cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

THE WORLD

ትኩስ ትኩስ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ይገኛል ➠የተለያዩ የአለምአቀፍ ዜናዎች ➠የተለያዩ አገር አቀፍ መረጃዎች ➠የተለያዩ ቅርንጫፎች ስላሉ ➠በዚህ ስልክ ገብታችሁ ጠይቁ 👇👇👇 0942564198 በፍላጎቶ እናቀርባለን አስታያየት ካሎት@THEWORLDChat2

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
198
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሪፖርት ፦ - በትግራይ አክሱም ከተማ ህዳር 19 እና 20፣ 2013 ዓ.ም በነበረው ውጊያ የኤርትራ ወታደሮች 110 ንጹሃን ሰዎች ገድለዋል። • 70 ሰዎች በአክሱም ከተማ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መንገድ ላይ እያሉ ተደገድለዋል ከሟቾቹ ውስጥ ወታደራዊ የደንብ ልብስ ባይለብሱም በጦርነቱ የተሳተፉ ሰዎች ነበሩ። • 40 ንጹሃን ሰዎች የኤርትራ ወታደሮች ቤት ለቤት ባደረጉት አሰሰሳ ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርገው እና በቤታቸው ውስጥ ተገድለዋል። - በከተማዋ በርከት ያሉ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ደርሷል፥ ከእነዚህም ውስጥ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች፣ ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ብራና ሆቴል ይገኙበታል። - ጠቅላይ አቃቤ ህግ በትግራይ በንጹሃን ግድያና በጾታ ጥቃት ላይ ትኩረት በማድረግ ባካሄደው ምርመራ፣ የወታደራዊ ግዴታ በሌለበት ወቅት በግድያ የተጠረጠሩ 28 የኢትዮጵያ ወታሮች ላይ ክስ መስርቷል። - የጾታ ጥቃት እና አስገድዶ መድፈር የፈጸሙ 25 ወታደሮች ክስ ተመስርቶባቸዋል። * ሙሉ የአቃቤ ህግ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል። #አል_ዓይን #የፌዴራል_ጠቅላይ_አቃቤ_ህግ @THEWORLDNEWS2
Показати все...
#Ethiopia #COVID19 ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 5,095 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 485 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነ ተገኝተዋል ፤ በዚህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 268,520 ደርሰዋል። በ24 ሰዓት ውስጥ የ12 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,060 ደርሷል። የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,584,156 ደርሰዋል። @THEWORLDNEWS2
Показати все...
❤️ LOVE OR MONEY 💴
Показати все...
❤️
💴
እስራኤልና ፍልስጤም ግጭት ከተጀመረ ወዲህ እንደ ትናንት እሑድ በርካታ ሞት የተመዘገበበት ዕለት የለም፡፡ የጋዛ ባለሥልጣናት እንደሚሉት በትንሹ 40 ሰዎች እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት ተገድለዋል፡፡ የእስራኤል ባለሥልጣናት በበኩላቸው የፍልስጤም ተዋጊዎች በድምሩ ሦስት ሺህ ሮኬቶችን አስወንጭፈዋል ይላሉ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ግጭቱ ወደማያባራ ጦርነት እንዳይሄድ ፍርሃት አለኝ ብለዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ በጋዛ የነዳጅ እጥረት እየተከተለ መሆኑ አሳስቦኛል ብሏል፡፡ ምክንያቱም ሆስፒታሎች ኃይል የሚያገኙት ከዚሁ ስለሆነ ነው፡፡ በርካታ ቁስለኛ ባለበት ሁኔታ ሆስፒታሎች ኃይል ከተቋረጠባቸው ለብዙዎች ሞት ምክንያት እንዳይሆን ስጋት አለ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም ማስተባበርያ ዴስክ ምክትል ኃላፊ ሊየን ሀስቲንግስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ለጋዛ ነዳጅ ለማቅረብ የእስራኤል ባለሥልጣናት እንዲፈቅዱ ጠይቀው ተከልክለዋል፡፡ ነዳጅ ለማቅረብ አካባቢው አስተማማኝ እንዳልሆነም ተነግሮናል ብለዋል፡፡ @THEWORLDNEWS2
Показати все...
የፌስቡክ እና ኢንስታግራም መቋረጥ ... የፌስቡክ እና ኢንስታግራም አገልግሎት ከተቋረጠ ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ ሆኖታል። ሁለቱም አገልግሎቶች ግን በVPN እየሰሩ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል። በተጨማሪ ሁለቱም አገልግሎቶች በOpera Browser ያለ ተጨማሪ VPN መተግበሪያ ይሰራሉ። አገልግሎቶቹ የተቋረጡበትን ምክንያት እስካሁን ለማወቅ ባይቻልም ፤ ይህን ፅሁፍ እስከተፃፈበት ደቂቃ ድረስ አይሰሩም። ምናልባትም ባላችሁበት ከተማ አገልግሎቱ ያልተቋረጠባችሁ ልታሳውቁን ትችላላችሁ። @THEWORLDNEWS2
Показати все...
#Ethiopia🇪🇹 ዛሬ 80ኛው ዓመት የኢትዮጵያውያን አርበኞች የድል በዓል እየተከበረ ይገኛል። የአርበኞች የድል በዓል ለምን ይከበራል ? ጣሊያን የአድዋን ድል ለመበቀል በሚል በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤኒቶ ሙሶሎኒ አማካኝነት፥ ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያን ወራ ነበር። በወቅቱ የነበሩት ኢትዮጵያውያንም ወራሪውን ሀይል ለአምስት ዓመታት በጽናት ታግለው 1933 ዓ.ም ድል ነስተውታል። የወቅቱ አርበኞቻችን ለሀገራቸው ነጻነት የከፈሉትን መስዋዕትነት እና ያስገኙትን ድል ለማሰብም ነው በየአመቱ ሚያዚያ 27 የኢትዮጵያ አርበኞች የድል በዓል የሚከበረው። እንኳን አደረሳችሁ ! @THEWORLDNEWS2
Показати все...
❤️ LOVE OR LAUGH🤣
Показати все...
❤️
🤣
"...ኢትዮጵያ የስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን" - ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ፥ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው የተነሱባት አገር በመሆኗ ኢትዮጵያን ለማዳን ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል ሲሉ ተናገሩ። ይህ ሲሉ የተሰሙት ዛሬ ቢሾፍቱ በነበረው መርሃ ግብር ላይ ነው። ኢትዮጵያ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን ያሉት ጄነራል ብርሃኑ፥ እነዚህ ጠላቶች አገሪቷን በማዳከም ከችግር እንዳትወጣ፣ ታላቅነቷን አስጠብቃ እንዳትሄድ እየሰሩ ነው ብለዋል። በዚህም በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የሚፈጠሩትን ግጭቶች ሰራዊቱ በየቦታው እየሄደ እያመከነ ይገኛል ነው ያሉት። ይህ ሁሉ ትንኮሳ፣ ማናቆር እና ህብረተሰቡን እርስበርሱ ማባላት ኢትዮጵያን ለማዳከም ነው ሲሉ ተደምጠዋል። የዚህ ፍላጎት ሀገሪቷ ስትዳከም ባላት ሃብት እንዳትጠቀም ለማድረግ መሆኑ ገልፀዋል። ጠ/ኤታማዦር ሹሙ ፥ "ከ100 ዓመታት ጀምሮ ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚሰሩ ኃይሎች ዛሬ ተጠናክረው አገራችን ላይ ዘምተዋል" ብለዋል። ባንዳዎችን ይዘው አገር ለማፍረስ እየተንቀሳቀሱ ያሉትን እነዚህን ኃይሎች በውጭ ወራሪ እንደማንቻል ስለሚያውቁ ከውስጣችን ሊያፈራርሱን ያስባሉ ሲሉ ተናግረዋል። ህዝቡ ከሰራዊቱ ጎን በመቆም የተደገሰውን ለማክሸፍ መታገል ይኖርበታል ሲሉም ነው ያሳሰቡት። ጄኔራል ብርሃኑ ፥ "ኢትዮጵያን ለማዳን ሁላችንም አንድ መሆን ይገባናል ፤ ተሳስተው የጠላት መሳሪያ የሆኑ አካላትም ቆም ብለው ማሰብ እንደሚገባቸውና ለሃገራቸው ጥፋት እየደገሱ ለሌሎች ታሪካዊ ጠላቶች በር መክፈት የለባቸውም" ብልዋል። @THEWORLDNEWS2
Показати все...
#Update የሱዳን ወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ልዑካቸው ካርቱም ኤርፖርት ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ወቅት ከአብዱል ፈታህ አልቡርሃን በተጨማሪ ዶክተር መርየም ሰዲቅ አልመሀዲ እና በሱዳን የኤርትራ ኤምባሲ አባላት ተገኝተው ነበር። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሁለት ቀን የስራ ጉብኝታቸው በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል። @THEWORLDNEWS2
Показати все...
#Update የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ ሒደት ያልተጀመረባቸው የምርጫ ክልሎችን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጠ። ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ በተወሰኑ ምርጫ ክልሎች ላይ መዘግየቱ አስታውሷል። ከክልል መስተዳድር አካላት ጋር አደረኩት ባለው ከፍተኛ የሆነ የትብብር ስራ የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው ቦታዎች የመራጮች ምዝገባን ለማስጀመር ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ ገልጿል። በዚህም መሰረት የመራጮች ምዝገባ ከሚያዝያ 29 ቀን 2013 እስከ ግንቦት 13 ቀን 2013 ድረስ በልዩ ሁኔታ እንዲከናወን ተወስኗል ብሏል። በዚህም ፦ • በምእራብ ወለጋ ዞን (ለቤጊ እና ሰኞ ገበያ ምርጫ ክልል ውጪ) • በምስራቅ ወለጋ ዞን (ከአያና እና ገሊላ ምርጫ ክልል ውጪ) • በቄለም ወለጋ ዞን • በሆሮ ጉድሩ ዞን (ከአሊቦ፣ ጊዳም እና ኮምቦልቻ ምርጫ ክልል ውጪ) ከሚገኙት 31 ምርጫ ክልሎች መካከል በ24ቱ ላይ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በከማሽ ዞን ከሚገኙት አምስት የምርጫ ክልሎች በአራቱ የመራጮች ምዝገባ (ከሴዳል ምርጫ ክልል ውጪ) ከላይ በተጠቀሱት ቀናት እንዲከናወን መወሰኑ ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ የመራጮች ምዝገባ በጸጥታ ችግር የተነሳ ሳይከናወንበት የነበረው የአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔር ልዪ ዞን የሚገኙት ዳዋ ጨፌ፣ ጨፋ ሮቢት እና ባቲ ምርጫ ክልሎች በተመሳሳይ ሁኔታ የመራጮች ምዝገባ ከሚያዝያ 29 - ግንቦት 13 ቀን 2013 ድረስ ይከናወናል ተብሏል። @THEWORLDNEWS2
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.