የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Відкрити в Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Показати більше4 374
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
4 374
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻የሱፍ አበባ የአምላክ እናት🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
👉ጠቢቡ ሰሎሞን በማሕ ፪፥፩‐፪ ላይ በመንፈሰ እግዚአብሔር በመቃኘት የቅድስት ድንግል ማርያምን ንጽሕና በሱፍ አበባ መስሎ ሲያስተምር፡- “አነ ጽጌ ገዳም ጽጌ ደንጐላት ዘውስተ ቈላት፤ ወከመ ጽጌ ደንጐላት በማእከለ አሥዋክ ከማሁ አንቲኒ እንተ ኀቤየ በማእከለ አዋልድ” (እኔ የዱር ጽጌረዳ፤ የቈላም የሱፍ አበባ ነኝ፤ በእሾኽ መኻከል እንዳለ የሱፍ አበባ እንዲኹ ወዳጄ በቆነዣዥት መኻከል ነሽ) በማለት የተናገረውን ምሳሌያዊ ኀይለ ቃል ሊቁ በድርሰቱ ላይ፡- “ወከመ ጽጌ ደንጐላት በማእከለ አሥዋክ ከማሃ አንቲኒ ኦ ወላዲተ አምላክ” (በእሾኽ መኻከል እንዳለ የሱፍ አበባ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ አንቺም እንደ ርሷ ነሽ) ሲል ያቺ ሰሎሞን የተናገረላት የሱፍ አበባ የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ መኾኗን ተርጒሞታል፡፡
👉ይኸውም ይቺ የሱፍ አበባ እሾኽ ዙሪያዋን ከቧት ሳለ በሾኽ መኻከል እንደምታብብ እንደምታፈራ ቅድስት ድንግል ማርያምም ኀጢአት እንደ እሾኽ በከበባቸው በአይሁድ መኻከል ሳለች ብቻዋን ከኀልዮ (ከማሰብ)፣ ከነቢብ (ከመናገር)፣ ከገቢር (ከመሥራት) ኀጢአት ተጠብቃ በሃይማኖት፣ በምግባር፣ በንጽሕና፣ በቅድስና፣ በድንግልና ጸንታ የሕይወት ፍሬ ክርስቶስን አብባ አፍርታ ተገኝታለችና ነው፡፡
👉አባ ጊዮርጊስም ይኽነን የሰሎሞንን ቃል በአርጋኖን መጽሐፉ ሲተረጒመው፡- “ጽጌ ደንጐላት እንከ እሰምየኪ እስመ ጽጌ ደንጐላት ዕዉድ በአሥዋክ... ” (በሱፍ ዕንጨት እመስልሻለኊ፤ የሱፍ አበባ በእሾኽ የተከበበ ነውና፤ አንቺም ከዳዊት ግንድ (ባሕርይ) የተገኘች የንጽሕት አበባ ቅንጣት ኾነሽ ሳለ፤ በጒስቁልናቸው የሚመኩ አንገታቸውን የሚያደነድኑ በዐይኖቻቸው የሚጠቃቀሱ በእግሮቻቸው የሚያሸበሽቡ የልብሶቻቸውን ዘርፎች የሚጐትቱ የሚዘፍኑትን የቆነዣዥት አለቆች የሚኾኑ የጽዮንን ልጆች እግዚአብሔር ያዋርዳቸዋል ያጐሳቁላቸዋል ብሎ ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት እንደተናገረባቸው (ኢሳ ፫፥፲፮‐፲፯)፤ አንቺም አንገተ ደንዳኖች በሚኾኑ በዕብራውያን ቆነዣዥት መኻከል እንደተቀመጥሽ) በማለት ግዙፉነ ክሣድ በኾኑ ኀጢአት እንደ እሾኽ በከበባቸው በአይሁድ ልጆች መኻከል ሳለች ርሷ ብቻ በንጽሕና በቅድስና ጸንታ የመገኘቷን ምስጢር ከሰሎሞንና ከኢሳይያስ ቃል በመጥቀስ ተንትኖታል፡፡
👉ሊቁ ቅዱስ አባ ሕርያቆስም ከዚኽ ምስጢር በመነሣት በቅዳሴው ላይ “ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልህቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሣዶን አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ” (ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ) በማለት ግዙፋነ ክሣድ በኾኑ በዘፈን፣ በቧልት፣ በጨዋታ፣ ኀጢአትን በመሥራት ይኖሩ ከነበሩ ከዕብራውያት ሴቶች ልጆች ተለይታ በቤተ መቅደስ ማደጓን አስተምሯል፡፡
👉አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ይኽነን የሰሎሞንን ቃል ሲያብራሩ:- “ጽጌ ደንጐላ ዘቈላ ወአኮ ዘደደክ ዘጸገይኪ ጽጌ በማእከለ አይሁድ አሥዋክ ተአምረ ድኂን ማርያም ዘልማድኪ ምሂክ መሀክኒ ለምእመንኪ እምጻዕረ ኩነኔ ድሩክ ተአምኖትየ ኢይኩን በበክ” (በእሾኾች አይሁድ መኻከል የደጋ ያይደለ የቈላ የሱፍ አበባን ያበብሽና ልማድሽ መራራት የኾነ የመዳን ምልክት ማርያም፤ ብርቱ ከኾነ ከጭንቅ የቅጣት ፍርድ ታማኝሽን አድኚኝ፤ በአንቺ ምልጃ መታመኔ ከንቱ ኾኖ እንዳይቀር) በማለት በሱፍ አበባ መመሰሏን አጒልተው ተርጒመዋል፡፡
[🌻የሱፍ አበባ የተባልሽ የአምላኬ የክርስቶስ እናት ሆይ ከማያልቀው በረከትሽ ጥቂቱን በእኔ ላይ አሳድሪ አሜን✞✞✞🌻] ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
🌻💐🌹 #Join us... 🌹💐🌻
#Share #Share #Share #Share
❀✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆❀
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @EOTC2921 👈
👉 @EOTC2921 👈
👉 @EOTC2921 👈 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
4 374
🌿🌿🌿🌿🌾🌾🌾🌾🌿🌿🌿🌿
✍እንዳሰብነው ሳይሆን በቸርነቱ በፈቃዱ እንዳሰበልን አኑሮናል ፤ ከዘመን ዘመን አድርሶናል ፤ መጪውንም ዘመን እርሱ እግዚአብሔር አብሮን ይሁን✞✞✞
😍ፈጣሪ⛪️👉ይህቺን ጳጉሜ የይቅርታና የምስጋና ቀን አድርጎ ስለሰጠን በእውነቱ፦፦
❣ሳናውቅ በስህተት❤
💙እያወቅን በእህል💔
❌🌷ያስቀየምነውን
❌🌷ያሳዘነውን
❌🌷ያስከፋነውን
⛪️ለሰው ብቻ ሳይሆን ለፈጣሪ ብለን
💜በንፁህ ህሊናችን
💙ከልብ ተፀፅተን
😍በፍቅር አይናችን
🌍ሁሉንም ፍጡር
💞ይ💕ይ
💞ቅ💕ቅ
💞ር💕ር
💞ታ💕ታ
🌺🌸🌼እንጠይቅ!!!🌼🌸🌸
🌺🌸🌼 እናድርግ!!!🌼🌸🌺
🌻💐🌹 #Join us... 🌹💐🌻
#Share #Share #Share #Share
❀✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆❀
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
4 374
አንዲት ሴት ነበረች ሀጢያቷን የምትፅፍ፤ ልቧ በሀጢያት የሰከረ ለሀጢያት ተገዢ የሆነች፡፡ ይህች ሴት የተለያዩ ሀጢያቶችን የምትሰራ ነች
😱🙈ትዘሙታለች,,ትሰርቃለች
🙊🤔ትዋሻለች,,ታማለች
☠👾ትገድላለች
🍺🍷ትሰክራለች......👉✝አምላክ ሆይ የለ ንስሀ አትጥራን🙏
👉👉 @EOTC2921 👈👈
4 374
🌿🌿🌾ቅዱስ ሩፋኤል🌾🌿🌿
✍ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
❖ ቅዱስ ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን፤ ሩፋ ማለት
ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር
ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት
አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)::
ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው፡፡ ነገደ
መናብርት ያላቸው ቅዱስ ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ
መላእክት ናቸው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም
ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል
ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ
ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን
ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ
የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ
በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚኽ ነገድ
24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡
አባ ጊዮርጊስም በሰዓታቱ ላይ፡-
“ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጽርሐ አርያም ማኅፈዱ
መካነ ትጉሃን ዐጸዱ
ካህናተ ሰማይ ቅዉማን በዐውዱ አክሊላቲሆሙ ያወርዱ
ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ ይርዕዱ
ወኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ”
(ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣
ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ
በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ
(ባሕርዩ) በሚበርቅ፣ ወገግ በሚል ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ) ይላል
ሊቁ እንደጠቀሰው በዕለተ እሑድ ሥሉስ ቅዱስ ሰባቱን ሰማያት ፈጥረዋል፤
ከዚያም ልዑል እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ ሊቁ
በአክሲማሮስ እንደገለጸው ከቅዱሳን መላእክት መኻከል፡-
“ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር እምሰራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ ወአቀሞሙ
ዐውደ መንበሩ፤ ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ
ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን
መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት” ይላል ከሰራዊተ ሩፋኤል ፳፬ት ሊቃናትን
መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ
አቁሟቸዋል (ሕዝ ፩፥፲፩-፲፪)፤ ቊጥራቸውን ኻያ አራት ማድረጉ በኻያ አራቱ
ጊዜያት ጸልየው ሌላውንም ራሳቸውንም ጠብቀው ዋጋቸውን ተቀብለው የሚኖሩ
በመኾናቸው ሲኾን እነዚኽንም መላእክት “ካህናተ ሰማይ” ሲላቸው የእሳት
የወርቅ ጽና ሲያሲዛቸው የብርሃን አክሊል ጳዝዮን የሚባል የብርሃን ዘውድ
ደፍቶላቸዋል፤ የብርሃን ዘንግ ማኅተሙ መስቀል የኾነ ሲያሲዛቸው የብርሃን ካባ
ላንቃ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ አልብሷቸዋል ( ራእ ፬፥፬-፭፤፲-፲፩)።
እነዚኽ ሰማያውያን ካህናት በአንድ ላይ ባጠኑ ጊዜ ዛሬ በክረምት ጊዜ ጉም
ተራራውን እንደሚሸፍነው ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፣
ድምፁ ነጐድጓድ፣ መዐዛው መልካም የኾነና ጽርሐ አርያም፣ መንበረ መንግሥት
የተባሉትን የብርሃን ሰማያት የሚሸፍንና የሚጋርድና ከጢሱ ጋር የቅዱሳን ጸሎት
ዐብሮ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይወጣል፤ “ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና
ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ
ለቅዱሳን ኹሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ
ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” እንዳለ ዮሐንስ
በራእዩ (ራእ ፰፥፫-፭)፡፡
ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ላይ “ወቦ ኪሩቤል ይቀውሙ በየማን በአምሳለ
ቀሳውስት ወሱራፌል ይቀውሙ በአምሳለ ዲያቆናት ወድኅሬሆሙ ካህናተ
ሰማይ ወቦ እልፍ አእላፋት ወትእልፊተ አእላፋት መብረቅ ወነጐድጓድ
ወሠረገላሆሙኒ ምሉኣነ አዕይንት” እንዳለ ኪሩቤል በቀኝ ሱራፌል በግራ ከፍ
ብለው ካህናተ ሰማይ ክንፍ ለክንፍ ገጥመው በስተኋላቸው ሲታዩ በሰማይ
ውዱድ ዙሪያ እልፍ አእላፋት መብረቅ፣ ነጐድጓድ፣ ሠረገላ፣ እንደ መስታየት
ብሩህ የኾነ ሲኖርበት እነዚኽ ቅዱሳን መላእክትም ሳያቋርጡ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣
ቅዱስ እግዚአብሔር” እያሉ ፈጣሪያቸውን በአንድነቱ በሦስትነቱ ያመሰግኑታል
(ራእ ፬፥፰)፡፡
ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስም ስለነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ሲገልጽ “ወኲሎሙ ሰራዊተ
መላእክት እለ ይቀውሙ ቅድሜሁ ይጸርሑ ወይባርክዎ ለእግዚአብሔር…” (በፊቱ
የሚቆሙ የመላእክት ሰራዊትም ኹሉ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ የመላእክት
አለቆችም ለማይታይ ለባለዚኽ ስም ዘንበል ብለው ይሰግዳሉ፤ እግዚአብሔርን
የሚያመሰግኑና የሚዘምሩ ዙፋኑን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳ ጩኸው
ያመሰግኑታል፤ ዕጣንን የተመሉ የወርቅ ማዕጠንት በእጆቻቸው ያለ ኻያ አራቱ
ካህናተ ሰማይ ይኸውም የቅዱሳን ጸሎት ነው እስከ ዘላለሙ ሕያው በኾነው
ፊት የሚቀበለው መሥዋዕት አድርገው ወደ ላይ ያሳርጋሉ) በማለት የቅዱሳንን
ጸሎት ቅድመ እግዚአብሔር በማዕጠንታቸው ለማሳረግ የተመረጡት መላእክት
ኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ መኾናቸውን አስተምሯል፡፡
ይኽ መልአክ ጦቢትን የተራዳ መልአክ ነው፤ ይኽ ጦቢት ዐሥሩ ነገድ በ፯፻፳
ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ሲማረኩ ዐብሮ የተማረከ ጻድቅ ሰው ነው፤ ይኽ ሰውን
በመርዳት በደግነቱ የታወቀው ጦቢት ከመንገድ ወድቆ የተገኘ በድን ቀብሮ፤
በዚያው ሌሊት ከቅጥሩ አጠገብ ፊቱን ተገልጦ ተኝቶ ሳለ አዕዋፍ ትኩስ ፋንድያ
ዐይኑ ላይ ጥለውበት እንደ ብልዝ ያለ ወጥቶበት ዐይኑ ጠፋ፤ ሚስቱም
ባለማስተዋል “አይቴ ውእቱ ምጽዋትከ ወጽድቅከ” (በጐነትኽ ምጽዋትኽ ያዳነኽ
ወዴት ነው?) በማለት በተናገረችው ጊዜ ዐዝኖ ሞትን ተመኘ (ጦቢ ፪፥፲፬)፡፡
ያን ጊዜ መልአኩ ሩፋኤል ርሱንና ባሎቿ ስለሞቱባት ቤተሰቦቿ ያንቋሽሿት
የነበረችውን የራጉኤል ልጅ ሳራን ለማዳን ተልኮ በመምጣት አስቀድሞ በርሷ
ላይ ዐድሮ ባሎቿን ይገድልባት የነበረውን ጋኔን አስወጥቶ የጦቢት ልጅ ጦብያ
እንዲያገባት አድርጓል፤ በዚኽም “ፈታሔ ማሕፀን” ተብሏል፡፡ በኋላም ወደ
ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት “አነ ውእቱ ሩፋኤል
መልአክ አሐዱ እምነ ሰብዐቱ ቅዱሳን መላእክት” (ከሰብዐቱ ሊቃነ መላእክት
አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ) ብሏቸው ተሰውሯል (ጦቢ ፲፪፥፲፭)፡፡የቅዱስ ሩፋኤል ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን✞✞✞
🌻💐🌹 #Join us... 🌹💐🌻
#Share #Share #Share #Share
❀✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆❀
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
4 374
ጳጉሜ/ጳጉሜን
👉ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት
ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም
በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ
የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ / Thirty months of sunshine / በመባል
ትታወቃች ፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት /
የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል
ይከበራል፡፡
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ
በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል
ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ
የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ
ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት
ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ
እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ
ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን
እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፡-2-7፡፡
እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ
የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ
ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ
በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡
ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን
ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ
በራስዋ ላይ ትብያ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት
የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ
ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፡-2 ፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን
በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡
ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ
ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን
ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ
ይጾማሉ፡፡
የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት
መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች
ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ
ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡
ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው
በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም
እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን
ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው፡፡ የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡
በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፣
የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም ህይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ (ጷጉሜ) ይሁንላችሁ፡
🌻💐🌹 #Join us... 🌹💐🌻
#Share #Share #Share #Share
❀✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆❀
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
4 374
🌿🌿🌿🌿🌾🌾🌾🌾🌿🌿🌿🌿
✍እንዳሰብነው ሳይሆን በቸርነቱ በፈቃዱ እንዳሰበልን አኑሮናል ፤ ከዘመን ዘመን አድርሶናል ፤ መጪውንም ዘመን እርሱ እግዚአብሔር አብሮን ይሁን✞✞✞
😍ፈጣሪ⛪️👉ይህቺን ጳጉሜ የይቅርታና የምስጋና ቀን አድርጎ ስለሰጠን በእውነቱ፦፦
❣ሳናውቅ በስህተት❤
💙እያወቅን በእህል💔
❌🌷ያስቀየምነውን
❌🌷ያሳዘነውን
❌🌷ያስከፋነውን
⛪️ለሰው ብቻ ሳይሆን ለፈጣሪ ብለን
💜በንፁህ ህሊናችን
💙ከልብ ተፀፅተን
😍በፍቅር አይናችን
🌍ሁሉንም ፍጡር
💞ይ💕ይ
💞ቅ💕ቅ
💞ር💕ር
💞ታ💕ታ
🌺🌸🌼እንጠይቅ!!!🌼🌸🌸
🌺🌸🌼 እናድርግ!!!🌼🌸🌺
🌻💐🌹 #Join us... 🌹💐🌻
#Share #Share #Share #Share
❀✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆❀
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
4 374
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
👉💟እምነት ብታጣ ይሉኝታ አትጣ፤ ወደ እግዚአብሔር ሽሽ እንጂ ከእግዚአብሔር አትሽሽሸ💟👈
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
✍ልጄ ጸጉርህ ወጣት ሳለህ ጥቁር፣ ጐልማሳ ስትሆን ገብስማ፣ ስትሸመግል ነጭ ይሆንልሃል። በወጣትነት ማስተዋል ያጥርሀልና ፀጉርሕ ጥቁር፣ በጎልማሳነትህ ጉልበትና ጥበብ ተዋህደውሃልና ገብስማ በሽምግልናህ እውቀትህ በዝቷልና ነጭ ይሆንልሃል።
👉ጉልበት ያለው ወጣት ማስተዋል ያጥረዋል። ማስተዋል ያለው ሽማግሌ ጉልበቱ ይከዳዋል። ጉልበትና ጥበብ የተዋሃዱት ጎልማሳ ስትሆን ግን ብዙ መስራት ይጠበቅብሃል።
👉ሀኪም ታማሚ ታካሚውን አስቀምጦ ወይም አስተኝቶ እንጂ በቁሙ እንደማያክመው ሁሉ እግዚአብሔርም አሳምሞ ወይም ጥሎ ያስተምርሃል። ደግሞም ያክምሃል። ሲያስተኛሕና ሲጥልህ "ጌታ ሆይ የምታስተምረኝ ምንድን ነው?" በለው እንጂ አትዘን አትማረር። ለሰው በቁሙ መማርና መለወጥ ብዙ ጊዜ ጭንቅ ነውና እግዚአብሔር ጥሎ ያስተምርሃል። ያነሣሃል።
👉ልጄ ሽምግልናን እንድታያት ወጣትነትህ ሽምግልናን ታክብራት። የናቅኸውን ነገር እግዚአብሔር አይሰጥህምና ሽማግሌ እንድትሆን ሽምግልናን አክብራት።
👉ልጄ አምስት አይነት ዘውዶች አሉ። አምስተኛው ግን ከሁሉም ይበልጣል።
✟ የመጀመሪያው የንግስና ዘውድ፣
✟ ሁለተኛው የትምህርት ዘውድ፣
✟ ሦስተኛው የተክሊል ዘውድ፣
✟ አራተኛው የክህነት ዘውድ ሲሆኑ
✟ አምስተኛው ግን የሽበት ዘውድ ናቸው።
አራቱም ዘውዶች ሲመሽ ይወልቃሉ። የማይወልቀው የተፈጥሮ ዘውድ ሽበት ግን ከሁሉም ይበልጣል መብለጡም በኑሮ ማስተዋልን መውለዱ ነው።
👉ልጄ የክብር ኑሮ አድካሚ ነውና አትመኘው ሀብትም ርካታ የለሽ ያደርጋልና ፍቅርን ምረጥ። አፈር ሥጋዬን ካላከበሩልኝ ብለህ ጠብ አታብዛ የምትረግጣት መሬት አንድ ቀን ትረግጥሃለችና አረማመድህ በዝግታ ይሁን። ገንዘብ ካለኝ ወዳጅ ይኖረኛል ብለሕ አታስብ። ገንዘብ ከድህነት እንጂ ከሞት አያስጥልም። ፍቅር በፍቅር እንጂ በገንዘብ አይገዛምና በገንዘብሕ ሀሰተኛ ወዳጅና እውነተኛ ጠላት እንደምታተርፍ እወቅ። ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ የተባለው ለአውሮፕላን እንጂ ለፅድቅ አይደለምና ገንዘብሕን ተማምነህ የድንግልን አማላጅነት የክርስቶስን ቤዛነት አትርሳ።
👉ልጄ እኔ ብቻ በችግር እኖራለሁ ብለህ ሌላው ባለመቸገሩ አትቅና። ሁሉም ለማኝ ሲሆን ደግ (ጥሩ) አይደለምና። ዛሬ ዓለም የተጨነቀው ሁሉም ሀገር በመቸገሩ ነው። ሁሉም ሲቸገር ደግ አይደለምና ይሕን አትመኝ።
👉ሲነጋ ወደ ዓለም ሲመሽ ወደ እግዚአብሔር አትገስግስ። መከራህን ለጌታ ደስታህን ለዓለም አታድርግ። እምነት ብታጣ ይሉኝታ አትጣ።ወደ እግዚአብሔር ሽሽ እንጂ ከእግዚአብሔር አትሽሽ። ሕፃን ልጅ ሲቆሽሽም የሚሸሸው ወደ እናቱ ነውና አንተም (ኃጢያትህ ሲበዛ) ወደ እናት ቤተክርስቲያንህ ሽሽና ንስሀ ግባ። ንስሃ ደግሞ ያጣኸውን ለማግኘት የብልጠት መንገድ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ስጦታ በትዕቢት ስለመያዝህ የምትፀፀትበት ሊሆን ይገባዋል።
👉ልጄ የወጣህበት ሰረገላ በመሬት ላይ ቆሟል! መሬት ደግሞ በእግዚአብሔር እጅ ላይ ተቀምጣለች። የተሸከመንን የተሸከመ እርሱ እግዚአብሔር ነው። የኮራንባቸው ነገሮች ሁሉ የእርሱ ናቸው። ከእርሱ በቀር የሚችለን ማንም የለም። ብዙ ዘመን ግን ያለ እግዚአብሔር በራሳችን ለመኖር እቅድ አውጥተናል፤ ያለ እግዚአብሔር መኖር ግን አይቻልም። ያለ እርሱ መኖር ፍፃሜው ሞት ነውና።
👉ልጄ ሆይ ከእግዚአብሔር ተለይተሕ መኖር አይቻልም። እርሱ በነፍስም በሥጋም ገዢሕ ነውና ከእርሱ ጋር ተጣበቅ። መንግስት ችግር ሳይመጣ ወታደሩን በችግር ያሰለጥናል፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን መቆም እንድንችል በትግል ውስጥ ያሰለጥንሃልና አትመረር።
👉ልጄ አንተ የሠማይ ኮኮብ ነህ። የተደበቅህ ቢመስልህም ሁሉ ያይሃል። የክዋክብት ሕልውናቸው ብርሃናቸው ነው። የአንተም ክርስትና ሕልውናው የተለወጠ ሕይወት መሆኑን አስተውል። አዎ የሰማይ ኮኮብ ነህ አገርህም በሰማይ እንደሆነ እወቅ። ስምህ ክርስቲያን አገርህ በሰማይ ዘርህ ክርስትና እናትህ ድንግል ማርያም ንጉስህ ክርስቶስ ነው።
👉ልጄ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል። ብዙዎች ስለጠሉህም ይጠላሃል። አንተ ግን የብዙሃን እውነት ነው ሳይሆን እግዚአብሔር እውነት ነው በሚል መመሪያ ተመራ። ለመልካምነትህ ክፉ ምላሽ ለወሮታህ ከሳሽ ቢነሳብህ የመልካም ነገር ደሞዝ ሰጪ እግዚአብሔር መሆኑን አምነህ ሥራህን ሥራ።
👉ልጄ መልካም ነገርህ ነገ ሊረሳ ይችል ይሆናል መልካም መሆንህንም ሰዎች ላይረዱልህ ይችላሉ እውነተኛ መልካምነት ግን ምስጋናን ሳያደምጡ የሚፈፀም መሆኑን እወቅ።
👉ልጄ ታማኝ ስትሆን ያለፈብሕ ትመስል ይሆናል፤ ግልፅ ስትሆን በቀላሉ ልትጠቃ ትችላለህ፤ ታማኝና ግልፅ መሆንህን ግን እግዚአብሔር ስለሚወደው ብቻ አጥብቀህ ያዘው።
👉ልጄ ልጅነት የለሰለሰ መሬት፣ ወጣትነት ያዝመራ ዘመን፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል። በሽምግልናሕም የምታጭደው የወጣትነትሕን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ።
"ምክር ከእማሆይ ፅጌ አሌልቱ ደብረ ሰዋሰው አደሬ ኪዳነ ምሕረት የሴቶች ገዳም
🌻💐🌹 #Join us...🌹💐🌻
#Share #Share #Share #Share
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
4 374
✍✝💟ነሐሴ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት💟✝✍
1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር (ፍልሠቱ)
2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱሳን ገርሲሞስና ቴዎዶጦስ (ሰማዕታት)
4.አባ ባስልዮስ ጻድቅ (ዘትግራይ)
👉👉ወርኀዊ በዓላት👈👈
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅድስት አርሴማ ድንግል
3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ(ጻድቅናሰማዕት)
🌼🌼🌼🌼🌼🌻🌻🌻🌻🌻
"እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ 'የማንጠቅም ባሪያዎች ነን: ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል'
በሉ::" (ሉቃ. 17:10)
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @EOTC2921 👈
👆👆👆👆👆👆👆☝️
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
4 374
4 374
ረት እንስገድ፤ በተጠቀለለበት በረት
እንበርከክ፤ ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና ይኹን በምድርም ሰውን ለወደደ
እንበል (ሉቃ ፪፥፲፬)፤ እግዚአብሔር ሰው ኾነ የሰው ልጅ ሴት ልጅም
የእግዚአብሔር እናት ኾነች፤ ለርሱ ምስጋና ይኹን ለርሷም ስግደት ይገባል
ለዘላለሙ አሜን ይኹን) በማለት በጥልቀት ገልጾታል፡፡
አቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከልክ የባሕርይ አምላክ የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ እውነተኛ ፈራጅ መኾንህን
የምታስተምረውን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንን ጠብቅ አሜን✞✞✞
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
ሰላም ሰላም ውድ ምዕመናን ተወዳጁን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ @EOTC2921 ቻናል ይቀላቀሉን#JOIN ሁሉንም በአንድ ቦታ የምናገኝበት፡፡
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇
👇 @EOTC2921 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉
4 374
🌿ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ ክርስቲያን🌿
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
💟✝✝✝💟ብዙዎች ኢየሱስ ክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን እንደማትሰብክ አድርገው ለማቅረብ
ይሞክራሉ፤ ነገር ግን ሐዋርያዊት የኾነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን
ስለክርስቶስ ያላስተማረችበት ጊዜ የለምም አይኖርም፤ ደግሞም እናት
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በጊዜያችን አንዳንዶች መናፍቃን
የኢየሱስን ክብር አሳንሰው ከአብ በታች አድርገው እንደሚያስተምሩት ሳይኾን
በእውነት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብሩ የተካከለ፣ ቅድመ ዓለም የነበረ
አኹንም ያለና ዓለምን አሳልፎ የሚኖር፤ ለፍርድ ዳግመኛ የሚመጣ፤ እውነተኛ
ፈራጅ የአማልክት አምላክ የነገሥታት ንጉሥ ነው ብላ የምታስተምረው፡፡ ይኽ
ብቻ ሳይኾን ሥጋውን ደሙን በምትሠዋበት በቃል ኪዳን ታቦቱም ላይ “ኢየሱስ
ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው” (የሕያው የአብ የባሕርይ ልጅ ኢየሱስ
ክርስቶስ) ብላ አክብራ ስሙን ትጽፋለች እንጂ በድፍረት ሆና ስሙን መቀለጃ
አታደርግም፡፡
ለምሳሌ ከፍሬ ቅዳሴዋ ውስጥ በዮሐንስ ቅዳሴ ላይም ስለክብሩ ስታስተምር
ላይ “ንሰግድ ለከ ወንሴብሐከ ነገረ ጥበብ ወቃለ ምክር መዝገበ ረድኤት
ወምሥያመ ትፍሥሕት…” (እንሰግድልኻለን እናመሰግንኻለንም የጥበብ ነገር፣
የምክርም ቃል፣ የረድኤት መዝገብ፣ የደስታም መኖሪያ፣ የጥቅም መገኛ፣
የትንቢትም ምንጭ፣ ደገኛ ፈሳሽ፣ በሐዋርያት የተመሰገንኽ፣ የክብር ጒድጓድ፣
የመንግሥት ጌጥ፣ የካህናት ንጹሕ ዘውድ፣ ዘውዱ የተመሰገነ ንጉሥ፣
የሚሰግዱለት የምስጋና መገኛ፣ የክብር ብርሃን፣ ...የበዛ ምናን፣ ዕጽፍ ድርብ
የኾነ መክሊት፣ ዱቄትን የቻለው ዕርሾ፣ አልጫ የኾነውን ያጣፈጠው ጨው፣
ጨለማን ያሳደደው ብርሃን፣ ዓለምን ኹሉ ያበራው ፋና፣ የማይነዋወጥ መሠረትና
የማይፈርስ ግንብ፣ የማይሰበር መርከብና የማይሰረቅ ማኅደር፣ የለዘበ ቀንበርና
የቀለለ ሸክም ርሱ ለአባቱ ኀይሉ ጥበቡም የሚኾን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤
ለኹሉ ያስባል፣
ኹሉንም ያጠግባል፣ ለዕውራን ያዩ ዘንድ ብርሃንን ይሰጣቸዋል፣ የተዘጉ
መስኮቶችንም ይከፍታል፣ ጽሙማንን ያሰማቸዋል፣ የተደፈነችውን ዦሮ
እንድትሰማ ያደርጋል፣ ነፍስን ወደ ሕዋሷ ይመልሳል፣ መንፈስንም በማደሪያዋ
ያኖራታል፣ አለቆች ባሏቸው አጋንንት የእሪያን መንጋ ያሰጥማል፣ ከደከመች
ሰውነት ደዌን ያርቃል፣ ከክንፍኽ (ከሥልጣንኽ) የእውነት ፀሓይና የጥቅም
ምንጭ የሚወጣ የጽድቅ ፀሓይ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንተ ጌትነትና ክብር
ምስጋናም ለዘላለሙ ይገባኻል) በማለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እስከ ዕለተ
ምጽአት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የምትሰብከውን ርቱዕ ትምህርትን በቊርባን
ምስጋናው ላይ አስቀምጧል፡፡
ዐምደ ሃይማኖት የሚባለው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ምስጢር
ላይ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተምር “ለሊሁ በግዕ ወደሙ ወይን፤ ለሊሁ
መርዓዊ ወገቦሁ ዐዘቅተ ማየ ሕይወት፤ ለሊሁ መምህር መክስተ አፉ መዐዛ
ዕጣን…” (ርሱ ራሱ በግ ደሙም ወይን፤ ርሱ ሙሽራ ጐኑም የሕይወት ውሃ
ምንጭ፤ ርሱ መምህር የአፉም ትንፋሽ የዕጣን መዐዛ፤ ርሱ መብራት መስቀሉም
መቅረዝ፤ ርሱም የገነት ዛፍ የጸጋውም ወንጌል መዐዛው ያማረ አበባ፤ ርሱ
የጽድቅ ፀሓይ ሐዋርያቱም የብርሃን ከዋክብት፤
ርሱ የበረከት ማዕድ ካህናቱም የምስጢር አገልጋዮች፤ ርሱ የቅድስና ልብስ ዲያቆናቱም በልብስነቱ ዘርፍ ኾነው ልብሰ ተክህኖውን የሚከብቡት የወርቅ
ጸናጽል፤ ርሱ እረኛ ያመኑበትም የምስጢር በጎች፤ ርሱ ንጉሥ ሰማዕታቱም የመንግሥትን አዳራሽ የሚያስጌጧት ዕንቊዎች፤ ርሱ አውነተኛ የወይን ስፍራ
መነኮሳቱም ለሚያዩት ሰዎች ለአይን ያማረ የጽድቃቸውም ፍሬ በሚያነብበው
ሰው አፍ የሚጣፍጥ የወይን ዘለላዎች ናቸውና፤
ኢየሱስ ክርስቶስ የቅዱሳን ኹሉ ንጉሥ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠራው ስሙ
የጣፈጠ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያዳምጠው ቃሉ የጣፈጠ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚበላው ሥጋው የጣፈጠ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠጣው ደሙ የጣፈጠ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ዜናውን ለሚነግር መታሰቢያው የጣፈጠ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ የሰውም ልጅ ነው) በማለት ቤተ ክርስቲያናችን በኢየሱስክርስቶስ ላይ ያላትን ንጹሑን ትምህርት አስተምሯል፡፡ ይኸው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በማሕፀነ ማርያም ከተከናወነው አንሥቶ በልደት እስከኾነው ታላቅና አስደናቂ ምስጢርን በመጽሐፈ ምስጢር ላይ
ሲገልጸው “ወሶበ ይቤላ መልአክ መንፈስ ቅዱስ ይመጽእ ላዕሌኪ ተቀደሰት
በርደተ መንፈስ ቅዱስ ለከዊነ እመ አምላክ..." (መልአክ መንፈስ ቅዱስ ባንቺ
ላይ ይመጣል ባላት ጊዜ የአምላክ እናት ለመኾን በመንፈስ ቅዱስ ተለየች
ይኽም ካንቺ የሚወለደው ቅዱስ ነው የልዑል ልጅ ይባላል ሲላት ያን ጊዜ ከርሷ
የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ እንደኾነ አስተዋለች (ሉቃ ፩፥፴፭)፤ ኅሊናዋን ወልድ ከአባቱ ጋር ወዳለበት ወደ ጽርሐ አርያም አሳረገች፤ ርሱም ዝቅ ብሎ
ከሰማያት ወረደ ራሱንም በማሕፀኗ ውስጥ አሳደረ (ዮሐ ፩፥፲፬)፤
ዳግመኛም ድንግል መልአኩን እንዳልኸኝ ይኹንልኝ አለችው ያን ጊዜ ቃል ከርሷ
ሥጋን ተዋሐደ (ሉቃ ፩፥፴፰)፤ አይታ እንዳትደነግጥ ተመልክታም እንዳትፈራ ሰው በኾነ ጊዜ ከርሱ ጋር አራቱን እንስሳውን አላመጣም በሰማይ ሥርዐት የተጠበቁ
ሰማያውያኑን በዚያ ተወ (ራእ ፬፥፮-፱)፤ በዚኽም ለቅዱሳን መላእክት የሚረባ
ምድራዊት ሥርዐትን ሠራ (ሉቃ ፪፥፲፫)፤ በዚያ በአባቱ ቀኝ አለ በዚኽም በእናቱ
ማሕፀን ውስጥ አለ፤ በዚያ ብቻውን የማይታይ ኀይል ነው በዚኽም የማይዳሰስ ኀይል ከሥጋው ጋር የሚዳሰስ ኾነ፤ በዚያ ተሸካሚዎቹ እሳት የተሣለባቸው አራቱ
እንስሳ ናቸው (ሕዝ ፩፥፬-፳፮) በዚኽም ተሸካሚዎቹ ለሰውነት መንገድ የተገቡ
አራቱ ጠባይዐት ናቸው፤ በዚያ ያለ እናት አባት አለው (መዝ ፪፥፯፤ ዳን ፯፥፲፫-፲፬)
በዚኽም ያለምድራዊ አባት እናት አለችው (ሉቃ ፪፥፯)፤ በዚያ ገብርኤል በፍርሀት
ይቆማል (ሉቃ ፩፥፲፱) በዚኽም ገብርኤል በሐሤት የምሥራችን ይናገራል (ሉቃ
፩፥፳፮)፤ በዚያ በጽርሐ አርያም የሚደነቅ ከማይታይ አብ የመወለድ ምስጋና
አለው በዚኽም በቤተልሔም ከድንግል መወለድ ምስጋና አለው (ሉቃ ፪፥፩-፯)፤
በዚያ ከሰማያውያን ካህናት በወርቅ ማዕጠንት የዕጣኑን መዐዛ ይቀበላል (ራእ፰፥፫-፬) በዚኽም ወርቅንና ከርቤን ዕጣንንም ከሰብአ ሰገል ተቀበለ (ማቴ ፪፥፲፩) ፤ በዚያ ኪሩቤልና ሱራፌል ከግርማው የተነሣ ይንቀጠቀጣሉ በዚኽም ማርያም
ዐቀፈችው ሰሎሜም አገለገለችው፤ በዚያ የመብረቅ ብልጭልጭታ በፊቱ
ይገለባበጣሉ የእሳትም ወላፈን ከአዳራሹ ይወጣል (ሕዝ ፩፥፲፫) በዚኽም አህያና
ላም በትንፋሻቸው አሟሟቁት (ኢሳ ፩፥፫)፤
በዚያ የእሳት ዙፋን አለ በዚኽም የደንጊያ በረት አለ፤ በዚያ የእብነ በረድ የሰማይ
ንጣፍ አለ በዚኽም የላሞች መጠጊያ በረት አለ፤ በዚያ የትጉሃን ሥፍራ
በሰማያት ያለች ኢየሩሳሌም አለችው በዚኽም የእንስሳት ጠባቂዎች ማደሪያ
በኣት አለው (ሉቃ ፪፥፯)፤ በዚያ ርዝማኔ የማይታወቅ የዳንኤል ብሉየ መዋዕል
አባት አለው (ዳን ፯፥፲፫-፲፬) በዚኽም የዓመቶቹ ቊጥር በሰው ልጅ ዐቅም መጠን የኾነ ሽማግሌ ዮሴፍ ተሸከመው …
የአምላክን ልጅ ሰው መኾኑን በዓል እናድርግ የተሸከመችውን ማሕፀን
እናመስግን፤ ላቀፉት ጉልበቶች እንስገድ፤ ላሳደጉት ጡቶች እንዘምር፤
የዳሰሱትን እጆች እናመስግን፤ ለሳሙት ከንፈሮች እናሸብሽብ፤ ከእረኞች ጋር
ምስጋናን እናቅርብ፤ ከሰብአ ሰገልም ጋር እጅ እንንሣ፤ እንደ ዮሴፍ እናድንቅ እንደ
ሰሎሜም እናገልግል በተኛበት በ
