cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ያሬድ አካሉ/YARED AKALU

(ልጄ ሆይ እንዳትሆን መናፍቅ ታሪክህንና ሃይማኖትህን እወቅ ።) በዚ ቻናል የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ዶግማ ቀኖና እና ትውፊትን እንዲሁም መፅሐፍተ ሊቃውንትን እና አስተማሪ የሆኑ መንፈሳዊ ኪናዊ ስራዎችን ይቀርብበታል ።

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
176
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Watch ""እግዚአብሔር ታማኝ ነው" - ዘማሪ ኤፍሬም አሰፋ | ቤተ ቅኔ - Bete Qene" on YouTube https://youtu.be/3jAgz8DPvYY
Показати все...

#ትምርተ_ሃይማኖት_ርትዕት እግዚአብሔር በ6ኛው ቀን አርብ #4 ፍጥረታትን ፈጠረ ። ከአዳም በስተቀር 3ቱ ፍጥረታት እግዚአብሔር #በቃሉ ባዘዘ ጊዜ ከየብስ ተገኝተዋል ። ዘፍ 1:24 እግዚአብሔር የብስን (ምድርን) ባዘዛት ጊዜ የእንስሳትና የአራዊት የአእዋፋትም አይነት ቁጥር የሌላቸው ታላላቅና ጥቃቅን ተባትና እንስትን አወጣች ብሏል #ኤጲፋንዮስ ። እነዚህም ደመ ነፍስ ያላቸው የደመነፍስ እውቀትና ድምፅ አላቸው የደመ ነፍስ እንስሳት በዓይነታቸውና በእንቅስቃሴያቸው #በ3 ይመደባሉ ። 1. #እንስሳት 2. #አራዊት 3. #አዕዋፍ ይባላሉ ። በእንቅስቃሴያቸው ደሞ 1. #በእግርየሚሽከረከሩ 2. #በደረታቸውየሚሳቡ 3. #በክንፋቸውየሚበሩ ተብለው #በ3 ይከፈላሉ ። በመጨረሻም #ቅድስት\ሥላሴ ለሰው አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ፈጥረው ካዘጋጁ ቡሃላ " ሰውን በመልካችን እንደ አምሳላችን እንፍጠር " ብለው አርብ እለት #ከ4ቱ ባህርያተ ስጋና #ከ3ቱ ባህርያተ ነፍስ አዋህደው አዳምን #የ30 ዓመት ጎልማሳ አድርገው በምድረ ቀራንዮ ፈጠሩት ። #አዳም ማለት እንደ #ረዓይት ሳይረዝም እንደ #ድንክ ሳያጥር ይህ ቀረው የማይባል ያማረ መልከ መልካም ማለት ነው ። ሰው በእግዚአብሔር #አምሳል ተፈጠረ ማለቱም #በአዋቂነቱ ፣ #በንፅህናው ፣ #በቅድስናው ፣ #በሕያውነቱ የእግዚአብሔር እንደራሴ ሆኖ በምድር ላይ የፍጥረታት ገዢ በመሆኑ ነው። #አንድም #1. #በንፅሀ ጠባይ #በእውቀት ፦ እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው በእውቀት አክብሮ በቅድስና ቀድሶ በንፅሀ ፀባይ ራሱን አስመስሎ ነውና ። #2. #በአገዛዝ ፦ እግዚአብሔር በባህርይ በነፍስ በፈቃድ የሚገዛውን ሰው በፀጋ ይገዛዋል ። ይህም ሰውን ሲፈጥረው የፍጥረታት አክሊል አድርጎ ስለፈጠረውነው ። #3. #በመልክ ፦ እኛ የሰው ልጆች እጅ እግር... እንዳለን እግዚአብሔርም የማይመረመር ረቂቅ አካል አለው #4. #በነፍስ እኛ የሰው ልጆች ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ እንዳለን ሁሉ ሥላሴም ልብነት ፣ ቃልነት ፣ እስትንፋስነት አላቸውና ። ሰው ረቂቅ ነፍስ ብትኖረውም መልአክ አይደለም ። ግዙፍ አካል ቢኖረውም እንስሳ አይደለም ። ስጋዊና ሟች በመሆኑ ከመላዕእት ይለያል ። ለባዊነት ፣ ነባቢነት ፣ህያዊት ነፍስ ያለው በመሆኑ ደግሞ ከእንስሳ ይለያል ። የሰው ነፍስና ስጋ ከእናትና ከአባት #ይከፈላሉ ። እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን ከፈጠራቸው ቡሃላ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት ብሎ የመረቃቸው ምርቃት እስከ እለተ ምፅአት ትፀናለችና።
Показати все...
አዋልድ መፅሐፍት አዋልድ መጻሕፍት” የሁለት ቃላት ጥምር ሐረግ ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ የመጻሕፍት ልጆች ማለት ነው፡፡ መጻሕፍት የተባሉትም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተለይተውና ተቆጥረው የምናውቃቸው ሰማንያ አንዱ መጻሕፍተ ብሉያትና ሐዲሳት ናቸው፡፡ አዋልድ መጻሕፍት የአሥራው መጻሕፍት ምሥጢር ትርጓሜ ተብራርቶ የሚገኝባቸው መጻሕፍት ናቸው፡፡ ቅዱሳን ነብያት እንዲሁም ሐዋርያት፤ በየዘመናቱ የተነሡ መምህራንና ሊቃውንት አዋልድ መጻሕፍት መጠቀማቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ /ኢያሱ 10፤13, 2ኛ ሳሙ.1፤18/ መጽሐፍ ቅዱስን ለማብራራት አዋልድ መጻሕፍት አስፈላጊ ናቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድ ወቅት ‹ሕግን አውቃለሁ›ለሚል ሰው ወንበዴዎች ደብድበው በሞትና በሕይወት መካከል ጥለውት ስለሄዱ አንድ መንገደኛ በምሳሌ አስተምሮታል፡፡ ይህን ቁስለኛ አንድ ሩኅሩኅ ሳምራዊ ወደ እንግዳ ማረፊያ ቤት ወስዶ ከጠበቀው በኋላ ለእንግዶች ማደረፊያ ቤት ጠባቂውሁለት ዲናር አውጥቶሰጠውና፤ “ጠብቀው፥ ከዚህ በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ አለው፡፡(ሉቃ.፲፥፴-፴፭) ይህ ምሳሌ ነው፡፡ በወንበዴዎች የቆሰለው ቁስለኛ፤ በኃጢአት መርዝ የተለከፈና የቆሰለ የሰው ልጅ ሁሉ ሲሆን፤ ወንበዴው ደግሞ ዲያብሎስ ነው፡፡ የአዳምን ቁስል የፈወሰው ርኁሩኁ ሳምራዊ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ይህን ቁስለኛ ያሳደረበት የእንግዶች ማረፊያ ቤት የተባለች ቤተ ክርስቲያን ናት (መዝ.፴፰፥፲፪፣ዘፍ.፵፯፥፱)፡፡ የእንግዶች ማረፊያ ቤት (የቤተ ክርስቲያን) ጠባቂዎች የተባሉት ደግሞ አባቶቻችን መምህራን ናቸው፡፡ (የሐዋ.፳፥፳፰) ራሱን በሩኅሩኁ ሳምራዊ የመሰለው ጌታችን ለቤተ ክርስቲያን መምህራን የሰጣቸው ሁለት ዲናር የተባሉት መጻሕፍተ ብሉያትና መጻሕፍተ ሐዲሳት ናቸው፡፡ ሁለቱን ዲናር ከሰጠ በኋላበነዚያ ብቻ ሳይወሰን “ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ” አለው፡፡ ይህ ቃል የሚያመለክተው በሁለቱ ዲናሮች (በብሉያትና ሐዲሳት) ተመሥርተው የረቀቀውን አጉልተው፣ የተሠወረውን ምሥጢር ገልጠው ምእመናንን የሚያስረዱ ልዩ ልዩ የትርጓሜ፣ የምክር፣ የተግሳጽ፣ የታሪክና የመሳሰሉትን መጻሕፍትን ጽፈው እንዲያስተምሩና እነዚህም ተጨማሪ መጻሕፍት በመጻፋቸው የድካማቸው ዋጋ እንደማይጠፋባቸው ሲገልጽ ነው፡፡ “እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ” ማለቱ በዳግም ምጽአቱ የድካማቸውን ዋጋ እንደሚከፍላቸው ያሳያል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዮስ አስቀድመን መከራ ተቀበልን ተንገላታንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን፡፡” (፩ኛ.ተሰ.፪፥፲፪) ብሏል፡፡ ገድል ያለው መከራውን ነው፡፡ የአዋልድ መጻሕፍት አስፈላጊነት፡- ፍቁረ እግዚእ የተባለ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ “ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤” ካለ በኋላ “ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ባልበቃቸው ይመስለኛል” (ዮሐ.፳፥፴፤፳፩፥፳፭) በማለት ተናግሯል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ሲመላለስ ያደረጋቸው ተአምራት እያንዳንዳቸው እንዳልተመዘገቡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በአጽንዖት አስረድቷል፡፡ በሌላ በኩል ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።”በማለት የአዋልድ መጻሕፍት አስፈላጊነት ምን እንደሆነ ገልጦ ተናግሯል፡፡ በዚህ የተነሣ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በልዩ ልዩ ጊዜና ቦታ ሆነው መጽሐፍ ቅዱስን ሲጽፉ አዋልድ መጻሕፍትን ለትርጓሜ፣ ለምክር፣ ለተግሳጽ፣ ለታሪክ አስረጂነት እንደተጠቀሙባቸው አስረድተዋል፡፡ (ኢያ. ፲፥፲፫፤ ፩ኛ.ሳሙ .፩፥፲፰፤ ይሁ.፱) እንግዲህ በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ከታነጽን በእነርሱ መንገድ መመራት ያሻናል፡፡ አዋልድ መጽሐፍቱ ከትምህርት ሰጪነት ባሻገርበእለት እለት ሕይወታችንለጸሎት የምንጠቀምባቸው ናቸው፡፡ በገመድ ያለ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚፈካውና የሚታየው በአምፖል ሲበራ እንደሆነ ሁሉ በአሥራው መጻሕፍት የሚገኝ ጥበብ፣ ትምህርትና ምሥጢርም የሚረዳው የሚገለጠው በአዋልድ መጻሕፍት ተብራርቶ ሲታይ ነው፡፡
Показати все...
ዳግመኛም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዕርገቱ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሞቱን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ነግሯቸዋልና፡፡ ሕማሙንና ሞቱንም እንዲዘክሩ አዟቸዋልና አሁንም ያንን ሁሉ የመድኃኔዓለምን ሞቱን ያላሰበና የሞቱን መታሰቢያ በዓል ያላከበረና እርሱንም የማይወደው ቢኖር ዕድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ከአይሁድ ጋር ነው፡፡ የአምላካችንን የመድኃኔዓለምን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ለመተባበር ያብቃን! ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
Показати все...
በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞት በአንድነት እናለቅስ ዘንድ ቅዱሳን ሁላችሁ ኑ! መድኃኒታችን ሙቷልና ፍጥረታት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ መያዝንና መታሠርን የተቀበለ መድኃኒታችን ሙቷልና፡፡ ጥፊንና ግርፋትን የተቀበለ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ መደብደብንና መመታትን የታገሰ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ ሄኖክ እግዚአብሔር ‹‹በሴም ቤት ይደር›› ብሎ አብ ስለራሱ የተናገረለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አብርሃም ቃልኪዳን የገባልህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ይስሐቅ ከሰይፍ ቤዛ የሆነህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ያዕቆብ በበረሃ የታገለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮብ በደመና የታየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሙሴ ስለ እርሱ ‹እንደእኔ ያለ ነቢይ ይነሣል› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳዊት ‹‹እነሆ በኤፍራታ ሰማነው፣ በበረሃ ዛፍም አገኘነው›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤርሚያስ ‹‹የክቡሩን ዋጋ ሠላሳ ብር ተቀበሉ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢሳይያስ ‹‹ወልድ ሰው ለመሆን ተገለጠልን፣ ሕፃን ተወለደልን፣ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅኤል ‹‹አምላክ ወደ ተዘጋች ደጃፍ ገባ፣ ከተዘጋች በርም ወጣ›› ብለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳንኤል ነጭ ሐር ለብሶ ያየኸውን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤልያስ ከሞት በፊት የሰወረህ በእሳት ፈረሶች ያሳረገህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅያስ የፀሐይ መግባቱን ያሳየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ምናሴ ችንካሮችህን ከእግር ብረት የፈታ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮስያስ ፋሲካውን ያደረግህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል ከእሳት ምድጃ ያዳናች የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አብያና ሲላ ፌንቶስ ከመወለዱ አስቀድሞ ያመናችሁበት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ የቀድሞ አባቶች ነቢያት ሁላችሁ ከፋራን ተራራና ከቴማን ይመጣል ያላችሁት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አሞፅ በአድማስ ቅጥር ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዘካርያስ በተራራዎች መካከል ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዕዝራ በአርፋድ በረሃ ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ስምዖን በክንድህ የታቀፍከውን ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዮሴፍ እንደ አንተ የተሸጠ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ጠራቢ ዮሴፍ በትከሻህ ያዘልከው በክንድህ የተሸከምከው ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ከሕፃንነትህ ጀምሮ በበረሃ ያለ እናት ያለ አባት ያሳደገህ መንገዱንም እንድትጠርግለት ያዘጋጀህና መለኮትን እንድታጠምቅ የመረጠህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢያቄምና ሐና ሆይ የልጃችሁን ልቅሶዋን የልቧንም መዘንጋት ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ ከሔዋን እስከ ፋኑኤል ልጅ እስከ ሐና ያላችሁ ሁላችሁ ቅዱሳት ሴቶች የድንግልን ልቅሶዋን ታዩ ዘንድ ኑ፣ አንድ ልጇ ሙቷልና፡፡ የለመለመ የሥጋ ሞት ሕንፃ የተጀመረበት የአቤል ተከታዩ፣ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ሔዋንን ከጥፋት ያዳናት የተገደለ መድኃኒታችን ነው፡፡ የናቡቴ ጓደኛው የተገፋው መድኃኒታችን ነው፡፡ አቤል ስለሚስቱ ሞተ፡፡ ናቡቴም ስለ ወይኑ ቦታ ሞተ፡፡ መድኃኒታችን ግን በቀኙ ያነጻት ዘንድ ስለቤተክርስቲያን ሞተ፡፡ ነፍሳችሁን ይወስዷታልና መውረዱንም አላወቁምና ስለ ወገኖቹ ኃጢአት እስከ ሞት ደረሰ ብሎ ስለ እርሱ የተናገረ አባቱን እንስማው፡፡ ሙሴም እርሱን ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፣ በሚመጣበት ቀንም አላወቁትም አለ፡፡ ዕዝራ በባሕር ጥልቅ ያለውን ማወቅ እንዳይችሉ ወልድንም ማወቅ እንዲሁ ሆነባቸው አለ፡፡ ጳውሎስም ብታውቁትስ ኖሮ የክብርን ጌታ እግዚአብሔርን ባልሰቀላችሁት ነበር አለ፡፡ በመሰደድ፣ ያለምንም በደልም በፍርድ አደባባይ በመቆም መከራ መስቀልን በመሸከም አብነት የሆናችሁ ሰማዕታት ሁላችሁ ኑ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት አስባችሁ በጋራ አልቅሱለት፡፡ ሁሉ የእርሱ ከእርሱ ለእርሱ ተፈጥሮ ሳለ በምድር ላይ ምንም ሳይኖረው ራሱን እንኳን የሚያስጠጋበት ቤት ሳይኖረው አብነት የሆናችሁ ባሕታውያንና መነኮሳት ሁላችሁ ኑ በዛሬዋ ዕለት ስለሞተው አምላካችሁ መሪር ዕንባን አልቅሱለት፡፡ ሕግ ጠብቆ፣ ሥርዓት አክብሮ፣ ነዳያንን በመመገብና ያዘኑትን በማጽናናት 33 ዓመት በምድር ላይ ኖሮ አብነት የሆናችሁ እናንት በዓለም ሆናችሁ ሕግ ጠብቃችሁ፣ አሥራት በኩራቱን አውጥታችሁ፣ ድሆችን በመርዳት የምትኖሩ ክርስቲያኖች ሁላችሁ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት ታስቡ ኑ፡፡ ‹‹የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና›› ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደጻፈልን (1ኛ ጴጥ 2፡21) እርሱ ንጹሕ ባሕርይ ሲሆን ወደ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ ለተጠመቅን ለእኛ ለተነሣሕያን ለሁላችን አብነት የሆነን መድኃኒታችን ስለእኛ ሞቷልና ሞቱን እናስብ ዘንድ ኑ በቤቱ ተሰብስበን እናልቅስለት፡፡ መታሰያውንም እናድርግለት፡፡ ጌታችን ሞቶ ተቀብሮ ካረገ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳን አባቶቻችን ለእነ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ ለእነ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንደነገራቸው የሞቱን መታሰቢያ የሚያደርግ ኃጠአተኛ እንኳ ቢሆን ሲኦልን አያያትም፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ሲኦል ራሷ አፍ አውጥታ ‹‹ይህችን ነፍስ ወደኔ አታምጡብኝ›› ብላ ትጮሃለች እንጂ ችላ አትቀበለውም፡፡ የጌታችን ወዳጆቹ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በድርብ በፍታና በመቶ ወቄት ሽቱ ገንዘው በሐዲስ መቃብር ሊቀብሩት ቢሉ ጌታችን ያን ጊዜ ዐይኑን ክፍቶ ‹‹በሰውነቴ መዋቲ ብሆን በመለኮቴ ሕያው ነኝ እንጂ ምነው እንደ እሩቅ ብእሲ ዝም ብላችሁ ትገንዙኛላችሁን?›› አላቸው፡፡ ይህን ጊዜም ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በታላቅ ድንዳጤ ሆነው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ! እንግዲያስ ምን እያልን እንገንዝህ?›› አሉት፡፡ መድኃኒታችንም እንዲህ እያላችሁ ገንዙኝ አላቸው፡- ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ተሣሃለነ እግዚኦ› እያላችሁ ገንዛችሁ ቅበሩኝ አላቸው፡፡›› ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ለወዳጆቹ ለ12ቱ ሐዋርያት፣ ለ72ቱ አርድእት፣ ለ36ቱ ቅዱሳት አንስት ‹‹እስከ ሦስት ቀን እነሣላችኋለሁ እዘኑ አልቅሱ፣ እህል ውኃ አትቅመሱ በሏቸው›› ብሎ ለዮሴፍና ለኒቆዲሞስ አክፍሎት አስተማራቸው፡፡
Показати все...
ስንክሳር ዘተዋህዶ: #መጋቢት_27 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መጋቢት 27 በዚች ቀን #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ፣ የመነኰሳት ሁሉ አባት የሆነ የከበረ አባት #ታላቁ_አባ_መቃርስ አረፈ፣ የኢትዮጵያ ንጉሥ #ሰማዕት_ገላውዲዎስ አንገቱን የተቆረጠበት ቀን ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #መድኃኔዓለም መጋቢት ሃያ ሰባት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ። ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳትለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር። እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋራ አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደሲኦል ወረደች። መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስለ ዓለም ሁሉ ድኅነት በሥጋ ተሰቅሏልና ሞቱን በአንክሮ እናዘክር ዘንድ የልቡናችን ዐይን ወደ ቀራንዮ እናንሳ! እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን ልባቸውን አስቶታልና እንደ ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደመርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው ስረወጽ አድርገው አክሊል ሠርተው ከፍላት አግብተው በጉጠት አንስተው ‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው በራሱ ላይ ደፉበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡ እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ ሞረድ 4 ማዕዘን አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ ወስፌ አድርገው 73 ችንካር ሠርተው በ73ቱ ስቁረት አግብተው በጌታችን በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ ገብቶ መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊለ ሦኩን በራሱ ላይ አድርገው ሲያበቁ ከቤት ወደ አደባባይ እያመላለሱ ‹‹ንጉሥ ሆይ!...›› እያሉ ምራቃቸውን እየተፉበት ተዘባበቱበት፡፡ መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ ሲወስዱት 136 ጊዜ በምድር ላይ ጣሉት፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት ደግሞ ‹‹ምን ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ ከዚህ በኋላ ክፉዎች አይሁድ ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር ስለታቸው ደግሞ እንደ ወስፌ የሆኑ 5 ችንካሮችን ሠርተው ሳዶር በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና በሮዳስ ደረቱን ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሰቅለውታል፡፡ ክፉዎች አይሁድ መድኃኔዓለም ክርስቶስን እንደያዙት የኋሊት አስረው አፍንጫውን 25 ጊዜ ቢመቱት ደሙ በመሬት ላይ እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ከጌቴሴማኒ እስከ ሐና ቤት ድረስ አስረው የፊተኞቹ ሲጎትቱት የኋለኞቹ እየለቀቁት የኋለኞቹም በተራቸው ሲጎትቱት የፊተኞቹ ይለቁታል፡፤ እንዲህ እያደረጉ 65 ጊዜ ከመሬት ጋር አጋጭተውታል፡፡ ሳውል በእግሩ ሲረግጠው ጌታችን ‹‹መመለስህ ላይቀር ለምን ትረግጠኛለህ?›› ቢለው ስለዚህ ንግግርህ ብሎ ሳውል 440 ጊዜ አስገረፈው፡፡ ክፉዎች አይሁድ መድኃኒታችንን በሁለት ግንዶች መካከል አድርገው 65 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡ ቀያፋ በሚመረምረው ጊዜ ጌታችን ‹‹አምላነቴን አንተው ራስህ ተናገርኽ›› ቢለው አይሁድ በእጃቸው ሲመቱት እጃቸውን ቢያማቸው ድንጋይ ጨብጠው 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡ አይሁድ ወደ ጲላጦስ ዘንድ ሲወስዱት ‹‹ምናልባት ጲላጦስ ባይፈርድበት እንኳ እንዳይቆጨን›› ብለው 305 ጊዜ በሽመል ደብድበውታል፡፡ በአምላክነቱ ቻለው እንጂ የአንዱ ምት ብቻ በገደለው ነበር፡፡ በርባን የይሁዳ የሚስቱ ወንድም (አማቹ) ስለነበር እርሱ እንደፊታለትም ከዋጋው ከ30ው ብር ጋር አብሮ ተደራድሮበት ነበር፡፡ ሰይጣን ልባቸውን ለክፋት ያስጨከናቸው ክፉዎች አይሁድ በጲላጦስ አደባባይ የጌታችንን ፂሙን 80 ጊዜ ነጭተውታል፡፡ ጲላጦስ እንደ ሕጋቸው 41 ብቻ ገርፈው እንዲለቁት ቢያዝም ክፉዎች አይሁድ ግን ጌታችንን ሲገርፉት ‹‹አሠቃቂ ግርፋቱን አይተን ልባችን እንዳይራራ›› ብለው ሰንጠረዥ ገበጣ ሰርተው ሲጫወቱ አንዱ ተነስቶ እስከ 60 እና 70 ድረስ ይገርፍና ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት ሲቀመጥ ሌላኛው ይነሣና እንደዛኛው ሁሉ በተራው 60 እና 70 ይገርፈዋል፡፡ ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ ወድቋል፡፡ የመድኃኔዓለም ወገኖች ሆይ! የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን እንነግራችኋለን፡፡ አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና ነበርና ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም አላዩትም ነበር፡፡ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም:- ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ፡፡›› ዮሐ 8፡56-59፡፡ ዳግመኛም በዮሐንስ ወንጌል ላይ እንደተጻፈው አይሁድ መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን ሰብስበው ወደ ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው ‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ›› ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ መቋቋም አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ ይህም ክስተት በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ (ዮሐንስ ወንጌል ላይ ምዕራፍ 18 ከቁጥር አንድ ጀምሮ ይመለከቷል፡፡) እናም የጌታችን ሞቱ በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ በተሠወራቸው ነበር አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ ባጠፋቸው ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን ጌታችን ወደዚህች ምድር የመጣበትን ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡ ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፡፡ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፡፡ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ለዚህ ባሕርይው አንክሮ ይገባል፡፡
Показати все...
#ጾም ጾም የመልካም ነገር ዋዜማና መጥቅዕ ስለ መሆኑ ሲናገር እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሴትም በዓላት ይሆናል ስለዚህ እውነትንና ሰላምን ውደዱ።" ዘካ. 8:19 ጾም #የአምልኮ መንገድ ነው። በአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን የነበሩበት ነቢያትና መምህራን ጌታን ካመለኩበት መንገድ አንዱ ጾም ነበር። ይህንንም ቅዱስ መፅሐፍት እንዲህ ይናገራል፦ "እነዚህም ጌታን ሲያያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ። በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከፀለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቷቸው። የሐዋ. 13: 1-2 እንዲሁም ጾም ለእግዚአብሔር ከሚደረጉ አገልግሎቶች አንዱና ዋናው ነው። ከአሴር ወገን የነበረችውና ሰማንያ አራት ዓመት በብቸኝነት በቤተ መቅደስ እግዚአብሔርን ስላገለገለች ስለ ነቢይቱ ሐና ሲናገር መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ አለ፦(በጾምና በፀሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም ነበር) ሉቃ. 2:37። የሐና አገልግሎት ጾምና ፀሎት ነበር።ምክንያቱም ጾም ታላቅ አገልግሎት ነውና። ጾም አጋንንትን የሚያወጣቸው ርኩሳን መናፍስትን የምንዋጋበት የምናስወግድበት መሣሪያ ነው። ውስጣችንን ተቆጣጥሮ በየመጠጡ ቤትና በየመሸታ ቤቱ በየጭፈራ ቤት አውሎ የሚያሳድረንን የመጠጥ መንፈስ የዝሙት የሌብነት በአጠቃላይም ክፉ መንፈስን ከውስጣችን የሚያወጣ ጾም ነው። "አሳድጌ አሳድጌ አሁን የት ልሒድ" የሚል አጋንንት ፀበል ሰፀበልና መስቀል ሲታሽ የሚስቸግር ርኩስ መንፈስ የጾም ተጋድሎ ሲጨመርበት ድራሹ ይጠፋል። ይንንም ጌታችን ደቀ መዛሙርቱ ማውጣት አቅቷቸው የነበረውን ጋኔን እርሱ ካወጣው በኋላ ወደ እርሱ ቀርበው "እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምን ነው?" ብለው ሲጠይቁት "ይህ ወገን በፀሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም" አላቸው። ማር. 9:29 ታዲያ ምን እንላለን ከጌታ ቃል ሌላ ምስክር አናመጣም። በውስጣችን መቼም አንድ ደንቃራ ወይ ኮተት አይጠፋም ሰውም አይደለን! በጾም ድራሹን ማጥፋት እንደምንችል ጌታ ነግሮናልና። ጾም ታላቅ የመንፈሳዊ ተጋድሎ መንገድ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋለ ሥጋዌው የሥራው ሁሉ መጀመሪያ ጾምን ያደረገው ለዚሁ ነበር። ቅዱስ ጳውሎስም የጌታውን አርአያ በመከተል "በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም" ይላል። 2ቆ. 11:27 ቅዱስ ጳውሎስ ከተጋደለባቸው ነገሮች አንዱ ጾም ነው። "ነገር በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን በብዙ መፅናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንፅህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር በእውነት ቃል ..." 2ቆሮ. 6: 4-6 በጾም የደከመ ሰውነት ንስሐ ለመግባት ቀዳሚ ነው። ንስሐና ፆም ሁለት ገፅታ አላቸው። በንስሐ ያለ ሁሌም በፆም፣ በፀሎት እና በስግደት የበረታ ነው። አንድ ጿሚ ስለ ቀደሞ በደሉና ኃጢአቱ ፈጥኖ ይመለሳል። ሲራክ "በቁጣው ልክ ምሕረቱም የበዛ ነው" እንዳለ የጿሚ ተስፋው የእግዚአብሔር ምሕረት ብዙ ነው ብሎ ይደክማል። ጿሚ በልቡ ጥርጣሬ የለበትም። ጌታችን፦ "በልቡ መጠራጠርን ያሰበ ቢኖር ይፀፀት፤ በሕሊናው አሳብ ዝሙት ያለበት አይቅረብ፤ በአሳቡ ድውይ የሆነ ቢኖር ይወገድ" በማለት ያወገዘውን ቃል ያስባል። እሱ ማለት ጿሚው እራሱን ለካህን አሳይቷልና።
Показати все...
🌿ይሄ ጥያቄ ከፍተኛ ደሞዝ በሚከፍለው በሽያጭ ሰራተኝነት ለመቀጠር የሚመጡ ሰዎች የተጠየቁት ነው እስቲ እናንተም ሞክሩት... አስታውስ ደንበኛ ሁሌም ክቡር ነው... በነገራችን ላይ ይሄን ጥያቄ ከተጠየቁት በሺዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች ውስጥ ጥቂት ሰዎች ወደ መልሱ ሲቀርቡ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ውስጥ በጣት የሚቆጠሩት ናቸው የመለሱት። እናንተ መኪና እየነዳቹ ስትመጡ... መንገዱ ዳር ላይ ሶስት ሰዎች ቆመዋል። ፩ በጣም የታመሙ ትልቅ እናት ፪ ከዚህ በፊት ውለታ የዋለላቹ የቅርብ ጓደኛቹ ቾክሎ እና ፫አንዲት ቆንጅዬ ሴት ምናልባት ድጋሚ ልታገኟት አትችሉም... በሚገርም ሁኔታ ደግሞ መኪናቹ ከአንድ ሰው በላይ አይዝም። ታዲያ እርሶ ማንን ይዘው ይሄዳሉ??? እስቲ ሞክሩት... ከዚህ በፊት ሳይሰሙት መልሱን በሚገባ ከመለሱ በእውነቱ እርሶ ብልህ ኖት። ነገ መልካም ይሆናል !
Показати все...
" የነዳጅ ዋጋ ኢትዮጵያን በ1 ወር ውስጥ ብቻ 10 ቢሊዮን ብር አክስሯታል " - አቶ ታደሰ ኃለለማርያም በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የጨመረው የነዳጅ ዋጋ በ1 ወር ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያን 10 ቢሊዮን ብር እንዳከሰራት ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት ፤ የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ይሸጥበት ከነበረው 60 እና 70 ዶላር ወደ 140 ዶላር ማሻቀቡ፣ ኢትዮጵያ 10 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ እንዳስወጣት ወይም እንዳከሰራት አመልክቷል። የድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ለሪፖተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፤ እንደ ሌሎቹ አገሮች ሁሉ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ኢትዮጵያንም ዋጋ እያስከፈላት ነው ብለዋል። በአንድ ወር ብቻ 10 ቢሊዮ ብር እንድታጣ ምክንያት መሆኑ እና ይህም ትልቅ ጉዳት መሆኑን ገልፀዋል። " በወርኃዊ የነዳጅ ወጪዋም ወደ 250 ሚሊዮ ዶላር ከፍ እንዲል አስገድዷል " ያሉት አቶ ታደሰ ይህም መንግሥት ይህንን ልዩነት በመሸፈን በዓለም ዝቅተኛ በተባለ ዋጋ ነዳጅ እየተሸጠ የሚገኝ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል ብለዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መጨመር የበለፀጉ አገሮችን ጭምር እየፈተነ የሚገኝ ሲሆን እንደ ፈረንሣይ ያሉ አገሮች በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ በማድረግ ህብረተሰቡ ነዳጅን ቆጥቦ እንዲጠቀም ሁሉ ማወጃቸውን አቶ ታደሰ አስታውሰው በኢትዮጵያ ነዳጅ ጭማሪ ባይደረግም ህብረተሰቡ በቁጠባ የመጠቀም ባህሉን ማዳበር አለበት ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ነዳጅ በምታስገባበት ዋጋ መሠረት ለገበያ ቢቀርብ የአንድ ሌትር የቤንዚን ዋጋ 76 ብር መሸጥ የነበረበት መሆኑንም የአቶ ታደሰ ገልፃ የሚያስረዳ ሲሆን አሁን ላይ ግን የአንድ ሌትር ቤንዚን ዋጋ 31 ብር ከ74 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል። ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#መክሊት አልተሰጠኝም እንዳንል ጠርቶ መክሊት ያልሰጠው ባሪያ የለም። ከአቅሜ በላይ ነው እንዳንል የተሰጣቸው እንደ ሰጪው ፍላጎት ሳይሆን እንደ ተቀባዮቹ አቅም ነው። ጊዜው አጠረብኝ እንዳንል የመካልዩ ጌታ የተመለሰው ከብዙ ዘመናት በኋላ ነው። እንግዲህ ላለማገልገል ምን ምክንያት እናቀርባለን ?
Показати все...