cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

Рекламні дописи
6 619
Підписники
+224 години
+267 днів
+2230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Repost from Tofik Bahiru
ኑ እንሰደድ! (ክፍል ሁለት) ** …ከክፉ ንግግር ወደ መልካም ቃል! ** ንግግራችን፣ ቃላቶቻችን፣ ፅሁፎቻችን… የአላህ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ራሳችንን እንድንገልፅባቸው፣ እንድንማማርባቸው፣ ህይወታችንን እንድናቀናባቸው የተሰጡን ስጦታዎች ናቸው፡፡ አላህ ህግ አለው። ስጦታ ከሰጠ እንዲመሰገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሰጠን ፀጋዎች ላይ ትዕዛዛትና ክልክሎችን ደንግጓል፡፡ ልሳንና ብዕር ሰጥቶን ሐቅን እንድንበይንበት ስህተትን እንድናጋልጥበት አዞናል፡፡ ፀያፍ ቃላት፣ ሃሜት፣ ስድብ እና ሌሎችንም እንድንርቅ አስጠንቅቆናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- وَقُل لِّعِبَادِي يَقُولُوا الَّتِي هِيَ أَحْسَنُ إِنَّ الشَّيْطَانَ يَنزَغُ بَيْنَهُمْ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلْإِنسَانِ عَدُوًّا مُّبِينًا ‹‹ለባሮቼም በላቸው፡- ያችን እርሷ እጅግ መልካም የኾነችውን (ቃል) ይናገሩ፡፡ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና፡፡ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና፡፡›› መልካም ንግግር እንድንናገርና ክፉን እንድንርቅ የታዘዝነው ሰይጣን በመሀላችን ያለውን ግንኙነት እንዳያበላሽ ነው እየተባልን ነው፡፡ በክፉ ቃል ውስጥ ሰይጣን ብዙ እድሎች ይከፈቱለታል፡፡ ልቦችን ማሻከር እና ማጋጨት የሚችልበት አጋጣሚ ያገኛል፡፡ ንግግሮቻችን ጥሩ ወይም በጣም ጥሩ ይሆናሉ፡፡ ወይም መጥፎና እጅግ በጣም መጥፎ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ወይም በመካከል ያሉ የሚፈቀዱ -ጥሩም መጥፎም የማይባሉ- ንግግሮችም አሉ፡፡ አላህ በዚህች አንቀፅ ያዘዘን እጅግ መልካም የሆነችዋን ንግግር ነው፡፡ ጥሩውን ሳይሆን እጅግ በጣም ጥሩ የሆነውን ቃል እንድንናገር መከረን፡፡… ** ይህንን ያዙልኝና ወደ ተጨባጫችን ተመልሰን ራሳችንን እንገምግም፡፡ ብዙዎቻችን የምንናገረውም ሆነ የምንፅፈው ፀያፍ ወይም እጅግ በጣም ፀያፍ ንግግር ነው፡፡… አንዳንዴም የሚፈቀዱ -ጥሩም መጥፎም የማይባሉ ንግግሮች አሉን፡፡ እጅግ በጣም ጥቂት ንግግሮቻችን እርከናቸው ከፍ ብሎ መልካም ንግግሮች ይሆናሉ፡፡ ነገርግን… መልካም ንግግሮች ብቻቸውን የሰይጣንን ተንኮል አይከላከሉም፡፡ እኛ የታዘዝነው እጅግ መልካም የሆነውን እንድንናገር ነው፡፡ እጅግ በጣም መልካም ቃል ብቻ ነው ከሰይጣን ማበላሸትና ክፋት የሚጠብቀን! ** የኔ አጀንዳ… ** ሶሺያል ሚዲያ ፀጋ ነው፡፡ ታላቅ የአላህ ስጦታ፡፡ ይኸውም ይህንን ስጦታ በአግባቡ ለሚጠቀሙበት ሰዎች ነው፡፡ ነገርግን በላእ ነው ፈተና፤ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት፡፡ አላህ በምላሳችንም ሆነ መረጃን ወደ ሁለተኛ ወገን ማስተላለፍ በምንችልባቸው ማናቸውም ሚዲያዎች ላይ ያዘዘን ታላቅ ነገር አለ፡፡ ወደርሱ ሰዎችን መጣራት፣ በበጎ ነገሮች ማዘዝና ከክፉ ነገሮች መከልከል፡፡ ሰዎችን ማስታረቅና ማቀራረብ፡፡ በተቅዋና በመልካም ነገሮች ዙርያ መወያየት፡፡… አላህ በሱረቱል—ዒምራን ላይ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡›› ሱረቱን—ኒሳእ ላይም እንዲህ ብሏል:— ‹‹ከውይይታቸው በምጽዋት ወይም በበጎ ሥራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውስጥ ደግ ነገር የለበትም፡፡ ይኸንንም (የተባለውን) የአላህን ውዴታ ለመፈለግ የሚሠራ ሰው ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን፡፡›› ሱረቱል—ሙጃደላ ላይም:— ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተንሾካሾካችሁ ጊዜ በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ፣ መልክተኛውንም በመቃወም አትንሾካሾኩ፡፡ ግን በበጎ ሥራና አላህን በመፍራት ተወያዩ፡፡ ያንንም ወደእርሱ የምትሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ፡፡›› ይላል። እነዚህ አንቀጾች በድምራቸው ሰዎች ሲናገሩ እጅግ መልካም የሆነውን ብቻ እንዲናገሩ ሌላውን ንግግር እንዲተዉ ያዝዛሉ፡፡… ** ልሳንና መሰሎቹ አደገኛ ጣጣ ያመጣሉ፡፡ በዝምታ እንጂ ከነዚህ አደጋዎች አንድንም፡፡ ለዚህ ነው ሐዲሶቹ ዝምታን የሚያበረታቱት፡፡ ‹‹መን ሶመተ ነጃ፡፡›› (ዝም ያለ ዳነ) ፣ ‹‹ዝምታ ጥበብ ነው፤ ሰሪዎቹ ግን ጥቂት ናቸው፡፡››… ሶሐቢዩ ከሰለመ በኋላ ‹‹ምንን ልጠንቀቅ?›› ሲላቸው -የአላህ መልእክተኛ [ﷺ]- ‹‹የተከበረው ምላሳቸውን እየጠቆሙ "ይህንን!"›› አሉት፡፡…፣ ‹‹መዳን እንዴት ይገኛል?›› ያላቸውን ሶሐባ ‹‹ምላስህን ያዝ፣ ቤትህ ይስፋህ (ከፍጡር አትከጅል)፣ ለኃጢኣትህ አልቅስ፡፡›› ብለው መለሱለት፡፡…፣ እሳት የሚያስገቡ ዋና ነገሮች ምንድን እንደሆኑ ሲጠየቁ ‹‹አፍና ብልት፡፡›› ብለውም መልሰዋል፡፡… አዎን! ዝሙትና የምላስ ጣጣ ሰዎችን በብዛት ጀሀነም የሚያስወረውሩ ኃጢያቶች ናቸው! ‹‹አብዝሃኛው የሰው ልጅ ኃጢኣት በምላሱ የመጣ ነው፡፡›› ይሉናል የአላህ መልእክተኛ (ﷺ)፡፡ በሌላ ሐዲስ ‹‹ምላሱን የጠበቀ ነውሩን አላህ ይደብቅለታል፡፡ ቁጣውን የተቆጣጠረ አላህ ከቅጣቱ ይጠብቀዋል፡፡ አላህን ምህረት የጠየቀ አላህ ምህረቱን ይቀበለዋል፡፡›› ብለዋል። ** ከሀሜትና ሒጃብን ከመጣል ወይም ወንድ የወርቅ ጌጥ ከመጠቀሙ አላህ ዘንድ የትኛው ከባድ ኃጢያት ነው?!... ሀሜትን ስለለመድነው ቀሎናልና ሁለተኛውንና ሦስተኛውን እንደምንጠየፍ አውቃለሁ፡፡ ነገርግን ሐቁ ሀሜት ከብዙ ከምንጠየፋቸው ኃጢያቶች በላይ አላህ ዘንድ የተጠላ ነው፡፡… ስድብ ፋሲቅ ያደርጋል፡፡ ተሳዳቢ ለምስክርነት ብቁ አይሆንም፡፡ "ሙስሊም ተራጋሚም ተሳዳቢም አይደለም!"፣ ‹‹ሙስሊምን መስደብ ፍስቀት ነው፡፡ እርሱን መጋደል ደግሞ ኩፍር ነው፡፡›› ይላሉ ታላቁ ሰው (ﷺ)፡፡ ነገርግን ሙስሊምን መሳደብ አሁን አሁን ዝንብን እሽ ብሎ ከአፍንጫ ላይ ከማባረር በላይ የቀለለ ተግባር ሆኗል፡፡ ነገር ማሳበቅ/ነሚማ ከባድ ኃጢኣት ነው። እዚህ ማህበራዊው ሚዲያ ላይ በስፋት የማየው ችግር ነው፤ ነሚማ። እንዴት መሰላችሁ!?… ሰዎች የሃሳብ ፀብ ይኖራቸውና ይጣላሉ። ያኔም ነገሩ እንዳይበርድ የሚያፋፍሙ ሰዎች ታውቃላችሁ!?… የሰዎች ፀብ የሚማርካቸው?!… ለስድድባቸው ላይክና ሼር በማድረግ የሚያጋግሉ!?… እነዚህ ነማሞች ናቸው። ሙስሊሞች ሲጣሉ ደስ የሚላቸው። እንደኔ ትዝብት ከሆነ በብዛት ሙስሊሞች የሚመሰጡበት አጀንዳ ፀብና ጥል ነው። በዳዒዎች ዙርያ የሚሰበሰቡ ሰዎችን ስብሰባቸው አለቃቸውን አግዝፈው ተቃራኒውን ለማራከስ ነው። በንግግር ራስን ማዳነቅ/ ማሞካሸት በፌስቡክ ቢሆንም አይፈቀድም። "ነፍሳችሁን አታወድሱ፤ እርሱ የተጠነቀቀውን ይበልጥ ያውቃል።" ይለናል፤ ረቡል—ዐለሚን። ፎቶን ለጥፎ ለአላፊ አግዳሚው "ቴንኪው!" እያሉ መኖር እንዴት ያስጠላል። በተለይ ሴቶች እናንተን ነው!… እንደኔ ሴትነት ትጋት፣ ጥረት፣ እዝነት፣ ፍቅር፣ ሰላም… እንጂ ቅርፅ ወይም ሥጋ አይደለም። ፍላጎታችሁን ከፍ ባለ ነገር ላይ አንጠልጥሉት። የእውቀትና የስብዕና ግንባታ ላይ አስተዋፅኦ አበርክቱ። -ማንበብ እንደማንወድ አውቃለሁና- እንዳላረዝምባችሁ ፌስቡክም ሆነ ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች ኦፖርቹኒቲ ይዘው እንደመጡ ሁሉ ማንነታችንን፣ የደረስንበትን የስነምግባር ዝቅጠት… አጋልጠዋል፡፡ እናም እባካችን… እባካችን… እባካችን… እጅግ በጣም መልካም ንግግሮች ሞልተው እያለ ለምን በሰፋሲፍ/ቂላቂል ነገር ጊዜ እናቃጥላለን!... መስጂድ ያለው አላህ እዚህም አለና ንግግራችንን እንመርምረው! ኑ ከክፉ ንግግር እጅግ በጣም መልካም ወደ ሆኑ ንግግሮች እንሰደድ! https://t.me/fiqshafiyamh
Показати все...
15
Repost from Tofik Bahiru
በዐሹራ ቀን ራስን እና ቤተሰብን ማስፋፋት ሱና ነው። ይህ አራቱ መዝሀቦች የተስማሙበት ሃሳብ ነው። ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «በዐሹራ ቀን ለራሱ እና ለቤተሰቡ ያስፋፋ ሰው አላህ በቀረው አመቱ ያስፋፋለታል።» ኢብኑ ዐብዲል‐በር 'አል‐ኢስቲዝካር' ላይ ሰይዲና ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህን [ረዲየላሁ ዐንሁ] በመጥቀስ ዘግበውታል። ጦበራኒይ፣ በይሀቂይ፣ ኢብኑ አቢድ‐ዱንያ ከአቡ ሰዒድ አል‐ኹድሪይ ዘግበውታል። ሰይዲና ጃቢር [ረዲየላሁ ዐንሁ] «ዐርባ አመታት ሞክሬዋለሁ።» ብለዋል። ሱፍያን ኢብኑ ዑየይና [ረዲየላሁ ዐንሁ] በበኩላቸው: ‐ «ሃምሳ ወይም ስድሳ አመታት ሞክረነው መልካምን ነገር እንጂ አላየንም።» በማለት በሐዲሱ መልእክት እንደተጠቀሙ ይናገራሉ። ከሻፊዒዮቹ ሱለይማን አል‐ጀመል "ፈትሑል‐ወሃብ" በተሰኘው የሸይኹል‐ኢስላም ዘከሪያ አል‐አንሷሪይ መፅሀፍ ላይ በሰሩት ማብራሪያቸው (ሓሺያ) ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐ «በእለተ ዐሹራ ለቤተሰብ እና ለዘመድ ማስፋት ለድኾችና ምስኪኖች ሶደቃ ማድረግ ይወደዳል። ነገርግን ራስን ከአቅም በላይ ማስጨነቅ አያስፈልግም። የሚያስፋፋበት ነገር ካጣ ጠባዩን ያስፋላቸው። ከበደልም ይታቀብ።» 🔺 ማስፋፋት: ‐ በሚበሉ እና በሚጠጡ ነገሮች ላይ ከሌላው ጊዜ የተሻለ ነገር ማድረግ ማለት ነው። አላህ ያግራልን! http://t.me/fiqshafiyamh
Показати все...
35👍 9
Repost from Tofik Bahiru
ከዓሹራእ ጾም ጋር የተያያዙ ዐስር ህግጋት: ‐ ❶ የዓሹራ ጾም ያለፈውን ዓመት ኃጢኣት ያስምራል። ይህ ሲባል ተውበት የሚያሻቸውን ከባባድ ኃጢኣት ሳይሆን ቀላል (ሶጛኢር) ኃጢኣቶችን ነው። ❷ ዓሹራን መጾም የተወደደበት ምክንያት አላህ ነቢዩ ሙሳን (ዐለይሂስ‐ሰላም) እና ህዝባቸውን ከፊርዐውን ያዳነበት ቀን መሆኑን በማሰብ አላህን ማመስገን ነው። ❸ የዓሹራ ጾም ደረጃዎች ሦስት ናቸው። በላጩ አስቀድሞ አንድ ቀን ከበስተኋላውም አንድ ቀን በድምሩ ሦስት ቀን መጾም ነው። ሁለተኛው ከበስተፊቱ ወይም አንድ ቀን ከበስተኋላው መጾም ነው። በድምሩ ሁለት ቀን መጾም። ሦስተኛው ሁኔታ እራሱን የዓሹራን ቀን (ሙሐረም 10ን) መጾም ናቸው። ❹ ከበስተፊቱ ወይም/እና ከበስተኋላው አንድ ቀን መጾም የተወደደበት ምክንያት ከአይሁዶች ለመለየት ነው። እነርሱ የዓሹራን ቀን ብቻ ነው የሚጾሙት። ❺ በዓሹራ ቀን ከጾም ውጪ ከሌሎች የዓመቱ ቀናት በተለየ ሁኔታ የተደነገገ ምንም ዓይነት ዒባዳ የለም። ነገርግን ቤተሰብን በሚበላና በሚጠጣ ነገር ማስፋፋት (ማንበሻበሽ) እንደሚወደድ የሚገልፅ ሐዲስ ተዘግቧል። አብዝሃኞቹ ልሂቃንም በሐዲሱ ሠርተዋል። ከዚያ ውጪ ለእለቱ መታጠብ፣ ሽቶ መቀባባት፣ መኳል… ተወዳጅ ነው የሚሉ የቅጥፈት (መውዱዕ) ሐዲሶች ተዘግበዋል። መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ❻ ከረመዳን ወር በኋላ ለጾም የተወደዱ ወራት አሽሁሩል‐ሑሩም (የተከበሩት ወራት) ናቸው። ከነርሱ ደግሞ በላጩ ሙሐረም ነው። ከዚያም ረጀብ፣ ዙል‐ሒጃ፣ ዙል‐ቀዕዳ በተከታታይ ለጾም የተመረጡ ወራት ናቸው። ከአሽሁሩል‐ሑሩም ቀጥሎ ሸዕባን ምርጥ የጾም ወር ነው። ❼ በዓሹራ ቀን ለረመዳን ቀዷ ነይቶ የጾመ ሰው የሁለቱንም ጾሞች ምንዳ ያገኛል። ፈርዱ ከጫንቃው ላይ ይነሳል፤ ሱና የሆነውን የዓሹራን ምንዳ ያገኛል። ❽ የዓሹራን ቀን ከእለቱ የዙህር ወቅት በፊት ባለው ጊዜ ነይቶ መጾም ይቻላል። ይኸውም እንደማንኛውም ሱና ጾም ማለት ነው። በሌሊት ነይቶ ማደር ግዴታ አይደለም። እንደሚታወቀው ፈርድ ጾሞች ግን ለነገ ጾም ከመግሪብ እስከ ፈጅር ባለው ካልተነየተ አይሆንም። ❾ የዓሹራ ጾም ያመለጠው ሰው ቀዷ ቢያወጣው ይወደዳል። የሻፊዒያ መዝሀብ ዐሊሞች መደበኛ ጾሞችን ቀዷ ማውጣት እንደሚወደድ በግልፅ ፅፈዋል። ❿ በመሰረቱ ሴት ባሏ በሀገር እያለ ያለፍቃዱ መጾም አትችልም። ነገርግን በተለይ እንደ ዓሹራ በዓመት አንዴ የሚዘዋወሩ ቀናትን ለመጾም አለመከልከሉ ብቻ ይበቃታል። ስለዚህ በግልፅ መፍቀዱ ወይም ማስፈቀድ አያስፈልጋትም። አላሁ አዕለም!
Показати все...
👍 6 4
Repost from Tofik Bahiru
ከዚህ ቀደም ስለ ዐሹራ የፃፍኳትን መቀስቀሻ ሚንበር ቲቪዎች እንዲህ አሳምረው ሰርተዋታል። አመሰግናለሁ!
Показати все...
Ashura.pdf4.11 KB
ከአቡሁረይራ [ረዲየላሁ ዐንሁ] የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «በጥፋት ውስጥ ከሚያሰምጡ ሰባት ኃጢኣቶችን ራቁ!» ሰዎች «የአላህ መልክተኛ ሆይ! የትኞቹ ናቸው?» በማለት ጠየቁ። እንዲህ መለሱ: ‐ 1] በአላህ ማጋራት፤ 2] ድግምት፤ 3] አላህ እርም ያደረገው ነፍስን መግደል፤ 4] አራጣ መብላት፤ 5] የየቲምን ገንዘብ መብላት፤ 6] ጦር በተፋፋመበት መሸሽ፤ 7] ጭምት፣ ከዝሙት የዘነጉ ምእመናትን በዝሙት ማጠልሸት [መስደብ]።» ቡኻሪ ዘግበውታል።
Показати все...
48👍 20
ኑ እንሰደድ! ======== (ክፍል አንድ) ======== አሁን ያለንበት ወር እንደ ሂጅራ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ነው። ካሌንደሩ የተመሰረተው ተወዳጃችን (ﷺ) ከመካ ወደ መዲና ካደረጉት ስደት ጋር ተያይዞ ነው። በእርግጥ ስደቱ የተከሰተው ከዚህ ወር ቀድሞ በወርሃ ዙልሒጃ ነው።… : መዲና ከመካ ከአራት መቶ ኪሎሜትር በላይ ርቃ የምትገኝ ስፍራ ናት። ከአዲስ አበባ እስከ ደሴ ወይም ከዚያም ዘልቆ ማለት ነው። ጉዞው ዘመናዊ መጓጓዣዎች ባሉበት ባለንበት ዘመን እንኳን ጉዞው አድካሚ ነው። ነገርግን በሂጅራ ጉዟቸው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እና ባልደረቦቻቸው ‐በእኔ እምነት‐ ለክፉ ነገር ያላቸውን ጥላቻ ለመግለፅና መልካምን ነገር ማፍቀራቸውን ለመበየን ዋጋውን ሁሉ ከፍለዋል።… : በዚህ ታላቅ ክስተት ዙርያ የበለጠ መረጃ ካሻችሁ ሌሎች ስፍራዎች ላይ ታገኟቸዋላችሁ። የጊዜው አጀንዳዬ አይደለም።… ውስጤ ያለውን ሃሳብ ግን አንድ ሁለት ልበላችሁ።… ▼ ▼ ▼ ▼ ▼ ▼ የሂጅራ ጽንሰ ሃሳብ ክፉን መጥላት ነው። ክፉን መጥላት ነፍስያን ከመጥላት ይጀምራል። ሰይጣንም ክፉ ነው፤ እርሱን መጥላትና ከርሱ መንገድ መራቅ ሂጅራ ነው።… ክፉ ጓደኛን መራቅ፣ ከክፉ ስፍራዎች መራቅ፣ መጥፎ ስነምግባርን መራቅ… ሁሉም ሂጅራ ነው።… : ኢብኑል—ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ:— "ሂጅራ አላህ የሚጠላውን ነገር መሸሽን ያካትታል። አላህ የሚወዳቸውን ነገሮች መስራትንም ያጠቃልላል። የመሰረቱት ከአንጀት መውደድ እና አምርሮ መጥላት በአንድነት ተደምረው ሂጅራን ፈጥረዋል። ከአንድ ነገር ተሰዶ ወደሌላ የሚሰደድ የተሰደደበትን ነገር ጠልቶ ተሰዶ የሚሄድበትን ወድዶ ነው። ስለዚህ ሰውየውም የሰይጣን፣ የስሜትና የነፍስ ጥሪን ጠልቶ ወደ ኢማን ጥሪ ከተሰደደ አላህ ያዘዘውን ስደት ፈፀመ ማለት ነው። ይህ ሂጅራ ሳይቋረጥ እስከ ህይወት ከዘለቀ ይህ ሰው በስደቱ ላይ እንዳለ ሞተ ማለት ነው።" : የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) "ሙስሊም ሙስሊሞች ከምላሱና ከእጁ ተንኮል ሰላም ያደረገ ሰው ነው። ሙሃጂር [ስደተኛ] ማለት አላህ ከከለከለው ነገር የተሰደደ ሰው ነው።" : በዚህ አካሄድ ሁላችንም መሰደድ አለብን ማለት ነው።… ስደት ክፋትን ከመጥላት ይጀምራል። አላህ ሲታመፅ መጥላት፣ በልብ መጠየፍ ሰደት ነው።… ጧት ከቤት ወጥተን ማታ እስከምንመለስ ድረስ ይህንን ስደት መሰደድ ግዴታችን ነው።… : ክፋት የተለመደ መሆኑ ተቀባይነት አያስገኝለትም። ለምሳሌ:— ዝሙት ስለበዛ ኒካሕ አይሆንም። ኸምር ህዝብ ስለተዘፈቀበት ወተት አይሆንም። ኩራት፣ ልታይ ባይነት፣ በልብስና በገንዘብ መወዳደር ፋሽን ወይም ስታይል በሚል ስያሜው ስለመጣ ርኩስነቱን አይገፈፍም።… ክፋትን አለመጥላት ኃጢኣት ነው።… : የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ:— "ወደፊት ፈተና ይመጣል። ከርሷ የራቀው የኃጢኣቱ ተካፋይ ነው። በቅርቧ የሆነው ደግሞ ነፃ ሰው ነው።" በአካል ቢርቅም ልቡ ክፉን ያልተጠየፈ ሰው የሐጢኣት ተካፋይ ነው። በአካል ቀርቦ ኃጢኣቱን የጠላ ግን ንፁህ ነው። : "ክፉን ነገር ያየ በእጁ ይከልክል። ካልቻለ በምላሱ። ያልቻለ በቀልቡ ይጥላ። ከዚህ ያነሰ ኢማን የለውም!" ነው ያሉት ነብያችን (ﷺ)። ▼ ▼ ▼ ▼ ▼ ▼ ስለዚህ ውዶቼ ሥራ እንጀምር። ለምን ከነፍስያችን አንሰደድም!?… ለምን ከክፉ ጠባይዋ አንከለክላትም!?… ቅጥ ካጣው ቀምጣላና ትርፍ ስሜቷስ ለምን አናቅባትም?!… ሐሰኑል በስሪይ አደንዲህ ይላሉ:— "የአደም ልጅ ባርያነው። ነፍሱን የተቆጣጠረ ጊዜ ንጉስ ይሆናል!" እውነት ነው! የሰው ልጅ ነፃ መሆን የሚችል ፍጡር አይደለም። ባርነቱ ተፈጥሮኣዊ ነው። ለአንዱ አላህ ባርያ ካልሆነ ለብዙ የነፍስያ ፍላጎቶቹ፣ ከዚያም የነፍሱን ፍላጎት በእጃቸው ላደረጉ ፍጡራን ተገዥ/ባርያ ይሆናል።… እና ምን ለማለት ነው?… ከክፉ ነገር ነፍሳችንን ተይ ማለት እንችላለን?… ካልቻልን የነፍሳችን ባርያ ነን ማለት ነው። ነፍሳችንን በአላህ ድንጋጌ ላይ ማስገደድ እንችላለን?… ካልቻልን ከነፍሳችን ተሰደን ወደ አላህ አልደረስንም ማለት ነው። ትንሿን አካላዊ ስሜት ከአኺራ ምንዳ ካስቀደምን አሁንም ነፍሳችን ጋር ነን ማለት ነው። ፡ ስለዚህ ለምን ወደ አላህ አንሰደድም?! ሂጅራችንን ከዚህ አንጀምር።… ጧት ላይ የፈጅርን አዛን ስንሰማ ከፍራሻችን ከመሰደድ እንጀምር። አዎን!… "አሶላቱ ኸይሩን ሚነንነውም" ውድ ንግግር ነው። ከዚህ ንግግር በኋላ ፍራሽህን ጠልተህ ወደ ውዱ ሚሕራብ ከገባህ አንተ ስደት ጀምረሃል። ሙሃጂር ነህ ማለት ነው። ነፍስህ በአካልህ ውስጥ እስካለ ድረስ ይህን ስደት ማድረግ ዋጂብህ ነው። በክራንቻህ ነክሰህ ያዘው። ኑ እንሰደድ!
Показати все...
45👍 18
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከተፈቃሪያችን [ﷺ] ጋር የተሰጠን ትልቁ የአላህ ፀጋ ከርሳቸው ጋር የተፈቀደልን ቅርበት ነው። ሶለዋት እና ሰላምታ ስናቀርብላቸው ይደርሳቸዋል። እርሳቸው ናፍቀናቸው አንብተዋል። እኛ የርሳቸው እጣ እርሳቸውም የኛ እድል እንደሆኑ ነግረውናል። የህይወት ውሏቸው፣ የአካል ገፅታቸው እና የቤተሰብ ግንኙነታቸው ሳይቀር ተሰንዶ ተዘግቦልናል። ከህይወታቸው ገፅታ እኛ ዘንድ ሳይደርስ ተዳፍኖ የቀረ የለም! ስለዚህ ፍቅር ያለው ወዳጃቸው ከእቅፋቸው ሳይወጣ፣ ተዝካራቸው ከህይወት ማእዱ ሳይርቅ ይመላለስበታል። እነሆ ዛሬ ዝክረ ሂጅራቸው ድምቀታችን ይሆን ዘንድ አላህ አድርሶናል! አልሐምዱሊላህ! እናም አደራ የምላችሁ!… ስለ ሂጅራቸው ለልጆቻቸን እንንገር። እለቱን ከታሪክ ዐውዱ ጋር አቆራኝተን ደማቅ ወጋችን እናድርገው። የመድረሳ ባለቤቶች፣ የመስጂድ አስተዳዳሪዎች፣ ዳዒዎች፣ የረሱልን ፍቅር በትውልድ ልብ ውስጥ መዝራት የሚሻ ሁሉ ዓመቱን ሁሉ ከህይወታቸው ክስተት እየቀዳ ይጠጣ። ለሌላውም ያጋራ። ከህይወት ቅኝታቸው የሚገኘውን አስተምህሮና ለዛ ይቋደስ! እንኳን ለ1446 ኛው ዓመተ ሂጅራ አደረሳችሁ! የከርሞ ሰው ይበለን!
Показати все...
54👍 9
የምእመናን እናት ዓኢሻ [ረዲየላሁ ዐንሃ]: – «ነቢዩ ሰአወ ሐላዋ እና ማር ይወዱ ነበር።» ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል። : ከሐዲሱ የምንማረው: ‐ ‐ ሚስት ባሏ ስለሚወደው ነገር በትኩረት ማወቅ እና እርሱን ለማስደሰት ጥረት ማድረግ አለባት። ‐ ለትዳር አጋር ስሜት መጨነቅ የትዳርን ህይወት የተሟላ እና ደስተኛ ያደርጋል!
Показати все...
46👍 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 35 6
ከአላህ ጋር አደብ ማጣት: አላህ የሰውየውን ጭንቀት ይገላግለዋል። ከዚያም የአላህን ትሩፋትና እገዛ ከማሰብ ይልቅ: ‐ «ጉዳዬ ቀላል ነበር! ከሚገባው በላይ አካብጄው ነበር!» ይላል። : ዐብዱላህ አል‐ሙዘኒይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐ «በሰውየው ላይ ከባድ ችግር ይወድቅበታል። አላህ እንዲገላግለው ዱዓም ያደርጋል። ከዚያም ሸይጣን ምስጋናውን ሊያሳጣው ሰውየው ዘንድ ይመጣና «ጉዳይህኮ እንዳሰብከው አልነበረም። ቀላል ነበር!» ይለዋል።» 📚 አል‐ሹክር፥ ኢማም ኢብኑ አቢድ‐ዱንያ [ረሒመሁላህ]
Показати все...
40👍 11😢 9
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.