ከእንቁ በላይ
Відкрити в Telegram
ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል?? ልባም ነሽ? ልባምነት ምንድነው? ሴት በመሆንሽ ብቻ ልዩ ነሽ አታስቢ ልባምነት ምን እንደሆነ በዚህ channel በደንብ እናያለን።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
197
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
197
'ሔዋን ተራቆተች'
ሔዋን ተራቆተች ዕርቃኗን ተገኘች
የከበረው ሥጋዋን ላለም እያሳየች
ራቁትነት ውርደት ነው ዕርቃን መገኘቱ
እንቅፋትን ፈጥሮ ሌላውን ማሳቱ
ገለጥ ገለጥ አርጎ ላለም ማሳየቱ
ማሰናከያ ነው ለአዳም ብዙ ነው ክፋቱ።
ሰውነትሽን ጌታ ሲፈጥረው ከጥንቱ
ቅዱስና ሕያው ለእርሱ መሥዋዕቱ
እንዲሆን አስተምሮሽ ጌታ በትዕዛዛቱ
ምነው አረከሽው ለወጥሽው በከንቱ?
ግድየለም ሔዋኔ ተለይ ከአለም
መጨረሻው ደርሷል ብዙ ጊዜ የለም።
ግድየለም እህቴ ይቅርብሽ ዕርቃኑ
ውበት የለም በራቆት ይሻላል መሸፈኑ።
የበላሻው በለስ እባቡ አታሎሽ
እሱ አይደለ ወይ ራቆት ያስቀረሽ?
ራቆትነት አሳፍሮሽ ያኔ ከሸፈንሽው
በምን እሳቤ ነው ዛሬ የገለጥሽው?
የሀጢአት ጅማሬ የምኞት መሠረት
በከፍታ መዋለል ቢመስልም ለቅጽበት
ውርደት ነው መራቆት ዝቅታ ነው ራቆትነት
ክብር የለውም ከቶ ዕርቃንሽን መገኘት!
ተይ ግን ሔዋኔ ተይ እህታለም
ከአለም መደባለቅ እርድና አይደለም!
ውበት በጌታ ነው በደንብ በመሠረቱ
ዕርቃንም ውርደት ነው ከድሮም ከጥንቱ።
"ውበት ሀሰት ነው ደምግባትም ከንቱ ነው እግ/ርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች።"[ምሳሌ 30:31]
09/04/2013
ገጣሚ😆 ሜላል ግርማ
197
💐ሬማ ዴይሊ/ሬማ በየእለቱ
ዕለታዊ የእግዚአብሔር እንጀራ
12/9/2013አ/ም እለተ ሐሙስ
አላማችሁን ከእግዚአብሔር መንግስት አንፃር ቃኙት
የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና። ወደ ዕብራውያን 10 : 36
💐እግዚአብሔር በእያንዳንዱ አማኝ የተለያየ አይነት አላማ አለው።
አላማ ማለት እንድታሳኩት በልባችሁ የሞላውና ያለው ሃሳብ ነው። አላማ በህይወት መኖርን ጣዕም ይሰጣል።
💐እግዚአብሔር በዘላለማዊ ሃሳቡ አላማውን በእናንተ ሊያሳካ ጠርቷችኋል።
አማኝ በመጀመርያ የሰማይን አላማ አንግቦ ለማሳካት ይተጋል።
እንደ አማኝ ዋነኛው አላማችን ከእግዚአብሔር መንግስት ጋር የተያያዘ ነው። አላማችሁ ሁሉ ከእግዚአብሔር መንግስት አንፃር የተቃኘና ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሆን በክብር ተጠርታችኋል።
💐ከእግዚአብሔር መንግስት አንፃር ያልተቃኘ የትኛውም አላማ ትርጉም የለሽ ነው።በምናስበውና በምናቅደው ነገሮች ውስጥ የእግዚአብሔር መንግስት አለበት??ከሌለ አላማን ለማስተካከል ጊዜው አሁን ነው።
እቅዶቻችሁን ሁሉ ከሰማይ ፈቃድ ጋር አቆራኙት።
ያኔ የተትረፈረፈ የህይወት ምልልስ መገለጫችሁ ሲሆን ታዩታላችሁ።
💐አማኝ የእግዚአብሔርን መንግስት ማዕከል ያደረገ ዕቅድ ሲኖረው እቅዱ እንዲፈፀም የሰማዩ መንግስት አስፈላጊውን በጀትና፣ ሃይል ወዘተ ሁሉ ይለቃል።
💐ስለ ሰማይ እያሰባችሁ ልታሳኩ የምትሄዱበትን እርምጃ ሁሉ ሰማይ እውቅና ይሰጣል።አንዳች የሚጎድልባችሁ አይኖርም።
እስቲ ቆም ብላችሁ እራሳችሁን ጠይቁ።
~የቀለም ትምህርት የምማረው ለምንድነው?መማሬ ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር ይገናኛል??የምማረው ለማነው?
~የምሰራው ለምንድነው??ስራዬ የእግዚአብሔርን መንግስት የሚገልጥ ነውን??ስራዬ ለእግዚአብሔር ክብር ማምጫ ነውን?
~በማገኘው ገንዘብ የእግዚአብሔርን መንግሰት(ቤ/ክ) እየደገፍኩ ነውን??በገንዘቤ ምን እያረኩ ነው?በገንዘቤ የእግዚአብሔርን ሃሳብ እያገለገለኩ ነውን??
~በሞያዬ የእግዚአብሔር መንግስት እየከበረ ነውን??
~በተቀበልኩት የፀጋ ስጦታ መንግስቱን እያገለገልኩ ነውን?
💐እነዚህን የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ለራሳችን መጠየቅ አላማችንን አውቀን እንድንኖር ይረዱናል።
💐ከእግዚአብሔር አላማ አንፃር ያልተቃኘ ሃሳብ ሁሉ ሰማይ የማያውቀው ሰማይ ድጋፍ የማይሰጠው ከንቱ ሩጫ ነው።
ሰማይ የማያውቀውን አላማ አንግቦ መኖር አሳዛኝ ነገር ነው።
💐ከእግዚአብሔር መንግስት አንፃር የተቃኘ አላማ እግዚአብሔርን ያከብራል። በአመታዊ እቅዳችሁ፣በወርሃዊ እቅዳችሁ፣ወዘተ ክርስቶስን ማዕከል አድርጉት።ያለ ክርስቶስ አታስቡ፣ያለ ክርስቶስ አታቅዱ፣ያለ ክርስቶስ አታልሙ፣ያለ ክርስቶስ አትልፉ።
ሻሎም!!
©በነቢይ መሳይ አለማየሁ
በተወዳጁ ቻናል | KALTUBE
"Daily Spiritual Feeding"
👇💐👇💐👇💐👇💐👇 💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
197
"መራራ እውነት የለም
ጣፋጭ ውሸትም የለም።"
ነኝ ያለውን አይደለህም ማለት እኔ ያልኩህን ሁን ከማለት በምንም አይተናነስም።
አማላጅ ነው ዛሬም ያማልዳል ለዚህ ፡ነው ከሰማይ ሰማያት ከ2000 አመታት በፊት ወርዶ ስለኔ ስላንቺ ስላንተ ስለሁላችን የተሰቀለው። (ለዘፋኝ፥ለዝሙተኛ፥ለነፍስ-ገዳይ፥ለክፉው፥ለልበ ደንዳናው፥ለመልካሙ፥ለሃይማኖተኛው፥ለፈላስፋው፥እምነት ለሌለው፥ለቄሱ፥ለፓስተሩ፥ለሼኹ፥ለጠንቋዩ... ለሰው ልጆች ሁሉ።)
እርሱ ሊቀ ካህን ካልሆነ የኔም የሁላችንም መዳን ጥያቄ ውስጥ ሊገባ ነው ማለት ነው! በብሉይ ኪዳን የነበሩት ካህናት እንዲሁም ሊቀ ካህኑ አስቀድሞ ስለራሱ ቀጥሎም ስለሌሎች ሐጢያት መስዋእትን ሊያቀርብ ግድ ይለው ነበር። ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት የህልውናው ጉዳይ ለካህኑ ጥያቄ እስከሚሆንበት ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ(መካከለኛ) ለመሆን ብቁ የሆነ አንድም ሰው አልነበረም!
ስለዚህ የጥልን ግድግዳ በመስቀሉ አፍርሶ ሞትን ገድሎ የሚያፀድቅ ፃድቅ ያስፈልግ ነበር። ያም ፃድቅ ሰው የሆነው ክርስቶስ ነው።(1ኛ ጢሞ.2:5
እብራውያን 8፣6 ፣9፥15፣12፥24)
የበፊቶቹ ካህናት ሞት ያሸንፋቸው ነበር ሐጢያት ይከሳቸው ነበር ሊቀ ካህኔ ኢየሱስ ግን በሐጥያት ያልተፈተነ በሞት ያልተሻረ እንደ መልከ ጼዴቅ ክህነት ለዘላለም የሆነ ክህነት አለው።ገና ክርስቶስ ሳይወለድ መዝሙረኛው ዳዊት አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ክህነት ለዘላለም ሹም ነህ ብሎ እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትም ብሎ ስለ ኢየሱስ ክህነት ተነበየ(መዝሙር 110፥4)
የኢየሱስ ክርስቶስ ምልጃው መስቀል ላይ እያለ ብቻ ያበቃ አልነበረም! የዛኔ ቢያበቃ ኖሮ የሰው ልጅ ዛሬ በስጋው ተታሎ ሐጥያትን ሲያደርግ ከአብ ዘንድ ምህረትን በምን ሃይሉ ያገኝ ነበር? ፍርድ ቤት ቆሞ ዳኛው ፊት ስለራሱ ሊከራከር ለማይችል ጠበቃ ያስፈልገዋል! ስለዚህ አብ ፊት የሚቆም ጠበቃ አለኝ ፦ ኢየሱስ ነው። ጠበቃዬ በአብ ፊት ስለኔ ይታይና ይማልድልኛል።(1ኛ ዮሐንስ 2፥1-2...ማንም ሃጥያትን፡ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ፃድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።)
ሌላ ጠበቃ እንዳይቆምልን ፃድቅ የሆነ የለም! ነገር ግን አሁን በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል ሁላችን እንዲያው በፀጋው ድነናል!
ኢየሱስ -እግዚአብሔር ወልድ- የእግዚአብሔር ልጅ-ሰው የሆነ አምላክ- በአብ ፊት ያለን ጠበቃ-በሰውና በአብ ፊት የሚቆም መካከለኛ-አማላጅ እና ፃድቅ ፈራጅ ነው።
"እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው።
"ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በህይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ አብ የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።" እብራውያን 7፥25
ሰውም እንደሌለ አየ ወደ እርሱም የሚማልድ እንደሌለ አየ ተደነቀም ሰለዚህ የገዛ ክንዱ መደሓኒት አመጣለት ጽድቁም አገዘው።" ኢሳይያስ 69፥16
@yedemufreforchrist
@yedemufreforchrist
197
ኢሳይያስ 53
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
² በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
³ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።
⁴ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
⁵ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
⁶ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
⁷ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
⁸ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
⁹ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።
¹⁰ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
¹¹ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።
¹² ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
197
#የሕይወት ዘንግ
ሰላም ቅዱሳን🙌🙌 ከተገነዘብኩት ጥቂት ላካፍላችሁ:-
ንጉሱ አርጤክስስ ይገዛ(ያስተዳድር) በነበረበት ወቅት በአይሁዳውያን ላይ የታወጀ አስደንጋጭና አሳዘኝ አዋጅ እንደነበር ከማናችንም አእምሮ የሚጠፋ ጉዳይ አይደለም፡፡
የታወጀው አዋጅ ለአይሁድ የለቅሶ የንጉሱ ቀኝ እጅ ለነበረው ለሐማ ደሞ የደስታ አዋጅ ነበር፡፡
የታወጀውን ይህን ክፉ አዋጅ ያስቀየረው አንድ ነገር አለ:- የተዘረጋው የንጉሱ የወርቅ ዘንግ!
የንጉሱ የወርቅ ዘንግ መዘርጋት በሕይወት የመኖር ዋስትና እና ፍቃድ ነው በተቃራኒው ደሞ የወረቅ ዘንጉ ካልተዘረጋ የመኖርን ህልውና አጥቶ የመሞት ሕግ እነደሆነ በዚሁ በአስቴር መፅሐፍ 4:11 በግልፅ ተቀምጧል፡፡
ለአስቴር ብሎም ለአይሁድ ሕዝብ የመኖር ሕልውና የሆነው ይህ ዘንግ ነው:-የሕይወት ዘንግ!!
ማንም ሰው ወደ ንጉሱ ይገባ ዘንድ ባልተፈቀደለት ጊዜ አስቴር ወደ ንጉሱ መግባት የቻለችው
1 የንጉሡ ሚሥት ስለነበረች
2 እሷም ንግስት👸👸 ስለሆነችና መብት ስላላት
3 ንጉሡ በጣም ስለሚወዳት
.
.
....አልነበረም፡፡
ምንም እንኳን እኚህ 👆👆👆 ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ብታሟላም በፍፁም🙅 ግን ምክንያት ሊሆኗት አይችሉም ፡፡
ብቸኛው ምክንያት 👉👉 በንጉሡ ፊት #ሞገስ ማግኘቷ ነበር፡፡
ንጉሡ ዘንጉን እንዲዘረጋላት ያደረገው ሞገስ ከዬት የመጣ ነው?🤔
መልከ-መልካምና ቆንጆ ስለሆነች አልያም ንግሥት ስለሆነች አይደለም 😲😲
ታድያ ከዬት መጣ?🙄🙄
#ከፀሎት 🙏🙏🙏
አስቴር ይህንን ሞገስ ያገኘችው ከራሷ አልፋ ለሕዝብ የመዳን ምክንያት የሆነችው አዎ በእግዚአብሔር ፊት ስለሆነችና ስለሆነች ብቻ ነው፡፡ በቃ ሌላ ምክነያት የለም🤷♀
ለአስቴር የተዘረጋላት የሕይወት ዘንግ እንዲዘረጋልህ/ሽ ትፈልጋለህ/ጊያለሽ?????
እንግዲያውስ👇👇
# እውቀት
# ማስተዋልና ጥበብ
# ገንዘብ
# ብልሃት
.
.
.
ሳይሆን ሚያስፈልግህ/ሽ ፀሎትና ፀሎት ብቻ ነው፡፡ አስተዉሉ እነዚህ ከላይ ያዘረዘርኳቸው ነገሮች አያስፈልጉም አላልኩም አስፈላጊ ናቸው አምናለው ግን ከፀሎት ቀጥሎ ነው ሚያስፈልጉን፡፡
ፀሎት ሞገስ ይሰጣል ሞገስ ደሞ የሕይወት ዘንግ!!
ሰላሙን ያብዛልን ጉልበታችን በፀሎት ይበርታ ሞገሱን ያልብሰን ጌታ የሕይወት ዘንጉን ይዘርጋልን አሜን፡፡
@libamset
@libamset
@libamset
197
የተባረከች የጌታ ሴት
ሁሉም ሰው ፊት ሞገስ ያላት(ለንግስና የሚያስመርጥ ህግን የሚያሽር ሞገስ የወርቁን ዘንግ የሚያዘረጋ ሞገስ)
በተቀመጠችበት ስፍራ ሰለሌሎች የምትኖር (ስፍራዋን የመጠነች)
በመኖሯ ውስጥ ብዙዎችን ያኖረች ድንቅ ሴት(የንጉሱንም የህዝቧንም ሞት እንዲሻር ያደረገች)
..... አስቴር!-ልባም ሴት
ልባም ሴት ነሽ? በመኖርሽ ሌሎችን አኑሪ
ለሌሎች ምሳሌ ሁኚ
የጌታን ፊት ፈልጊ
ከጌታ ዘንድ ሞገስን ተቀበይ...
ልባም ሁኚ ልክ እንድ አስቴር!
If u have any comment @sumuniye
To invite ur sister and friends @libamset
@libamset
@libamset
197
ባለፈው ጊዜ አስቴር ንግስናን በውበቷ ሳይሆን በሞገሷ እንዳገኘች እንዲሁም ከሷ የተነሳ ንጉስ አርጤክሥ ለሚገዛው ሀገራት በሙሉ ምህረትን እንዳደረገ እና የንጉሱንም ህይወት ከሞት ኣንዳተረፈች ተመልክተናል።
ዛሬ በመጨረሻ ደግሞ አስቴር ህዝቧን መታደግ የቻለች ጀግኒት የእግዜአብሔር ሴት እንደሆነች እንመለከታለን!
ልባም ሴት ከራሷ መኖር አልፎ ተርፎ ሌሎችን የምታኖር ናት። ልባም ከሆንሽ ባንቺ መኖር የሚኖሩ(የሚተርፉ) ሰዎች ሊኖሩ ይገባል። እግዜብሔር በምድር ስንኖር ህይወታችንን ስለወንድሞቻችን አሳልፈን መስጠት እንዳለብን ከራሳችን በላይ ስለሌኮች መኖር ግድ እንዲለን ይነግረናል!(1ኛ ዮሐ 3፥16)
ክርስቶስ በመኖሩ ውስጥ እኛን አኑሮናል!
ስለዚህ ልባም ሴት ከሆንሽ በህይወትሽ ክርስቶስን መግለጥ አለብሽ! ለእህቶችሽና ለወንድሞችሽ ለሌሎች ኑሪላቸው። ባንቺ መኖር ብዙ ነፍሳት ይኑሩ። ይህ ነው ልባምነት።
በዚህ ክፍል እንደምንመለከተው ሐማ በክፋት ተነሳስቶ ባዘጋጃው እቅድ ሙሉ አይሁዳውያን ሊደመሰሱ(ሊገዳሉ) በንጉሱ ቀለበት ታትሞ በማይፈርስ ውል የአይሁዳውያን መኖር እንዲያበቃና ተረት እንዲሆን ተደርጓል። ምንም እንኳን አስቴር ወደ ንጉሱ ለመግባት ብትፈራም በስተመጨረሻ ግን ህጉን ተላልፋ በንጉሱ ፊት ለመግባት ወስናለች! ለምን? አይሁዳዋያንን ወይም ህዝቧን ለማዳን። ህጉን መተላለፏ ህይወቷን እንደሚያሳጣት ብታውቅም መርደኪዮስ እንደነገራት አስቴር ንግስት መሆኗ ያለ ምክንያት አይደለምና በተቀመጠችበት ቦታ ለምትፈለግበት አላማ መኖር እንዳለባት ውስና ውድ ህይወቷን ሰውታ በድፍረት ወደ ንጉሱ ገብታለች!
ነገር ግን አንድ ልናስተውለው የሚገባው ጉዳይ አስቴር ንጉሱ ፊት ከመግባቷ በፊት የወሰነችው ትልቅ ውሳኔ አለ! ይሄም ሁሉም አይሁዳውያን አስቴርንና ደንገጠሮቿን ጨምሮ ለህዝቡ መዳን እንዲሁም ለአስቴር በንጉሱ ፊት ተቀባይነት ማግኘት ትክክለኛው መንገድ የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ እንደሆነ ወስናለች። ምን አይነት የምትገርም ሴት ናት!?
ለምታደርገው ነገር ሁሉ ፀሎትን እንደመፍትሄ የምትቆጠር ከየትኛውም እርምጃዋ በፊት የጌታን ፊት የምትፈልግና የእግዚአብሄርን ፍቃድ የምትጠይቅ አስተዋይና ልባም ሴት!
በስንት ጉዳዮችሽ እስከዛሬ ጌታ ሆይ ቅድሚያ አንተ ምን ትላለህ? ብለሽ ታውቅያለሽ?
ልባም ሴት ከምንም ነገር በፊት በእግዚአብሄር ፊት የምትቀርብ ናት። ንጉሱ ፊት ከመቅረብ በፊት በጌታ ፊት መቅረብ ቀዳሚ ነው ለልባሟ ሴት!
ያለ ህግ ወደ ንጉሱ ገብታ ህጉን አስፈርሳ ነገሩ እንዲገለበጥ አድርጋ በሱሳ ግምብ ያሉትን አይሁዳውያን ሙሉ ልትታደግ የቻለች ድንቅ ሴት -አስቴር !
"ያለ ህግም ቢሆን ገብቼ..." ብላ በህይወቷ ጨክና ትውልድን የምታድን
ከማንም በፊት የጌታን ፊት የምትፈልግ
197
ዛሬ ከሰላምታ በፊት ይቅርታ ላስቀድም!
የልባሟ ሴት የአስቴርን ህይወት በጅምር ስለተውኩት ይቅርታ ጠይቂያለው ከልብ🙏🙏🙏
ባላችሁበት ሁሉ ሰላማችሁ ይብዛ
197
አስቴር 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ መርዶክዮስም አክራትዮስን፦ ሂድና ለአስቴር እንዲህ በላት አለው። አንቺ፦ በንጉሥ ቤት ስለ ሆንሁ ከአይሁድ ሁሉ ይልቅ እድናለሁ ብለሽ በልብሽ አታስቢ።
¹⁴ በዚህ ጊዜ ቸል ብትዪ ዕረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?
¹⁵ አስቴርም እንዲህ ብሎ ለመርዶክዮስ እንዲመልስ አዘዘችው።
¹⁶ ሄደህ በሱሳ ያሉትን አይሁድ ሁሉ ሰብስብ፥ ለእኔም ጹሙ ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑን አትብሉም፥ አትጠጡም እኔና ደንገጥሮቼ ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን፤ ምንም እንኳ ያለ ሕግ ቢሆን ወደ ንጉሡ እገባለሁ፤ ብጠፋም እጠፋለሁ።
¹⁷ መርዶክዮስም ሄዶ አስቴር እንዳዘዘችው ሁሉ አደረገ።
197
አስቴር 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ሐማም ንጉሡን አርጤክስስን፦ አንድ ሕዝብ በአሕዛብ መካከል በመንግሥትህ አገሮች ሁሉ ተበትነዋል፤ ሕጋቸውም ከሕዝቡ ሁሉ ሕግ የተለየ ነው፥ የንጉሡንም ሕግ አይጠብቁም፤ ንጉሡም ይተዋቸው ዘንድ አይገባውም።
⁹ ንጉሡም ቢፈቅድ እንዲጠፉ ይጻፍ፤ እኔም ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት ያገቡት ዘንድ አሥር ሺህ መክሊት ብር የንጉሡን ሥራ በሚሠሩት እጅ እመዝናለሁ አለው።
¹⁰ ንጉሡም ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ፥ ለአይሁድም ጠላት ለአጋጋዊው ለሐመዳቱ ልጅ ለሐማ ሰጠው።
¹¹ ንጉሡም ሐማን፦ ደስ የሚያሰኝህን ነገር ታደርግባቸው ዘንድ ብሩም ሕዝቡም ለአንተ ተሰጥቶሃል አለው።
¹² በመጀመሪያውም ወር ከወሩም በአሥራ ሦስተኛው ቀን የንጉሡ ጸሐፊዎች ተጠሩ፤ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ወዳሉ መቶ ሀያ ሰባት አገሮች፥ በየአገሩ ወዳሉ ሹማምትና አለቆች ወደ አሕዛብም ሁሉ ገዢዎች እንደ ቋንቋቸው በንጉሡ በአርጤክስስ ቃል ሐማ እንዳዘዘ ተጻፈ፥ በንጉሡም ቀለበት ታተመ።
¹³ በአሥራ ሁለተኛው ወር በአዳር በአሥራ ሦስተኛው ቀን አይሁድን ሁሉ፥ ልጆችንና ሽማግሌዎችን፥ ሕፃናቶችንና ሴቶችን፥ በአንድ ቀን ያጠፉና ይገድሉ ዘንድ፥ ይደመስሱም ዘንድ፥ ምርኮአቸውንም ይዘርፉ ዘንድ ደብዳቤዎች በመልእክተኞች እጅ ወደ ንጉሡ አገሮች ሁሉ ተላኩ።
¹⁴ በዚያም ቀን ይዘጋጁ ዘንድ የደብዳቤው ቅጅ በየአገሩ ላሉ አሕዛብ ሁሉ ታወጀ።
¹⁵ መልእክተኞቹም በንጉሡ ትእዛዝ እየቸኰሉ ሄዱ፥ አዋጁም በሱሳ ግንብ ተነገረ። ንጉሡና ሐማ ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ከተማይቱ ሱሳ ግን ተደናገጠች።
197
|| አባት ሴት ልጁን የመከረው ምክር ||
ክፍል አንድ
ይህ አባት ለሴት ልጁ የመከረው ምክር ነውና በማስተዋል አንብቡት !
👉ወጣት ሴቶች ልጆች እንዲጠነቀቁ
👉 ወላጆች ሴቶች ልጆቻቸውን እንዲመክሩ ይረዳችኃልና !
ወድ ልጄ በምድር እንድትኖሪበት የተሰጠሽን ሕይወት ዳግመኛ ተመልሰሽ አትኖሪበትም ! የተፈጠርሽበትን ዓላማ ከፈጠረሽ አምላክ ጠይቂ ! በተሰጠሽ ዘመን ለፈጠረሽ አምላክ ፈቃድ ተገዢ !
☞ሴት ልጅ ውድ ነች ርካሽ ብትሆን ለውዷ ቤተክርስቲያን በምሳሌ አትሰየም። በእግዚአብሔር ላንቺ የተመዘነው ዋጋ የክርስቶስ ደም ነው። ራስሽን ማየት ያለብሽ እግዚአብሔር በሚልሽ እንጂ ሰይጣንም፣ ሰውም፣ ሁኔታም፣ በሚገልጽሽ ማንነት አይደለም። በእግዚአብሔር እንተወደደች እንደ ውድ ዕንቁ ሴት ራስሽን ቁጠሪ ፤
☞ እግዚአብሔር በልጁ ሞት ሕይወት የሰጠሽ የከበርሽ ልጁ ነሽ !
☞ እግዚአብሔር በዓላማ ፈጥሮሻል!
☞ ከእግዚአብሔር ሐሳብ ወደ ግራም ወደ ቀኝም እንዳትይ ተጠንቀቂ !
☞ በሰይጣንና በሰው የሚሰጥሽን መደለያ ፈጽሞ አትቀበይ ወጥመድ ነውና !
☞ ክብርሽ ስኬትሽ ደስታሽ ያለው በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ነው !
☞ ለገንዘብ ራሳቸውን የሸጡትን ምክር አትስሚ ! ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችይምና ! አምላኬ ገንዘብ ሳይሆን እግዚአብሔር ነው በያቸው !
☞ ሁል ጊዜ ነፍሱን ሰጥቶ ያዳነሽን ጌታ ፍቅር አስቢ !
☞የእግዚአብሔርን የፀጋ ክብር በሙላት ይግባሽ፤
☞ሰይጣን በላከው ተራ ወንድ አትሸወጂ ስላንቺ ያለው እይታ ከቤት ዕቃ አያልፍምና ! (የቤቱን እቃ አሟልቶ አሁን ደግሞ ሚስት ብሎ ከሚያቅድ ነገ እንደ ቁምሳጥን፣አንደ መኪና የቤት እቃ አድርጎ ሊቆጥርሽ ከሚችል እይታው ከጠበበ ወንድ ተጠበቂ)፤
☞እግዚአብሔር ፀጋውንና የክርስቶስን ልብ ሰጠን እንጂ ለእባብ የሚስቅ የሄዋንን ልብ አልሰጠንምና የቀረበሽ ወንድ ሁሉ ያንቺ አይደለምና ተጠንቀቂ።☞ፍቅር የዘኝ ብሎ ለሚፈጥነውም ረጋ በል ብሎ መመርመር ይገባል። ወዲያው አፈቀርኩ አበድኩ ነደድኩ ብሎ የሌለን አለም ታሪክ ዲስኩር ከሚቀድ ወንድ ተጠበቂ ተጠንቀቂ ውድቀትሽን ስብራትሽን ሐዘንሽ ለማፈጠን ከሰይጣን የተላከ የስሜት ፈረስ ጋላቢ ሊሆን ይችላልና።
☞አበድኩ አፈቀርኩ ብሎ ኃላ የጥላቻ ቁንጮ የሆነውን አሲድ ከሚደፋ ወንድ ጋር ህብረት አታድርጊ አሲድ ባይደፋም በእርኩሰቱ ወደ ሲኦል የሚመራሽ ከዚያ ይብሳልና ተጠበቂ !
☞ከማታውቂው መልአክ የምታውቂው ሰይጣን ይሻላል አየተባለ ከሚደሰኮር ተረት ራቂ ለሞትና ለጥፋት የሚያዘጋጅ ነውና።
☞ ይልቅ ለፈጠረሽ አምላክ ለእግዚአብሔርን የተሰጠ እውነተኛ ወንድም ከእግዚአብሔር እጅ ለመቀበል ጸልይ ከአምላክሽ ጋር የጠበቀ ሕብረት ይኑርሽ ! በጸሎት በአምልኮ በቃል ጥናት በመንፈስ ቅዱስ ሙላትና ምሪት የተቃኘ ሕይወት ይኑርሽ !
☞ የተፈጠርሽበትን ዓላማ ለማሳካት ጌታን በሚያስከብር ሕይወት የአገልግሎት ጸጋሽን በመለየት አገልግይ!
☞ የሚገርመው ጌታ በውስጥሽ ያስቀመጠው የሚገርም የተዳፈነ ፀጋ አለሽ በጸሎት በቃሉና በመንፈሱ ሙላት ይገለጣልና ቀድሞ ከነበረሽ ይልቅ በጌታ ፊት ወድቆ የመጮህ ጊዜ ይብዛልሽ ! ☞ጸጋው በተገለጠ ጊዜም ለሰጪው ክብር በማብዛት በስርዓት ወደ መድረክ ይዘሽው ውጪ ለብዙዎች መዳን ምክንያት ትሆኛለሽና !
☞በትንቢት ቃል አትታሰሪ/ትዳር/ አትመስርቺ ለነብይ የነገረው አባትሽ እግዚአብሔር ከሆነ ላንቺ በቀጥታ ይነግርሻል ልጁ ነሽና እንደ ነጎድጓድ የሚነገር ልሳን አትፍሪ አትደንግጪ !
☞አንቺ ልባም ሴት ልጅ ነሽ የክርስቶስ ልብ ያለሸ፤
☞አንቺ ከመውለድ ልጅ ከማሳደግ ንብረት ከመሰብሰብ ያለፈ መለኮታዊ ፕሮግራም ያለብሽ በደሙ የተገዛሽ ዕንቁ ልጁ ነሽ !
☞ የአምላክሽ ዋና ዓላማና ግብ ማግባት ብቻ አይደለም ለዘላለም ሕይወት ክብር በክርስቶስ መመረጥሽ እንጂ ! በምድር ከሚሆንልሽ እና ከሚደረግልሽ ያለፈ ክብር አለሽ !
☞ የሰርጉ ሆታ ጭፈራ እልልታና ሽብሸባ የአንድ ቀን ነው። በክርስቶስ የተዘጋጀው ክብር ግን የዘለዓለም ነው !
☞ በአምላክሽ የታሰበልሽን ግብና የተሰጠሽን ተስፋ አስቢ !
☞በጊዜው የሚመጣ ክብርሽ የሚሆንልሽ የትዳር አጋር ዘውድ የምትሆኚለት ወንድ በእግዚአብሔር እንደተወሰነልሽ አስቢ፤
☞☞☞ይህ ከሆነ በእውነት ልባሟ ሴት አንቺ ነሽ ! ተባረኩልኝ።
Alex
@Biblicalmarriage
197
ምሳሌ⓮
(ጠቢብ ሴት👌😊)
“ብልሃተኛ ሴት ቤትዋን ትሠራለች፤ ሰነፍ ሴት ግን በእጅዋ ታፈርሰዋለች።”
— ምሳሌ 14፥1
“ጠቢብ ሴት ቤቷን ትሠራለች፤ ተላላ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች።”
— ምሳሌ 14፥1 (አዲሱ መ.ት)
“Every wise woman buildeth her house: but the foolish plucketh it down with her hands.”
— Proverbs 14፥1 (KJV)
197
💐 መንፃት እፈልጋለሁ....
ሰው መሆን ያምረኛል ... እንደ ሰው መቆጠር ... ከሰው እኩል መሆን! በብርሃን መመላለስ... የማን አየኝ ኑሮዬ እንዲያበቃ እፈልጋለሁ። አጥፍቻለሁ ... ደጋግሜ በድያለሁ ... ስህተቴን ላስተባብል አፌን አልከፍትም። አዎን በድያለሁ። ግን መንፃት እፈልጋለሁ! ረፍዶብኝ ይሆን? አላውቅም።
በጀርባዬ ተንጋልዬ ተኝቼ የቤቴን ጣሪያ እያየሁ ትናንትን በጊዜ ቀለበት ውስጥ የኋልዮሽ ተጉዤ ቃኘሁ። ምንም ልክ የሆነ ነገር የለኝም። ከየት እንደመጣሁ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም። መንገድ መርጬ አልተጓዝኩም። ምከንያቱም መድረሻዬን አላውቀውም። እግዚአብሔር ነው ከእኔ የራቀው? ወይስ እኔ ነኝ ከእግዚአብሔር የራኩት? እኔ ነኝ የተውኩት ወይስ እርሱ ነው የረሳኝ? ፀፀት ያንገላታት ነፍሴ በስጋዬ ታፍና ሰሚ የሌለው ጩኸት ታሰማለች። ህሊናዬ ደጋግሞ ይወቅሰኛል። ልክ አንዳልሆንኩ ይነግረኛል። ተከራክሬው አላውቅም ... ብቃቱ የለኝም። ሲነጋ ይከፋኛል ... ብርሃን ያስጠላኛል። ጨለማው ከሰው ሸሽጎ ለራሴ አጋልጦኛል። ራሴን አላውቀውም ... ይኼ ነው ብዬ ለሰው ማሳየው ማንነት የለኝም። ከገባውበት የውድቀት አዘቅት ውስጥ ሆኜ ቀን ተለሊት ማስናለሁ። መውጫ ቀዳዳ ማትራለሁ። ሆኖም ግን ዕድሌ ከመርፌ ቀዳዳ ይበልጥ የጠበበ መስሎ ይሰማኛል።
መንፃት እፈልጋለሁ.....
💐 ግን ህይወት ምንድነው? የመኖር ትርጉሙስ? ለምን ተፈጠርኩ? እንዲህ ሆኜ እንድኖር? እንድቅበዘበዝ? ጥያቄ አለኝ ... መልስ ግን የለኝም። ለጫወታ የጀመርኩት መንገድ ኑሮዬ ሆኖ እዚህ አድርሶኛል። በገዛ እጄ ነፃነቴን አጥቻለሁ። ባሪያ ነኝ። የስጋዬና የምኞቴ እስረኛ የሆንኩ ሴት ... የውበት አፍላዬን ለመጣው ለሄደው ሁሉ ሽጬ የምኖር ሴት። ከነፍሴ ጋር ፍቺ የፈፀምኩ ሴት። ለሁሉም ወንድ የተገባሁ ግን ደግሞ የማንም ያልሆንኩ ሴት። የተናቅሁ፣ የተረገምኩ፣ በማህበረሰቡ ዘንድ አይንሽን ላፈር የተባልኩ፣ የተጠላሁ ሴት። ማንም በስሜ ጠርቶኝ አያውቅም። "ያቺ አመንዝራይቱ ሴት" መታወቂያዬ ነው.........
👇👇👇
ሙሉ ለማንበብ ይጫኑ
💐ከቃልኛ ስድስተኛ መፅሔት የተወሰደ
© KALTUBE
197
መዝሙር 30
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ቍጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፥ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን፤ ልቅሶ ማታ ይመጣል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል።
⁶ እኔም በደስታዬ፦ ለዘላለም አልታወክም አልሁ።
⁷ አቤቱ፥ በፈቃድህ ለሕይወቴ ኃይልን ሰጠሃት፤ ፊትህን መለስህ፥ እኔም ደነገጥሁ።
⁸ አቤቱ፥ ወደ አንተ ጠራሁ፥ ወደ አምላኬም ለመንሁ።
⁹ ወደ ጥፋት ብወርድ በደሜ ምን ጥቅም አለ? አፈር ያመሰግንሃልን? እውነትህንም ይናገራልን?
¹⁰ እግዚአብሔር ሰማ ማረኝም፤ እግዚአብሔር ረዳቴ ሆነኝ።
¹¹ ክብሬ ትዘምርልህ ዘንድ ዝምም እንዳትል ልቅሶዬን ለደስታ ለወጥህልኝ፥ ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ።
¹² አቤቱ አምላኬ፥ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ።
197
ከመገደል እንደተረፈ እንዲሁ ክፉ ያሰቡት ገበታና ታራ በእንጨት ተሰቅለው እንደሞቱ እናያለን።
እናስተውል ንጉሱ ከመገደል ተረፏል በመርዶክዮስና በአስቴር ምክንያት!
እኒህ ሰዎች ምርኮኞች ቢሆኑም ከዘራቸው የተነሳ ለንግስና ባይፈለጉም አስቴር ንግስት ሆናለች መርደክዮስና አስቴርም የንጉሱን ነፍስ አትርፈዋል!
የአስቴርን ልባምነት ዛሬ ባጭሩ ስናጠቃልል፥
1-በሁሉ ዘንድ ሞገስ የነበራት ሴት ናት
2- ለንግስና በመታጨቷ ምክንያት ለ127 አገራት ምህረት ተደርጓል እንዲሁም ንጉሱ እንደልግስናው መጠን ስጦታ ሰጠ።
3-ለመርደክዮስ ተዛዥ ነበርች
4-የንጉሱን ህይወት ከሞት ልታተርፍ ችላለች።
ዛሬ በጸሎትሽ ይሄን አስቢ፥ የእግዚአብሔር ሞገስ ባንቺ ላይ ኣንዲሆን ታዛዥ እንዲያደርግሽ ባምቺ ምክንያት ሰዎች ከሞት እንዲተርፉ እንዲሁም ካንቺ የተነሳ ለሌሎች ምህረት እንዲደረግ። ከዚች ልባም ሴት ብዙ እንደተማርን ተስፋ አደርጋለሁ። ፀጋው ይሸፍናቹ።
ሊንኩን forward በማድረግ ሌሎችን invite በማድረግ ቻናሉን በማስፋት ተባበሩኝ።
እወዳችኋለሁ።
ይቀጥላል...
@libamset
@libamset
@libamset
@sumuniye for any comment.
197
ስላም ከእንቁ በላዮች እንደምን ሰነበታቹ?
ስለጠፋሁ ይቅርታ እየጠየኩ ባለፈው ጊዜ ጀምረን ያልጨረስነውን ትምርት ዛሬ እንቀጥላለን።
ለማስታወስ ያክል ባለፈው ያየናት ልባም ሴት አስቴር ነበረች። በክፍል አንድ ውስጥ ንግስት አስጢን ከንግስናዋ ከወረደች በኋላ ንግስትን ተክታ የምትነግስ አንዲት ሴትን ፍለጋ ብዙ የሃገሪቷ ቆንጆዎች ተሰብስበው ለንገስና በሚታጪበት ግዜ አስቴር ከዉበቷ ባለፈ በሞገሷ(ሁሉ ፊት ባገኘችው ሞገስና መወደድ)የተነሳ ለንግስና ታጭታ እንደነበር አይተናል።
አስተውሉ እግዚአብሔር በፍጹም አይሳሳትም! ቃሉም በጭራሽ እርስ በርስ አይጋጭም!!
ለዚህ እኮ፡ነው በምሳሌ 31፥30 ላይ ውበት ሃሰት ድምግባትም ከንቱ ነው ብሎ የሚናገረው። ዉበት ሃስት ባይሆን ኖሮ እነዛ ለንግስና ተፈልገው የተሰበሰቡት ሴቶች በሙሉ ዉበታቸው ከንቱ ሆኖ ባልተሸነፉ ነበር!
የባለፈውን ክፍል ይሄን ያክል፡ካስታወስን ወደዛሬው እንለፍ። ከዛ በፊት ግን ሁላችሁም እየሰጣቹኝ ስላለው አስተያየትን ድጋፍ ምስጋናዬ ከልብ ነው ተባረኩልኝ።
ንጉሱ አርጤክስ አስቴር ንግስት እንድትሆን ከወሰነና በራሷ ላይ የንግስናን ዘዉድ ከጨነላት በኋላ ለ7 ቀን በንጉሱ ቤት ስለአስቶአር ግብዣ አደረገ።
በዚህም ግብዣ ላይ ለአገሮቹ ሁሉ ይቅርታ አደረግ ይላል! እንደ ንጉሱም ለጋስነት መጠን ስጦታ ሰጠ።(2፥18)
ንግሱ አስቴርን ከመውደዱና ሞገስ ከማግኘቷ የተነሳ በተደረገው ግብዛ ላይ ለአገሮቹ ሁሉ ይቅርታን አደረገ ይላል። ለስንት ሃገራት ብለን ከጠየቅን በምእራፍ 1 ላይ እንደተጠቀሰው ንጉስ አርጤክስ ይገዛ የነበረው በ127(ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ) ሃገራት ላይ ገዢ እንደነበር ይናገራል!
ከአስቴር የተነሳ ለ127 ሃገራት ሙሉ ምህረት ተደርጎላቸዋል! ምን አይነት የእግዚአብሔር ሞገስና መወደዲ ያላት ሴት ናት!?
መርደኪዮስ አስቴርን እንድ አባት ሆኖ ልጅነቷ ጀምሮ ስላሳደጋት እንደኣባትነቱ በመጨነቅ አስቴር የለችበትን ሁኔታ ይከታተል ዘንድ ዘወትር በሴቶቹ በር ወለልና በንጉሱ በር ይቀመጥ ነበር።
አይሁዳዊያን በባቢሎን ሃገር ምርኮኞች ሆነው ስለተወሰዱ መርደክዮስ ለአስቴር ስለ ወገኗ እንዳትነጋር አስጠንቅቋት ነበር። አስቴርም ካሳደጋት ከመርደክዮስ ታእዛዝ ከልጅነቷ ጀምሮ ስለማትዋጣ መርደክዮስ እንደዛዘት እንዲሁ ስለዋጋኗ አልተናገረችም፡ነበር።
መልከ መልካም ባለሞገስ በሁሉ ዘንድ ተወዳጅ እንዲሁም ታዛዥ ነበርች! ልባሟ ሴት አስቴር።
በዚህ በምእራፍ 2፥21-23 እንደምንመለከተው ገበታና ታራ የሚባሉ የንጉሱ በር ጠባቂዎች በንጉሱ ላይ ተቆጥተው ንጉሱን ለመግደል ባሰቡ ጊዜ ነገሩ ለመርዶክዮስ ግልጥ ሰለሆነለት በንጉሱ ላይ የተመከረውን ክፉ ምክር ለአስቴር በመንገር የንግሱ ህይወት...
197
ቃልህን መርሳት ነው ጎዶሎነት
መፀለይ ማቆም ነው ድርቀት
መንፈስህን መተው ነው ቅዠት
ውሎ ማደር አንተ በሌለህበት
አንተን ማጣት ነው ብቸኝነት
ሳይሰሙህ መውጣት ነው ዙረት
ያለድምፅህ መስራት ነው ክስረት
ውሎ ማደር አንተ በሌለህበት
Singer Aster Abebe
💐Live Worship Song
Share💐Share💐Share
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
197
እኔ ደካማ ነኝ
አንዳንድ የስነልቦና ተማራማሪዎችና ምሁራን የሰው ልጅ ጥንካሬውንና ሃያልነቱን አሸናፊነቱን እንዲያምን ከዚያም ለራሱ እንዲናገር ማለትም በራሱ ላይ እንዲያውጅና (fully confident) ያለ ልክ በራሱ እንዲተማመን ይመክራሉ።
ለምን? ሰው ይሄን ባደርገ ቁጥር እራሱን እያነጸና እየበረታ ይሄዳል ብለው ስለሚያምኑ እንዲሁም የሰው ልጅ እምቅ ሃይሉን እንዲጠቀምበት ይረዳዋል ስለሚሉ።
የእግዚአብሔር ቃል ግን ይሄን ጉዳይ ምን ይለዋል?
"በመንፈሴ እንጂ በሃይልና በብርታት አይደለም ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር"ት.ሕዝ.4:6
ስለዚህ ከቃሉ እንደምንረዳው በእግዚአብሔር ሃይልና ብርታት እንጂ በኛ ሃይልና ብርታት ሚሆን፡ነገር እንደሌለ ነው።
የሰው ልጅ በራሱ ብርታት ሲደገፍ ኣዋቂዎቹ(psychologists)እንደሚሉት ብርቱ ሳይሆን፡ሚሆነው እጅግ ደካማና ምንም ማያውቅ ከሰው በታች ነው የሚሆነው! ለዚህ ማስረጃ ደሞ ናቡከደናጾርን መመልከት እንችላለን በራሱ ሲደገፍ ከሰው ተራነት ወጥቶ እንድ ከብት ሣር እስከሚግጥ ድረስ ነበር የተዋረደው!
መጽሐፍ ቅዱሳችን ግን ነገሮችን ለመቻልና ለማድረግ አንድ ነገር ያስተምረናል:-"ሃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ" ፊሊ.4፥13
እራሳችንን ክደን ከተከተልነው እንግዲህ አለን ብለን የምናስበውንም ሃይልና ብርታት ክደን የጌታን ሃይልና ብርታት መንፈሱን ብቻ መታመን ይኖርብናል።
እንግዲህ እኛ በክርስቶስ የሆንን ልንለውና ልናምነው የሚገባው ጉዳይ
*እኔ ደካማ ነኝ ጌታ ግን ሃይሌ ነው
*እኔ አቅም የለኝም ክርስቶስ አቅሜ ነው
*በኔ ብርታት ሳይሆን በመንፈሱ ነው
*ከኔ የሆነ አንዳች የለም ሁሉ ከርሱ ልርሱ በሱ ሆኗል
በመጨረሻም በክርስቶስ ግን ሁሉን እችላለው በራሴ ደሞ ኣንዳች እንዳልችል አውቂያለው! ይሄንን ነው ክርስቲያን ማመን ያለበት።
ይቀጥላል...
@yedemufreforchrist
@yedemufreforchrist
Join for more
