cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

basnael

basnael chanal xebedawi serawoch gexem ena kal music . . . 🎼🎶🎤🎵〽 . . . 🎻🎺🎷🎹 . . @alembeqagn Eyesus yadnal

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
137Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ልዩ የውይይት ጊዜ በ አማኑኤል ባብቲስት ቤተክርስቲያን እምነት ምንድነው ? መፅሐፍ ቅዱስስ እንዴት ይፈታል ? መልሶትን በሕብረት እና በውይይት ማወቅ ከፈለጉ 9/8/2013 ቅዳሜ ከቀኑ 10:30, ጀምሮ አይቀርም!!!!!!!!!!!!!!!!! @adama___01qebele_condeminyemu_fitltfit_50meter_geba_belo
Показати все...
ሰው መሆን የጊዜ እስረኛ መሆን ነው። - ሌላ ሰው ጊዜ የዘላለም አሽከር ሲሆን፣ ሰው ደግሞ የጊዜ ባሪያ ነው። ሰው ጊዜን በደቂቃና በሰዓት፣ በወራትና በዓመታት ሸንሽኖ፣ ከግድግዳው ላይም ሰቅሎ በእጁ ላይ ጠፍሮ ሊገዛው ልቆጣጠረው ይሞክራል። ጊዜ ደግሞ ሰውን ከልጅነት ወደ ወጣትነት፣ ከጉልምስና ወደ እርጅና እያክለፈለፈ ከሞት ደጃፍ ያደርስና መቃብር ይጨምረዋል። በክረምትና በበጋ፣ በጸደይና በመጸው እየተመሰለ መልኩን እየቀያየረ ሲመጣና ሲሄድ፣ ሲዞርና ሲፈራረቅ፣ ... የጊዜ ጉዞ ያዙሪት እንጂ የወደፊት አይመስልም። በድል ፈረስ ላይ ተቆናጦ በስኬትና በውድቀት፣ በቀጠሮና በድንገት፣ በጥበቃና በጥድፊያ ተጠቅሞ የሰውን እጣ ፈንታ የሚወስን ጊዜ መሆኑን በቀላሉ እንዘነጋለን። ጊዜን መግዛት ሲባል ራስን እንጂ ጊዜን ማስገዛት አይደለም። በጊዜ ውስጥ ትናንትን የትዝታ፣ ነገ ደግሞ የተስፋ ጎተራ ናቸው። ካመለጠ ትናንት ... ያልመጣ ነገ ይሻላል። #በእጅ_ያለ_ዛሬ_ግን_ከሁሉም_ይበልጣል። ዛሬ ሁሌም ያለ እየመሰለ የማደገም ... ተመልሶም የማይመጣ ... ላንድ አፍታ ለቀጽበት ታይቶ ዳርቻ ከሌለው የዘላለም ጠፈር ገብቶ የሚሰወረ ... በትናንትና በነገ መሃል የተሸነቆረ እንቁ ነው። #የዛሬ ምስጢሩና ጉልበቱ ያለው ደግሞ አሁን ላይ ነው። ' ቅድም' እና 'በኋላ' ግን ያለቦታቸው ዛሬ ውስጥ የተደነቀሩ የትናንትና የነገ ሽርፍራፍዎች ናቸው። D.r mhret Debeb ( ሌላ ሰው ) @seb_ena @seb_ena
Показати все...
🖌አበርታኝ🖌🙇‍♀️ ✍️የተቀበልኩህለት~ያኔ እንዳወኩህ ድሮ እተጋ ነበር~አሁን ግን ዝያለሁ ከመሰዊያዬ ላይ~ከራቅሁ ሰነበትኩ ትናንት ምራበውን~ፀሎቴን ችላ አልኩ : ✍️ስምህን ለማውራት~ሰበብ እንዳልፈለኩ ✍️አሁን ግን ቀሎብኝ~መናገሬን አቆምኩ ✍️በፊትህ ወድቄ~ላወራህ እንዳልሮጥኩ ✍️ዛሬ ግን በአለም~ግሳንግስ ተወጠርኩ : ትናንት..እንዳልቀለለብኝ~ካንተ ወዲያ ወሬ ፀሎት ስባል አሁን~ትቼ እጠፋለሁ ሰበቤን ደክሬ ሰው መሳይ በሸንጎ~በጓዳዬ ከንቱ..... እንደሆንኩ ተሰማኝ~አበርታኝ አቤቱ : ምን እንደሁ ባላውቅም~አስሮ የያዘኝን ላንተ ጊዜ እንዳልሰጥ~ያደነዘዘኝን😢 ግን አውቃለሁ አሁን~የጥንቱን ትጋቴን ብርታቴን እንዳጣሁ😢 ባዶነት ተሰማኝ ታስፈልገኛለህ~ይህንን አውቃለሁ🙌 : ዛሬም በድካሜ በህልውናህ ውስጥ~መዋኘት ናፍቆኛል አግዘኝ አልቻልኩም~በራሴ መፍጨርጨር በጣም ሰልችቶኛል😭🙇‍♀️ ✍️እርግጥ ነው ደክሜአለሁ ✍️ዛሬ ላይ ተኝቻለሁ ✍️ግን ቢሆንም ሁሌም~የጥንቱን ብርታቴን እናፍቀዋለሁ በህልውናህ ውስጥ ሰምጬ መኖርን~ዛሬም እሻዋለሁ እናም አባብዬ~አበርታኝ~አበርታኝ~አበርታኝ~እላለሁ🙇‍♀️🙏 🖌ኤልሳ_አንበስ🖌 👉share it ሼር ይደረግ👈 💁‍♂💁‍♀ አሜን TUBE ETH🙏 👉👉 @AMENtubeET 👉👉 @AMENtubeET 👉👉 @AMENtubeET 👆👆👆👆👆 ተ🀄️ላ🀄️ሉን JOIN US
Показати все...
ሰላም ሰላም
Показати все...
ሰላም ✋✋
Показати все...
▫#ለእግዜር_የተፃፈ_ደብዳቤ ▫▫▫▫ እንደምነህ እግዜር ሰማይ ቤት እንዴት ነው እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው? እኛማ..... ለእልፍ አእላፍ አለቃ… ማመልከቻ ፅፈን ለወፈ ሰማይ ህዝብ …መድረክ ላይ ለፍፈን ፆለት ቤታችንን ….እኛው ላይ ቆልፈን የምድር አተካራ …..ህግጋቱን አልፈን ደብዳቤ ላክንልህ፤ አይንህን ካየነው ሁለት ሽ ዘመን እንደቀልድ አለፈ የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ እንደውም እንደውም... ‹‹በመጣለሁ ተስፋ ሁለት ሽ ዘመን ቀጥሮን ከጠፋ በቀጠሮው ሰአት መምጣት ከተሳነው ‹‹እግዜር ሀበሻ ነው›› እያሉ ያሙሃል!! እኔ ምን አውቃለሁ... አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ ቃሉን ስማ ሲሉኝ ...ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ እግዚኦ በሉ ሲባል ...እንባየን የማፈስ ሃሌ ሉያ ሲሉኝ ...በሳቅ ልቤ እሚፈርስ ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ እኔ ምን አውቃለሁ... ግን አንተ ደህና ነህ? ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ ? የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አትከፋም አንዳንዴ! ከሆነስ ሆነና ሰማይ ቤት እንዴት ነው? አብረሃም ሰላም ነው... እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው ? እኛማ ይሄውልህ... በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን ‹‹ኤሎሄ›› እንላለን ጎጆ እንድጥልልን.... ወደ ላይ ገነባን ወደ ጎን አሰፋን ወደ ላይም ከላይ ወደ ጎንም ከጎን እ ን ደ ጉ ድ ተገፋን ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን !! አባታችን ሙሴ እነዴት ነው ለክብሩ ውቂያኖስ መክፈያው ደህና ናት ብትሩ? እኛማ ይሄውልህ.... እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን ን ገ ር ል ን ና ብትሩን ያውሰን ?! እናልህ እግዜር ሆይ.... ከተስፋዋ ምድር ወደ ሌላ ተስፋ አለን እየኳተን መሄጃው ሲገርመን መመለሻ መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን...! ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን... ‹‹የመሄድ ዘመን ነው ባህር የመሻገር ‹‹ዱላህን ላክልን›› ብሎሃል በልልኝ!! ሰማይ ቤት እንዴት ነው? ....ዳዊትስ ደህና ነው? ዛሬም ይዘምራል ...ዛሬም ይፎክራል ? ሰላም ነው ጠጠሩ .... ሰላም ናት ወንጭፉ? እዛስ አቅል ገዛ ጎሊያድ ተራራው ጎሊያድ ግዙፉ? እልፍ አላፍ ጎሊያድ ከቦን ሲደነፋ ወንጭፉን ጠቅልሎ ምነው ዳዊት ጠፋ ? ብሎሃል በልልኝ!! ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ ‹‹ወንጭፍህን ስጠው ለዚህ ታሪክ አውሪ›› ብለህ እዘዝልን!! እንዴት ነህ ጌታ ሆይ... ሰማይ ቤት እንዴት ነው? የሙሴ አልጋ ወራሽ እያሱ ሰላም ነው....? ያቆማትን ፀሀይ ግቢ ቢላት ምነው?! ያው እንደምታውቀው አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሀይ የምንሞቀው... ኧረ ፀሀይ በዛ ኧረ ፀሀይ በዛ ኧረ ፀሀይ በዛ የመጣው ወር ሀሉ ፀሀይ እያዘለ የተሸመው ሁሉ ‹ፀሀይ ነኝ› እያለ ያስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሀይ ያስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር ባቃጠላት ምድጃ አገር ምን ታምር ሊኖር ይችላል ፀሀይ ሁኖ እንደመፈጠር!! ኧረ እግዜር በናትህ.... ኧረ እግዜር በናትህ...በጭንቅ አማላጇ ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና ሙቀት ገደለና!! እናልህ እግዜር ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል... ጳውሎስ ሲሉን ...አቤት ጴጥሮስ ሲሉን ...ወይየ ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን ስማችንን ሸጠን ...ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን! ስንቱ ባለካባ ክብርህ የተሰጠው ለሰላሳ ፍራንክ ለተራ ጭብጨባ አደራህን ሸጠው ! ተወው የኛን ነገር ...ሰማይ ቤት እንዴት ነው .... ሂዋንስ ደህና ናት? ያው የልጅ ልጆቿ በግሯ ተተክተው የፍሬው ሲገርምህ ግንዱንም አንክተው ለፍጥረተ አዳም ባይኑ ያገምጡታል ሰይጣንም ደህና ነው ኑሮ ተስማምቶታል.... ሰውን ለማሳሳት ላይ ታች ማለት ትቷል ሳይጠራው የሚጎርፍ ህዝብ በዝቶለታል...! ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና ሙቀት ገደለና.......!! ©✍አሌክስ አብርሃም @yetbgb @Eduka19
Показати все...
በአንድ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መምህሯ ተማሪወቿን አንድ Assignment መስጠት ፈለገች..!! ተማሪወቿን ድንች ይዘዉ እንዲመጡ አዘዘች፡፡ ድንቾቹ ላይም የሚጠሏቸዉን ሰወች ስም እንዲፅፉ አዘዘቻቸዉ.. የሚያመጡት የድንች ብዛትም በሚጠሏቸዉ ሰወች ብዛት ልክ እንዲሆን አለች፡፡ በሁለተኛዉ ቀን አንዳንዶቹ 3፡ሌሎች 5 ቀሪወቹ ደግሞ 8 ድንቾቹን የሚጠሏቸዉን ሰወች ስም ፅፈዉ አመጡ..መምሯ ደግሞ <<ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት እኒህን ድንቾች በሻንጣችሁ ይዛችሁ ትዞራላችሁ...ሽንት ቤት ስትሄዱ እንኳ መተዉ አትችሉም!>> ብላ አዘዘች . ቀኑ እየጨመረ ሲሄድ ድንቹ በመበላሸቱ ሽታዉ ይረብሻቸዉ ስለጀመረ ተማሪዎቹ ቅሬታ ማቅረብ ጀመሩ..በተለይም 8 የያዙት ከሽታው በተጨማሪ ክብደቱ እንደበዛባቸው መናገር ጀመሩ፡፡ . ከሳምንት በኋላ የአሳይመንቱ ገደብ ስላበቃ ተማሪወች ድንቹን አዉጥተዉ እንዲጥሉ ተፈቀደላቸዉ:: ከዛም መምህሯ<<እህ እንዴት ነበር?>> ብላ ጠየቀቻቸዉ...ሁሉም ማጉረምረም ጀመሩ ..."አረረረ ከክብደቱ ሽታዉ...አረ በጣም ነዉ የሚያስጠላዉ"...አሉ . . መምህሯ<<አያችሁ በልባችሁ የምትሸከሙት ጥላቻም እንዲሁ ነዉ...ጥላቻt ልብን ይመርዛል.. በምትሄዱበት ሁሉም እየተከተለ ይረብሻችኋል...ለአንድ ሳምንት የተበላሸ ድንችን ሽታ መቋቋም አልቻላችሁም..አስቡት ደሞ በጥላቻ የተመረዘን ልብ እድሜ ልካችሁን ይዛችሁ ስትኖሩ!!>> አለቻቸዉ . . ጥላቻን ከዉስጣችሁ አዉጡት..ና ከእዳ የፀዳችሁ ሁኑ!! እዉነተኛ ፍቅር እንከን አልባን ሰዉ ማፍቀር ሳይሆን ንፁህ ያልሆነን ሰዉ በንፁህነት መዉደድ ነዉና!!! @yetbgb
Показати все...
💢በጊዜ ⚜የወጣት ክብሩ ጉልበቱና አቅሙ💪 በውስጡ ያለው ራዕይና አላማ ነው ። በወጣትነቴ መሸበት አለብኝ ሽበታም ብሆን እከብራለሁ ቢል😳 የማይሆን ነገር ነው ። ⚜የሸመገለ ሰውም ሽበት አልፈልግም ብሎ እንደ ወጣት መሆን ቢፈልግና ጡንቻ ማውጣት ፈልጎ እንደወጣትነቱ ስፖርት ቢጀምር በዚያም የሚከበር ቢመስለው የማይሆን ነገር ነው ። ⚜እኛም የዛሬው ወጣቶች ፀሎትንና ትጋትን አቁመን ፣ወንጌል መስራትን ዘንግተን ፣ዛሬ ላይ ቆመን ነጋችንን መስራት ሰልችተን ለጥ ብለን ተኝተን ስኬትንና ክብርን አናገኝም ። ✳️በጊዜአችን ካልተጋን ነገ በ3 እግር አንተጋም የሚያምርብን እንዳረጀ ሽማግሌ ተኝተን ከfb tg ,ከinsta tik talk ወይ you tube እየዞርን በወሬ ጊዜአችንን ስናጠፋ ሳይሆን ኢየሱስን ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ስናወራና ኢየሱስን ለመኖር ስንሯሯጥ ነው ። ✳️ዛሬአችን ላይ ካልሰራንበት ዛሬአችን በራሱ ይንቀናል🙊 በጊዜአችን የሚገባንን ስናደርግ ግን ያከብረናል ። ✳️ቆም ብለን እናስብ እስኪ እናድምጥ እግዚአብሔር ምን እያለን ነው? ወጣትነታችንን ለምን ይፈልገዋል ?ለምንስ በዚህ ጊዜ ተፈጠርን ? ያለ አላማ አልተፈጠርንም እኮ።🙊 📌ምን እየሰራን ነው ? ያከብረን ይሆን? ለምንድነው የምንሰራው? አላማችንን አግኝተናል? 👈የሁላችንም ጥያቄ ይሁን ። 📌በጊዜአችን የምንከብርበትን መርጠን እንኑር። “የጎበዛዝት ክብር ጕልበታቸው ናት፥ የሽማግሌዎችም ጌጥ ሽበት ነው።” — ምሳሌ 20፥29 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇⏰⏰⏰⏰✝⏰⏰⏰⏰ BE INFORMED FIRST TELEGRAM CHANNEL @Jesuschristinheaven @Jesuschristinheaven
Показати все...
“ዘመኑን በማስተዋል ይህን አድርጉ፤ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁበት ጊዜ አሁን ነው፤ መዳናችን መጀመሪያ ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን ወደ እኛ ቀርቦአልና።” — ሮሜ 13፥11 (አዲሱ መ.ት) በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ በማመን ወደ እግዚአብሔር ሕይወት የተጠራችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሁሉ የይሳኮር ልጆች በእስራኤላውያን መካካል ዘመኑን የሚያስተውሉ እና እስራኤል በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ይችል ዘንድ የሚመሩ እንደሆኑት ሁሉ እኛም አሁን ዘመንን በማስተዋል እና በመንቃት ሌሎችንም የምናነቃበት ትክክለኛው ጊዜ ለይ ነን! ተወዳጆች ሆይ መዳናችን ከምታስቡት በለይ ቀርቧል የተባረከው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ከመምጣቱ በፊት ቤተክርስቲያን መነጠቅ አለባት። ጌታ የምነጥቃት ቤተክርስቲያን “...ጒድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም አንዳች እንከን ሳይገኝባት ቅድስትና ነውር አልባ የሆነች ክብርት ... " ቤተክርስቲያን ናት። አሁን ባለንበት ሁኔታ በጣም የሚያስፈራ ነዉ። ተወዳጆች ሆይ እንንቃ ስለቤተክርስቲያን ሁሉን ወደምችል አምላክ እንጩህ!!! እግዚአብሔር እንደልቡ የሆኑ መጋቢዎች እንድያስነሳ እና ቤተክርስቲያንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሪቫይቪ እንድያደርጋት እናልቅስ። እንባ ለአይኖቻችሁ ቅርብ ይሁን ስለ ቤተክርስቲያን አልቅሱ!!!! እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ለክርስቶስ የሚያዘጋጃትን የመጨረሻውን ዘመን እንቅስቃሴ በዚህ ትውልድ መካከል ይጀምረዋል!!! “በስሜ የተጠራው ሕዝቤ ራሱን አዋርዶ ቢጸልይ፣ ፊቴን ቢፈልግና ከክፉ መንገዱ ቢመለስ፣ ከሰማይ እሰማዋለሁ፤ ኀጢአቱን ይቅር እላለሁ፤ ምድሩንም እፈውሳለሁ።” — 2 ዜና 7፥14 (አዲሱ መ.ት)
Показати все...