ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Відкрити в Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Показати більше602
Підписники
-124 години
-87 днів
-1830 днів
Архів дописів
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
መስከረም ፳፰ (28) ቀን።
እንኳን #ከብሉይ_ኪዳን_መጽሐፍ ውስጥ አንዱ በስማ ለተሰየመ #ለታማኟ_ለኬልቅዩስ_ልጅ #ለቅድስት_ሶስና_ለዕረፍት በዓል፣ #ለቅዱስ_አባዲርና_ለእኅቱ_ቅድስት_ኢራኢ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕታት #ኢራኢ_ከጳውፍርና_ከሐና_መነኰስ_ሉቃስም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
#የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እስመ አድኀንካ ለነፍስየ እሞት። ወለአዕይንትየኒ እምአንብዕ። ወለእገርየኒ እምዳኅዕ"። መዝ 55፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥8-22፣ 2ኛ ያዕ 4፥11-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 12፥12-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 8፥3-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
🌹🌹🌹🌹✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹
ማሕሌተ ጽጌ በግራር ደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን መስከረም 26 / 2016 ዓ.ም
ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
✨✨✨✨✨✨✨
▭▭▭ ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝ ▭▭▭
🔎
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የሳምንት ሰው ይበለን
✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
መስከረም ፳፯ (27) ቀን።
እንኳን #አስቀድሞ_በማንም_ላይ_ርኅራኄ የሌለው (ንፉግ) ለነበረ፤ በሕልሙ እግዚአብሔር በሳየው ራእይ ተመልሶ ስለ ምጽዋት ሲል ያለው ንብረት በሙሉ ከሰጠ በኋላ እራሱ ለሸጠ ለቀራጭች አለቃ ለነበረ #ለቅዱስ_አንጢላርዮስ_ለዕረፍት_በዓል መታሰቢያ፣ #በሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ ትምህርት አምና ለተጠመቀች ያለ ደም መፍሰሰ ሰማዕት ለሆነች #ለቅድስት_ጤቅላ (ቴክላ) ለዕረፍቷ በዓል መታሰቢያ፣ #ለቅዱስ_ኤዎስጣቴዎስ_ለሁለት_ልጆቹና_ለሚስቱም ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከመድኃኒታችን ከስቅለቱ #ከመድኃኔዓለም ከወራዊ ከመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
"#ሰላም_ለጤቅላ (ቴክላ) ዘሞአቶ ለተኵላ በገድል ንጽሕት ድንግል"። ትርጉም፦ ንጽሕት ድንግል በገድል ተኵላውን ያሸነፈችው ለኾነች #ለቅድስት_ጤቅላ (ቴክላ) ሰላምታ ይገባል። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ።
በመጨረሻ ግን ያ ሁሉ የመከራና የስቃይ ስደት ሲያበቃ «አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ» ሲል በመኃልየ ማኀልይ ዘሰሎሞን ተነግሮ የነበረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ከዚያ ሁሉ መከራና ስደት በኋላ ልጇን ይዛ ወደ ናዝሬት ተመልሳለች፡፡
ይህንንም የእመቤታችንን ስደት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ድረስ በማኅሌትና በመዝሙር ትዘክራለች፡፡ ካህናቱም በቀዳሚት ሰንበት ከምሽት ጀምረው በማኅሌትና በመዝሙር ምስለ ፍቁር ወልዳን /የልጇ እና የእርሷ/ ሥዕል ይዘው ቤተክርስቲያኑን ይዞራሉ፡፡ ይህም የእመቤታችንን ስደት ለማጠየቅ ነው፡፡ ሌሎችም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደረሰባቸውን መከራ ለማስታወስ የፍቃድ ጾም ይጾማሉ፡፡
እኛ ክርስቲያኖች በቅድስት ቤተክርስቲያን ተገኝተን በማኅሌተ ጽጌ ድርሰታችን በዜማ «መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ንጹሕ፣ ፀአዳ ፣ቀይህና ብሩህ የሚሆን ልጅሽን ታቅፈሽ ርኅሩኅ የሆነ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤልን አስከትለሽ ከሐዘናችንና ከችግራችን ታረጋጊን ዘንድ ፈጥነሽ ድረሽልን» ልንላት ያስፈልጋል፡፡ በቅዳሴያችንም «ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ ሄሮድስ ዘመን ከልጅሽ ጋር ከሀገር ሀገር ስትሸሺ ከአንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ከዓይንሸ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ፡፡ ድንግል ሆይ ረሐቡንና ጥሙን፣ ችግሩንና ሐዘኑን፣ ከእርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ›› እንላለን፡፡
✨✨✨✨✨✨የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ እና በረከት አይለየን።✨✨✨✨✨✨
የእመቤታችን ስደት የመጀመሪያው የሐዲስ ኪዳን ስደት ነው፡፡ ከገነት የተሰደደውን አዳምን ወደ ቀደመ ክብሩና መንበሩ ከዚያም ወደ ሚበልጥ ክብር ለመመለስ የተወለደው ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገና ከህፃንንቱ ጀምሮ ስደትን እና መከራን ተቀብሏል፡፡ ወንጌላዊው ማቴዎስ እንደጻፈው፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ጊዜ ሰብአ ሰገል «የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት አለ? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንስግድለት መጥተናል» እያሉ በኮከብ እየተመሩ በመጡ ጊዜ በይሁዳ፣ በገሊላና በሰማርያ የሮማውያን ተወካይ የነበረው ንጉሥ ሄሮድስ የጌታችን ንግሥና ምድራዊ ንግሥና መስሎት መንግስቴን ሊቀማኝ ነው ብሎ ደነገጠ፡፡ ፊሪሳውያን «መሲህ ተወልዶ ከሮማውያን አገዛዝ ነጻ ያወጣናል፡፡» ብለው ያምኑ እንደነበር ስለሚያውቅም ይህ የተፈጸመ መስሎት ጭንቀቱ በረታ፡፡ የተወለደውን ሕጻንን ለመግደል ተነሳ፡፡
ስለዚህም ሰብአ ሰገልን አስጠርቶ «ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔም እንድሰግድለት ወደ እኔ ተመልሳችሁ ያለበትን ንገሩኝ» በማለት በሽንገላ ተናገራቸው፡፡ ጠቢባኑም ከሄሮድስ ከተለዩ በኋላ በኮከቡ እየተመሩ ጉዞአቸውን ቀጥለው ጌታችንን ከእናቱ ጋር አገኙት ፤ ተንበርክከው ሰገዱለት፤ ወርቅ ፣ ዕጣን፣ ከርቤ እጅ መንሻ አቀረቡለት፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ሄሮድስ እንዳይመለሱ፤ ነገር ግን መንገድ ቀይረው ወደ ሀገራቸው እንዲሄዱ በነገራቸው መሠረት በሌላ መንገድ ወደ መጡበት ተደብቀው ተመለሱ፡፡ ሄሮድስም ሰብአ ሰገል እንደተሳለቁበት ባወቀ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ ጌታን ለማስገደል በማሰብ በአማካሪዎቹ ግፊት ጌታ በተወለደባት ከተማ በቤተልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን ከአንድ ዓመት ተኩል እስከ ሁለት ዓመት የሚሆን ዕድሜ ያላቸውን ሕጻናትን አስገደለ፡፡ ማቴ. 1፥13-18
እነርሱም (ሰብአ ሰገል) ከሄዱ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ «ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነስ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሸ፤ እስክነግርህም በዚያ ተቀመጥ አለው፡፡» ማቴ 2፥13-14 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ ልጄን ከግብጽ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብጽ ሔደ፡፡ ሄሮድስ እስኪሞት ድረስም በዚያ ኖረ፡፡ ማቴ 2-13-15 ተብሎ እንደተጻፈ ሁሉ፤ ዮሴፍም ተነሣ፤ በዕድሜዋ በጣም ልጅ የነበረችው እመቤታችን ገና የተወለደውን ሕፃን አቅፋ የምትቀመጥበት አህያም ተዘጋጀ፡፡ ጉዞአቸውን ጀመሩ፡፡ ከእስራኤል ወደ ግብጽ በእግር ለመሔድ የሲናን በረሃ ማለፍ የግድ ነው፡፡ በዚያን ዘመን ከእስራኤል ወደ ግብጽ የሚወስዱ ሦስት የተለያዩ መንገዶች ነበሩ፡፡ በሽፍቶች ላለመጠቃት መንገደኞች በቡድን በቡድን ሆነው በእነዚህ መንገዶች ይሔዱ ነበር፡፡
እነርሱ ግን ንጉሥ ሔሮድስ ተከታትሎ ሊይዛቸው ስለሚችል በእነዚህ መንገዶች መሔድ እንደሌለባቸው ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም በእግዚአብሔር መልአክ እየተመሩ ባልታወቁ መንገዶች መሔድ ነበረባቸው፡፡ ለበርካታ ቀናትና ሳምንታት ሸለቆዎችን በመውረድና ኮረብታዎችን እየወጡ ጉዛአቸውን ቀጠሉ፡፡ ሽማግሌው አናጢ ዮሴፍ ከፊት ሁኖ አህያዋን ባልተስተካከለውና ማለቂያ የሌለው በሚመስለው የበረሃ መንገድ ላይ ይመራ ነበር። ሰሎሜም ስንቃቸውን ይዛ ከኋላ ትከተል ነበር፡፡ በጣም አስቸጋሪ እና አስጨናቂ ጉዞ ነበር፡፡ ቀን ቀን የሚያቃጥለውን የፀሐይ ሐሩር ሌሊት ሌሊት ደግሞ የበረሀውን ውርጭ /ብርድ/ መታገል ነበረባቸው ምግባቸውንም በተአምራት ያገኙ ነበር፡፡
በመጨረሻም በመጽሐፈ ስንክሳር እንደተመዘገበው ግንቦት 24 ቀን ግብጽ ደረሱ፡፡ በግብጽም ባሉ የተለያዩ ከተሞች ተዘዋወሩ፣ ጌታም በተለያዩ ቦታዎች በርካታ ተአምራትን አደረገ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ተቀብለው ሲያስተናግዷቸው ሌሎች ደግሞ አሳድደዋቸዋል፤ መከራንም አጽንተውባቸዋል፡፡ በዚሁ ስደታቸው ወቅት ጌታ እና እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያም መጥተው ሀገራችንን ባርከዋል።
ለሦስት ዓመት ተኩል ያህል በስደት ከቆዩ በኋላ ሄሮድስ ሞተ። ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በግብጽ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ «የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ አለው፡፡ እርሱም ተነስቶ ሕጻኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል ሀገር ገባ» ማቴ 2-19-21/፡፡
ቅዱስ ዮሴፍ ይህንን «.. ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ..» የሚለውን የመልአኩን ቃል የሰማው ቁስቋም በምትባል በግብጽ ባለች ቦታ ነው፡፡ በኋላ በዚህች ቦታ ላይ ቤተክርስቲያን በእመቤታችን ስም ተሰርቶ ቅዳሴ ቤቱ ኅዳር 6 ቀን ተከብሯል። ሃያ ሦስተኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ (384-412 ዓ.ም) ደግሞ በጌታ እና በእመቤታችን ስደት ወቅት የሆነውን ነገር እንዲገለጥለት ለብዙ ጊዜ ጸሎት ካደረገ በኋላ ህዳር 6 ቀን እመቤታችን ተገልጣለት በጉዞው ወቅት የሆነውን ነገር ሁሉ ነግራዋለች፡፡ ስለዚህ ኅዳር 6 ቀን በሁሉም ምሥራቃውያን አብያተ ክርስቲያናት የእመቤታችን ከስደት የመመለሷ ነገር የሚታሰብበት ሁኗል ፡፡
ነቢያት ስለጌታ ትንቢት በመናገራቸው፣ እመቤታችን የጌታ እናት በመሆኗ፣ ሐዋርያት ስለጌታ በማስተማራቸው ተሰደዋል፡፡ የጌታ አገልጋይም እናትም የሆነችው የእመቤታችን ስደት ግን ከሁሉ የሚለይ ነው፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስደት ልዩ የሚያደርገው ሕግን በመተላለፉ ከገነት ተሰዶ የነበረውን አዳምን ለመካስ የተደረገ በመሆኑ እና በግብጽ ነግሦ የነበረውን አምልኮት ጣኦት ለማሳደድ የተደረገ ስለሆነ የጌታችንና የእናቱ ስደት ልዩ ነው፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከናዝሬት ወደ ግብጽ ስትሰደድ የቀን ሐሩር የሌሊት ቁር አግኝቷታል፡፡ እሾህ እየወጋት እንቅፋት እየመታት ተጉዛለች (ተሰዳለች)፤ በስደቷም ረሃብና ጥም፣ ችግርና መከራ ደርሶባታል፡፡ በበረሃው ወንበዴዎችን ባየች ጊዜም በስደት ከሄሮድስ ጭካኔ ከሀገር ያወጣሁትን ልጄን ይገድልብኛል ብላ መሪር እንባ አልቅሳለች፡፡በስደቷ ወቅት በደረሰባት ረሐብና ጥም የተነሣ ወደ መንደር ገብታ ብትለምን በችግር ምክንያት የሰው ፊት ማየት ከእሳት የበለጠ ወላፈኑ ስለሚያቃጥል የሰው ፊት ገርፏታል፡፡ የትእማን ቤተሰቦች ዘብተውባታል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም የመጣው ሸክማችንን ሊሸከም ነውና ውኃውን ለፍጥረታት የሚሰጥ እርሱ እየጠማው፤ እንስሳትን የሚመግብ እየራበው ምድርን በልምላሜ የሚያለብስ ተራቁቶ ፣የኛን ከገነት መሰደድ የመጣብንን ዕዳ ሊክስልን ከእናቱ ጋር ተሰደደ፤ ድንግል ማርያምም የአምላክ እናት ሆና መከራን ቀመሰች፡፡ ጌታን አዝላ በረሐብ አለንጋ ተገረፈች፡፡
✨✨✨የእመቤታችን ስደት ✨✨✨
«ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ ሄሮድስ ዘመን ከልጅሽ ጋር ከሀገር ሀገር ስትሸሺ ከአንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ ፤ ድንግል ሆይ ከዓይንሸ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ረሐቡንና ጥሙን፣ ችግሩንና ሐዘኑን፣ ከእርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ››
💫 ቅዳሴ ማርያም💫
የሰማዕታቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይፈጸማል።
በአዳማ ዙሪያ ወረዳ ቤተ ክህነት በአርቱ መካነ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል፡፡
---------------------------------------------
መስከረም 24/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያንን በማገልገል ላይ የሚገኙ ታላቁ የጸሎት አባት አባ ተክለ አብ እና ቀሲስ መሠረት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን መሪጌታ ፍሰሐ እና መርጌታ ተቅዋም የተባሉ አገልጋዮችን ታፍነው ባልታወቁ ኃይሎች መወሰዳቸውን የሀገረስብከቱ ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ዘግቧል።
በአዳማ ወረዳ ዙሪያ በቤተ ክርስቲያንና አገልጋዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የቀጠለ ሲሆን በታላቋ የጸበል ቦታ በመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ የተፈጸመው ይኼ አሰቃቂ ድርጊት ነውርና ግፍ አሰቃቂና አሳዛኝ ጥቃት ስለሆነ አሁንም መሰል ጥቃት እንዳይስተናገድ የሚመለከተው አካል በርካታ ጸበልተኛ በቦታው ስለሚገኝ አስፈላጊ ጥበቃ እንዲደረግ ጥያቄ ቀርቧል።
በተፈጸመው ግፍና በደል የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ማዘኑን የገለጸ ሲሆን ከሚመለከተው አካል ጋር በጉዳዩ ዙሪያና ጥብቅ ጥበቃ በሚደረግበት ዙሪያ እየተነጋገረ መሆኑን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ገልጿል::
EOTC MK
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
መስከረም ፳፮ (26) ቀን።
እንኳን #ለእናታችን_ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም ለልጇ ለወዳጇ ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለመድኃኒታችን ##ለኢየሱስ_ክርስቶስ ለስደታቸው መታሰቢያ #ለፈቃድ_ጾም_ለጽጌ ጾም (ለዘመነ ጽጌ) እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
"#ሰላም_ለፅንሰትከ_በሠሌዳ_ከርሣ_ዘተገልፈ። ለኤልሳቤጥ እምከ እምድኅረ ወርኃ ኀለፈ። ዮሐንስ መልአክ እንተ ትኴንን አእላፈ። ከመ እፈጽም ዘወጠንኩ ስብሐቲከ ትሩፈ። በውስተ ዕዝንየ አልኆስስ መጽሐፈ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_26።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
እንኳን ለጽጌ ጾም (ዘመነ - ጽጌ) በሰላም አደረሰን/ አደረሳችሁ።
☞ ጾመ ጽጌ በየአመቱ መስከረም ፳፮ ተጀምሮ ኅዳር ፮ የሚጠናቀቅ ጾም ነው።
☞ ይህ ጾም የሚጾመውም ለ፵ ቀናት ወይም ለ፩ ወር ከ፲ቀን ነው።
☞ ጽጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ጸገየ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው ነው።
☞ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ስትሆን ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ብቻ ይጾሟታል።
☞ ይህች ጾም የሚጾምባት ምክንያት እመቤታችን ስደቷን በማሰብ ነው።እመቤታች ጌታችንን ይዛ መሰደዷን መራቧን መጠማቷን በማሰብ ነው።
☞ ይህች ጾም ምንም እንኳን ከ፯ቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል ባትሆንም እንድንጾማት በአዋጅ ባንታዘዝም በፈቃዳችን በመጾማችን ከጾሟ ረድኤት በረከት የምናገኝባት ነች።
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ከመስከረም ፳፮ (26) ጀምሮ እስከ ሕዳር ፮ (6) ያሉት ሳምንታት ውብ ናቸው ምክንያቱም በማኅሌተ ጽጌ እና ጾመ ፅጌ (የፈቃድ ጾም ) እማምላክን ከነልጇ እንለምንበታለን ስደቷን እናስብበታለን፣ የእመቤታችንን ፍቅሯን እናትነቷን አማላጅነቷን ከሊቃውንቱ ጋር ሆነን በዝማሬ እናወድስበታለን ፣ ሰንበትን ከጌታ ከኢየሱስ ከኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ሌሊቱን በምስጋና በያሬዳዊ ዜማ ሳምንቱን ደግሞ በፈቃዳችን ማንም ሳያዘን የድንግል ማርያም ፍቅሯ አክብረን እንጾማለን።
♥️♥️እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ !!!
♥️የእመቤታችን ፍቅሯ ይብዛልን !!!
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
*ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ*
✝️ *አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም።*
መላካም ንባብ!
✝️ *ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ በሥዕሉ ላይ አድሮ ቅዱሳን የሆኑ ባስልዮስንና ጎርጎርዮስን በመርዳት ከሃዲውን ንጉሥ ዑልያኖስን እንደቀሰፈው እኛንም ሀገራችን ኢትዮጵያንም ከክፉዎች ሁሉ ይታደገን።*
✝️ *መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ወላጆቹ አስሊጥ ከምትባል ሀገር ቢሆኑም እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡*
✝️ *በከሃዲው ንጉሥ በዑልያኖስ ዘመነ መንግሥት ሁለት ደጋግ የቂሳርያ ኤጲስ ቆጶሳት ነበሩ የአንዱ ስም ባስልዮስ የሁለተኛውም ስም ጎርጎርዮስ ነበር።*
✝️ *ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ሁለቱን ኤጲስ ቆጶሳት ጠርቶ ለረከሱ ጣዖቶቹ እንዲሰግዱ አዘዛቸው። እነርሱም እግዚአብሔርን አንክድም ለሰይጣን አንሰግድም አሉ።*
✝️ *ከዚህ በኋላ ንጉሡ ዑልያኖስ እኔ ወደ ጦር ግንባር እየወጣሁ ነው : ድል አድርጌ እስክመለስ ለአምላኬ ለአጵሎን ባትሰግዱ ታላቅ ቅጣትን እቀጣችኋለሁ አንገታችሁንም እቆርጠዋለሁ አላቸው።*
✝️ **ቅዱሳኑ ባስልዮስ እና ጎርጎርዮስም እኛስ ለጣዖት አንሰግድም ከጦርነቱ በ ሰላም ከመጣህ በእኛ ላይ የወደድከውን አድርግ አሉት።*
✝️ *በዚህ የተበሳጨው ንጉሥ ከውጊያ እስክመለስ ብሎ ሁለቱን ኤጲስ ቆጶሳት ወደ ወህኒ ወረወራቸው።*
✝️ *ቅዱስ ባስልዮስ እና ጎርጎርዮስ በታሰሩበት ወህኒ ቤት ውስጥ በእንጨት ላይ የተሰቀለ የሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕል ነበረ።*
✝️ *ኤጲስ ቆጶሳቱ በስዕሉ ፊት በጊዜ ቆመው እግዚአብሔር የመረጠህ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሆይ ወደ አንተ ተማጽነናል፣ አትጣለን፣ አትናቀንም ጨካኙን ንጉሥ ዑልያኖስንም ወደ እኛ አትመልሰው ከስቃይ አድነን ፣ ከእጁም ታደገን ሥጋችን ደካማ ነውና ብለው ጸለዩ።*
✝️ *ከጸሎታቸው በኋላ ተኙ። የእኩለ ሌሊት ጸሎት ሊያደርሱ ከመኝታቸው ሲነሱ ቀን የተማጸኑት የቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕል በተሰቀለበት ቦታ ላይ አልነበረም: ቢፈልጉትም ሥዕሉን አጡት።*
✝️ *እጅግ እየተገረሙ የእኩለ ሌሊት ጸሎታቸውን ፈጽመው ተኙ። ደግሞ ለማለዳ ጸሎት ሲነሱ ግን የቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕል ቀድሞ በተሰቀለበት ቦታ ላይ ተመልሶ ተሰቅሎ አገኙት!*
✝️ *ኤጲስ ቆጶሳቱ ተደንቀው ወደ ሥዕሉ ቀርበው ቢመለከቱ ሥዕሉ ላይ ካለው የቅዱስ መርቆሬዎስ ጦር ጫፍ ላይ ትኩስ ደም ይንጠፈጠፍ ነበር፡፡ ኤጲስ ቆጶሳቱ በመገረም እንዲህ አሉ አሉ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሆይ የት ጠፋህብን? የክርስቶስ ምስክር ጌታችን መርቆሬዎስ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን? ከእጁም ታደግከንን? አሉት: : በዚያን ጊዜ ሥዕለ ቅዱስ መርቆሬዎስ አዎን እንደሚል ሁሉ እየተንቀሳቀስ አንገቱን ዘንበል አደረገ።*
✝️ *በነጋታው ከሃዲው ንጉሡ ዑልያኖስ መሞቱ እውን መሆኑ በሀገሩ ሁሉ ተነገረ። ኤጲስ ቆጶሳትም ቅዱስ መርቆሬዎስ ያደረገላቸውን ተአምር አደነቁ።*
✝️ *ዛሬ በባለ ጥቁር ፈረሱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕል ላይ ከጎኑ አብረው ተስለው የምናያቸው ሁለቱ ኤጲስ ቆጶሳት ባስልዮስ እና ጎርጎርዮስ ናቸው። ሥዕሉ ላይም በጦሩ ጫፍ የምናየው ደምም የዚህ ድንቅ ተአምር መዘከሪያ ነው።*
✝️ *ፍጡነ ረድኤት ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሆይ እባክህን ቅዱስ ባስልዮስ እና ቅዱስ ጎርጎርዮስን እንዳዳንካቸው እኛንም ከክፉ ሁሉ አድነን። የቅድስት ሀገር የኢትዮጵያን እና የከበረች የተዋህዶ ጠላቶችን ዑልያኖስን በወጋህበት ጦርህ ውጋልን።*
*የቅዱስ መርቆሬዎስ በረከት በየቤታችን ይድረስ።*
✨✨✨ብሩህ ቀን✨✨✨
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://instagram.com/finotebirhanarsema?igshid=ZGUzMzM3NWJiOQ==
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
መስከረም ፳፭ (25) ቀን።
እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት አንዱ ለሆነው #ለየዋሁ_ለቅዱስ_ዮናስ_ለዕረፍት_በዓል፣ #ለክረምት_መውጫ (ማብቅያ) ቀን በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ከፎቃ፣ #ከዮሐንስ_ከእንድራዎስ_ከጴጥሮስ_ከጳውሎስ፣ #ከእንጦንዮስ_ከበርባራ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
"#ሰላም_ለዮናስ_በከርሠ_አንበሪ_ዘኖመ። አምሳለ ክርስቶስ ይኩን በውስተ መቃብር ተኀትሙ። እግዚአብሔር ይቤሎ ጊዜ በሑሩር ሐመ። ኢይሣሃላኑ ለነነዌ ወኢይምሕካኑ ፍጹመ። እንዘ አንተ ትምሕክ ዘኢተከልከ ሐምሐመ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ አርኬ የመስከረም 25።
#የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠፅኮ እግዚኦ። ወዘመሀርኮ ሕገከ። ከመ ይትገኃሥ እመዋዕለ እኩያት።" መዝ 93፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥21-24።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔የንግስ በዓል ጥሪ🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
✨✨✨መስከረም 29 ሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ በዓለ ዕረፍት ✨✨✨✨
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
በዖታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኅብሪ ዖታ።እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልሀተ ኩያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታ።ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ። ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ።ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ።
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
✨✨✨✨ እንኳን ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ
ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
✨✨✨✨✨✨✨
▭▭▭ ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝ ▭▭▭
🔎
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
መስከረም ፳፬ (24) ቀን።
እንኳን #ከሰባ_ሁሉቱ_አርድእት ለአንዱ ለሐዋርያው #ለቅዱስ_አድሊጦስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ #ከላይኛው_ግብጽ ለሆኑ ለ#ቅዱስ_አባት_ለመነኰስ_ለአቡነ_ጎርጎርዮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
#ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት_አንዱ_የሆነው #ሐዋርያው_ቅዱስ_አድሊጦስ፦ ይህም ሐዋርያ ትውልዱ ከአቴና አገር ከታላላቆቿና ከምሁራኖቿ ነው እርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ አገለገለውም።
"ሰላም ለጎርጎርዮስ ወለደብራጦስ አያዩ። ዘውኂዘ መንፈስ ሰትየ ከመ ሐዋርያት ሰትዩ። ሶበ ገደፈ ቅድሜሁ እስከ ዘዕለት ሲሳዩ። ዘሎቱ ለሊሁ ወዘአበዊሁ አጥረዩ። ሥርዓተ ማኅበር ሐነፀ ጳኵሚስ በንዋዩ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 24።
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
መስከረም ፳፫ (23) ቀን።
እንኳን #ለቅዱሳን_ጻድቃን መነኰሳት #አውናብዮስና_እንድርያኖስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና #ለሰማዕቱ_ቅዱስ_ኤዎስጣቴዎስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከመርዓተ_ክርስቶስ (ከክርስቶስ ሙሽራ) #ከቅድስት_ድንግል_ቴክላ ለመታሰቢያ በዓል፣ #ከአርባ_አራት_ሰማዕታት፣ #ከመንክራዊ_ጎርጎርዮስ #ከእንጺናና_ከብሊናም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
# ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
"#ሰላም_ለአውናብዮስ_ወለእንድርያስ_ውሉዳ። ለምድረ ጊዮርጊስ ልዳ። እለ ኮኑ ስምዐ ለምድረ ዮልያኖስ በዐውዳ። ወሰላም ለቴክላ መርዓተ ክርስቶስ እንግዳ። ከመ ስንክሳር ወደሳ ወንዕዳ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ_የመስከረም_23።
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
መስከረም ፳፪ (22) ቀን።
እንኳን #ለፋርስ_ንጉሥ_ለሳቦር_ልጆች ለከበሩ #ለቅዱስ_ኮቶሎስና_ለእኅቱ_ቅድስት_አክሱ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለከበረ #ለቅዱስ_ዮልዮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕት_ከቅዱስ_ባላን ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
#የፋርስ ንጉሥ የሳቦር ልጆች ሰማዕታት ቅዱስ ኮቶሎስና እኅቱ ቅድስት አክሱ፦ ለቅዱስ ኮቶሎስም ጣጦስ የሚባል ክርስቲያን ወዳጅ አለው ይህም ንጉሥ ሳቦር እሳትን የሚያመልክ ነው ብዙዎች ምእመናንን ስለሚያሠቃያቸው ክብር ይግባውና የክርስቶስን ስም ይጠራ ዘንድ በዚያ ወራት የደፈረ የለም።
"#ሰላም_ለኮቶሎስ_አኅወ_እክሱ_ብፅዕት። ወፍቁረ ጣጦስ ሰማዕት። ሶበ አተበ በመስቀል ትእምርተ ሕይወት። መጠነ ዐሠርቱ ወክልኤቱ በእመት። እምዐውደ ምኵናን ሰሰለ እሳት"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_22።
✨✨✨✨✨✨✨ሰንበተ ክርስቲያን ✨✨✨✨✨✨
˝አሁንም ክብርት በምትሆን በዚች ዕለት በሕይወታችን ዘመን ሁሉ በፍጹም ሰላም ሁሉን የሚይዝ አምላካችን እግዚአብሔር ይጠብቀን ዘንድ እንለምነው ‟
˝ወዮ ይህች ዕለት አብ የቀደሳት ወልድ የባረካት መንፈስ ቅዱስ ከፍ ከፍ ያደረጋት ናት።
በእርሷ ደስ ይበለን ። በእርሷም ሀሴትን እናድርግ ትከብሩባት ዘንድ አክብሯት !
ዘመን ወር ለመባል በእርሷ የታወቃችሁ ሌሎች ዕለታት ሆይ የበዓላትን በኩር ኑ አመስግኗት ይህቺውም የከበረች ሰንበተ ክርስቲያን ናት።‟
✨✨✨ሰንበተ ክርስቲያን ✨✨✨ፍ/ብ/ሚ መስከረም 20
የብፁዕ አቡነ ሰላማ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፀመ።
መስከረም 20 /2016 ዓ.ም (ፍ.እ.ሚ. /አዲስ አበባ )
የብፁዕ አቡነ ሰላማ ሥርዓተ ቀብር ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፀመ ።
የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን
