uk
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Відкрити в Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Показати більше
4 374
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
🌿🌾✞ #ንጹም_ጾመ ✞🌾🌿 ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ/፪/ ወንትቅፋቀር/፬/ ንትፋቀር በበይናቲነ//፪// | | |...፫ #ትርጉም፦ ጾምን እንጹም ወንድሞቻችንን እንውደድ እርስ በእርሳችን እንዋደድ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Orthodox2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌾✞ #ያከብርዋ_ለሰንበት ✞🌾 ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት ||፪ ወኩሉ ፍጥረት ዓሣት ወአናብርት እለ ውስተ ደይን ያዕረፋ ባቲ እስመባቲ አዕረፈ እምኩሉ ገብሩ |||፪ 🌾✞¤¤¤~~~✞~~~¤¤¤✞🌾 ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት ጻድቃንም በገነት ||፪ ፍጥረታት በሙሉ ዓሣዎችና አንበሪዎች በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ በእርሷ እንዳረፈ ከሥራው ሁሉ |||፪ ➤➤➤➤➤➤✞➤➤➤➤➤➤ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Orthodox2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ክርስቲያን ነኝ @EOTC2921.3gp1.16 MB

ተስፋዬ ድንግል ናት @EOTC2921 ግጥም.3gp4.68 KB

አንዲት ሴት ነበረች ሀጢያቷን የምትፅፍ፤ ልቧ በሀጢያት የሰከረ ለሀጢያት ተገዢ የሆነች፡፡ ይህች ሴት የተለያዩ ሀጢያቶችን የምትሰራ ነች 😱🙈ትዘሙታለች,,ትሰርቃለች 🙊🤔ትዋሻለች,,ታማለች ☠👾ትገድላለች 🍺🍷ትሰክራለች......👉✝አምላክ ሆይ የለ ንስሀ አትጥራን🙏 👉👉 @EOTC2921 👈👈

​​🌾✞ #መልክአ_ፍልሰታ ✞🌾 ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን ✞ ፩ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ሕያዊት ከምትሆን ነፍስሽ ጋር በፍጹም ተዋህዶ ለተከናወነው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ አንቺ ወለተ ማቲ የተባልሽ በነፍስ በስጋ በውስጥ በአፍአ አማናዊት ድንግል ነሽ እኮን ብልሆችና አዋቂዎች የአፌዝን ወርቅ አሳፍረው የሚጓዙብሽ ሰሎሜናዊት የተርሴስ መርከብ አንቺ ነሽ፡፡ ፪ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ኅዘንን ወደሚረሱበት ትካዜን ወደማያስቡበት የተረጋጋ ፍጹም ደስታ ወዳለበት ለተጓዘው ፍልሰተ ስጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ቅድመ አለም በአምላክ ልቡና ታስበሽ ያለሽ ነሽ እኮን፡፡ እንግዲህ በፍልሰትሽ በፍጹም ደስታ ዛሬ ደስ ተሰኝቻለሁ ነገር ግን ፊትሽን የማየው መቼ ይሆን፡፡ ፫ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ በሰው ልብ የማይታሰበውን ግርማ ሞገስን የተላበሰ ጸጋ ክብርን ለተጎናጸፈ ፍልሰተ ስጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ሥጋሽ ዕንቈ ባሕርይ ነው፡፡ ስለዚህም በደመና ሲያርግ በተመለከተ ጊዜ ሞት በፍጹም ኃፍረት አፈረ፡፡ ፬ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ከባረካ ልጅ ከኄኖክ ፍልሰት ከፍ ከፍ አድርጎ እግዚአብሔር አክብሮ ለባረካት ፍልሰተ ስጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ከብርሃናት ሁሉ የምትበልጭ ብርህትና አስደሳች ነሽ እኮን ስለዚህም የብዙ ብዙ የሚሆኑ የሰማይ መላእክት በአንቺ ምክንያት በሰማያዊት አዳራሽ ታላቅ ደስታን ያደርጋሉ፡፡ ፭ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ክብሩ ባለሟልነቱ ለማይገሰስ የምስጋናው ባሕር (ባሕርይ) ለማይጎድል ፍልሰተ ስጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ የእግዚአብሔር የልዩ ምስጋናው አዳራሽ ነሽ እኮን ስለዚህ በፍልሰትሽ ጊዜ አንቺን የተቀበሉ መላእክት ማርያምስ በሰማይም በምድርም የከበረች ነች ተባባሉ፡፡ ፮ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ከጌታ ወዳጅ ከያዕቆብ ፍልሰት ይልቅ ክብር ምስጋና ለተገባው ፍልሰተ ስጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ቀናንሞ የተባለ ሽቱ ነሽ። የልዩ ሽቱ አይነትም መገኛ ነሽ፡፡ ስለዚህም ብርሀን ለብሰው በብርሃን ነፀብራቅ ተጎናጽፈው የፍልሰትሽን በዓል መላእክት ያከብራሉ፡፡ ፯ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ከፀሐይና ከጨረቃ ሥነ ጸዳል ይልቅ ፈጽሞ ለሚያበራውና ፍጹም ምስጋና ለተገባው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ሁሉን ከሚያስደስትና የደስታ መገኛ ከሚሆን ልጅሽና ያለ አንቺ የሞትን ማሰሪያ በጣጥሶ የሲኦልን ደጃፍ ሰባብሮ ነፍሳትን ከዲያብሎስ የባርነት አገዛዝ ነጻ ያወጣ ማንም የለም፡፡ ፰ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ሱራፊ መልአክ እየጠበቃት በኪሩቤል ከተማ ትኖር ዘንድ ከዚህ ከአላፊውና ከጨለማው ዓለም ለተዛወረችው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ከጥቅምት ወር የጽጌ የአበባ ሽታ ይልቅ የመዓዛሽ ጣዕም እጅግ የጣፈጠ ነው፡፡እነሆ በስህተት ባሕር ልሰጥም ተቃርቤአለሁና በንጽሕናሽ በቅድስናሽ መርከብ አሳፍረሽ እኔን አገልጋይሽን አሻግሪኝ፡፡ ፱ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ በቅድስተ ቅዱሰን ቆሞ የነግሁን መስዋዕት ሲያሳርግ የካህናቱን አለቃ ለአስደነቀው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ አምላክ ያተመው የፍልሰትሽ ግርማ ሞገስ ያን የቂም በቀል መልአክና የክፉ መጨረሻ የሆነ መልዐከ ሞት ምንኛ አሰቃየው ምንኛ መከራውን አሳየው እሰይ እሰይ። ፲ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ የይቅርታው ክናድ ለዘላለሙ ጸንቶ ለሚኖረውና የኃይለኞች ኃይለኛ ለሚሆን ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል። #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ መታሰቢያሽ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለዘላለም ሲታሰብ ይኖራል። በምድር ላይ ለሚኖሩ ኃጥአን ሁሉ አማልደሽ ምህረት የምታስገኝ ነሽና እመቤቴ ሆይ የተባረክሽ የክርስቶስ አካሉን ነሽ፡፡ ፲፩ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ለተመረጡት ልጆች እናት ትሆኛቸው ዘንድ ምጡቅ በሆነ በብርሀን ሰረገላ ለመጠቀ ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል። #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ብዙዎች ወገኖች በሁለት ድሪም በአስፈላጊው ጊዜ በትጋትና በመፋጠን ወገንን እንደሚዋጁ እኔን አገልጋይሽን በይቅርታሽ ወርቅ ዋጅተሽ ገንዘብ አድርጊኝ፡፡ ፲፪ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ እግዚአብሔር ለተዋሐዳትና ስነ ስርአቷንም ለተካፈላት ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ በፍልሰትሽ ጊዜ በምድረ ይሁዳና በኢየሩሳሌም አደባባይ የተርሴስና የደስያት ነገስታት ለመታሰቢያሽ መዓዛቸው የጣፈጠ ሽቶና ልዩ ልዩ እጅ መንሻዎች ይዘው ቀረቡ፡፡ ፲፫ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ከሴሎ ነቢይ ከኤልያስ ፍልሰት ይልቅ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ላደረገው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ ሁሉን እንዳውሬ የሚያድን ሞት ተከትሎኝ የኔ በተድላ ደስታ መኖር ምኔም ስለአይደለ በአውሎ ነፋስ ክንፍ ጠልፈሽ ጻድቅ ካለበት ቦታ ወስደሽ ከዚያ አድርሽኝ። ፲፬ #ለፍልሰተ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ተጠባቢዋና መጋቢዋ እግዚአብሔር የሆነ ወደ አማረችውና ወደ ተደላደለችው ሀገር ለፈለሰው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ መሪር ከሆነ የሞት አገዛዝ ነፃ አውጪኝ የሰማይና የምድር ንግሥት ሆይ አንቺ እኮ ከፈቀድሽ ኃጥኡን ባሪያ ነፃ ማውጣት አይሳንሽም ፡፡ ፲፭ #ለትንሣኤ_ሥጋኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ ሕያው ባሕርዩን በውስጧ ሰውሮ ለተነሳባት የክርስቶስ ትንሳኤ መንትያ ለሆነች ትንሣኤ ስጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ በዚያች በቁርጥ ቀን የፍርድ ምርመራ በተደረገ ጊዜ ምድርም አደራዋን በመለሰች ጊዜ አንቺ የኤፍራታ ርግብ ሆይ በክንፈ ረድኤትሽ ሠውሪኝ በጥላሽም ሥር ሸሽገሽ አድኚኝ፡፡ ፲፮ #ለዕርገተ_ሥጋ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ አንቺን ለሚያመሰግኑ ቅዱሳን ሰዎች ሁሉ የዕርገታቸው መመሪያ ለሆነ ዕርገተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ የሊቀ ካህናቱ የካህኑ የአሮን የሽልማቱ ጌጥ ነሽ እኮን በአንደበታችን የሚነገረው የምስጋናሽ ፍሬ ሁሉ በውስጥም በውጭም ላለው ልብስሽ ላይ በስዕል መልክ ተቀርጾ ይኑር፡፡ ፲፯ #ስብሐት_ለኪ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፦ በሥጋዊ በደማዊ አንደበት ሁሉ ለአንቺ ምስጋና ይገባል፡፡ በመላእክትም አንደበት ያለማቋረጥ ለአንቺ ምስጋና ይገባል፡፡ #ድንግል_እመቤቴ_ሆይ የደብተራ ኦሪት ቃል ኪዳን የተጻፈብሽ የሕግ ታቦት ላንቺ ሰላምታ ይገባል፡፡እንደዚሁም ለኔ ለአገልጋይሽ ለ........ የክብር ጌጥ ወይም ሽልማት ሆኖኝ ይኖር ዘንድ የልዩ ችሮታሽን የነጭ ሐር ልብስ አጎናጽፊኝ፡፡ ይልቁንም በሥጋ በነፍስ ጥበቃሽ አይለየኝ፡፡ አሜን። ---✞ #አቡነ_ዘበሰማያት ✞--- ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

❖ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም መፀነስ ከሊቃውንት መኻከል አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ “ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ ወፈረየኪ ለሕይወት ኢያቄም መዋቲ እሴብሕ ተአምረኪ ርግብየ አሐቲ ወድኀኒተ ኲሉ ዓለም እስመ ኮንኪ አንቲ” (ሐና አንቺን የፀነሰችባት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ አንዲቱ ርግቤ ማርያም አንቺ የዓለሙ ኹሉ መድኀኒት ኾነሻልና ታምርሽን አመሰግናለኊ) በማለት ዓለምን ኹሉ በደሙ ፈሳሽነት ያዳነ ንጉሣችን፣ ፈጣሪያችን ክርስቶስን በድንቅ ተአምር ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ የወለደችልን ምክንያተ ድኂን ርግበ ሰሎሞን የተባለች የቅድስት ድንግልን የመፀነሷን ነገር በአድናቆት ገልጸዋል፡፡ ❖ ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በአርጋኖን መጽሐፉ ላይ የዜና ጽንሰቷን ነገር ሲገልጽ “ወይእዜኒ ኦ ውሉደ እግዚአብሔር ወማኅበረ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናስተብፅዖሙ ለሐና ወለኢያቄም...” (አኹንም የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆችና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማኅበሮች ሆይ ይኽቺን የተባረከችና የተመረጠች ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናመስግናቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግልን የተባረከችዋን ፍሬ ያፈራችበትን ንጽሕት የምትኾን የሩካቤያቸው ዕለት እንደምን ያለች ዕለት ናት? ከይሁዳ ወገን ለኾነችው ንጽሕት ርግብ መፀነስ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ የጾታዊ ተዋሕዷቸው ቀን ይኽቺ እንዴት ያለች የተመረጠች ቀን ናት፤ ለንጉሥ ማደሪያ አዳራሽ መመሥረት የተደረገባት (የኾነባት) የደስታ ቀን እንዴት ያላት ቀን ናት?) በማለት የፅንሰቷን ነገር አድንቋል። ❖ ሊቁ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም መጽሐፉ በቊ ፴፰ ላይ “ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ” (ድንግል ሆይ በኀጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለሽም በሕግ በኾነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ) በማለት ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንተ ኀጢአት ካመጣው መርገም በፅንሰቷ ጊዜ እንዳትያዝ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የተጠበቀ መኾኑን ተናግሯል፡፡ ❖ “ወእምድኅረ ስድስቱ አውራኅ ተዐውቀ ፅንሳ ለሐና” ይላል፤ ከስድስት ወርም በኋላ የሐና ፅንሷ እየታወቀ ሲመጣ ጎረቤቶቿ መፅነሷን ይረዱ ዘንድ በአድናቆት ማሕፀኗን ይዳስሱ ነበር፤ በተለይም ዐይኗ የታወረ የሐና ዘመዷ የአርሳባን ልጅ የምትኾን አንዲት ሴት የሐናን ማሕፀን ዳስሳ ዐይኗን ብትነካው በርቶላት በታላቅ ደስታ ኾና “ብፅዓን ለኪ ኦ ሐና እስመ እም ፍጥረተ ዓለም አልቦ ዘከማኪ ዘይፌውስ በከርሡ አዕይንተ ዕውራን” (ሐና ሆይ ብፅዓን ይገባሻል ዓለም ከተፈጠረ ዠምሮ እንዳንቺ በማሕፀኑ የዕውራንን ዐይን የሚያበራ የለምና) በማለት አመስግናታለች፤ ከዚኽ በኋላ ዝናዋ በሀገሩ ኹሉ ተሰምቶ ሕሙማን ኹሉ ማሕፀኗን እየዳሰሱ ይፈወሱ ነበር፡፡ ❖ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ይኽነን ሲገልጹ፦ “ጸግይየ ሣዕረ ዘኪሩቤል ልሳነ ተአምረኪ በነጊር እመ ኢፈጸምኩ አነ ባሕቱ አአኲት ማርያም ዘጾረተኪ ማሕፀነ እንዘ ሀለወት ፀኒሳ ኪያኪ ርጢነ ለለገሰስዋ ላቲ ትፌውስ ዱያነ” (ሳርን የኾንኊ እኔ የኪሩቤል አንደበትን ገንዘብ አድርጌ ታምርሽን በመንገር በማስተማር ባልፈጽምም ነገር ግን ማርያም የተሸከመቺሽን ማሕፀን አመሰግናለኊ፤ መድኀኒት አንቺን ፀንሳ ሳለች ርሷን የዳሰሷትን ድዉያንን ኹሉ ትፈውስ ነበር) በማለት እመ መድኅነ ዓለም ገና ሳትወለድ የተሠራውን ድንቅ ተአምር አመስግነዋል፡፡ ❖ ይኽ የቅድስት ድንግል ማርያም የፅንሰት በዓል በመላው ዓለም የሚታወቅ ሲኾን ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት የኾነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን የአምላክ እናት የተፀነሰችበት ይኽነን በዓል ነሐሴ ፯ ቀን በታላቅ ድምቀት በማሕሌት፣ በቅዳሴ የምታስበው ሲኾን በዓሉም “ፅንሰታ ለማርያም” በመባል ይታወቃል፤ በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ደግሞ በዓሉን “The conception of the Theotokos” (የአምላክ እናት መፀነስ) በማለት ሲያከብሩት ወሩን ግን የልደት በዓልን ለማክበር በሚዘጋጁበት በታኅሣሥ አድርገው በ፱ኛው ቀን “December 9” ላይ ያስቡታል፡፡ ✍ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌾✞ #ፅንሰታ_ለማርያም ✞🌾 #የአምላክ_እናት_የተፀነሰችበት ❖ ነሐሴ ፯ የአምላክ እናት የፅንሰቷ በዓል በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል። በነገረ ማርያም ላይ እንደተጻፈ በእናቷ በሐና በኩል ያሉ የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ጴጥሪቃ ቴክታ ሲባሉ “ወኮኑ ክልኤሆሙ ጻድቃን ወፈራህያነ እግዚአብሔር ወይትአመንዎ ለአምላኮሙ በጥቡዕ ልብ እንበለ ኑፋቄ” ይላል (ኹለቱም ሰዎች ደጋጐችና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ያለምንም መጠራጠር በፍጹም ልቡናቸው በአምላካቸው የሚተማመኑ ነበሩ)። ❖ እነርሱም በጊዜው ይኽ ቀራችኊ የማይባሉ ባለጠጎች ነበሩ፤ ከሀብታቸው ብዛት የተነሣ ወርቁን ብሩን እንደ ዋንጫ እያሠሩ በላሙ በበሬው ቀንድ ላይ ይሰኩት ነበር፤ ይኽን ያኽል አቅርንተ ወርቅ፣ አቅርንተ ብሩር እየተባለ ይቈጠር ነበር፤ የዕንቊ ጽዋ እንኳ ፸፣ ፹ ያኽል ነበራቸው ይላል ፡፡ ❖ ከዕለታት ባንዳቸው ጴጥሪቃ ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ የሀብቱን ብዛት አይቶ ሚስቱ ቴክታን “ለመኑ ዘዘገብነ መዛግብቲነ አልብነ ውሉድ ዘይወርሰነ አንቲኒ ወአነሂ መካን ንሕነ” (የሰበሰብነው ገንዘብ ስንኳን ለኛ ለልጅ ልጅ ይተርፍ ነበር አንቺም እኔም መካኖች ነንና የሚወርሰን ልጅ የለንም) በማለት ተናገራት፤ ርሷም እንዲኽ ማለቱ ወላድ የፈለገ መስሏት በሐዘን ኾና “አምላከ እስራኤል ከኔ ልጅ ባይሰጥኽ ከሌላ ይሰጥኽ ይኾናልና ሌላ አግብተኽ ውለድ” አለችው። ❖ ርሱም “አነሂ ኢይፈቅድ የአምር አምላከ እስራኤል ከመ ኢየሐስቦ ለልብየ” (ይኽንስ እንዳላደርገው በልቤም እንዳላስበው የእስራኤል አምላክ ያውቃል) በማለት ተናገረ፡፡ ርሷም ዐዝና ሳለ ራእይ ታያለች፤ ነጭ እንቦሳ ከማሕፀኗ ስትወጣ እንቦሳዪቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ሰባት ስትደርስ ሰባተኛዋ ጨረቃን ስትወልድ፤ ጨረቃ ፀሓይን ስትወልድ አይታ በአድናቆት ለባሏ “ግሩም ግብሩ ለእግዚአብሔር ትማልም ርኢኩ በሕልምየ ጸዐዳ ጣዕዋ ወጽአት እምከርሥየ ይእቲኒ ወለደት ጸዐዳ ጣዕዋ እስከ ሰብዐቲሆን ወሳብዕታኒ ወለደት ወርኀ ወወርኅኒ ወለደት ፀሓየ” (የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው፤ ትናንትና ማታ በሕልሜ ነጭ ጥጃ ከማሕፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ደግሞ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንደዚኽ እየኾነ እስከ ሰባት ትውልድ ሲደርሱ ሰባተኛዪቷም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየኊ) በማለት አስረዳችው። ❖ ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ሕልም ወደሚፈታ ሰው ዘንድ በመኼድ የሚስቱን ራእይ ነገረው፤ ያም ሕልም ተርጓሚ ምስጢር ተገልጾለት ሰባት አንስት ጥጆች መውለዳችኊ ሰባት ሴቶች ልጆች ይወለዳሉ፤ ነጭ መኾናቸው ደጋጎች ልጆች መኾናቸው ሲኾን “ወሳብእታኒ ትከብር እመላእክት ወትትሌዐል እምኲሉ ሰብእ ወበእንተ ፀሓይኒ ኢያእመርኩ” (ሰባተኛዪቱ ጨረቃን መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ናት፤ የፀሓይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም) በማለት ተረጐመለት፤ ርሱም ለሚስቱ ነገራት፤ ርሷም “የእስራኤል አምላክ የሚያደርገውን ርሱ ያውቃል” በማለት ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ ❖ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች ስሟንም ሔሜን አሏት፤ ሔሜን →ዴርዴን ወለደች፤ ዴርዴም →ቶናን፤ ቶናም →ሲካርን ወለደች፤ ሲካርም→ ሴትናን፤ ሴትናም →ሔርሜላን ወለደች፤ ሔርሜላም የተከበረችና የተመረጠች ዓለሙን ኹሉ ለፈጠረ ጌታ አያት ለመኾን የበቃች ሐናን ወልዳለች፤ የዝማሬና የትንቢት ጸጋ ከእግዚአብሔር የተሰጡት ክቡር ዳዊት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በተለይም ስለ ሥርወ ልደቷ አስቀድሞ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት በመዝ ፹፮፥፩‐፯ ላይ “መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን” (መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ላይ ናቸው) በማለት የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥት ከቤተ ክህነት ከኾኑት ከተቀደሱት ከቅዱሱ ኢያቄምና ከቅድስቲቱ ሐና የመኾኑን ነገር በምሳሌ የገለጸው። ❖ ሐና በመልካም አስተዳደግ አድጋ አካለ መጠን ስታደርስ ከነገደ ይሁዳ ከመንግሥት ወገን የተወለደ የቅስራ ልጅ የአልዓዛር የልጅ ልጅ ከሚኾን ከኢያቄም ጋራ አስተጫጭተው አጋቧት፡፡ ሐናና ኢያቄምንም “ወክልኤሆሙ ኄራን ወሥሙራን እሙንቱ ወየሐውሩ በሕገ እግዚአብሔር እስመ እግዚአብሔር ኀረዮሙ ወአፍቀሮሙ ትካት” ይላቸዋል እግዚአብሔርን የሚወድዱ በሕጉ የሚኖሩ ደጋጎችና አምላክም የመረጣቸው ሲኾኑ ሐና መካን በመኾኗ ምክንያት ኹለቱም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ዕለት ዕለት በመኼድ ለዐይናቸው ማረፊያ ለልባቸው ተስፋ የሚኾን ልጅ እንዲሰጣቸው ይለምኑ እንደነበር፤ “Protoevangelium of James” (ፕሮቶቫንጊሊዩም ኦፍ ጀምስ) የሚለው ያዕቆብ የጻፈው ጥንታዊዉ መጽሐፍ በስፋት ይገልጻል፡፡ ❖ ከዕለታት ባንደኛው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ሲመለሱ “ወርእዩ አርጋበ እንዘ ይትፌሥሑ ምስለ ውሉዶሙ” ይላል ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ደስ ብሏቸው ሲጫወቱ አይተው ሐና “አቤቱ ጌታዬ ግዕዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠኽ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሣኸኝ” ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፤ ወዲያው ሱባዔ ይገባሉ፤ ኢያቄም ወደ በረሓ ኼዶ ሲጸልይ ሐና ደግሞ በቤቷ ዙሪያ ባለው የተክል ቦታ ሱባዔ ያዘች፤ በሱባዔያቸው ፍጻሜ ኹለቱም ራእይ አይተው ተነጋግረዋል፡፡ ❖ “ይቤላ ኢያቄም ለሐና ብእሲቱ እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ” ይላል ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዎፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ብሎ የተገለጸለትን ለሐና ነግሯታል፤ ይኸውም የራእዩ ምስጢር፡- ዎፍ የተባለው አካላዊ ቃል ክርስቶስ ሲኾን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፤ ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየኊ ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ ሲያጠይቅ ሲኾን፤ ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ምልአቱ፣ ስፍሐቱ፣ ርቀቱ፣ ልዕልናው፣ ዕበዩ ናቸው፡፡ ❖ ሐናም ተገልጾላት “ትቤሎ ሐና ለኢያቄም ብእሲሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ” ይላል ለባሏ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ብላዋለች፤ ይኽ የራእይ ምስጢር፦ ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትኾን፤ ነጭነቷ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፤ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ ወደ ዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በዦሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መኾኗን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ❖ ኢያቄምና ሐናም ይኽነን ራእይ ሐምሌ ፴ ቀን ካዩ በኋላ “ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ይኾናል፤ ሴትም ብንወልድ ለቤተ እግዚአብሔር መጋረጃ ፈትላ ትኑር” ብለው ስእለት ከተሳሉ በኋላ ራእይ አየን ብለው ዕለቱን አልተገናኙም፤ አዳምንና ሔዋንን “ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት” ብሎ የተናገረው አምላክ ለእኛም ይግለጽልን ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ሰባት ቀን ድረስ እየብቻቸው ሰነበቱ። ❖ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን “ከሰው የበለጠች ከመላእክት ኹሉ የከበረች ልጅ ትወልዳላችኊ" ብሎ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለሐና ነግሯት በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን ነሐሴ ሰባት እሑድ ተፀንሳለች፤ በእናቷ ማሕፀን ሳለችም “መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እምከርሠ እማ” እንዲል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥንተ አብሶ ባመጣው መርገም እንዳትያዝ ጠብቋታል፡፡ ~~~✞ #ይቀጥላል ✞~~~

#እግዚኦ_መሐረነ_ክርስቶስ {ለምን እንላለን}? ✞✞✞ —“#ሚስጢሩ ”— በቤተክርስቲያናችን ስርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔር ከታሰራችሁበት ኃጥያት ማሰሪያ ይፍታቹ ሲሉ 12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና 12 ጊዜ ደግሞ በእንተ እግዝትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ያስብላሉ ። ካህናትና ምእመናን በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህኑን 12 ጊዜ እንላለን ። እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት አቤቱ ክርስቶስ ማረን ሲሆን በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ደግሞ ስለ እመቤታችን ማርያም ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን ማለት ነው ። አስራ ሁሉት ጊዜ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12 ሰዓት በእንተ እግዝእትነ ማርያም ደግሞ ለሊቱን 12 ሰዓት ሲሆን በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሰራነው ኃጥያት በሃያ አራቱ 24ቱ ሰዓት ምሕረት እናገኝ ዘንድ ነው። ሌላው አስራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት፦ #1ኛው በስመ ሥላሴ ነው በእያንዳንዱ ፊደል #አ_ብ_ወ_ል_ድ_መ_ን_ፈ_ስ_ቅ_ዱ_ስ ፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪ #2ኛው የድህነታችን ምክንያት በሆነች በእመቤታችን ስም ፊደል ነው ። #ቅ_ድ_ስ_ት_ድ_ን_ግ_ል_ማ_ር_ያ_ም ፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪ ———✞ “እግዚኦ” ✞——— አቆጣጠረም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራ ጣት እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ፣ ቀጥሎ በመሐል ጣት ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደ ታች ተደርጎ በማርያም ጣት /በትንሿ/ ጣት ወደ ላይ ነው ። ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ~ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር መመላለሱን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን ። መሐል ጣት ወደ ላይ ~ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን በቀለበት ጣት ወደ ታች ስንቆጥር ወደዚች አለም ለፍርድ መምጣቱን፤ በትንሿ ጣት ወደ ላይ ስንወጣ ደግሞ በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደ ሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው። ———✞ “ብእንተ” ✞——— በእንተ እግዝትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ ከትንሿ ጣት ወደ ታች ይጀመርና በጠቋሚ ጣት ወደ ላይ ይፈጸማል ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና ከፍ ማለቷን የሚያሳይ ምሥጢር ነው ። ብእንት ሲባል በትንሿ ጣት ወደ ታች የሚጀመር ራሷን ዝቅ አድርጋ የትህትናዋ ምሳሌ ስለሆነ ነው ከላይ ወደ ታች ሚጀመረው። “ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል” - የማቴ፡ 23፥12 ደግሞ የበእንት ፍጻሜ ወደላይ የሚያልቀ ሚስጢሩ እመቤታችን በመቃብር አልቆየችም ወደላይ አረገች ማለት ነው። “ አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት” መዝ፡ 132፥8 ስንዱዋ እመቤት ቅድስት ቤተክርስቲያን ማንኛውም ነገር ያለ ትርጉም አታደርግም።

photo content

🌿🌾✞ #ንጹም_ጾመ ✞🌾🌿 ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ/፪/ ወንትቅፋቀር/፬/ ንትፋቀር በበይናቲነ//፪// | | |...፫ #ትርጉም፦ ጾምን እንጹም ወንድሞቻችንን እንውደድ እርስ በእርሳችን እንዋደድ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Orthodox2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌾✞ #ያከብርዋ_ለሰንበት ✞🌾 ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት ||፪ ወኩሉ ፍጥረት ዓሣት ወአናብርት እለ ውስተ ደይን ያዕረፋ ባቲ እስመባቲ አዕረፈ እምኩሉ ገብሩ |||፪ 🌾✞¤¤¤~~~✞~~~¤¤¤✞🌾 ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት ጻድቃንም በገነት ||፪ ፍጥረታት በሙሉ ዓሣዎችና አንበሪዎች በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ በእርሷ እንዳረፈ ከሥራው ሁሉ |||፪ ➤➤➤➤➤➤✞➤➤➤➤➤➤ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Orthodox2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

☞✞ አንድ ንጉሥ መዝሙረ ዳዊትን ስንጸልይ ለዕለቱ የታዘዘውን ሃያ እና ሰላሳ መዝሙር ማድረስ ባንችል እንኳን አንድ ንጉሥ ማድረስ ይገባናል። አንድ ንጉሥ የሚባለው፦ ✔አስር መዝሙር ነው፡፡ ለምሳሌ፡ ከሰኞ አንድ ንጉስ ለማድረስ ከፈቀዱ ከ1–10 ያለውን ያደርሳሉ፡፡ ከማክሰኞ ከሆነ ደግሞ ከ30–40 ያውን የመጀመሪያውን አስር መዝሙር ያደርሳሉ ማለት ነው፡፡ ይህን ሁሉ ማድረስ ያልተቻለው ግን የተወሰኑ መዝሙራትን መርጦ በየእለቱ ያደርሳል፡፡ ፪. #ውዳሴ_ማርያም ውዳሴ ማርያም ከተቻለ የሰባቱን ዕለታት ካልተቻለ የእለቱን ማድረስ ተገቢ ነው። የዘወትር ጸሎት ካደረስን በኋላ የዕለቱን ውዳሴ ማርያም አድርሰን ይዌድስዋ መላዕክትን ደግመን ከእመቤታችን በረከት ተሳታፊ መሆን ተገቢ ነው፡፡ ✔በዋልድባ የሚኖሩ መነኮሳት ውዳሴ ማርያም ከቅዳሴ ማርያም ሳያደርሱ ውለው አያድሩም፡፡ ✔በየአብነት ትምህርት ቤቱ የሚገኙ መምህራንና ተማሪዎችእና በየገዳማት ያሉ መነኮሳት ሁሉ ውዳሴ ማርያምን በየዕለቱ ያደርሳሉ፡፡ ✔እኛም ከአበው ተምረን ማታ ከመኝታ በፊት ወይም ጠዋት ስንነሳ ይህን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው፡፡ ፫. #ወንጌል_ዘዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌልን በየምዕራፍ ከፋፍለን በየእለቱ ማንበብ ሌላው ጸሎት ነው፡፡ ✔አባቶች ይህንንጸሎት በየእለቱ እያደረሱ ብዙ ተጠቅመውበታል። ፬. #ሌሎች_ጸሎታት ውዳሴ አምላክ፣ ሰኔ ጎለጎታ፣ መልክአ ኢየሱስ፣ መልክአ ማርያም፣ በመዝገበ ጸሎት እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍት ላይ ያሉትን ሌሎች ጸሎታት፣ እንዲሁም ገድላት፣ ተአምራትን፣ እንደ ችሎታችን በየዕለቱ እናደርሳለን፡፡ ቢያንስ ግን ይህ ሁሉ ባይሆንልን ከላይ የጠቀስነውን የመዝሙረ ዳዊትና ውዳሴ ማርያምን ጸሎት ማድረስ ይገባናል፡፡✔አጭር ጸሎት በተቻኮልን እና መጻሕፍትን ለማንበብ ጨርሶውን ጊዜ በማይኖረን ሰዓት ይህንን እንድንጸልይ አንዳንድ አባቶች ይመክሩናል። አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ ሃይማኖት፣ ሰላም ለኪ /ስለውዳሴ ማርያም ፈንታ/፣ አቡነ ዘበሰማያት፣ አንድ ከመዝሙረ ዳዊት(መዝሙር 150) /በመዝሙረ ዳዊት ፈንታ/ በመጨረሻም አቡነ ዘበሰማያት ማድረስ ብንችል መልካም ነው። ✔ጸሎተ ሃይማኖት የህይማንት መግለጫ በምሆኑ እንጸልየዋለን። በመካከል ሰላም ለኪ በመድገማችንም የውዳሴ ማርያም በረከት ይደርሰናል። መዝሙረ ዳዊት 150 ስናደርስ ደግሞ ሁሉንም መዝሙራት የደገምን ያህል ይሆንልንና የዳዊቱን በረከት እናገኛለን፡፡ ይህንን ሁሉ ማድረስ ካልተቻለን ግን ቢያንስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን አቡነ ዘበሰማያት ብለን ከቤታችን ልንወጣ ይገባናል። ✔አጭር ጸሎት ከሥፍራ ሥፍራ ሊለያይ ይችላል፡፡ ዘጠኝ ሰላም ለኪ፣ አስራ ሁለት አቡነ ዘበሰማያት በገዳማት ያሉ አበው ያደርሳሉ። ✔አጭር ጸሎትን እነደ መደበኛ ማድረግ ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ✔አጭር ጸሎት የምንጸልየው በጣም በተቸገርንበት፣ ጊዜ ባጣንበት ሰዓት ነው። ይህንን ጸሎት እንደመደበኛ ይዞ በየእለቱ አንድ አቡነ ዘበሰማያት ብቻ መድገም ግን ስንፍና እንዳይሆን ያስፈራል። ይልቁንም በክርስትና ሕይወት ጅማሬ ላይ ያሉ ምእመናን/ወጣንያን/ክርስትናውን እስኪላመዱ ጸሎታቸው አጭር ሊሆን ይችላል። እየቆዩ ሲሄዱ ግን በጸሎት እየበረቱ ወደ መደበኛው ጸሎት መድረስ አለባቸው። ሁልጊዜ ወተት መመኘት ሁልጊዜ አልበረታውም እያሉ አጭር ጸሎት እያደረሱ መተኛት ተገቢ አይደለም። ይህ አይነቱ አካሄድ የእግዚአብሔርን ቸርነት ለስንፍና ምክንያት አድርጎ መጠቀምም ነው። ✔ከዚህ ጋር በቤተክርስቲያን አገልገሎት ላይ ያለንም ዳዊት መድገም ውዳሴ ማርያም ማድረስ ይጠበቅብናል። የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ መዘምራን ወዘተ እነዚህን ጸሎታት መጸለይ ይጠበቅባቸዋል። አልያ ግን እያወቅን ጸሎት ማድረስ እንዳለብን ብዙ ጊዜ ተምረን እንዳልተምርን ቸል ብንል ለፈተና መጋለጥ ይመጣል። ከእግዚአብሔርም ቸርነት እንድንርቅ ያደርገናል። ✔አቡነ ዘበሰማያት የጸሎታችን መነሻና መድረሻ ጸሎት ስናደርስ የጸሎታችን መነሻ (መጀመሪያ) አቡነ ዘበሰማያት ነው፡፡ ✔በመካከል ጸሎት አቋርጠን ከሰው የምንነጋገርበት ጉዳይ ቢገጥመን በአቡነ ዘበሰማያት ማሰር ተገቢ ነው፡፡ በአቡነ ዘበሰማያት አስረን የገጠመንን ጉዳይ ፈፅመን እንመለሳለን፡፡ ከዚያም አቡነ ዘበሰማያት ብለን ካቆምንበት እንቀጥላለን። ጸሎታችንን በአቡነ ዘበሰማያት ሳናስር በመሃል እንዳሻን እንዳናቋርጥ አበው ያስተምሩናል፡፡ ✔የማህበር ጸሎት በቤታችን ከምንጸልየው ጸሎት በተጨማሪ በቤተክርስቲያን ተገኝተን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት እንደመሆኗ በእርሷ የሚጸለይ ጸሎት ከጸሎታት ሁሉ የላቀ ነው። በካህናት እየተመራ፣ በሕብረት ሆነን የምናደርሰው በመሆኑ ታላቅ ኃይል አለው። እግዚአብሔር በቤተ መቅደስ የምንጸልየውን ጸሎት እንደሚሰማ ሲያመለክተን እንዲህ በማለት ነግሮናል። "አሁንም በዚህ ሥፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ፣ ጆሮቼም ያደምጣሉ። ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም ዓይኖቼ እና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።"/2 ዜና መዋ 7-15/ ከዚህ አንጻር በቤተ መቅደስ እየተገኘን መጸለይ ተገቢ ነው። በሰንበት ቀን ኪዳን ማድረስ፣ ቅዳሴ ማስቀደስ የመጀመሪያው እና ዋነኛው ተግባራችን መሆን አለበት። በሰንበት ያለ በቂ ምክንያት ቅዳሴ የሚያስታጉል በቀደሙ አባቶች /አባ ሚካኤል ወአባ ገብረኤል/ ቃል መወገዙን የተአምረ ማርያም መቅድም ይነግረናል። ከዚህ ጋር በሰዓታት፣ በማኅሌት ጸሎታት ላይ በመገኘት ቤተ ክርስቲያናችን ካዘጋጀችልን የማይጠገብ ማእድ ልንሳተፍም ይገባናል፡፡ ✔የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች የሐይማኖታችን ፍጹም ፍቅር የሚኖረን ከእነዚህ ጸሎታት ጋር ስንተዋወቅ ነው። አልያ የእንጀራ ልጅ መሆን ይመጣል። የመናፍቃንን አዳራሽ መናፈቅ ይመጣል። ✔ከላይ በተመለከተው የጸሎት ጊዜ እየተጠቀምክ፣ የጸሎት ዓይነቶችንም በምትችለው መልኩ እያደረስህ፣ በቤተ መቅደስ እየተገኘህ ኪዳን እያደረስህ፣ ቅዳሴ እያስቀደስህ ከፈጣሪህ ጋራ እለት እለት ተነጋገር ጸሎት ከሌለ መንፈሳዊነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ ከጄነሬተሩ ተቋርጦ ገመዱ ተበጥሶ ብቻውን እንደተንጠለጠለ አምፖል መሆንይ መጣል፡፡ ስለዚህ በርታና ጸልይ ፈጣሪ ለሁላችንም ብርታቱን ያድለን፡፡ አሜን፡፡ 🙏✞ የእግዚአብሔር አብ በረከት፤ የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፤ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፤ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፤ የጻድቃን የሰማዓታት ፀሎት፤ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖታችን ይጠብቅልን፡፡ አሜን ለዘላለሙ፡፡ ✞🙏

❀♣✞ #ጸሎት ✞♣❀ #ምን_ዓይነት_ጸሎት_ልጸልይ? #ሊነበብ_የሚገባው_ድንቅ_አስተምሮ ☞✞ ጸሎት በክርስትና ሕይወት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በጥያቄዎቻችሁ መሠረት የምንጸልይባቸውን ጊዜያት፣ የምንጸልየውን የጸሎት ዓይነት፣ ምን መምሰል እንዳለበት ለማየት እንሞክራለን፡፡ #1. የጸሎት ጊዜያት ልበ አምላክ ነቢየ ልዑል ቅዱስ ዳዊት”ስብዓ ለእለትየ እሴብሐከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ፣ ስለ ጽድቅህ ፍርድ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለው”/መዝ 118-164/ ብሎ እንደተናገረ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ሰባት ጊዜ በየእለቱ እንዲጸልይ ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡ ሰባቱ የጸሎት ጊዜያትም የሚከተሉት ናቸው፡፡ ➊. #ጸሎተ_ነግህ ቅዱስ ዳዊት “አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ” መዝ 62÷11 እንዳለ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ፣ ከመኝታችን ስንነሳ ምንጸልየው የጸሎት ዓይነት ጸሎተ ነግህ ይባላል፡፡ በዚህ ጊዜ የሚከተሉትን ምስጢራት እያሰብን መጸለይ ይገባናል፡፡ ✔ሌሊቱን አሳልፎ ቀኑን ስለተካልን እያመሰገንን ወጥተን እስክንገባ በሰላም ጠብቆ ውሎአችንን የተባረከ እንዲያደርግልን እንጸልያለን። ✔የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረበትም ሰዓት በመሆኑ ያንን እያሰብን እንጸልያለን፡፡ ✔የሰውን ልጅ በመዓልትና በሌሊት የሚጠብቁ መላእክት ለተልዕኮ ሲፋጠኑ የሚገናኙበት ሰዓት ነው፡፡ ✔የሌሊቱ መልአክ ሲሄድ የቀኑ መልአክ ሲቀርብና ሲተካ የሚገናኙበት በመሆኑ በዚህም ሰዓት እንጸልያለን፡፡ ✔ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች በደል በጲላጦስ አደባባይ የቆመበት ሰዓት በመሆኑ እንጸልያለን። ➋ #ጸሎተ_ሠለስት ከነግህ በመቀጠል የምንጸልየው ጸሎት ጸሎተ ሠለስት (የሦስት ሰዓት) ጸሎት ይባላል፡፡ ይህ የጸሎት ጊዜም የምናስበው፦ ✔ሔዋን የተፈጠረችበት ✔እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት የሰማችበት ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት ✔ነቢዩ ዳንኤል ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ መልሶ የቤቱን መስኮት ከፍቶ የጸለየበት ✔ለአባቶቻችን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት /በኢየሩሳሌም ጸንተው በመቆየታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይህንን ታላቅ ጸጋ የተቀበሉበት/ ሰዓት ነው፡፡ ➌. #ጸሎተ_ቀትር በእለቱ እኩሌታ(6 ሰዓት) ላይ የምናገኘው ይህ የጸሎት ጊዜ ነው፡፡ ይህንም ጊዜ የምናስበው፦ ✔ሰይጣን አዳምን ያሳተበት ✔በዕፀ በለስ ምክንያት ለስሕተት የተዳረገውን አዳምን ለማዳን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ የዋለበት ✔የቀን እኩሌታ በመሆኑ የፀሐይ ሙቀት የሚያይልበት የሰው ልጅ ለድካም የሚዳረግበት በዚህም ምክንያት አጋንንት የሚበረታቱበት ጊዜ ነው። ✔ስለዚህ የአዳምን ስሕተት፣ የዳግማዊ አዳም የኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀልና መሞት፣ እያሰብን የቀን እኩሌታ በመሆኑ መዳከማችንን ተገን አድርጎ አጋንንት እንዳይሰለጥንብን እየለመንን እንጸልያለን፡፡ ➍. #ጸሎተ_ተሰዓተ ዘጠኝ ሰዓት ላይ አራተኛውን ጸሎት እናደርሳለን። በዚህ ጊዜ የምናስበው፦ ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ነጻ ለማውጣት በፈቃዱ ቅዱስ ሥጋውን ከቅድስት ነፍሱ የለየበት ሰዓት ነው። ✔ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን በጎም ሆነ ክፉ ተግባር ወደ ፈጣሪ የሚያሳርጉበት ነው፡፡ ✔ቆርኖሌዎስ የተባለ መቶ አለቃ በጸሎት ጸንቶ ደጅ ሲጠና ከሰነበተ በኋላ ከፈጣሪው ምላሽ ያገኘበት ሰዓት ነው፡፡(ሐዋ 10÷9) ✔በዚህ ጊዜ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ እና ሞት አያሰብን ቅዱሳት መላእክት ከፈጣሪያቸው እንዲያስታርቁን እየለመንን የቆርኖሌዎስ እድል እንዲገጥመን እየተማጸንን እንጸልያለን፡፡ ➎. #ጸሎተ_ሰርክ አምስተኛው የጸሎት ጊዜ(11 ሰዓት) የሠርክ ጸሎት ነው፡፡ ✔ስለዚህ የጸሎት ሰዓት ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል፡፡ "ጸሎቴን እንደ ዕጣን በፊትህ ተቀበልልኝ እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን" (መዝ 140÷2) ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ወደ መቃብር የወረደበት ሰዓት ነው፡፡(ማቴ. 27÷57) ➏. #ጸሎተ_ንዋም ይህ የመኝታ ጊዜ ጸሎት ዕለቱን በሰላም ስላሳለፈን ለሌሊቱ ዕረፍት የምንዘጋጅበት ነው፡፡ እኛ ተኝተን የሚሆነውን አናውቅም እርሱ ግን የማያንቀላፋ እረኛ ስለሆነ ይጠብቀናል። ስለዚህ ከመተኛታችን በፊት ሊሌሊቱን እንዲባርክልን እንጸልያለን። በዚህ ጊዜም የምናስበው፦ ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በጌቴሴማኒ ጸሎት አስተምሯቸዋል፡፡ ✔ቀኑ አልፎ በሌሊቱ ይተካል ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለጸሎት ማስተማሩን እያሰብን እንጸልያለን፡፡ ✔ሰላም አሳድረንም ብለን ለፈጣሪ ራሳችንን በእምነት አደራ እናስረክባለን፡፡ ➐. #ጸሎተ_መንፈቀ_ሌሊት ይህ እኩለ ሌሊት እንደ ቀናቱ የጸሎት ሰዓታት የተለያዩ ትርጉሞች አሉት። ቅዱሰ ዳዊት ‘’መንፈቀ ሌሊት እትነሣእ ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ” “ስለ ጽድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት አመሰግነህ ዘንድ እነሳለሁ”/መዝ 118-62/ በማለት ይህ ሰዓት ከእግዚአብሔር ጋራ የሚነጋገርበት እንደሆነ ገልጿል፡፡ ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ዋሻ የተወለደበት ሰዓት ነው። ✔ሞትን ድል አድርጎ በታላቅ ኃይልም የተነሳው በሌሊት ነው። ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ለፍርድ ሚመጣበትም ሰዓት ነው። ከዚህ የተነሳ ለእኛ ሲል ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን በማሰብ ሞትን ድል እንደነሳልንም አስበን በማመስገን ዳግመኛ ለፍርድ ሲመጣ በቀኙ ከሚያቆማቸው ወገን እንዲያደርገን እየለመንን በዚህ ሰዓት እንጸልያለን፡፡ ☞✞ሰባቱን የጸሎት ጊዜያት ጠብቀን መጸለይ ካልተቻለንስ? በሰባቱ የጸሎ ሰዓታት የታቻለንን ያህል እንድንጸልይ ታዘናል፡፡ እነዚህን የጸሎት ሰዓታት በገዳም ያሉ መነኮሳት በየበረሃው የሚዞሩ ባሕታውያን ይጠብቋቸዋል፡፡ ይጸልዩባቸዋልም፡፡ በከተማ በሥራ ምክንያት ሩጫ በዝቶበት በሁሉም ሰዓት መጸለይ የማይችል ክርስቲያን ግን ቢያንስ በማለዳ ከእንቅልፉ ሲነሳ እና ማታ ወደ መኝታው ሲያመራ መጸለይ ይገባዋል። ጠዋት እና ማታ በመጸለይ ከፈጣሪ ጋራ ያለው የአባትና ልጅ ግንኙነት እንዳይቋረጥ ማድረግ ይገባዋል፡፡ ☞✞ ምን ዓይነት ጸሎት እንጸልይ? በመደበኛነት ልንጸልያቸው የሚገቡ ጸሎታት /በቤተክርስቲያናችን አባቶች በገዳማቱ በአድባራቱ የሚዘወተሩ እለታዊ ጸሎታት/ እነኚህ ናቸው፡፡ ፩. #መዝሙረ_ዳዊት መዝሙረ ዳዊት በገዳማት ከሚኖሩ አበው መነኮሳት ባህታውያን ጀምሮ በካህናት፣ ምእመናን በሁሉም ዘንድ በየእለቱ የሚጸለይ ጸሎት ነው። አባቶች ከፊደል ቆጠራው ቀጥሎ ዳዊቱን ያጠኑና ከዚህ ጊዜ ጀምረው እየደገሙት፣ እየጸለዩበት ይኖራሉ። ዳዊት ሳይደግሙ ወደ ዕለታዊ ተግባራቸው አይሰማሩም። መዝሙረ ዳዊት እንደሌሎች ጸሎታት ሁሉ በየዕለቱ ተለይቶ የሚጸለይ አለው። ቀጥለን እንመልከት፦ ሰኞ (ከ1–30)፣ ማክሰኞ (ከ31–60)፣ ረቡዕ(ከ61–80)፣ ሐሙስ (ከ81– 110)፣ አርብ (ከ111–130)፣ ቅዳሜ (ከ131–150)፣ እሁድ (ጸሎተ ነቢያት እና መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን) ይጸለያል፡፡

#የስርዓተ_ቅዳሴ_ተሰጥኦ_መቀበያ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌾✞ #ሱባዔ_ምንድን_ነው? ✞🌾 🌾 #ሱባኤ በሰዋሰው ትርጉሙ "ሰባት"ማለት ሲሆን በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከ ዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ ጋር እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፦ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ፥ ለጸሎት የሚተጉ ምዕመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ [ዘፍ ፪፥፪፣ መዝ ፻፲፰፥፻፷፬] አንድ ሰው 7 ቀናት ቢጾም "አንድ ሱባኤ ጾመ" ይባላል ፡፡ 🌾 #ሱባኤ_መቼ_ተጀመረ ? የተጀመረው ከውድቀት በኃላ በመጀመርያው ሰው በአዳም ነው። ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት እንዳስተማሩት የቤተ ክርስቲያናችን መዛግብት ያስረዳሉ በምላሹም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ስጋን ተዋህጄ ከ፭ ቀን ተኩል በኋላ አድንኀለሁ የሚለውን ቃል ኪዳን የሰማው ሱባኤ በመግባቱ ነው፡፡ 🌾 #ሱባዔ_ለምን? የሰው ልጅ ኃጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ በፈፀመው በደል ኅሊናው ይወቅሰዋል ይጸጸታል፡፡ በመጀመርያ ደፍሮ በሰራው ሀጢአት በኋላ ይደነግጣል ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፍጥረት ኅሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኝት ያስባል ይተክዛል፡፡ ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ ዓለም ሲያስጨንቀው ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይኸውም በጥቂት ድካመ ሥጋ ያልተወሰነ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባኤ ነው፡፡ 🌾 #እግዚአብሔርን_ለመማጸን፦ ማንኛውም ሰው ሱባኤ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ ምንም የምንጠይቀው (የምንማፀነው) ነገር ሳይኖር ሱባዔ ብንገባ የምናገኝው መልስ አይኖርም፡፡ ስለዚህ ሱባኤ ከመግባታችን በፊት፦ ሱባዔ የምንገባው ለምንድር ነው? በማለት እራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ #የቅዱሳንን_በረከት_ለመሳተፍ ቅዱሳን አባቶችና እናቶች የተጋደሉትን ተጋድሎ በማዘከር ቃል ኪዳን በተሰጣቸው ገዳማትና አድባራት የሚገባ ሱባኤ የቅዱሳንን በረከት ተካፋይ ያደርጋል፡፡ በጾመ ነቢያት የነቢያትን፤ በጾመ ሐዋርያት የሐዋርያትን፤ በጾመ ፍልሰታ የእመቤታችንን በረከት ለመሳተፋ ሱባኤ መግባት የነበረ ነው፡፡ 🌾 #የሱባኤ_አይነቶች ፩ኛ. #የግል_ሱባኤ(ዝግ ሱባኤ)፦ አንድ ሰው ብቻውን አመቺ ቦታ ማንም ሳያየው በግሉ የጸሎት በአቱን ዘግቶ በሰቂለ ኅሊና ሆኖ ፈጣሪው ብቻ እንዲያየው በኅቡዕ የሚፈፅመው ሱባኤ ነው፡፡ ፪ኛ. #የማህበር_ሱባኤ፦ ካህናት፣ ምዕመናን፣ ወንዶችና ሴቶች፣ ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ በአንድ ሆነው በቤተ ክርስትያንና አመቺ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ተሰብስበው የሚገብት ሱባዔ ነው፡፡ ፫ኛ. #የአዋጅ_ሱባዔ፦ በሀገር ላይ ድንገተኛ አደጋ፤ አባር ቸነፈር ጦርነት ሲነሳ እንዲሁም በማህበረ ምዕመናን ላይ አስጊ የሆነ መቅሰፍት ሲከሰት እግዚአብሔር መዓቱን በምህረት ቁጣውን በትዕግስት እንዲመልስ የሚያዝ የሱባዔ አይነት ነው፡፡ 🌾 #ቅድመ_ዝግጅት ሱባኤ ከመግባታችንም ሆነ ከገባን ጊዜ እንዲሁም ከጨረስን በኋላ ምእመናን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይገባናል። #ሱባኤ_ከመግባት_አስቀድሞ ፩ ኛ.በመጀመርያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ፪ ኛ.ሱባኤ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሃ አባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ፫ኛ.ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ሱባኤ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡ ፬ ኛ.ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡በቤተ ክርስቲያናችን በአብዛኛው ግዜ ሱባኤ የሚገባው በአጽዋማት ወቅት በመሆኑ ይህንን መለየት ነው። ምክንያቱም በጾም ወቅት ብዙ አባቶች ጸሎት የሚይዙበት ስለሆነ ጸሎታችን ከእነርሱ ጋር አብሮ ያርግልናልና ነው፡፡ እዚህ ላይ በማንኛውም ግዜ ሱባኤ አይያዝም ለማለት አይደለም በማንኛውም ግዜ ፈተና ያጋጠመው ሰው ሱባዔ ሊይዝ ይችላል፡፡ 🌾 #በሱባኤ_ግዜ ሀ. በጸሎት ሰአት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ምስራቅ መልሶ መቆም ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰቂለ ህሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡ ለ. በቅደም ተከተል መጸለይ ይገባል በመጀመርያ አአተብ ከሚለው ተጀምሮ አቡነ ዘበሰማያትን ጠቅሶ ጸሎተ ሀይማኖትን መጨረስ፡፡ ሰግዱ እና ስለ መስቀል በሚያነሳው ላይ እየሰገዱና እያማተቡ መጸለይ፣ ስብሐትን መጸለይ በማስቀጠል አቡነ ዘበሰማያትን ከዚያም መዝሙረ ዳዊት በመቀጠል ሰላም ለኪን ቀጥሎ ውዳሴ ማርያም ሌሎችንም ማስከተል ከዚያ 41 ግዜ ኪራላይሶ ይባላል፡፡ ሐ. በሱባዔ ጊዜ ከተሐራሚው የሚጠበቀው ነገር ኃጢአቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ለእያንዳንዱ በደል ማልቀስ ማዘን ይገባዋል፡፡ መ. በመጨረሻም ሱባዔ የገባው ሰው ሱበዔውን ሳይጨርስ ወይም አቋርጦ ከማንኛውም ሰው ጋር ፈፅሞ መገናኘት የለበትም፡፡ 🌾 #ከሱባዔ_በኋላ ላቀረብነው ተማጽኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ "ሱባዔ" የገባ ሰው ሁሉ ራዕይ ላያይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡ ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኝው የኅሊና ሰላም ነው፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባኤ ገብተን ያሰብነውን ካላገኝን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት በመማጸን መጽናት ይኖርብናል፡፡ ጾመ ፍልሰታ (የእመቤታችን ጾም) በመባል የሚታወቀው እና ቤተ ክርስቲያናችን አበይት አጽዋማት ብላ ከደነገገቻቸው ወስጥ አንዱ ነው፡፡ በዚህ ወራት ብዙዎቹ አባቶቻችንና እናቶቻችን በረከተ ስጋ ወነፍስ ያገኙበት የበረከት ጾም ነው እኛም ቢቻለን በሱባኤ ባይቻለን አቅማችን የፈቀደውን እየጾምን በጸሎት አምላካችንን መጠየቅ እንዲሁም እመቤታችን በምልጃዋ ታስበን ዘንድ መማጸን ያስፈልገናል፡፡ 🙏✞ እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን የበረከት የዲያቢሎስ ድል መንሻ የመንግስተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን በሰላም እንዳስጀመረን በሰላም እንዲያስፈፅመን የእርሱ መልካም ፍቃድ ይሁንልን የእመቤታችን አማላጅነቷን በረከተ ጣዕመ ፍቅሯ አይለየን የቅዱሳን የፃድቃን ሰማዕታት ሁሉ በረከታቸው አይለየን። ✞🙏

🌾✞ #ኢየሱስ_ክርስቶስ_አልፋና_ዖሜጋ_ዘላለማዊ_ነው። ✞🌾 ❖ልዑል እግዚአብሔር መዠመሪያና መጨረሻ የሌለው ዘላለማዊ እንደኾነ የሚያስረዱን ሲኾኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል የእግዚአብሔር ልጅ ፍጹም እግዚአብሔር ነውና ዘላለማዊነቱ በቅዱስ መጽሐፍ ላይ እንዲኽ ተገልጧል፡- #ማስረጃ_አንድ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቈጠር መቅደም መቀዳደም ሳይኖርበት ከባሕርይ አባቱ ከአብ ያለ እናት አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ መወለዱንና ይኽነን ቀዳማዊነቱን እና ዘላለማዊነቱን በነቢዩ በዳዊት ዐድሮ ሲያናግር፤ ይኽ ቀዳማዊዉ አምላክ በኋላ ዘመን በቤተልሔም እንደሚወለድ ደግሞ በሚክያስ ዐድሮ እንዲኽ አናግሮለታል፡- ❖ “ከአንተ ጋር ቀድሞ በኀይልኽ ቀን በቅዱሳን ብርሃን ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከኾድ ወለድኹኽ፤ እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘላለም ካህን ነኽ ብሎ፥ እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትም” (መዝ ፻፱፥፫-፬) ❖ “አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትኾኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ዠምሮ ከዘላለም የኾነ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚኾን ይወጣልኛል” (ሚክ ፭፥፪) እንዲል #ማስረጃ_ሁለት እናት ትኾነው ዘንድ የመረጣትን ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዲያበሥርለት የላከው ቅዱስ ገብርኤልም፤ ድንግል ማርያም የምትወልደው ጌታ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት እንደኾነና መንግሥቱም የማያልፍ መነሻ መድረሻ የሌለው እንደኾነ እንዲኽ ሲል መስክሮላታል፡- ❖ “በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም” (ሉቃ ፩፥፴፫፤ ዳን ፯፥፲፬) እንዲል #ማስረጃ_ሦስት ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስም አካል ከህልውና ተገልጦለት፤ ከንጽሐ ሥጋ፣ ከንጽሐ ነፍስ፤ ከንጽሐ ልቡና በመድረስ በወንጌሉ መዠመሪያ ላይ የገለጠው የአካላዊ ቃል የኢየሱስ ክርስቶስን ቀዳማዊነት ሲኾን፤ በመቀጠል በአብ ህልው መኾኑን፤ በሦስተኛ ደረጃ የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት፤ በአራተኛ ደረጃም በመንፈስ ቅዱስ ህልው መኾኑን እንዲኽ በማስረዳት ነበር፡- ❖ “በመዠመሪያው ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፤ ይኽ በመዠመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር… ቃልም ሥጋ ኾነ” (ዮሐ ፩፥፲፬) እንዲል #ማስረጃ_አራት የኢየሱስ ክርስቶስን ቀዳማዊነት የመሰከረው ሌላው ከእናቱ ማሕፀን ዠምሮ በመንፈስ ቅዱስ የተመላው፤ በእናቱ ማሕፀን ኾኖ በደስታ የዘለለው፤ በበረሓ ያደገው፤ የቀዳማዊዉ አምላክ የክርስቶስ መንገድ ጠራጊ የነበረው መጥምቁ ዮሐንስ ሲኾን ርሱ ከተፀነሰ በኋላ በስድስተኛው ወር የተፀነሰው ቀዳማዊዉ አምላክ ወደ ርሱ ሲመጣ አይቶ እጅግ በሚደንቅ አገላለጥ ምስክርነቱን እንዲኽ ሲል ተናግሮታል፡- ❖ “በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ ርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲኽ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፥ ከእኔም በፊት ነበርና ከእኔ ይልቅ የከበረ ኾኗል ብዬ ስለ ርሱ ያልኹት ይኽ ነው” (ዮሐ ፩፱-፴) እንዲል #ማስረጃ_ዐምስት አብርሃምም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ሲኼድ መልከ ጼዴቅን አገኘው፤ ርሱም ከያዘው ኅብስትና ወይን ለአብርሃም ሰጥቶ ባርኮታል፤ አብርሃምም ከያዘው ኹሉ ዐሥራትን ሰጠው (ዘፍ ፲፬፥፲፮-፲፰)፡፡ ይኽ አብርሃምም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሥጋውን ደሙን በኅብስት በወይን የሚሰጥ መኾኑን በማወቁ እጅጉን ተደስቷል፤ ዳግመኛም ቤዛ ይሥሐቅ ሊኾን በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ የወረደውን በግን አይቶ፤ ወደፊት ዓለም በቀዳማዊዉ አምላክ መሥዋዕትነት እንደሚድን ዐውቆ መደሰቱን ሥጋን ተውሕዶ የተገለጠው ቀዳማዊዉ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እንዲኽ ተናግሮ ነበር፡- ❖ “አባታችኊ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ አየም ደስም አለው፤ አይሁድም ገና ኀምሳ ዓመት ያልኾነኽ አብርሃምን አይተኻልን? አሉት፤ ኢየሱስም እውነት እውነት እላችኋለኊ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለኊ” (ዮሐ ፰፥፶፮-፶፯) እንዲል በእጅጉ የሚደንቀው በተዋሕዶ የቃል ገንዘብ ለሥጋ፤ የሥጋ ገንዘብ ለቃል ኾኗልና አብርሃም ሳይወለድ በመለኮቴ አለኊ ሳይል በአንድ አካል በአንድ ባሕርይ በኾነ አገላለጽ “እኔ አለኊ” ብሎ ማስተማሩ የኢየሱስ ክርስቶስን አንድ አካል አንድ ባሕርይ መኾኑን ያሳያል፡፡ #ማስረጃ_ስድስት ዓለም ሳይፈጠር በባሕርዩ ምስጉን የኾነው የአብ የባሕርይ ልጅ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን፤ ምስጋናን ከማንም ያላገኘው የራሱ ገንዘቡ እንደኾነና ይኽም ምስጋናው ዓለም ሳይፈጠር እንደነበር እንዲኽ ሲል አስተምሮናል፡- ❖ “አኹንም አባት ሆይ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስኽ ዘንድ አክብረኝ” (ዮሐ ፲፯፥፭) እንዲል #ማስረጃ_ሰባት ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስም ኢየሱስ ክርስቶስ ቀዳማዊ አምላክ እንደኾነና ኹሉንም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ ፈጣሬ ፍጥረታት እንደኾነና ይልቁኑ “ዘትማልም” (ትላንት) በማለት ቅድመ ዓለም መኖሩን፤ “ወዮም” (ዛሬ) በማለት አኹንም ያለ እንደኾነ፤ “ወክመ ውእቱ እስከ ለዓለም” (እስከ ዘላለም ያው ነው) ማለት ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ዘላለማዊ አምላክ ስለመኾኑ ሲጽፍልን፡- ❖ “ከፍጥረት ኹሉ በፊት በኲር ነው፤ ኹሉ በርሱና ለርሱ ተፈጥሯል ርሱም ከኹሉ በፊት ነው ኹሉም በርሱ ተጋጥሟል” (ቆላ ፩፥፲፭-፲፯) ❖ “ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ዘላለምም ያው ነው” (ዕብ ፲፫፥፰) #ማስረጃ_ስምንት የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት፤ መድኀኒትነት፤ ይልቁኑ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቈጠር የነበረ ምስጋና፤ ገናንነት፣ ኀይል፣ ሥልጣን ገንዘቡ እንደኾነ ሐዋርያው ቅዱስ ይሁዳ በመልእክቱ ላይ እንዲኸ ሲል አስተምሮናል፡፡ ❖ “ብቻውን ለኾነ አምላክና መድኀኒታችን ከዘመን ኹሉ በፊት አኹንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኀይልም ሥልጣንም ይኹን አሜን” (ይሁ ቊ.፳፭) እንዲል #ማስረጃ_ዘጠኝ አስቀድሞ በኢሳይያስ ዐድሮ በምዕ ፵፬፥፮ ላይ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲኽ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም” በማለት ቅድመ ዓለም የነበረና ዓለምን አሳልፎ የሚኖር እንደኾነ የተናገረው አምላክ በኋላ ዘመን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ፴፫ ዓመት ከ፫ ወር በምድር ላይ ተመላልሶ፤ በቀራንዮ ተሰቅሎ ዓለምን አድኖ፤ ሞቶ፣ ተቀብሮ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ የተነሣ ነውና፤ ይኽነኑ ለዮሐንስ እንዲኽ ሲል ነግሮታል፡- ❖ “ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርኊ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ” (ራእ ፩፥፲፯-፲፱) ❖ “አልፋና ዖሜጋ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መዠመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ” እንዲል (ራእ ፳፪፥፲፫)፨ 🙏✝ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የነበርኽ ዛሬም ያለኽ ዓለምን አሳልፈኽ የምትኖር ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እናመሰግንኻለን፨ ✝🙏 ✍ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌾✞ #ጾመ_ፍልሰታ ✞🌾 ✅✞ "ፍልሰታ" የሚለው ቃል "ፈለሰ፣ ተሰደደ፣ ተጓዘ" ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን እመቤታችንም ከጌቴ ሴማኒ ወደ ገነት መፍለሷን በኃላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረችበት መነሳቷን ለማመልከት አስቀድሞ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት "ተንሥእ እግዚኦ ውስተ እረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ"(አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦትም) መዝ ፻፴፩፥፲ በማለት ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የእመቤታችንን ምልጃዋን ትንሣኤዋን አስቀድሞ በትንቢቱ ተናግሮ ነበር። t.me/EOTC2921 ✅✞ የፍልሰታ ጾምም ሁሌ በየአመቱ ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን ይሆናል። በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ጥር ፳፩ ቀን አርፋ በ፷፬ ዓመት እድሜዋ በ፵፱ ዓ/ም አይሁድ ለምቀኝነት አያርፋም ነበርና ቀድሞ ልጅዋን ተነሣ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖረዋል አሁን ደግሞ እሷን ተነሣች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን? "ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ"(ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው) ብለው ተነሱ። ከመካከላቸውም አንድ ታውፋንያ የሚባል ጎበዝ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ የአልጋውን ሸንኮር መያዣ ሲይዝ ቅዱስ ገብርኤል በእሳት ሰይፍ እጆቹን ቆረጣቸው። እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ። ታውፋንያም ወደ ሐዋርያት ዞሮ በድያለሁ ይቅር በሉኝ ብሎ ቢማፀን፤ የምሕረት እናት የሆነች እመቤታችን አይኖቹዋን ገልጣ ቅዱስ ጴጥሮስን እጆቹን መልስለት ብላው እጆቹንም እንደ ነበሩ መልሶለት ተፈውሷል። ✅✞ ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ። ከዚያም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና ቅዱስ ዮሐንስን በደመና ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡፡ ወዲያውኑ የወርቅ ማዕጠንት ለዮሐንስ አምጥተውለት፤ የቅድስት ድንግል የከበረ ሥጋዋን በመዓልትና በሌሊት ዕጠን አሉት፤ ዮሐንስም ይኽነን ክብር በመቀበሉ ደስ ብሎት ሥጋዋን እያጠነ ሰርክ ሲኾን ራጉኤል መልአክ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ መጠጥ እያመጣለት ያን እየተመገበ በገነት ቆይቷል፡፡ ኋላም በጌታ ፈቃድ ከተቀሩት ሐዋርያት ጋር ተገናኘ። ሐዋርያትም የእመቤታችንን ነገር እንደምን እንደኾነ ሲጠይቁት ርሱም በገነት ያየውን ነገር ነገራቸው፤ ሐዋርያትም ይኽነን ታላቅ ምስጢር ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በአረፈች በስምንተኛው ወር ነሐሴ ፩ ሱባኤ ጀመሩ ነሐሴ ፲፬ ቀን በኹለተኛው ሱባኤ ጌታ የእናቱን ሥጋ አምጥቶ ሰጥቷቸው በምኅላና በደስታ በጌቴሴማኒ አሳረፋት። ✅✞ ከዚህም በኃላ በሦስተኛው ቀን ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ በተወደደች ዕለት ነሐሴ ፲፮ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ምድርን ይጠሯት ዘንድ አዘዛቸው እነርሱም ምድርን “ይኤዝዘኪ እግዚእነ ከመ ታውጽኢ ሥጋሃ ለእሙ ቅድስት” (ጌታችን የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ ያዝሻል) አሏት፤ ያን ጊዜ ልጇ “ንዒ ኀቤየ ወላዲትየ ከመ አዕርጊ ውስተ መንግሥተ ሰማያት”(ወደ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ እናቴ ወደኔ ነዪ) አላት፤ በልጇም ሥልጣን የቅድስት ድንግል ማርያም ነፍሷና ሥጋዋ ተዋሐዱ፤ በነሐሴ ፲፮ ዕለትም እመቤታችን ከሞት ተነሣች፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ከሰማይ በታላቅ ግርማ ወረዱ፤ ነቢዩ ዳዊትም "ንግሥቲቱ ወርቀ ዘቦ ግምጃ ደርባ ደራርባ በቀኝኽ ትቆማለች" እያለ ይዘምርላት ነበር፤ አየሩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመላ፤ እጅግ የሚያስደንቅ መዐዛ አካባቢን ዐወደው። በታላቅ ክብርም በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ፤ ጥሪው ከሰዱቃውያን ትውልዱ ሕንዳዊ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ ሰማዩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመልቶ የአምላክ እናት በክብር ስታርግ ተመለከተ፤ ያን ጊዜ ነገሩ ረቆበት ምን ይኾን እያለ ሲል ቅዱሳን መላእክት የእመቤታችን ዕርገት እንደኾነና እጅ እንዲነሣ ነገሩት፡፡ ቅዱስ ቶማስም ትንሣኤዋን ከእርሱ ሰውራ ያደረገች መሥሎት፤ “ከቶ ምን አርጌ ይኾን፤ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ ቀረኊ ዛሬ ደግሞ የርሷን ትንሣኤ ሳላይ ልቅር?” ብሎ ከደመና ተወርውሮ ሊወድቅ ወደደ። http://t.me/EOTC2921 ✅✞ እመቤታችንም “አይዞኽ አትዘን እነሱ ሞቴን አይተዋል እንጂ ዕርገቴን አላዩም። አኹንም እመቤታችን ተነሣች፤ ዐረገች ብለኽ ንገራቸው” ብላ ለቀሩት ሐዋርያት ምልክት የሚሆን ሰበን ወይም መግነዟን ሰጥታው ተለያዩ። እርሱም በደስታ ተመልቶ ሐዋርያት ያሉበት በመኼድ የእመቤታችን ነገር እንደምን ኾነ ብሎ ጠየቃቸው፤ እመቤታችን ሞተች ቀበርናት አሉት፤ “መቼ ሞተች?” አላቸው በጥር አሉት፤ “መቼ ቀበራችኋት?” አላቸው በነሐሴ አሉ፤ ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተዉ ይኽ ነገር እንዴት ይኾናል? አላቸው፤ ቅዱስ ጴጥሮስም ቶማስን ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ አላምን ብለኽ የጌታን ጐን የዳሰሰ እጅኽ ተቃጥሎ ነበር፤ አኹን ደግሞ እኛ ብንነግርኽ አላምን ትላለኽ ብሎ፤ መቆፈሪያ ይዞ ኼዶ ይቆፍር ጀመር፤ እርሱም የያዘውን ይዟልና ጸጥ ብሎ ይሰማቸዋል፤ ቈፍረው ሲያጧት ደነገጡ፤ ቶማስም አይዟችኊ አትደንግጡ እመቤታችን እኮ በመላእክት ምስጋና ወደ ሰማይ አረገች ብሎ ሰበኑን አሳያቸው፤ እነርሱም ለበረከት ሰበኑን ተካፍለውታል፡፡ ዛሬም ሐዋርያዊት የኾነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ይኽነን በማሰብ ዛሬም ቀዳሽ ዲያቆኑ ከመስቀል ሥር ከመፆሩ ጋር የሚይዘው መቀነት መሳይ ጨርቅ የእመቤታችን የሰበኗ ወይም የመግነዝዋ ምሳሌ ነው። ✅✞ ከዚህም በኃላ በዓመቱ ሁሉም ሐዋርያት ተሰባስበው ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በድጋሚ ሱባኤ ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፬ ቢጾሙ ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ነፍሷን ከስጋዋ አዋህዶ ትንሣኤዋንም ዕርገቷንም አሳይቷቸዋል። ክብር ይግባውና ጌታችን በደመና ነጥቆ ወስዶ ሥርዓተ ቊርባንን ፈጽሞላቸው፤ ስለ እናቱ ዕርገት በዓለሙ ኹሉ ዙረው እንዲያስተምሩ አዝዟቸዋል፡፡ እነርሱም ዓለምን ዞረው ወንጌልን ሲያስተምሩ የእመቤታችንን ትንሣኤና ዕርገትም ሰብከዋል አስተምረዋል፡፡ እኛም ከበረከቷ ለመሳተፍ በመላው ዓለም የምንገኝ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆንን ሁሉ ከሕፃን እስከ አዋቂ ድረስ በፍቅርና በዕምነት የምንጾመው የሱባዔ ጾም ነው። ✅✞ እመቤታችን ከእናቷ ማሕፀን ዠምራ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀች አዳማዊ ኀጢአት ያላገኛት፣ ኀጢአት አልባ የኾነች እንዲያውም አዳምና ሔዋን ከእርግማን በፊት ከነበራቸው ንጽሕና የበለጠ ንጽሕናን ገንዘብ ያደረገች ስትኾን ክብር ይግባውና አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽነን ንጹሕ ሥጋዋንና ነፍሷን በመንሣት በተዋሐደው ሥጋ በመስቀል ተሰቅሎ፤ ሦስት መዓልትና ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ፤ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሞትንና ኀጢአትን ድል ነሥቷልና፤ አማናዊት ታቦቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን ተነሥታለች። "በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝ ትቆማለች።"(መዝ ፵፬፥፱)፡፡ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌾✞ #እርሱ_አምላኬ_ነው። 🌾✞ ❖ በአጭር ቁመት፣ በጠባብ ደረት ተወስኖ፣ በጨርቅ ተጠቅልሎ፣ በግርግም ውስጥ በድንግል እቅፍ ውስጥ ብታገኙት፣ እንዳይመስላችሁ፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡ ❖ በዮርዳኖስ መሀል ቆሞ፣ በዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ፣ በገዳመ ቆሮንቶስ ሲራብና ሲጠማ ሲጸልይ ብታዩት፤ እንዳይመስላችሁ እርሱ በእሳት የሚያጠምቀው፤ መናን ከሰማይ፣ ውሃን ከአለት የሚያፈልቀው፣ ጸሎትን የሚቀበለው፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡ ❖ ከተናቀችው ከናዝሬት ከገሊላ ቢመጣ፣ በአህያ ጀርባ ላይ ተጭኖ ኢየሩሳሌም ሲገባ ብታዩ፣ እንዳይመስላችሁ፤ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ፣ በሱራፌል የሚመሰገነው፣ አለምን የፈጠረው፤ እርሱ አምላኬ ነው። ❖ በምድራዊ ንጉስ በጲላጦስ ፊት ቆሞ ሲከሱት፣ በደለኛ ነው ብለው በሀሰት ሲወነጅሉት ብታዩት፤ እንዳይመስላችሁ፤ ስለ እኔ ተገብቶ ነውና፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡ ❖ የእሾህ አክሊል በእራሱ ላይ ደፍቶ፣ ቀይ ልብስ ደርቦ፣ በአይሁድ ፊት እርቃኑን ቆሞ ብታዩት፤ ለእኔ ተገብቶ ነውና፣ የብርሃን አክሊል ያለው፣ የማይተረጎም ልብስ የሚጎናጸፈው፣ እርቃኔን የሸፈነው፤ እርሱ አምላኬ ነው። ❖ መስቀል አሸክመው፣ እንደ በደለኛ ሲገፉት፣ ሲገርፋት፣ ሲጎትቱት፣ በጥፊ ሲያጣፉት፣ በእርግጫ ሲረግጡት፣ በገመድ ሲጎትቱት፣ ምራቅ ሲተፉበት በቡጫ ሲመቱት ብታዩት፤ የእኔን ሀጢያት ተሸክሞ ነውና እንዳይመስላችሁ፤ እርሱ መዳህኒቴ ነው፡፡ ❖ ከፕራይቶርዮን እስከ ቀራንዮ፣ ጎልጎታ ደም እየጎረፈው፣ ወዝ እየነጠበው፣ እልፍ ጊዜ ከመሬት ሲወድቅ ሲነሳ፣ መስቀል ሲጎትት፣ አቅም ሲያጥረው ብታዩት፤ እውነት እላችኃለሁ እርሱ የእኔን በደል ተሸክሞ ነውና፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡ ❖ በቀትር ጊዜ ተፈርዶበት፣ በወንበዴ መሀል በእንጨት መስቀል ተሰቅሎ፣ እጅ እግሩ ተቸንክሮ፣ ከኮረብታው ላይ ብታዩት፤ እንዳይመስላችሁ እኔ ወንበዴው ተላልፌ፣ ቀጥፌ በበላሁት በለስ ነውና፣ ለእኔ ተገብቶ ነው እንጅ፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡ ❖ "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ" እያለ ከመስቀል ላይ ሲጸልይ፣ ሲጮህ ብታዩት፤ እውነት እውነት አላችኃለሁ የእኔን ጩኸት እየጮኸ ነውና፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡ ❖ በዕለተ አርብ ጀንበር ሲያዘቀዝቅ፣ ጎኑን ተወግቶ፣ ደምና ውሃ ሲፈሰው፣ አንገቱን ደፍቶ፣ ስጋውን ለመቃብር፣ ነፍሱ ወደ ሲኦል ሲያወርድ ብታዩት፤ እኔን ከሲኦል ወደ ገነት እየመለሰኝ ነውና፤ እርሱ አምላኬ ነው። ❖ ሲገንዙት፣ በበፍታ ሲሸፍኑት፣ በአዲስ መቃብር ስጋውን ብታዩት፣ ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት፣ በከርሰ መቃብር ቢቆይ፣ እንዳይመስላችሁ ሲኦልን በዝብዞ፣ ገነትን እየከፈተ ነውና፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡ ❖ ዛሬ በዚች ዕለት፣ ንጽሕት ከሆነችው፣ ከልጅ ልጄ ተወልዶ፣ ደሙን አፍስሶ፣ ስጋውን ቆርሶ፣ በደሌን ክሶ፣ ከወደኩበት አንስቶ፣ ጨለማውን ያጠፋልኝ፣ መድኅን አለም ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ሰው እንዳይመስላችሁ፤ እርሱ አምላኬ ነው፡፡ ❖ እውነት እላችኃለሁ፤ እንዳይመስላችሁ እሩቅ ብዕሲ፤ እርሱ አምላኬ ነው!!!፡፡ ❖ ክብርና ምስጋና፣ አምልኮና ውዳሴ፣ ለእርሱ ለአምላካችን፣ ለመድኃኒታችን፣ ለፈጣሪያችን፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ዘወትር ለዘለዓለሙ ይሁንልን አሜን። 📖✞ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✞📖 ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

t.me/EOTC2921 ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ #ክፍል_፫