cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ጥበበ ኢትዮጵያ💚💛❤️

የጥበብ መጀመሪያው እግዚአብሔርን መፍራት ነው ። ጥበብ እግዚአብሔር ነው 🙏🙏🙏 የተሰወረውን የአባቶቻችን ጥበብ እና እውቀት ለዓለም ያበራ ዘንድ እንገልጣለን። ይህንን ቻናል Join በማድረግ ስለ ቀደምት አባቶቻችን እምቅ የሆነ ጥበብ እና እውቀት አውቀን ለሌሎችም በማሳወቅ ሀገራችንን ወደቀደመ ክብሯ በጋራ እንመልሳት።

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
589
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሰላም ወድ የጥበበ ኢትዮጵያ አባላት:- ለዛሬው አንድ ጥሩ የግእዝ መማሪያ ቻነል ልጠቁማችሁ። በዚህ ቻነል ላይ የግስ ጥናት ከ "ሀ" ጀምሮ ታገኛላችሁ። ከትንሽ ጊዜያት በኋላ ተከታታይ ትምህርት ይጀመርበታል። ይህም የጥበብ ቤት ነውና ገባ በሉ። @yewewketmaed @geezforstudents
Показати все...
🌷🌷የግስ ጥናት🌷🌷 🌷🌷የ "ደ" ግስ🌷🌷 🌷🌷 ክፍል አንድ🌷🌷 🌷የ #የ ን ግስ ለማግኘት🌷 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 Open ➺ የ "የ" ግስ ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ 1) ኀለደ (ቀደ) = ጨረሰ፣ፈጀ፣ከተተ 2) ሐመደ (ቀደ) = አከሰለ፣አመድ አደረገ 3) ሐረደ (ቀተ) = አረደ 4) ሐርበደ (ተን) = ተስበደበደ፣ ተንበደበደ (የፍርሀት) 5) ሄደ/ሀየደ (ቀተ) = ቀማ፣ነጠቀ 6) ሐደደ (ቀተ) = ፈጨ 7) ልሕደ (ክህ) = ተደላደለ፣ተቀማጠለ 8) ለመደ (ቀተ) = ለመደ 9) መለደ (ቀደ) = ሰበሰበ 10) መሰደ (ቀደ) = ሸመተ 11) መረደ (ቀደ) = ጠበጠበ፣ተራመደ 12) መርደደ (ተን) = ጨከነ፣ደፈረ፣ተጋ፣ፈጠነ 13) ምዕደ/መዐደ (ቀተ) = መከረ 14) መደ/መደደ (ቀተ) = ቆረጠ 15) ሞገደ (ጦመ) = ማዕበል አደረገ፣አነሳሳ፣አወከ . 🌹🌹መክሥት (መግለጫ)🌹🌹 ➽ ቀተ.......➺ ቀተለ ➽ ቀደ...... ➺ ቀደሰ ➽ ተን....... ➺ ተንበለ ➽ ባረ........➺ ባረከ ➽ ማሕ......➺ ማሕረከ ➽ ሴሰ.......➺ ሴሰየ ➽ ክህ.......➺ ክህለ ➽ ጦመ.... ➺ ጦመረ የበለጠ ለማግኘት TG Channel ➺ @yeweketmaed TG Group ➺ @geezforstudents አስተያዬት ካለዎት @GeezYimaru ይጠቀሙ።
Показати все...
ግእዝ ይማሩ ➺Ethio Geez Media

🌷🌷የግስ ጥናት🌷🌷 🌷🌷የ "የ " ግስ🌷🌷 🌷🌷 ክፍል ዐሥራ አንድ 🌷🌷 🌷ክፍል ዐሥር ን ለማግኘት🌷 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 Open ➺ ክፍል ዐሥር ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ 151) ጥዕየ (ክህ) = ዳነ 152) ጠወየ (ቀተ) = ጠመመ 153) ጻሕየየ (ማህ) = አረመ 154) ጸለየ (ቀደ) = ለመነ፣ጸለየ 155) ጸምሐየ/ጸመሐየ (ተን) = ጠወለገ 156) ጸማሕየየ (ማህ) = ጠወለገ፣ደረቀ 157) ጸረየ (ቀተ) = ጦረ፣ነጻ 158) ጸበየ (ቀተ) = ወረደ፣ፈሰሰ 159) ተብለየ (ተን) = ትቢያ ኾነ 160) ጸደየ (ቀተ) = ዘመነ በልግ ኾነ 161) ጸገየ (ቀተ) = አበበ 162) ፈለየ (ቀተ) = ለየ፣መረጠ 163) ፈረየ/ፈርየ (ቀተ) = አፈራ 164) ፈደየ (ቀተ) = ከፈለ 165) ፋጸየ (ባረ) = አፏጨ . 🌹🌹መክሥት (መግለጫ)🌹🌹 ➽ ቀተ.......➺ ቀተለ ➽ ቀደ...... ➺ ቀደሰ ➽ ተን....... ➺ ተንበለ ➽ ባረ........➺ ባረከ ➽ ማሕ......➺ ማሕረከ ➽ ሴሰ.......➺ ሴሰየ ➽ ክህ.......➺ ክህለ ➽ ጦመ.... ➺ ጦመረ የበለጠ…

ትርጉም አማኝ ሊቃውንቱ የሚወዱትም የሚቀበሉትም አይመስለኝም። ሆኖም፣ ይህ የሕይወት ትርጉም፣ የመጨረሻዎቹን አወዛጋቢ ስንኞች ከላይኞቹ ጋር በዐውድ ስምም እንዲሆኑ ያደርግልናል። ከኤፍሬም ሥዩም ትርጉም የተሻለ የሚያሰኘውም ዐውዱ ነው። “የሰው ልጅ በገዛ’ጁ፥ ላስቀመጠው ፈጥሮ ይገ:ዛል ባንክሮ ሰው ፈርቶ እንዲገ:ዛ፥ እንዲሰላ ኑሮ ለዚኽም ማስረጃው የሙሴ ነገር ነው አምላኩን መፍጠሩ አምላኩም ፈጠረው በአምሳሉ በግብሩ።” (ሕይወት ታደሰ/ሕይወት ተፈራ/ኀሠሣ) መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ዘፍጥረት” የሚባለው የመጀመሪያው መጽሐፍ የተጻፈው በሙሴ ነው። (የመጽሐፍ ቅዱስ ጥራዝ ውስጥ የመጀመሪያዎቹ 5 መጽሐፍት በሙሴ እንደተጻፉ ብዙ ጥናቶች ይናገራሉ፤ ራሱ መጽሐፉ ይህንን ይጠቅሳል። ለምሳሌ ዘፀአት 24፥4 "ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ" ይላል፣ ሌሎችም ይህንኑ ያረጋግጣሉ።) የተዋነይ ፍልስፍና እዚህ ላይ ነው የሚገለጠው። ሙሴ እንዲህ ጻፈ፣ “እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ” (ዘፍጥረት 1፥26)። ተዋነይ ሲያነበው፣ የሙሴ ጽሑፍ ውስጥ የሰው ምኞት የታየው ይመስለኛል። የፈጣሪን በራሱ በሰው አምሳል የመሳል ነገር (ቀናተኝነት፣ ቁጡነት፣ መመለክ/መከበር መፈለግን፣ ወዘተ…)፣ የሰው ልጅ የሌሎች ፍጥረታት ገዢ የመሆን ምኞትም እዚሁ የዘፍጥረት ጥቅስ ላይ ተጽፏል። ስለዚህ መጀመሪያ ሰው ሳይሆን ፈጣሪ ነው በሰው አምሳል የተፈጠረው (“ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ”)፣ ከዚያ በሙሴ ቃል ውስጥ ነው፣ ፈጣሪ ሰውን የፈጠረው ( "ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ")። ተዋነይ ዘ ጎንጅ የሙሴን ድርጊት እንደፍትሓዊ እርምጃ የቆጠረው ይመስላል። እስራኤላውያን ፈርተው የሚታዘዙለት አንድ ሕግ አውጪ መኖር ነበረበት። ለዚያም ነው በአምሳሉ መልሶ የሚፈጥረውን ፈጣሪ ሙሴ ቀድሞ በአምሳሉ የፈጠረው እያለን ይመስላል። https://t.me/tibebethuopia https://t.me/tibebethuopia https://t.me/tibebethuopia #ለወዳጅዎ #ያጋሩ🙏
Показати все...
ጥበበ ኢትዮጵያ💚💛❤️

የጥበብ መጀመሪያው እግዚአብሔርን መፍራት ነው ። ጥበብ እግዚአብሔር ነው 🙏🙏🙏 የተሰወረውን የአባቶቻችን ጥበብ እና እውቀት ለዓለም ያበራ ዘንድ እንገልጣለን። ይህንን ቻናል Join በማድረግ ስለ ቀደምት አባቶቻችን እምቅ የሆነ ጥበብ እና እውቀት አውቀን ለሌሎችም በማሳወቅ ሀገራችንን ወደቀደመ ክብሯ በጋራ እንመልሳት።

መጽሐፍ የሚወጣው፣ የተዋነይ ዘ ጎንጅ 5 መሥመር ቅኔ ጎንጅ ቅኔ ያጠናበት ደብር ሥም ነው። ደብረ ጥበብ ጎንጅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም። ተዋነይ የባለቅኔው ሥም ነው። (የግዕዝ ትርጉሙ "ዋናተኛ" ማለት ነው።) ሊቁ ተዋነይ የልኅቀቱን ያክል እምብዛም አይወራለትም፤ ነገር ግን በዘመኑ ወደር የሌለው ልኂቅ ስለመሆኑ ሥራው ይናገራል። የሕይወት ተፈራ "Mine to Win" የተሰኘ ድርሰት መቼቱን በዐፄ ዮሓንስ ንግሥና ዘመን፣ በጎጃም/ጎንደር የቅኔ መማሪያ ደብሮች ያደረገ ልብወለድ ነው። ልቦለዱ የቅኔ ትምህርት ስርዓትን ያስተዋውቀናል፤ በበኩሌ የቅኔ ትምህርትን እና የቅኔ ሊቃውንት ታላቅነት ቀድሞ ከነበረኝ ግንዛቤ የበለጠ እንዲሆን አድርጎኛል። በተለይ የተዋነይ ዘ ጎንጅ (በውኑ ዓለም የነበረ ባለቅኔ) ተከታይዋ አምስት መሥመር ቅኔ መጽሐፍ የሚወጣት እንደሆነች ልቦለዱ አሳሰበኝ። ወይም በአጭሩ ብዙ ምዕራባውያን ስንት መጽሐፍ የጻፉለት ፍልስፍናን በአምስት መሥመር ይዟል። የቅኔው ትርጓሜ የመጽሐፍ ቅዱስን እና የመጽሐፍ ቅዱሱን ፈጣሪ ኅልውና ይሞግታል። “የአምን ወይገኒ ኵሉ ዓለም በዘፈጠረ ለሊሁ ብዙኃን እንዘ ይገንዩ ይስግዱ ቅድሜሁ ለነጽሮ ዝኒ ነገር እሥራኤል ከመይፍርሑ ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ።” (ተዋነይ ዘ ጎንጅ። ምንጭ፣ሕይወት ታደሰ ወደአማርኛ የተረጎመችው የሕይወት ተፈራ መጽሐፍ) ትርጉሙን በኋላ እመለስበታለሁ። ስለተዋነይ መጀመሪያ የሰማሁት የበውቀቱ መጽሐፍ ላይ ነበር። እሱም በጨረፍታ - “የሌሊት ዜማዎች” የሚለው ግጥሙ ውስጥ። በውቀቱ ተዋነይን በግጥሙ ግርጌ ማስታወሻው አስተዋውቆን ያልፋል፣ “ተዋነይ በቅኔ ቤት አፈ ታሪክ ሞትን በግዝት ለሰባት ዓመታት ያቆመ ጀግና ነው"። ከዚያ በኋላ፣ አዲስ አድማስ ላይ የወጣ አንድ ጽሑፍ ተዋነይ የተላከበትን መልአከ ሞት ደጃፉ ላይ በምትሐት 7 ዓመት አቁሞት በማርያም አማላጅነት ነው ገብቶ ነፍሱን እንዲወስድ የፈቀደለት የሚል አፈ ታሪክ አለ ይለናል። በሌላ በኩል ዕፀ ሕይወት አግኝቶ ነገር ግን በአጠቃቀም ስህተት ግማሽ ሰውነቱ ሞቶ ግማሹ ሲኖር፣ ፈጣሪውን ለምኖ ነው ሙሉ ለሙሉ የወሰደው የሚል ሌላ አፈ ታሪክም አለ። የኋላ ኋላ ቴዲ አፍሮም አንድ ዘፈኑ ላይ ሥሙን ጠቅሶት ያልፋል። በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን የተጻፈው የአለቃ ተክለየሱስ ዋቅጅራ "የኢትዮጵያ ታሪክ" (በሚል በሥርግው ገላው የተሰናዳው መጽሐፍ) ላይም ሥሙን እንዲሁ በአጭሩ ተጠቅሶ አገኘሁት። እንዲህ ይላል፣ “ዐፄ በካፋ በዘመኑ ከክፉ ሥራ በቀር ፩ ቀን በጎነት ሥራ አልሠራም። ያን ግዜ ተዋነይ የሚባል የጎንጅ ደብተራ ጠንቋይ ነበረው። ሙያው ከርሱ ጋራ ነበረ። በካፋም ፱ ዓመት ነግሦ [በ1723] በክፉ ሞት ሞተ።" ተዋነይን የቀድሞ ታሪክ የሚያስታውሰው እንዲህ ነው ማለት ነው? በርግጥም ይህን መሰል ቅኔ እየጻፈ መልካም ሥም ቢኖረው ነበር የሚገርመኝ። የፍቅር እስከመቃብሩ "ጉዱ ካሣ" የእውነተኛ ባለታሪክ ቢሆን ኖሮ (የእውነተኛ ሰው መነሻ ተደርጎ ነው የተጻፈው የሚሉ አሉ) በታሪክ የሚታወሰው እንደቀውስ ነበር። ከዚህ አንፃር የተዋነይ ዘ ጎንጅ እንደ ጠንቋይ መታወስ ላይገርም ይችላል። በነገራችን ላይ፣ ተዋነይ የዐፄ በካፋ አማካሪ ከመሆኑ በፊት የንጉሡን ምግብ ዕፀ መሰውር ለብሶ (እንዳይታይ ሆኖ) ይበላባቸው ነበር የሚባል አፈ ታሪክም አለ። ከዚያ በኋላ ደግሞ ገጣሚው ኤፍሬም ሥዩም “ተዋነይ" በሚል ርዕስ “ብሉይ የግዕዝ ቅኔያት ፍልስፍና” ትርጉም የያዘ መጽሐፍ አሳትሟል። "ቅድመ መግቢያ"ውን የጻፉለት ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን የተዋነይን ሁለት ቅኔዎች መርቀውልን ያልፋሉ። ከሁለቱ አንዱ የታችኛው ነው። ፀሐየ ሰማይ ያውዒ ሀገረ መርቄ ርኁቅ፣ እንዘ ቅርብቶ ደደከ ኢያመውቅ።" ትርጉሙ እንዲህ ነው፦ አንቺ ፀሐይ - አፍንጫሽ ሥር ያለው - ደጋ ምንም ሳይሞቅ፣ እንደምን ተቻለሽ - ቆላውን ከሩቁ - እንደዚህ ማወበቅ። [ሳይንስ ለዚህ የተዋነይ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ የአየር ጥቅጥቅነት (ዴንሲቲ) ከፍታ ቦታ ላይ የሚቀንስ መሆኑን ነው። ሙቀት ደግሞ በባዶ ቦታ (ቫኪዩም) ላይ አይቆምም። ዞሮ፣ ዞሮ ሳይንስ የሚመልሰው ጥያቄው ቀድሞ የተገኘ እንደሆነ ነው።] ተዋነይ የነበረው ጭንቅላት እንዲህ ዓይነት ጠያቂ ነበር፤ አጠያየቁ ደግሞ በቅኔ። ስለተዋነይ ሕይወት ይሄ ነው የሚባል መረጃ አላገኘሁም። ነገር ግን የዛሬ ሰዎች ለተዋነይ ቅኔ ያስተማረው መንፈስ ቅዱስ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ሰምቻለሁ። በመጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ በውኃ ላይ እንደተራመደ ሁሉ፣ ተዋነይም በጣና ውኃ ላይ የሚራመድ ምትሐተኛ ነበር የሚሉትም አሉ። በደመና ተጭኖ ዓለምን ጎብኝቷል እስከማለትም ይደርሳሉ። "ተዋነይ በጣና፣ ይመስላል ደመና" ይባላል።  ኤፍሬም "የቅኔ ፈጣሪዋ" ይባላል ይለናል - ተዋነይን። ነገር ግን በትርጉሙ ላይ በመግቢያዬ የጠቀስኳትን፣ ይሄን ሁሉ ለመዘብዘብ ያበቃችኝን ቅኔውን፣ ከሌሎች ተርጓሚዎች በተለየ ነው የተረጎማት። ሲጀመር፣ የመጨረሻዎቹን ሁለት ስንኞች ብቻ ነው የሚተረጉማቸው። ሲቀጥል፣ የአማርኛ ትርጉሙ ላይ አምስቱንም መሥመሮች ነው የሚተረጉማቸው። "የሚያነቡት አማርኛውን ብቻ ነው" ብሎ ነው ብለን እንዳንገምት ደግሞ መግቢያው ላይ "ምጣኔነቷ ሁለት መሥመር ነው" ይለናል። ትርጉሙን እነሆ፣ “የሕግ ባለሟል የፍት’ አባት ሙሴ ከሕግ አንቀፅ በፊት ሊያመልከው ‘ሚሻውን ፈጣሪን ፈጠረው። ፍትሕ ‘ሚባል እግዜር ሕግ የሚባል እግዜር ሙሴ እርሱን ለመውደድ ሲጨነቅ አይና ፈጣሪ ወደደው ሙሴን ፈጠረና ይህ የኤፍሬም ትርጉም፣ በኔ እምነት፣ የተዋነይን ፍልስፍና ግልጽ አያደርገውም። የመጨረሻዎቹን ሁለት ስንኝ ትርጉሞች ያየን እንደሆነ፣ ‘ፈጠረ’ የሚለውን ቃል ለሙሴ ሲሆን ‘ወደደ’፣ ለፈጣሪ ሲሆን ደግሞ ‘ፈጠረ’ እያለ ተርጉሞታል። ይህ “ሙሴ ፈጣሪውን ፈጠረ” ብሎ አንድ ክርስቲያን ሊጽፍ አይችልም ከሚል አዕምሮ የፈለቀ ትርጉም ይመስላል። ይህንን ይዤ አንዲት በፒኤችዲ ደረጃ የግዕዝ ተማሪ ወዳጄ የሆነችው ሔዋን ስምኦን ጋር ሔድኩኝ። እሷም [‘አዋቂዎች ጠይቃ’] ‘ፈጠረ’ የሚለው የግዕዝ ቃል ሊኖሩት ከሚችሉት ትርጉሞች መካከል ሁለቱ “ወደደ” እና “ፈጠረ” የሚሉት መሆናቸውን ነገረችኝ። (የሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን ግዕዝ - አማርኛ መዝገበ ቃላት ግን ‘ፈጠረ’ ለሚለው እና ለ11 ብዜቶቹ አንድም ‘ወደደ’ የሚል ወይም ተቀራራቢ ትርጉም አይሰጥም።) የሆነ ሆኖ፣ በእርሷ የስድ ንባብ ትርጓሜ፣ የሙሉ ቅኔው እያንዳንዱ ስንኝ እንዲህ ሊተረጎም ይችላል። “ያምናል ይገ:ዛል ዓለም ሁሉ ራሱ ለፈጠረው ብዙዎች አምነው በፊቱ ሲሰግዱ ይሄንንም ነገር ለማስተዋል እሥራኤል ይፈሩ ዘንድ ሙሴ ፈጣሪውን ወደደው ፈጣሪውም እሱን ወደደው” ይሁን እንጂ በእሷ ትርጉም ውስጥ ያሉት የመጨረሻዎቹ ሁለት ስንኞች፣ ከላይኞቹ ስንኞች ጋር በዐውድ አይገጥሙም። ትርጉማቸው እንዲያ ከሆነ ቅኔውን ተራ ያደርጉታል። ይህ ትርጉም የሚስማማቸው ሊቃውንት፣ ‘ተዋነይ የተቸው ከእሱ በፊት የነበረውን የጣኦት አምልኮ ነው’ ብለው ያምናሉ ብላኛለች። ነገር ግን እንደብሉይ ኪዳን ከሆነ ሙሴም ቢሆን መሰዊያ አስቀርፆ ነው እንዲያምኑ የሰበካቸው - መጽሐፉም የሚነግረን እንደዛ ነው። በዚህ የቅኔው ትርጉም ሔዋን እንዳለችኝ፣ "ብዙ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የተስማሙበት ነው"። እኔ ግን ስምምነቱን አሳምኖኝ አልተቀበልኩትም። የቤተ ክርስትያን ሊቃውንት ሥራ አማኞችን መጨመር እንደሆነ አውቃለሁ። ስለዚህ የሕይወት ተፈራ መጽሐፍ (የአማርኛው ትርጉም) ላይ ያለውን የቅኔውን
Показати все...
ምሁር ኢየሱስ ገዳም ከተገደመ ከ250 በላይ ዓመታትን ያስቆጠረ ጥንታዊ ገዳም ነው። በጉራጌ ሀገረ ስብከት ምሁር ወረዳ ውስጥ ይገኛል። ስያሜውን ያገኘው ከሰባት ቤት ጉራጌ የአንዱ ቤት መጠሪያ በመሆነው “ምሁር” ነው። ገዳሙ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ከፊደል ገበታ ትምህርት ጀምሮ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ስለማበርከቱ የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ። ብዕር ቀርጾ፣ ቀለም በጥብጦ፣ ብራና ፍቆ ታሪክን የመሰነድ ስልጣኔ በደቡብ ኢትዮጵያ እንዲስፋፋ የትምህርት ማዕከል ሆኖ ስለማገልገሉ በብዙዎች ተመስክሮለታል።   ሳይንሳዊም ሆነ ባህላዊ ስያሜአቸው በአካባቢው አስጎብኚዎች ጭምር በውል ያልታወቀ እድሜ ጠገብ ዛፎች፣ ጥቅጥቅ ደኑን የተጠለሉ ብርቅዬ እንስሳትም የገዳሙ ድምቀቶች ናቸው። ነብር፣ ጦጣ፣ ድኩላ እና ሌሎችም የዱር እንስሳት እንደሚገኙ ሰምተናል። በገዳሙ ከዘመነ ዮዲት ጉዲት በፊት በ804 ዓ.ም. እንደተተከለ ታሪክ ያስረዳል። በገዳምነት የተመሰረተው (የተገደመው) በኢትዮጵያዊው ፃዲቅ አቡነ ዜና ማርቆስ በ13ኛው ክ.ዘ በ1250 ዓ.ም. መሆኑን መዛግብት ይጠቁማሉ። አካባቢዉ ከባህር ወለል በላይ 2,330 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል። የገዳሙ ስፋት ወደ 10 ሄክታር የሚጠጋ ሆኖ ከ6 በላይ  ትልልቅ ግቢዎች የተከፈሉ ናቸው። ዘመናዊ የት/ቤት ግቢ፣ የመንፈሳዊ ት/ቤት ግቢ፣ የካህናት ማሰልጠኛ ግቢ፣ የዋናው የቤተክርስቲያን ግቢ፣ የወንድ መነኮሳት ግቢ፣ የከብት ርባታ ግቢ እና ሌሎችም ይገኛሉ። ገዳሙ በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ጥንታዊያን አድባራትና ገዳማት መካከል ከቀዳሚዎቹ ተርታ እንደሚሰለፍ ብዙዎች ይስማማሉ። ክርስትና ኢትዮጵያ ውስጥ የገባው በ350 ዓ.ም. ክርስትና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት መሆኑን በማንሳት ለአባባላቸው ማስረጃ ያስቀምጣሉ። በዚህ ታሪክ ክርስትናን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣታቸው የሚነገርላቸው ዘጠኝ መነኮሳት ናቸው። እነኝህ መነኮሳት ቋንቋን ተምረው ክርስትናን ካስፋፉ በኋላ አብያተ ክርስቲያናት ታነፁ፣ ገዳማት ተገደሙ። የምንኩስና ህይወትም በዚያን ጊዜ ተጀመረ። በ"ምሁር እየሱስ ገዳም" ዙርያ የተጻፉ የታሪክ መዛግብት እንደሚያስረዱት ገዳሙ ከሀገር በቀል ባህላዊ ዕምነቶች ውጭ ያለ ሃይማኖት በመስበክ በአካባቢው ቀዳሚ ነው። ከወይራ ዛፍ የተሰሩት እድሜ ጠገብ ቤቶች የጎብኚዎችን ቀልብ ይስባሉ። ቤቶቹ ከሕጻን እስከ አዋቂ እንደ ደረጃቸው መንፈሳዊ ትምህርት የሚያገኙባቸው ናቸው። በገዳሙ ግቢ ሰባት ጉባዔ ቤቶች ይገኛሉ። ከቀለም ትምህርት ውጭ ሁሉም ዓይነት የቤተ-ክህነት ትምህርቶች ይሰጡባቸዋል። ሰባቱ የጉባዔ ቤቶች የንባብ ቤት፣ ቅዳሴ ቤት፣ ዜማ ቤት፣ መጽሐፍ ትርጓሜ፣ አቋቋም ቤት፣ የቅኔ ቤት እና በገና ቤት (በገና ቤት የመጨረሻው ደረጃ ሲሆን የበገና ድርደራ ትምህርት የሚሰጥበት ነው) ይባላሉ። የገዳሙ የአብነት ተማሪዎች በእነዚህ የጉባዔ ቤቶች እንደ ደረጃቸው ትምህርታቸውን ይከታተላሉ። በ"ምሁር ኢየሱስ ገዳም" ውስጥ ያለፈው ትውልድ ለአሁኑ ምን እንዳወረሰ የሚያሳይ ቤተ-መዘክር ይገኛል። ቤተ-መዘክሩ በወቅቱ የገዳሙ የበላይ ጠባቂ በነበሩት አቡነ መልከ ጼዴቅ አማካኝነት በ1995 ዓ.ም. እንደሆነ ይነገራል። በቤተ መዘክሩ ውስጥ የኢትዮጵያን ታሪክ በየፈርጁ የሰነዱ መዛግብት ተሰንደው ይገኛሉ። የአፄ ምኒልክ የጦር መሳሪያ፣ ባልቻ አባ ነፍሶ ለቤተክርስቲያኗ ያበረከቱት ብራና መጽሐፍ፣ በይዘት እና በክብደት የገዘፈ በግእዝ ቋንቋ የተጻፈ የብራና መጽሐፍ፣ አጼ ኃይለ ሥላሴ በጦርነት ወቅት እንዲጸለይላቸው ለቤተክርስቲያን የላኩት ደብዳቤ እና ሌሎች ታሪካዊ መዛግብት ይገኛሉ። የገዳሙ በረከት በሁላችን ላይ ይደር🙏🙏🙏 ይህ ጥበበ ኢትዮጵያ ነው ። ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት @Kineeti ላይ አድርሱኝ👈 https://t.me/tibebethuopia https://t.me/tibebethuopia https://t.me/tibebethuopia #ለወዳጅዎ #ያጋሩ🙏፦
Показати все...
ጥበበ ኢትዮጵያ💚💛❤️

የጥበብ መጀመሪያው እግዚአብሔርን መፍራት ነው ። ጥበብ እግዚአብሔር ነው 🙏🙏🙏 የተሰወረውን የአባቶቻችን ጥበብ እና እውቀት ለዓለም ያበራ ዘንድ እንገልጣለን። ይህንን ቻናል Join በማድረግ ስለ ቀደምት አባቶቻችን እምቅ የሆነ ጥበብ እና እውቀት አውቀን ለሌሎችም በማሳወቅ ሀገራችንን ወደቀደመ ክብሯ በጋራ እንመልሳት።

📜 የግእዝ ትምህርት ክፍል ፪ መጋቢ ሐዲስ አማኑኤል መንግሥተ አብ https://t.me/tibebethuopia https://t.me/tibebethuopia https://t.me/tibebethuopia #ለወዳጅዎ #ያጋሩ🙏
Показати все...
ክፍል_ሁለት_የግእዝ_ትምህርት_EOTC_32kbps.mp34.74 MB
የዓመቱ መስከረም 1 ቀን መቼ መቼ ትውላለች? መስከረም አንድ ቀን መቼ እንደምትውል ለማወቅ ዓመተ ዓለምን ከመጠነ ራብዒት ጋራ ደምረን በእለታቱ መጠን በ7 አካፍለን ቀሪው 1 ከሆነ ማክሰኞ ፤ቀሪው 2 ከሆነ ረቡእ፤ቀሪው 3 ከሆነ ሐሙስ፤ቀሪው 4 ከሆነ አርብ፤ቀሪው 5 ከሆነ ቅዳሜ፤ቀሪው 6 ከሆነ እሑድ፤ ያለ ቀሪ ከተካፈለ ሰኞ ይውላል። የ2015 ዓ.ምየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 🌏                              ========= 👉በኢትዮጵያ ዘመን  አቆጣጠር ከክርስቶስ ልደት በፊት ዘመን የተቆጠረበት ጊዜ 5,500 ዓመት ነው ። 👉ይህም ዘመን ዘመነ ፍዳ፣ዘመነ ኩነኔ፣ ዘመነ ብሉይ ይባላል ። 👉ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ጀምሮ  ያለው ዘመን 2,015 ዓመት ሲሆን ይህም ዓመተ ምህረት ፣ዘመነ ሥጋዌ ፣ዘመነ ሀዲስ ፣ዘመነ መሲሕ  ይባላል ። 👉ዘመነ ብሉይ እና ዘመነ ሐዲስ  ሲደመሩ ውጤታቸው  ዐመተ ዓለም ተብሎ ይጠራል ። 👉5,500ዓመተ ፍዳ+2,015 ዓመተ ምሕረት                 =7,515 ዓመተ ዓለም 👉የዓመተ ዓለም  ጥቅም  ዓመተ ወንጌላውያንን ለማውጣት  ይጠቅመናል። 👉የ2,015 ዓ.ም ወንጌላውያኑን ለማወቅ ዓመተ ዓለምን  ለአራት ማካፈል ነው ።                ሲካፈል ቀሪው 1ከሆነ ማቴዎስ  2ከሆነ ማርቆስ 3ከሆነ ሉቃስ ያለቀሪ ከተካፈለ ዮሐንስ ነው። 👉የ2,015 ዓ.ም ወንጌላውያኑን ለማግኘት ዓመተ ኩነኔ+ዓመተ ምህረት =ዓመተ ዓለም                    5,500+2,015 =7515       7515÷4 =1878  ቀሪው 3️⃣ነው ። ምክንያቱም 1878×4=7512 ሲሆን               7515-7512=3️⃣ነው ። ስለዚህ  የ2015ዓ.ም ወንጌላዊ  ቅዱስ ሉቃስ ነው። 👉ለ4️⃣ተካፍሎ የሚደርሰው 1878 ቁጥር መጠነ ራብዒት ይባላል ። 👉መጠነ ራብኢት ማለት  ለ4️⃣ተካፍሎ የደረሰ ማለት ነው ።          👉ለኢትዮጵያውያን የዘመን መለወጫ መስከረም አንድ ቀን ነው። 👉መስከረም 1️⃣ቀን ለማግኘት ዓመተ ዓለምን እና መጠነ ራብኢትን እንደምራለን ። 👉የተደመረውን ቁጥርለሰባት ቀናት ማካፈል ። በዚህም  መሠረት ለ7️⃣ቀናት ተካፍሎ የሚቀረው 1ከሆነ  ማክሰኞ 2ከሆነ ረቡዕ 3ከሆነ ሐሙስ 4ከሆነ ዓርብ 5ከሆነ ቅዳሜ 6ከሆነ እሑድ ያለቀሪ ከተካፈለ ሰኞ ይሆናል ። 👉ስለዚህ የ2,015ዓ.ም መስከረም 1️⃣ቀን 7515+1878=9393 //9393÷7=1341ቀሪ 6️⃣ነው ምክንያቱም 1341×7======9387ይሆናል ።                      9393-9387===6 ነው ስለዚህ የ2,015 ዓ.ም መስከረም 1️⃣ቀን በዕለተ ዕሑድ ይውላል ። መስከረም 1 በዋለበት ሚያዝያ 1 ይውላል ጥቅምት 1 በዋለበት ግንቦት 1 ይውላል ህዳር 1 በዋለበት ሰኔ 1 ይውላል ታሕሣሥ 1 በዋለበት ሐምሌ 1 ይውላል ጥር 1 በዋለበት ነሐሴ 1 ይውላል። ይህም ማለት ለምሳሌ መስከረም 1 ቀን እሁድ ከዋለ ሚያዝያ 1 ቀንም እሁድ ይውላል ማለት ነው። ምንጭ ፦ ፈለገ ጥበባት https://t.me/tibebethuopia https://t.me/tibebethuopia https://t.me/tibebethuopia #ለወዳጅዎ #ያጋሩ🙏
Показати все...
ጥበበ ኢትዮጵያ💚💛❤️

የጥበብ መጀመሪያው እግዚአብሔርን መፍራት ነው ። ጥበብ እግዚአብሔር ነው 🙏🙏🙏 የተሰወረውን የአባቶቻችን ጥበብ እና እውቀት ለዓለም ያበራ ዘንድ እንገልጣለን። ይህንን ቻናል Join በማድረግ ስለ ቀደምት አባቶቻችን እምቅ የሆነ ጥበብ እና እውቀት አውቀን ለሌሎችም በማሳወቅ ሀገራችንን ወደቀደመ ክብሯ በጋራ እንመልሳት።

እንኳን ለዘመነ ሉቃስ አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር በአጭሩ .... በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓመታት ሁሉ በአራት መደባት ይዞራሉ፤ እነሱም ስለ ሐዋርያት ስሞች ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ (ተጨማሪ የጳጉሜ ቀን የሚቀበለው) እና ዘመነ ዮሐንስ ይባላሉ።   በኢትዮጵያ ታላቅ የጊዜ ቀመር መፃህፍ የሚያስረዳ  ባህረ ሀሳብ የሚባል መፃህፍ አለ እወቀቱ እና ሰፊ ምርምሩ  በአቡሻህር(አቡሻክር) አዋቂወች  የእወቀት ልኬት የሚወሰን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር የጁልያን ዘመን ኣቆጣጠር ኣይደለም። በኣሁኑ ጊዜ በጁልያና በጎርጎርዮስ ካለንደሮች መካከል ያለው የ13 ቀናት ልዩነት ሲሆን የዓመታቱ ቍጥሮች ልዩ ኣይደሉም። ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የ ኢትዮጵያ (እንዲሁም በ ኤርትራ አብያተ ክርስትያናት) ዋና ካሌንደር ነው። አዲስ ዓመት በ ጁሊያን ካሌንደር አቆጣጠር በ ኦገስት 29 ወይም 30 የሚጀምር ሲሆን በግሪጎሪያን ካሌንደር ደግሞ ከ 1901 እ.ኤ.አ. እስከ 2099 እ.ኤ.አ. ድረስ በሴፕቴምበር 11 ወይም 12 ይጀምራል። ለመሆኑ የኢትዮጵያ አዲስ አመት ስንት ሰአት ነው የሚገባዉ ? አንድ አመት የሚባለው የመሬትና የፀሀይ ኡደት ነው መሬት ኡደቷን ለመጨረስ አንድ አመት ወይም 365 ከ 1/4 ቀን ይፈጅባታል ስለዚህ  ማቴወስ (12ወር *30ቀን +5ቀን ጳጉሜ)+ 6 ሰአት( 1/4 ቀን ማለት 6 ሰአት ነው) መሬት ኡደቷን ለመጨረሳ ከ365 ቀን ትርፍ 6 ስአት ያስፈልጋታል ፡፡ ማርቆስ እንደዚህዉ  እንደሉቃስ ይቆጠራል ሉቃስም ያው ነው ከእያንዳንዱ ያልተቆጠሩ 6 ስአት አሉ  የማቴወስ 6 ማርቆስ 6 ሉቃስ ስድስት ሲደመር ዮሐንስ 6  አንደ ቀን ሙሉ ትሆንና ጳጉሜ 6 ቀን ትሆናለች ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የዘመን መለወጫ ሰአቱ ስንቶ ሰአት ይሆናል ?   ይህንን ብዙ ጊዜ ካስተዋላችሁ ከነጮቹ የተወሰደውን ከለሊቱ 6 ስአት የዘመን መለወጫ ነው ተብሎ እኛው ጋም ይከበራል ግን ስተት ነው፡፡ ለምን ካላችሁኝ ኑ ላሳያችሁ..... ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት መሬት ኡደቷን ለመጨረስ ከ 365ቀን + 6 ስአት ትፈልጋለች ስለዚህ ለምሳሌ ዘመኑ ማቴወስ ኑሮ  ማርቆር ሊገባ ቢሆን በስንት ሰአት  ሊገባ ይችላል፡፡ ማቴወስ አመቱን የሚጨረሰዉ ልክ ጳጉሜ 5 ከንጋቱ 12 ስአት ነው ነገር ግን ትረፏ 6 ስአት ስላለች በትክክለኛው ከቀትሩ  6 ስአት  የማቴወስ  ዘመን መለወጫ ይሆናል ማረቆስ ምሽት 12 ስአት ሉቃስ ለሊት 6 ስአት ዮሀንስ ደግሞ ከንጋቱ 12 ሰአት ይሆናል ማለት ነው፡   እንዴት የአጽዋማት  እና በአላት እንደሚወጡ እንመለከታለን ብእር አዘጋጁ ወረቀትም አቅረቡ፡፡ የኢትዮጵያውያን የዘመን ስሌት.... ጠቢባን የሆኑ አባቶቻችን የዘመን ስሌትን በሚገባ ተንትነው ዘመናዊቷ አለም ከምትጠቀምበት አቆጣጠር ረቀቅ ባለ መልኩ እስከ ሳድሲት ማለትም 0.00000185 ሰከንድ ድረስ አስለተዋል። መሬት በፀሐይ ላይ በምታደርገው ኡደት ን ተረድተው የጊዜ መለኪያ እና መቁጠሪያ አስቀመጠውልናል .... 1ኛ ሳድሲት ይህ ቁጥር 0.00000185 ሰከንድ ነው። 2ኛ ኀምሲት ይህ ቁጥር 0.00011 ሰከንድ ነው። 3ኛ ራብዒት ይህ ደግሞ 0.0067 ሰከንድ ነው። 4ኛ ሣልሲት ይህ ደግሞ 0.4 ሰከንድ ነው። 5ኛ ካልዒት ይህ ደግሞ 24 ሰከንድ ነው 6ኛ ኬክሮስ ይህ ደግሞ 24 ደቂቃ ነው። 60 ኬክሮስ=1 ዕለት ወይም 24 ሰዓት ነው። ይህ ደግሞ 1 ሰዓት 2.5 ኬክሮስ ነው ማለት ነው። ጨረቃ በቀን ከፀሐይ 1 ኬክሮስ ከ 52 ካልዒት ከ 31 ሣልሲት በአነሰ ነው። በቀን 1 ኬክሮስ በ30 ቀን 30 ኬክሮስ ይሆናል። በ2 ወር 60 ኬክሮስ ይሆናል። 60 ኬክሮስ ደግሞ 1 እለት ስለሆነ።በ2 ወር 1 እለት በ12 ወር 6 እለት ታበራለች ማለት ነው። በ12 ወር ወይም በአንድ አመት 5 ቀንና 15 ኬክሮስ ከ1 ሣልሲት ይሆናል።...... የቀረችው 52 ካልዒትን ልቀይረው.... 52 ካልዒት×30 ቀን×12 ወር=18720 ካልዒት በአመት ይገኛል። ይህንን ወደ ኬክሮስ ስንለውጠው 312 ኬክሮስ ይመጣል።በመቀጠል 30 ሣልሲት×30 ቀን×12 ወር 10800 ሣልሲት ይመጣል ይህንን ወደ ኬክሮስ ስንቀይረው 3 ኬክሮስ ይሆናል። ይህ ማለት የ 52 ካልዒትየ 30+(1) ሳልሲት ጠቅላላ ስንደምረው ... 312+3=315 ኬክሮስ ይሆናል። ይህንን ወደ እለት ስንቀይረው 5 ቀን ከ15 ኬክሮስ ይሆናል።.... ይህች 5 ቀን ተሰብስባ ጷግሜን ናት.....። የተረፈችው 15 ኬክሮስ ለ4 አመታት ስትጠራቀም... በ4 ዓመት 4×15=60 ኬክሮስ ወይም አንድ እለት ይሆናል። በአራት ዓመት አንድ ጊዜ ጳጉሜን 6 የምትሆን በዚህ ምክንያት ነው።..... ከላይ የ 30 ዋን ሳልሲት ሰርቸ አንዷን አላሰላሆትም....አንዷ ሣልሲት በ600 ዓመት 1 ቀን ትሆናለች።ይኽውም 1 ሣልሲት×30 ቀን×12 ወር×600 ዓመት 216000 ሣልሲት ይገኛል ይህንን ወደ ኬክሮስ ስንቀይረው 60 ኬክሮስ ይሆናል።60 ኬክሮስ ደግሞ አንድ ቀን ወይም እለት ነው። ስለዚህም በ600 ዓመት አንድ ጊዜ ጳጉሜን 7 ትሆናለች ማለት ነው።... ወይም በቀላል መንገድ ላሳያችሁ... አንድ ቀን =365 እለት ከ 15 ኬክሮስ ከ 6 ካልዒት / ወይም 365 ቀን ከ 6 ስዓት ከ 2 ደቂቃ ከ 24 ሰከንድ ነው...36o ቀን + 5 ቀን ጳጉሜ .. ይሆንና 6 ስአት ከ 2 ደቂቃ ከ 24 ሰከንድ ትተርፍለች... የተሰባሰበችው 6 ስአት በ አራተኛው አመት 24 ስአት ወይም አንድ ቀን ስትሆን ጳጉሜ 6 ትሆናለች። ትራፊ 2ደቂቃ ከ 24 ሰከንዷ ትሰበሰባለች ይህ ማለት በ 600 አመት 24 ስአት ወይም አንድ ቀን ትሞላለች። ይህ በ 600 ኛው አመት ጳጉሜን 7 ያደርጋታል ማለት ነው..... አበቅቴ እና መጥቅእ አበቅቴ ማለት ተረፈ ዘመን ማለት ነው።ይህም ማለት ጨረቃ ከፀሐይ ባነሰ የምታበራበት የጊዜ መጠን ነው።ፀሐይ በዓመት 365 ቀን ከ15 ኬክሮስ ከ1 ሣልሲት ታበራለች።ጨረቃ ደግሞ 11 ቀን አንሳ 354 ቀን ታበራለች።በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት አበቅቴ ይባላል። ስለዝህ በባቶች በተገለጠላቸው መጠን 11 ጥንተ አበቅቴ ይባላል። መጥቅዕ ማለት ትረጉሙ ደወል ሲሆን አጽዋማትን እና በዓላትን የሚያስገኝ ነው ከዚህ ላይ ተንተረሰን በዚህ ቀን ይህ ጾሜ በዚህ ዕለት ይህ በዓል ለማለት ያስችላል...። መጥቅዕ እና አበቅቴ ተደምረው 30 መሆን ስላለባቸው መጥቅዕ 30-11=19 ይሆናል። ስለዚህ በመጀመሪያው ዓመት 11 አበቅቴ ከሆነ በሁለተኛው አመት 22 ይሆናል በሦስተኛው 33 ይሆናል።ከ30 በላይ ሲሆን በ30 አካፍለን ቀሪውን እየያዝን አበቅቴን እናወጣለን ስለዚህ 3 ይሆናል።ከዚያ በአራተኛው 3+ 11=14 እያለ ይሄዳል።አበቅቴና መጥቅእ ሁለቱ ተደምረው 30 ስለሚሆኑ አንዱ ከተገኘ ሌላኛውን ከ30 በመቀነስ እናገኘዋለን። አለም ከተፈጠረች ጠቅላላ ዕድሜ 5500+2015=75135አመት....ስለዚህ በሚቀጥለው ዓመት ዘመኑ ዘመነ ማን ነው የሚለውን ለማወቅ ስንፈልግ ዓመተ ዓለሙን ለ4 አካፍለን ቀሪው 1 ከሆነ ዘመነ ማቴዎስ ፤ቀሪው 2 ከሆነ ዘመነ ማርቆስ ፤ቀሪው 3 ከሆነ ዘመነ ሉቃስ ያለ ቀሪ ከተካፈለ ዘመነ ዮሐንስ ነው።
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.