cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Wolaita Soddo Christan students fellowship(wscsf)Gf

Рекламні дописи
385
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

እንጀራ ልንበላ አልተከተልንህም ሃብት ብልጥግና ወደ አንተ አልጠራንም ለምድር በረከት ታይቶ ለሚጠፋ መች ደምህ ፈሰሰ ለሚያልፍ ተስፋ የዘላለም ሕይወት ማግኘታችን ጉዳይ ሁሌም ብርቃችን ነው ከምን ጋር ሊተያይ ሕይወት ያካፈልከን ኢየሱስ አንተ ነህ ሌላ አላየንም በነፍሱ የጨከነ ግን ዛሬ ሲመጣ በየአደባባዩ ትኩረት የሚፈልግ የሚል እኔን እዩ አንተን አደብዝዞ ራሱን የሚያጐላ አባብሎ ወሰደን ሆነናል ተላላ አቤቱ ሕዝብህን መልሰን ሳንጠፋ ቀድመህ ድረስልን አቤቱ ልጆችህን አስበን ከድፍረት ከውድቀት ታደገን በጐ በሚመስል ሃሳብ እየተሳበ በመልካም ንግግር ሕዝብ ተሰበሰበ ዓመጸ ማይከለክል የረሳ ፍርድህን እራሳችንን እንዳናይ አደንዝዞ አሰረን በዘመን ፍጻሜ ጫፍ ላይ ቆመን ሳለን ልባችን እንዳያይ ምንው ተደለለ ዘይታችንን እንሙላ ጊዜው ሳይገባደድ ፈጥነን እንመለስ ከሄድንበት መንገድ አቤቱ ሕዝብህን መልሰን ሳንጠፋ ቀድመህ ድረስልን አቤቱ ልጆችህን አስበን ከድፍረት ከውድቀት ታደገን - መስከረም ጌቱ -
Показати все...
ከጥቂት ዓመታት በፊት በሱዳን የሚኖሩ የአግልግሎት አጋሮቻችን እርዳታን ጠየቁን።በምሥራቅ ሱዳን የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር አጠገብ የምትገኝ አሮማ የምትባል ከተማ በጋሽ ወንዝ ሙላት ምክንያት በጎርፍ ተጠለቅልቃ ነበር።ጎርፉም 7000 ያህል ቤቶችን አውድሞ ነበር።አጋሮቻችንም ገንዘብ አሰባስበን ብንረዳቸው ለአሮማ ሕዝቦች እንደሚያደርሱላቸውና ይህም መልካም ሥራቸው ለወንጌል በርን እንደሚከፍተላቸው ነገሩን።እኛም ይህንን ዜና በገንዘብ ለሚደግፉን አሜሪካውያን አጋሮቻችን አካፈልናቸው።ሁለት ወጣት እጮኛሞች ከተጠየቀው ገንዘብ አብዛኛውን ሰጡንና ለአሮማ ሕዝቦች በችግራቸው ልንደርስላቸው ቻልን።ከጥቂት ጊዜ በኋላ የእነዚህን ለጋስ ጥንዶች ታሪክ ሰማሁና ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር መረዳት ቻልኩ። እነዚህ ሰርገኞች በሱዳን ስለደረሰው የጎርፍ አደጋ የሰጠነውን መግለጫ ሲሰሙ ሊሞሸሩበት ያቀዱትን ድል ያለ ድግስ ቅልብጭ ባለችው ለወጡት።በሆቴል ቤት የመጋባት አሳባቸውንም ቀይረው በአንድ ግለሰብ ጓሮ ቤት አደረጉት።ብሎም ታዳሚ እንግዶቻቸው ለሰርጉ የሚሆነውን ምግብ በየቤታቸው አዘጋጅተው ይዘው እንዲመጡ አደረጉ።ለትልቅ ሰርግ ያሰቡትን ገንዘብ ወደ ሱዳን እንድንልከው ሰጡን።በዚህም ለብዙ የጎርፍ አደጋ ተጠቂዎች በረከት ሆኑ። እግዚአብሔርን መውደዳችን ሙሉ የሚሆነው እንደዚህ ባልንጀራችንን ስንወድ ነው።... ©ማርቆስ ዘመደብርሃን(ዶ/ር) ፤ልኡካን፤ገጽ 26-27 📚ከመጽሐፍት ማዕድ
Показати все...
🎁🍞DAILY BREAD🍞🎁 🎀ይቅርታ🎀          ማርቆስ 11፥20-26 ዓላማ-  አባታችን እግዚአብሔር ወደ ፊቱ በፀሎት ቀርበን የምንለውን ቃላችንን ብቻ ሳይሆን የምናድርገውን የዕለት ተዕለት የህይወት ምልልሳችንንም ያያል ያውቃልም። ይቅርታውን ፈልገን ወደ እርሱ ስንመጣ ሌላውን ይቅርታችንን ነፍገን ከሆነ እርሱም እንደ ቃሉ ይቅርታውን ይከለክለናል። ቁልፍ ጥቅስ - “ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።”   — ማርቆስ 11፥25 የፀሎት ርዕስ - እስቲ ወደ ህይወታችን እንመልከት። ይቅር ያላልናቸው ምንያህል ሰዎች አሉ? ስለዚህ እግዚአብሔር ያሳየንን ምህረትና ይቅርታ እኛም ለሌሎች እንድናሳይ ጸጋው እንዲረዳን እንፀልይ። TRUE LOVE❤️ ONE FAMILY🤗 STRONG FELLOWSHIP💪 ❤️የማርቆስ ወንጌል ጥናት❤️ #ታማኝ_የመንግስቱ_ምስክሮች #Faithful_Witnesses_of_the_Kingdom #DigitalEvangelismMedia @WolaitaSodoEvaSUE
Показати все...
ወደ ፊልጵስዩስ 2 14-15፤ በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤
Показати все...
12 በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።
Показати все...
🎁🍞DAILY BREAD🍞🎁 🎀ድንገትኛ አልነበረም!🎀          ማርቆስ 10፡32-34 ዓላማ- የክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ዛሬ ብዙ ሰዋች እንደሚሉት አጋጣሚ ወይም ድንገተኛ ወይም እውነት ያልሆነ ተረት አየደለም። ይሄ ሁሉ ገና ሳይፈጥር ክርስቶስ ምን ሊሆን እንዳለ ያቅ ነበርና። ቁልፍ ጥቅስ - " እንዲህም አላቸው፤ “ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለጸሐፍት ዐልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም የሞት ፍርድ ይፈርዱበታል፤ አሳልፈው ለአሕዛብ ይሰጡታል፤ ያፌዙበታል፤ ይተፉበታል፣ ይገርፉታል፣ ከዚያም ይገድሉታል፤ እርሱ ግን ከሦስት ቀን በኋላ ይነሣል።” — ማርቆስ 10:33-34 የፀሎት ርዕስ - እግዚአብሔር አቅዶና አስቦበት ሰለሰራው እኛን የማዳን ስራ እናመስግነው። TRUE LOVE❤️ ONE FAMILY🤗 STRONG FELLOWSHIP💪 ❤️የማርቆስ ወንጌል ጥናት❤️ #ታማኝ_የመንግስቱ_ምስክሮች #Faithful_Witnesses_of_the_Kingdom #DigitalEvangelismMedia @WolaitaSodoEvaSUE
Показати все...
የእግዚአብሔር መንግስት፡ የመንግስቱ ባህሪያት ክፍል 1 | ሮቤል ጨመዳ | መንግስትህ ትምጣ S1:E7 https://www.youtube.com/watch?v=QwtUrmMrUoo&ab_channel=EvaSUE
Показати все...
የእግዚአብሔር መንግስት፡ የመንግስቱ ባህሪያት ክፍል 1 | ሮቤል ጨመዳ | መንግስትህ ትምጣ S1:E7

መንግስትህ ትምጣ | Your Kingdom Come መንግስትህ ትምጣ በኢቫሱ ሚድያ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ሳምንታዊ የትምህርት ዝግጅት ነው። በዚህ ዝግጅት ላይ የሚቀርቡ ትምህርቶች እና ውይይቶች የኢቫሱ ተቀዳሚ አላማ የሆነው ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት ዙርያ ነው። በተለይም የእግዚአብሔር መንግስት ትርጉም፣ የየዕለት የአማኝ ኑሮን እንዴት እንደሚቃኝ እና ምሳሌነቶች ይዳሰሱበታል። ይህ ዝግጅት የበለጠ እግዚአብሔርን ለማውቅ፤ እግዚአብሔርን እና ባልንጀሮቻችንን የበለጠ ለመውደድ፤ ቃሉን ለመታዘዝ፤ እና ወደ ተግባራዊ ህይወት እንዲመራን የልብ መሻታችን ነው። የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ተማሪዎች እና ምሩቃን ማህበር - የኢቫሱ | EvaSUE የኢቫሱ | EvaSUE - ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝና ጌታ አድርገው ሊከተሉና ምስክሮቹ ሊሆኑ ራሳቸውን የሰጡ ተማሪዎች እና ምሩቃን ህብረት ነው። የኢቫሱ ተቀዳሚ ዓላማ ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት ነው። Don't forget to subscribe! YouTube:

https://youtube.com/c/EvaSUE

በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ያግኙን | Connect with us on our social media pages: Telegram:

https://t.me/EvaSUE58

Website:

https://www.evasue.net

TikTok: http://tiktok.com/@evasue58 Instagram:

https://www.instagram.com/evasue_58

#EvaSUE #YourKingdomCome #የእግዚአብሔርን_መንግስት #Godskingdom #KingdomofGod

🎁🍞DAILY BREAD🍞🎁 🎀ይሻልሃል...🎀          ማርቆስ 9፥14-32 ዓላማ -  ክርስቶስ ስለ ኃጢአት ሲያስተምር  ምን ያህል አደገኛ እና ሰውን ወደ እሳት ባህር መጣል እንደሚችል ተናግሯል። እኛም ይህንን አውቀን ከኃጢአት ልንርቅ ይገባናል። ቁልፍ ጥቅስ — “ዓይንህ ብታሰናክልህ አውጣት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነመ እሳት ከመጣል አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል።” — ማርቆስ 9፥47-48 የፀሎት ርዕስ - በህይወት ዘመናችን ሁሉ ከኃጢአት ሊያነጻን ደግሞም በቅድስና ሊያኖረን ወደሚችለው ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እና ከእርሱ ጋር መሆን እንዲሆንልን። በኃጢአት ላይ መጨከን የምንችልበትን ጸጋ እንዲሰጥን። TRUE LOVE❤️ ONE FAMILY🤗 STRONG FELLOWSHIP💪 ❤️የማርቆስ ወንጌል ጥናት❤️ #ታማኝ_የመንግስቱ_ምስክሮች #Faithful_Witnesses_of_the_Kingdom #DigitalEvangelismMedia @WolaitaSodoEvaSUE
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🌼🌼መልካም አዲስ ዓማት 2015 ዓ ም 🌼🌼 “አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ።” — መዝሙር 8፥9 “አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ።”   — መዝሙር 8፥9 #ታማኝ_የመንግስቱ_ምስክሮች https://www.facebook.com/104553912193905/posts/104571238 @WolaitaSodoEvaSUE
Показати все...
ጳጉሜ 1   📝 እግዚአብሔር መልካም ነው።   🔶 ስለ መልካምነቱ እናመስግን እግዚአብሄርን ለማመስገን ብዙ ምክኒያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እግዚአብሄርን ለማመስገን የሁሉም ሰው የጋራ ምክኒያት የሆነው አንድ ምክኒያት ነው፡፡ ሰው ሌላ ምክኒያት ቢያጣ እንኳን በዚህ ምክኒያት እግዚአብሄርን ሊያመሰግን ይገባዋል፡፡ ሰው ምክኒያት ቢያጣ እንኳን ይህ ምክኒያት እግዚአብሄርን ለማመስገን በቂ ነው፡፡ መፅሃፍም ቅዱስም ይህን ምክኒያት እግዚአብሄርን ለማመስገን ምክኒያት አድርጎ ደጋግሞ ፅፎታል፡፡ እግዚአብሄር መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁለንተናው መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄር አይለወጥም ሁልጊዜም መልካም ነው፡፡ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ። በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። ያዕቆብ 1፡16-17 የመልካምነት ትርጉሙ ቢያከራክር እንኳን ለመልስ እግዚአብሄርን ማየት በቂ ነው፡፡ እግዚአብሄር የመልካምነት ማጣቀሻ (Refrence) ነው፡፡ ሰው በሚያነበው መፅሃፍ ላይ ያለን ቃል ትርጉም ባይረዳ ማጣቀሻን ይፈልግና የቃሉን ትርጉም ያያል፡፡ እንደዚሁ የመልካምነት ትርጉሙ ቢያጠራጥር እግዚአብሄር ጋር መልሱ አይታጣም፡፡ እግዚአብሄር መልካም ብቻ ሳይሆን የመልካምነትም ደረጃ መዳቢ ነው፡፡ እሱ መልካም ያለው መልካም ነው እርሱ መልካም አይደለም ያለው መልካም አይደለም፡፡ ስለ መልካምነት የመጨረሻው ወሳኝ አካል እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚያርመው የለም፡፡ 👇👇👇👇👇👇👇👇 #ታማኝ_የመንግስቱ_ምስክሮች #Faithful_Witnesses_of_the_Kingdom #DigitalEvangelismMedia @WolaitaSodoEvaSUE
Показати все...