ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Відкрити в Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Показати більше607
Підписники
-124 години
-47 днів
-1230 днів
Архів дописів
"ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ፤ ደማቸውን ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ፤ስለመንግስተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ።"
ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ቁ.፮
አቅራቢ ፦እንዳልክ ሲሳይ
ዋሽንት ፦ማኑሄ ደረጄ
💥እንኳን ለእናታችን ለቅድስት አርሴማ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን ።
✍️ ኪነ-ጥበብ ክፍል
+3
🔴🔴 የአራተኛ ቀን መንፈሳዊ ጉባኤ እነሆ 🔴🔴
➖➖➖➖➖➖⛪️➖➖➖➖➖➖
በደብራችን ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን
የአራተኛ ቀን መንፈሳዊ ጉባኤ እነሆ
በእለቱ :➺
⛪️ መ/ሃ ተስፋዬ ሞሲሳ
ተገኝተው የእለቱን ትምህርት
➖ እግዚአብሔርን ማወቅ ➖ በሚል ርዕስ ተነስተው
በሚገባ አስተምረዋል ።
➖➖ ቃለ ሕይወትን ያሠማልን ➖➖
⛪️ ዘማሪ ሊቀ ዲያቆናት ነብዩ ሳሙኤል
በተሰጣቸው የዝማሬ ሃብተ ጸጋ ከመሳሪያ ተጫዋች ወንድም በሃይሉ ጋር እና ከደብራችን ሰ/ት/ቤት አባላት ጋር ሲያገለግሉ አምሽተዋል ።
➖➖ ዝማሬ መላዕክት ያሰማልን ➖➖
🔶 ጉባኤው ነገም በልዩ ሁኔታ የሚቀጥል ይሆናል ።
🔶🔶🔶 እግዚአብሔር ይመስገን 🔶🔶🔶
➖➖➖➖➖➖⛪️➖➖➖➖➖➖
በደብራችን ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የሦስተኛ ቀን መንፈሳዊ ጉባኤ እነሆ ።
በእለቱ :➺
⛪️ መ/ሐ ቀሲስ አንድነት አሸናፊ
ተገኝተው የእለቱን ትምህርት በሚገባ አስተምረዋል ።
➖➖ ቃለ ሕይወትን ያሠማልን ➖➖
⛪️ ዘማሪ ዲ/ን እንዳለ ደረጄ
በተሰጣቸው የዝማሬ ሃብተ ጸጋ በዝማሬ ከመሳሪያ ተጫዋች ወንድም ብሩክ ጋር እና ከደብራችን ሰ/ት/ቤት አባላት ጋር ሲያገለግሉ አምሽተዋል ።
➖➖ ዝማሬ መላዕክት ያሰማልን ➖➖
🔶🔶🔶 እግዚአብሔር ይመስገን 🔶🔶🔶
➖➖➖➖➖➖⛪️➖➖➖➖➖➖
በደብራችን ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የዛሬው ጠዋት መንፈሳዊ ጉባኤ እነሆ ።
በእለቱ :➺
⛪️ ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደሳለኝ
ተገኝተው የእለቱን ትምህርት በሚገባ አስተምረዋል ።
➖➖ ቃለ ሕይወትን ያሠማልን ➖➖
⛪️ መ/ሰ/ቀሲስ ዘማሪ እንግዳወርቅ በቀለ
በተሰጣቸው የዝማሬ ሃብተ ጸጋ በዝማሬ ሲያገለግሉ አርፍደዋል ።
➖➖ ዝማሬ መላዕክት ያሰማልን ➖➖
በመጨረሻም በደብራችን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር መልአከ ብርሃን መ/ር ተ/ሃይማኖት ቃለ ምዕዳንና አባታዊ መመሪያ ተላልፎ የእለቱ ጉባኤ ተጠናቋል ።
🔶 ጉባኤው ማታም የሚቀጥል ይሆናል ።
🌹 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹
🌹 #መስከረም ፳፮ (26) ቀን።
🌹 እንኳን #ለእናታችን_ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም ለልጇ ለወዳጇ ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለመድኃኒታችን ##ለኢየሱስ_ክርስቶስ ለስደታቸው መታሰቢያ #ለፈቃድ_ጾም_ለጽጌ ጾም (ለዘመነ ጽጌ) እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
🌹 "#አዘክሪ_ድንግልንግደቶ_ዘምስሌኪ እንዘ ትጐይዪ ምስለ እምሀገር ለሀገር በመዋዕለ ሄሮድስ ርጉም። #አዘክሪ_ድንግል_አንብዐ_መሪረ ዘውኅዘ እምአዕንትኪ ወወረደ ዲበ ገጸ ፍቁር ወልድኪ። #አዘክሪ_ድንግል_ረኃበ_ወጽምዐ_ምንዳቤ_ወኀዘን ወኵሎ ዐፀባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ"። ትርጉም፦ #ድንግል_ሆይ_ርጉም_በሆነ_በሄሮድስ ዘመን ከእርሱ (ልጅሽ) ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስትሸሺ ከአንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ። #ድንግል_ሆይ_ከዓይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር ዕንባ አሳስቢ፡፡ #ድንግል_ሆይ_ርኃቡንና_ጥሙን ችግሩንና ኀዘኑን ከእርሱ ጋር በመሆን የደረሰብሽን ጭንቅ (መከራ) ሁሉ አሳስቢ"። #ሊቁ_አባ_ሕርያቆስ_በቅዳሴ_ማርያም_በቁጥር_167_169_ላይ።
✝ ✝ ✝
🌹 #የዘመነ_ስደት_መታሰቢያ ለምን በዚህ ጊዜ ሆነ?
#ከመስከረም_26_እስከ_ህዳር_5።
🌹 እመቤታችን ከልጅዋ ጋር ስደትን የጀመረችው ጥር 3 ነው፥ አገረ ግብጽ የገባችው ግንቦት 24 ነው፥ በግብፅ እና በኢትዮጵያ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ከቆዩ በኋላ ስደቱ አብቅቶ ተመለሱ ብሎ መልአኩ ሲነግራቸው ካሉበት ተነስተው ቁስቋም ከተባለች ቦታ ኅዳር 6 ደርሰዋል ።
🌹#የስደት_መታሰቢያ_ለምን_በመነሻው_ጥር_3 አልሆነም?
ይህ ወቅት ዘመነ አስተርእዮ የደስታ ጊዜ ነው ታኅሣሥ 29 ልደቱን ጥር 11 ጥምቀቱን የምናከብርበትና በልደቱ እና በጥምቀቱ የተደረገልንን እያሰብን ደስ የምንሰኝበት ጊዜ በመሆኑ ለስደት መታሰቢያ ለማድረግ አይመችም።
🌹 #ግንቦት_24_አገረ_ግብፅ_የገባችበትን ይዘን ለምን ስደትን አናስብም?
🌹 ግንቦት 24 በዓለ ሃምሳን የምናከብርበት እንደመሆኑ በዚህ ወቅት ጌታችን በትንሳኤው የሰጠንን ነጻነት የምናስብብት ደስ የምንሰኝበት ጊዜ ስለሆነ መስገድ መጾም ስለማይፈቀድ የስደት መታሰቢያ ለማድረግ አይመችም።
🌹 ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ዕፅዋት አበባን ፍሬን የሚያሳዩበት ወቅት ነው።
🌹 ወቅቱ ለምሳሌ የተመቸ ነውና።
"ትወጽእ በትረ እምሥርወ እሤይ ወየዓርግ ጽጌ እምኔሃ" ኢሳ 11፥1 እንዲል የዕሤይ የዘር ግንድ ከተባለች ከእመቤታች ጽጌ ጸኣዳ ወቀይህ የተባለ የፍጥረት ሁሉ ጌጥ ጌታችን የተገኘ ነውና በዚህ መስሎ ለማስተማር የሚያመች ወቅት ነውና። በተጨማሪም ጽጌ በእመቤታች ፍሬ በጌታችን ይመሰላል።
🌹 #አንድም፦ ተመለሰ ከማለት በፊት ተሰደደ ማለት ይቀድማል።
🌹 በዓመት ውስጥ ያሉት የወራት ቅድመ ተከተል ኅዳር 6 ከጥር 3 እና ከግንቦት 24 ይቀድማል። ኅዳር ላይ ከስደት ተመለሰ ብለን ካከበርን በኋላ ጥር ተሰደደ ግንቦት ግብፅ ገባ ብንል አመቺ አይደለም።
ስለዚህ ከጥር 3 ወይም ከግንቦት 24 ይልቅ ኅዳር 6 መታሰቢያ ለማድረግ አመቺ በመሆኑ ቤተክርስቲያን በዚህ ወቅት የስደቱን መታሰቢያ ታደርጋለች።
🌹 በቅዱስ ያሬድ አባባል ስደት #ከመስከረም_26_እስከ_ጥቅምት_20 ሲነገር፤ #ከጥቅምት_21_እስከ_ኅዳር_6 ድረስ ሚጠት (መመለሳቸው) ይነገራል። ይኼውም ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት የሚለው ሰላም እንዲቀርብ በማኅሌት ስለተወሰነ ነው። ምንጭ፦ አምኃ ሥላሴ መኩሪያ ተስፋዬ።
🌹 ጾሙ ከአገራችን ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያጠፋ እና ሰላም፣ ፍቅርን አንድነትንና መተሳሰብ የሚያመጣ ያድርግልን። መልካም ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።
+8
➕ እግዚአብሔር ይመስገን ➕
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
ዛሬ በደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ለ5 ተከታታይ ቀን የሚቆየው መንፈሳዊ ጉባኤ ጀምሮ በጥሩ ሁኔታ አምሽቷል ።
በእለቱም :➺
⛪️ መጋቤ ሐዲስ ሄንክ ፈንቴ
🔴 ልጄን ከግብጽ ጠራሁት 🔴 ማቴ 2÷14 በሚል ርዕስ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የተሰደደበትን ምክንያት በአስር ከፍለው በሰፊው አስተምረዋል።
➖➖➖ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን ➖➖➖
⛪️ ዘማሪ ዲ/ን መለሰም በድንቅ የዝማሬ ጸጋው ሲያገለግል አምሽቷል ።
➖➖➖ዝማሬ መላዕክት ያሰማልን➖➖➖
⛪️ የደብራችን ሰ/ት/ቤት አባላትም በዝማሬ እና
ድንቅ ትረካ በማቅረብ አገልግለዋል ።
➺የአገልግሎት ዘመናችሁን እግዚአብሔር ይባርክ
🔴 ጉባኤያችን ነገም የሚቀጥል ይሆናል 🔴
🌹 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹
🌹 #መስከረም ፳፮ (26) ቀን።
🌹 እንኳን #ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ገብርኤል ወደ በራክዩ ልጅ ወደ #ቅዱስ_ዘካርያስ_ለተላከበት #መጥምቀ_መለኮትን ከእርሱ ስለ መወለዱ ለአበሰረበት፤ ( #ለመጥምቀ_መለኮት #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ለጽንሰት_በዓል)ና ለሰማዕቱ #ለቅዱስ_ዮስጦስ_ልጅ_ለቅዱስ_አቦሊ ለሥጋው ፍልሰት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከዐሥር_ሽህ_ሰማዕታት፣ #ከቅድስት_አጋታ_ከበርባራ_ከዮልያና፣ #ከአባት_ጊዮርጊስም_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
🌹 #የየመላእት_አለቃ_ቅዱስ_ገብርኤል #ለቅዱስ_ዘካርያስ_የመጥምቀ_መለኮትን_የቅዱስ_ዮሐንስ_መጸነስ_እዳበሰረው፦ ስሙ የተመሰገነ እግዚአብሔር ልጅን ይሰጠው ዘንድ አስቀድሞ ሁል ጊዜ በመጸለይ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ነበር። ልጅ ያልወለደውን እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርን ምሉዋት ያለውን በረከት ያጣ ነው በማለት እስራኤል ይገዳደሩት ነበርና።
🌹 ልመናውንም ሰማ በቤተ መቅደስም ቁሞ ዕጣንን ሲያሳርግ መልአኩን ላከለት በከበረ ወንጌልም እንደተባለ መንገዱን ይጠርግ ዘንድ በንጉሥ ክርስቶስ ፊት እንደሚሔድ የተነገረለት ታላቅ ነቢይ ዮሐንስ ከእርሱ መወለዱን አበሠረው።
🌹 ዘካርያስም የሰውነቱን መድከም የመውለጃውም ዘመን እንዳለፈና ፈጽሞ እንዳረጅ የሚስቱም እንዲሁ ዘመኗ እንዳለፈና ፈጽማ እንዳረጀች መካንም እንደሆነች ያውቃልና ስለዚህ ይህ ነገር እንዴት ይሆንልኛል "እኔ ያረጀሁ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም እንዲሁ ዘመኗ አልፎ መካን ሁናለች" ብሎ የእግዚአብሔርን መልአክ ተከራከረው።
🌹 መልአኩም "እኔ ይህን ልነግርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወዳንተ ተልኬ ነበር ልትጠራጠር ባልተገባህም ነበር አሁንም ይህ በጊዜው እስቲፈጸም ዲዳ ሁነህ መናገር ይሳንሃል" ብሎ ገሠጸው። ዘካርያስም የወልደ እግዚአብሔርን መንገድ የሚጠርግ ዮሐንስ እስከሚወለድበት ጊዜ ድረስ ዲዳ ሆነ።
🌹 በሚገረዝበትም ቀን የሕፃኑን አባት ዘካርያስን የሕፃኑን ስም ምን ብለው እንደሚሰይሙት ጠየቁት እርሱም ብራና ለምኖ "ስሙ ዮሐንስ ነው" ብሎ ጻፈ በዚያም ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው። ስለ ልጁ ዮሐንስም እርሱ የልዑል ነቢይ እንዲባል መንገዱንም ይጠርግ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዘካርያስና በቅድስት ኤልሳቤጥ በልጃቸው በቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
🌹 "#ሰላም_ለፅንሰትከ_በሠሌዳ_ከርሣ_ዘተገልፈ። ለኤልሳቤጥ እምከ እምድኅረ ወርኃ ኀለፈ። ዮሐንስ መልአክ እንተ ትኴንን አእላፈ። ከመ እፈጽም ዘወጠንኩ ስብሐቲከ ትሩፈ። በውስተ ዕዝንየ አልኆስስ መጽሐፈ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_26።
ወርኃ ጽጌ
[ ከመስከረም ፳፮ [ 26 ] እስከ ኅዳር ፮ [ 6 ]
“እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ጸዐዳ ወቀይሕ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ”
[ ነጭም ቀይም አበባ የተባለ ልጅሽን እያቀፍሽው በተአምርና በንጽሕና ቀን ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ርግቤ ድንግል ማርያም ሆይ ከልቅሶ ከሐዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ መልካማዬ ከደስተኛው ገብርኤልና እንዳንቺ ርኅሩኅ ከኾነው ከሚካኤል ጋር ነዪ ]
[ አባ ጽጌ ድንግል ]
🌷🌷🌷
❤ እግዚአብሔርም ዮናስን "በቅሊቱ መድረቅ እጅግ አዘንክን" አለው እርሱም "አዎን ልሙት እስከ ማለት ደርሼ አዘንኩ" አለ። እግዚአብሔርም "አንተስ በአንድ ሌሊት በቅላ በአንድ ሌሊት ለደረቀች ውኃ ላላጠጣሃት ላልደከምክባት ቅል ታዝናለህ። ቀኝና ግራቸውን ላልለዩ ከዐሥራ ሁለት እልፍ የሚበዙ ሰዎች እንዲሁም ብዙ እንስሶች ላሉባት ታላቅ አገር ለሆነች ነነዌ እኔ አላዝንላትምን ከበደሉ ተመልሶ ንስሐ ለሚገባ እኔ መሐሪና ይቅር ባይ ነኝና" አለው።
❤ ከዚህም በኋላ ዮናስ ተነሥቶ ወደ አገሩ ተመልሶ በሰላም ዐረፈ መላው ዕድሜውም መቶ ሰባ ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ዮናስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 25 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለዮናስ_በከርሠ_አንበሪ_ዘኖመ። አምሳለ ክርስቶስ ይኩን በውስተ መቃብር ተኀትሙ። እግዚአብሔር ይቤሎ ጊዜ በሑሩር ሐመ። ኢይሣሃላኑ ለነነዌ ወኢይምሕካኑ ፍጹመ። እንዘ አንተ ትምሕክ ዘኢተከልከ ሐምሐመ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ አርኬ የመስከረም 25።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠፅኮ እግዚኦ። ወዘመሀርኮ ሕገከ። ከመ ይትገኃሥ እመዋዕለ እኩያት።" መዝ 93፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥21-24።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወአይቴ እጐይይ እምቅድመ ገጽከ። እመኒ ዐረጉ ውስተ ሰማይ ህየኒ አንተ። ወእመኒ ወረድኩ ውስተ ቀላያት ህየኒ ሀሎከ"። መዝ138፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 2፥1-12፣ 2ኛ ጴጥ 3፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 20፥9-28 የሚነበበው ወንጌል ማቴ 12፥38-43። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ። መልካም የነቢዩ ዮሐንስ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መስከረም ፳፭ (25) ቀን።
❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት አንዱ ለሆነው #ለየዋሁ_ለቅዱስ_ዮናስ_ለዕረፍት_በዓል፣ #ለክረምት_መውጫ (ማብቅያ) ቀን በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ከፎቃ፣ #ከዮሐንስ_ከእንድራዎስ_ከጴጥሮስ_ከጳውሎስ፣ #ከእንጦንዮስ_ከበርባራ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ነቢዩ_ቅዱስ_ዮናስ፦ ይህም እውነተኛ ነቢይ ዮናስ የሲዶና ክፍል በምትሆን ስራጵታ በምትባል አገር ለምትኖር መበለት ልጅዋ የሆነ ነቢይ ኤልያስም ከሙታን ለይቶ ያሥነሣው ኤልያስንም ያገለገለውና የትንቢት ጸጋ የተሰጠው ነው።
❤ ከዚህም በኋላ ስሙ ከፍ ከፍ ያለና የተመሰገነ እግዚአብሔር "ወደ ነነዌ አገር ሒደህ ሀገራቸሁ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ትጠፋለች" ብለህ አስተምር ብሎ አዘዘው። እግዚአብሔርም ይህን በአለው ጊዜ ዮናስ በልቡ እንዲህ ብሎ አሰበ "እግዚአብሔር ሊአጠፋቸው ቢወድ ኖሮ ሒደህ አስተምር ብሎ ባላዘዘኝ ነበር እግዚአብሔር መሐሪ ነውና ሲምራቸው እኔ በእነርሱ ዘንድ ሐሰተኛ ነቢይ እንዳልባል እፈራለሁ ከቶ ትምህርቴን አይቀበሉኝም ወይም ይገድሉኛል ወደዚያች አገርም ሒጄ እንዳላስተምር ከእግዚአብሔር ፊት ብኰበልልና ብታጣ ይሻለኛል"።
❤ ወንድሞች ሆይ ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር ፊት ለፍጡር ማምለጥ ይቻለዋልን። ይህስ ዮናስ የእስራኤልን ልጆች ከሚያስተምሩ ነቢያት ውስጥ ሲሆን ይህን አያውቅምን ነገር ግን አግዚአብሔር በረቀቀ ጥበቡ ይህን አደረገ እንጂ የዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት አድሮ መውጣት መድኃኒታችን በመቃብር ሆድ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት አድሮ ከዚህ በኋላ ከሙታን ተለይቶ ለመነሣቱ ምልክት ይሆን ዘንድ ነው።
ዮናስም ከዓሣ አንበሪ ሆድ ያለ ምንም ጥፋት እንደመጣ እንዲሁ መደኃኒታችን ያለመለወጥ ተነሥቷልና።
❤ እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ፊት ዮናስ ሸሽቶ ወደ ተርሴስ አገር ሊሔድ ተነሣ ወደ ኢዮጴ አገርም ወርዶ ወደ ተርሴስ አገር የሚሔድ መርከብን አግኝቶ በገንዘቡ መርከቡን ተከራየ። ከእግዚአብሔር ፊት ኰብልሏልና ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሔድ ዘንድ ወደ መርከቡ ወጣ እግዚአብሔርም ታላቁን ነፋስ ወደ ባሕር አመጣ የባሕሩም ማዕበል ከፍ ከፍ አለ መርከባቸውም ሊሰበር ቀረበ። ቀዛፊዎችም ፈርተው ወደ ጣዖቶቻቸው ጮኹ መርከባቸውም ይቀልላቸው ዘንድ ገንዘባቸውን፣ ዕቃቸውን አውጥተው ወደ ባሕር ጣሉ። ዮናስ ግን በዚያን ጊዜ ወደ ከርሠ ሐመሩ ወርዶ ተኝቶ ያንኰራፋ ነበር።
❤ መርከቡንም የሚቀዝፍ ቀዛፊ ወደ ርሱ ወርዶ "ምን ያስተኛሃል እንዳንሞት እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ ተነሥተህ የፈጣሪህን ስም ጥራ" አለው። "ይህች መከራ ያገኘችን ስለማናችን ኃጢአት እንደ ሆነ እናውቅ ዘንድ እርስ በርሳቸው ኑ ዕጣ እንጣጣል" ተባባሉ በተጣጣሉም ጊዜ ዕጣ በዮናስ ወጣበት። እነርሱም "ይህች መከራ ያገኘችን በማናችን ኃጢአት እንደሆነ ንገረን አንተስ የምታመልከው ምንድንነው ከወዴትስ መጣህ አገርህስ የት ነው ወዴትስ ትሔዳለህ ወገንህስ ማንነው" አሉት።
❤ ዮናስም እኔስ "የእግዚአብሔር ባርያው ዕብራዊ ነኝ ፈጣሪዬም ምድርንና ሰማይን ባሕሩንና የብሱን የፈጠረ እግዚአብሔር ነው" አላቸው። እነዚያም ሰዎች ታላቅ ፍርሀትን ፈርተው "ምን አድርገሀል" አሉት እሱ ነግሮአቸዋልና ከእግዚአብሔር ፊት ኰብልሎ እንደሔደ እነርሱም አወቁት። ባሕሩ ይታወክ ነበርና ታላቅ ማዕበልም ተነሥቶ ነበርና "ባሕሩ ይተወን ዘንድ እንግዲህ ምን እናድርግህ" አሉት። ዮናስም "አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ ባሕሩም ይተዋችኋል ይህ ታላቅ የማዕበል ሞገድ የመጣባችሁ በእኔ ምክንያት እንደ ሆነ አውቃለሁ" አላችው።
❤ ባሕሪቱ ትታወካለችና ማዕበሊቱም በእነሣቸው ትነሣለችና እነዚያ ሰዎች ወደ ምድር ሊመለሱ ወደዱ ነገር ግን ተሳናቸው። ሁሉም አንድ ሁነው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ "አቤቱ ስለዚህ ሰው በእውነት ልታጠፋን አይገባህም አቤቱ እንደ ወደድክ አድርገሃልና የጻድቅ ሰው ደም አታድርግብን" አሉ። ከዚህም በኋላ ዮናስን አንሥተው ወደ ባሕር ጣሉት ባሕርም ድርጎዋን ተቀብላ ጸጥ አለች። እነዚያም ሰዎች እግዚአብሔርን ፈሩት ለእርሱም መሥዋዕትን ሠዉ ስእለትንም ተሳሉ።
❤ እግዚአብሔርም ታላቅ ዓሣ አንባሪን ዮናስን ይውጠው ዘንድ አዘዘው ዮናስም በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ኖረ። ዮናስም በአንበሪ ሆድ ውስጥ ሳለ ጸሎትን ጸለየ ከዚህም በኋላ በነነዌ አገር በኩል ያ ዓሣ አንበሪ ዮናስን ወደ የብስ ምድር ተፋው። የእግዚአብሔርም ቃሉ ዳግመኛ ወደ ዮናስ መጣ "ቀድሞ አስተምር ብዬ እንደ ነገርኩህ ወደ ታላቂቱ የነነዌ አገር ተነሥተህ ሒደህ አስተምራቸው" አለው።
❤ ዮናስም እግዚአብሔር አስተምር ብሎ እንደ ነገረው ተነሥቶ ወደ ነነዌ ሔደ። ነነዌ ግን ለእግዚአብሔር ታላቅ አገር ናት በዙሪያዋ ያለ ቅጽርዋም ከበር እስከ በር ድረስ በእግር የሦስት ቀን ጐዳና ነው። ወደ ከተማም ሊገባ ደርሶ ያንድ ቀን መንገድ ሲቀረው "ነነዌ እስከ ሦስት ቀን ትጠፋለች" ብሎ አስተማረ። የነነዌም ሰዎች በእግዚአብሔር ቃል አመኑ "ጾምን እንጹም" ብለው አዋጅ ነገሩ የክት ልብሳቸውንም ትተው ማቅ ምንጣፍ ትልቁም ትንሹም ለበሱ። የነነዌ ንጉሥም ይህን ሰምቶ ከዙፋኑ ተነሣ ልብሰ መንግሥቱንም ትቶ ማቅ ለበሰ በአመድ በትቢያ ላይም ተቀመጠ።
❤ "ሰዎችም ቢሆኑ ከብቶችም ምንም ምን አይብሉ ትልልቆችም ትንንሾችም አይጠጡ እንስሶችም ወደ ሣር አይሠማሩ ውኃም አይጠጡ" ብሎ አዋጅ ነገረ። እግዚአብሔርም ከክፉ ሥራቸው እንደ ተመለሱ አይቶ በእነርሱ ላይ ያደርገው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ በእነርሱ ላይም ክፉ ጥፋትን አላደረገም።
❤ ዮናስም ጽኑ ኀዘንን አዘነ ወደ ፈጣሪው እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ለመነ "ጥንቱን በአገሬ ሳለሁ እንዲህ ብዬ የተናገርሁ አይደለሁምን አንተ ይቅር ባይ ርኅሩኅም ከመዓት የራቅህ ቸርነትህ የበዛ እውነተኛ የሆንክ ክፉ ነገርን ከማምጣት እንደምትመለስ አውቃለሁ ስለዚህ ከአንተ ኮብልዬ ወደ ተርሴስ ሔድሁ። ነቢየ ሐሰት እየተባልኩ ከመኖር ሞት ይሻለኛልና አቤቱ አሁን ነፍሴን ከሥጋዬ ለያት" አለ። እግዚአብሔርም ዮናስን "በዚህ ነገር አንተ እጅግ ታዝናለህን?" አለው እርሱም "አዎን አዝናለሁ" አለ። ከዚህም በኋላ ዮናስ ከከተማ ወጥቶ ከከተማው ውጭ ተቀመጠ ጎጆም ለራሱ ሠራ በአገር ላይ የሚደረገውን ነገር እስኪያይ ድረስ ከጥላዋ ሥር ተቀመጠ።
ይበቅል ዘንድ በዮናስ ራስ ላይ ይሸፍነው ዘንድ እግዚአብሔር ቅልን አዘዘ ቅሉም በዚያን ጊዜ በቅሎ የዮናስን ራስ የፀሐይ ትኩሳት እንዳያሳምመው በዮናስ ራስ ላይ ሸፈነው ዮናስም በቅሊቱ መብቀል ታላቅ ደስታ አደረገ።
❤ እግዚአብሔርም በማግሥቱ "ትሉን ይምጣ ቅሉንም ይምታ" ብሎ አዘዘ ቅሊቱንም ቆረጣት እርሷም ደረቀች እግዚአብሔርም ፀሐይ በወጣ ጊዜ "የሚያቃጥል ሐሩር ያለበት ነፋስ ይምጣ" ብሎ ዳግመኛ አዘዘ። ነፋሱም መጥቶ የዮናስን ራስ አሳመመው እርሱም አእምሮውን እስከማጣት ደርሶ በልቡናውም ተበሳጭቶ "ከመኖር ሞት ይሻለኛል" አለ።
+1
መስከረም ፳፬በዚህች ቀን ቅዱስ አባት መነኰስ ጎርጎርዮስ አረፈ። የዚሕም ቅዱስና የተመሰገነ ጎርጎርዮስ ወላጆቹ ደጎች እና ባለጸጎች ነበሩ ይህን ልጃቸውን ጎርጎርዮስንም የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን ሁሉ ሥጋዊም የሆነ ጥበብንና ቋንቋንም አስተማሩት። የሀገራቸው ኤጲስቆጶስ አባ ይስሐቅ እጁን ጭኖ አናጒንስጢስነት ሾመው ዳግመኛም ወደ ጳጳስ ወስደው ዲቁናን ተሾመ። ከወላጆቹም ብዙ ገንዘብ ወስዶ ወደ አባ ጳኵሚስም ቀርቦ ለሕንጻ ለቤተክርስቲያን፣ በገዳማቱ ለሚሰሩ ስራዎችና ለመነኮሳት ቤት መሥሪያ ተሳትፎ አደረገለት። ከዚህም በኋላ ወደ አባ ጳኵሚስም ገዳም ሄዶ የምንኩስናን ልብስ ለብሶ በጾም በጸሎት በመትጋት በመስገድ ከትሕትና ከቅንነት ከፍቅር ጋር ይጋደል ጀመረ። ፈሪሃ እግዚአብሔርን ከእርሱ ተምረው አመንዝራዎች ንስሐ ገብተው ንጹሐንም እስከሆኑ ድረስ ተጋደሉ። ከአባ ጳኵሚስም ዘንድ ዐሥራ ሦስት አመት ኖረ። ዳግመኛም በአስቄጥስ ገዳም ከአባ መቃርስ ጋር ብዙ ዘመናት ኖረ። ከዚሕም በኋላ በዋሻ ውስጥ ሰባት አመት ኖረ። አባ መቃርስም በከበረ በጌታችን የልደት በዓል እና የክብር ባለቤት ጌታችን በተነሳበት በትንሣኤ በዓል ቀን ይጎበኘው ነበር ከእርሱ ጋርም ሥጋውንና ደሙን ተቀብሎ ይመለስ ነበር። ሃያ ሁለት ዓመታት በተጋድሎ ፈጸመ j እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ ከሦስት ቀን በኋላ ከዚህ ዓለም ወጥተህ ወደ ዘለዓለም ሕይወት ትገባለህ አለው። ከሦስት ቀንም በኋላ አርፎ ወደ ዘለዓለም ሕይወት ገባ። በረከታቸው ይደርብን! አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
ረቡዕ ነገ ጠዋት መስከረም 22 በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ የሚሰራ የልማት ስራ ስለሚኖር የቻለ ሁሉም አባል ከጠዋቱ 2:30 ላይ በመገኘት የበኩሉን እንዲወጣ በሰማዕቷ ስም እንጠይቃለን።
