cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Super christian tube ሱፐር ክርስቲያን ቱብ

የሁሉ ነገር መጨረሻ ተቃርቧል ስለዚህ መጸለይ እንድትችሉ ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ ራሳችሁንም የምትገዙ ሁኑ። 1ጴጥ. 4÷7 ይህ ሱፐር ክርስቲያን ቱብ ነው! # አላማችን 👉 በተግባሩና በህይወቱ የሚመሰገን በመንፈስ የጋለ ንቁ ክርስቲያን መፍጠር ነው። በተጨማሪ በዩቱብ https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1

Більше
Рекламні дописи
15 780
Підписники
+1124 години
+2577 днів
+85230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ክብር ለኢየሱስ ይሁን። ወዳጆቼ በሁለቱም ቀን በውስጥ መስመር እና አንዳንዶች ደግሞ በስልክ መስመር በመደወል እስከ ሃያ(20) የሚደርሱ ልጆች ተሳስተው ከነበሩበት መንገድ ተመልሷል። በንስሐ ፤ ከአሕዛብ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምሮ የነበሩ፤ ትክክለኛ ከልሆነ ሰው ጋር ፍቅር የጀመሩ፤ በpornography እና ማስተርቤሽን ይሰቃዩ የነበሩ ልጆች ብዙ ከወራን በኃላ ከስህተት ጓደናቸው ተመልሷል። ከዚህ በፊት የነበሩትን ጭምሮ ከ50 በላይ የሆኑ ልጆች ትክክል ከልሆነ አካሄዳቸው ተመልሷል። አሁንም ይሄን ሁሉ ላደረገው አምላክ ክብር ይሁን። እንዴት ደስ ይላል ትውልድ ስይማልጥ😥🙏🙏🙏 በጣም እርግጠኛ ሆኜ የማወራው ነገር ቢኖር ከዚህ በኃላ በእኛ ዘመን ትውልድ አይበላም።    👤ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ👤 🙏ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ❤❤ በብዙ የኃጢአት ልምምድ ውስጥ ያላችሁ ወይም የሆነ ጊዜ ተሳስታችሁ የነበራችሁ ልጆች በንስሐ መመለስ የምትፈልጉ በውስጥ አውሩኝ  👉 @abit9  @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @superchristiantube7 @superchristiantube7 @superchristiantube7 sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
Показати все...
👍 50🥰 8 6👏 1
ከወሲብ በፊት እና በኋላ(  ከጋብቻ በፊት ) በፊት ወንዱ፦ ወሲብ ማድረግ አለብን ። ፍቅራችንን በተግባር መገላለፅ አለብን ሴቷ፦አይሆንም  እግዚአብሄር ያዝናል ። ያልተጋቡ ሰዎች ወሲብ ከፈፀሙ ዝሙት ነው። ወንዱ፦ አይ እኛ እኮ መጋባታችን እንደሆነ እርግጥ ነው ። ስለዚህ ችግር የለውም። ሴቷ፦ እሱማ እርግጥ ነው ቢሆንም ግን እስከትዳር ድረስ ብንጠብቅ ይሻለናል ። ይቅርብን ! ወንዱ፦ አትወጂኝም ማለት ነው ! ሴቷ፦ እንዴት እንደዚ ትላለህ በጣም እንደምወድህማ ታውቃለህ። ወንዱ፦ብትወጂኝማ ኖሮ እምቢ አትዪኝም ነበር። እንደውም ቢበቃን ይሻላል ! ሴቷ፦ (ብዙ ተጨንቃ) እሺ በቃ እናድርግ ። ግን አንድ ቀን ብቻ ነው ከዛ በኋላ እናቆማለን። ወንዱ፦ አዎ ችግር የለውም አንዴ ብቻ ነው ሴቷ ፦ ግን ከዛ በኋላ ብትጠላኝስ ወንዱ፦ እንዴት እጠላሻለው!? እንደውም ፍቅራችን እጥፍ ነው ሚሆነው 🚫ወሲብ ፈፀሙ 🚫አንድ ቀን ብቻ ሳይሆን ብዙ ቀን በኋላ 👉 ሁለቱም ድብርት ፀፀትና የሃጢያት ወቀሳ ሰላም ነሳቸው 👉 የሆነ ቀን ወንዱ ጓደኛውን ሊያማክር ሄደ__ ወንዱ ፦ ከእጮኛዬ ጋር ወሲብ ፈፀምን !  እና ከዛ በኋላ ለሷ ያለኝ  ስሜት በጣም ቀዘቀዘ »»> እንደውም ልጠላት ነው መሰለኝ »»» አሁን ራሱ ለSex ስል ነው አብሬያት ያለሁት የጓደኛው ምክር ለመልዕክቱ ጠቃሚ ስላልሆነ ትተነዋል ፡፡ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ይህ በፅሁፋዊ ጭውውት መልክ የቀረበው ፅሁፍ የብዙዎችን የህይወት ገፅታ የሚያሳይ መስታወት ነው ፡፡ ምናልባትም አንዳንዶች የእኔ ታሪክ ነው እንዴ? ትሉ ይሆናል ታዲያ ከዚህ ምን ተማራችሁ? አንኳር ነጥቦቹ ▶️  ወሲብ ከጋብቻ በፊት ሲሆን ከሚያመጣው ጊዜያዊ እርካታ እጅግ የገዘፈ ፀፀት እና የስሜት መዋዠቅ ያመጣል ፡፡ ▶️ ፍቅርን ያደፈርሳል ▶️ የግንኙነቱ(relationship) መሰረት ፍቅር ሳይሆን ወሲብ እንዲሆነ ያደርጋል ፡፡ ያ ከሆነ ግንኙነቱ ለመፍረስ ትንሽ ሰበብ ብቻ ነው ሚፈልገው። 🎼የሆነ ልጅ አንድ ጊዜ እንዲህ ብሎኝ ነበር #ከፍቅረኛዬ_ጋር_በመሃላችን_ያለው_ፍቅር_ከመጀመሪያው_ይልቅ_ሚጨምር_መስሎኝ_ወሲብ_አደረገን_ግን_ከዚያ_በኃላ_እንዲሁ_በመሃላችን_ያለው_ፍቅር_በጣም_ቀዘቀዘ" ብሎኝ ነበር።    👤ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ👤 🙏ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ❤❤ ምን አልባት በዚህ የዝሙት ልምምድ ውስጥ ያላችሁ ወይም የሆነ ጊዜ ተሳስታችሁ የነበራችሁ ልጆች በንስሐ መመለስ የምትፈልጉ ከሆነ  እኔን በውስጥ መስመር አውሩኝ ሳይመሽ በጊዜ ተመለሱ  👉 @abit9  @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @superchristiantube7 @superchristiantube7 @superchristiantube7 sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
Показати все...
🥰 37👍 36 26👏 10
ወገኖች ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን የከዚህ በፊቱን ሳይጨምር ከትላንት ማታ ጀምሮ እስከዚህ ሰዓት ድረስ በጣም ብዙ የሆኑ ወጣቶች በውስጥ መስመር ከእኔ ጋር አውርተው በንስሐ እየተመለሱ ነው። በእውነት ደስታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም🙏😥😥 ክብር ለኢየሱስ ይሁን። እንዴት ደስ ይላል ነፍሳት ከጨለማ ስያመልጡ🙏🙏 አሁንም በብዙ የኃጢአት ልምምድ ውስጥ ያላችሁ ንስሐ መግባት እፈልጋለሁ ምትሉ ልጆች በውስጥ አውሩኝ ለእናንተ መጸለይ እፈልጋለሁ።👉 @abit9 @abit9
Показати все...
49👏 18👍 15🥰 4
እጮኝነት የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች 🔴ቅድመ ጋብቻ የግብረ ስጋ ግንኙነትን መፈጸም ወጣቶች በእጮኝነታቸው ወቅትም ሆነ ከዚያ በፊት በአካል እድገት ለውጥ የተነሳ ከፍተኛ የሆነ የወሲብ ፍላጎት አላቸው፡፡ በዚህ ምክንያት በእጮኝነታቸው ወቅት በፍቅር መያዝ፣ተቀጣጥሮ የሚያውቃቸው ሰው በሌለበት ቦታ ላይ መገናኘት፣ወደ ወንዱ እጮኛ ቤትመሄድ፣አልፎ አልፎም መተቃቀፍ፣የመራቢያአካላትን መነካካት፣የከንፈር መሳሳም; የመሳሰሉትን ነገሮች በማድረግ የወሲብ ስሜትን ለማርካት ጥረት ማድረግ በብዙ እጮኛሞች መካከል የሚታይ ሐቅ ነው፡ የቅድመ ግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ ወጣቶች ይፈተናሉ ብሎ መናገር ይቻላል፡ አንዳንዶችም ይህን ከፍተኛ ፍላጎት መቋቋም አቅቷቸው በዝሙት ፈተና ላይ ይወድቃሉ፡፡ ይህን ድርጊት ከበደ በከሬ እንዲህ በማለት ያስቀምጠዋል፡፡ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የቅድመ ጋብቻ የወሲብ ግንኙነትም ኃጢአት ነው(የሐዋ 15፡20፣1ቆሮ6፡9፣ 13፣18፣7ላ5፡19 ፣ቆላ3፡5፣1ተሶ4፡3)፡ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ወደ ፊት እንጋባለን _ ምንም _ አይደለም ብለው ከጋብቻ በፊት ወሲብ መፈጸማቸው ለአሁንም ሆነ በወደ ፊት የትዳር ሕይወታቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አለው ይላል፡፡6 በዚህ ምክንያት የወደቁ እጮኛሞች ክብረ ነጽህናቸውን ከሰጡ በኋላ በወንዶች በኩል የመጋባት ፍቅራቸው እየቀነሰ በመምጣት የነበረው ከፍተኛ ናፍቆት ውሳኔ እየተራዘመ ወደ ፊት ይሄዳል፡፡ ይህ ነገር የሚያሳየው የጋብቻው ሁኔታ ከፊቱ ላይ ቀይ መብራት የበራበት መሆኑን የሚያመላክት መሆኑን የሚጠቁም ነገር ነው፡፡ እንዲሁም በመቀጠል በወንዱ ወይም በሴቷ በኩል ለማግባት ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ብዙ ጊዜ ሲናገሩ ይሰማሉ። 🔵ዶክተር ብራንድት “Collegiate Challenge” በሚለው መጽሔት በጻፉት መጣጥፍ ላይ በማማከር አገልግሎታቸው ውስጥ አንድ የተገነዘቡትን ነገር አስፍረዋል። 👉ይኸውም ብዙ ጊዜ ሁለት የፍቅር ጓደኛሞች እሳቸው እኔ ጋ ምክር ፍለጋ ሲመጡ እንዲህ ይላሉ «በመጀመሪያ ወሲብ ስንፈጽም እጅግ በጣም አስደሳች ነበር፤ ጥቂት ቆይቼ ስለሆነው ነገር ሳስብ ስለራሴ መላቅጡ የጠፋና የንዴት ስሜት ተሰማኝ። በጣም በጸጸት ተሞለሁ። ጥቂት ቆይቼ ስለ ፍቅር ጓደኛዬ የተሰማኝ ስሜትም ደስ የማይልና ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ሆነ። ከዛም ጥቂት ቆይተን እርስ በርሳቸን መጨቃጨቅና አልፎ ተርፎም መጣላት ጀመርን፤ በመጨረሻም ተጣላን፣ አሁን ጠላቶች ሆነናል። ብለው ይነግሩኛል። » በማለት ልምዳቸውን በመጽሔቱ ላይ አስፍረው ነበር። ✨ይህንን ዓይነት የሥነ ልቡና በሽታ የንጋት በሽታ ብዬዋለሁ። ከእንቅልፋችን ብንን ብለን ከመኝታችን ስንነሳ ያ ፍቅርና መቀራረብ እውነት እንዳልሆነና በቦታውም እንደሌለ እንረዳለን። 🔴ከዛን ጊዜ ጀምሮ የወሲብ ግንኙነት ደስታን የሚፈጥርልን ነገር አይሆንም። መጨረሻው እንደጠበቅነው አይሆንም።    👤ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ👤 🙏ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ❤❤ ምን አልባት በዚህ የዝሙት ልምምድ ውስጥ ያላችሁ ወይም የሆነ ጊዜ ተሳስታችሁ የነበራችሁ ልጆች በንስሐ መመለስ የምትፈልጉ ከሆነ እኔን በውስጥ መስመር አውሩኝ ሳይመሽ በጊዜ ተመለሱ 👉 @abit9 @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @superchristiantube7 @superchristiantube7 @superchristiantube7 sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
Показати все...
👍 77 9🥰 4👏 3
እንዲህ ልባርካችሁ ወንዶችዬ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም የሚያስፈልገውን ሁሉ አዘጋጅቶለትና ሰጥቶ የምትመች እረዳት ፈጥሮ ወደ እሱ እንዳመጣ እንዲሁ ወደ እናንተም ተስማሚ እረዳት የሆነች ሴት ያምጣላችሁ ሴቶችዬ ሔዋንን አስፈላጊውን ነገር ወደ ሰጠው ወደ አዳም እንዳመጣት እንዲሁ እናንተንም እግዚአብሔር አስፈላጊውን ነገር ወደ ሰጠው ወንድ ያምጣችሁ (ይውሰዳችሁ)!!
Показати все...
84👍 26🥰 9👏 8
በጌታ ያላመኑ ወጣቶች ጋር የፍቅር ግኑኝነት ብንጀምር ምን ችግር አለ? ይህ ጥያቄ ብዙ የክርስቲያን ወጣቶች ነው እንደውም አሪፍ ነው በእኔ ምክንያት ወደ ጌታ መምጣት ትችላለች/ይችላል።   ይቺ ልጅ ስለምትወድህ እንዳትጎዳ ብለክ ከሷ ጋር ግንኙነት ብትጀምር ከእሷ በላይ #የሚወድህን #ጌታ #ልትጎዳው ነው ። ምንም ወስን ምን ወይ #ልጅቷ #ወይ #ጌታ #መጎዳታቸው #አይቀርም ። በእርግጥ ልጅቷ ጌታን ምታገኝበት መንገድ ቢሆንስ ብለሃል ። ግን ደሞ አንተ ከጌታ የምትርቅበት መንገድ ቢሆንስ? ይሄንንስ አስበኸዋል? ነገ እራስህን ያላሠብከው ውድቀት ላይ ብታገኘው ተጠያቂው ማነው አንተ ወይስ ጌታ?  እሷን ወደጌታ ለማምጣት ብለህ ገብተህበት አለም አቅፋ ደግፋ እሹሩሩ ብላ ብትቀበልህ ... አባብላ ወደማትነቃበት እንቅልፍ ብትወስድህስ???💁የኔ ወንድም, ሰይጣን እኮ ሰይጣን ነኝ ብሎ ቢመጣ የዓለም ህዝብ ባልጠፋ ነበር ። ሲጀመር ጨለማ ከብርሃን ምን ህብረት አለው...? ክርስትና ውስጥ ማመቻመች አይሠራም! የውሳኔ ሰው ሁን! ሰው አድናለሁ ብለህ እራስህ ጉድ እንዳትሆን!!  አትሳሳት... ጌታን ከተቀበለች በኃላ ከእሷ ፍቅር ባይዝህ የሆነ ስዓት መለያየታችሁ አይቀርም... በዚያ ስዓት ጌታ ካልረዳት አንተን የተበቀለች መስሏት #back ብታረግስ? እስኪ አስበው ያ ሁሉ ነገር ውሃ በላው ማለት ነው ... እሷን ለመርዳት ከልብ ፍላጎት ካለህ ፀልይላት። በግልፅ አስረዳት ... ጌታን ብትቀበል ላንተ ሳይሆን ለራሷ ስትል ይሁን እንጂ መዳኗ አይቅለልባት... በፀሎት የማይፈታ ነገር የለም ...  ጌታ ፈቃዱ ከሆነ ልቧን ይከፍተዋል... እንጂማ ነገም ሌላዋ ደሞ ብትወድህስ ስንቱን ከጨለማ ለመናጠቅ ስትል relation ጀምረህ ትችለዋለህ?💁💁🤔, ስለዚህ ተው ይቅርብህ ከማተምን ልጅ ጋር ወይም ከማያምን ወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነት አትጀምሩ። እንደ እናንተ በጌታ የሆነ ሀገሩን ሞልቷል እኮ። ከማያምን ይልቅ የሚያምን ደካማ አማኝ 100 እጅ ይሻላችኋል።    👤ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ👤 🙏ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ❤❤ ማንኛውም ጥያቄ ሀሳብና አስተያየት ካላችሁ እኔን ለመገኘት 👉 @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @superchristiantube7 @superchristiantube7 @superchristiantube7 sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
Показати все...
🥰 17👍 15 13🔥 2
     ፋሽን👉ዘመናዊነት እና ክርስትና    አሁን አሁን ፋሽን የአብዛኛው የክርስቲያን ወጣት ሀሳብ እየሆነ ነው። እኔም ወጣት ነኝ ይህ ነገር አሳስቦኝ ያውቃል። ፋሽንን መከተል የዘመናዊነትም ዋነኛ መገለጫ ተደርጎም እየተወሰደ ነው። ከዛሬ አምስትና ስድስት አመት በፊት የነበሩትን ፋሽን እና የተለያዩ ስታይሎችን ያስተዋለ ሰው አሁን ላይ ካሉት ጋር ማነፃፀር ይችላል። ይህን ፅሑፍ ስታነቡ ማስተዋል ያለባችሁ አላማዬ ማንም ላይ መፍረድ እንዳልሆነ እና ምናልባት እየፈረድኩ እንኳን ከመሰላችሁ እኔም ላይ እየፈረድኩ እንደሆነ ተረዱ። ዛሬ ላይ ቡቲክ ወጥቶ ልብስ ሊገዛ ያሰበ ሰው ጥቂት አመታት ውስጥ ከተማዋን ከወረራት የምእራባዊያን ፋሽን አያመልጥም። በየማህበራዊ ገፁ ላይ በየቴሌቪናችን ላይ የምናያቸው የተለያዩ ፋሽኖች አሁን እሩቅ ሳንሄድ አፍንጫችን ስር እናገኛቸዋለን። እመኑኝ እነዚህን ልብሶች ባንለብስ እንኳን ለመልበስ ተመኝተናቸው እናውቃለን። ለብሰናቸው አደባባይ ባንወጣም በጓዳችን ፎቶ ተነስተንባቸው እናውቃለን። መነሳት ብቻ ሳይሆን ውበቴን እዩ በሚል አይነት አቋም በየማህበራዊ ድረ-ገፅ ለቀናቸው እናውቃለን። በማህበራዊ ድረ-ገፅ ባንለቃቸው እንኳን በስልኮቻችን ይዘን እንዞራለን። ይሄን ድርጊት እየተቃወምኩ አይደለም። ስለ ውበት መጨነቅ ያስፈልጋል አምናለሁ። መልበስ ባንፈልግ እንኳን ቡቲኩን የወረረው የልብስ ፋሽን እንድንለብስ ያስገድደናል። ይህን ፅሁፍ ወደ እናንተ ሳደርስ ስለ አለባበስ ምንም እውቀት ከቃሉ አንፃር የላችሁም እያልኩ ሳይሆን ስለዘነጋነው እንድናስታውሰው ያክል ነው። 📌 እንደ ክርስቶስ ተከታይ ስንዘምን እና ፋሽን ስንጠቀም ምን ማስተዋል አለብን? ፠ ክርስቲያን እንደመሆናችን በአንደበታችን ፍሬ የጌታን ማንነት የሚረዱ እንዳሉ ሁሉ ከርቀት አስተውለውን እና ህይወታችንን አጢነው ስለምናመልከው አምላክ ለማወቅ የሚጓጉ አሉ። ስንቶቻችን በንግግራችን እና በአለባበሳችን ምክንያት "እሷ ክርስቲያን ናት እንዴ?" "ማን እሱ ክርስቲያን ነው?" ተብለን ይሆን?  ፠ አለባበሳችን እና አካላዊ ገፅታችን ከአንደበታችን በላይ ስለራሳችን እንደሚናገሩ ማስተዋል አለብን። አለባስ ያስከብረናል ደግሞ አለባበስ ሊያስንቀን ይችላል። ፠ እመኑኝ የማይሆን አይነት አለባበስ ከራሳችን አልፎ በውስጣችን ያለውን ቅዱሱን መስፈስ ያስንቃል። ይህን ክፍል እናስተውል እስቲ:-      "ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።"                                   1ኛ ጴጥ.2:12 📌 ታዲያ እንዴት ብንዘምን እና ፋሽንን ብንከተል መልካም ነው? ፠ ለዚህ ጥያቄ መልስ ሊሆን የሚችለው አንዱ እና ዋነኛው አለባበሳችንን ስናስብ ክርስቶስን ምን ያክል ያስከብራል ብሎ ማሰቡ ነው። ፠ እህቶች ደግሞ ከምንም በላይ በዙርያቹ ላሉ ወንድሞቻችሁ አስቡ። መፅሐፍ ሲናገር ሴትን ያየ እና የተመኘ አመንዝራ ነው ይላል። ስለዚህ በአንቺ እንዲያመነዝር አትፍቀጂ።           ትልቅ ምክር ለሴቶች ፠ ቀን ገላሽን ያየ ወንድ ማታ ከአንቺ ጋር ዝሙት ሊፈፅም ይችላል። እመኚኝ ያላገባ ወጣት ብቻ ሳይሆን ያገባውም ከሚስቱ ጋር ሩካቤ-ስጋ(sex) እየፈፀመ መንፈሱ ግን ቀን ካየው ገላሽ ጋር ነው የሚዘሙተው። ፠ አንዳንዴ በsocial media ለምትለቂያቸው ፎቶዎችም ተጨነቂ። ምክንያቱም ገላሽን እያሰበ ፎቶሽን እያየ ራሱን በራሱ የሚያረካ(masterbate) የሚያደርግም አለ። ፠ ማታ ማታ ስልክ አምሽቶ ደውሎ ድምፅሽን እየሰማ ራሱን በራሱ የሚያረካ ወንድ አለ። ስለዚህ ወንድ ልጅ በሚያየው ነገር እንደሚስት ማወቁ ለጥንቃቄ ይጠቅምሻል። በጣም ማስተዋል ያለብሽ ከላይ የጠቀስኳቸውን ነገሮች አንድ ወንድ በድካሙ ቢያደርግም ነገር ግን ምክንያቷ አንቺ መሆን የለብሽም። ይህ ክርስቶሳዊ አይደለምና። እነዚህን ጥቅሶች በማስተዋል አንብበን ይህን ፅሑፍ እናጠናቅቅ!! "እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፤ እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ፥ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ ወይም በዕንቍ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ።"                              1ኛ ወደ ጢሞ 2:9 "ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፥ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።"                          1ኛጴጥ3:3-4    👤ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ👤 🙏ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ❤❤ ማንኛውም ጥያቄ ሀሳብና አስተያየት ካላችሁ እኔን ለመገኘት 👉 @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @superchristiantube7 @superchristiantube7 @superchristiantube7 sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
Показати все...
👍 33 16🥰 9
ሰሞኑን አንድ ቪዲዮ በሶሻል ሚዲያ አይቼ ጌታን በጣም ገረመኝ። የሆነ ልጅ የቴዲን እንደገና የሚለውን መዝሙር እንዲህ ብሎ ስዘምር ሰማሁ🤔 የገጠር ልጅ ነው ስሉ🤔 አማርኛ አይችሉም ስሉ🤔 ቁመቱ አጭር ነው ስሉ🤔 ከየት የመጣ ነው ስሉ🤔 ይመለሳል ስሉ🤔 ደብደቤ ስጽፉ🤔 በጌታ ግን አሽሙር ነው ወይስ መዝሙር🤔🤔 አንተም ፍሬ እንደዚህ ዘምር ብሎኛል ብላህ ዘምር አሉ🤔🤔 አረ ግን ወገን ወዴት እየሄድን ነው? መዝሙር ጠፍቶ ነው እንዲህ ሚዘመረው?🤔 እግዞኦ ድረስልን🙏🙏
Показати все...
🔥 13👍 10👏 3😁 1🤔 1
14👍 5👏 4🤔 2
11:39
Відео недоступнеДивитись в Telegram
7👍 5😁 1