uk
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Відкрити в Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Показати більше
603
Підписники
-324 години
-87 днів
-1730 днів
Архів дописів
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #መጋቢት 6 ቀን። ❤ እንኳን #ከግብጽ_ወደ_አገራች_ኢትዮጵያ ከተሰዓቱ ቅዱሳ ቀጥሎ በመምጣት በወሎ የምትገኘው #ቸርተከል_ማርያምን_ለቆረቆሩና በዚያም ሳያርፍ #ለ21_ዓመት_ቆሞ_ለጸለዩ፤ እጃቸውን በማጨብጨብ በአንድ ጊዜ አምስት መቶ ርግቦችን ይጠሩ ለነበሩ፤ እነርሱንም ወደፈለጉበት ቅዱሳን ይልካቸው ለነበሩ #ለታላቁ_አባት_አቡነ_አርከሌድስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።                              ✝ ✝ ✝            ❤ #አቡነ_አርከሌድስ፦ አገራቸው ግብፅ ሲሆን ከተሰዓቱ ቅዱሳ ቀጥሎ ነው ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የመጡት፡፡የነበሩበትም ጊዜ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በነበሩበት ጊዜ ነበር፡፡ወደ አገራችን ከመጡ በኋላ ወሎ ውስጥ ያለችውን እጅግ ጥንታዊቷን ቸር ተከል ማርያምን ቆረቆሯት፡፡ጻዲቁ የሚታወቁበት ትልቁ ገድላቸውም ሳይንት ውስጥ በቸር ተከል ማርያም ገዳም ውስጥ ለ21 ዓመታት ሳያርፉ ሳይቀመጡ በመቆም ጸሎት ያደረጉ ታላቅ አባት መሆናቸው ናቸው፡፡ ❤ አቡነ አርከሌድስ እጃቸውን ሲያጨበጭቡ 500 ርግቦች በአንድ ጊዜ ይሰበሰቡላቸው ነበር፡፡ እነርሱንም ወደፈለጉት ቅዱሳን መልእክት ይልኳቸው ነበር፡፡በዚህ አስደናቂ ሥራቸውም በቅዱሳን ዘንድ ትልቅ ክብር ነበራቸው፡፡ለቅዱሳን የተለያየ ታሪክ አላቸው፣ለአንዱ አንበሳ፣ለአንዱ ጅብና አጋዘን፣ለአንዱ ንብ፣ለአንዱ ነብር፣ለአንዱ አጋንንት ይታዘዙላቸው ነበር፡፡ጻዲቁ በመጨረሻ ወደ ምረድ ግብፅ ተመልሰው ከሰማዕታት ጋር ተሰይፈው በሰማዕትነት ያረፉ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ዕረፍታቸውም መጋቢት 6 ቀን ነው። ከአባታች ከአቡነ አርኬሌድስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሰላም በያላቹበት ውድ የፍኖተ ብርሃን ቤተሰቦች እንደሚታወቀው የእናታችን የቅድስት አርሴማ ህንፃ ቤተክርስትያን በመሰራት ላይ ይገኛል። ስለሆነም እኛም በህብረት በሰንበት ት/ቤታችን
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሰላም በያላቹበት ውድ የፍኖተ ብርሃን ቤተሰቦች እንደሚታወቀው የእናታችን የቅድስት አርሴማ ህንፃ ቤተክርስትያን በመሰራት ላይ ይገኛል። ስለሆነም እኛም በህብረት በሰንበት ት/ቤታችን ስም የበረከቱ ተሳታፊ እንሆን ዘንድ የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅብናል። ገቢ ለማድረግ💵💴🧾 1,በአካል ፅ/ቤት በመምጣት             ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን               ✍️✍️✍️ፅ/ቤት✍️✍️✍️

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #መጋቢት ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊቷ_ጻድቅ በዝዋይ ደብረ ጽዮን ሐይቅ ውስጥ ገብታ ለአምስት ዓመት ለጸለየች ለታላ
+1
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #መጋቢት ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊቷ_ጻድቅ በዝዋይ ደብረ ጽዮን ሐይቅ ውስጥ ገብታ ለአምስት ዓመት ለጸለየች ለታላቋ እናት #ለቅድስት_ሐይመተ_ሥላሴ ለዕረፍቷ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።       ❤ #ቅድስት_ሐይመተ_ሥላሴ፦ የትውልድ ሀገሯ ጎጃም ደብረ ጽላሎ ነው፡፡ ብዙ እናቶች በጣና ደሴት ውስጥ እየገቡ እንደጸለዩ ሁሉ እሷም ወደ ዝዋይ ሄዳ በዝዋይ ደብረ ጽዮን ሐይቅ ውስጥ ገብታ አምስት ዓመት ከባሕሩ ላይ የጸለየች ቅድስት እናት ናት፡፡ በታዘዘ መልአክ መሪነት ከሐይቁ ውስጥ ከወጣች በኋላ በገዳሙ ውስጥ ዐሥራ ዘጠኝ ዓመት ቆማ ጸልያለች፡፡ ❤ በመልአኩ መሪነት ወደ ቡልጋ ሄዳ በዚያም ዐሥራ አምስት ዓመት በታላቅ ተጋድሎ ኖራለች፡፡ ሰውነቷም እጅግ ከስቶ ሥጋዋ አልቆ ይታይ ነበር፡፡ በመጨረሻም መልአኩ ተገልጦ ጊዜ ዕረፍቷን ከነገራት በኋላ ወዲያው መጋቢት 4 ቀን በሰላም ስታርፍ ሦስት አክሊላት ወርደውላታል፡፡ ቅድስት ሐይመተ ሥላሴን ስንክሳሩም "የጽድቅ ኮከብ" እያለ ይጠቅሳታል፡፡ ቅዱስ ገድሏ በደብረ በግዕ ይገኛል፡፡ ከእናታችን ቅድስት ሐይመተ ሥላሴን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #መጋቢት ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን #ለእስክንድርያ_ሃምሳ_ስምንተኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለብፁዕ_ወቅዱስ_ለአባ_ቆዝሞስ ለዕረፍት በዓልና ከፎንዮስ አገር ለሆነ #ለአባ_በርፎንዮስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                    ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ቆዝሞስ፦ ይህም እውነተኛና ንጹሕ፣ የዋህ ርኅራኄው የባዛ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍትና ትርጓሜያቸውን የሚያውቅ ነበር። እግዚአብሔር በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ መንበር ላይ ለሊቀ ጵጵስና ሹመት መረጠው የግብጽ ንጉሥ መቅትር በነገሠ በዐሥራ ስምንት ዓመት ሊቀ ጳጳሳት ሁኖ ተሾመ። ❤ በተሾመም ጊዜ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መንጋዎች በፈሪሃ እግዚአብሔር በጥበብ ጠበቃቸው። ለእርሱ ከሚገባው ከግብሩ ገንዘብ የሚተርፈውን ለጦም አዳሪዎች ይሰጣቸው ነበር ደግሞም ለቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ማሠሪያ ያወጣ ነበር። ❤ መልካም ተጋድሎውንም በአየ ጊዜ ሰይጣን ያለ ኀዘን አልተወውም ነገር ግን የሚያዝንበትን ምክንያት በላዩ አመጣ። ይኸውም እንዲህ ነው ጴጥሮስ የሚባል ጳጳስ ለኢትዮጵያ አገር ሹሞ ነበር  አባ ጴጥሮስም ወደ ኢትዮጵያ በደረሰ ጊዜ ጥቂት ዘመን በሰላም ኖረ። ከዚህም በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሥ ታመመ አባ ጴጥሮስንም ጠርቶ ሁለቱን ልጆቹን አቀረበ ዘውዱንም ከራሱ ላይ አንስቶ ለአባ ጴጥሮስ ሰጠው "እንሆ እኔ ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እሔዳለሁ እንሆም ሁለቱ ልጆቼ በፊትህ ናቸው አንተም ከሁለቱ አንዱን ከእኔ በኋላ አንግሥ" አለው። ንጉሡም ካረፈ በኋላ ጳጳሱ መንኳንንቱና የጦር ሥራዊቱ አለቆችና የመንግሥት ሠራዊት አለቆች ተማከሩ እርስ በርሳቸውም ለመንግሥት የሚሻል የሚያንሰው ነው ተባባሉ። ጳጳሱ አባ ጴጥሮስ ታናሹን የንጉሥ ልጅ ቀብቶ አነገሠው በኢትዮጵያ መንግሥት ዙፋን ላይም አስቀመጠው ጥቂት ዘመንም በሰላም ኖረ። ❤ በዚያም ወራት ከሶርያ አገር በሆኑ በሁለት መነኰሳት ልብ ሰይጣን አደረ ከአባ እንጦንስ ገዳም እስከ ሚደርሱ ከቦታ ወደቦታ ይዞሩ ነበር። በዚያም በአባ እንጦንስ ገዳም ጥቂት ቀኖች ተቀመጡ ስለ ሥራቸውም ክፋት አባረሩአቸው። ከዚያም በኋላ አንዱ ጳጳስ ሁለተኛውም ረዳት ሊሆን እርስ በርሳቸው ተስማሙ። ተነሥተውም ወደ ኢትዮጵያ ደረሱ። የሐሰት ጽሑፍንም ጻፉ ያ ጽሑፋቸውም እነርሱ ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ከአባ ቆዝሞስ ዘንድ ተሹመው እንደ መጡ የሚገልጥ ነበር። በዚያ ጽሑፍም "እኛ ያልሾምነውና ወደ እናንተ ያልላክነው ራሱን ጳጳስ ያደረገ ስሙ ጴጥሮስ የተባለ ሰው ወደ እናንተ እንደመጣ ሰምተናል እርሱ ሐሰተኛ ነው እንጂ እውነተኛ አይደለም። ይህን ጽሑፍ ይዞ የሚመጣው ግን ስሙ ሚናስ የሚባል ጳጳስ በእውነት እኛ የሾምነውና ወደ እናንተ የላክነው እውነተኛ ነው" አሉ። ሁለተኛም እንዲህ ብለው ጻፋ "ጳጳሱ ጴጥሮስ ታላቁን ትቶ ታናሹን የንጉሥ ልጅ አነገሠው ይህም የማይገባ ነው ዐመፅ ነውና"።                             

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #መጋቢት ፪ (2) ቀን። ❤ እንኳን #ለኒቅዮስ_ኤጲስቆጶስ ለአቅፋስ ከተማ ሹም ለሆነ ለዮልስዮ ስሙ አውካሪስጦስ የሚባል እጆቹና
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #መጋቢት ፪ (2) ቀን። ❤ እንኳን #ለኒቅዮስ_ኤጲስቆጶስ ለአቅፋስ ከተማ ሹም ለሆነ ለዮልስዮ ስሙ አውካሪስጦስ የሚባል እጆቹና እግሮቹ ሽባ የሆነ ልጅ ለፈወሰው ለታላቁ አባት #ለአባ_መከራዊ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለሮሀ አገር ለሆነ የተሰወረውን ለሚያይ #ለቅዱስ_ጎርጎርዮስ ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ለአባ_መከራዊ፦ይህም አባት በግቡጽ ደብቡ ከምትገኝ ከእስሙናይ ከታላላቆቹቿ ወገን ነው። ለኒቅዮስ ከተማም ኤጲስቆጶስነት ተሾመ። የስደቱና የመከራ ወራት በሆነ ጊዜም ስሙ ዮፋንስ የሚባል መኰንን ወደዚያች አገር ከንጉሥ ተልኮ መጣ። የክርስቲያን ወገኖችንም ያሠቃይ ዘንድ ጀመረ። የዚህንም የቅዱስ ኤጲስቆጶስ አባ መከራዊን ዜና ሰምቶ ወደርሱ ያመጡት ዘንድ ወታደሮቹን ላከ እርሱም ወደ መኰንኑ ከመሔዱ በፊት ወደ ቅዱስ መሠዊያው ገባ እጆቹንም ዘርግቶ ጸለየ። ንዋየ ቅዱሳቱንና የመቅደሻውን ልብሶች በመቅደሱ ውስጥ አኖረ። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ትሞታለህ እና ቤትህን አስተካክል እንኳን ለአብይ ፆም በሰላም አደረሳችሁ። ፆሙ የይቅርታ የፍቅር የመተሳሰብ የአንድነት እንዲሁም ለጥያቄያችን መልስ ምናገኝበት በፈተና ሊጥለን የማይተኛውን ዳቢሎስ ድል የምናደርግበት ፆም ያድርግልን።     ኪነጥበብ ክፍል

† [ 🕊 የዐቢይ ጾም ሳምንታት 🕊 ] ዐቢይ ጾም በያዘው በ፶፭ ቀኑ ውስጥ ሰባት ቅዳሜና ስምንት እሑዶቸን ይዟል ፤ የእነዚህ የስምንቱ እሑዶች የተለያየ ስያሜ አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም የሰጣቸው የ
                       †                        [  🕊 የዐቢይ ጾም ሳምንታት  🕊  ] ዐቢይ ጾም በያዘው በ፶፭ ቀኑ ውስጥ ሰባት ቅዳሜና ስምንት እሑዶቸን ይዟል ፤ የእነዚህ የስምንቱ እሑዶች የተለያየ ስያሜ አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም የሰጣቸው የቤተ ክርስቲያናችን የዜማው ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ዘወረደ ፣ ቅድስት ፣ ምኩራብ ፣ ደብረዘይት ፣ ገብረ ኄር ፣ ኒቆዲሞስ ፣ መፃጉዕ ፣ ሆሣዕና ናቸው፡፡   [     ፩ ኛ. ዘወረደ ፦     ] በመጀመርያው ሳምንት ዘወረደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማያት መውረዱን ፣ ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን እና እኛን ማዳኑን በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚወሳበትና የሚዘከርበት ወቅት ሲሆን ይህንንም የሚዘክሩ መዝሙሮች ይቀርባሉ ፤ ትምህርቶች ይሰጣሉ ፤ ይህንንም እያሰብን ጾሙን እንጾማለን፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፥ ለሐዋርያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን በሥርዓቱ ጹመን እንዲንጠቀም እርዳን ፤ አሜን ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፥ ወለወላዲቱ ድንግል ፥ ወለመስቀሉ ክቡር ! †                       †                       †

🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 ሰላም እንዴት ናችሁ የፍኖተ ብርሃን ቤተሰቦች ከህንፃ አሰሪ ኮሚቴ የመጣ መልክት ነው። በማንኛውም ቀን የብዙኃን ስራ ስለተጀመረ የጉልበት ስራ አስተዋፅኦ እንድታረጉ በእግዚአብሔር ስም አንጠይቃለን እናሳስባለን። 🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን #ለታላቁ_ነቢይ፣ ሰማዕት፣ ሐዋርያ ፣ካህን #ለመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ ሕግ አፍራሽ
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               ❤ #የካቲት ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን #ለታላቁ_ነቢይ፣ ሰማዕት፣ ሐዋርያ ፣ካህን #ለመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ ሕግ አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ኄሮድስ እጅ አንገቱን ከተሰየፈ በኋላ አንገቱ ክንፍ አውጥታ በዓለም ላይ በመዞር ዐሥራ አምስት ዓመት አስተምራ ከዐረፈች በኋላ በዓረቢያ ምድር #የከበረች_ራሱ_ለተገኘችበት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰበው፦ ከእስክድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ከአባ_ሚናስ ከመታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የመጥምቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ_የከበረች_ራሱ መገኘት፦ ይህም እንዲህ ነው ከሐዲ ኄሮድስ የከበረ ዮሐንስን ራሱን ይቆርጡት ዘንድ በአዘዘ ጊዜ በእሥር ቤት ራሱን ቆርጠው ወደ ኄሮድስ አቀረቧት እርሱም ለወገኖቹ በማሳየት በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ስለ አደረገው ሥራ እደሚያዝን ገለጠላቸው የክብር ዮሐንስንም ራስ በቤቱ ውስጥ አስቀራት። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #የካቲት ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊቷ_ጻድቅ በአጤ (ዐፄ) #ሱሱንዮስ አንገቷን ተሰይፈ ሰማዕት ከሆነች በኋላ #ቅዱስ_ሚካኤል ገነትንና ሲኦልን አሳይቶ 14ቀን በሰማያዊት ኢየሩሳሌም ከተቀመጠች በኋላ እንደገና እንደተኛ ወይም ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ከሞት ተነስታ ብዙ ገዳማትን (ታላቁን ገዳም ራማ ኪዳነ ምሕረትን) ላቀናች #ለታላቋ_ለጻድቅ_ወሰማዕት_ለቅድስት_ፍቅርተ_ክርስቶስ (እመ ምዑዝ) ለዕረፍቷ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #ጻድቅ_ወሰማዕት_ቅድስት-ፍቅርተ_ክርስቶስ (እመ ምዑዝ)፦ በጎንደር ክፍለ አገር ደራ ፎገራ አንበሳሜ ወረዳ ልዩ ስሙ አቡነ ሐራ ገዳም አጠገብ ኮክታ ማርያም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ውስጥ ተወለደች፡፡ዛሬም ይህ አካባቢ እመ ምዑዝ መንደር ይባላል፡፡የአባቷ ስም ቅዱስ ላባ የእናትዋ ስም ቅድስት ወንጌላዊት ይባላል፡፡ እነዚህም ወላጆቿ እጅግ ደጋግ ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ለተራበ፣ ለተጠማ የሚያዝኑና የሚራሩ እንደ አብርሃምና እንደ ሣራ በጎ ምግባር ያላቸው ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን በረከት ሁሉ በሥራ ላይ የሚያውሉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ልጅ ስላልወለዱ ወደፈጣሪያቸው ወደ እግዚአብሔር ልጅ እንዲሰጣቸው ይለምኑ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የለመኑትን የማይነሳ የነገሩትን የማይረሳ ቸር አምላክ ስለሆነ እንደ ቅድስት ሐና እመ ሳሙኤል ጸሎታቸውን ሰምቶ የተመረጠች ደግ ሴት ልጅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በሚያዚያ 4 ቀን ተፀንሳ ታኀሣሥ29 ቀን ከእነሱ ተወለደች፡፡ ስመ ጥምቀቷ ማርያም ጸዳላ የዓለም ስሟ ሙዑዚት ሲሆን ሙዑዚት ማለት ጣፋጭ ማለት ነው፡፡ (ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ደግሞ የቆብ ስሟ ነው።) √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት፳፰ (28) ቀን። ❤ እንኳን #ለአርእስተ_አበው_ለቅዱሳን #ለአብርሃም_ለይስሐቅና_ለያዕቆብ ለበዓላቸው መታሰቢያና #ለሮማ
+1
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት፳፰ (28) ቀን። ❤ እንኳን #ለአርእስተ_አበው_ለቅዱሳን #ለአብርሃም_ለይስሐቅና_ለያዕቆብ ለበዓላቸው መታሰቢያና #ለሮማዊ_ቅዱስ_ቴዎድሮስ በነገሥታት መክሲሞስና መክስምያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ቴዎድሮስ_ማኅበር ከሆኑ #ስድስት_ሺህ_ሦስት_መቶ_አራት ሰዎች በሰማዕትነት ከዐረፉ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                          ✝ ✝ ✝ ❤ #ሮማዊው_ሰማዕቱ_ቅዱስ_ቴዎድሮስ፦ እርሱም ከእስያ አውራጃ አስጢር ከሚባል አገር ነው። ይህንንም ቅዱስ በነገሥታት ዘንድ አማልክትን በማምለክ እርሱ እንደማይስማማ ወነጀሉት በዚያንም ጊዜ አስጠርተው "ለአማልክት ለምን አትሰግድም" አሉት፡እርሱም "እኔ ክርስቲያን ነኝ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አላመልክም" ብሎ መለሰላቸው። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፳፯ (27) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ታላቁን ገዳም #ማኅበረ_ሥላሴ_ለመሰረቱና እንደ መሶበ ወርቅ ከፍ አ
+3
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #የካቲት ፳፯ (27) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ታላቁን ገዳም #ማኅበረ_ሥላሴ_ለመሰረቱና እንደ መሶበ ወርቅ ከፍ አድርገው ላስባረኩ፤ #ንጉሥ_ሱሱንዮስ የካቶሊክን እምነት በተቀበለ ጊዜ ምላሱ ተጎልጉሎ የነበርው በመስቀላቸው ባርከው ለፈወሱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ዓምደ_ሥላሴ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ዓምደ_ሥላሴ(ጎጃም)፦ የትውልድ አገራቸው ጎጃም ሲሆን በአጤ (ዐፄ) ሱስንዮስ ዘመን የነበሩ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደርጉ የነበሩ ገዳማዊ መነኵሴ ናቸው፡፡ ጻድቁ ማኅበረ ሥላሴን ያቀኑ ታላቅ አባት ሲሆኑ በተለይም አንድ የሚታወቁበት ትልቅ ታሪክ አላቸው፡፡ እርሱም አጤ (ዐፄ) ሱስንዮስ ካቶሊካውያን ደግፈው 8ሺህ የአገራችንን ሊቃውንት በአንድ ቀን ባሳረዱ ጊዜ ንጉሡ ወዲያው "ኦርቶዶክስ ይርከስ ካቶሊክ ይንገስ" ብሎ ያወጀበት ምላሱ ተጎልጉሎ ወጣ፡፡ እንደ አርዮስም ሆዱ አብጦ አንጀቱ ተልቶ ሊሞት ባለ ሰዓት አቡነ ዓምደ ሥላሴ አዘዞ ድረስ ሄደው "ፋሲል √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

26/06/2016                    የዕለቱ የወንጌል ክፍል                    ማቴዎስ 10:36-ፍጻሜ    ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል። “ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም። ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል። “እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።”              የዕለቱ የጳውሎስ መልእክት                     ሮሜ 9:24-30     የምሕረቱ ዕቃዎችም ከአይሁድ ብቻ አይደሉም፥ ነገር ግን ከአሕዛብ ደግሞ የጠራን እኛ ነን። እንዲሁ ደግሞ በሆሴዕ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ ያልሆነውን ‘ሕዝቤ፡’ ብዬ፥ ያልተወደደችውንም፡ ‘የተወደደችው፡’ ብዬ፡ እጠራለሁ፤” እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም፡ በተባለላቸውም ስፍራ፡ በዚያ የሕያው እግዚአብሔር ልጆች፡ ተብለው ይጠራሉ። ኢሳይያስም፦ “የእስራኤል ልጆች ቁጥር ምንም እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን ቅሬታው ይድናል፤ ጌታ ነገሩን ፈጽሞና ቆርጦ በምድር ላይ ያደርገዋልና፡” ብሎ ስለ እስራኤል ይጮኻል። ኢሳይያስም እንደዚሁ፦ “ጌታ ፀባዖት ዘር ባላስቀረልን እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር፡” ብሎ አስቀድሞ ተናገረ።             2 ጴጥሮስ 1:19-ፍጻሜ      ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ። ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ  አሜን"። ❤                ❤ #የካቲት ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት ለአንዱ ዖዝያ ይባል ለነበረው ለዕውነተኛ #ለቅዱስ_ሆሴዕ ለዕረፍቱ በዓልና ለከበሩ #ለቅዱሳን_ሳዶቅና ከእርሱ ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉ #ሁለት_ሺህ_ስምንት ሰዎች ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ ነቢዩ ቅዱስ ሆሴዕ፦ ዳግመኛም ይህ ነቢይ በአራቱ የይሁዳ ነገሥታት ዘመን ትንቢት ተናገረ። እሊህም ዖዝያን፣ ኢዮአታም፣ አካዝና ሕዝቅያስ ናቸው። በትንቢቱም ድንቆች ሥራዎችን ተናገረ የእስራኤል ልጆች ገሠጻቸው "የአመንዝራ ልጆች" ብሎም ጠራቸው እግዚአብሔርም ቊጣውን ከእርሳቸው እንደማይመለስ አሰረዳቸው። እንዲህም አለ "የእስራኤል ልጆች ቊጥራቸው እንደማይሠፈርና እንደማይቆጠር የባሕር አሸዋ ቢሆን ከጥቂት በቀር አይተርፍም" አለ። ❤ ስለ አሕዛብም በእግዚአብሔር ማመን ተናገረ እንዲህም አለ "እኔ ወገኖቼ ያልሆኑትን እጠራቸዋለሁ እነርሱም ይሰሙኛል። ዳግመኛም ስለ መድኃኒታችን መከራ መቀበልና በደሙ ስለ መዳናችን ስለ ትንሣኤውም እንዲህ ብሎ ተናገረ "እሱ በመከራ ገርፎ ያድነናል እርሱም በመከራ አቊስሎ ይቅር ይለናል ሲያድነንም በሁለተኛው ቀን ነው በሦስተኛውም ቀን ድነን በእሱ ፊት እንነሣለን" እግዚአብሔርንም አውቀን እንከተለው ዘንድ ስለ ሞት ሥልጣን መሻር ስለ መቃብርም መሸነፍ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "ሞት ይዘህ ማስቀረትህ መቃብርስ ድል መንሳትህ ወዴት ነ" ትንቢትን እየተናገረ ሰባ ዓመት ያህል ኑሮ በበጎ ሽምግልና የካቲት26 ቀን ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሆሴዕ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፬ኛ ፓትርያርክ የ፪ኛ ዓመት የእረፍት መታሰቢያ ::
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፬ኛ ፓትርያርክ የ፪ኛ ዓመት የእረፍት መታሰቢያ ::

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #የካቲት ፳፭ (25) ቀን። ❤ እንኳን ለከበሩ #በቅዱስ_ጳውሎስ ትምህርት ላመኑ #ለቅዱሳን_አውሳንዮስ_ፊልሞ፣ ለድንግል #ቅድስት_ሉቅያ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለከበረ #ሐዲስ_አባ_እንጦኒ ይህም ረውሕ ለሚባለው ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ከግብጽ አገር ከእስሙናይን አውራጃ ለሆነ ዐሥራ ስምንቱ ዓመት ቆሞ ሳይቀመጥ ለጸለየ #ለአባ_አቡፋ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሮሜ አገር #ከዲያቆን_ቶና ከአገረ ቊስ #ሚናስ_ከጋዛ_ይልማድዮስ በሰማዕትነት ከዐረፉ፣ #ከደማይልናልና_ከርጊኖስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ  ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የከበሩ_ቅዱሳን_አውሳንዮስ_ፊልሞና_ሉቅያ፦ እሊህ ቅዱሳንም በአፍራቅያ አገር ሳለ በከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ያመኑ ናቸው ከሀድያንም ዝሑራ በሚባል ኮከብ ስም ለሚጠሩት ለአርታዳሚ ጣዖት በዓልን በአደረጉ ጊዜ አይተው በስሕተታቸው ሊዘብቱ እሊህ ቅዱሳን ተስብስበው ወደ ጣዖቱ ቤት ገቡ ሰዎችም ለጣዖቱ ሲሠዉና ከፍ ከፍ ሲያደርጉት በአዩአቸው ጊዜ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እሳትነት ልባቸው ነደደ ከጣዖቱም ቤት ወጥተው ወደ ክርስቶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሔደው የክብር ባለቤት የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብሩንና ልዕልናውን አብዝተው አመሰገኑ። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እንኳን ለ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላምና በጤና አደረስዎ ! የ
+2
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት  እንኳን ለ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላምና በጤና አደረስዎ ! የቅዱስነትዎ ቡራኬ አይለየን ! The 11th Anniversary Of Enthronement Of His Holiness Abune Matthias I, Patriarch Of Ethiopia Archbishop Of Axum Echege Of The See Of St. Tekelhaymanot √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #የካቲት ፳፬ (24) ቀን። ❤ እንኳን #ለከበረ_አባት ለንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ወታደር አለቃ ለነበረው ብዙ ተአምራትን ላደረገ፤ ብዙ ሰዎችን ያጠፋውን ታላቅ ከይሲ በጸሎቱ ለገደለው #ለኤጲስቆጶስ_ቅዱስ_አጋቢጦስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ በጋዛ ሰማዕት ከሆኑ #ከጢሞቴዎስ፣ ከቆጵሮስ ከአገረ #ከሚናስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ኤጲስቆጶስ_ቅዱስ_አጋቢጦስ፦ ይህም አባት በከሀድያን ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክስምያኖስ ዘመን ነበር። ወላጆቹም ደጎች ምእመናን ነበሩ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምረውት ዲቁና ተሾመ። ከዚያም በኋላ እናትና አባቱን ትቶ ወደ አንድ ገዳም ሔደ የሸመገሉ መነኰሳትን አገለገለ። ከእርሳቸውም በጎ አምልኮትን አገለገለ። ከእርሳቸው በጎ አምልኮትን ተማረ አረጋውያኑንም እያገለገለ በገድል ተጠመደ ያለ ማቋረጥም በጾም በጸሎትና በስግደት ይተጋል ከጥዋትም እስከ ምሽት በመጾም የሽንብራ አሠር የሚመገብ ሆነ። ከእንቅልፍም ጋር ሊታገል በወደደ ጊዜ ከሽምብራ አሠር ጋር አመድ እየተመገበ ሰማንያ ቀን ኖረ ከዚህም ተጋድሎ ውስጥ እያለ ኃይሉ ግን ይጨመርለት ነበር። ለአረጋውያንም አገልግሎቱን አላስታጐለም ሲጠራቸው ጌቶቼ ይላቸዋል የጽድቅንና የትሩፋትን ሥራ ሁሉ ፈጸመ። ❤ እግዚአብሔርም የሚያስደንቁ ብዙዎች የሆኑ ታላላቅ ተአምራቶችን በእጆቹ ገለጠ። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨                              

🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የአባታች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ወርሀዊ በአለ ንግስ የካቲት 25 (ሰኞ)
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የአባታች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ወርሀዊ በአለ ንግስ የካቲት 25 (ሰኞ) ከ 10:30 ጀምሮ በደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ፀጋው ከበዛላቸው መምህራንና ዘማርያን ጋር እናክብር ። ረድኤተ ቅዱስ መርቆሬዎስ አይለየን!!! 🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ የካቲት ፳፫ (23) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያ°ገበዝ (ጠባቂ) ለአድዋው አርበኛ፣ ለፍጡነ ረድኤት፣ ለገባሬ ተአምር #ሊቀ_ሰማ
+4
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ የካቲት ፳፫ (23) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያ°ገበዝ (ጠባቂ) ለአድዋው አርበኛ፣ ለፍጡነ ረድኤት፣ ለገባሬ ተአምር #ሊቀ_ሰማዕታት_ለቅዱስ_ጊዮርጊስ_በ1888ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ንጉሠ ነገሥትን ምኒልክና ሠራዊቱ ለረዳበት፤ ኢትዮጵያ በሮማውያንን (ጣልያንን) ድል ለተቀዳጀችበት ለ128 (ለአንድ መቶ ሃያ ስምንተኛው) ለአድዋ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                             ✝ ✝ ✝ ❤ ልመናው ጸሎቱ በረከቱ አማላጅነቱ በዕውነት በመላው ሕዝበ ክርስቲያን ይደረግልንና #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ያደረገው_ተአምር_ይህ_ነው፦ በዚያን ወራት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ አራት ዓመት በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ በነገሡ በሃያ ስድስት ዓመት የምኒልክ የጦር አለቃ ገበየሁ ድል ከአደረጋቸው በኋላ እንደገና ምኒልክም ወግተው ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ሊገዙ የሮም ሰዎች መጡ። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨