ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Відкрити в Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Показати більше608
Підписники
-124 години
-37 днів
-1130 днів
Архів дописів
ኅዳር 22 /፳፪/በዚች ቀን ቅዱሳን ቆዝሞስና ድምያኖስ ወንድሞቻቸውም አንቲቆስ ዮንዲኖስ አብራንዮስ በሰማዕትነት አረፉ። እሊህም ድዮማ ከምትባል ከተማ ስለ እግዚአብሔር ልጅ የታነፀች ግምብ ከአለችበት አረምያ ከምትባል አገር ናቸው። እናታቸውም ቴዎዳዳ እግዚአብሔርን የምትፈራና የምትራራ መጻተኞችንና ዶኆችን የምትወዳቸው የምትረዳቸው ናት አባታቸውም ከሞተ በኋላ ልጆቿን እያስተማረች አሳደገቻቸው። እሊህም ሁለቱ ቆዝሞስና ድምያኖስ የሕክምና ጥበብን ተምረው በሽተኞችን ያለ ዋጋ የሚፈውሷቸው ይልቁንም ድኆችን አብዝተው የሚረዷቸው ሆኑ። ወንድሞቻቸው ሦስቱ ግን ወደ ገዳም ሒደው መነኰሱ በጾምና በጸሎትም ተጠመዱ። ከአባ አጋግዮስ አደራ በአስጠበቀው በንጉሠ ቊዝ ልጅ ምክንያት ዲዮቅልጥያኖስ ክዶ የረከሱ ጣዖታትን በአመለከ ጊዜ በምእመናን ላይ መከራ ሆነ። ቆዝሞስና ድምያኖስ በሀገሩ ሁሉ ስለ ክርስቶስ እነርሱ እንደሚያስተምሩ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ወደእርሱ እንዲአቀርቧቸው አዘዘ በደርሱም ጊዜ ለአገረ ገዢው ለሉልዮስ እንዲአሠቃያቸው ሰጠው። እርሱም ከሦስቱ ወንድሞቻቸው ጋር በብዙ ሥቃዮች አሰቃዩአቸው። ቴዎዳዳ እናታቸውም አንገቷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትንት አክሊልንም ተቀበለች የህርማኖስ ልጅ ቅዱስ ፊቅጦርም ሥጋዋን ገንዞ ቀበራት። ንጉሡም እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸ ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ከመከራውም ዘመን በኋላ ቤተ ክርስቲያን ተሠርታላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእርሳቸውም ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የቅዱሳንም በረከታቸው ይደርብን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
❤ ከዚህም በኋላ አገሪቱን ማጥፋትን ስለ አባ ዮሐንስ ይተው ዘንድ መልሱን ለመኰንኑ ንጉሡ ጽፎ ደብዳቤዋን ወደ ደመናው ወረወራት የተሰበሰቡትም እያዩ እጅ ተቀበለችውና ወደ ደመናው ገባች ወዲያውኑ አባ ዮሐንስ በዚያች ደመና ወደበዓቱ ተመለሰና በማግሥቱ ያቺን ደብዳቤ ለመኰንኑ ሰጠው በላይዋም የንጉሡ ፊርማውና ማኅተሙ አለ በአያትና በአነበባት ጊዜ ደነገጠ አደነቀም ስለ አገሪቱ ድኅነትም እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ አገሩ ተመለሰ። የንጉግሥ ዘመድ የሆነች የከበረች ሴት ዜናውን በሰማች ጊዜ ከደዌዋ ይፈውሳት ዘንድ ወደርሱ መጣች በጸሎቱም ተፈወሰች።
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ በሞተ ጊዜ መናፍቁ መርቅያን ነገሠ። ቅዱስ አባ ዲዮስቆሮስንም አሠቃየው። የቀናች ሃይማኖትን ስለመለወጡ አባ ዮሐንስ እየዘለፈና እየረገመው ወደ ርሱ ደብዳቤ ላከ ከጥቂት ወራትም በኋላ እግዚአብሔር ቀሠፈው። ለእርሱም ዕድሜው መቶ ሃያ አምስት ዓመት ሲሆነው ዕረፍቱ እንደደረሰ አወቀ እየጸለየም ግምባሩን በምድር አስነክቶ ሰገደ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ ከመቃብሩም ቊጥር የሌላቸው ድንቆች የሆነ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 21 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለኪ_ማርያም_እምነ። ዘሰመናይናኪ ጸወነ። ሶበ እምርኁቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ። ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየሐይድ ዐይነ። ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የኅዳር _21።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ። ወተናገሩ በውስተ ማኅፈዲሃ። ደዩ ልበክሙ ውስተ ኃይላ"። መዝ 47፥12። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 23፥1-ፍ.ም።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ለጽዮን። ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ። ዛት ይዕቲ ምዕራፍየ ለዓለም"። መዝ 131፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 6፥12-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥5-11 እና የሐዋ ሥራ 7፥44-59። የሚነበበው ወንጌል # ማቴ 21፥42-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጽዮን ማርያም በዓልና የጾም ጊዜ ። ለሁላችንም ይሁንልን።
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta):
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ኅዳር ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን #ለእናታች_ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_ታቦተ_ጽዮን የፊልስጥኤማውያን ጣዖት ዳጎንን ለሰባበረችበት (ታሪኩ በመጽሐፍ ቅዱስ # 1ኛሳሙ 5)፣ #ወደ_ኢትዮጵያ_ገብታ_አክሱም ለመጀመርያ ጊዜ ለከበረችበትና ታቦተ ጽዮን ከነበረችበት ድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት #በተአምራት_አብርሃና_አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በመንፈስ ቅዱስ ገብታ ለተገኘች ለዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና ለኢትዮጽያዊው ጻድቅ #ለአቡነ_ተወልደ_መድኅን ለበዓላቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሮሜ አገር ከሆነ ተአምራት ከሚያደርግ (ከገባሬ መንክራት) #ከቅዱስ_ጎርጎርዮስ ዕረፍት፣ ከእስክድርያ ሃምሳ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_ቆዝሞስ ዕረፍት ከእስሙናይ አገር ሰማዕታት #ከእልፍዮስ_ከዘኬዎስ_ከሮማኖስ፣_ከዮሐንስ፣ #ከፊቅጦርና_ይስሐቅ ከመታሰቢያቸው፣ ከብርሌና ከብርጭቆ ሠሪዎች ልጅ ከሆነ ከአስዩጥ ሀገር #ከቅዱስ_አባት_ከአባ_ዮሐንስ_ዕረፍትና፣ ጫብሬ ከምትባል ከአገር ድልበት #ከቅድስት_ዲቦራ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን #የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል_ማርያም_የበዓልዋ_መታሰቢ ነው። በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የሮሜ_አገር_የሆነ_ገባሬ_መንክራት #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የቀናች ሃይማኖትንም ተምሮ እውነተኛ ክርስቲያን ሆነ። ከዚህም በኋላ የዚህን ዓለም ኃላፊነት የማታልፍ የመንግሥተ ሰማያትንም ኑሮ አሰበ ኀሳቡንም ሁሉ ስለ ነፍሱ ድኅነት አደረገ።
❤ የዚያችም አገር ኤጲስቆጶስ በኤጲስቆጶስነት ሥራ ይረዳው ዘንድ ለመነው እርሱ ግን አልፈቀደም ከውዳሴ ከንቱ የሚሸሽ ሁኗልና ወደ ገዳምም ገብቶ ጽኑዕ የሆነ ተጋድሎንም መጋደል ጀመረ። የዚችም አገር ኤጲስቆጶስ በዐረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶስ የሚያደርጉት ፈልገው አጡ ስለዚህም ተሰብስበው ሳሉ የመለኮትንም ነገር የሚናገር ጎርጎርዮስ ከእርሳቸው ጋር ሳለ ገዳማዊ ጎርጎርዮስን ፈልጋችሁ በእናንተ ላይ ሹሙት የሚል ቃል ከሰማይ ወደ እነርሱ መጣ። በበረሀም ውስጥ በፈለጉት ጊዜ አላገኙትም እየፈለጉትም ብዙ ቀን ኖሩ እርሱ ግን በአቅራቢያቸው ይኖር ነበር። ባላገኙትም ጊዜ በአንድ ምክር ተስማምተው በሌለበት ወንጌል ይዘው በላያቸው ኤጲስቆጶስነት ሾሙት ስሙንም የመለኮትን ነገር በሚናገር በጎርጎርዮስ ስም ጎርጎርዮስ ብለው ሰየሙት።
❤ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ተገልጦ "ተነሥተህ ወደ እነርሱ ሒድ እነሆ በላያቸው ኤጲስቆጶስነት ሹመውልሃልና ይህም ከእግዚአብሔር የሆነ ነው" አለው። ያን ጊዜም ወደ እነርሱ ወረደ የአምላክን ትእዛዝ መተላለፍ ፈርቷልና በአዩትም ጊዜ ወጥተው በታላቅ ክብር ተቀበሉት የሹመቱንም ሥርዓት ፈጸሙ። እግዚአብሔርም ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ተአምራትን በእጆቹ ገለጠ ስለዚህ ገባሬ መንክራት ጎርጎርዮስ ተብሎ ተጠራ።
❤ ከብዙዎች ተአምራቱም አንዲቱ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ ከእርሷም ብዙ ዓሣዎችን የሚያጠምዱባት ታናሽ ባሕር ነበረቻቸው አንዱም አንዱ የኔ ናት በማለት እርስ በርሳቸው ተጣሉ ስለዚችም ባሕር በመካከላቸው ይፈርድ ዘንድ ወደ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ለመሔድ ተስማሙ እርሱም ከሁለት ተካፈሉ ብሎ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም ባልተስማሙ ጊዜ ስለዚች ባሕር እግዚአብሔርን ለመነው በዚያንም ጊዜ ባሕሪቱ ደርቃ የምትታረስ ምድር ሆነች ስለሚደረጉ ድንቆች ተአምራቴ ዜናው በሁሉ አገር ተሰማ በጎ አገልግሎቱንም ከፈጸመ በኋላ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ቅዱስ አባት በገባሬ መክራት ጎርጎርዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የብርሌና_የብልጭቆ_ሠሪዎች_ልጅ #አባ_ዮሐንስ፦ ይህንም ቅዱስ በወለዱት ጊዜ በበጎ ተግሣጽ አሳደገውታል የጥርብ ሥራንም አስተማሩት ከጥቂት ዘመናትም በኋላ አባቱና እናቱ ዐረፉ። ያን ጊዜ ወደ ቅዱስ ኢስድሮስና ወደ አባ ባይሞን ዘንድ ሒዶ መነኰሰ በጾምና በጸሎት በገድል ሁሉ ተጠምዶ ተጋደለ ዜናውም በራቀ ገዳማት ሁሉ ተሰማ።
❤ ከዚህም በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጠለት ወደ አገሩ ሒዶ ወገኖቹን የጽድቅን ጎዳና ይመራቸው ዘንድ አዘዘው። ቅዱስ ቊርባንንም ሳይቀበል ከበዓቱ የማይወጣ ሆነ። በአንዲት ዕለትም ሁለት ቅዱሳን አረጋውያን አባ አብዢልና አባ ብሶይ ወደርሱ መጡ ገና ወደርሱ ሳይቀርቡ ከሩቅ ሳለ ስማቸውን በመጥራት ሳያውቃቸው አባቶቼ ለመምጣታችሁ ሰላምታ ይገባል ብሎ ተናገረ እጅግም አደነቁት አባ ሲኖዳም ከግብጽ አገር እየመጣ ብዙ ጊዜ ይጎበኘው ነበር።
❤ የከዳተኞችም ጠብ በግብጽ አገር ላይ በተነሳ ጊዜ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ የላከው የጦር መኰንን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጣ። በጸሎቱም ይረዳው ዘንድ ለመነው ቅዱስ ዮሐንስም መስቀሉን አንሥቶ መኰንኑን "አይዞህ አትዘን አንተ ጠላቶችህን ድል ታደርጋለህና"፧ አለው እንደ ቃሉም ሆነ። ዳግመኛም በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ላይ ጠላት በተነሣበት ጊዜ ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ላከ እርሱም "አትዘን ጠላትህን ታሸንፋለህ" አለው ያን ጊዜም ጠላቶቹን አሸነፈ።
❤ ከዚህም በኋላ በእነዚያ ወራት ንጉሥ ቴዎዶስዮስ የርኵሰትን ሥራ ስለ ሠሩ የአስዩጥን ሰዎች እንዲገድላቸው ሀገራቸውንም እንዲአጠፉ አዘዘ። ንጉሡም የላከው መኰንን ሳይደርስ የእግዚአብሔር መልአክ ይህን ነገር ለአባ ዮሐንስ አሳወቀው የአገርም ሰዎች የንጉሡን ትእዛዝ በሰሙ ጊዜ ወደ አባ ዮሐንስ ገዳም ወጥተው ስለ መጥፋታቸው በፊቱ አለቀሱ አባ ዮሐንስም "አትጨነቁ አይዟችሁ እግዚአብሔር ያድናችኋላና" አላቸው። መኰንኑም በመጣ ጊዜ ከእርሱ በረከትን ይቀበል ዘንድ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሰ አባ ዮሐንስም ንጉሡ ያዘወውን ሁሉ ነገረው መኰንኑም ሰምቶ ደነገጠ ለቅድስናውም ተገዢ ሆነ ለመኰንኑም ርኵስ መንፈስ ያደረበት የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረው ያድንለት ዘንድ ቅዱስ ዮሐንስን ለመነው በዚያንም ጊዜ ዘይትን ቀብቶ አዳነው።
❤ ከዚህም በኋላ የአስዩጥ ሰዎችን መገደላቸውን እንዲተው ወደ ንጉሥ ይጽፍለት ዘንድ መኰንኑን አባ ዮሐንስ ለመነው መኰንኑም ጽፎ ለአባ ዮሐንስ ሰጠው አባ ዮሐንስም ተቀብሎ ወደ ዋሻው ገባ ወደ ጌታችንም ጸለየ ብርህት ደመናም መጣች ተሸክማም ወደ ንጉሡ አደሰገችው ያን ጊዜም ንጉሥ ከማዕድ ላይ ነበረ ያንንም ደብዳቤ ከወደላይ ጣለለት ንጉሡም አንሥቶ በአነበበው ጊዜ ከመኰንኑ የተጻፈ እንደሆነ በመካከላቸው በአለ ምልክት ተሸፎ አገኘው የተጻፈውም ቃሉ ስለ አባ ዮሐንስ ልመና ሀገሪቱን ማጥፋትን እንዲተው የሚል ነበር ቀና ባለ ጊዜም ደመና አየ ንጉሡም አደነቀ።
ኅዳር ፳ /20/በዚች ቀን ቅዱስ አባት አንያኖስ አረፈ እርሱም ለወንጌላዊ ማርቆስ ሁለተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ነው። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ አረማውያን ናቸው እርሱም ጫማ ሰፊ ነበር ቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስም ወደ እስክንድርያ አገር መጀመሪያ በገባ ጊዜ እግሩን ተደናቅፎ ጫማው ተቆረጠ እንዲሰፋለትም ወደ ጫማ ሰፊ አንያኖስ ዘንድ ሔደና ጫማውን ሰጠው መስፋትም በጀመረ ጊዜ መስፊያው ጣቱን ወጋው በዮናኒም ቋንቋ አታኦስ አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም የእግዚአብሔርን ስም ሲጠራ በሰማ ጊዜ ደስ ብሎት የክብር ባለቤት ክርስቶስን አመሰገነው። ከዚህም በኋላ ወንጌላዊው አንያኖስን አዳነው። አንያኖስም ወደ ቤቱ ወሰደውና ብዙ ነገር ይጠይቀው ጀመር። ቅዱስ ማርቆስም ስለቀናች ሃይማኖት አስተማረው የአንያኖስም ልቡ ብሩህ ሆኖለት በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ከቤተሰቡ ሁሉ ጋር ተጠመቀ። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላያቸው ወረደ አዘውትሮ በመጠመድ የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ትምህርት የሚሰማ ሆነ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ሕጓንና ሥርዓቷንም ተማረ። ቅዱስ ማርቆስም ወደ ሌሎች አገሮች በሔደ ጊዜ እጆቹን በአንያኖስ ላይ ጭኖ ሊቀ ጵጵስና ሾመው እርሱም ብዙዎችን አስተምሮ አጠመቃቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ቤቱንም ቤተ ክርስቲያን አደረጋት እርሷም በስተምዕራብ ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ ያለች ዛሬ የሰማዕት ቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሁና የታወቀች ናት። ይህም አባት በወንጌላዊ ወንበር ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ኅዳር ፲፱ (19) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ለዓለም_ብርሃን ለሆኑት እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው #ከሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ_ጋር_የሥላሴን_መንበር ላጠኑት #ለአቡነ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት_ለልደታቸው በዓል #እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት፦ አባታቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊት እናታቸው ዳግም ሞገሳ ይባላሉ፡፡ ትውልድ ሀገራቸው ወሎ መቄት እንጂፋ ነው፡፡ አባታችን አባ ዮሴፍ ኅዳር 19 ቀን ሲወለዱ በርካታ ሙታን ተነሥተዋል፡፡ ይህም ቅዱስ ያዩትና የሰሙት እስቲያደንቁት ድረስ በአባቱ ቤት ሳለ የዚህን ዓለም ጥበብ ሁሉ ተማረ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ተረጐመ ከዚህም በኋላ ዲቁና ሾሙት።
❤ የነፍሱንም ድኅነት እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ብርሃናዊ መልአኩን ቅዱስ ሚካኤልን ላከለትና "ዮሴፍ ሆይ ይህን ኃላፊውን ዓለም ትወድዋለህን አስጸያፊ አይደለምን በውስጡም ያለ ሁሉ" አለው። ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ እርሱ የመረጠውን መንገድ ይመራው ዘንድ #እግዚአብሔር እየለመነ ጾምና ጸሎትን ጀመረ።
❤ ከወለቃ አውራጃም ስሙ አባ ዘካርያስ የሚባል ነበረ እርሱም ለዮሴፍ ዘመዱ የሆነ በጭልታም ዮሴፍን ወስዶ የምንኵስና ልብስ አለበሰው። ወደትግራይ ምድርም ወስደውና በዚያ ተግባረ እድ ለምንኵስና ሥራ የሚገባ ጽሕፈትን ስፌትን ተማረ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ በረሀ ዱር ገብተው የእንጨት ፍሬ እየበሉ ከዝኆኖች ከአንበሶችና ከዘንዶዎች እየተፈተኑ በየአይነቱ በሆነ ተጋድሎ በመድከም ኖሩ። በጽድቃቸውም ኃይል ብዙ ተአምራትን አደረጉ አባ ናትናኤልም የጋለ ምንቸት በመሐል እጁ ይዞ በመነኰሳቱ ፊት ዞረ። አባ ዮሴፍም የሚያበስሉበት ማሰሮ በተሰበረ ጊዜ ወጡ ሳይፈስ አገናኝቶ እንደ ቀድሞው አደረገው። ገብረ ኄርም ሕዝባዊ ሲሆን በሞተ ጊዜ ሊአጠምቁት ሲሉ " #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኤጲስቆጶስነት ሹሞኛልና እኔ በእጄ አጠምቃችኋለሁ" አላቸው። እሊህም ቅዱሳን የትሩፋታቸውንና የጽድቃቸውን የአማረ ሥራቸውን አሳዩ።
❤ ከዚህም በኋላ አባ ዮሴፍን ወደ ጳጳስ ወሰዱትና ቅስና ተሾመ። አባ ዘካርያስም በዐረፈ ጊዜ አባ ዮሴፍ ወደ ሌላ ገዳም ሒዶ ሳይቀመጥ ቁሞ አርባ መዓልትም አርባ ሌሊት ጾመ። ከድካም ጽናትም በወደቀ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል አነሣው። ሁለተኛም ከገደል አፋፍ እጁን ዘርግቶ ሳይሰበስብ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ቆመ። ሰይጣንም መጥቶ ወደ ቆላ ወረወረው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ተቀብሎ ወደ መቆሚያው መለሰው። ደግሞም ከደንጊያ ወሻ ውስጥ ገብቶ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ያለ መብልና ያለ መጠጥ ኖረ። ሰይጣናትም ወደርሱ እየመጡ በየራሳቸው ምትሐት በማሳየት ያስፈራሩት ነበር መላእክትም ያበረቱትና ያጸኑታል። ናላው በአፍንጫው እስቲፈስ ድረስ በየእልፍ እልፍ እየሰገደ ኖረ።
❤ ከዚያም የትራይን አውራጃዎች ሁሉ ዞረ። ወደ ሰሜንም ምድር ተሻግሮ ከቅዱስ ያሬድ መቃብር ገባ በደጃፉም ላይ ተቀርጾ አግኝቶ አንቀጸ ብርሃን ተማረ። ሲመለስም ሽፍቶች አግኝተውት በደንጊያ ወገሩት በበትርም ደበደቡት በጦርም ወግተው ጥለውት ሔዱ። አምላክን የወለደች እመቤታችንም ቅድስት #ድንግል_ማርያም ወደርሱ መጥታ አዳነችው። አንዲት ቀንም የሴት በድን አግኝቶ በላይዋ ባማተበ ጊዜ ተነሣች።
❤ ወደ ኢየሩሳሌምም ሦስት ጊዜ ሒዶ ከከበሩ ቦታዎች ተባርኳል ወደ አባቶቻችን ሐዋርያት መቃብም እስከ አገረ ባርቶስና ሕንደኬ ደረሰ። ውኃው ከመላበት ወንዝም በሚደርስ ጊዜ በላዩ አማትቦ እንደ የብስ በእግሩ እየረገጠ ይሻገረዋል። አንበሶችና ነብሮች ይከተሉታል ምግብ በአጡ ጊዜ ድንጊያውን ባርኮ ሥጋ አድርጎ ይሰጣቸዋል።
❤ ከዚህ በኋላም ወደ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ገዳም ደብረ ሊባኖስ ሔደ። ከአባ ተወልደ መድኅንም እጅ አሰሰኬማ ተቀበለ። አባ ተወልደ መድኅንም ሊፈትነው ወዶ ሰባት የጽድ ቅርንጫፍ ሰብሮ ትከለው ብሎ ሰጠው በተከላቸውም ጊዜ ወዲያውኑ በቅለው አደጉ እስከ ዛሬም አሉ። ብዙዎችም ወደርሱ መጥተው በእርሱ እጅ መነኰሱ #እግዚአብሔር_አብና አምላክን በወለደች በእመቤታችን #ድንግል_ማርያም ስም በአነፃቸው አብያተ ክርስቲያን በአንድነት ኖሩ።
❤ በአንዲት ዕለትም እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም ዕጣንን ሰጠችውና ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋራ የአሸናፊ የ #እግዚአብሔርን መንበር አጠነ። ብዙ ጊዜም ወደርሱ ሐዋርያት እየመጡ ይባርኩታል። በአንዲት ዕለትም ነብር ከእናቱ እጅ ሕፃንን ነጥቆ ወሰደ በአባ ዮሴፍም ስም በአማጸነችው ጊዜ በሦስተኛው ቀን መለሰላት።
❤ ለልጆቹም ገንዘብም ሆነ የእንስሳ ጥሪት እንዳያደርጉ ሥጋ እንዳይበሉ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ ትሕትናን ቅንነትን እንዲማሩ ከንቱ ነገር ቧልትን እንዳይናገሩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዳይስቁ ይህ ሁሉና የመሳሰለውን ሥርዓትን ሠራላቸው።
❤ ከዚህም በኋላም ሩጫውን በፈጸመ ጊዜ ግንቦት19 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈ ደብረ ታቦር ብሎ በሰየማት ቤተ ክርስቲያንም ተቀበረ ከእርሱም ቊጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለ #እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሴፍ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ምንጭ፦ የግንቦት19 ስንክሳር።
ኅዳር ፲፰ /18/በዚችም ዕለት ከሮሜ አገር ቅዱስ ኤላውትሮስና እናቱ እንትያ በሰማዕትነት አረፉ። ይህም ቅዱስ እግዚአብሔርን ከሚፈራ አንቂጦስ ከሚባል ኤጲስቆጶስ ዘንድ አደገ። በዚያንም ወራት ንጉሥ እንድርያኖስ ወደ ሮሜ አገር መጣ ስለ ኤላውትሮስም ሰምቶ ወደርሱ ያመጣው ዘንድ ፊልቅስን አዘዘው ፊልቅስም በሔደ ጊዜ ቅዱሱን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ሲያስተምር አገኘው። ፊልቅስም ትምርቱን በሰማ ጊዜ በጌታችን አምኖ ተጠመቀ። ንጉሱም ኤላውትሮስንም ወደ ንጉሥ እንድርያኖስ በአደረሱት ጊዜ ክርስቶስን እንዲክድ ጠየቀው ባልሰማውም ጊዜ በጽኑ አሰቃየው ነገር ግን ጌታ ከእርሱ ጋር ነው እና አንዳች አልሆነም ነበር። ቆሊሪቆስ የሚባለውም መኰንን አይቶ በቅዱስ ኤላውትሮስ አምላክ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። ከዚህም በኋላ ፈረሶችን አምጥተው ቅዱሱን በገመድ አሰሩት ጌታም መልአኩን ልኮ ማሠሪያውም ፈትቶ ወደ ከፍተኛ ተራራ ወሰደው በዚያም እግዚአብሔርን እያመሰገነ ከአራዊት ጋር ተቀመጠ። የንጉሱ ወታደሮች ለአደን በሔዱ ጊዜ ቅዱሱን አግኝተው ወደ ንጉሱ ወሰዱት። ንጉሡም ለአንበሳ እንዲሰጥ አዘዘ አንበሶችም የፊቱን ላብ ጠረጉለትና እግሮቹን ሳሙ ከዚህም በኋላ ተመልሰው ከአረማውያን መቶ ሃምሳ ሰው ገደሉ እንድርያኖስም አይቶ ቁጣን ተመላ። ሁለት ወታደሮችን ከእንትያ እናቱ ጋር በጦር እንዲወጉት አዘዘ እርሷንም ብዙ ከአሠቃይዋት በኋላ የልጅዋን አንገት እንዳቀፈች ከእርሱ ጋር ወጓት ነፍሳቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
ኅዳር ፲፯ /17/
በዚች ቀን ታላቅና ክቡር የሆነ የዓለሙ ሁሉ መምህር የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት የዮሐንስ አፈወርቅ ሥጋው የፈለሰበት ነው።
ይህም እንዲህ ነው መበለቲቱን ቦታዋን በግፍ ነጥቃታለችና እርሱም እንድትመልስላት ቢያዛት ስለ አልሰማችው ስለ መበለቲቱ ቦታ ቅዱስ ዮሐንስ ንግሥት አውዶክስያን በአወገዛት ጊዜ በእርሱ ላይ ተቆጣች ሰይጣንም በልቧ አደረና ስለ ክፉ ሥራቸውና ስለ በደላቸው አውግዞ የለያቸውን ኤጲስቆጶሳት በእርሱ ላይ ሰበሰበች።
እነርሱም ስለ መሰደዱ ከእርሷ ጋር ተስማምተው አድራኮስ ወደምትባል ደሴት አጋዘችው በዚያም ጥቂት ዓመታት ኑሮ ወደ መንበረ ሲመቱ ተመለሰ። ከዚህም በኋላ ዳግመኛ መናፍቃን የሆኑ ኤጲስቆጶሳትን ሰበሰበችና ወደ አርማንያ አጋዙት ከዚያም በረሀ ወደ ሆነ ሩቅ አገር ሰደዱትና በዚያ አረፈ።
የአርቃዴዎስም ልጅ ታናሹ ቴዎዶስዮስ በነገሠ ጊዜ መልክተኞችን ልኮ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ብዙ በመዘመርና በማመስገን በታላቅ ክብር ወደ ቊስጥንጥንያ አፍልሶ አስመጣው ይህም ከዕረፍቱ በኋላ በሠላሳ አምስት ዓመት ነው። በሌላ በቅብጢ መጽሐፍ በግንቦት ወር ሃያ ሁለት ቀን እንደ ደረሰ ይናገራል በሮማውያን መጽሐፍ ግን በየካቲት ወር ሃያ ሁለት ቀን ተባለ የዕንቊ ፈርጾች ባሉት የዕብነ በረድ ሣጥን ውስጥ አድርገው ወደ ቤተ መቅደስ አስገቡት ከሥጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
ኅዳር ፲፮ /16/በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ስምንተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ዮሐንስ አረፈ። ይህም ቅዱስ አባት የቆጵሮስ ሀገር ሰው ነው እጅግም ባለጸጋ ነው በእስክንድርያ አገርም የሚኖር ሆነ አባቱ አገረ ገዥ ነበርና ሚስትም አግብቶ ልጆችን ወለደ ከዚህም በኋላ ሚስቱም ልጆቹም ሞቱ። በዚያንም ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ መጸወተ እርሱም መንኵሶ በታላቅ ገድል የተጠመደ ሁኖ በጎ ሥራዎችን ትሩፋትን ጨምሮ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው ። ከበጎ ሥራዎቹና ከትሩፋቱም ከቀናች ሃይማኖቱ ከአገልግሎቱና ከደግነቱ ከጽድቁ ማማር የተነሣ በግብጽ አገር የሚኖሩ ኤጲስቆጶሳት ሁሉም ተሰማምተው ይዘው ወሰዱት ያለ ፈቃዱም በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙትና በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ አስቀመጡት። ያን ጊዜ የከበረ ወንጌልን አነበበ በሹመቱና በክህነቱም ብርሃን ተገለጸ ብዙዎች ድንቆች የሆኑ ተአምራትንም አደረገ። ለድኆችና ለችግረኞች ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የሚሹትን የሚሰጣቸው ሆነ ስለዚህም የሚራራ ዮሐንስ ተብሎ ተጠራ። በአይሁድና በአረማውያን ዘንድ የሚያስፈራ ሆነ በመጽሐፈ ገድሉ እንደተጻፈ እጅግ ይፈሩትና ያከብሩት ነበርና መንጋዎቹንም በበጎ አጠባበቅ ጠበቃቸው እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
ላይ ድርቅ የውኃም ማነስ አይሁን"።
❤ መድኃኒታችንም "የለመንከኝ ሁሉ አስጥሃለሁ አንተም በቀኜ ትኖራለህ ሥጋህንም ኤልያስ በዐረገበት ሠረገላ ውስጥ አኖራለሁ" አለው ሕፃን ቂርቆስ በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት ጌታችንን አመሰገነው። ከዚህም በኋላ በሌሊቱ እኩሌታም ከእናቱ ጋር አንገቱን ተቆረጠ መድኃኒታችንም በማይጠፋ አክሊል ጋረደው ነፍሶቻቸውንም በታላቅ ክብር ከእርሱ ጋር አሳረገ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቂርቂቆስና በእናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር 15 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11 ወይም 33፥10። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 5፥1-5 ወይም ሉቃ 6፥24-27።
❤ መኰንኑም "ሴትዮ ተናገሪ ከወዴት ሕዝብ ወገን ነሽ ነገድሽ ምንድን ነው አገርሽስ ወዴት ነው" አላት። የከበረች ኢየሉጣም እንዲህ ብላ መለሰችለት "የአንጌቤን ሰው ለሆንኩ ለእኔ ወገኖቼ ኤሳውሮሳውያን ናቸው እኔም በአንተ ምክንያት ሸሽቼ ነበር እነሆ ዛሬ ግን በእጅህ ውስጥ ነኝ" አለችው። መኰንኑም "በእጄ ውስጥ እንደተገኘሽ ታውቂያለሽን" አላት "አሁንም የሚሻልሽን ምረጪ ስምሽንም ተናገሪ እኔንም እሺ በይኝና ለአማልክት ሠዊ" የከበረች ኢየሉጣም አለችው "ለረከሱ አማልክት እኔ
አልሠዋም" አለችው መኰንኑም "ስምሽን ስጪ ተናገሪ" አላት እርሷም "የኔ ስም ክርስቲያን መባል ነው" አለችው። መኰንኑም "ይህስ ስንፍና ነው የሚጠቅምሽ አይደለም እንዳትሞቺ ስምሽን ስጪ ተናገሪ" አላት። የከበረች ኢየሉጣም "የኔ ስም ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞት የሚሽረው በሰዎች ዘንድ የምጠራበትን ከፈለግህ ስሜ ኢየሉጣ ነው" ብላ መለሰችለት። መኰንኑም "ጽኑ የሆኑ ሥቃዮችን በላይሽ ሳያመጡ ተነሥተሽ መሥዋዕትን ለአማልክት አቅርቢ" አላት። የከበረች ኢየሉጣም "ዕውነት ነገርን ለመሥራት የምትሻ ከሆነ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነ ሕፃን ልጅ ይፈልጉ ዘንድ ወደ አገሩ መንደር ላክ ወዳንተም ያምጡትና የምንገዛለትንና የምናመልከውን እርሱ ይነገረን" አለችው።
❤ ያን ጊዜም የሦስት ዓመት ልጅ ይፈልጉ ዘንድ መኰንኑ ወታደሮችን ላከ የአገር ሰዎችም ልጆቻቸውን ሠውረዋልና አላገኙም ከዚያም ከከተማው ቅጽር ውጭ በፀሐይ መውጫ ወዳለው በረሀ በኩል ወጡ የቅድስት ኢየሉጣንም ልጅ አገኙት ይህ ሕፃን "የስንት ዓመት ልጅ ነው" ብለው ስለርሱ ጠየቁ ሰዎችም "ይህ ሕፃን የሦስት ዓመት ሲሆን የክርስቲያናዊት መበለት ልጅ ነው" አሏቸው። ያንንም ሕፃን ይዘው ወደ መኰንኑ ወሰዱት መኰንኑም መልኩ የሚያምርና ደም ግባት ያለው እንደሆነ በአየ ጊዜ "ደስ የምትል ደስተኛ ሕፃን ሰላምታ ይገባሃል" አለው። ሕፃኑም "እኔን ደስተኛ ማለትህ መልካም ተናገርክ ላንተ ግን ደስታ የለህም እግዚአብሔር ለዝንጉዎች ደስታ የላቸውም ብሏልና ብሎ መለሰለት መኰንኑም ሕፃኑን "ሳልጠይቅህ ይህን ያህል ትመልስልኛለህን" አለው። ሕፃኑም "ገና ከዚህ የሚበዛ ነገርን እመልስልሃለሁ" አለው።
❤ መኰንኑም "ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ "ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውኃ የተገኘ ሕፃን ስሜ ክርስቲያን መባል ነው" ብሎ መለሰለት። መኰንኑም "ዳግመኛ እንዳትሞት ስምህን ንገረኝ" አለው የከበረ ሕፃንም "ስሜ ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞክሼ ስም የምትሻ ከሆነ እናቴ የሰየመችኝ ቂርቆስ ነው" በማለት መለሰለት፡፡ መኰንኑም ሕፃን ቂርቆስን "እሺ በለኝና እሾምሃለሁ በብዙ ወርቅና ብርም አከብርሃለሁ" አለው። ሕፃኑም "የሰይጣ መልእክተኛ ለዕውነትም ጠላቷ የሆንክ ከእኔ ራቅ" አለው። መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ደሙ እንደ ውኃ እስከሚፈስ ቆዳውን እንዲጨምቁትና እንዲግፉት አዘዘ። የከበረች ኢየሉጣሜ የልጅዋን ትዕግሥት በአየች ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነችው።
❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ "ጨውና ሰናፍጭ አምጡ አለ። የሁለቱንም አፍንጮቻቸውን ከፍተው ያንን ጨውና ሰናፍጭ እንዲጨምሩባቸው አዘዘ ያን ጊዜ ሕፃኑ "ትእዛዝህ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ሆነ ከማርና ከስኳርም ለአፌ ጣመኝ" ብሎ ጮኸ። ሁለተኛም መኰንኑ እንዲህ ብሎ አዘዘ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች አምጡ ሰባቱን በእናቱ አካላት ውስጥ ጨምሩ በሕፃኑም ሁለት ጆሮዎቹ ሁለት በዐይኖቹ ሁለት በአፉና በአፍንጫው አንድ በልቡ ጨምሩ እንዲህ ሲጨመርበት ጆሮዎቹ እንዲአሩ ዐይኖቹም ይጠፋ ዘንድ አንደበቱም ይቃጠል ዘንድ ወደ ልቡም ጽኑ ሕማም ገብቶ እርሱ ከዚህ ዓለም በሞት እንዲለይ ለእናቱም እንዲሁ አድርጉ ችንካሮችም በቅዱሳኑ በሥጋቸው ሁሉ ተጨመሩ። የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ትእዛዝ የብረቶቹ ግለት ጠፍቶ እንደ በረዶ ቀዘቀዘ ጤነኞችም ሆኑ መኰንኑም "ወደ ወህኒ ወስዳችሁ በዚያ አሥራችሁ ዝጉባቸው" አለ።
❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ "የሥቃይ መሣሪያን ይሠራ ዘንድ እንዳዝዘው ብረትን የሚያቀልጥ ሰው አምጡልኝ" አለ። በአመጡለትም ጊዜ ሰይጣን ወደ መኰንኑ ልብ ገብቶ አንደበቱን ዘጋውና መናገር ተሳነው ሕፃኑ ፈጥኖ አክሊልን ለመቀበል እንደሚተጋ ሰይጣን ስለ አወቀ ስለዚህ ዘጋው።
❤ ከዚህም በኋላ ሕፃኑ ሠራተኛውን ጠርቶ "እኔንና እናቴን የሚያሠቃዩ በትን የሥቃይ መሣሪያ መሥራት ትችላለህ ይህ መኰንን ግን ምንም የሚያውቀው ነገር የለም" አለው። ሠራተኛውም እንደምትሻው በል ንገረኝ እምታዝዘኝ እኔ መሥራት እችላለሁ" አለው። ሕፃኑም ቅዱስ ቂርቆስ እያዘዘው...። ብረት ሠሪውም ሰምቶ እጅግ አደነቀ የሚረዱትንም ከአገር ውስጥ መቶ ሠራተኞችን ሰብስቦ መሥራት ጀምረ በአርባ ቀንም ጨረሰ።
❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ እለእሰሰክድሮስ ቂርቆስንና እናቱን ወደ አደባባይ ያመጡአቸው ዘንድ አዘዘ ያን ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ ነበርና እንዲህ አለ "ሕፃኑንና እናቱን ከቆዳቸው ጋር ራሳቸውን ላጩአቸውና በላያቸው የእሳት ፍሞችን ጨምሩ እርር ብለው እንዲቃጠሉ ዳግመኛም አራት ችንካሮችን ከትከሻዎቹ እስከ ተረከዙ ድረስ እንዲተክሉበት አዘዘ የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ ሥቃዩን ከርሱ አራቀ። ዳግመኛም ከጥዋት እስከ ማታ ከሥቃይ መሣሪያዎች ውስጥ ጨምረው አዋሏቸው ግን ማሠቃየት ተሳናቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ከማምጠቂያው ውስጥ ጨምረው መገዙአቸውና አመድ እስከሆኑ ከቅባትና ከጨው ጋር በብረት ምጣድ ውስጥ ቆሉአቸው ጌታችንም አስነሥቶ አዳናቸው። ወደ መኰንኑም በገቡ ጊዜ እንዲህ አላቸው "በእውነት ከሙታን ተለይታችሁ የተነሣችሁ ከሆነ ይህ ጫማዬ በእግሬ ወጥቶ እንደ ቀድሞው ሕያው እንዲሆን አድርጉ ሕፃን ቂርቆስም በጸለየ ጊዜ ያ ጫማ ታላቅ በሬ ሆነ ከአንገቱም ፍየል ወጣ። በዚያንም ሰዓት ለዐሥራ አንድ ሽህ አራት ሰዎች በሬውንና ፍየሉን አርደው ምሳ እንዲአደርጉላቸው መኰንኑ አዘዘ እንዲህም አለ ይህ "በቅቷቸው ከጠገቡ ከዚህም ሌላ ምግብ ካልፈለጉ የተሠራው ሁሉ ዕውነተኛ ነዋሪ ነው"።
❤ ከዚህም በኋላ አርደው ምሳ አደረጉላቸውና ከፍየሉ ሥጋ ስድስት እንቅብ ከበሬው ሥጋ አራት እንቅብ አተረፉ መኰንኑም የተረፈውን ሥጋ አይቶ ወደ ባሕር እንዲጥሉት አዘዘ። መኰንኑም ቢያፍር የሕፃኑን ምላስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ጌታችንም ምላሱን መለሰለት ዳግመኛም በታላቅ ጋን ውኃ አፍልተው ሕፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ እናቱም አይታ ፈራች። ልጅዋም ወደ እግዚአብሔር በጸለየላት ጊዜ አምላካዊ ኃይልን አሳደረባትና ከልጅዋ ጋር ወደ ጋኑ ገባች። እንደ ውርጭም ቀዝቃዛ ሆነ ደግሞም በውስጡ መንኲራኵር ወዳለበት የብረት ምጣድ እንዲጨምሩአቸውና ሥጋቸው እስከሚቦጫጨቅ እንዲስቡአቸው አዘዘ የእግዚአብሔርም መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም በሕይወት አወጣቸው።
❤ መኰንኑም እነርሱን ማሸነፍ በተሳነው ጊዜ ቸብቸቧቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በዚያን ጊዜ ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወረደ ሕፃን ቅዱስ ቂርቆስንም "የምትሻውን ለምነኝ" አለው። ሕፃኑም "ሥጋዬ በምድር አይቀበር ስሜን ለሚጠራ መታሰቢያዬን ለሚያደርግ ቤተ ክርስቲያኔን ለሚሠራ የተጋድሎዬን መጽሐፍ ለሚጽፍና ለሚያጽፍ ወይም ለሚያነበው ለቤተ ክርስቲያኔ መባ ለሚያገባ በውስጧም ለሚጸልይ ለሁሉም ፍላጎታቸውን ስጣቸው ኃጢአታቸውንም ይቅር በል ስሜም በሚጠራበት በዚያች ቦታ የከብት ዕልቂት አይምጣ በሰውም ላይ አባር ቸነፈር በእህልም
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta):
❤ "በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ኅዳር ፲፭ 15 ቀን።
❤ እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት የስሙ ትርጓሜ ቡሩክና የታመነ ለሆነ #ለቅዱስ_ሚናስ_ለዕረፍት_በዓል፣ #ለታላቁ_ሰማዕት_ለሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስ_ለልደት መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰ። በተጨማሪ በዚችን ቀን ከሚታሰበው፦ ከአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ አንደኛ ከእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ከቅዱስ አባት ከሁለተኛው #አባ_ሚናስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ታላቁ_ሰማዕት_ቅዱስ_ሚናስ፦ የዚህም ቅዱስ አባቱ አናቅዮስ ከሚባል አገር ነው ስሙም አውዶክስዮስ ነው እርሱም አገረ ገዥነት ተሹሞ ሳለ ወንድሙ ቀንቶበት በንጉሥ ዘንድ ነገር ሠራበት ንጉሡም ወደ አፍራቅያ አገር ሰደደውና በዚያም አገረ ገዢ አድርጎ ሾመው የአገር ሰዎችም ሁሉ ደስ አላቸው እርሱ ለሰው የሚራራ እግዚአብሔርም የሚፈራ ደግ ሰው ነውና።
❤ እናቱም ልጅ አልነበራትም በአንዲት ዕለት ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በበዓልዋ ቀን ገብታ የክርስቲያንን ወገኖች ያማሩ ልብሶችን ለብሰው ከልጆቻቸው ጋር ደስ እያላቸው ሲገቡ አየቻቸው። በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት አለቀሰች ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ ልጅዋ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምንላትም ለመነቻት በዚያን ጊዜ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል አሜን የሚል ቃል ወጣ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ቤቷ ገብታ ይህን ቃል ለባሏ ነገረችው እርሱም "የእግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁን" አለ። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ እግዚአብሔር ይህን የተባረከና የከበረ ልጅን ሰጣት የእመቤታችንም ሥዕል "ሚናስ" ብላ እንደሰየመችው ስሙን ሚናስ ብለው ሰየሙት። ጥቂት በአደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማሩት። ዐሥራ ሁለት ዓመትም ሲሆነው በመልካም ሽምግልና አባቱ ዐረፈ ከእርሱም በኋላ በሦስተኛ ዓመት እናቱ ዐረፈች ቅዱስ ሚናስም ብቻውን ቀረ። መኳንንቱም አባቱን አብዝተው ከመውደዳቸው የተነሣ ሚናስን በአባቱ ፈንታ ምስፍናን ሾሙት እርሱም የክርስቶስን አምልኮት አልተወም።
❤ ዲዮቅልጥያኖስም በካደ ጊዜ ሁሉንም ሰዎች ጣዖታትን እንዲአመልኩ አዘዛቸው ብዙዎችም ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ። በዚያንም ጊዜ ቅዱስ ሚናስ ሹመቱን ትቶ ወደ ገዳም ገባ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ ብዙ ዘመናት ኖረ። በአንዲትም ዕለት ሰማይ ተከፍቶ ሰማዕታትን የብርሃን እክሊሎችን ሲአቀዳጁአቸው አየ "ስለ ክርስቶስ ስም በመከራ የደከመ ይህን አክሊል ይቀበላል" የሚል ቃልን ሰማ። በዚያንም ጊዜ ወደ ከተማ ተመለሰና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ ሰዎችም አብዝተው አባበሉት በወገን የከበረ እንደሆነ እነርሱ ያውቁ ነበርና። መኰንኑም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት ባልሰማውም ጊዜ ጽኑዕ በሆነ ሥቃይ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ኅዳር 15 ቀን ተቀበለ ብዙዎችም በእርሱ ምክንያት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ።
❤ የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ወደ እሳት እንዲጥሉት መኰንኑ አዘዘ እሳትም አልነካውም ምእመናን ሰዎችም የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ወስደው በአማሩ ልብሶች ገነዙት የስደቱ ወራትም እስከሚፈጸም በአማረ ቦታ ውስጥ አኖሩት።
❤ በዚያንም ወራት የመርዩጥ አገር ሰዎች ከአምስቱ አገሮች ሠራዊትን ሊአከማቹ ወደዱ የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ረዳት ይሆናቸው ዘዘንድ በመንገድም እንዲጠብቃቸው ከእርሳቸው ጋር ወሰዱት። እነርሱም በባሕር ላይ መርከብ ውስጥ ሳሉ ፈታቸው እንደ ከይሲ አንገታቸው እንደ ግመል አንገት ያለ አውሬዎች ከባሕር ወጡ ይልሱትም ዘንድ ወደ ቅዱስ ሚናስ ሥጋ አንገታቸውን ዘረጉ ከቅዱ ሚናስም ሥጋ እሳት ወጥታ እነዚያነሰ አራዊት አቃጠላቻቸው ሰዎችም አይተው አደነቁ ደስታም አደረጉ ፈርተው ነበርና።
❤ ወደ እስክንድርያ አገርም ደርሰው ሥራቸውን ፈጽመው ወደ አገራቸው በሚመለሱ ጊዜ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ከእርሳቸው ጋር ሊወስዱ ወደው በገመል ላይ በጫኑት ጊዜ ገመሉ ከቦታው የማይነሣ ሆነ። ሁለተኛም በሌላ ገመል ጫኑት እርሱም መነሣትን እመቢ አለ አብዝተውም ደበደቡት ገመሉም ከቶ አልተንቀሳቀሰም እነርሱም ያቦታ እግዚአብሔር የፈቀደለት መሆኑን አወቁ ቦታውንም አዘጋጅተው ቀበሩት።
❤ ጌታችንም በበግ እስከገለጠው ድረስ ብዙ ዘመናትን በዚያ ቦታ ኖረ ይህም ቤተ ክርስቲያኑ በከበረችበት በሰኔ ዐሥራ አምስት ቀን ተጽፎአል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚናስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የእስክንድርያ_ስልሳ_አንደኛ_ሊቀ_ጳጳሳት #ሁለተኛ_አባ_ሚናስ፦ ይህም ቅዱስ ሚናስንም ከታናሽነቱጨያለ ፍላጎቱ ወላጆቹ ሚስት አጋቡት ትእዛዛቸውን መተላለፍ ስለአልፈለገ የጋብቻውን ሥርዓት ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ፈጸመ። ለርሱ ይህ ሁሉ ሕልም ይመስለው ነበር ወደ ሙሽሪትም ወደ አዳራሽ በአስገቡት ጊዜ ተቀምጦ እንዲህ ብሎ ተናገራት "እኅቴ ሆይ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ካጠፋ ምን ይጠቅመዋል እንደ ተጻፈ ሁሉ ያልፋልና ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ለዘላለሙ ይኖራል አሁንም ድንግልናችንን እንድንጠብቅ ነይ ቃል ኪዳን እናድርግ" እርሷም ቃሉን ተቀብላ ከእርሱ ጋር ተስማማች።
❤ ከዚህም በኋላ ትቷት ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒዶ በአባ መቃርስ ገዳም ውስጥ መነኰሰ ብዙ ዘመናትም በገድል ተጠምዶ ኖረ። ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳትም በዐረፈ ጊዜ ይህን ቅዱስ አባት ሚናስን ያለውዴታው ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስም ወንበር ላይ መንጋዎቹን በቅን ፍርድ እየጠበቃቸው እያስተማራቸው ዐሥራ ስምንተሰ ዓመት ኑሮ ኅዳር 15 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የአባ ሚናስ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር15 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #ሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስ፦ በዚያንም ወራት የክብር ባለቤት የሆነ ክርስቶስን በሚያምኑ የክርስቲያን ወገኖች ላይ ታላቅ መከራና ስደት ሆነ። ስሟ ኢየሉጣ የሚባል አንዲት ሴት ነበረች እርሷም ከታናሽነቷ ጀምራ ደግ ናት ስደትም እንደሆነ በሰማች ጊዜ መኰንኑን ከመፍራት የተነሣ ሕፃኗን ይዛ ከሮሜ ከተማ ተሰዳ የኪልቅያ አውራጃ ከሆነ ከጠርሴስ ደርሳ ከዚያም በአገሮች ውስጥ እየተዘዋወረች ተቀመጠች። ወደዚያች አገርም ያ ከእርሱ የሸሸችው መኰንን እለእስክድሮስ መጣ ጭፍሮቹም ክርስቲያኖችን ፈለጓቸው። ይቺንም ቅድስት ኢየሉጣን አግኝተው ያዝዋትና ወደ መኰንኑ አደረሷት የክርስቲያን ወገንም እንደሆነች ነገሩት።
ጾመ ነቢያት
[ የጾመ ነብያት ምስጢር ምንድነው ? ]
ጾመ ነቢያት [ የገና ጾም ] ከልደት አስቀድሞ የሚጾም ጾም ነው ከህዳር ፲፭ [ 15 ] ጀምሮ ለ ፵፫ [43] ቀናት የሚጾም ሲሆን ፋሲካው [ ፍቺው ] በልደት በዓል ነው ይህም ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳንና ምዕመናን ጾመውታል፡፡
ጾመ ነብያት ስያሜውን ያገኘው ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት ነው በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምስጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ የረቀቀው ገዝፎ ጎልቶ እየተመለከቱ ትንቢት ተናገሩ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ጾሙ ጸለዩ፡፡
ነቢያት ከእመቤታችን ስለ መወለዱ ወደ ግብፅ ስለ መሰደዱ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ ብርሃን በሆነው ትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ ፥ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ ፥ ስለ ትንሣኤው ፥ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፡፡
ለአዳም የተሠጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ በየዘመናቸው ፦ "አንሥእ ኃይልከ ፈኑ እዴከ" እያሉ ጮኹ በጾምና በጸሎት ተወስነውም እግዚአብሔር ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት ፣ በሳምንታት ፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ኤርምያስ ስለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ በ፬፵፮ ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡
ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር ፦ "አያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር" ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩ እነ ነቢዩ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም [ኢሳ.፶፰፥፩] በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለተፈጸመበት ይህ ጾም "የነቢያት ጾም" ይባላል የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ስለሆነም "ጾመ ስብከት" ይባላል፡፡
ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት እነርሱም፦
† ፩. [ ጾመ አዳም ]
አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገነት ከተባረረ በኋላ በፈጸመው በደል አዝኖ ተክዞ አለቀሰ [እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ] ጾመ ጸለየ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው "ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በደጅህ ድኼ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ ሞቼ አድንሃለሁ" የሚል ነው [ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ] ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት "ጾመ አዳም" ይባላል፡፡
† ፪. [ ጾመ ነቢያት ]
ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው በተለይ አባታችን አዳም ቅዱስ ሙሴ ቅዱስ ኤልያስ ቅዱስ ዳንኤልና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: [ዘዳ.፱፥፲፱ ፣ ነገ.፲፱፥፰ ፣ ዳን.፱፥፫ መዝ.፷፰፥፲ ፻፰፥፳፬] ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል ለሞትም አብቅቶታል::
† ፫. [ ጾመ ሐዋርያት ]
ሐዋርያት "ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?" ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡
† ፬. [ ጾመ ማርያም ]
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና "ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?" ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና "ጾመ ማርያም" ይባላል፡፡
† ፭. [ ጾመ ፊልጶስ ]
ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡
† ፮. [ ጾመ ስብከት ]
የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡
† ፯. [ ጾመ ልደት ]
የጾሙ መጨረሻ [ መፍቻ ] በዓለ ልደት ስለሆነ "ጾመ ልደት" ይባላል፡፡
በጾማችን በጸሎታችን - ስለ ቤተክርስቲያን ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝብ በማሰብ እራሳችንን ዝቅ በማድረግ እንጾም ዘንድ ይገባል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!
❤ "በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ኅዳር ፲፬ (14) ቀን።
❤ እንኳን #ለአገረ_ጠራክያ_ኤጲስ_ቆጶስ ለቅዱስ አባት #ለአባ_መርትያኖስ_ለዕረፍት_በዓል፣ ለፋርስ ንጉሥ ተአምራት ላደረገና ክቡር ይግባንና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላሳመነ #ለአባ_ዳንኤል_ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን #ሱራስጦስ_ከእንድራዎስ_ከመብራኖስ_ከራጢስና #ከይስጥ_ከጋርሴስ_ከበጥላንና ከመታሰቢያቸው #በደብረ_ቀልሞን ከተሠራች ቤተ ክስትያን ከከበረችበት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #የአገረ_ጠራክያ_ኤጲስ_ቆጶስ_አባ_መርትያኖስ፦ ይህ ቅዱስ ሶርያ ከምትባል አገር ነው ወላጆቹም ክርስቲያን ናቸው እርሱም በገድል የተጠመደ ተጋዳይ ነው። አርዮሳውያንንም የሚቃወማቸው ከሀድያን የሚላቸው አውግዞም የሚያሳድዳቸው ሆነ። ስለዚህም በእርሱ ላይ ታላቅ መከራ ደረሰበት። በሚያልፍባትም ጎዳና ጠብቀው ይይዙታል አብዝተውም ገርፈው እግሩን ይዘው በሜዳ ውስጥ ይጎትቱታል እንዲህም ብዙ ጊዜ አደረጉበት።
❤ ከዚህም በኋላ ከእርሳቸው ሸሽቶ ወደ ሩቅ አገር ተጒዞ ከኤርትራ ባሕር ዳር ደረሰ ከምድር የሚበቅሉ ቅጠሎችን እየተመገበ በዚያ ዋሻ ውስጥ ብዙ ዓመታትን ኖረ። ኤጲስቆጶስም ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር መረጠው እነሆ የተጋድሎውና የትሩፋቱ ዜና በተሰማ ጊዜ ከዚያ ወስደው ጠራክያ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት እንደ ሐዋርያት ሥርዓት በሹመቱ በጎ አካሔድን ተጓዘ በዘመኑም በብዙዎች ላይ ሰላም ፍቅር ቸርነት ሆነ።
❤ እግዚአብሔርም በእጆቹ ታላላቅ ተአምራትን አደረገ በጐዳናም አልፎ ሲሔድ የሞተ ሰው አየ ሌላም ዓመፀኛ ልቡ የደነደነ በሐሰት "ከእርሱ ላይ አራት መቶ የወርቅ ዲናር አለኝ ያንን ካልሰጠኝ አላስቀብርም" ብሎ ዘመዶቹን ሲከለክል ነበር። ይህም ቅዱስ "የሞተውን ይቅበሩት ተዋቸው" ብሎ ብዙ ለመነው እርሱ ግን አልሰማውም። በዚያንም ጊዜ ይህ ቅዱስ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየ ማለደ ያን ጊዜ የሞተው ሰው ተነሥቶ ምንም ምን ዕዳ እንደሌለበት ተናገረ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርትያኖስ ያንን ዓመፀኛ በሰፊት እንዲህ አለው "ለምን በሐሰት ተናገርክ የተሠወረውን የሚያውቅ እግዚአብሔርን አትፈራውምን" በዚያንም ጊዜ ያ ዓመፀኛ ሞተ ከሞት የተነሣው ግን በሰላም ወደ ቤቱ ገባ።
❤ ከዚም በኋላ ይህ ቅዱስ መርትያኖስ ብዙ ዘመናትን ኖረ መልካም አገልግሎትንም ፈጽሞ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ ኅዳር 14 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ መርትያኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ዳንኤል፦ ይህም አባት ለፋርስ ንጉሥ ተአምራት ያደረገና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳመነው ነው። የእምነቱም ምክንያት እንዲህ ነው ይህ ንጉሥ ጽኑዕ የሆነ የሆድ በሽታ ታሞ ነበር ባለ መድኃኒቶችም ሊአድኑት አልቻሉም ንጉሡም ከማዕዱ የሚመግበው አብሮት የሚኖር ሥራየኛ ሰው ነበርው ንጉሡም እንዲህ አለው "ያንተ ከእኔ ጋር መኖር ጥቅሙ ምንድን ነው ከዚህ በሽታ ካልፈወስከኝ እገድልሃለሁ"። ሥራየኛውም ንጉሡን በተንኰል እንዲህ ብሎ ተናገረው "ንጉሥ ሆይ የምነግርህን ካደረግህ ከደዌህ ትድናለህ። አሁንም ለአባትና እናቱ አንድ ብቻ የሆነ ልጅ ይፈልጉልህ እናቱ አሥራ ትያዘው አባቱም ይረደው በእርሱም ደም ትድናለህ" መሠርዩ ይህን ማለቱ ግን እንዲህ ያለ ሥራ መሥራትን ንጉሥ ይፈራል ወይም ልጁን የሚሰጥ አይገኝ ብሎ አስቦ ነው።
❤ ንጉሥም በሚገዛው አገር ውስጥ ፈልገው በአንድ ሺህ የወርቅ ዲናር ሕፃን ልጅ ይገዙለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ። በዚያችም አገር አንድ ልጅ ያላቸው ድኆች የሆኑ ባልና ሚስት ነበሩ እነርሱ ይህን ነገር ሲሰሙ ልጃቸውን ወደ ንጉሥ ወሰዱ ልጁም በማልቀስ "እኔ በፈጠረኝ እግዚአብሔር ላይ ተማምኛለሁና እርሱም ያድነኛል" ይል ነበረ። እናቱም አጥብቃ አሠረችው አባቱም ሊያርደው በንጉሡ ፊት ሾተሉን መዘዘ በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ አይኖቹን ወደ ሰማይ ቀና አድርጎ ወደ እግዚአብሔር በልቡ ሲጸልይ ከንፈሮቹን አንቀሳቀሰ እግዚአብሔርም በንጉሡ ልብ ርኅራኄን አሳደረ ፈትታችሁ ልቀቁት ብሎ አዘዘ ወደርሱም አቅርቦ "ዐይኖችህን ወደ ሰማይ በአቀናህ ጊዜ ምን አልክ" አለው "ጌታዬ ሆይ ልጅን የሚገፋው ቢኖር አባቱና እናቱ ያድኑታል ከዚያም የጸና ሥራ ቢኖር ንጉሥ ዳኛ ያድነዋል እኔ ግን ከሁላችሁም ርዳታ በአጣሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ለመንኩ" አለው። ንጉሡም ሰምቶ ራራለት አንድ ሽህ የወርቅ ዲናርንም ሰጠው።
❤ ስለዚህም እግዚአብሔር ይቅር ልለው ወዶ መነኰስ አባ ዳንኤልን ላከለት እርሱም ወደ ንጉሡ በደረሰ ጊዜ በፊቱ ተአምራትን አደርጎ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሳመነው ከበሽታውም ፈወሰው ከቤተሰቦቹ ሁሉ ጋርም አጠመቀው ከዚህም በኋላ ወደ በዓቱ ተመልሶ እየተጋደለ ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ኅዳር 14 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የአባ ዳንኤል በረከቱም ትድረስን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 14 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለመርትያኖስ_ምሉአ_ጸጋ_ወሀብት። ከመ ይስብክ ሃይማኖተ በመጣርያ አንተ ተውህበቶ ሢመት። እምአርሳውያን ሕዝብ ሶበ ረኮቦ ስደት። ኀበ ሖረ ወፈለሰ ውስተ ምድር ርኅቅት። በኃይለ ጸሎቱ ተንሥአ ምውት"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የኅዳር_14።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "እስመ አቡየ ወእምየ ገደፉኒ። ወእግዚአብሔር ተወክፈኒ። ምርሐኒ እግዚኦ ፍኖተከ"። መዝ26፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥12-24፣ 1ኛ ጴጥ 5፥6-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 23፥6-10። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 4፥46-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ዮሐንስና የአቡነ ቄርሎስ ዘሽሬ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
ሕዳር 13 /፲፫/በዚች ቀን የከበረ ባለጸጋ አስከናፍር አረፈ። ይህም አስከናፍር ከሮሜ መኳንንት አንዱ ነው እርሱም ለድኆችና ለምስኪኖች ምጽዋትን የሚሰጥ እንግዶችንና መጻተኞችን የሚቀበል ነው። በዚያም ወራት ያገኙትን ሰው ሁሉ የሚነጥቁና የሚያጠፉ ዐሥራ ሦስት ሽፍቶች ነበሩ እንግዳ እንደሚቀበል ይልቁንም መነኰሳትን እንደሚወድ የአስከናፍርን ዜና በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ ሒደው በተንኮል ይገድሉት ዘንድ ገንዘቡንም ሁሉ ሊወስዱ ተማከሩ። ከዚህም በኋላ የምንኲስና ልብስ ለብሰው ከደጁ ቆሙ በአያቸውም ጊዜ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት እንደሆኑ አንዱ ጌታ ክርስቶስ እንደሆነ አሰበ ሰገደላቸውም ወደ ቤቱም አስገብቶ ማዕድ አቀረበላቸው እግራቸውንም አጠበ ሠላሳ አምስት ዓመት ሽባ ሆኖ በኖረ ልጁ ላይ ያንን እግራቸውን የታጠቡበትን ውኃ ረጨ ወዲያውኑ ልጁ ዳነ። እነዚያ ሽፍቶችም የሆነውን በአዩ ጊዜ እጅግ ደነገጡ እርሱ አስከናፍር ግን አባቶቼ ሆይ ጌታ ክርስቶስ ከእናንተ መካከል የቱ እንደሆነ ንገሩኝ እሰግድለት ዘንድ አላቸው የአገር ሰዎችም የመኰንኑ ልጅ እንደዳነ በሰሙ ጊዜ ወደ እርሳቸው መጥተው ሰገዱላቸው እንዲህም አሏቸው የእግዚአብሔር ቅዱሳኖች ሆይ ባርኩን በሽተኞቻችንን አድኑልን። ከዚህም በኋላ እኒያ ወንበዴዎች ሾተሎቻቸውን አውጥተው አንተን ልንገድልህ በወደድንበት እኛን ይገድሉን ዘንድ እሊህን ሾተሎች ውሰድ አሉት እግዚአብሔር በአንተ ጽድቅ የራራልን ባይሆን በአጠፋን ነበር። ይህንንም ከአሉት በኋላ ተሰናበቱት ወደ ምድረ በዳ ተጓዙ። ከዚህም በኋላ ከሀዲ መኰንን በመጣ ጊዜ እርሱ ወዳለበት ሒደው በጌታችን ታመኑ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
