የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Відкрити в Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Показати більше4 374
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
4 374
ት ያቀረበውን መሥዋዕት ቅድመ እግዚአብሔር በማድረስ የእግዚአብሔርን
ምሕረት ወደ ሰው በማምጣት ሰውን ከአምላካቸው ጋር በማማለድ ጸንተው ያሉ
እንደኾኑ በብዙ ሥፍራ ላይ ተዘርዝሯል፡- ለምሳሌ ያኽል ዘፍ 48፥15፤ ዘጸ
23፥20፤ መሳ 6፥11፤ ኢዮ 33፥23፤ መዝ 33፥7፤ 88፥6፤ 90፥11፤ 1ነገ
19፥5፤ 2ነገ 6፥15፤ ዳን 3፥17፤ 4፥13፤ 8፥15-19፤ ዘካ 1፥12፤ ማቴ
18፥10፤ ሉቃ 1፥19፤ 13፥6-9፤ 15፥7፤ ዮሐ 20፥11፤ የሐዋ 12፥6፤ ዕብ
1፥14፤ ራእ 8፥3-4ን ይመልከቱ)፡፡
የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን✞✞✞
✍✍ @EOTC2921 ✍✍
4 374
✞የቅዱስ ሚካኤል ክብር✞
❖ መልአክ የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲኾን “ለአከ” ማለት (ላከ) ማለት
ነው፤ ስለዚኽ መልአክ ማለት መልእክተኛ ማለት ነው፤ ይኸውም ሰው የጸለየውን
ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ የእግዚአብሔርን
ምሕረት ወደ ሰው የሚያመላልሱ ስለኾነ የተሰጣቸው ሥያሜ ነው፡፡
❖ ልዑል እግዚአብሔር ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ በዚያው በዕለተ
እሑድ መላእክትን “እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ” (ካለመኖር ወደ መኖር) ማእምራን
(ዐዋቂዎች) ለባውያን (አስተዋዮች) አድርጎ ፈጥሯቸዋል፡፡ ከነዚኽ መላእክት
ውስጥ አንደኛውና የመላእክት አለቃ የኾነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
❖ ቅዱስ ሚካኤል የሚመራቸው ነገደ ኀይላት የሚባሉ በኢዮር ሰማይ
የሚኖሩ መላእክትን ነው፤ ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ
“ወለራብዕ ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ ኀይላት ወሊቆሙ ሚካኤል ወአንበሮሙ በራብዕ
ሰማይ” ይላል አራተኛው ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን ኀይላት ሲላቸው እነዚኽም
ባለሰይፍ ሲኾኑ የእግዚአብሔርን ወዳጆች ሲጠብቁ ጠላቶቹን ይቀጣሉ፤
የእነዚኽ ነገደ መላእክት አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ሲኾን በኢዮር በአራተኛው
ከተማ አስፍሯቸዋል እንዲል፡፡
❖ ሳጥናኤል “እኔ ፈጣሪ ነኝ” ብሎ የክሕደት ንግግርን በተናገረ ጊዜ
አስቀድሞ ሰራዊቱን በመያዝ ከነገደ ዲያብሎስ ጋር የተዋጋ መልአክ ነውና፤
ዮሐንስም ስለ ቅዱስ ሚካኤል ኀያልነት በራእ ፲፪፥፯-፱ ላይ፡- “በሰማይም ሰልፍ
ኾነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፤ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ
አልቻላቸውምም ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም ዓለሙንም
ኹሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ ርሱም የቀደመው
እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከርሱ ጋር ተጣሉ” በማለት
ዲያብሎስን የተፋለመ መልአክ መኾኑን ገልጾታል፤ በዚኽም “መልአከ ኀይል”
ተብሏል፡፡
❖ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ስለኾነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፣
ውበት፣ ምልጃ ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው እንዲኽ
ይላል፡-
ስለ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃነቱ ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይለዋል፡-
╬ “ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ
በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ
ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ
ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ”
(የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤
በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን
ይለምናል) ይላል፡-
የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ከመኾኑ ጋር ይልቁኑ ዮሐንስ በራእዩ በምዕ 8፡2
ላይ “በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም
መለከት ተሰጣቸው” ካላቸው፤ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በመዠመሪያ
የሚጠቀሰው ቅዱስ ሚካኤል ነውና ሊቁ፡-
╬ “እስመ እምአፉሁ ይወጽዕ ነጐድጓድ
ሕብረ ክነፊሁ ያንበለብል ነድ
እምሊቃነ መላእክት የዐቢ በዐውድ
ሚካኤል ውእቱ መልአኩ ለወልድ”
(የወልድ አገልጋዩ ሚካኤል ነው፤ በዙሪያው ኹሉ ካሉት ከሊቃነ መላእክት
ይበልጣል፤ የክንፉ መልክ ነባልባላዊ እሳትን ያቃጥላል፤ ከአንደበቱ ነጐድጓድ
ይወጣልና)
╬ “አዕበዮ ንጉሠ ስብሐት
ለሚካኤል ሊቀ መላእክት
ዘይስእል በእንተ ምሕረት
መልአከ ሥረዊሆሙ ለመላእክት”
(የምስጋና ባለቤት ክርስቶስ ለመላእክት ጭፍሮች አለቃቸው የኾነ ስለ ምሕረት
የሚማልድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ከፍ ከፍ አደረገው) በማለት
ይጠቅሰዋል፡፡
❖ የስሙ ትርጓሜንም ስንመለከት ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን
ሚ- ማለት “ማን”፤ ካ- “እንደ”፤ ኤል- “አምላክ” ማለት ነውና ሚካኤል ማለት
“መኑ ከመ አምላክ” (ማን እንደ አምላክ) ማለት ነው፡፡
❖ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ይዞ
╬ “ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ
ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ”
(የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም ጋር ለተባበረ ስም አጠራርኽ
ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡
ቅዱስ ያሬድም፡-
╬ “መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ
ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ
መልአኮሙ ሥዩሞሙ
የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ”
(ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤
የተሾመላቸው አለቃቸው ርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል) ይላል
❖ በብሉይ ኪዳን ለአበው ነቢያት እየተገለጠ፤ ለሐዋርያትም በስብከት
አገልግሎታቸው እየተራዳ፤ ለሰማዕታት፣ ለቅዱሳን አበው በተጋድሏቸው
እየተገለጠላቸው አስደሳች መልኩን ያዩት ነበር።
❖ ይኽነን የቅዱስ ሚካኤልን ውበት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡-
╬ “መልአከ ፍሥሐ ዘዐጽፉ መብረቅ
ሐመልማለ ወርቅ ሚካኤል ሊቅ”
(መጐናጸፊያው መብረቅ የኾነ የደስታ መልአክ፤ አለቃ ሚካኤል የወርቅ
ዐመልማሎ ነው)
❖ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ውበቱን ሲገልጠው፡-
╬ “ሰላም ለአክናፊከ እለ በሰማያት ያንበለብሉ
ከመ ሠርቀ ፀሓይ ሥነ ጸዳሉ”
(የጸዳሉ ውበት እንደ ፀሓይ አወጣጥ የኾነ በሰማያት ለሚያንበለብሉ ክንፎችኽ
ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡
❖ ቅዱስ ያሬድ ደግሞ፡-
╬ “ውእቱ ሊቆሙ ወመልአኮሙ ሚካኤል ስሙ
ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ
ሐመልማለ ወርቅ”
(ዐይኑ የርግብ (እንደ ርግብ የዋህ፣ ጽሩይ) የኾነ ልብሱ የመብረቅ መጐናጸፊያ
የኾነለት የወርቅ ዐመልማሎ ስሙ ሚካኤል የተባለ ርሱ የመላእክት አለቃቸው
መሪያቸው ነው) ይላል፡፡
❖ መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብብ ሙሴን ከፈርዖን፣ ኢያሱን ከአማሌቅ፣
ሕዝቅያስን ከሰናክሬም፣ ዳዊትን ከጎልያድ እጅ በተራዳኢነቱ የጠበቀ ሲኾን፤ ስለ
ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነትና ተራዳኢነት ነቢዩ ዳንኤል፡- “ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ
ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ…ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርኻለኊ
በዚኽም ነገር ከአለቃችኊ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም… በዚያም
ዘመን ስለ ሕዝብኽ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል” በማለት
አማላጅነቱን መስክሮለታል (ዳን ፲፥፲፫፤ ፲፥፳፩፤ ፲፪፥፩)፡፡
❖ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና አማላጅነት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ
ይገልጠዋል፡-
╬ በ፲ወ፬ቱ ትንብልናከ ዐቢይ ልዕልናከ
በመንክር ትሕትናከ
አስተምህር ለነ ሰአልናከ”
(በዐሥራ አራቱ ልመናኽ ምልጃኽ፤ በታላቅ ልዕልናኽ በሚያስደንቅም ትሕትናኽ
ሚካኤል ትለምንልን ዘንድ ማለድንኽ)
╬ “ዘወሀበ ትንቢተ ለኤልዳድ ወሙዳድ
አመ ምጽአቱ ይምሐረነ ወልድ
ሰአል ለነ ሚካኤል መንፈሳዊ ነገድ
ከመ ንክሃል አምስጦ እምሲኦል ሞገድ”
(ለኤልዳድና ለሙዳድ የትንቢትን ጸጋ የሰጠ የሚኾን ወልድ በሚመጣ ጊዜ
ይምረን ዘንድ ከረቂቅ ነገድ ወገን የኾንኸው ሚካኤል ከሲኦል እሳታዊ ሞገድ
ማምለጥ እንችል ዘንድ ለእኛ ለምንልን) ይላል፡፡
╬ “ከናፍሪሁ ነድ ዘእሳት አልባሲሁ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ውእቱ
ይዕቀብክሙ ነግሀ ወሠርከ ሌሊተ ወመዐልተ” (ከናፍሮቹ የእሳት ልብሶቹ
የመብረቅ የኾነ የመላእክት አለቃ ሚካኤል በተራኢነቱ በጠዋትም፤ በሠርክም፤
በቀንም በሌሊትም ይጠብቃችኊ) እንዲል፤ ሙሴን ከፈርዖን፣ ኢያሱን ከአማሌቅ፣
ዳዊትን ከጎልያድ፣ ሕዝቅያስን ከሰናክሬም፤ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት፣ ሶስናን
ከረበናት፤ ቅድስት አፎምያን ከዲያብሎስ እጅ በምልጃው የታደገው፤
አስቀድሞም ዘንዶው ዲያብሎስን ተፋልሞ የጣለው ይኽ መልአክ ቅዱስ
ሚካኤል፤ ራሶቹ ሰባት ቀንዶቹ ዐሥር ከተባለው ዓለምን እየተበተባት ካለው
ከዘንዶው ከ666 የሐሳዌ መሲሕ ክፉ አሠራር በቀንም በሌሊትም ተራድቶ
ይጠብቀን እላለኊ (ራእ 12፡7፤ ራእ 13፡1-3)፡፡
❖ ቅዱስ ሚካኤልን ጨምሮ እነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ሰው የጸለየውን
ጸሎ
4 374
☞♣❀✞ #ጥምቀት ✞❀♣☜
በአብ ስም በወልድ ስም በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ አሜን፡፡
✔ጥር ፲፩ በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአጥማቂው ዮሐንስ ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ተጠመቀ፡፡
✔ይችም ዕለት በዮናኒ ቋንቋ ኤጲፋንያ ትባላለች። ትርጓሜው መለኮት የተገለጠበት ማለት ነው።
✔ልዩ የሆነች የሦስትነቱን ምሥጢር ገልጦባታልና አብ ከሰማይ ሁኖ የምወደው በርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት እያለ ሲመሰክር ወልድም በዮርዳኖስ ወንዝ ቁሞ ሳለ መንፈስ ቅዱስም በነጭ ርግብ አምሳል በወልድ ራስ ላይ ሲቀመጥ ታየ፡፡
✔ይህን አጥማቂው ዮሐንስ እንዲህ ሲል መሰከረ፡፡ "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ ከውኃ በወጣ ጊዜ ወዲያውኑ ሰማይ ተከፈተ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በጌታችን ራስ ላይ ተቀመጠ ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል መጣ ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ነው እርሱንም ስሙት፡፡" የሚል።
✔በዚች ዕለት ጌታችን ራሱን ገልጦአልና ከዚህ በፊት ሠላሳ ዓመት ያህል ራሱን አልገለጠም ነበር፡፡
✔በዚች ዕለት ለእስራኤል ልጆች ራሱን ገለጠ፡፡ እንሆ የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ ብሎ መጥምቁ ዮሐንስ እንደገለጠው የከበረ ወንጌል ምስክር ሆነ፡፡
✔እኔ አላውቅም ነበር ነገር ግን እስራኤል ያውቁት ዘንድ በውኃ ላጠምቅ ስለዚህ መጣሁ አለ፡፡
✔በዚህም በዓል የእግዚአብሔር ልጅ የክርስቶስ የጌትነቱ ክብር ተገልጧል እርሱም የዓለሙን ሁሉ ኃጢአት ለማስወገድ የሚሠዋ የእግዚአብሔር አማናዊ በግ ነው፡፡ ስለዚህም ይህ በዓል በክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ዘንድ የከበረና ከፍ ከፍ ያለ ሆነ፡፡
✔በርሱም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ በአከበረው ውኃ ይነጹበታል፡፡
✔የተቀበሉትንም ንጽሕና ጠብቀው ቢኖሩ በውስጡ የኃጢአታቸውን ሥርየት ያገኛሉ፡፡
✔ስለዚህ ከክፉ ነገር ሁሉ ተጠብቀን የፈጣሪያችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የቸርነቱ ብዛት ልናመሰግን ይገባናል፡፡ እርሱ ስለ እኛ ሰው ሁኖ ከኃጢአታችን አድኖናልና።
☞ "እውነት እውነት እልሃለሁ ዳግመኛ ከውሃና ከመንፈስቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም።" ዮሐ 3÷5
☞ "እንሆም፥ድምፅ፡ከሰማያት፡መጥቶ፦ በርሱ፡ደስ፡የሚለኝ፡የምወደ፟ው፡ልጄ፡ይህ፡ነው፡አለ።"ማቴ፡3፥17
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላምና በጤና አደረሳቹ፡፡
4 374
🌾✞ #ከተራ_የጥምቀት_ዋዜማ ✞🌾
✔ #ከተራ ማለት "ከበበ" ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን፡ ትርጕሙም ውሃን መከተር ወይም ውሃ መገደብ (መዝጋት፥ ማቆም፥ ማገድ፥ ማጠር፥ ዙሪያውን መያዝ፥ መክበብ፥ መከልከል) ማለት ነው፡፡
✔ #ከተራ_ለምን_ተባለ?
በጥምቀት በዓል ዋዜማ በጥር 10 ቀን ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ወይም ጉድጓድ ተቆፍሮ፤ ድንኳን ይተክላል፥ ዳስ ሲጣል ይውላል (ምክንያቱም ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናምና የበረዶ ወራት ስለሆነ ቅዝቃዜውም በወንዞች አጠገብ ስለሚያይል በባሕረ ዮርዳኖስ፥ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ድንኳን ተክለው፥ ዳስ ጥለው ያድሩ ስለነበረ ነው)፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት የምንጮች ውሃ ደካማ በመሆኑ ውሃው እንዲጠራቀም ወንዶች ጉድጓድ እየቆፈሩ፥ ሴቶች ውኃ በእንስራ እየቀዱ ከወንዞችና ከምንጮች ውኃውን ይከትራሉ፥ ይገደባሉ (አሁን በከተሞች ሰው ሰራሽ ግድብ ይገደባል)፡፡ የምዕመናኑ አብዛኛው ስራ ውሃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ #ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
✔ አንድም በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ባሕር ሲሻገሩ ታቦቱን ያከበሩ (የያዙ) ካህናት ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ከወንዙ መሃል ቆመው ነበር ውኃውም እንደ ባሕረ ኤርትራ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ቆሞ ነበርና ይህንንም ለማስታወስ ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡
✔ አንድም ጌታችን በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የላይኛው ሸሽቶ እንደ ክምር ተቆልሏል (ከአዳም ጀምሮ እስከ መድኅን መወለድ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ተቋርጦ ለመቅረቱ፥ ከአበው ወደ ውሉድ ላለመተላለፉ ምሳሌ)፤ የታችኛውም ወደ ታች ሸሽቶ በመድረቁ (የአዳም ኀጢአት ከሥሩ እንደተነቀለ ዛፍ ሆና ለመውደቋ ምሳሌ) ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡
✔ውኃ የሚከተርበት ቦታ " #ባሕረ_ጥምቀት (ጥምቀተ ባሕር)" (የታቦት ማደሪያ) እየተባለ ይጠራል፡፡ ውኃው የሚከተረውም በማግስቱ ጥር 11 ቀን ለሚከበረው የጥምቀት በዓል መጠመቂያና የጥምቀትን በዓል ለማክበር እንዲሆን ነው፡፡ ሌሊት ማኅሌት ተቁሞ፥ ቅዳሴ ተቀድሶ፥ ጠዋት ጸሎት ተደርሶ የሚጠመቅ ሕፃን ካለ እዚያው ውስጥ ይጠመቃል፡፡ ጐበዛዝትም ለቡራኬ ይዋኙበታል ምዕመናንም እንዲሁ ለቡራኬ ይረጩታል፡፡ ያ ስፍራ በዘልማድ ጥምቀተ ባሕር ተብሎ ይጠራል፡፡
✔ #ሥርዐተ_ከተራ ታቦተ ሕግ ይዞ መጓዝና ወደ ወንዝ መውረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ቀድሞ በሙሴ ኋላ በኢያሱ መሪነትም ታቦተ ሕጉን ይዘው የዮርዳኖስን ባሕር መሻገራቸውንም ልብ ይሏል፡፡ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁት ጊዜ ከስፍራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት፡፡ /ኢያ.3፥3/ እንዲል፡፡
✔ የከተራ ዕለት ድንኳኑ ተተክሎ፥ ዳሱ ተጥሎና ውሃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የደወል ድምፅ እንደተሰማ ከልጅ እስከ አዋቂ በነቂስ ተወጥቶ በዐፀደ ቤተ ክርስቲያንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ይሰበሰባሉ፤ የየአድባራቱና የገዳማቱ ታቦት በካህናት አማካይነት በወርቅና በብር በተንቈጠቆጠ መጐናጸፊያ እየተሸፈኑ በታቦት ጉዞ (በዝግታ) ወደ ጥምቀተ ባሕሩ ይጓዛሉ፡፡ በዚህም ጊዜ፤ ባለ መስቀል መፆር ሰንደቅ ዓለማና ዓርማ የያዘው ግን ከሁሉም ፊት ፊት እያለ ቀድሞ ይሄዳል፡፡ የወርቅ (ወርቀዘቦ) ካባና ላንቃ የለበሱና ጥላ የያዙት ቀሳውስትና መነኰሳት ከታቦቱ ጐን፤ መስቀልና ጽንሐሕ የያዙት ከታቦቱ በፊት ማዕጠንት እያጠኑ ይሄዳሉ፡፡ እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብስ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ ድባብ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ በፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡ ወደ ባሕረ ጥምቀቱም ሲወረድ ካባ ላንቃ፥ ጥንግ ድርብ በለበሱ፥ የብር፣ የነሐስ፣ የወርቅ መቋሚያና ጽናጽል በያዙ በማኅሌታውያን መዘምራን ደባትር ሃሌታ፣ በሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ዝማሬና ሽብሸባ፣ በወጣት መዘምራን ደስታ፣ በወንዶች ሆታ፣ በሴቶች እልልታ ዲያቆናቱን ቀድመው እያጀቡ ይሄዳሉ፡፡ የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ ሕዝቡም "ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ" እንዲሉ እንደየ ችሎታው ያለውን ልብስ (ጃኖ፣ ለምድ፣ በርኖስና የመሳሰለውን) ለብሶና አጊጦ፥ ሽማግሌዎችና የጐበዝ አለቃዎችን በማስቀደም ታቦቱን በመከተል በስተኋላ ይሄዳሉ፡፡ ነገር ግን ሴቶችና ልጆች እንደፈለጋቸው ከፊትም ከኋላም ሆነው ይሄዳሉ፡፡
✔ ባሕረ ጥምቀትም እንደደረሱ ታቦቱ በድንኳን አጠገብ ቆሞ የዓመቱ #ተረኛ_ደብር (የምራት ባለተረኛ) “ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥምቃት፤ በፍሥሓ ወበሰላም" (እግዚአብሔር ወልድ በሰላምና በደስታ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከሰማያት ወደ መጠመቂያው ወረደ) የሚለው ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተድርጐ ሲያልቅ ታቦቱ ወደ ድንኳኑ ይገባል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ ግሱን ለመቃኘትና ለማሸብሸብ፣ ማኅሌት ለመቆም፣ ቅዳሴ ለመቀደስና ሌላውንም ሥርዐት ለመፈጸም ኃላፊነት ያለባቸው ተረኛ ደብር (የምራት ባለተረኞች) ሲሆኑ ለቀጣዩ (ለከርሞ) ዓመት ተረኞች የሚሆኑና በአሁኑ ዓመት የምራት ባለተረኞችን የሚረዱት ገዳማትና አድባራት ደግሞ ‹‹አንሺዎች›› ይባላሉ፡፡
✔የከተራ ዕለት የየአጥቢያው ሕዝብ በየዓመቱ ተራ እየገባ ራት ከየአካባቢው ስለሚያመጣ ያ ሲበላና ሲጠጣ ከቆየ በኋላ ወዲያው የሌሊቱ ጸሎት(ስብሐተ ማኅሌቱ) በተረኛው ደብር ካህናት ተጀምሮ አገልግሎቱ መላ ሌሊቱን ሲካሄድ ያድራል (እንደ ቀጨኔ ባሉ ታላላቅና የሊቃውንት መፍለቂያ አድባራት ተረኛ ቢሆኑም /በጥምቀተ ባሕሩና በቤተ ክርስቲያናቸው ጭምር/ ባይሆኑም በቤተ ክርስቲያናቸው ማኅሌቱን ቆመውና ቅዳሴውን ቀድሰው ያድራሉ)፡፡ ቅዳሴው የሚቀደሰው ከሌሊቱ 7-9 ሰዓት ነው፡፡
✔ በከተራ ዕለት የሚከናወኑ ድርጊቶች ምሳሌነት አላቸው እነዚሁም፤
#ታቦቱ የጌታችን ምሳሌ
#ታቦቱን_አክብሮ_ይዞ_የሚሄደው_ካህን የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ምሳሌ
#ባሕረ_ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ ምሳሌ
#ታቦታቱን_አጅበው_የሚሄዱት_ምዕመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩ ሰዎች ምሳሌ
#ታቦታቱ_በከተራ_ዕለት_ከመንበራቸው_ወደ_ጥምቀተ_ባሕር_መውረዳቸው መድኀኔዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተራውን ሲጠብቅ አድሮ መጠመቁን ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡››ማቴ፡ 3፥13
#ጥምቀቱ የሞቱ፤ አርአያ፤ የመቃብሩ አምሳል ነው፡፡
✔ በዓለ ጥምቀት ሰንበት (ቅዳሜና እሑድ ላይ) ካልዋለ የሚታረሰው መሬት ረድኤት በረከት ስለሚገኝበት ገበሬው አንድ ሁለት ፈር ያርሳል፡፡
✔ በዓለ ጥምቀት ዐቢይ በዓል ስለሆነ የጥሉላት (የፍስክ) ምግብም ጭምር ስለምንመገብበት ዘንድሮ ሰኞ ስለሚውል ዋይዜማውን እሑድን የጋድ ጾም (ከጥሉላት መባልዕት) እንጾማለን፡፡ የሚቈርብ ሰው ግን አክፍሎ ያድራል፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾✞ #ጾመ_ገሃድ ✞🌾
#ለህዝበ_ክርስቲያን_በሙሉ
✔በመጀመሪያ እግዚአብሔር አምላክ ብርሃነ ልደቱን በሰላም አድርሶ እንዳሳለፈን አሁንም ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላምና በጤና ያድርሰን አሜን፡፡
ስለ ጾመ ገሃድ ብዙ ክርክሮችን እንሰማለን፡፡ እናም መቼ እንደሚውልና ስለ ጾሙ ምንነት ልናካፍላችሁ ወደድን እነሆ ሁሉም ላልሰማ ያሰማ፡፡
#ገሃድ ማለት ለውጥ ወይም ልዋጭ ማለት ሲሆን። የቃሉ ፍቺ ግን ከዘይቤው ጋር አይገናኝም። ይህ ማለት “ገሃድ” ቀጥተኛ ትርጉሙ “ግልፅ” ማለት ነውና።
✔ቤተ ክርስቲያናችን ከሏት አጽዋማት አንዱ “ጾመ ገሃድ” ነው፡፡ የገሃድ ጾም የሚጾመው በጥምቀት ዋዜማ ብቻ ነው። በዓለ ጥምቀት ረቡዕ ወይም ዓርብ ባይውልም ዋዜማው (ጾመ ገሃድ) በመባል ይጾማል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን ባለማወቅ የልደትን ዋዜማም "ገሃድ" ብለው ይጾማሉ። ነገር ግን የልደት (ገና) ዋዜማ መጀመሪያውኑ በጾመ ነቢያት ውስጥ ያለ በመሆኑ ድርብ ጾም የለምና ለብቻው አይጾምም።
✔ጾመ ገሃድ ጥምቀት ረቡዕና ዐርብ በሚውሉበት ጊዜ ቀድመው ያሉት ማክሰኞና ሐሙስ የፍስክ ቀንነታቸው ወደ ጾምነት ተለውጦ ይጾማሉ። በነሱ ለውጥ ጥምቀት የሚውልባቸው የጾም ቀናት (ረቡዕና ዐርብ) የፍስክ ቀን ሆነው ይከበራሉና።
✔ገሃድ የረቡዕና ዐርብ ለውጥ ነው ብለናል። ነገር ግን ጥምቀት በሌላም ቀን ቢውል የጥምቀት ዋዜማ ይጾማል። በዓለ ጥምቀት እሑድ ቢውል ቅዳሜ የግድፍት/የፍስክ ምግብ አይበላም። ጥምቀት ሰኞ ቢውል እሑድም አይበላም። እንደሌሎች የአጽማዋት ቀናት ግን የፆም ምግቦች እህልና ውሃ ግን አይከለከሉም። ወይም ዋዜማው ከሰኞ እስከ አርብ ከሆነ እነደ ማንኛውም ጾም ይጾማል ማለት ነው፡፡
✔አንዳንድ ሰዎች ግን ጥምቀት ሰኞ ሲውል ከቅዳሜና እሑድ አዋጥተው በመጾም ቅዳሜና እሑድ ጥሉላት አይበላባቸውም ወይም ይጾምባቸዋል ይላሉ። ነገር ግን “ገሃድ” አንድ ስለሆነ (ስንክሳር ጥር 10 “ሰላም ለዕለት ዋሕድ ዘስሙ ገሃድ” እንዲል) ጥምቀት ሰኞ ሲውል ቅዳሜን መጾም አጉል የገባ ልማድ ወይም ከስርዓት ውጭ የሆነ አስተምሮ ነው።
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡
✔የጥር ሥላሴ በዓል አስደናቂ ታሪክ
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ(ዶ/ር)
✔✞ በጥር 7 ሥሉስ ቅዱስ የሰናዖርን ሕንፃ ማፍረሳቸውና የከለዳውያንን ቋንቋቸውን እንደበተኑ የሚነገር ሲኾን፤ በተጨማሪም በዐጼ ኢያሱ አድያም ሰገድ የተሠራው የሥላሴ መቅደስ ቅዳሴ ቤቱ ነው።
✔✞ይኽስ እንደምን ነው ቢሉ? ከ፲፮፻፸፬-፲፮፻፺፰ (1674-1698) ዓ.ም. ኢትዮጵያን የመሩት ታላቁ ንጉሥ ዐጼ ኢያሱ ቀዳማዊ (አድያም ሰገድ) ሥላሴን በእጅጉ ከመውደዳቸው የተነሣ የአድባራት ኹሉ ንግሥት ብለው የሠየሙትን የሥላሴን ቤተ ክርስቲያን ለየት ባለ መልኩ ማሳነጽ ጀመሩ።
✔✞እጅግ ድንቅ ኾኖ እንዲታነጽ ካላቸው ታላቅ ፍላጎት በመነሣት የሕንጻ አዋቂዎች የኾኑ በጊዜያቸው አሉ የተባሉ ታላላቅ ባለሙያዎችን መረጡ፤ ለረዥም ዘመናት ሊቆዩ የሚችሉ ዕንጨቶችን ከያሉበት በማስመጣት እጅግ ድንቅ የኾኑ በድንቅ መልክ የተጠረቡ ደንጊያዎችን አስመጥተው በዘመናቸው በጎንደር ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ተወዳዳሪ የሌለው ኾኖ እንዲታነጽ አደረጉ፡፡
✔✞ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት ካለው ታላቅ ፍቅር በመነሣት ቤተ መቅደሱን በወርቅ እንዳሣነጸው፤ ንጉሥ ዐጤ ኢያሱም ለቤተ ክርስቲያኑ የወርቅ ጉልላት በላዩ ላይ አሠርተው ከወርቅ የተሠራ መስቀል በላዩ ላይ እንዲደረግ አደረጉ፤ ከወርቁ ጽርየት የተነሣ በቀን እንደ ፀሓይ በሌሊት እንደ ጨረቃ ያንጸባርቅ ነበር ይላሉ፤ ከማይነቅዝም ዕንጨት በአዋቂዎች እጅ አስደናቂ መንበር አሠርተው በዝኆን ጥርስ አስጊጠው እንዲያምር ተደረገ፡፡
✔✞በዕውቅ ሠዓሊ አማካይነት እጅግ አስደናቂዎች ቅዱሳት ሥዕላት ተሣሉ፤ ጣራውም በመላእክት ሥዕል ተመላ፤ ቅጽረ ኢያሪኮ ሰፊ እንደነበረ የቤተ ክርስቲያኑ ግቢው እንዲሰፋ ተደርጎ ዙሪያው ረዥምና ሰፊ ኾኖ ታጠረ፤ በፊት ለፊትም መውጪያና መግቢያ ሊኾኑ ኹለት በሮች እንዲሠሩ አደረጉ፤ በበሮቹም ላይ የርእሰ አንበሳ ቅርጽ ያለው ባለ ግርማ ግንብ ተሠርቶ በዙሪያው ዐሥራ ኹለት እንቁላል ግንቦች ታነጹ፡፡
✔✞ለሥላሴ መቅደስ የሚኾኑ ግዙፋን የኾኑ ኹለት ታላላቅ ደውሎች በጠንካራ ገመድ ታስረው እንዲንጠለጠሉ ኾኑ፤ ከጽርየቱ የተነሣ በጊዜው ከእነዚኽ ደውሎች የሚወጣው ድምፅ ከጎንደር ዐልፎ ወጣ ወደሚሉ ግዛቶች ጭምር ይሰማ ነበር ይላሉ፡፡ ከዚያም ለቅዳሴ ቤቱ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ንዋያተ ቅድሳት እንዲዘጋጁ ተደርገው ካህናቱ ዲያቆናቱ ልብሰ ተክህኖ ለብሰው፤ ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው ዐጤ ኢያሱም ከመሳፍንቱ ከመኳንንቱ ጋር በታላቅ ደስታ ከቤተ መንግሥት ወደ ቤተ መቅደሱ ጉዞ ተደረገ፡፡
✔✞ታቦተ ጽዮን በታላቅ ግርማ ትታጀብ እንደነበር፤ በተመሳሳይ መልኩ የመሰንቆ፣ የእንቢልታ፣ የነጋሪት፣ የእንዚራ ድምፅ እየተሰማ፤ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ መዘምራን ከፍተኛ የምስጋና ድምፅን እያሰሙ፤ ንጉሥ ዐጤ ኢያሱም
በሰራዊታቸው ታጅበው “ጒቤን” በሚባለው ፈረሳቸው ተቀምጠው፤ እጨጌ አባ ጸጋ ክርስቶስ ታቦተ ሥላሴን ተሸክመው ጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴ በር ላይ ሲደርሱ፤ ንጉሥ ኢያሱ ለሥላሴ ካላቸው እጅግ ጥልቅ ፍቅር ተነሥተው ታቦቱ ገና አልተባረከም ነበርና ጳጳሱን አስፈቅደው ታቦቱን ከእጨጌው ተቀብለው እስከ ቅድስት አደረሱ፤ ካህኑም ከቅድስት ተቀብሎ ወደ መቅደስ ካገባው በኋላ የሥላሴ ታቦትን ግብጻዊዉ ጳጳስ አቡነ ማርቆስ በቅብዐ ሜሮን ባርከው ቅዳሴ ቤቱ ተቀደሰና የታቦቱ አገባብ በታላቅ በዓል ጥር 7 ታስቧል፡፡
✔✞እንደ አዛዥ ሐዋርያ ክርስቶስ ያሉ ሊቃውንት ዐጼ ኢያሱን በቅኔ ያወደሷቸው
ሲኾን፤ ሥላሴ በተባለው የቅኔ ዐይነት፡-
“አምላክ ዘኢፈቀድከ ደቂቀ ቆሬ ወዖዝያን
ሶበ ማዕጠንተ ወርቅ ነሥኡ ከመ ይኩኑ ካህናተ ነሥኡ ተቀሥፎ ወለብሱ እሳተ
እለ ይፈርሁከ ሰብአ ባሕቱ እምኀበ ረከብከ አንተ በዘወሀብኮሙ ትእምርተ
አመ ርኅበ በልዐ ዳዊት መሥዋዕተ
ወኢያሱ አንሥአ ጽላተ”
(የዖዝያንና የቆሬ ልጆች ካህናት ለመኾን ዐስበው አምላክ ያልፈቀድኸውን የወርቅ ማዕጠንት በወሰዱ ጊዜ ተቀሥፈው እሳት በላቸው፤ አንተን የሚፈሩኽ ሰዎች ግን በሰጠኻቸው ምልክት ተመርተው፤ ዳዊት ቢራብ መሥዋዕትን በላ፤ ኢያሱም ጽላትን አነሣ) እያሉ ተቀኙላቸው፡፡
✔✞የዐማርኛ ገጣሚውም በጊዜያቸው በአንክሮ ኾኖ፡-
“ ወዴት ኼዶ ኖሯል ሰሞነኛ ቄሱ
ታቦት ተሸከመ ዘውዱን ጥሎ ኢያሱ
የተሸሸገውን ያባቱን ቅስና
ገለጠው ኢያሱ ታቦት አነሣና
አየነው ኢያሱ ደብረ ብርሃን ቆሞ
ልክ እንደ ኪሩቤል ሦስቱን ተሸክሞ
ሥላሴን ቢሸከም ኢያሱ ገነነ
ለአራቱ ኪሩቤል ዐምስተኛ ኾነ”
በማለት ገጠመላቸው፡፡
✔✞ካህናቱም ሕዝቡም፡- “የልዑል እግዚአብሔር ወዳጆች ደጋግ ነገሥታት
የነበሩ የእነ ቆስጠንጢኖስን፣ የእነ አኖሬዎስን፣ የእነ አርቃዴዎስን … የክቡራን
ነገሥታትን ኹሉ በረከት ያሳድርብዎ” እያሉ ንጉሡ ዐጼ ኢያሱን አመሰገኗቸው፡፡
ቅዳሴ ቤቱ ጥር 7 ተደርጎ ከዚያም ዐጤ ኢያሱ ለሦስት ቀናት በቤተ መንግሥታቸው እጅግ ታላቅ ግብዣ አደረጉ፤ የጥር ወር በገባ በ፯ኛው ቀን
ኹሌም በዓሉ እንዲከበር አዘዙ፤ ለሥላሴ መቅደስም 170 ካህናት እንዲያገለግሉ አድርገው እጅግ ብዙ ርስት ሰጥተዋልና የመልክአ ሥላሴ ደራሲ አባ ስብሐት ለአብም ይኽነን የዐጤ ኢያሱ አድያም ሰገድን ውለታ ባለመዘንጋት በዚኽ መጽሐፉ ላይ ይኽነን ታሪክ እንደ ወርቅ አንከብልሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ
ታሪኩን፦
“ ሰላም ለርእስክሙ ዘአስተዋደደ ርእሰ
አጋዕዝተ ሥጋ ሥላሴ እንዘ ኢትሌልዩ ነፍሰ
በርእሰ ኢያሱ አንብሩ አክሊለክሙ ሞገሰ
በስምኩሙ አሐዱ እስመ ያመልክ ሥሉሰ
ወበስምክሙ ሐነጸ መቅደሰ”
(ራስን ያስማማ ለኾነ ራሳችኊ ሰላምታ ይገባል፤ ነፍስን ሳትለዩ ሥጋን የፈጠራችኊ ሥላሴ ሆይ ባለሟልነት ዘውዳችኹን በኢያሱ ራስ ላይ አኑሩ፤ እግዚአብሔር በሚባል አንድ ስማችኊ፤ ሦስት አካላትን ያመልካልና፤ በስማችኹም ቤተ መቅደስን ሠርቷልና) በማለት ይገልጣል፡፡
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
#ተባረኩኝ_ጠራኝ_ጸሎቷ
ተባረኩኝ ጠራኝ ጸሎቷ
ልሳለማት ልሂድ እቤቷ
ፍቅሯ ልዩነው ደግነቷ
እናቴ አርሴማ ሰማእቷ
እግሩ ያነከሰ ክንዱ የዛለበት
ደስታ የራቀው ሰው ህመም የጸናበት
ልቡ የደከመ መንገድ የጠፋበት
አፍሮ አይመለስም ደጅሽ የመጣለት
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ያንሁሉ ቁልቁለት ያንሁሉ ጋራ
እንዴት ልጓዝ ብዬ ስፈራ ስፈራ
ድረሽልኝ ብዬ ላንቺ ስናገር
እንደእንቦሳ ጥጃ እዘለው ጀመር
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ላይድን መችይመጣል ላይለቀው ችግሩ
አንቺስ መችልጠሪው ሲነሳ ከክብሩ
አቤት ቃል-ኪዳንሽ እንዴት ይገለፃል
አምኖ የመጣ ሰው ድኖ ተመልሶል
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
የውስጥ ደዌውን ህመሙን ደብቆ
ገስግሶ የመጣ ካለሽበት ዘልቆ
ድኖ ተመለሰ ዝናሽን አሰማ
ሰማቷ እናቴ እያለሽ አርሴማ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
አንደበትን ስጪኝ እመሰክራለው
በሶስት ፍሬቆሎ ስታድኚ እያየው
ነግሬሽ ነበረ ችግሬን በሙሉ
አላሳፈርሽኝም ተፈታልኝ ሁሉ
4 374
#አርሴማ_ቅድስት
አርሴማ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት(፪)
ሞገስ አግኝተሻል በክርስቶስ ፊት
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ተዐምርሽ ልዩ ነው.......አርሴማ
ገድልሽ አስደናቅ.........አርሴማ
ስምሽ ብርሃን ነው.......አርሴማ
ማለዳ ፈንጣቅ............አርሴማ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ሥምሽን እየጠሩ..........አርሴማ
ይጠግባል የተራበው.....አርሴማ
ምስኪኑም ዘመረ...........አርሴማ
በአንቺ አልፎ መከራው......አርሴማ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ጽኑ ነው ኪዳንሽ..............አርሴማ
የተሰጠሽ ከአምላክ........አርሴማ
በአይኔ አይቻለው............አርሴማ
ጠላት ሲንበረከክ............አርሴማ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ዓለም ይስማው ዛሬ........አርሴማ
ስለ ተጋድሎሽን..............አርሴማ
ይገረም ይደነቅ...............አርሴማ
ይመስክር ዝናሽን.........አርሴማ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ሥምሽን እየጠሩ.........አርሴማ
ይጠግባል የተራበው......አርሴማ
ምስኪኑም ዘመረ...........አርሴማ
በአንቺ አልፎ መከራው.......አርሴማ።
4 374
#አርሴማ_ነይ_ነይ
ጽኑ ሰማዕት የእምነት አርበኛ፣
አርሴማ ነይ ነይ ወደኛ፡፡
ነይ ነይ ቅዱስ አትናትዮስ
›› ›› በስዕለት ያገኙሽ
›› ›› ብሉይን ከሀዲስ
›› ›› ጠንቅቀሽ የተማርሽ
›› ›› በፍፁም ትህትና
›› ›› በጸሎት የተጋሽ
›› ›› አርሴማ ልዩ ነሽ
›› ›› አምላክ የመረጠሸ
•••••••••••✞••••••••••••
ነይ ነይ ውበትም ሀሰት ነው
›› ›› ደም ግባትም ከንቱ
›› ›› ንብረት ትዳር ሁሉ
›› ›› አላፊ ውዕቱ
›› ›› ንግስት መባልን
›› ›› በፍጹም ሳትሻ
›› ›› አለምንድርጣድስ
›› ›› ገባች ወደዋሻ
•••••••••••✞••••••••••••
ነይ ነይ አረመኔው ድርጣድስ
›› ›› ቢያሰቃይሽም
›› ›› ውበቴ ክርስቶስ
›› ›› ነው ብለሽ ሰበክሽ
›› ›› አንገትሽን ለሰይፍ
›› ›› አሳልፈሽ ሰጠሸ
›› ›› ክብርሽም ተገልጾ
›› ›› ለአለም አበራሽ
•••••••••••✞••••••••••••
ነይ ነይ አርያ ልትሆኝን
ነይ ነይ ለእኛ ለሁላችን
ነይ ነይ ፈፅመሽ አሳየሽ
ነይ ነይ ታላቅ ተጋድሎሽን
ነይ ነይ አንገትሽን ለሰይፍ
ነይ ነይ አሳልፈሽ ሰተሽ
ነይ ነይ ክብርሽም ተገልፃ
ነይ ነይ ለአለም አበራሽ
ጽኑ ሰማዕት የእምነት አርበኛ፣
አርሴማ ነይ ነይ ወደኛ፡፡
ነይ ነይ ሀኪምም አልሿ
ነይ ነይ ምን ያደርግልኛል
ነይ ነይ አዋቂም አልሻ
ነይ ነይ ምን ያደርግልኛል
ነይ ነይ በአርሴምዬ ፀበል
ነይ ነይ አይኔ በርቶልኛል
•••••••••••✞••••••••••••
