uk
Feedback
Saint George Sport Club - Offical Page/የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል

Saint George Sport Club - Offical Page/የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል

Відкрити в Telegram

Professional Sport Club Website -http://saintgeorgefc.com/blog/ Facebook - https://www.facebook.com/Saint-George-SA-177342563049631 YouTube -https://www.youtube.com/channel/UC1M4f0IYEbdcwjMz-QQrepg 💛❤️አንድ ክለብ አንድ ቤተሰብ 💛❤️

Показати більше
8 393
Підписники
+424 години
+227 днів
-930 день
Архів дописів
ፀጋ ከድር በፈረሰኝነቱ ይቀጥላል 🖌
ፀጋ ከድር በፈረሰኝነቱ ይቀጥላል 🖌

📝 signed and sealed ብሩክ 💛❤️ መልበሱን ይቀጥላል 💯
📝 signed and sealed ብሩክ 💛❤️ መልበሱን ይቀጥላል 💯

ጥቅል መረጃ ✅ ስፖርታዊ ጉዳዮች ✅ መሰረተ ልማት ✅ አስተዳደር ✅ ህጋዊ ጉዳዮች ✅ ፋይናንስ ✅ የኛ ሳንጃው 💯
ጥቅል መረጃ ✅ ስፖርታዊ ጉዳዮች ✅ መሰረተ ልማት ✅ አስተዳደር ✅ ህጋዊ ጉዳዮች ✅ ፋይናንስ ✅ የኛ ሳንጃው 💯

ትንንሾቹ ዛሬም ተጋጣሚያቸውን በሰፊ የጎል ልዩነት ደምስሰዋል ቅዱስ ጊዮርጊስ 7 - 1 ካራ አንድነት አክረም 4 ጎል ሲያስቆጥር ፥ ብሩክ ፥ ዮሀንስ እና ረመዳን አንድ አንድ አግብተዋል!!
+2
ትንንሾቹ ዛሬም ተጋጣሚያቸውን በሰፊ የጎል ልዩነት ደምስሰዋል ቅዱስ ጊዮርጊስ 7 - 1 ካራ አንድነት አክረም 4 ጎል ሲያስቆጥር ፥ ብሩክ ፥ ዮሀንስ እና ረመዳን አንድ አንድ አግብተዋል!!

ልሳነ_ጊዮርጊስ_ዕትም_082_አርብ_ሐምሌ_17_ቀን_2018_ዓ_ም.pdf5.74 MB

ልሳነ-ጊዮርጊስ በዛሬው ዕትም፡- (082) "ታዳጊዎቹ ቅዱስ ጊዮርጊስን እዲወዱና ክለቡን ለስኬት ያበቁትን መርሆዎች እንዲጠብቁ እያደረግን እንገኛለን!! (ከ17 ዓመት በታች ቡድን አሰልጣኝ ዮናስ እስ
+1
ልሳነ-ጊዮርጊስ በዛሬው ዕትም፡- (082) "ታዳጊዎቹ ቅዱስ ጊዮርጊስን እዲወዱና ክለቡን ለስኬት ያበቁትን መርሆዎች እንዲጠብቁ እያደረግን እንገኛለን!! (ከ17 ዓመት በታች ቡድን አሰልጣኝ ዮናስ እስክንድር)   ሐምሌና ቅዱስ ጊዮርጊስ (ከታሪክ ማህደር)     የዝውውር ገጠመኞችና እውነታዎች   ሌሎች ጉዳዮችንም አካተናል፡፡ ሙሉ ፒዲኤፉን በቴሌግራም ቻናላችን ያገኙታል መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ ተመኘን፡፡ Telegram (https://t.me/stgeorge123) Saint George Sport Club - Offical Page/የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል Professional Sport Club Telegram (https://t.me/stgeorge123) Saint George Sport Club - Offical Page/የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይፋዊ

Lets all wish a very happy birthday to the honourable sheikh Mohammed 🎂
Lets all wish a very happy birthday to the honourable sheikh Mohammed 🎂

ቅዱስ ጊዮርጊስ ብሩክ እንዳለ እና ተመስገን ብርሃኑን ለማስፈረም ተስማማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የ2019 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድሮችን በተሻለ ዝግጅትና በጠንካራ ስብስብ ለመሳተፍና ውጤታማ ለመሆን እያከናወነ ባለው የቡድን ግንባታ ሂደት ብሩክ እንዳለ እና ተመስገን ብርሃኑን ለማስፈረም መስማማቱን ሲገልፅ ደስታ ይሰማዋል፡፡ በዛሬው እለት በተደረገው ውይይት ብሩክ እና ተመስገን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለመጫወት የተስማሙ ሲሆን የህክምና ምርመራ አድርገው በቀጣይ በሚከፈተው የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት በፌዴሬሽን ተገኝተው ፊርማቸውን የሚያኖሩ ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ድንቅ አቋሙን በማሳየት ከተስፋ ሰጪ ወጣት ተጫዋቾች መካከል ስሙን ያስጠራው ብሩክ እንዳለ ስምምነቱን አስመልክቶ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመቀላቀል በመስማማቱ ከፍተኛ ደስታ እንደሚሰማው በዚህ መልኩ ገልጿል። "ቅዱስ ጊዮርጊስ ታሪካዊና ትልቅ ክለብ ነው። የዚህ ክለብ አካል መሆን ለእኔ ትልቅ ክብር ነው፤ የተጣለብኝን ኃላፊነት በሙሉ አቅሜ ለመወጣት እሰራለሁ።" ብሏል። በፍጥነቱ፣ በግብ የማግባት ብቃቱና በተፅዕኖ ፈጣሪ አጨዋወቱ የሚታወቀው ተመስገን ብርሃኑም ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለመጫወት በመስማማቱ የተሰማውን ስሜት ሲገልፅ "ቅዱስ ጊዮርጊስን የማውቀው ከድልና ከዋንጫ ጋር ነው። ከአዲሶቹ የቡድን አጋሮቼ ጋር በጋራ በመሆን ክለቡን ወደሚገባው የድል መንገድ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ።" ብሏል። የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ ነሲቡ ጫኮ በበኩላቸው፤ ክለቡን ወደ ቀደመ ክብሩና ስኬቱ ለመመለስ በሜዳ ላይም ሆነ ከሜዳ ውጪ የሚከናወኑ ስትራቴጂያዊ ስራዎች በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥሉ ገልጸው በዛሬው እለት ለክለቡ ለመጫወት የተስማሙት ተጫዋቾች የዚህ ረጅም ጊዜ የቡድን ግንባታ እቅድ አስፈላጊ አካል መሆናቸውን ጠቁመዋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ የቡድን ግንባታውን በማጠናከር በመጪው የውድድር ዘመን ለሁሉም ዋንጫዎች በጠንካራ ፉክክር ለመቅረብ ያለመ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች የቡድን ማጠናከሪያ እርምጃዎችን በተከታታይ ያሳውቃል። ክቡራን የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችም ትክክለኛውን የክለባችሁን መረጃ ከክለቡ ኦፊሻል የሶሻል ሚዲያዎች እና ከምንጊዜም ጊዮርጊስ የሬዲዮ ፕሮግራም ብቻ እንድታገኙ እንጠይቃለን፡፡

ልሳነ_ጊዮርጊስ_ዕትም_081_አርብ_ሐምሌ_3_ቀን_2018_ዓ_ም.pdf3.40 MB

ልሳነ-ጊዮርጊስ በዛሬው ዕትም፡- (081) የውድድር ዓመቱ የወጣቶቻችን እንቅስቃሴና የተመዘገበው ውጤት  ኢንስትራክተር መንግስቱ ወርቁን የዘከረችው ጎንደር ከተማ  8ተኛ ሳምንት ጨዋታቸውን የሚያደ
+1
ልሳነ-ጊዮርጊስ በዛሬው ዕትም፡- (081) የውድድር ዓመቱ የወጣቶቻችን እንቅስቃሴና የተመዘገበው ውጤት   ኢንስትራክተር መንግስቱ ወርቁን የዘከረችው ጎንደር ከተማ   8ተኛ ሳምንት ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ከ17 ዓመት በታች ታዳጊዎች    የ20 ሚሊዮን ብር ሽልማት የተበረከተላቸው የክለባችን ተጨዋቾች   መስተንክራዊ ድል  (ሐምሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከታሪክ ማህደር)    ሌሎች ጉዳዮችንም አካተናል፡፡ ሙሉ ፒዲኤፉን በቴሌግራም ቻናላችን ያገኙታል መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ ተመኘን፡፡ Telegram (https://t.me/stgeorge123) Saint George Sport Club - Offical Page/የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል Professional Sport Club Telegram (https://t.me/stgeorge123) Saint George Sport Club - Offical Page/የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል

በዚህ የውድድር አመት ፉክክር በዝቶባቸው ከነበሩ የቡድናችን ክፍሎች መሀከል ቀዳሚው የአማካይ ክፍላችን ነው፡፡የአማካይ ክፍላችን ለአንድ ቡድን ከሚያስፈልገው በላይ የተሰጥኦ ስብስብ የተከማቸበት የሜዳ
በዚህ የውድድር አመት ፉክክር በዝቶባቸው ከነበሩ የቡድናችን ክፍሎች መሀከል ቀዳሚው የአማካይ ክፍላችን ነው፡፡የአማካይ ክፍላችን ለአንድ ቡድን ከሚያስፈልገው በላይ የተሰጥኦ ስብስብ የተከማቸበት የሜዳ ክፍል ነበር፡፡ስለዚህም በዚህ ቦታ ላይ ቋሚ ለመሆን ፍልሚያው ቀላል አልነበረም፡፡ሀብታሙ ፥ የአብስራ ፥ ብርሀኑ ፥ ፉአድ ፥ ፋኑኤል ፥ አበባየሁ ፥ ይትባረክ ፥ አማረ እና አሚር በቦታው ላይ የመሰለፍ ጥያቄ ማቅረብ የሚያስችል ከበቂ በላይ አቅም ነበራቸው፡፡ቋሚነትን ግን ከሀብታሙ ላይ መንጠቅ ቀላል አልነበረም፡፡ ሀብታሙ በዋነኝነት ከየአብስራ ጎሳዬ ጋር መንታ የሚያስመስለውን ጥምረት ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ከብርሃኑ አሻሞ ፥ ከፋኑኤል አዳሙ ፥ ፉአድ እና አበባየሁ ጋርም የነበረው ጥምረት ስኬታማ ነበር፡፡ከጥሩ ተጫዋች ብቃት አንዱ ደግሞ አብረውት የሚጫወቱ ተጫዋቾች ምርጥ የሚባል ብቃታቸውን እንዲያሳዩ ማገዝ ነአ፡፡ሀብታሙ ያንን አድርጓል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሀብታሙ ወደፊት ሄዶ ጎል አስቆጥሯል ፥ ወደኋላ መጥቶ ለተከላካይ ክፍሉ ሽፍን ሆኗል ፥ ግራና ቀጥ ተሯሩጦ ለጓደኞቹ በቅርብ ርቀት ተገኝቷል፡፡ሜዳ ላይ ብዙ የሚታየው ልጅ ከሜዳ ውጭ ግን ዝምተኛ እንደሆነ ጓደኞቹ ይናገራሉ፡፡እሱ ዝም ቢልም ግን ኳስን የሚያውቁ ሰዎች ተገቢውን ድምጽ ሰጥተውት የአመቱ ተስፈኛ ተጫዋች ተብሎ ተሰይሟል፡፡ቀጣይ የአመቱ ኮከብ ለመባል የሚያስፈልገው የውድድሩ መጀመር ብቻ ነው፡፡ልጁ ገና ስራ መጀመሩ ነው፡፡

የሁለት ሴቶች ወግ በግራ በኩል የሚታዩት ወ/ሮ ጸጋ አብርሃ ይባላሉ፡፡በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት የእግር ኳስ ክለብ ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ወቅቱም ከ1978 - 84 ዓ.ም ነው፡፡የመሩት
+1
የሁለት ሴቶች ወግ በግራ በኩል የሚታዩት ወ/ሮ ጸጋ አብርሃ ይባላሉ፡፡በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት የእግር ኳስ ክለብ ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ወቅቱም ከ1978 - 84 ዓ.ም ነው፡፡የመሩትም ከክለቦች ሁሉ ታላቁ የሆነውን ቅዱስ ጊዮርጊስን ነው፡፡ወ/ሮ ጸጋ በሴት የእግር ኳስ መሪነት ፈር ቀዳጅ ናቸው፡፡ቅዱስ ጊዮርጊስም ሴቶችን ወደ እግር ኳስ አመራር በማምጣት ቀዳሚው ነው፡፡ በቀኝ የሚታዩት ወ/ሮ ከነአን በለጠ ይባላሉ፡፡የሲዳማ ቡና የወቅቱ ስራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ክለባቸው የ2018 የውድድር አመት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ወ/ሮ ከነአን ፕሪምየር ሊጉ አሁን ባለው ቅርጽ መከናወን ከጀመረ ወዲህ የመጀመሪያዋ ሴት ስራ አስኪያጅ ባይሆኑም ዋንጫ በማንሳት ግን የመጀመሪያዋ ሴት የፕሪምየር ሊግ ሻምፒየን ፕሬዚደንት ናቸው፡፡ በወ/ሮ ፀጋ በኩል ሴቶችን ወደ እግር ኳስ አመራር በማምጣት ቀዳሚ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ወ/ሮ ከነአንን እንኳን ደስ ያለዎት ማለት ይወዳል፡፡በሁሉም ነገር ፈር ቀዳጅ የሆነው ክለባችን ወደፊትም በርካታ ሴቶች በክለቦች አመራር ውስጥ እንዲገቡ ያበረታታል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሁን ባለው ቅርጽ መካሄድ ከጀመረ በኋላ 29 ጊዜ ተካሂዷል፡፡ቅዱስ ጊዮርጊስ 16 ጊዜ ሲያሸንፍ ሌሎች ቡድኖች በድምር 12 ጊዜ ዋንጫውን አንስተዋል፡፡1 የውድድር አመት በኮ
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሁን ባለው ቅርጽ መካሄድ ከጀመረ በኋላ 29 ጊዜ ተካሂዷል፡፡ቅዱስ ጊዮርጊስ 16 ጊዜ ሲያሸንፍ ሌሎች ቡድኖች በድምር 12 ጊዜ ዋንጫውን አንስተዋል፡፡1 የውድድር አመት በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጧል፡፡በዚህም መሰረት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጠቅላላ ዋንጫው 55 በመቶውን ሲወስድ ሌሎች ክለቦች 41 በመቶውን ይከፋፈላሉ፡፡

አሰላለፍ ✅ 👉 ፋሩክ 👉 አሚኑ ፥ ብሩክ ፥ ጳውሎስ ፥ ቶሎሳ 👉 ፋኑኤል ፥ የአብስራ ፥ ሀብታሙ 👉 ፍጹም ፥ ጸጋ ፥ ብሩክ ተቀያሪ ✍ 👉 ተመስገን ፥ አሸናፊ ፥ ሄኖክ ፥ ጥኡመልሳን ፥ አበባ
አሰላለፍ ✅ 👉 ፋሩክ 👉 አሚኑ ፥ ብሩክ ፥ ጳውሎስ ፥ ቶሎሳ 👉 ፋኑኤል ፥ የአብስራ ፥ ሀብታሙ 👉 ፍጹም ፥ ጸጋ ፥ ብሩክ ተቀያሪ ✍ 👉 ተመስገን ፥ አሸናፊ ፥ ሄኖክ ፥ ጥኡመልሳን ፥ አበባየሁ ፥ አሚር ፥ ብርሃኑ ፥ ፉአድ ፥ ክብር ፥አሮን ፥ እንየው ፥ ቴዎድሮስ

መሀሉ አይነገርም አመቱ ሲጀመር አጀማመራችን ምርጥ ነበር ፥ የአመቱ መዝጊያም ውብ ሆኖልናል፡፡በሁለቱ መሀል ግን ብዙ ስቃይ ነበር፡፡መሀሉ አይነገርም!
መሀሉ አይነገርም አመቱ ሲጀመር አጀማመራችን ምርጥ ነበር ፥ የአመቱ መዝጊያም ውብ ሆኖልናል፡፡በሁለቱ መሀል ግን ብዙ ስቃይ ነበር፡፡መሀሉ አይነገርም!