cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

DW Amharic

Doische Welle /amharic Page Dwamharic.gmail.com

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
172
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሄዳል ******************* የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን መደበኛ ስብሰባውን ነገ እንደሚያካሄድ አስታወቀ፡፡ ምክር ቤቱ ነገ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባው የ6ኛ አመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን መርምሮ በማጽደቅ ይጀምራል፡፡ ምክር ቤቱ የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ መንግስት እና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም እንዲሁም ለሴቶች ኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡ በኢትዮጵያ መንግስት እና በዳንስኬ ባንክ ኤ.ስ መካከል ለብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የሜቲዎሮሎጂ ምልከታ መሰረተ ልማት እና የትንበያ አቅም ግንባታ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያፀድቅም ተነግሯል፡፡ በተጨማሪም የምርጫ ጉዳዮች በፍርድ ቤት የሚስተናገዱበት የሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ረቂቅ ደንብንም መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራው ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Показати все...
"በትግራይ ክልል ምርጫ አይካሄድም" - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ እስካሁን ባለው እቅዱ በፀጥታ ችግር ምክንያት በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የትግራይ ክልልን አለማካተቱን የምርጫ ቦርድ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተሯ ሶሊያና ሽመልስ ለአብመድ ተናገሩ። የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ያለባቸው አካባቢዎች ምርጫ አይካሄድባቸውም ወይ ? ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ፥ ቦርዱ ምንም እንኳን የፀጥታ ጉዳይ ተቋማዊ አብይ ተግባሩ ባይሆንም ስለ ሰላማዊነቱ በምርጫው ሂደት የፀጥታ ጉዳዮችን ከመንግስት ከሚከታተለው መዋቅር እና ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጥምረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ የወሰንና ማንነት ጉዳዮች በሚመለከታቸው አካላት ውሳኔ ሲያገኙና ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታዎች ካሉ ቦርዱ ምርጫ ማካሄድ ይችላል ብለዋል። ሆኖም እንደ ሀገር ለታለመው ፍሐዊና ሰላማዊ ምርጫ በተለይም በፀጥታው ዘርፍ ተግባር ላይ የምርጫ ቦርድና የፀጥታ ተቋማት ብቻ ውጤታማ ማድረግ ስለማይችሉ ሁሉም ተሳታፊነቱንና አጋርነቱን ማሳየት ይኖርበታል ብለዋል። (AMMA)
Показати все...
በአዲስ አበባ አያት አደባባይ አካባቢ በሱቆች ላይ የተነሳው እሳት ወደ ሌሎች ሳይስፋፋ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ ትላንት ምሽት 3 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ አያት አደባባይ አካባቢ በሱቆች ላይ የተነሳው እሳት ወደ ሌሎች ሳይስፋፋ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ ። በሱቆች ላይ የተነሳው የእሳት አደጋ በተደረገው ፈጣን ከፍተኛ ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት አስታውቋል። የከተማ አስተዳደሩ የእሳት አደጋው ወደ ሌሎች ሱቆች እንዳይዛመት የእሳት እና አደጋ መከላከል ሰራተኞች ፣የአካባቢው ማህበረሰብ እና የጸጥታ አካላት ላደረጉት ርብርብ ምስጋና አቅርቧል። ህብረተሰቡ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ በማድረግ አካባቢውን እንዲጠብቅም ጥሪ ቀርቧል፡፡
Показати все...
በሕገ ወጥ መንገድ ተይዘው የተገኙ 21 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ ይተላለፋሉ በአዲስ አበባ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ ለግለሰቦች ተላልፈው የተገኙ 21 ሺሕ ሕገ ወጥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ እንደሚወጣባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። ከተማ አስተዳደሩ በአዲስ አበባ በተለያዩ ጊዜያት ተካሂደዋል ያላቸውን የመሬት ወረራዎች በጥናት ማረጋገጡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥር 18/2013 በሸራተን አዲስ ሆቴል በሰጡትጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። ምክትል ከንቲባዋ መግለጫውን በሰጡበት ወቅት በሕገ ወጥ መንገድ ለግለሰቦች ተላልፈው የተገኙ 21 ሺሕ 697 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ እንዲወጣባቸው በምክር ቤት መወሰኑን አስታውቀዋል።
Показати все...
በትግራይ ክልል በሰላማዊ ዜጎች በደረሰው አደጋ ማዘኑን መንግስት ገለፀ የመንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፦ ያለፈው ጥቅምት በተጀመረውና መንግሥት «የሕግ ማስከበር» ባለው ዘመቻ ወቅት በንፁሃን ዜጎች ለደረሰው ማንኛውም ጉዳት የኢትዮጵያ መንግስት ማዘኑን አስታውቋል። መንግስት አያይዞም በዘመቻው ወቅት በአንድ ሰላማዊ ሰው ላይ የሚደርሰው ሞት እንኳ አሳዛኝ መሆኑን ገልፆ ሆኖም ዘመቻው በጥንቃቄ የተካሄደ በመሆኑ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች አልተጎዱም ማለቱን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ያሳያል። በክልሉ የንፁሃን ዜጎችን ሞት በተመለከተ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሚሰራጨው ዘገባም «ከእውነት የራቀና በመረጃ ያልተደገፈ» ነው ብሏል። የሞቱ ሰላማዊ ዜጎች ምን ያህል እንደሆኑ ግን ቁጥራቸውን ከመግለፅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያው ተቆጥቧል። (የጀርመን ድምጽ )
Показати все...
ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን በካፒቶል ሂል አመጽ የሞተውን ፖሊስ ያላቸውን ክብር ገለጹ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደንና ባለቤታቸው ጂል በካፒቶል ሂል በተፈጠረው አመጽ ቆስሎ ለሞተው ብሬን ዲ.ሲክኒክ ለተባለው ፖሊስ ያላቸውን ክብር ገልጸዋል፡፡ የፖሊሱ አስከሬን ለክብሩ ሲባል በካፒቶል ሂል በሚገኘው በታሪካዊው ሮቱንዳ ነበር የተቀበረው፡፡ የ42 አመቱ ሲክኒክ ጭንቅላቱን መመታቱን አባቱ ገልጿል፡፡ ሲክኒክ በአመጹ ከተጠቁት አምስት ሰዎች አንዱ ነበር፡፡
Показати все...
ባለፉት ስድስት ወራት ህግን በተላለፉ 46 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ ባለፉት ስድስት ወራት ህግን በተላለፉ የንግድ እና የማምረቻ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባካሄደው ክትትልና ቁጥጥር ህግ ተላልፈው በተገኙ 46 ድርጅቶች ላይ ከማስጠንቀቂያ እስከ እገዳ የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን በሚኒስቴሩ የገበያና ፋብሪካ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሬ ዳይሬክተር አቶ ተከተል ጌቶ ተናግረዋል፡፡ የንግድ እና የማምረቻ ድርጅቶቹ እርምጃ የተወሰደባቸው ከተሰጣቸው የንግድ ስራ ፈቃድ ዉጪ በመነገድ፣ ባልታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ በመነገድ፣ በምርት ጥራት መጓደል እና ብሄራዊ የምልክት አጠቃቀም መመሪያን ተግባራዊ ባለማድረግ ምክንያት መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ የንግድ ድርጅቶችም ሆኑ የማምረቻ ተቋማት ስራቸውን በስነ ምግባር መስራት እንዳለባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ በቀጣይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለጥራት ብሎም ለአዋጆች ተግባራዊ መሆን ልዩ ትኩረተ ሰጥቶ እንደሚሰራ የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ህግና ሥርዓትን ተላልፈው የሚሰሩ ድርጅቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ልማሳሰባቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ብስራት ራዲዮ ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
Показати все...
የሸማቾች ጥበቃ እና ውድድር ባለስልጣን ሸማቾችን ያሳስታሉ በሚል 3 ማስታወቂያዎችን አገደ። ባለስልጣኑ ከአዋጁ ጋር የሚጻረሩ የንግድ እቃዎችና የአገልግሎት ማስታወቂያዎች ላይ እርምጃ መዉሰዱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ ገልጿል። በግማሽ ዓመት አፈፃፀም የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለ ስልጣን ባወጣው ሪፖርት መሰረት ከአዋጅ ቁጥር 813/2006 ጋር የማይጣጣሙ የንግድ ዕቃዎችና የአገልግሎት ማስታወቂያዎችን 48 ጊዜ በመከታተል እና ከአዋጁ ጋር የሚፃረሩ የንግድ ማስታወቂያዎች ላይም በግማሾቹ ላይ የማስታወቂያ እግድ ሲወጣ ቀሪዎቹ ላይ ይዘታቸው እየተጣራ መሆኑን አስታዉቋል፡፡ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ላይ ሲተላለፉ የነበሩ ከሴራሚክ ሽያጭ፣ የቀለም ሽያጭ፣ ከዲኮደር ሽያጭ፣ ከታሸገ ዉሃ ማስታወቂያ እና ለትራንፖርት አገልግሎት ከሚዉሉ ታክሲዎች ከቀረጥ ነፃ አቅርቦት ጋር በተገናኘ የሚተላለፉ የንግድ ማስታወቂያዎች ግልፀኝነት የጎደላቸዉና ሸማቹን ሊያሳስቱ ይችላሉ በማለት 3ቱ ሲታገዱ የ 2 ማስታወቅያዎች ይዘት እየተጣራ ይገኛልም ተብሏል በሪፖርቱ፡፡ በተጨማሪም የ2013 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓላትን ምክንያት በማድረግ በ14 የሴትና የወንድ ልብስና ጫማ መሸጫ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ፈርኒቸር መሸጫ የንግድ መደብሮች ስለዋጋ ቅናሽ የተለጠፉ የውጭ ማስታወቂያዎች ላይ ክትትል በማድረግ በ 10 የንግድ መደብሮች የተለጠፉ የንግድ ማስታወቂያዎች ግልፀኝነት የጎደላቸው እና አሳሳች ናቸው ተብለዋል፡፡ በዚህም በአዋጁ አንቀፅ 7 እና 8 መሠረት ማስታወቂያዎችን እንዲያስተካክሉ ከመደረጉም በላይ ተመሳሳይ ድርጊት ለወደፊቱ እንዳይፈፅሙ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡ በተያያዘም የህትመት ሚዲያ ላይ አሳሳች ማስታወቂያዎችን ከመከታተል አንፃርም የተለያዩ የህትመት ሚዲያ ላይ እየተሰራጩ የሚገኙ የንግድ ማስታወቂያዎች ይዘት ትክክለኛ ስለመሆኑ ምርመራ እንዲጀመር ተደርጓልም ተብሏል፡፡ (Ethio fm)
Показати все...
በመቐለ ከተማ ትምህርት የካቲት 1 ይጀምራል። በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ከፊታችን የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ/ም አንስቶ እንደሚጀመር የከተማዋ ጊዜያዊ ከንቲባ ኣቶ አታኽልቲ ኃለስላሴ ለኢፕድ አሳውቀዋል። በከተማዋ በመጀመሪያ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በኋላም መንግስት ህግን ማስከበር ዘመቻ ምክንያት ትምህርት ተቋርጦ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት የከተማዋ ሰለምና ጸጥታ የተረጋጋ በመሆኑና የኮሮኖ መከላከያ ጥንቃቄን ተግባራዊ በማድረግ በሁሉም ደረጃ ባሉ የትምህርት ክፍሎች ከየካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም አንስቶ ትምህርት መስጠት ይጀመራል ተብሏል። ወላጆች ልጆቻቸውን ከተጠቀሰው እለት ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ አቶ አታኽልቲ ጥሪ አቅርበዋል። በአሁኑ ወቅት በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መደባኛ ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንም ከንቲባው አስታውቀዋል። (EPA)
Показати все...
337 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ ወደ አገር የተመለሱ ዜጎችን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Показати все...