cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

አትራኮሰ-ጥበብ/ATRACOSE-TEBEBE

አትራኮሰ-ጥበብ/ATRACOSE-TEBEBE ስለ ጥበብ በጥበብ እናወራለን ከኛ ጋራ ሁኑ! ግጥም፣ ወግና መጣጥፍ፤ ታሪክና ታሪካዊ ንግሮች፤ ምርጥ ምርጥ እባባልና ምስሎች፤ ሰበርና ወሳኝ መረጃዎች፤ የድምጸ መልካሞች ሙዚቃ፤ . . በሥነ-ኪን አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን! . . . . አትራኮሰ-ጥበብ!!!

Більше
Рекламні дописи
988
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-1230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

በቀራንዮ ላይ ታየ (ሙዚቃ) ትንቢተ ኢሳያስ (ባቢ) 🎤🎤🎤 https://t.me/ATRACOSE 🎤🎤🎤
Показати все...
"የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነጻነት፤ ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካጥንት!" እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) እንኳን ለአርበኞች የድል በዓል አደረሳችሁ!
Показати все...
ለሌላኛው ድርብ የድል በዓላችንም እንኳን አደረሳችሁ!
Показати все...
መልካም በዓል!
Показати все...
በስቀለት ማግስት የሚውለው የዛሬው ቅዳሜ /ቀዳም ሰዑር/ ስያሜዎችና ምክንያቱን ለማታውቁ፤ እነሆ፦ በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ በጾም ታስቦ ይውላል። በበዓሉ ላይ በአዳም በደል ምክንያት የሰው ልጆች የውድቀት ዘመን ማብቃቱ የሚታወጅበት ቄጤማም በአባቶች አማካኝነት ለምዕመናን ይሰጣል። ይህ እለት የተለያዩ ስያሜዎች እንዳላትም ይነገራል። እነሱም፦ ፩. ቀዳም ሥዑር በሰሞነ ሕማማት በስቀለት ማግስት የሚውለው ቅዳሜ ቀዳም ሥዑር በመባል ይጠራል። በዚህ ዕለት ከድሮው በተለየ መልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምና ልጆቹን ከዲያብሎስ አገዛዝና እስራት ነጻ ለማውጣት የተቀበለውን መከራ፣ እንዲሁም ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ማደሩን በማሰብ በጾም ታስቦ ስለሚውል ቀዳም ስዑር ወይም የተሻረው ቅዳሜ ተብሏል። የማይጾመው ቅዳሜ ስለሚጾም ስዑር /የተሻረ/ ተብሏል። ፪. ለምለም ቅዳሜ ካህናቱ ሌሊት ለምእመናን ለምለም ቄጤማ ስለሚያድሉ ዕለቲቱ በዚህ ስያሜ ተሰይሟል። ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለ ዓዋዲ/ እየመቱ “ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ” የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ። ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ። ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ። ይህም አይሁድ ኢየሱስ ክርስቶስን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው። ፫. ቅዱስ ቅዳሜ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው። በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል። በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ መባሉን ለዚህ ነው! መልካም የትንሳኤ ዋዜማ🙏
Показати все...
✍በርባን መች ተፈታ?✍✍ ይፈታ አሉ እንጂ በርባን መች ተፈታ፤ ፈቺው አይደለም ወይ ያለው ጎለጎታ። መሀሪውን ለሞት ገፍተው እየሰጡ፤ ምህረት ለበርባን ሲሉ መንገድ ወጡ። ታድያ በክርስቶስ ያንን ሁሉ ደባን፤ የፈጸሙበትን አይቷል ወይ ግን በርባን? ሳዶር ለማርያም ልጅ አዴራና ዳናት፤ ለአብ ልጅ አላዶር የህመሙን ፅናት፤ በእሾህ ጉንጉናቸው ከድነውት አናቱን፤ ደሙ ልባስ ሆኖ ወዝ የሌለው ፊቱን። ማልቀስ እንኳ ሳይችል ሳያወጣ እንባን፤ ያየውን መጨነቅ አይቷል ወይ ግን በርባን? ከከርቤ የቀረፋ የዘባቾች ምራቅ፤ ልብን የሚያቃጥል የክፉዎች ስላቅ። ወጪት በተጋራው ወዳጅ መከዳቱን፤ አሳሳሙ ህማም ከሞት መበርታቱን። የገዛ ወዳጁ የክህደት ካባን፤ ደርቦ ሲመጣ አይቷል ወይ ግን በርባን? ቀሚሱን ተቃደው እጣ ሲዋሰዱ፤ የኋሊት ሲጠፈር የበረታ ክንዱ። ከዋክብት በምድር ለኢየሱስ ክብር፤ ሙታን ከመቃብር የተፈጥሮ ህብር፤ ፀሐይ ጽልመት ለብሳ ለጌታ አበሳ፤ በደካሞች ሲወድቅ የአይሁዳ አንበሳ፤ ይፈታል ወይ በርባን እንዴት ነው ፍታቱ? ላልገባው ንሰሐ ስርየት መመኘቱ። እንደው ለመሆኑ....፣ ደጃፉ ላይ ቆሞ ጠይቆ ሚገባን፤ ያንኳኳውን ጌታ አይቷል ወይ ግን በርባን? መስቀል ይዞ ካህን...፣ አዳምን ለማዳን የእግዜር ልጅ ሲሰቃይ፤ ምድር መሀል ወድቆ እሱ ቤቱ ሰማይ፤ ይፈታል ወይ በርባ እንዴት ነው ፍታቱ? ላልገባው ንሰሐ ስርየት መመኘቱ።         አይቷል  ወይ ግን በርባን? ከጀርባው ላይ ጅራፍ ስጋ ደሙን ጠግቦ፤ ሲቀር ከመንግስቱ ገራፊው ተርቦ። ተጠማሁ ሲል ውሀ እንደ ሩቅ ሀገር ሰው፤ እሱ ሆኖ ምድርን በዝናም 'ሚያርሰው። ይፈታ አሉ እንጂ በርባን መች ተፈታ፤ ፈቺው አይደለም ወይ ያለው ጎለጎታ። በአርያም ቤቱ ማን አየና ፊቱን፤ አይሁድ ነኩት እንጂ ደፍረው መለኮቱን። ሚካኤል ዝም ቢል ገብርኤል ተደምሞ፤ ከወንበዴ መሀል ጻድቅ ንጉሥ ቆሞ። ይፈታል ወይ በርባን እንዴት ነው ፍታቱ? ምንድን ነው ቀኖናው ስንት ነው ሀጥያቱ? ላልገባው ንሰሐ ስርየት መመኘቱ።       ንገሩት ለበርባን....! ቀራንዮ ሆኖ ጎንበስ ቀና ያለው፤ መስቀል ተሸካሚው መስቀል ላይ የዋለው፤ እሱ ነው ካህኑ ፈትቻለሁ ሚለው።      ለአይሁድ ንገሩ....! በቀይ ከለሜዳ ያለው ጎለጎታ፤ መንግሥተ ሰማያት እሱ እኮ ነው ጌታ!🙏        ✍️ፍሬህይወት ታምራት✍️✍️             ቀን፦ 22-26/8/2016 ዓ.ም.
Показати все...
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱ የስቅለት በዓት አደረሳችሁ። አትራኮሰ-ጥበብ!
Показати все...