ ለማርያም 2፡ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 3፡ ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ 4፡ ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት 5፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና =>+"+ እንዲህም አላቸው:- "ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ:: አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ አትዘኑ:: አትቆርቆሩም:: እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከእናንተ በፊት ሰዶኛልና . . . እግዚአብሔርም በምድር ላይ ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ: በታላቅ መድኃኒትም አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ::" +"+ (ዘፍ. 45:4-8) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/felegetibebmedia
2381Loading...
30
Media files
2520Loading...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
††† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሳሙኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል ††† ††† እሥራኤል ከግብጽ ባርነት ወጥተው ከነዓንን ከወረሱበት ዘመን ጀምረው መሳፍንትና ካህናት ያስተዳድሯቸው ነበር:: በወቅቱ ታዲያ ክህነት ከምስፍና ተስማምቶለት ኤሊ የተባለ ሊቀ ካህናትና ልጆቹ (አፍኒና ፊንሐስ) ያስተዳድሩ ጀመር:: በዘመኑ ደግሞ ማኅጸኗ ተዘግቶባት ዘወትር የምታለቅስ ሐና የሚሏት ደግ ሴት ነበረች:: እግዚአብሔር የእርሷን ጸሎትና የሊቀ ካህናቱን ምርቃት ሰምቷልና ቅዱስ ልጅን ሰጣት:: "ሳሙኤል" አለችው:: "ልመናየን አምላክ ሰማኝ" ማለት ነውና:: ሐና ስዕለቷን ትፈጽም ዘንድ ሳሙኤልን በሦስት ዓመቱ ለቤተ እግዚአብሔር ሰጠችው:: በዚያም ስብሐተ እግዚአብሔርን እየሰማ : ማዕጠንቱን እያሸተተ : ከደብተራ ኦሪቱ ሳይለይ በሞገስ አደገ:: የኤሊ ልጆች (አፍኒና ፊንሐስ) ግን በበደል ላይ በደልን አበዙ:: ወቅቱ የአሁኑን ዘመን ይመስል ነበር:: ሁሉም ሰው ክፋተኛ የሆነበት በመሆኑ : እግዚአብሔር ርቆ ስለ ነበር ትንቢትና ራዕይ ብርቅ ነበር:: አምላክ ተቆጥቷልና ሳሙኤልን በሌሊት ሦስት ጊዜ ጠራው:: ነቢዩም ታጥቆ የፈጣሪውን ቃል ሰማ:: በዚሕም የተነሳ ታቦተ ጽዮን ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ ተማረከች:: ከሰላሳ አራት ሺ በላይ ሕዝብ በኢሎፍላውያን አለቀ:: አፍኒና ፊንሐስም ተገደሉ:: ኤሊም ወድቆ ሞተ:: ከዚህች ቀን በኋላ ቅዱስ ሳሙኤል በእሥራኤል ላይ ነቢይና መስፍን ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ ሁሉ እንደሚገባው እየኖረ : የእግዚአብሔርን ለእሥራኤል : የእሥራኤልን ለእግዚአብሔር ሲያደርስ ኑሯል:: ሕዝቡ ንጉሥ በፈለጉ ጊዜ ሳዖልን ቀብቶ አነገሠላቸው:: እርሱ (ሳዖል) እንደ ሕጉ አልሔደምና ፈጣሪ ናቀው:: ሳሙኤል ግን ደግ አባት ነውና ክፋተኛውን (ሳዖልን) ከጌታው ጋር ያስታርቅ ዘንድ ብዙ ደከመ:: አለቀሰም:: እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን:- "አትዘን! እንደ ልቤ የሆነ : ፈቃዴን የሚፈጽም ዳዊትን አግኝቸዋለሁና እርሱን በእሥራኤል ላይ አንግሠው" አለው:: ቅዱስ ሳሙኤልም ወደ ቤተ ልሔም ሔዶ : ከእሴይ ልጆችም መርጦ ልበ አምላክ ዳዊትን ቀባው : አነገሠውም:: ቅዱስ ሳሙኤል በተረፈው ዘመኑ ለፈጣሪው እየተገዛ ኑሯል:: ነቢዩ ዘወትር ከእጁ የሽቱ ሙዳይና የቅብዐት እቃ (ቀንድ) አይለይም ነበረ:: እነዚህም የድንግል ማርያም ምሳሌዎች ናቸውና አባ ሕርያቆስ :- "ሙዳየ ዕፍረት ወቀርነ ቅብዕ ዘሳሙኤል" ብሎ አመስግኗታል:: ነቢዩም በወገኖቹ መካከል በዚሕች ቀን አርፏል:: እሥራኤልም አልቅሰውለታል:: ††† ቅዱስ ሉክያኖስ ††† ††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ቅዱስ ሉክያኖስ ይታሠባል:: በቀደመ ሕይወቱ ጣዖት አምላኪና አጣኝ የነበረው ቅዱሱ ማንም ሳያስተምረው ክርስቲያኖቹን በመመልከት ብቻ አምኗል:: የወቅቱ ክርስቲያኖች አኗኗራቸው : ትጋታቸው : ጽናታቸውና ፍቅራቸው እንዲሁ ይስብ ነበር:: ከእነርሱ እምነት መውጣቱን የተመለከቱ ኢ-አማንያን አታልለው ሊመልሱት ሞከሩ:: እንቢ ቢላቸው በድንጋይ ጥርሱን አረገፉት:: ደሙን አፈሰሱ:: አሁንም በሃይማኖተ ክርስቶስ በመጽናቱ በዚሕ ቀን (ሰኔ 9) ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ በመስቀል ላይ ሰቅለው ገድለውታል:: ††† የቅዱሳኑን በረከት አምላካቸው ያድለን:: ††† ሰኔ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ 2.ቅዱስ ሉክያኖስ ሰማዕት 3.ቅዱስ ዮሐንስ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ) 3. ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮጵያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) ††† "እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅንም አደረጉ . . . " ††† (ዕብ. ፲፩፥፴፪) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Показати все...