uk
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Відкрити в Telegram

EEP Communication

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу EEP Communication

Канал EEP Communication (@eepcommuication) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 533 підписників, посідаючи 8 368 місце в категорії Технології та додатки та 2 174 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 533 підписників.

За останніми даними від 30 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 10, а за останні 24 години на -6, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 24.86%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 16.87% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 3 862 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 2 620 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 9.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
EEP Communication

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 01 липня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Технології та додатки.

15 533
Підписники
-624 години
-207 днів
+1030 день
Архів дописів
photo content
+5

የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፉ በወቅቱ በመድረሱ ብዙ ሰው ከጉዳት ታድጓል- የካራ ቆርጮ ቀበሌ ነዋሪዎች . .......///......... የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፉ በወቅቱ በመድረሱ ምክንያት የአካባቢውን ማህበረሰብ ከከፋ ችግርና ረሃብ መታደጉን በደቡብ ኦሞ ዞን የሐመር ወረዳ ካራ ቆርጮ ቀበሌ ነዋሪዎች ገለፁ። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍና ሥርጭት ክትትል ኮሚቴ በሐመር ወረዳ የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው የምግብ እጥረት ሳቢያ ድጋፍ የተደረገላቸውን የካራ ቆርጮ ቀበሌ አርብቶ አደሮችን ጎብኝቷል። በጉብኝቱ ወቅት ከአካባቢው የጎሳ መሪዎች፣ የማህበረሰብ ተወካዮችና የቀበሌው አመራሮች ጋር በሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሥርጭቱ ዙሪያ ውይይት አካሒዷል። የካራ ቆርጮ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ላሌ አራዳ እንደገለፁት ለነዋሪዎቹ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ድርቁ የከፋ ችግር ሳያደርስ ማስቀረት አስችሏል። የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሥርጭቱ የመረጃ ልውውጥ ክፍተት ችግሮች ቢኖሩበትም በአካባቢው የሚኖረውን አርብቶ አደር ተጠቃሚ ማድረጉን ሊቀመንበሩ ገልፀዋል። አቶ ጴጥሮስ ለማ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ በመደረጉ መደሰታቸውን ገልፀው የአርብቶ አደሩን ህይወት በዘላቂነት ለመለወጥ በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀዋል። የተደረገላቸው የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ወቅቱን የጠበቀ በመሆኑ እርዳታውን ላደረገው ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና ሥርጭቱን ላከናወነው ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አቶ አይላ ቆልፎ በበኩላቸው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሥርጭቱ ግልፅ የሆኑ መስፈርቶችን ባለማስቀመጡ ምክንያት በምዝገባው ሂደት ላይ ቅሬታዎች መፈጠራቸውን ጠቁመዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍና ሥርጭት ክትትል ኮሚቴ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ድጋፉ በደቡብ ኦሞ ዞን የኦሞ ሸሽ እርሻ ያርሱ የነበሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በሙሉ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አብርተዋል። ተቋሙ በሐመር ወረዳ በሚገኙት ካራ ዶስ፣ ካራ ሉቡክ እና ካራ ቆርጮ ቀበሌዎች የሚገኙ ሁሉም አርብቶ አደሮች የእርዳታው ተጠቃሚ እንዲሆኑ አቅዶ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል። በተያያዘ ዜና ኮሚቴው ከኛንጋቶም ወረዳ ናሮጎይ ቀበሌ አርብቶ አደሮች ጋር በተከናወነው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሥርጭት ዙሪያ ውይይት አካሂዷል። አርብቶ አደሮቹ እንደገለፁት በቦታ ርቀት ምክንያት መመዝገብ ካልቻሉት በቀር ሁሉም የአካባቢው ነዋሪዎች የእርዳታው ተጠቃሚ ሆነዋል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content

12/2/2016 ዓ.ም ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሾፌር 4ኛ የስራ መደብ ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ጳጉሜ 01 ቀን 2015 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሰረት ጥቅምት 6 ቀን 2016 የጽሁፍ ፈተና ተፈትናችሁ ለተግባር ፈተና ያለፋችሁ ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች በሙሉ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መ/ቤት ተሽከርካሪ ጥገና አስተዳደር ቢሮ የተግባር ፈተና ስለሚሰጥ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡ ማሳሰቢያ የፅሁፍ ፈተና ወስዳችሁ ስማችሁ ያልተገለጸ ተፈታኞች በመንገድ ትራንስፖርት ህግና ደንብ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ያላመጣችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

photo content
+4

የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ለአራት ከተሞች አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበ ነው ……….///……... የቀይ አፈር ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለጂንካ፣ ወይጦ፣ ዲመካ እና ቀይ አፈር ከተሞች በቂና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበ እንደሚገኝ የጣቢያው ባለሙያዎች ገለፁ። የማከፋፈያ ጣቢያው ባለሙያ አስጨናቂ ጀዋኔ እንደገለፁት ጣቢያው ለከተሞቹ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከ10 ዓመት በላይ አስቆጥሯል። በአሁኑ ወቅት ጣቢያው መስጠት ከሚችለው 20 ሜጋ ዋት አቅም ውስጥ በአማካይ እስከ 3 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት ብቻ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበ እንደሚገኝ ባለሙያው ጠቅሰዋል። አቶ ትዕዛዙ ለማ የተባሉ ሌላው የጣቢያው ባለሙያ በበኩለቸው የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ከሳውላ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የሚመጣ አንድ ገቢ መስመር እንዳለው ገልፀው ለአራቱ ከተሞች በ33 ኪሎ ቮልት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። በቅርቡም ለጂንካ ዩኒቨርስቲ ተጨማሪ በ33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመር በማዘጋጀት ኃይል ለመስጠት እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ተናግረዋል። ማከፋፈያ ጣቢያው አንድ ባለ 25 ሜጋ ቮልት አምፔር አቅም ያለው ፓወር ትራንስፎርመር እንዳለው የገለፁት የጣቢያው ባለሙያ አቶ አበባው ቦጋለ ደግሞ ጣቢያው ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ጥያቄዎችን የመመለስ አቅም እንዳለውና ዝግጁ መሆኑን አብራርተዋል። እንደ ባለሙያዎቹ ገለፃ ከዚህ ቀደም ብልሽት ገጥሞት የነበረው ወደ ወይጦ ከተማ የሚሄደው የድንገተኛ ችግር ማሳወቂያ መሳሪያ ተጠግኖ ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content

photo content
+3