cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የኔ ዕይታ

ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች እስኪ በቀናነት share አርጉ

Більше
Рекламні дописи
348
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከርሶ ጵጵስና ቅድስት ቤተክርስቲያን ትበልጥብናለች የምር እየሄዱ አብራችሁ ስታሽቃብጡ የነበራችሁ ታዋቂ ሰባኪዎች እና ካህናት አሁን ደሞ ምን እንደምትሉን እናያለን ዲ/ን አሸናፊ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"እንጀራ በአዋዜ አለ" አንዳንድ ፎቶዎች እጅግ ልብ የሰብራሉ። እኒህ እናት በራቸው ላይ እንዲህ እጥፍጥፍ ብለው ተቀምጠው ሲታዩ እጅግ ልብ ይሰብራል። ወጥ ሰርተው እንጀራ በወጥ መሸጥ ቢያቅታቸው አቅማቸው ባይችል ባላቸው ነገር ህይወትን ለመግፋት ሞክረዋል። እግዚአብሔር ሆይ እባክህ እናቶቻችንን ጠብቅልን
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አንድ ሴትዮ ነበረች በቤቷ ውስጥ እባብን በጏደኛነት አወዳጅነት ታኖር ነበር:: አብረው ከመኖራቸው የተነሳ እንደ ቤት እንስሳ ትወደው እና ትንከባብከበው ነበር:: ትንሽ ቆይቶ ግን እባቡ የባህሪ ለውጥ አመጣ ምግብ መብላት አቁሞ ከጎኗ ተሸጉጦ መተኛት ብቻ ሆነ:: ሴትዮዋ ተጨነቀችና ብዙ ሞከረች ግን ምንም ለውጥ የለም:: ሴትዮዋም እባቡን የእንስሳት ሀኪም ጋር ወስዳው ችግሩን አስረዳችው:: ምግብ እንደማይመገብ እና ጎኗ ተሸጉጦ ብቻ እንደሚያድር ነገረችው:: ሀኪሙም "እባቡ ምንም አልሆነም🤗 ጎንሽ ተሸጉጦ የሚተኛው የሰውነትሽን መጠን በሆዱ ስፋት እየለካ ነው:: ምግብ የማይበላው ደግሞ አጣጥሞ ሊበላሽ ሆዱን ባዶ እያደረገ ነው:: ስለዚህ ሊበላሽ እያመቻቸሽ ነውና ማዘኑን ትተሽ ተጠንቀቂ" ብሎ አማከራት:: ዌል እንግዲህ ከማን ጋር ነው የምንወዳጀው? ከማን ጋር ነው የምንውለው? ከማን ጋር ነው ህብረታችን? ከማን ጋር ነው ተኝተን በእቅፍ የምንዋደቀው? እርግብ ሆነን ከእባብ እንዲሁም በግ ሆነን ከተኩላ ጋር እየዋልን እያደርን እንዳይሆን🤗🙌🏼 ይህን መልዕክት Zemelak Endrias ነው ያደረሰን! fb account ashenafi mesfin Instagram account @Ashenafi225
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ደጉ_ሳምራዊ "አንድ #ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ #በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ።" "ድንገትም አንድ "ካህን በዚያ መንገድ ወረደ አይቶትም ገለል ብሎ አለፈ።እንዲሁም ደግሞ አንድ #ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ።" "አንድ #ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥ ቀርቦም #ዘይትና_የወይን_ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፥ በራሱ #አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም።" "በማግሥቱም ሁለት #ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና፦ ጠብቀው፥ ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ አለው። አንተ ደጉ ሳምራዊ ቅደም በመንገዴ ጥሎኛል እና ሺፍታ ወንበዴ።
Показати все...
ወጣት መነኩሴ ወደ አባ እንጦንዮስ መጣ። እየተማረረ እንዲህ አለ "አባቴ ሆይ ከመነኮስሁ ዓሥር ዓመታት አለፉኝ። ነገር ግን የዲያቢሎስን ፈተናውን መታገስ አቃተኝ ፣ እጅግ እየታገለኝ ነው" አባ እንጦንስም ለዚህ መነኩሴ የሚገባውን ምክርና ተግሣፅ ሠጥቶ አሰናበተው። መነኩሴው ከወጣ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ አባ እንጦንስ ቀርቦ እንዲህ አለ። "በሕያው እግዚአብሔር እምላለሁ ፣ ይኼ ሰው መመንኮሱንም አላውቅም" እኛ በዲያቢሎስ ተፈተንሁ ለማለት ራሱ ገና ነን ፣ ምክንያቱም የራሳችንን ድካምና ምኞት ገና ድል አልነሣንም። "ምንም እንደ መቅደሱ መንጻት ባይነጻ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን የሚያቀናውን ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው"  (2 ዜና 30: 19) #Ashu (d/n) https://t.me/yeneeyeta
Показати все...
የኔ ዕይታ

ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች እስኪ በቀናነት share አርጉ

እምነት! አንዳንዴ ፈጣሪ ላንተ ያደላ እስኪመስልህ ድረስ ያለፍካቸው ከባድ ጊዜያት አሉ፤ አንተም እንደዚህ ጠንካራ ነኝ እንዴ እስክትል ድረስ ያለፍካቸው ፈተናዎች አሉ፤ አየህ ትክክለኛው ማንነትህ እሱ ነው! ገና ምኑን አይተህ አንተ አማኝ ከሆንክ የማትሻገረው ባህር፤ የማታሳካው ህልም አይኖርም! መሬትን ስትረግጣት የምታምናትን ያህል በፈጣሪህ ታምናለህ? ከዛስ በተሰጠህ አቅም ትተማመናለህ? በቃ ልዩነት የሚፈጥሩት ሁለቱ ጥያቄዎች ናቸው። መልካም ዕለት ይሁንላቹ🙏 #ashu (d/n) https://t.me/yeneeyeta
Показати все...
የኔ ዕይታ

ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች እስኪ በቀናነት share አርጉ

ለማን ብለህ? ለእግርህ የተሰራ ጫማ ትፈልጋለህ እንጂ ለጫማው ስትል እግርህን አትሰራውም፤ ታዲያ ለማን ብለህ ነው የማታምንበትን የምታደርገው? አየህ አንድን ነገር ልብህ ካላመነበት እና አይምሮህ በቂ ምክንያት ካላገኘበት ያንን ነገር ማድረጉ ራስን አለማክበር ነው። ህልምህን ማሳደድ አላማህን መኖር እየቻልክ፤ ልብህ የሚያምንበት ብዙ ነገር እያለ ለሰዎች ስትል ለምን ነገ የሚቆጭህን ዋጋ አሁን ትከፍላለህ? ባልጠፋ ጫማ እግርህን ለምን ታሰቃየዋለህ? መልካም ምሽት 🙏 #asheu (diyakon)
Показати все...
አንድ ፈረስ ብቻ የነበረው አንድ ገበሬ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን፥ ፈረሱ ለግሞ ከቤቱ ያመልጣል። ጎረቤቶቹም እቤቱ መጥተው “ፈረስህ መጥፋቱንና ማዘንህን ሰማን። ልናፅናናህ መጥተን ነው።” አሉት። ገበሬውም “ አላዘንኩም! ለበጎ ነው” አላቸው። ከጥቂት ቀናት በኋላ ፈረሱ ከጠፋበት ቦታ ብዙ ወርቅና ማዕድናት፥ አስለምዶ ከጫነው ሰው አምልጦ ገበሬው ጋ ይመለሳል። ጎረቤቶቹ ወደ ቤቱ መጥተው "እንኳን ደስ አለህ። ፈረስህ ብዙ ወርቅና ብር ይዛልህ በመምጣቱ እንደተደሰትክ ሰምተን መጣን። " አሉት። እሱም "ብዙም አልተደሰትኩም። ለበጎ ነው!" አላቸው። ከጥቂት ጊዜም በኋላም ፈረሱ የብቸኛ ወጣት ልጁ እግር በርግጫው ይሰብረዋል። ጎረቤቶቹም አሁንም መጥተው " የልጅህ እግር መሰበር አይተህ እንዳዘንክ ሰምተን ልናፅናናህ መጣን። " አሉት። እሱም በመቀጠል እንዲህ አላቸው "ብዙም አላዘንኩም። ለበጎ ነው!" ከጥቂት ቀናት በኋላ በሀገሪቱ ከፍተኛ ጦርነት ተከፍቶ፤ ሁሉም ጤነኛ ወጣት በግዴታ እንዲዘምት አዋጅ ተላለፈ። የጎረቤቶቹም ልጆች ሲዘምቱ፤ የእርሱ ልጅ እግሩ ስለተሰበረ ከዘመቻው ይቀራል። ከጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነቱ አለቀ። ከጦርነቱ የተረፈ አንድም ወጣት አልነበረም። ጎረቤቶቹም ልጆቻቸው መሞታቸው ተነገራቸው። ገበሬውም ወደ ሰማይ አንጋጦ "የልጄ እግር መሠበር ለበጎ ሆነለት። ተመስገን!" አለ። ወዳጄ በነገር ሁሉ 'ሁሉም ለበጎ ነው!' በል 😍🙌 https://t.me/yeneeyeta #ashu
Показати все...
የኔ ዕይታ

ሰላም የቻናላችን ቤተሠቦች ይሔ ቻናል ለማስተማር ብቻ ነው ሌላ አላማ የለውም ስለዚሕ በቀናነት share አርጉ

መከፋትትን ነግረኸው በአንተ መከፋት የሚከፋው የሚያዝንልህ ሰው ካለህ በጣም እድለኛ ነህ 💚 መከፋትህን ሳትነግረው በፊት አይቶህ ወይም ከድምፅህ ወይ ከፅሁፍህ የሚረዳ ሰው ካለህ ደግም እጅግ በጣም እድለኛ ነህ 💚 በአንተ ላይ የሆነ ችግር ሲመጣብህ እኔ አለሁልህ የሚል የልብ ወዳጅ ካለህ ከአንተ በላይ እድለኛ የለምና እግዚአብሔር ሆይ አመሰግንሀለሁ ማለትን አትርሳ ያንን ሰው"ም አጥብቀህ ያዥ/ያዝ💚 ሳታመነታ ሁለቴ ሳታስብ ሙትለት ❤ ~መልካም~ምሽት 😍 #ashu
Показати все...
ስስቅ ብታዩኝ ደስ ብሎኝ አደለም ሳቄ ውስጥ በኔ ተስፋ መቁረጥ የሚሞቱ የሚከፉ ብዙ ነፍሶች አሉ አለመኖር ፈልጌ በሰው በመወደዴ ብቻ መትረፌ ሳቄ ውስጥ አለ ሳቄ ውስጥ ከሐኪም ቤት ለ4ተኛ ጊዜ ሲወጣ ብርድ ልብሱ እዚህ ይቅር ብሎ ነርሶችን ያሳቀ ጥቁር ቀልድ አለ በኔ ሳቅ ውስጥ ከፍቅሬ ተጣልቼ ቤቴ ጨንቆኝ ምን ላድርግ እያልኩ መስታወት ድንገት አይቶ የሚያፍር ጅል ነፍስ አለ በኔ ሳቅ ውስጥ የምሰርዘው ብዙ ጥቁር ትዝታ አለ ግን ከልቤ ጥሩ እንድሆን የሰው መከፋት ሰበብ መሆንን እንድጠየፍ ያደረገኝ ማንነትን ወላጆቼ እና ጎረቤቶቼ ሰጥተውኛል "ያልፋል ብዘይገድስ ሂንደርባ" አቦ ብለው በአቦአቸው አስቀውኛል የምስቀው እነሱን እና እናንተን ለማሳቅ ነው እንጂማ ከፊኡኒሎ
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.