cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

Addis abeba Ethiopia

Більше
Рекламні дописи
1 210
Підписники
-124 години
Немає даних7 днів
-1730 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Ethiopia ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢንጂነር አይሻ መሀመድ እና ዶ/ር አብርሃም በላይን የስልጣን ቦታ ቀያየሩ። ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመት ሰጥተዋል። በዚህም ፦ 1. ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር ፣ 2. ዶ/ር አብረሃም በላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚንስትር ፣ 3. ዶ/ር መሀመድ እንድሪስ ደግሞ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል አድርገው ሾመዋቸዋል። ኢ/ር አይሻ መሀመድ በ2011 ዓ/ም የመጀመሪያዋ ሴት የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኃላ 6 ወር እንዳገለገሉ ከቦታው ተነስተዋል። ዶ/ር አብርሃም በ2014 ነበር የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት። ዶ/ር አብርሃም በላይ የአሁኑ ሹመት እስኪሰጥ ድረስ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴርን በሚኒስትርነት እያገለገሉ የነበሩ ሲሆን አሁን በኢ/ር አይሻ መሀመድ ተተክተው የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ሆነዋል።
Показати все...
የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከሎች የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ እየተወጡ እንደሚገኙ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 09 ቀን 2016 ዓ.ም የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አሰልጥኖ ባስመረቃቸው 42ኛ ዙር የኮማንዶ አባላት ምረቃ የዕዙ የማሰልጠኛ ማዕከላት እንቅስቃሴን አብራርተዋል። የኮማንዶ ፣ የአየር ወለድ ፣ የፀረ-ሽብር ፣ የልዩ ሀይል እና የአመራር ትምህርት ቤቶች  ከባቢያዊና አለም አቀፉዊ ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ ለሀገራችን ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ለተቋማዊ ሪፎርሙ የማይተካ ሚናን እየተጫወቱ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የኮማንዶና የአየር ወለድ ዕዝ በስሩ የሚገኙ የስልጠና ማዕከሎች በቀጣይነት አቅማቸውን ለማሳደግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የገለፁት አዛዡ ፣ ዕዙ የአሰልጣኞችን አቅም ለማሳደግ ወደ ተለያዩ ወዳጅ ሀገራት ልኮ እያሰለጠነና በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካላቸው ሀገራትም አሰልጣኞችን በማስመጣት የልምድ ልውውጥ እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል። የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ  ማሰልጠኛ ማዕከል ለአየር ወለድና ለፀረ ሽብር ማሰልጠኛ ማዕከሎች በአካልና በአስተሳሰብ ብቁ የሆኑ ወታደሮችን እያፈራ እንደሚገኝ የገለፁት አዛዡ የፀጥታ አካላትን የማብቃት ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ኮሎኔል ቦጃ አጋ  በምረቃው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የዘንድሮ ተመራቂዎች ለየት የሚያደርጋቸው ሰራዊታችን ያሳለፋቸው የውጊያ ውሎዎች ልምድና ተሞክሮ ተቀምሮ  በተሻሻለ የስልጠና ካሪኩለም መሰልጠናቸው መሆኑን ተናግረው፣ ተመራቂ ኮማንዶዎቹ ለረጅም ወራት በስልጠና መቆየታቸውን ገልፀዋል። በማዕከሉ የሚሰጡ ስልጠናዎች በአካል ብቃትና በወታደራዊ አቅም የጎለበቱ ወታደሮች ከማፍራቱ በተጨማሪ ሀገር ወዳድና ፕሮፌሽናል  ኮማንዶዎችን ለማፍራት በተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤት መገኘቱንም ጠቁመዋል። ተመራቂዎች በማዕከሉ በነበራቸው  ቆይታ ባገኙት አቅም ማንኛውንም ግዳጅ ለመወጣት እንደሚያስችላቸው የገለፁት ኮሎኔል ቦጃ አጋ  ፣ ሰልጣኞች ስለሀገራቸው በጥልቀት እንዲያውቁና አንድነታቸው እንዲጠናከር በአስተሳሰብና በባህሪ ቀረፃ ላይ በትኩረት መሰራቱን ገልፀዋል። የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ኢትዮጵያ የሚል ስያሜ የተሰጣቸውና  ከመከላከያ ሠራዊቱ ፣ ከባህር ሀይልና ከፌዴራል ፖሊስ የተውጣጡና ለረጅም ወራት የሰለጠኑ የኮማንዶ አባላትን የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙና ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት አስመርቋል። ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ ፎቶግራፍ ገነት አወቀ
Показати все...
👍 4
የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ42ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎችን እያስመረቀ ነው የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ42ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች በብላቴ የኮማንዶ እና አየር ወለድ ማስልጠኛ ማዕከል እያስመረቀ ይገኛል፡፡ በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ተመራቂዎቹ “ኢትዮጵያ” የሚል ስያሜ የተሰጣቸው እና ከመከላከያ ሠራዊቱ ፣ ከባህር ኃይል እና ከፌዴራል ፖሊስ ተውጣጥተው ለረጅም ወራት የሰለጠኑ የኮማንዶ አባላት መሆናቸው ታውቋል። በዝግጅቱ ላይ ተመራቂዎች የተለያዩ ወታደራዊ ትዕይንት የሚያሳዩ ሲሆን፣ በእለቱ የክብር እንግዳ እና በኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ንግግር እንደሚደረግ ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
Показати все...
👍 2
👇👇👇👇👇👇👇 subscrib አድርጉን ❤🙏🇪🇹❤🙏 https://www.youtube.com/@Commando_1998
Показати все...
Показати все...
🇪🇹 ኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ🇪🇹 | WhatsApp Channel

🇪🇹 ኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ🇪🇹 WhatsApp Channel. ስለ ባለቀይ ቦኔቶች የግዳጅ ውሎ በስፋት እንዳስሳለን 🙏🇪🇹🙏. 5 followers

"ስለ ኢትዮጵያ እስከሆነ ከጸሃይ በታች አንዳች የሚበግረው እንደሌለ ያስመሰከረ ነው" የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ያልተሸረበበት የተንኮል ጥግ የለም።ያልወረደበት የሃሰት ናዳም እንዲሁ። ጉዳዩ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሆነና ምኞት ወለድ ሆኖ እንዲቀር እውነት አስገደደ እንጂ። እሱ ላይ የተሞከሩ የክፋት ወጀቦች በአንዳንድ  ሀገራት መዓት ጣጣ ፈጥሮባቸው...... ሀገረ-መንግስታዊ ቅስማቸውን ሰብሮ፣ ዜጋ አስበትኖ፣ሰላም እንደ ሰማይ አስርቆ፣ ሰንደቅ አስወርዶ፣በድሮ ናፋቂነት ብርድ ያስመታቸውን ሀገራት እኛን ደጅ ጠንተው ሲጠለሉ አይተናል። በእውነት ሚዛን ላይ የቆመ፣ራስ አስቻይ ሀቅን የተንተራሰ፣ ስሜት የማይንጠው፣ብስለት የሚመራው፣ አሁናዊ ዝማኔን ከዓለማዊ ቴክኖሎጂ ወለድ ተለዋዋጭ አውድ ያስማማ፣ከባቢን ቃኝቶ፣አህጉር ተመልክቶ፣ ዓለምን በዳሰሰ አመክንዮ ተልቆ ሀገር የማተለቅ ብርሃናማ ተቋማዊ ሃሳብ ተግባሩን ለማጨለም ያልተሞከረ የደንቃራ መዓት እና ሟርት ባይኖርም፤እሱ ግን የስኬት ካባ ደርቦ ነበር።አለ።ይኖራል።የሀገሬ የሀገራችሁ ጀግናው ወታደር። የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም አማታሪው፣ፈተናን ወደ ዕድል ቀያሪው፣የትኛውንም አስቸጋሪ ጋሬጣና መሰናክል በማይበርድ የጋለ የሀገር ፍቅር እና ሞያዊ ዲሲፕሊን ብሎም ተዓምራዊ ጀግንነት በድል ጥሶ የሚረማመደው የኢትዮጵያ ወታደር ሀገር የማጽናት ታሪካዊ ሃላፊነቱንና ትውልዳዊ አደራውን የመወጣት ሂደቱ በውል ሲጤን የባላንጣዎቹ ድብቅ መሻት እርቃኑን ፈጦ ይታያል። ጸንቶ ኢትዮጵያን በማጽናት ጀግንነታዊ ተጋድሎው ስለ ጋራ ሀገራችን አንድነትና ሰላም ሲል ስለሚከፍነው መስዋዕትነት ቅንጣት አለማቅማማቱ ሲታሰብ የጽናቱ ጥግ ድረስ መሆን በእጅጉ ይደንቃል። እንደወርቅ በእሳት በተፈተነ ቁጥር በግርማ ሞገስ ከፍ ብሎ፣በድል ደምቆ፣በአሸናፊነት እንዲያንጸባርቅ የሚያደርገው  መቼም የማያወላዳው የጋለ የሀገር ፍቅሩ መሆኑ ለሰከንድ አያጠራጥርም። ለሀገር ኩራት አለኝታው የኢፌዲሪ መከላከያው ጀግና ወታደር አድናቆትና አክብሮት ያለው ህዝብ እልፍ አዕላፍ ነውና ለጥቂቶች ጫጫታ ፊት የሚሰጥ ማንነት ስለሌለው ኢትዮጵያን ከነ ሰንደቋ በልቡ አትሞ ስለ ክብሯ ይዋደቃል። በበረታ ፈተና በእሳት መካከል በድል እየተረማመደ፣ ሀገር ወዳድ ቅን የሆነ ዜጋን ሁሉ እያኮራ፣በገዛ ሀገራቸው አሟራች ለሆኑ ኢትዮጵያ ጠል ባላንጣዎች የማይቆረጠም የብረት ቆሎ እንደሆነ የቀጠለ የሚቀጥልም ነውና እሱን መረታት ከቶውንም የሚቻል አይደለም። በየዘመናት የትውልድ ቅብብሎሽ እሱ ዘንድ በመስዋዕትነት የደረሰችን ኢትዮጵያ ከነሙሉ ክብሯ ለቀጣዩ ትውልድ በኩራት የማሻገር ጀግናዬ ስለ ኢትዮጵያ እስከሆነ ከጸሃይ በታች የሚበግረው አንዳችም ሃይል እንደሌለ ያለፈባቸው በብርቱ መስዋዕትነት በድል ያደመቃቸው መንገዶቹ ህያው ምስክር ናቸው። በአስቻለው ሌንጫ
Показати все...
3
"የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አመራሮች እና የፀጥታ ሀይሉ ጋር  በጋራ በመሆን በተሰራ ስራ የተሻለ ውጤት ማምጣት መቻሉን ብርጋዴር ጀነራል አበባው ሰይድ ተናገሩ "። ጀነራል  አበባው ታደሰ የማእከላዊ ኮማንድፖስት ዋና ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ሹማ አብደታን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችና የሰሜን ሸዋዞንና የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አመራሮች በተገኙበት በተሰሩ የሰላም ስራዎች ላይ በከሚሴ ከተማ ገምግመዋል። ብርጋዲየር ጀነራል አበባው ሰይድ እንደተናገሩት የሁለቱን አጎራባች ዞኖች በጋራ በማድረግ በተደረገ ግምገማ ጥሩ ውጤት  የታየ ሲሆን እስካሁን በሁለቱ ዞኖች አስቸግሮ የነበረ የፀጥታና ደህንነት መደፍረስ የሰላም ማስከበር እንቅፋት የሆኑ የሁለቱን ዞኖች የብሄረሰብ ግጭት በማስመሰል ባለፋት ጊዜያት መንገድ እስከመዘጋት ድረስ የሚያደርስ ሁለቱን ብሄረሰብ የማያቋርጥ ግጭት ለማስገባት በሸኔና ፅንፈኞች  አለመረጋጋት እንዲፈጠር ሲሰሩ ነበር ያሉት ጀነራሉ በዚህም የሁለቱ ዞኖች  አመራሮችና የፀጥታ ሀይሉ ጋር በጋራ በመሆን  በተሰራ ስራ የተሻለ  ውጤት መምጣት መቻሉን ገልፀዋል። የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ እንደገለፁት በተሰጠው አቅጣጫ  የሁለቱ ዞን አመራሮች ችግሮችን እንዲፈቱ በተቀመጠው መሰረት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል።በዚህም የሁለቱን ህዝቦች አንድነት ወንድማማችነት ትስስር የሚያጠናክር የቀጠናውን ሰላም ለማምጣት ሊለውጥ የሚችል ስራ መሰራቱን ገልፀው በዚህም በተሰራ የህዝብ ግንኙነት ሰራ ከ62ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማወያየት መቻሉን ገልፀዉ የህግ ማስከበር ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ በበኩላቸው የማእከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት አጠቃላይ በቀጠናው የተሰሩ የህግ ማስከበር ስራዎች በዝርዝር የተገመገመ ሲሆን አቅጣጫ ተቀምጧል በሁለቱ ህዝቦች ጥርጣሬ እንዲፈጠር ሲሰሩ የነበሩ ፅንፈኞ መኖሩን ገልፀዉ ከሁለቱም ዞኖች  የአመራር ድክመት መኖሩን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው የሁለቱን አጎራባች ህዝቦች ለመለየት የመሳሪያ ነጋዴዎችና ፅንፈኞች ላይ በተሰራ የህግ ማስከበር በሁለቱም በኩል በተሰራው ስራ ችግሮች እንዲፈቱ አመራር በአዲስ የማደራጀት በተሰራ ስራ የህዝባችን  ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በትኩረት  መሰራቱን ተናግረዋል ። መረጃው የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው።
Показати все...