cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

💌 " ቃልም ሥጋ ሆነ..."/"And the Word was made flesh..." (John 1:14)💒

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
273
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የተሠጠህን ቁጠር ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው:: የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም:: ዕባብ ደግሞ የስይጣን አንደበት ነበረ:: ሰይጣን እንዲህ አላት :- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። ልብ አድርጉ እግዚአብሔር "ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ" አላለም:: የከለከለው አንዲት ዛፍ ነው:: ሰይጣን ግን ሁሉን ተከልክላችሁዋል? ብሎ እንዳላዋቂ ጠየቀ:: ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግግሩን የከፈተው በውሸት ነበረ:: ዓላማው ከሔዋን መረጃ ለማግኘት አልነበረም:: ሔዋን እስከዛሬ ያላሰበችውን ማሳሰብ ነበር:: ብሉ ተብሎ ከተሠጣቸው ብዙ ሺህ ዛፍ ይልቅ የተከለከሉትን አንዲት ዛፍ አሳይቶአት ሔደ:: ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስላልተሠጣት ማሰብ ጀምራ ደስታዋን አጣች:: የተከለከለችውን በልታ የተሠጣትን ብዙ ሥጦታ ከነሠጪው አጣች:: ወዳጄ የቀደመው እባብ ዛሬም መርዙን ይረጫል በሕይወታችን ከተሠጠን ብዙ ነገር ይልቅ ያልተሠጠንን ጥቂት ነገር እናስባለን:: ገንዘብ እንደሌለህ እያሰብክ ጤና እንዳለህ ትረሳለህ:: ጫማ እንደሌለህ እያሰብክ እግር እንዳለህ ትረሳለህ:: አልጋ እንደሌለህ እያሰብክ እንቅልፍ እንዳለህ ትረሳለህ:: ስለዚህ ውስጥህ ያለውን የዕባቡን ድምፅ አትስማ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ይበልጣልና የተሠጠህን ቁጠር:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ሰኔ 9 2012 ዓ ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Показати все...
+ ከመሞትህ በፊት ተናገር ብትባል + ዝንጀሮ ዕድሜ ጠግቦ ሊሞት እያቃሰተ ነው፡፡ ልጆቹ ከብበውት የመጨረሻ ቃሉን እየሰሙ ነው ፦ ‘እንግዲህ ልጆቼ አደራ ... ስሞት በክብር ቅበሩኝ ... ቀብሬን አክሱም ጽዮን አድርጉልኝ ... ፍትሐቴን ደግሞ ጎንደር አድርጉት ... ተዝካሬን ደግሞ ላሊበላ አድርጉት ...’ አለ እያቃሰተ፡፡ ልጆቹ ደንግጠው ተያዩ በመጨረሻ ግን የተናገረው ዐረፍተ ነገር ግን ከድንጋጤአቸው አረጋጋቸው ‘... ልጆቼ ይህንን የምናዘዘው ችላችሁ ታደርጉታላችሁ ብዬ ሳይሆን ... አያ ዝንጀሮ እንዲህ ብሎ ሞተ ተብሎ እንዲወራልኝ ፈልጌ ነው ...’’ ብሎ አረፈው፡፡ ይህችን አስቂኝ ወግ ያነበብኳት ነፍሱን ይማረውና ጋሽ ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር ከጻፋቸው መጻሕፍት በአንዱ ላይ ነበር፡፡ እውነትም ባይፈጸምም ደህና ነገር ተናግሮ መሞት ጥሩ ነው፡፡ ሌላው በጣም ያሳቀኝ ደግሞ የአንድ ወንጀለኛ የመጨረሻ ቃል ነው፡፡ ሀገር የበጠበጠ ወንበዴ ነው አሉ፡፡ በአንገቱ ገመድ አስገብተው ‘በል እስቲ የመጨረሻ ቃል ካለህ ተናገር’ አሉት፡፡ የተናገረው ቃል ግን ሰቃዮቹን በሳቅ ያፈረሰና እሱንም በሳቅ ታጅቦ እንዲሞት ያደረገ ነበር ፦ ‘ይብላኝ ለእናንተ እኔስ ትምህርት ወስጃለሁ!’ እውነት የዛሬዋ ቀን በሕይወት ለመቆየት የመጨረሻዋ ቀንህ ብትሆንና የመናገር ዕድል ቢሠጥህ ምን ብለህ ትሞታለህ? የግድ ትሞታለህ ባትባልም እንኳን የዛሬዋ ቀን የመጨረሻ በሕይወት የምትቆይባት ዕለት ልትሆንም ትችላለች፡፡ ከቤት ስትወጣ ምን ብለህ ወጣህ? አብረውህ ለሚውሉትስ ምን አልካቸው? ክርስቶስ መሳደብን ከመግደል ጋር ያመሳስለዋል፡፡ በቃልህ ማንን ገደልህ? ማንንስ አዳንህ? በብዕርህ ማንን ወጋህ? ማንንስ ጠገንህ? ይህን ጽሑፍ ከማንበብህ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ የተናገርከው ቃል ምን ነበር? አሁኑኑ ብትሞት ተናግረህ በነበረው ቃል ትኮራበታለህ? ያንተ ንግግር እንደ ዝንጀሮው እንዲህ ብሎ ሞተ የሚያሰኝ ነው ወይስ የሚያስቅ? በጣም ይገርማል በዓለም ታሪክ ከመሞታቸው በፊት የማይረሳ ቃል የተናገሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሊሞቱ ሲሉ እየተሳደቡ ፣ የተወለዱበትን ቀን እየተራገሙ ፣ ገዳዮቻቸው ላይ እየዛቱ የሞቱ ብዙ ናቸው፡፡ ሊሞት ሲል የተናገረውን ብቻ ሰምተህ ሰውዬው ምን ዓይነት ሰውዬ እንደነበረ ትረዳለህ፡፡ ታሪክ የማይረሳው ድንቅ ንግግር ከመሞታቸው በፊት ያደረጉ በእኛም በሌሎችም ሀገራት አሉ፡፡ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ስንመለስ ‘’ፍልስጤማውያንን እንድበቀል አንድ ጊዜ ብቻ አበርታኝ’’ ብሎ ጠላቶቹን ገድሎ የሞተውን ሶምሶንንም እናገኛለን፡፡ ሶምሶን ሲሞት የገደላቸው ሰዎች እጅግ ብዙ ነበሩ፡፡ ሮማውያን ወንጀለኞችን ሲሰቅሉ በጣም ለጆሮ የሚቀፍፍ ስድብ ከሟቾቹ አፍ ይወጣ እንደነበር ሲሴሮ ጽፎአል፡፡ የአንዳንዶቹ ስድብ ከማስጸየፉ ብዛት ምላሳቸው ተቆርጦ የሚሰቀሉም ነበሩ፡፡ ዐርብ ዕለት የተሰቀለው ናዝራዊ ግን የተናገረው ከአፉ የተሰማው የመጨረሻ ቃል የሮም ወታደሮችን ግራ ያጋባና ተሰምቶ የማይታወቅ ነበር፡፡ እርሱ ሁሉ በጠላትነት የተነሣበት ሳር ቅጠሉ የጠላው የሕማም ሰው ነበር፡፡ እንጨት መስቀል ሆኖ ተጫነው ፣ ብረት ሚስማር ሆኖ ጨከነበት ፣ አበቦች እሾህ ሆነው ወጉት ፣ ሰዎች እንደማያውቁት ከዱት ፣ ተማሪዎቹም ጥለውት ሸሹ፡፡ ይህ ሁሉ መከራ ወርዶበት ግን በዓለም ተሰምቶ የማያውቅ የጸሎት ቃል ከአፉ ፈሰሰ - የሚያደርጉትን አያውቁና ይቅር በላቸው፡፡ እርሱ እንደሶምሶን በሞቱ ሰዎችን አልገደለም:: በሞቱ ያስነሣቸው ግን ብዙ ነበሩ:: ሞቱ ለብዙዎች መነሣት ምክንያት የሆነው እርሱ የመጨረሻ ቃሉን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው በማለት ጀመረ:: ጌታ ሆይ የማደርገውን አላውቅምና እባክህን እኔንም ይቅር በለኝ፡፡ አዎን በኃጢአቴ ቸንክሬሃለሁ ፣ በበደሌም አቁስዬሃለሁ ነገር ግን የማደርገውን አላውቅምና ይቅር በለኝ፡፡ ባውቅህ ኖሮ የክብርን ጌታ እሰቅልህ ነበር? ጌታ ሆይ ባላውቅህ ነው፡፡ ያስከፋሁህ አይሁድ ሆኜ ነው ፤ ያደማሁህ ሮማዊ ሆኜ ነው፡፡ የማደርገውን አላውቅምና ይቅር በለኝ፡፡ ጌታ ‘የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው’ ሲል አይሁድ ከሥር ቆመው ‘ተአምርህን አሳይ ከመስቀሉ ውረድ’ ይላሉ፡፡ ለጠላቶቹ ከመጸለይ በላይ ፣ የሚጠሉትን ከመውደድ በላይ ፣ ምን ተአምር ያሳያችሁ? ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 25 2013 ዓ.ም. ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/ Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4 Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
Показати все...
Log in to Facebook

Log in to Facebook to start sharing and connecting with your friends, family and people you know.

✝✝"፤ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።"✟✟ (የዮሐንስ ራእይ 13: 9)✞✞: ❖ ‹‹ልጆቼ አታልቅሱ፤ ነገር ግን የሽማግሌውን የአባታችሁን ቃል ስሙ፤ መጀመሪያ እምነታችሁ በእግዚአብሔር ላይ ይሁን፤ በዚህ ዓለም እንደተያዙ እንደ ዓለም ሰዎች ስለ ልብስና ስለ ምግብ አሳብ አታብዙ፤ በየጊዜው ሁሉ መጸለይን አታቋርጡ፣ ለቤተ ክርስቲያን ሌትና ቀን አገልግሉ፤ እግዚአብሔር በሚወደው ገንዘብ ንጽሐ ሥጋንና ጾምን ውደዱ፤ ውዳሴ ከንቱም የሚቀረውንም የዚህን ዓለም ክብር አትውደዱት፤ እናንተስ የቀደሙትን አባቶች በመከራና በድካም ብዛት ከዓለም የወጡትን በመጋደላቸውም ክፉውን ሀሳብ ድል የነሡትን ምሰሏቸው፤ ፍለጋቸውንም ካልተከተላችሁ ልጆቻቸው አትባሉምና፤ በመከራቸው ካልመሰላችኋቸው በደስታቸው አትመስሏቸውም፤ በድካማቸውም ካልተባበራችሁ ወደ ቤታቸው አትገቡም፤ የቀደሙትን ቅዱሳን አባቶቻቸሁን መስላችሁ ኃጢአተኛ አባታችሁን እኔን ደግሞ ምሰሉ፤ ስለትኅርምቱም በመብል በመጠጥ ልባችሁ እንዳይከብድ፣ ሥጋ ከመብላትና ጠጅ ከመጠጣት ተጠበቁ፤ ለመመካትም በዓለማዊ ልብስ አታጊጡ፤ የመላእክት አስኬማ ከዓለማዊ ሥራ ጋር አይስማማምና፤ ዓለምንም በዓለም ላይ ያለውን ሁሉ አትውደዱ፤ ዓለሙም ፈቃዱም ሓላፊ ነውና፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዓለም ይኖራል፤ ልጆቼ ሆይ ትሩፋትን ሁሉ በችኮላ ሠርታችሁ በጎይቱን ሃይማኖታችሁን አስከትሏት፤ ለነፍሳችሁ እንጂ ለሆዳችሁ አትገዙ፤ ሁላችሁ ወንድማማች ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁም ተፋቀሩ፤ ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ፍቅር ኃጢአትን ያጠፋልና፤ የነፍስና የሥጋን ርኲሰት ያነጻልና፤ ይህንንም ብትጠብቁ በእውነት ልጆቼ ናችሁ፤ የሕይወትንም ፍሬ የምታፈሩ ትሆናላችሁ፤ ወደ እግዚአብሔር ፊት በክብር ትደርሳላችሁ…ልጆቼ ሆይ ሰላም ለእናንተ ይሁን› የአባታችን አቡነ ተክለሐይማኖት ኑዛዜ በረከት ረድኤታቸው ይደርብን!!!
Показати все...
ምክር ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የምንወደው ጓደኛችን ቢሞትብን ለቀናት ሐዘን እንቀመጣለን። ብር ቢጠፋብንም እንዲሁም እንቆጫለን። ዕለት ዕለት ሐጢአት ስንሠራ ግን ጥቂትስ እንኳ አናስብም ። መቼ ይሆን የምንነቃው? ልብስ የተሰጠን ከብርሃናዊ ልብሳችን ስለተራቆትን ነው /ዘፍ. 3፥20/። ታድያ በኃጢአታችን ምክንያት በተሰጠን ልብስ ልባችንን ከፍ ከፍ የምናደርገው ስለምንድ ነው? ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ንገሩኝ ከእኛ መካከል የሚኖርበትን ቤት በቆሸሸ ቁጥር የማያጸዳው ማነው?ታድያ የእግዚአብሔር ማደርያ የኾነው ሰውነታችንን በንስሐ መወልወያ የምናጸዳው መቼ ነው? ልጆቼ ንስሐ ግቡ እንጂ በኃጢአታችሁ ምክንያት በፍጹም ተስፋ አንዳትቆርጡ። ወዳጄ ሆይ! ማፈር የሚገባህ ኃጢአት ስትሰራ እንጂ ንስሐ ስትገባ አይደለም። ኃጢአት ሕመም ነው። ንስሐ ደግሞ መድኃኒቱ ነው። ከኃጢአት ቀጥሎ ህፍረት አለ ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ። ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን።                                            
Показати все...
ምክረ አጋንንት 🗝🗝🗝🗝🗝🗝🗝 * ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ። ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ። ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ። በዝሙት እንድትጠመድ አዛዝኤል የሚባል የአጋንንት ጭፍራ በሰውነትህ ተሰራጭቶ ጠዋት ማታ ከዝሙት ውጪ ደስታ ገንዘብ እርካታ እንደሌለ ይነግርሃል እንድትተኛ ጸራሞና ደራሞ የሚባሉ ጭፍሮቹን በዓይኖችህ ያሰለጥናል ቤተክርስቲያን እንዳትሔድ እንዳትጸልይ ተኛ ይሉሃል ያለድካም ያለፍላጎትህ መጽሐፍትን ስታነብ ትምህርት ስትማር እንቅልፍ እንቅልፍ ድካም ድካም እንዲሰማህ እንድታዛጋ ያደርግሃል ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ ላስቀድስ ትላለህ ፤ ተው ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ። ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል። ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ። አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ። በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት ትወድቃለህ። # በመጨረሻም_የተወሰነልህ_ግዜ_ያልቃል ። ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ ይወስዷታል። # ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል። # ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል! # ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል! # ልጣለው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል። # ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ ፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው ትገፋበታለህ። # ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ወደመዝናኛ ቤት መሔድ ይሆናል። በእነዚህ ሁሉ ስጋህ ሲመቸው ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል። መስገድ ያቅትሃል። መጾም ይከብድሃል። ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል። ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል። የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል። ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል። ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል። # ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር ያደርጋታል። # በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ ነበር። # ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ ያደርገዋል።እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች ወደ ሲዖል ትወረወራለች።
Показати все...
+++ ንጹሕ እጆች ግን ባዶ እጆች! +++ አንድ ሰዉ እጁን ወደ እግዚአብሔር አነሳና ፣ "ጌታ ሆይ! ተመልከት እጆቼ ንጹሖች ናቸዉ። አልሰረቁም ፤ አልገደሉም" አለ። እግዚአብሔርም ፣ "አዎ ልጄ እጆችኽ ንጹሖች ናቸዉ ምንም ኃጢአት አልሰሩም። ነገር ባዶ ናቸዉ። አልሰረቅህም ነገር ግን አልመፀወትክም። አልገደልክም ነገር ግን የተቸገረ አልረዳኽም" አለዉ። እናም እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልገዉ መጥፎ ነገር አለማድረጋችንን ብቻ ሳይሆን መልካም ነገር ማደረጋችንንም ይፈልጋል! © ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
Показати все...
✥✥✥✥ በዚህች ዓለም ውስጥ የማይለወጥ ምንም የለም " ✥✥✥ እግዚአብሔርን የምትወዱት ይልቁንም እግዚአብሔር የሚወዳችሁ ክርስቶሳውያን ይህን እናውቅ ዘንድ እላችኋለሁ ። በዚህች ዓለም ያለ ነገር ሁሉ መለወጡ አይቀርም ። ጤንነት በደዌ መለወጡ አይቀርም ፤ ሀብት በድህነት ፤ ክብር በውርደት ፤ ሹመት በሽረት ፥ ጥጋብ በረኀብ ፥ ሰላም በጦርነት ፥ ኃይል በድካም ፤ መግዛት በመገዛት ፥ ውበት በጉስቁልና ፥ ነጻት በባርነት ፥ አንድነት በብቸኝነት ፥ ዝና በኀፍረት ፥ ደስታ በኀዘን ይለወጣል ። ሕይወት በሞት ይለወጣል ። ሰዎች እነዚህን ጉዳዮች መዘንጋታቸው ሁለት ችግሮን ያመጡባቸዋል ። የመጀመሪያው እጅግ ከመቀናጣት የተነሣ ቸልተኞቾ ፥ ለመንፈሳዊነት ግድ የለሾች ፤ ለሥርዓተ ቤተክርስቲያን ደካሞች ፥ ጥጋበኞች ይሆናሉ ። እነዚህ ሰዎች ለፍላጎታቸው የሚስማማ እምነት በተነሣ ቁጥር ይኮበልላሉ ። ለሰውም የማያዝኑ አረመኔዎች ፥ ድኻ አስጨንቀው ቀምተው የሚከብሩ ፥ ሕዝብ ገድለው የሚሾሙ አውሬዎች ይሆናሉ ። ሁለተኛ ደግሞ እንዲህ አይነት ሰዎች ቁሳዊያን ናቸውና የዓለምን ከንቱነትን ያልተረዱ የዓለምን ግሣንግሥ መሠረት አድርገው የሚደሰቱ ስለሆኑ አንድ ነገር በጎደለ ቁጥር ጭንቀታሞች ናቸው ። ሳይነኳቸው ይደማሉ ፥ ሳይገድሏቸው ይሞታሉ ፥ እየተመሰገኑም ተሰደብን ይላሉ ። የዓለም ነገር ደስታነቱ ለዚያች ሰአት ብቻ ስለሆነ ቀጥሎ ደግሞ ሌላ ደስታ ያሻልና ዓለምን የሚወድ ሰው ሁል ጊዜ ብኩን ይሆናል ። ከቅዱሳን አንዱ እንዲህ አለ ። ይህቺን ዓለም የሚወድ ሰው የአዳኞችን ውሻ ይመስላል ። የአዳኞች ውሻ አድኖ እንስሳ ባይዝም ይደበደባል ። ቢይዝም ይደበደባል ። ቢይዝ የሚደበደበው የያዘውን እንስሳ በአዳኞች ስለሚፈለግ እንዳይበላው ነው ። ባይዝ መደብደቡ ለምን አልያዝክም ተብሎ ነው ። ይህቺን ዓለም የሚከተል ሰውም እንዲሁ ነው ። ባያገኝ በማጣቱ ያዝናል ፤ ቢያገኝ በመለየቱ በማለፉ ያዝናልና ። እንዲህም ስለሆነ በተሾምህ ጊዜ እንደምትሻር አስብና ቅን ፍረድ ። ባገኘህ ጊዜ እንደምትደኸይ አስበህ ሥጥ ፥ ንብረትህ ፈጥኖ ሳይሸሽህ አንተ ለድኾች በመስጠት ቅደመው ፥ በጤንነትህ ጊዜ ደዌ እንዳለ አውቀህ የታመመ ጠይቅ ካለህ ጊዜ ድኾችን የታመሙትን ለመጎብኘት ጊዜ ይኑርህ ፤ ዝና ባለህ ጊዜ የሚበልጡህ ዝነኞች ሲመጡ እንዳትዋረድ ሰዎችን አታዋርድ ። ኃይል ባጣህ ጊዜ ኃይለኞች እንዳያስጨንቁህ በኃይልህ ዘመን ሰው አትግፋ ። ደስ ሲልህ የኀዘን ቀን አለና ከተጨነቁት ጋር አብረህ እዘን ። ውበትህ የሚጎሰቁልበት ዘመን ይመጣልና ውበቴ ይታወቅልኝ አትበተል ፥ ነገ በሚገሰቁል ውበትህ ሰዎችን አሰናክለህ የዘለዓለም ጉስቁልና እንዳያስከትልብህ ተጠንቀቅ ። ይህ ዓለም ቁም ነገር አይምሰልህ ፤ ለመጣል ይስብሃል እንጅ ስትወድቅ የሚያነሣህ አይምሰልህ ። ስለዚህ ብላሽ የሆነን ዓለም አገኘሁ ብለህም ደስ አይበልህ አጣሁት ብለህም አትዘን ። ዓለምን መውደዴን በምን አረጋግጣለሁ ትለኝ እንደሆነ አንድን ነገር ፈልገኸው ስታጣው የምታዝን በመሆንህ ነው ። ዳግመኛም አግኝተኽ በማጣትህም ስትተክዝ ነው ። ዓለም ከንቱ ነው ካልክ መመሪያህ የጻድቁ ኢዮብ ሕይወት ይሆናል ። ስታገኝ እግዚአብሔር ሰጠ ስታጣም እግዚአብሔር ነሣ ትላለህ ማለት ነው ። ክርስቲያናዊ ሕይወትህ በማጣትና ማግኘት ላይ እንዳይመሠረት ተጠበቅ ። ሳገኝ እንዲህ አደርጋለሁ አትበል ፥ በሌለህ ነገር እግዚአብሔር አይፈርድብህምና ። ስለሌለኝ ነው መልካም ያልሆንኩት ብለህም አታመካኝ ። ድኽነት ከጽድቅ አያስቀርምና ። መንግሥተ ሰማያትን ሰብከው ያወረሱ አንዳች የሌላቸው ሐዋርያት ናቸውና ። ዓለም መለወጡ የማይቀር ነው ስንል በክፉ ብቻ አይደለም ። በመልካምም ነው እንጅ ። መልካሙ በክፉ እንዳለፈ ክፉውም በመልካም ማለፉ አይቀርም ። ሠለስቱ ደቂቅን ያከበሩ ባቢላውያን ማክበራቸውን ትተው በእሳት የወረወሩበት ቀን መጥቷል ። ከእሳቱ ደኅና ወጥተው ንጉሡ ራሱ እንደሰገደላቸውም ግን አትዘንጋ ። የፈርዖን ጭካኔ እንደነበረ የሙሴ ነጻነት መጥቶ የለምን ? ምን በዚህ እንደነቃለን ! የአምስት ሺው ዘመን የዲያብሎስ መንግሥት በክርስቶስ መስቀል ፈርሶ የለምን ! ምንም መከራ ቢደርስብን መከራው እንደሚያልፍ እንወቅ ፥ እስንሞት የማያልፍ ቢሆን እንኳን ስንሞት እናርፈዋለንና ለመንግሥቱ እንቸኩል ። ይህን በዐይነ መንፈስ ያየ ቅዱስ ይስሐቅ እንዲህ አለ ፦ " ኢተሃሊ ከመ ምንትኒ ዘውስተ ዓለም ዘኢይትወለጥ ከመዝ ሀሉ - በዚህ ዓለም ካለው ምንም ምን ቢሆን አይለወጥም አትበል ። ዓለም ኃላፊ ነው እያልክ እንዲህ ሆነህ ኑር እንጅ " ይቆየን ! የላይኛውን የሚያስብ ርቱዕ ልቡና ያድለን አባ ገብረ ኪዳን ሰኔ ፳ - ፳፻፲፪ ዓም
Показати все...
"ቃለ እግዚአብሔር ": ሰይጣን ራሳችንን ስንገዛና ከራሳችን ጋር ስንሆን ኃጢአታችንንም ስናስተውል ስለንሰሐም ስናስብ ይፈራል።በዚህ ጊዜ ከእርሱ ማምለጥ ይቻላል። በእናንተ ሳይፈረድባችሁ አስቀድማችሁ እናንተ በራሳችሁ ላይ ፍረዱ” ቅዱስ መቃርዮስ እንባህ ከመፍሰስ እንዳይቆም ከወደድህ በጸሎት ጽሙድ ሁን አንድም በተዘክሮ ጽሙድ ሁነህ ኑር። መከራ መጥቶብህ መከራውን ለማራቅ ከምትጸልየው ጸሎት አስቀድሞ ለሚገባ ንሰሀ ተዘጋጅ። እኛ ሀጢአታችንን ያስታወስን እንደሆነ እግዚአብሔር ይተዋቸዋል። እኛ ግን ኃጢአታችንን የዘነጋን እንደሆነ እግዚአብሔር ያስታውሰናል” ቅዱስ እንጦስ """""""""""""""""""" በንሰሀ ሕየወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደርና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም። አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ :::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች። አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ አንተ ሌሎችን የምትምር ከሆነ እግዚአብሔርም አንተን ይምርሃል። ነገር ግን አንተ እቁጡና ጨካኝ ሆነህ ሳለህ የእጅህን ዋጋ ብታገኝ እንዳታማርር። አቡነ ሺኖዳ የዋህ ሰው ሰለ እርሱ ሰዎች ይከላከሉለታል እንጂ እርሱ አይከላከልም። አቡነ ሺኖዳ ክርስቲያን በተፈጥሮው የማስተዋል የአርምሞ የጥንቃቄና የሰላም ሰው ነው። አንተ ካስፈለገህ ሁለት ጊዜ ከተጠየቅህ በመጠኑ ተናገር፣ መልስህም በጥንቃቄ እና በ’እውቀት ባጭሩ የሰዎችን አእምሮ የማያስጨንቅ ይሁን። እውነትን ከመስማት የበለጠ ለጆሮውች ጌጣጌጥ የላቸውንማ ሴቶች ለምድራዊ ጌጣጌጦች ጆሯቸውን አይብሱ፣ እውነትን ለመስማት የተበሱ ጆሮዎች ቅዱስ ነገርን መለኮታዊ ቃልን ያደምጣሉና። አንደበትህ በአርምሞ በዝምታ የተመላ ይሁን ልብህን በእርጋታ አአኑረው የሁሉም መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ፣ ለከንቱ ንግግር (ወሬ) ዘገምተኛ እና ሰነፍ ሁን፣ ነገር ግን ቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድህነት የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን። ማንኛውንም ነገር ለማውቅ የክፋት መርዝ በአምሮህ እንዳይሰራጭ ጉጉት አይደርብህ የመንፈስ ስጦታዎች ልዩ ልዩ እንደመሆናቸው መጠን እና አንዱ አገልጋይ ሁሉንም ገንዘብ ማድረግ ሰለሚችል በተሰጠው ጸጋ በማመስገን ቢቀመጥ መልካም ነው። ለመስበክ የተመረጠው ሰባኪ ወንጌልን ለመስበክ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይጠብቅ እንጂ የራሱን አይደለም ሰነፍ ሰው ሲስቅ ይጮሀል ድምጹንም ከፍ ከፍ ያደርጋል። የሚስት አክሊሏ ባሏ ነው፣ ፣የባልም ጋብቻው ለሁለቱም የጋብቻቸው አበባም አንድነታቸው ልጆቻቸው ናቸው። ይኸውም በመለኮታዊ አመሰራረት ከስጋ እርሻ የተገኘ ነው ። ድንቁርና በሃጢአት እንድንወድቅ ስለሚያደርግ እውነትንም በግልጽ የምናይበትን ችሎታን ስለማይሰጥ ጨለማ ነው። እውቀት ግን የድንቁርናን ጨለማ አስወግዶ እውቀትን ሰለሚያጎናጽፈን ብርሃን ነው። ልብህን በእርጋታ አኑረው፤የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር (ወሬ) ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን። ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድህነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን ። ታላቁ ባስልዮስ የቂሳሪያ ሊቀ ጳጳስ። ትህትና መድኅን ነው ከሰይጣን አሽክላ ያድንሃል። /አባ እንጦንስ/ ትህትና የሰው ዘመድ ነው። / አባ አሞን/ ትህትና የማይናድ ደልዳላ መሬት ነው። /አባአርሳንዮስ/ ትህትና ክርስቲያናዊ ምልክት ነው። /አባ መቃርስ/ ትህትና ከትሩፋት ሁሉ ይበልጣል። /አባ አሞን/ ትህትና መስቀል ነው። /አባ ታድራ/ ትህትና የሰው ሁሉ ጋሻ ጦር ነው። /አባ በሐይ/ ትህትና ግድግዳን የሚያስጌጥ የአፈር ወይዘሮ ነው።/አባ አጋቶን/ ትህትና የመንግስተ ሰማያት መመላለሻ በር ነው። /አባ ሚልኪ/ ትህትና ሕፀጽን የሚያስታውቅ መስታወት ነው። /አባጰርዬ/ ትህትና የነፍሳት ወደብ ነው። /አባ ዮሐንስ/ ትህትና የወንጌል ትእዘዝ መጀመሪያ ነው። /አባዮሐንስ ሐፂር/ ትህትና ወደ ንፁሐ ልቡና ሰገነት የሚወጡበት ዕፀሕይወት ናት።/አባመቃርስ/ የእግዚአብሔር ቸርነትና ምህረት ከሁላችንም ጋር ይሁን
Показати все...
" አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ።" (መጽሐፈ ምሳሌ 22: 28) አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ....... ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊን በሙሉ!!!!! የኦርቶዶክስ እየመሰላችሁ እዚህ group ውስጥ ያላችሁ የተዋሕዶ ልጆች አሁንም ደግመን እናሳስባለን ...... ይህ group የተሐድሶ መናፍቃን group ነው ።
Показати все...
እነዚህ መናፍቃን ተሐድሶች የዲያብሎስ መልክተኞች በስማችን በእኛ መገለጫ ይነግዱብናል። ተመለከቱ እነዚህ የዲያብሎስ ልጆች profile picture የድንግል ማርያም ሥዕል ነው። ስማቸሁም በድንግል ማርያም እና በቅዱሳን ሰይመዋሉ። ነገር ግን ነጣቂ ተኩላዎች ናቸው። አሁንም ደግመን እናሳስባለን የተዋሕዶ ልጆች ከነዚህ መናፍቃን እራሳችሁን ጠብቁ።
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.