uk
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Відкрити в Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Показати більше
4 374
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
1. መቃኘት፡- ቃለ እግዚአብሔርን መምራት እንዲያስታውሱትና በአንድ ቃል እንዲዘምሩ ማድረግ፡፡ 2. መቀበል ፡- የተቃኘውን ቃለ እግዚአብሔርን ተቀብሎ በማስተካከል መዘመር ነው፡፡ ትርጉሙ ግን የአይሁድ ጭፍሮች ጌታን ከይሁዳ ተረክበው ፈቃዳቸውን ለመፈጸማቸው ምሳሌ ነው፡፡ 3. መምራት፡-ቃለ እግዚአብሔርን ከመሪው ተቀብሎ ማሰማት ነው፡፡ ይህም፡- ሀ. የአይሁድ ጭፍሮች በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ጌታን ይዘው መጀመሪያ ከሌዊ ካህናቱ ሐና ፊት ለማቅረባቸው ምሳሌ ነው፡፡ ዮሐ. 18፥13 ለ. ከግራ ቀኝ የመሪውን ቃል ማንሳታቸው ጌታን በየተራ ተቀብለው የፈረዱበት የቀያፋ፣ የጲላጦስ የሄሮድስ ምሳሌ ነው፡፡ ሉቃ. 23፥7 ዮሐ. 18፥24 ሐ. በመጨረሻ ቃለ እግዚአብሔርን ተመልሶ በመሪው በእርሱ ማለቁ ነገረ መስቀሉ በሊቀ ካህናቱ ሐና ተፈጽሟልና በዚያ ምሳሌ እንዲሆን ነው፡፡ 1. ዝማሜ ፡- ዘንግ ከመቋሚያው ጋር ግራና ቀኝ መዘመርና ቀና ብሎ መቋሚያውን ከዜማው ጋር አስማምቶ በመሬት ላይ መጣልና መደለቅ ነው፡፡ ምሳሌው ግን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐና ወደ ቀያፋ ከጲላጦስ ወደ ሄሮድስ መመላለሱን በቀራንዮ መስቀሉን ለማመልከት ነው፡፡ደግሞም ‹‹መኑ ኰርዓከ ተነበየ ለነ›› እያሉ በዘንግ እራስ እራሱን ደብድበውታልና ኩርዓተ ርዕሱን ለማስታወስ ነው፡፡ ማቴ. 26፥66-68 2. ቁም /ንዑስ መርግድ/ ፡- በወርኀ ጾም ሽብሸባ /ዝማሜውን በዘንግ ከጨረሱ በጽናጽልና በከበሮ ብቻ በንዑስ ዓመታት ረጋ አድርጎ መዘመር ነው፡፡/ 3. ዐቢይ መርግድ ፡- ቁሙን ዜማ በከበሮው ለቀቅ አድርጎ በልዩ ዜማ የሚዘመር ነው፡፡ይህ ዜማ በከበሮ አመታት በጽናጽሉም አጣጣልና አወራረድ የተለየ መልክ አለው የአካልን ንቅናቄ ጭምር የሚያስከትል ነው፡፡ ይህም አይሁድ በሕጋቸው 40 ሲገርፉት ረጋ ብለው ከጀመሩ በኋላ ግርፋቱን በማክበድ ተሳሳትህ መልስ እያሉ 6666 ጊዜ እንደገረፉት ለማስታወስ ነው፡፡ 4. ጽፋት ሀ. ከአመላለስ /መልስ ወረብ/ ጋር ቃለ እግዚአብሔርን እያፋጠኑ በጽናጽልና በከበሮ መዘመር ነው፡፡ ምሳሌውም ጽፋት ማለት በጥፊ መምታት ማለት ነው፡፡ ጌታ በጥፊ መመታቱን ለማሰብ ነው፡፡ ለ. ወረብ ወይም ለዘብ ባለ አመላለስ የተመረገደውን ቀለም ዐረፍተ ነገር በመጨመር ወይም በመለወጥ መልሶ የተባለውን ዜማ በመሰብሰብ መወረብና በታላቅ ስሜት ተመስጦ በልዩ ከበሮ አመታትና ጭብጨባ መዘመር ነው፡፡ ሐ. ድርብ መርግድ፡- በተለይ በክብረ በዓላት ቀን ወረብ ሲወረብ በርጋታ ተጀምሮ የነበረውን በማድመቅ በዐቢይ መርግድ ላይ የነበረውን አመታትና ሽብሸባ ወይም ዕርግጫ ጠበቅ አድርጎ በመዘመር ማደራረብ ነው፡፡ ምሳሌውም ጌታን ደጋግመው እንደገረፉትና እንደደበደቡት ማስታወስ ነው፡፡ ግራ ቀኝ ሆነው ማስረገጣቸውም አይሁድ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው 340 ጊዜ ረግጠውታል እንደዚያም አድርገውታልና ነው፡፡ከዚህም በላይ በክርስቶስ ስቃይና መከራ ስቅላትና ሞት ጠላት ዲያብሎስ ተረገጠ ለማለት ነው፡፡ 1. ድርብ ጽፋት ፡- በጽናጽሉ አጣጣልና በዜማው ቃና /ጉሮሮው/ ከተራው ጽፋት ባይለይም በከበሮው አመታት ለየት አድርጎ መዘመር ነው፡፡ ምሳሌውም አይሁድ ጌታን ደጋግመው በጥፊ እንደመቱት እንደገፉት ለማስታወስ ነው፡፡ 2. የጭብጨባ ጽፋት ፡- ጽፋት ከተራው ጽፋትና ከድርብ ጽፋት ጋር በጉሮሮው በአጣጣሉ በመጠኑ ዘለግ አድርጎ በጽናጽል ፈንታ እያጨበጨቡ በከበሮው መዘመር ነው፡፡ ምሳሌውም ከላይ በጉሮሮ ዝማሬ በ8ኛና በ9ኛ ተራ ቁጥር ላይ እንደተገለጸው ነው፡፡ ✝ወስብሐት ለእግዚአብሔር✝ ✝ወለወላዲቱ ድንግል✝ ✝ወለመስቀሉ ክቡር✝ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

7⃣ሰባት ቁጥር ምስጢራት7⃣ በመጽሐፍ ቅዱስና በስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ ሰባት ቁጥር ብዙ ምሳሌ እንዳለው ይታወቃል፡፡ በዕብራዊያን ዘንድም ሰባት ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ምሳሌ 24፡16 እግዚአብሔር ከሰኞ እስከ እሑድ ያሉትን ቀናት በሰባት ቁጥሮች ወስኗል:: ሕዝበ እስራኤል ከግብጽ ባርነት ወጥተው በሲና በርሀ ሲጓዙ ይመሩት የነበሩት በ7 ደመና እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ዘዳ 13፡21 ከዚህ ቀጥለንም ለቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ የ7 ቁጥር ምስጢራትን ምሉዕነትን የሚያስረዱ ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን በዝርዝር እንመለከታለን፡፤ 7⃣ ሰባቱ አባቶች 1. ሰማያዊ አባታችን እግዚአብሔር 2. የነፍስ አባት 3. ወላጅ አባት 4. የክርስትና አባት 5. የጡት አባት 6. የቆብ አባት 7. የቀለም አባት 7⃣ ሰባቱ ዲያቆናት 1. ቅዱስ እስጢፋኖስ 2. ቅዱስ ፊልጶስ 3. ቅዱስ ጵሮክሮስ 4. ቅዱስ ጢሞና 5. ቅዱስ ኒቃሮና 6. ቅዱስ ጳርሜና 7. ቅዱስ ኒቆላዎስ 7⃣ ሰባት የጌታ ቃላት /እኔ ነኝ 1. የሕይወት እንጅራ እኔ ነኝ 2. የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ 3. እኔ የበጎች በር ነኝ 4. መልካም እረኛ እኔ ነኝ 5. ትነሣዔና ሕይወት እኔ ነኝ 6. እኔ መንገድና ሕይወት ነኝ 7. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ 7⃣ ሰባቱ ሰማያት 1. ጽርሐ አርያም 2. መንበረ መንግሥት 3. ሰማይ ውዱድ 4. ኢየሩሳሌም ሰማያዊት 5. ኢዮር 6. ራማ 7. ኤረር 7⃣ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት 1. ቅዱስ ሚካኤል 2. ቅዱስ ገብርኤል 3. ቅዱስ ሩፋኤል 4. ቅዱስ ራጉኤል 5. ቅዱስ ዑራኤል 6. ቅዱስ ፋኑኤል 7. ቅዱስ ሳቁኤል 7⃣ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት 1. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን 2. የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን 3. የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን 4. የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን 5. የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን 6. የፊልድልፍልያ ቤተ ክርስቲያን 7. የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን 7⃣ ሰባቱ ተዐምራት ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት 1. ፀሐይ ጨልሟል 2. ጨረቃ ደም ሆነ 3. ከዋክብት ረገፉ 4. ዐለቶች ተሠነጠቁ 5. መቃብራት ተከፈቱ 6. ሙታን ተነሡ 7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ 7⃣ ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት 1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ 2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው 3. ዛሬ ከእኔ ጋራ በገነት ትሆናለህ 4. እነሆ ልጅሸ እናትህ እነሆት 5. ተጠማሁ 6. ተፈጸመ 7. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እስጥሃለሁ 7⃣ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን 1. ምሥጢረ ጥምቀት 2. ምሥጢረ ሜሮን 3. ምሥጢረ ቁርባን 4. ምሥጢረ ክህነት 5. ምሥጢረ ተክሊል 6. ምሥጢረ ንስሐ 7. ምሥጢረ ቀንዲል 7⃣ ሰባቱ ዐበይት አጽዋማት 1. ዐቢይ ጾም 2. የሐዋርያት ጾም 3. የፍልሰታ ጾም 4. ጾመ ነቢያት 5. ጾመ ገሀድ 6. ጾመ ነነዌ 7. ጾመ ድኅነት 7⃣ ሰባቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ነገሮች 1. ትዕቢተኛ ዓይን ምሳ 16፡6-19 2. ሃሰተኛ ምላስ 3. ንፁህን ደም የምታፈስ እጅ 4. ክፉ ሃሳብን የምታፈልቅ ልብ 5. ለክፋት የምትፈጥን እጅ 6. የሐሰት ምስክርነት 7. በወንድሞች መካከል ጠብን የምታፈራ ምላስ 7⃣ ሰባቱ ፀሎት ጊዜያት 1. ነግህ የጠዋት ጸሎት 2. ሠለስት (የ3 ሰዓት ጸሎት) 3. ቀትር (የ6 ሰዓት ጸሎት) 4. ተሰአቱ (የ9 ሰዓት ጸሎት) 5. ሰርክ (የ11 ሰዓት ጸሎት) 6. ነዋም (የምኝታ ጸሎት) 7. መንፈቀ ሌሊት (የሌሊት ጸሎት) ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል? የካህኑን እጅ መሳለም፦ አንዳንድ ሰዎች ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል ይላሉ። ነገርግን ሚስጢሩ ይሄ ነው የካህኑ እጅ እኮ እሳታዊያን የሆኑ መላዕክት መንካት የማይቻላቸውን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ነው። በቅዳሴ ላይ ቅዱስ ሥጋውን መንካት የሚችለው ዋናው ካህን ብቻ ነው ፤ ሁለተኛው ካህን እንኳን መንካት አይችልም። ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ስለሆነም ካህኑ በእጁ ያሳልመናል እኛም የተቀደሰውን የጌታ ስጋና ደም የተዳሰሰበት እጅ እየተሳለምን የቅዳሴው በረከትና የአምላካችን ምህረት በእኛ ላይ እንዲሆን አሜን አሜን እንላለን። ድንቅ መለኮታዊ ሚስጢር ማለት እንዲህ ነው... አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስ ፦ ዲያቆኑ ይህን በሚልበት ጊዜ ንፍቁ ካህን ማሕፈዱን ከጻሕሉ ላይ ያነሳል ፤ ይህም የጌታ መልአክ የመቃብሩን ድንጋይ የማንከባለሉ ምሳሌ ነው። ከዚህ በኋላ ጌታችን በምሴተ ሐሙስ ሕብስቱን እንደያዘው ዋናው ካህንም ሕብስቱን ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ፤ ይህም የጌታ ትንሣኤ ምሳሌ ነው። እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ፦ በእግዚኦታ ላይ ካህኑ ሕብሥቱን ይበልጥ ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ይህም የዕርገቱ ምሳሌ ነው። ከካህኑ ጋር ሆነን 41 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ እንላለን ፤ ይህም አርባው እግዚኦታ አይሁድ ጌታችንን 40 ግዜ እንገርፋለን ብለው እያዛቡ ብዙ ግዜ የመግረፋቸው ምሳሌ ሲሆን በመጨረሻ ካህኑ ብቻውን የሚላት እግዚኦታ ደግሞ የአዳምና የሔዋን የንስሃ ምሳሌ ነው። 12 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ ስንል ደግሞ ስለስምህ ብለህ ይቅር በለን ስንል ነው።“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና!!እንዲሁም 12ግዜ በእንተእግዚትነ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ ስነንል ደግሞ ስለእናትህ ብለን ማረን ማለታችን ሲሆን*ቅድስት ድንግል ማርያም*የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና ነው ወንጌል፦ የመጀመሪያው መልዕክት ሲነበብ ዲያቆኑ ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ ያነባል; ሁለተኛው ዲያቆን ፊቱን ወደ ሰሜን አዙሮ ያነባል; ንፍቅ ካህን ወደ ደቡብ ዙሮ የሐዋርያት ሥራን ሲያነብ ዋናው ካህን ደግሞ ወደ ምሥራቅ ዙሮ ወንጌልን ያነባል ፤ ይህም ግሩም የሆነ ምሳሌ አለው፦ አንድም ወንጌል በአራቱም አቅጣጫ መሰበኩን ለመግለጽ ነው; አንድም ገነትን የሚያጠጡ 4 ወንዞች አሉ; ኤፍራጠስ ጤግሮስ ጊዮን [ዓባይ] እና ፊሶን ናቸው። ገነትን አጠጥተው ለምለም እንደሚያደርጓት ጌታችን የተጠማ ቢኖር የህይወትን ውሃ በነፃ ይጠጣና ይርካ እንዳለው ወንጌሉም እንዲሁ ያለመልማል ሲሉ ነው። ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ ያስተምራል ፤ ባህረ ጥበብ ቤተክርስቲያን እየተናገረች ታስተምራለች ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለች!! ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አያናውጧትም ቤተክርስቲያን አ..ት..ታ..ደ..ስ..ም! ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር) ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን-ይቆየን። ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

#ቅዱስ #ዮሐንስ #አፈ #ወርቅ:- ወዳጄ ሆይ! የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡ አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና #ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡ ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

የጣልያንን ወረራ ለመከላከል በ1928 አዋጅ በታወጀ ጊዜ በወቅቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ጴጥሮሥ ንጉሠነገሥቱን ተከትለው ወደማይጨው ዘመ ቱ። በ1928 ሐምሌ21 ቀን የተባበሩት የአርበኞች ግምባር አዲስ አበባ ላይ የሠፈረውን የጠላት ጦር ለ መዋጋት በአደረገው ቀጠሮ መሠረት አቡነ ጴጥሮሥ በነደጃዝማች አበራ ካሣ ይመራ ከነበረው የሠላሌ ጦር አብረው ወደ አዲስ አበባ ገቡ። ይህ ጦር ግን የሚፈ ለገው ውጤጥ አለመምጣቱን በመገንዘብ ወደ መጣበት ሢያፈገፍግ አቡነ ጴጥሮሥ የአዲስ አበባን ህዝብ ሠብከው በጠላት ላይ ለማሥነሣት በማሠብ ከጦሩ ተለይተው አዲስ አበባ ቀሩ። ብዙም ሣይቆዩ አንድ ቀን ብቻ እንደቆዩ የጦር አለቆች ፊት ቀረቡ። አቡነ ጴጥሮስ ጳጳሰ ዘምስራቅ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ ብፁእነታቸው ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በጠላት የጥይት እሩምታ እስከተገደሉበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሂደት ' ኮርየር ዴላሴራ' (corriere della sera) የተባለው ጋዤጣ ወኪል እና የምስራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋ ጅ የነበረው 'ፖጃሌ' የተባለ ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ. ሰኔ 15 ቀን 1936 ዓም አዲስ አበባ በነበረ ጊዜ ሂደቱን ባየውና በተመለከተው መንገድ እንደሚከተለው ፅፎ ነበር "ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም ፊታቸውም ዘለግ ያለና መልካቸው ጠየም ያለ ዐዋቂነታቸውና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብሰ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ ለፍርድም የተሠየሙት ዳኞች ሦስት ሲሆኑ እነዚህም ጣሊያኖችና የጦር ሹማምንት ናቸው፡፡ የመካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር፡፡ የቀረበባቸውም ወንጀል 'ሕዝብ ቀስቅሰዋል፣ ራስዎም ዐ ምፀዋል፣ ሌሎችንም አንዲያምፁ አድርገዋል' የሚል ነበር፡፡ ዳኛውም 'ካህናቱም ሆኑ የቤተ ከህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቂርሎስም የኢጣሊያንን መንግሥት ገዢነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ አርስዎ ለምን ዐመፁ፣ ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?' ሲል ጠየቃቸው ፡፡ አቡነ ጴጥሮስም የሚከተለውን መለሱ''፡፡ 'አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፣ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ አኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ሐላፊነትም ያለብኝ የቤተ ከርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ከርስቲያኔ አቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣረዬ ብቻ የምናገረውን አናገራለሁ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ' አሉ፡፡ ይሀንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲያይ ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእከት አስተላለፉ፡፡ ''አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው፡ እንጂ በጎ ለመሥራት፣ እውነተኛ ፍርድ ለመስጠት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፡፡ ስለ ውድ ህገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከለ። ነጸነታችሁን ከሚረክስ ሙታቹህ ስማ ችሁ ሲቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ። የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለ ሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን። በፈጣሪየ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን።'' እኒህ ጳጳስ ሐቀኛ ነበሩ። ነገር ግን ለኢጣሊያ ለጋስዮን ታዝዞ የመጣው አስተርጓሚ ዳኞች የሚሉትን ብቻ ከማስተርገ፡ም በቀር ጳጳሱ የሚናገሩትን ሐቀኛ ንግግር አላስተረጎመም፡፡ አኔ እንኳን የሰማሁት በአዲስ አበበ ለሠላሳ ዓመት የኖረው የእቴጌ ሆቴል ሐላፊ የነበረው የግሪክ ዜጋ ማንድራኮስ አጠገቢ ተቀምጦ ስለ ነበር የተናገሩትን ሁሉ ስለ ገለጠልኝ ነው፡፡ እኔ እንደ ሰማሁት ፍርዱን ለመስማት በብዛት የተስበስቡት ጣሊያኖችና ታዝዞ የወጣው የአዲስ አበበ ሕዝብ ሐቀኛ የሆነውን ንግግራቸውን ቢሰማ ኖሮ ልባቸው ይነካ ነበር"። ሆኖም አስተርጓሚው በጳጳሱ ላይ ተጽዕኖ ስላሳደረበቸው እውነተኛ ንግግራቸው ሳይገለጥ ቀረ። ቀጥሎም ብፁእነታቸው በፍርድ ችሎት ላይ እንዳሉ ሕዝቡ ሁሉ ስለ ርሳቸው እያዘነ ሳለ መስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡን ባረኩ። ወዲያው የሞታቸው ፍርድ ሲሰማ ሕዝቡ በኢጣልያ የእጅ ሰላምታ ዓይነት እጁን እንዲያነሣ ታዘዘ። በዚያን ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ የሞታቸው ሰዓት መድረሱን ዐውቀው ስዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ። በዚህ ጊዜ ሁሉ ምንም ፍርሃት አይታይባቸውም ነበር። የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረው ኢጣሊያዊ ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ ታላቅ ፍርሃትም በፈቱ ላይ ይታይ ነበር። ይሙት በቃ የተፈረደባቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በችሎት ፊት ለብዙ ሰዓታት ቆመው ስለዋሉኖ ደከሞአቸው ስለ ነበር ለመቀመጥ ፈልገው ዳኛውን በትሕትናና በፈገግታ ጠየቁት። እንዲ ቀመጡም ፈቀደላቸው፡፡ በመጨረሻም የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኩዋቸው። ብፁዕነታቸው እስከ መቃብር አፋፍ ድረስ የፍርሃትና የድንጋጤ ምልክት ያይደለ ከልብ የሆነ ፍጹም ቆራጥነት ይታይባቸው ነበር፡፡ የሀገራቸው በጠላት መወረር የሕዝበቸው መገደልና መታስር የቤተ ከርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒህ እውነተኛ ጳጳስ ለመገደል ሊወስዱ ጥይት አልፎ ሌላ ስው እንዳይጎዳ ግንብ ይፈለግ ጀመር፡፡ ሩቅ ባለመሔድ ከመካነ ፍትሑ 10 ሜትር ርቆ ግንብ ያለው መግደያ ቦታ ተገኘና ወደዚያ ተወስዱ። ከገዳዮቹም አንዱ 'ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉገ?' ሲል ጠየቃቸው፡፡ 'ይህ የአንተ ሥራ ነው' ሲሉ ብፁዕነታቸው መለሱ'፡፡ ከመግደያውም ቦታ እንደ ደረሱ ወንበር ቀረበላቸውና ፊታቸውን ወደ ግንቡ ጀርባቸውን ወደ ሕዝቡ እድርገው እንዲቀመጡ ሆኑ። ከዚያ በኋላ ስምንት ወታደሮች በስተጀርባቸው ሃያ ርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተጠንቀቅ ቆሙ። ወዲያው አዛዡ 'ተኩስ' በማለት ትእዛዝ ሲስጥ ስምንቱም ተኩስው መቱዋቸው። ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ። መሞታቸውንና አላመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ። ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ። ከዚያም ሌላ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው፡፡ የብፁዕነታቸው አሰክሬን ማንም እንዳይወስደው በአስቸኳይ ከአዲስ አበባ ውጭ ማንም በማያውቀው ቦታ በምሥጢር አንዲቀበር ተደሪገ። በዚያች ሌሊት በአዲስ አበባ ውስጥ በየቤቱ ልቅሶና ዋይታ ሆነ" በተጨማሪም ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ "አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ" ሲል ሙሴ ፓይላክን ጠይቆአቸው እርስቸውም የሚክተለውን ተናግረዋል። "አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ። መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳ ቸውን ተሳለሙት። ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝ ቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከ ኪሳቸው ክተቱት። ወዲያው ወታደሮች በሩምታ ተኩስው ገደሉ ዋቸው። ይህ እንደሆነ አስገድዶ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ። ማታ ከአስገዳዩ ኮለኔል ጋር ተገኖኝተን ስንጫወት 'በዚህ ቄስ መገደል አኮ ሕዝቡ ተደሰቷለ' እለኝ 'እንዴት?' ብለው 'አላየህም ሲያጨበጭብ' አለኝ። እኔም 'ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጤበጭባል' አልኩት። 'እንዴት?' ቢለኝ እጄን እያጨበጨብኩ አሳየሁት። እሱም አሳየኝ። ከዚህ በኋላ " የሆነው ቢሆን እኔ ትልቅ ማስታወሻ አግኝቼአለሁ" ብሎ አቡነ ጴጥሮስ

ዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

☞አንብበው ካልጨረሱት አይጀምሩት! ስለ # አዳምና_ሄዋን_ጥያቄ_ከነ_መልሱ 1/ እግዚአብሔር አዳምን ከፍጥረታት መጨረሻ ለምን ፈጠረው? 2/ እግዚአብሔር ሌሎችን ፍጥረታት አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳምን አቅንቶ ለምን ፈጠረው? 3/ እግዚአብሔር አዳምን ለሚቆም ፣የሚተኛ አድርጎ ለምን ፈጠረው? 4/ እግዚአብሔር ለአዳም ስንት ሀብታትን ሰጠው?ምንምን ናቸው? 5/ እግዚአብሔር ሄዋንን ከአዳም ከጎኑ አጥንት ለምን ፈጠራት ?ከግንባር ወይም ከ እግር ለምን አልፈጠራትም? 6/ በገነት ውስጥ ስንት አይነት ዛፎች ነበሩ? 7/አዳምና ሄዋን የእግዚአብሔርን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ቆዩ? 8/ አዳምና ሄዋንን በእባቢቱ ላይ አድሮ ያሳታቸው ሰይጣን ስም ማን ይባላል? 9/አዳምና ሄዋን ስንት ልጆች ነበራቸው ? 10/ አዳም በተፈጠረ በስንት አመቱ አረፈ? # አዳም ማለት ከመሬት የተፈጠረ ያማረ መልከ መልካም ማለት ሲሆን የተፈጠረው ከአራት ባህርያተ ስጋ ማለትም ከነፋስ፣ከእሳት ፣ከውሀ፣ከመሬት እንድሁም ከሶስቱ ባህርያተ ነፍስ ማለትም ከልብ ፣ከቃል፣ከእስትፋስ የስነ ፍጥረት መካተቻ በሆነች በእለተ አርብ በ3 ስዓተከህቱም ምድር ሚያዝያ 4 ቀን በምድር መካከል በምትገኘው <ኤልዳ> በተባለች ስፍራ የ30 አመት ጎልማሳ ሁኖ በእግዚአብሔር አርአያነት መልክ ተፈጠረ፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 1፣27 ፣ኩፉሌ 5፣6 # መልስ ፡- 1/አዳም ከፍጥረታት መጨረሻ ለምን ተፈጠረ? ☞መጨረሻ የተፈጠረበት ምክንያት እግዚአብሔር አምላካችን "በጎ አምላክ" ስለሆነ በጎ አባት ለልጁ አብሮት ከብት ያረባለታል ፣ጥማጅ ያጠምድለታል፣ የኑሮ ጓደኛ ያመጣለታል አስቀድሞየሚበላው፣የሚጠጣው፣የሚገዛውና የሚነዳውን ፈጥሮለት በመጨረሻም በሁሉ ላይ ሊያሰለጥነው አዳምን ፈጠረው፡፡ 2/ ሌሎችን ፍጥረታት አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳምን ለምን አቅንቶ ፈጠረው? ☞ እሱ ገዥ እናተ ተገዥ ናችሁ ሲል ነወ፣እንድሁም እናተ ፈርሳችሁ በሰብሳላችሁ ትቀራላችሁ እሱ ግን" ትንሳኤ ሙታን " አለው ሲል አቅንቶ ፈጠረው፡፡ 3/ አዳምን የሚቆም የሚተኛ አድርጎ ለምን ፈጠረው? ☞ መቆሙ- ሰማያዊ ፣ ☞መቀመጡ- ምድራዊ ነህ ሲለው ነው፣ ☞የሚተኛ ፣ የሚነሳ አድርጎ መፍጠሩ ደግሞ ☞መተኛቱ ሞቱን ☞መነሳቱ - ትንሳኤውን ሲነግረው ነው፡፡ 4/ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም ስንት ሀብታት ሰጠው?ምን ምን? ☞ሰባት ሀብታትን የሰጠው ሲሆን እነሱም፡- ➊ሀብተ መንግስት (የማስተዳደር ሀብት ➋ሀብተ ክህነት ( የመቀደስ፣የመባረክ፣መስዋዕት የማቅረብ ➌ ሀብተ ትንቢት (የመጣውን የመናገር ➍ሀብተ መዋኢ (የማሸነፍ ➎ሀብተ ሀይል (የጥንካሬ ➏ሀብተ ፈውስ ( የመዳን ፣የመፈወስ ➐ሀብተ ዝምሬ (የመዝሙር 5/ ሄዋን ከአዳም ከጎኑ አጥንት ወስዶ ለምን ተሰራች?ከግንባር ወይም ከእግር ለምን አልሰራትም? ☞ አዳም ለእንሰሳት፣ለሰማይ ወፎች ና ለምድር አራዊቶች ሁሉ ተባእትና እንስት ሁነው ሲመጡ ስም ያወጣላቸው ነበር፡፡ነገር ግን ለአዳም እንደ ራሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር ፡፡ "እግዚአብሔርም " ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረዳት ልፍጥርለት አለ ፡፡ኦዘፍ 2፣18 ከዚያም በአዳም ላይ እንቅልፍ አመጣበትና ፈፅሞ ሳይተኛ ፣ፈፅሞ ሳይነቃ ከጎኑ አጥንት አንስት አንስቶ ያችን ስጋ አልብሶ የ15 አመት ቆንጆ አድርጎ ፈጠራት ፣ኦዘፍ 2፣18 አዳምም ስሟንም "ሄዋን" አላት ፣ሄዋን ማለት "ሀይው" ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም" የህያዋን ሁሉ እናት "ማለት ነው፡፡ ፈፅሞ ሳይተኛ ፣ፈፅሞ ሳይነቃ ሄዋንን መፍጠሩ ☞ፈፅሞ ተኝቶ ቢሆን ኑሮ ምትሀት መስሎት ከየት መጣች ብሎ ይፈራታል ☞ፈፅሞ ነቅቶ ቢሆን ኑሮ ከአካሉ አጥንት ሲነሳለት ያመው ነበርና ይጠላት ነበር ፡፡ ☞ከፍ አድርጎ ከግባር ዝቅ አድርጎ ከእግር ያልሰራት ግባርና እግር በልብስ አይሸፈንም ጎኑ ግን በልብስ ይሸፈናልና ተሰውራ ወይም ተሸፍና መኖር ይገባታል ሲል ነው፡፡ በሌላ በኩል ግንባር የባለቤት እግር፣ የቤተሰብ ምሳሌ ነው ፡ እሷም ከባለቤቷ በስተታች ከቤተሰብ በላይ ሁና ትኑር ሲል ነው ፡፡1ኛ ቆሮ 12፣19-22 እንድህ አድርጎ አዳምና ሄዋንን እስከ 40 ቀን ድረስ በተፈጠሩበት በማዕለ ምድር በቀራንዮ አስናበታቸው ጌታችን አምላካችንና መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የሚሰቀልበት ቦታ ነውና ከዛም በ40ኛው ቀን አዳምን ብርሃን አልብሰው ፣ብርሀን አጎናፅፈው፣የብርሀን ዘውድ አቀናጅተው በብርሃን ሰረገላ አስቀምጠው ወደ ገነት አስገቡት፡፡ ሄዋንንም በ80 ቀኗ እንደ አዳም ባለ ክብር ወደ ገነት አስገቧት ፡፡ኩፉሌ ፈ 4፣12-15 አዳምና ሄዋን ከእግዚአብሔር የባህሪ ደግነት የተነሳ እርሱን ለማመስገንና ክብሩን ለመውረስ ተፈጠሩ፡፡ኩፋሌ 4 ፣3-5 እግዚአብሔር ለአዳም ረዳት የፈጠረለት ስለ ሶስት ነገሮች ሲል ነው፡፡ ➊ዘርን ለማብዛት ➋ ከዝሙት እንድፀዳና ➌ረዳት እንድትሆነው ነው 6/ በገነት ውስጥ 3 አይነት ዛፎች ነበሩ ➊ ዕፀ መብል -እንድበሉት የተፈቀደላቸው ምግብ ነው ➋ዕፀ በለስ-እንዳይበሉ የታዘዙት ነው ➌ዕፀ ህይወት - እንደ <እግዚአብሔር > ፈቃድ የሚመገቡት የዘለዓለም ህይወት የሚሰጥ ምግብ ነው፡፡ ህግን ጠብቀው በገነት ውስጥ 1000 አመት ከኖሩ ብኀላ እፀ ህይወት በልተው ከገነት ወደ ሰማያዊ እየሩሳሌም (መንግስተ ሰማይ ) እንድገቡ ለበለጠ ክብርና ፀጋ ሽልማት እንድሎናቸው ነበር፡፡ነገር ግን ያለ ጊዜው ሳቱ እንጅ 'እፀ በለስ ' እንዳይበሉ የታዘዙበት ህግ አዳም ፈጣሪ እንዳለው ፣ለፈጣሪው ያለውን ፍቅር የሚገልፅበትና ተገዥነቱን የሚያሳይበት ነው፡፡ 7/ አዳምና ሄዋን የእግዚአብሔርን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ቆዩ? ☞አዳምና ሄዋን ይህን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ለ7 አመት ከ 2ወር ከ 17 ቀን ኖሩ፡፡ 8/ አዳምና ሄዋንን በእባብ ላይ አድሮ ያሳታቸው ሰይጣን ስም ማን ይባላል ? ☞አዳም በሳጥናኤል ተተክቶ መቶኛ ሁኖ ከመላእክት ጋር ተቆጥሮ ነበር ሰይጣንም በእባብ አድሮ አሳቻቸው ጽድቃቸውም ተገፈፈ አዳምና ሄዋንን በእባብ ላይ አድሮ ያሳታቸው ሰይጣን ስም ' ጋርድኤል ይባላል፡፡ በመሆኑም አትብሉ የተባሉትን እፀ በለስ ህጉን አፈረሱ ከገነት ተባረሩ ፡ኦዘፍ 3፣1 ኦዘፍ 3 ፣22-24 9/ አዳምና ሄዋን ስንት ልጆች ነበሯቸው? ☞ ከገነት ከተባረሩ ብኀላ በደብረ ቅድስት ይኖሩ ነበር፡ አዳምና ሄዋን በሰሩት ሀጢያት በመፀፀታቸውና በንሰሀ በመመለሳቸው "እግዚአብሔር" መሀሪ ነውና 5 ቀን ተኩል ወይም 5500 ዘመን ሲፈፀም ሰው ሁኖ በመወለድ እንደሚያድናቸው ቃል ኪዳን ገባላቻው ፡፡ኦዘፍ 3፣15-22 አዳም ግን የራሱን ደም በስንደ ለውሶ ሲሰዋ ጌታችን በአንተ ደም አይደለም አለም የሚድነው በእኔ ነው ብሎ ተስፋ ሰጠው፡፡ አዳምና ሄዋንም በምድር ላይ ዘርን ተክተዋል ገብርኤል ፣ሚካኤል ፣ሩፋኤል ወርቅ ,እጣን,ከርቤ አምጥተው ለአዳም ሲሰጡት ወርቁን ማጫ ይሁንሽ ብሎ ሰጣት ከዛም አዳምና ሄዋን በ 30 ሩካቤ 60 ልጆችን ወልደዋል 10/ አዳም በተፈጠረ በስንት አመቱ አረፈ? ☞ አዳም በተፈጠረ በ930 አመቱ አረፋ ፡አዳም ለሄዋን የሰጣት ወርቅ ለሴት ሰጠችው ሴትም ለኖህ አስተላለፈው እጣኑንም ኖህ አፅመ አዳም እያጠነ ድኖበታል ፡፡ በአዳም ስም በሀገራችን የተሰሩ ቤተክርስቲያኖች ብዛታቸው 5 ናቸው በአዳም ስም የተቀረፀው ታቦት ከሶሪያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያመጣው ፃድቅ አባት 'መልከአ እግዚአብሔር ' ይባላል፡፡ እንድከበር ያደረገው ቅዱስና ሊቁ ያሬድ ማህሌት ነው፡፡ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስር

ክርስቶስን መውደድ እንዴት? (በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) አንድ በጣም የምንወደው እንግዳ ወደ ቤታችን ሲመጣ እጅግ በጣም ከመደሰታችን የተነሣ የምናደርግለት ኹላ ሊጠፋብን ይችላል፡፡ እንደምንወደው፣ እንደናፈቀን እንነግሯለን፡፡ ከዚያም በላይ የሚወደውን እናቀርብለታለን፡፡ ባይኖረን እንኳን ስላላቀረብንለት እናዝናለን፡፡ ያለንን፣ ቤት ያፈራውን ግን እናቀርብለታለን፡፡ ስለምንወደውና ስለናፈቀን ርሱን የሚያስከፋ ነገር ምንም አናደርግም፡፡ ብናደርግም ወዳጃችንን ኾን ብለን ለማስከፋት ብለን የምናደርገው አይደለም፡፡ እንወዷለን የምንለው እንግዳችንን ትተን ሌላ ሥራ አንሠራም፡፡ በቃላት ብቻ እወድኻለኁ ብንለው፥ ነገር ግን በተግባር እንግዳችንን መውደዳችን ባንገልጥ ግን እንግዳችን ያዝንብናል፡፡ ከቃላችን በላይ ተግባራችንን ስለሚያይም እንደምንወደው ብንነግረውም አያምነንም፡፡ መውደድ የቃላት ጨዋታ ሳይኾን በተግባር የሚገለጥ ነውና፡፡ ልክ እንደዚኹ ፍጹም ሰው ኾኖ፣ ባሕሪያችንን ባሕርይ አድርጐ ወደ እኛ የመጣውን ክርስቶስን እንደምንወደው እየተናገርን፥ ነገር ግን በተግባር የምናሳዝነው ከኾነ መውደዳችን ትክክለኛ መውደድ አይደለም፡፡ ብንወደው ኖሮ ልክ ከላይ እንደገለጥነው እንግዳችን የሚበላ ነገርን እናቀርብለታለን፡፡ የክርስቶስ መብሉስ ምንድነው? እርሱ እራሱ እንዲኽ ሲል ነግሮናል፡- “የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው” /ዮሐ.4፡34/፡፡ ተርቦ ስናየው የሚበላ ነገርን እንስጠው፤ ተጠምቶ ስናየው የሚጠጣ ነገርን እንስጠው፤ ርሱም ይቀበለናል፡፡ የሚቀበልንም ስለሚወደን ነው፤ ከማንወደው ሰው ስጦታን አንቀበልምና፡፡ ስጦታችን ትንሽ ሊኾን ይችላል፤ ነገር ግን አፍቃሪያችን ነውና ስለ ስጦታችን ታናሽነት አልቀበላችኁም አይለንም፡፡ ስጦታችን በርሱ ዘንድ ትልቅ ነው፡፡ በስንፍና አንያዝ እንጂ ስጦታችን አምስት ሳንቲምም ልትኾን ትችላለች፤ ርሱ ግን ወዳጃችን ነውና አምስት ሳንቲም ናት ብሎ ስጦታችንን አያቃልላትም፡፡ እንደ ድልብ ስጦታ አድርጎ አምስት ሳንቲሟንም ይቀበልልናል እንጂ፡፡ ስጦታችንን የሚቀበለው ድኻ ስለኾነ አይደለም፡፡ ስጦታችንን የሚቀበልልን ስለ ስጦታችን ታላቅነት ሳይኾን ስለ ልቡናችን ኀልዮት (intention) ነው፡፡ ስለዚኽ ስንሰጥ ክርስቶስ ስለተቀበለን ትንሽዋንም ስጦታችንን ይቀበል ዘንድ በቤታችን ታዛ ስለገባ ልናመሰግነው ይገባል፡፡ እውነተኛ ሐሴት ማለትም ይኸው ነው፤ በመቀበል ሳይኾን በመስጠት የምናገኘው፡፡ ወደ ቤታችን፣ ወደ ሕይወታችን የመጣው ለእኛ ሲል ነው፡፡ ነፍሱን አሳልፎ ለሞት የሰጠው ለእኛ ሲል ነው፡፡ ፍቅሩ ግን እዚኽ ላይ አላበቃም፡፡ አኹንም እኛ ጋር እየመጣ ነው፡፡ ሐዋርያው “ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን” ብሏል /2ኛ ቆሮ.5፡20/፡፡ ስለዚህ ተርበውና ተጠምተው ወደ እኛ የሚመጡት ሰዎች የክርስቶስ መልእክተኞች ናቸው ማለት ነው፡፡ የንጉሡን መልእክተኛ፡የሚያባርር ታድያ ማን ሞኝ ነው? ነገር ግን ብዙዎቻችን ሞኞች ኾነናል፡፡ የነገሥታት ንጉሥ የክርስቶስ መልእክተኞችን እያባረርናቸው ነውና፡፡ ክርስቶስን እንወድኻለን እያልን በተግባር ግን እናባርረዋለን፡፡ ከዚኽ የበለጠ ምስኪንነት ከወዴት ይገኛል? ክርስቶስን በቃል እወድኻለኁ እያሉ በተግባር ግን ርሱን ማባረር የማይጠቅም ብቻ ሳይኾን የሚጐዳን ጭምር ነው፡፡ እንኪያስ ተወዳጆች ሆይ! ክርስቶስን በቃልም ገቢርም እንውደደው፡፡ በታላቁ እንግዳችን በክርስቶስ ደስ መሰኛታችንን በተግባር እንግለጠው፡፡ ይኽን እንድናደርግ ርስቱንና መንግሥቱንም እንደ ቸርነቱ እንዲያወርሰን እኛን በመውደዱ ወደ እኛ የመጣው ደግሞም የሚመጣው ክርስቶስ ይርዳን አሜን!!! ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✝ አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል በመከራ ውስጥ ይመጣል ። አንድ ሰው መፍትሔ የሌለው የሚመስል መከራ ሊገጥመው ይችላል ። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ መከራው የገጠመው ጥቂት ኃጢአቶችን ስለ ፈጸመ መሆኑን ከማስጠንቀቂያ ጋር ይነግረዋል ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቃሉ ንስሓ ከገባህ መከራው ፍጻሜ ያገኛል እያለ ውስጡን ሲመክረው ይሰማል ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ንስሓው ሲል ለሰውየው ይራራለታል ። የእግዚአብሔር ድምፅ አንድ ሰው ሲ ታመም ወይም እርሱ የሚወደው ሌላ ሰው ሲታመም ሊመጣ ይችላል ። በዚህ ጊዜ እንዲጸልይ ወይም ስእለት እንዲሳል የሚመክረውን ድምፅ ከውስጡ ይሰማል ይህ ድምፅ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው ። የዮሴፍ ወድሞች እህል ሊገዙ ወደ ግብጽ ከወረዱ በኋላ በዚያ ችግር ሲገጥማቸው እርስ በእርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋግረው ነበር ፦ " በእውነት ወድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውና ። ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን ።"/ ዘፍ 42*21/ ። ከዚህ በኋላ ለዮሴፍ እንዲህ ብለውታል ፦ " ለጌታዬ ምን እንመልሳለን ? ምንስ እንናገራለን ? ወይስ በምን እንነጻለን ? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ ..."/ዘፍ 44*16/ ኃጢአታቸውን እንዲያስታውሱ ኀላም እንዲገሰጹ ያደረጋቸው የእግዚአብሔር ድምፅ ነው ። ነቢዩ ዳዊት የጌራ ልጅ በሆነው በሳሚ ሲሰደብ የእግዚአብሔር ድምፅ ውስጡን ስላለፈ ኃጢአቱ እየወቀሰው መሆኑን አዳምጧል ። ስለሆነም በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች " "እግዚአብሔር ዳዊትን ስደበው ብሎታልና ይርገመኝ ። / 2ኛ ሳሙ 16*10/ በማለት በግልጽ ተናግሯል ። ረሀብና የመሬት መንቀጥቀጥ በዓለም ሲደርስ የእግዚአብሔር ድምፅ በመላው ዓለም ውስጥ ይሰማል ። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ የሚናገረን " ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ ።" / ሚል 3*7/ እያለ ነው ። ይህ ድምፅ በረሀቡ ወይም በመሬት መንቀጥቀጡ ጉዳት ለደረሰባቸው ሀገሮች የሚሆን የእርዳታ ጥሪ ለማሰማት ወይም ሌሎቹ ከእነርሱ ትምህርት በመውሰድ ንስሓ እንዲገቡ ለማድረግ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኝት ዝግጅት እንዲያደርጉ ነው ። ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት መከራ ውስጥ ስትገቡ ከውስጣችሁ ያለውን የእግዚአብሔር ድምፅ አድምጡት እርሱ ለእናንተ ሊነግራችሁ የሚወደው ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁና ። ብጹዕነታቸው አቡነ ሺኖዳ ፫ኛ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

@EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ከክርስቶስ ልደት በኋላ ፡ በአንደኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በንግሥት ህንደኬ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የገባው የጥምቀት ዜና በአራት ኛው ክፍለ ዘመን በኦብርሃና አጽብሐ ዘመነ መንግሥት በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ስብከት ተስፋፍቶ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስብከተ ወንጌልን አምኖ ጥምቀትንና ክርስትናን ተቀበለ፡፡ እጅግ በጣም ጥቂት የሆኑ የአይሁድ (ጁዳይዝም) ሃይማኖት አማኞች በወንጌል አናምንም ክርስቲያን አንሆንም ፣ ሕገ ኦሪትን አንለቅም በማለት በ፱፻፹፪ (982) ዓ. ዓለም ግደማ በቀዳማዊ ምኒልክ ዘመን የመጣውን እምነተ እሥራኤል መከተልን ቀጠሉ፡፡ የክርስትና ሃይማኖት አንቀበልም ብለው በአይሁድ (የኦሪት) እምነታቸው የፀኑት ሕዝቦች በነገሥታቱ ትእዛዝ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ከሆነችው ከአክሱምና ከዙሪያዋ አየለቀቁ በመውጣት በወልቃይት፣ በሰሜንና ፥ በወገራ ፣ በደምቢያ ፥ ዛአገው ፥ በላስታ ፥ በሰቆጣና በመሳሰሉት ሊኖሩ እንደሚችሉ ስለ ተገለጸላቸው አክሱምንና አካባቢዋን እየለቀቁ በመሔድ ተበታትነው ይኖሩ ጀመረ ። በዚህ ምክንያት ፈላሻ ተባሉ ፡፡ ፈላሻዎች እምነታቸው ሕገ ኦሪት ቢሆንም ኢትዮጵያዊነታቸው የተረጋገጠ ስለሆነ ፥ በመንግሥት ትእዛዝ በተፈቀደላቸውና በሚኖሩባቸው በሰሜንና በላስታ እንዲሁም በተለያዩ ሥፍራዎች ለረዥም ጊዜ በመኖር ቁጥራቸው እየበዛ ሔደ ፡፡ የሕዝቡ ቁጥር አየበዛ ሲሄድም ለአክሱም መንግሥት ግብር እየክፈለ በሰላም ይኖር ጀመር፡፡ ዮዲት ጉዲት በዘጠነኛው ምዕተ ዓመት ፰፻፶፪ (852) ዓ.ም ገደማ ዮዲት የተባለችው የጌዴዎን ልጅ ንግሥት ዘሯ ከፈላሻ ውስጥ በመሆኑ ፈላሾችን ይዛ ተነሣች። በላስታ የሚኖር የክርስትያን ሃይማኖት ተከታይና የቡግና ባላባት በዮዲት ውበትና ኃይለኛነት ስለተማረከ ሃያማኖቱን ለውጦ አገባት። በዚህም ምክንያት ተጨማሪ ኃይል ለማግኘት ቻለች ፡፡ በዚህ ዘመን በአክሱም ዙፋን ላይ የተቀመጠው የንጉሥ ድግናዣን ልጅ አንበሳ ውድም ነበር ። አንበሳ ውድም አባቱ ሲሞት ገና የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ቢሆንም የንግሥና ሥልጣኑን ያዘ፡፡ ዮዲትም ንጉሡ ገና ሕፃን ስለሆነ የሧን ጥቃት የሚቋቋም ኃይል ሊያሰባስብ እንደማይችል በመገመት አጋጣሚውን ተጠቅማ ልትወጋው አሰበች ፡፡ በዚያን ጊዜ አክሱም የእስልምናን ሃይማኖት ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት የተነሣ ጠረፎቿ በመወረራቸው በቀይ ባሕር የነበራትን የበላይነት ያጣችበት ወቅት ነበር ፡፡ ይህች የክርስቲያን ባላጋራ የሆነች ንግሥት ፈላሾች የሆኑትን ሁሉ በአንድነት አስባስባና አሥተባብራ የአክሱም ንጉሥ አንበሳ ውድምን ለመውጋት ተነሣች ፡፡ ከላስታ ፣ ስሜንና ወልቃይት የተሰበሰቡትን ፈላሾችና ሌሎችም ቀሥቅሣና አስፈራርታ በማሥነሣት ብዙ ሠራዊት እየመራች ወደ አክሱም ዘመተች ፡፡ ወደ አክሱም በምትጓዝበት ጊዜ ያለፈችበትን ሥፍራ ሁሉ ሠራዊቷ ይመዘብርና ያጠፋ ነበር ። አብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናትና ሌሎችም ውድ የሆኑ የባህል ቅርሶች የተቃጠሉትና የወደሙት በዮዲት ጭካኔ የተሞላበት ወረራ ነበር ፡፡ ብዙ ጊዜ አምረውና ደምቀው ግርማ ሞገስ የነበራቸው አብያተ ክርስትያናትና ሐውልቶች፡ ጭራሽ ከወደሙት ሌላ ለታሪክ ምሥክርነት በእሳት ጋይተው ፍርስራሻቸው ብቻ የሚታየው ብዙ ናቸው፡፡ በዮዲት ጉዲት ወድሞ በሇላ በንግስት እሌኒ ታድሶ የነ በረው የአብረሃ ወ ዓጽብሃ ቤተክርስትያን፣ መርጡለ ማ ርያም፣ ጎጃም ብዙ ክርስትያኖች ሲጨፈጨፉና የቀሩትንም በታላቅ አደጋና ሥጋት ተውጠው የመከራ ዘመናት አሳልፈዋል፡፡ የዮዲት ፍላጉት የክርስትና ሃያማኖትንን አጥፍታ የአይሁድን እምነት ለማስፈን ነበር፡፡ ይህን በስፋት ይካሄድ የነበረውን ጭፍጨፋ ለመቋቋም የተሳናቸውና በሥጋት ላያ ወድቀው የነበሩት የአክሱም መሳፍንትና መኳንንት ፋታና ጊዜ አግኝተው መልሰው ለማጥቃት እስኪችሉ ድረስ ሕፃኑን ንጉስ ይዘው ሸዋ ውስጥ ወደሚገኘው ወደ መንዝ ሸሹ ፡፡ መንዝ የተመረጠበትም ዋናው ምክንያት የመልክዓ ምድሩ አቀማመጥ ገደላማና ዋሻ በመሆኑ ጠላት ስለማይደፍረው ፥ ገፍቶም ቢመጣ ለመከላከል አመቺ በመመሆኑ ነበር ፡፡ ዮዲት የክርስትናን ሃይማኖት አጥፍታ የፈላሻን ሃይማኖት በሰፊው እንዲሰበክና እንዲስፋፋ ስለፈለገች በአክሱም ሕዝቦች የተገነባውንና ሁለት ሺህ ዓመታት ያህል አብቦ የቆየውን ሥልጣኔና የሥልጣኔ ውጤት የሆኑትን ታሪካውያን ሥራዎች ማፈራረሷን ተያያዘችው ፡፡ አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠልና ካህናትን መግደል የዕለት ሥራዋ ሆነ፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከተረፉትና እስካሁን ድረስ ካሉት ጥቂቶች በስተቀር ሐውልቶችን ውብ የሆኑ የሥነ ጥበብ ቅርሶችንሞ አፈራርሳለች፤ አብያተ ክርስትያናትን አቃጥላለች ። የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ተራው ሕዝብና ቄሶች ተሰየፉ ። የመንግሥት ዘርነት የነበራቸው የመሳፍንት ልጆችም መንግሥቱን አንዳይቀናቀኑና አንዳይሸፍቱ ሕዝቡንም እንዳያነሣሡ ተብሎ ወደ ደብረ ዳሞ ተራራ አየተወሰዱ በእስር እንዲቀመጡ ይደረግ ነበር ። በቆየው ሥርዓት በዚህ ገዳም ውስጥ የመሳፍንት ልጆች በቁም አስረኛነት አየተጠበቁ ይቆዩና ንጉሡ ሲሞት ከመሳፍንቱ ውስጥ ሕዝቡ የመረጠው ይነግሥ ነበር ፡፡ በዚሁ ምክንያት የተሰበሰቡበትን ፬፻ (400) የሚሆኑ የመሳፍንት ልጆች በጅምላ አሳረደቻቸው። ዮዲት በፈጸመችው ጭካኔ ሥራና ከፍተኛ ጥረት የተነሣ ተግባሯንና ክፋትዋን የሚገልጹ የተለያዩ ቅጥያ ስሞች ተስጥቷታል። በትግራይ ሕዝብ ጉዲት (ጉደኛ) በአፋር ሕዝብ ጋፅዋ (አስፈሪ አውሬ) በመባል ስትታወቅ በአማራ ሕዝብም እሳቶ (የምታቃጥል) ብለዋታል፡፡ ጉዲት ሕፃኑን ንጉሥ አንበሳ ውድምን በመንዝ የመደበቁን ዜና በሰማች ጊዜ ኃይሉን ሰብሮ እሱን ማርኮ እንዲያመጣ ጦር ልካ ነበር ነገር ግን የላከችው ሠራዊት በመሸነፉ ሐሳቧ ሳይሰምር ቀረ ፡፡ ስለዚህ አንበሳ ውድምንና ተከታዮቹን አጥፍታ እርካታ ለማግኘት በማሰብ ራሷ ሠራዊቷን እየመራች ወደ መንዝ ዘመተች። አንበሳ ውድምና ተከታዮቹ ግን ለማጥቃት ይበልጥ አስቸጋሪ ወደ ሆነውና እዚያው ሸዋ ውስጥ ወደሚገኘው ወደ መርሐቤቴ ሸሹ። ዮዲትም በዚሁ ሳትገታ ልትከታተለው ሞክራ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከመሬቱ አቀማመጥ አስቸጋሪነት ሌላ የንጉሡ ወታደሮች የመንዝና የመርሐቤቴ ሕዝብ በየጊዜው ያደርሱባት የነበረው ጥቃት አንድ ላይ ተዳምረው ስሳደክሚት ዓላማዋ ሳይሳካላት ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ እንደገና እንድትመለስ ተገደደች ፡፡ ከዚህ በሇላ ለ፲፫ (13) ዓመታት ስትገዛ ቆየች ፡፡ ይህች ጨካኝ ንግሥት አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ቅርሶች ያጠፋችበትን የ፵ (40) ዓመታት ዕድሜ ገዝታ ማክተሚያ ላይ የእብርሃ ወአጽብሐን ቤተክርስቲያን አቃጥላ በምትመለስበት ጊዜ እግዚአብሔር መንገዷን አሳስቶ አዲንፋስ ከሚባለው ቦታ ከፍተኛና አስፈሪ አውሎ ነፋስ አስነሥቶ ወርውሮ አደካውህ ከሚባለው ቦታ ላይ አንደ ጣላትና በዚሁ ምክንያት አንደ ሞተች ብዙ ሊቃውንት ይናገራሉ። መቃብሯም ከውቅሮ ከተማ በታች በሚገኘው አደካውህ አጠገብ የድንጋይ ምልክት ተቀምጦበት ይገኛል ፡፡ በ ዮዲት ጉዲት ከፊሉ ተቃጥሎ የነበረው የአብርሃ ወአፅብሃ ቤተክርስት ያን፣ ትግራይ ምንጭ:- 1. "የኢትዮጵያ ሥልጣኔ" ፣ በላይ ግደይ፣ መጋቢት ፲፱፻፹፫ 2. "ቅዱሳን መካናት በኢትዮጵያ"፣ ዘመድኩን በቀለ፣ የካቲት ፩፱፱፪ 3. "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ታ ሪክ"፣ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ሴኔ ፲፱፻፸፬ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮

ኢትዮጵያዊው ርእሰ ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ ፡ ሚያዝያ ፭ (5) ቀን ፬፻፺፫ (493) ዓ፡ም፡ በአክሱም ከተማ ተወለደ ። አባቱ አዳም የሚባል ሲሆን ፥ እናቱ ታውክሊያ ትባላለች ። የትውልድ ሐረጉም ከአክሱም ካህናት ነው ፡፡ የ፮ ዓመት ሕፃን ሲሆን ፡ አባቱና እናቱ ይስሐቅ ለሚባል ለአክሱማዊው መምህር አስተምርልን ብለው ሰጡት ፡፡ ይሁን እንጂ ትምህር አልገባው ብሎ ስለተቸገረና መምህሩንም ስላስቸገረ መምህሩ ያሬድን መልሶ ወደ አባቱ ዘንድ ላከው ፡፡ በመሐሉም ወላጅ አባቱ ስለሞተበት እናቱ ታውክሊያ ለወንድሜ ለአክሱም ቄሰ ገበዝ ለአባ ጌዴዎን እንዲያሳድገ ውና እንዲያስተምረው ሰጠችው ፡፡ አባ ጌዴዎንም በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት መምህር ነበርና በግዕዝ ፡ በእብራይስጥ በግሪክና በዓረብ ቋንቋዎች ይተረጉማቸው ነበር ፡፡ አባ ጌዴዎን ያሬድን አብሯቸው እንዲኖር በማድረግ ቢያስተምሩ ትም ለብዙ ዓመታት መዝሙረ ዳዊትን ማጥናት አቅቶት አብረውት ከሚማሩት ሕዓናት ጋር ሊወዳደር ባለመቻሉና ወደኋላ በመቅረቱ አባ ጌዴዎን ያሬድን በየጊዜው ይመክሩትና ይገሥፁት ነበር ፡፡ ያሬድ በትምህርት ደካማ ስለነበረ አስተማሪዎች የሚስጡትን ትምህርት ደጋ ግሞ ቢያጠናም አልሆንለት ስለአለ የትምህርት ጓደኞቹ ሲቀልዱበትና ሲያፌዙበት ይውሉ ነበር ። አጎቱ አባ ጌዴዎን በያሬድ ስንፍና ተማሮ አንድ ቀን ለምን እንደሌሎቹ ጓደኞችህ በደምብ አታጠናምመ ብሎ ያሬድን ክፉኛ ገረፈው ፡፡ ያሬድ በአጋጠመው የትምህርት አለመሳካትት ተስፋ ቆርጦ የትም ሔዶ አዲስ ሕይወት ለመጀመር ቁርጥ ሐሳብ አደረገ ፡፡ ያሬድ ከተማሪ ቤቱ ጠፍቶ ወደ አጎቱ አገር ወደ መደባይ ወለል ሲሔድ ኃይለኛ ዝናብ ስለዘነበ ከአክሱም ከተማ ፬ (4) ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ክምትገኝ ማይከራኸ ከምትባል ምንጭ ውኃ አጠገብ ወደአለው ዛፍ ሥር ተጠግቶ መጠለል ግድ ሆነበት ፡፡ ዛፉን ተጠግቶ ደገፍ ብሎ አንደቆመ በምን ምክንያት በትምህርት ከጓደኞቹ በታች እንደሆነ ሊያስብና ሲያሰላስል ሲያዝንና ሲተክዝ ከቆየ በኋላ ፡ ሐሳቡን የሚያስለውጥ ነገር በድንገት ተመለከተ ፡፡ ይኸውም አንድ ጉንዳን አንድ የእህል ፍሬ ተሸክሞ ወደዛፍ ለመውጣት ከፍተኛ ሙከራ ሲያደርግ አየ። ጉንዳኑ የተሸከመውን ይዞ ስድስት ጊዜ ለመውጣት ጥረት ቢያደርግም ሊሳካለት አልቻለም ፡፡ ነገር ግን ተስፋ ሳይቆርጥ ክብዙ ድካምና ጥረት በኋላ በሰባተኛወ ሙከራ የተሸከማትን የእህል ፍሬ ይዞ ወጣ ። በሙሉ አትኩሮት ይመለከተውና ይከታተለው የነበረው ያሬድም በድንገት ስሜቱ ተነካ ፡፡ ይህ አነስተኛ ፍጡር ከብዙ ጥረት በኋላ ያሰበውን ሲፈጽም የእኔ ተስፋ መቁረጥ ምን ይባላል ሲል ራሱን በራሱ ወቀሰ ከጉንዳኑ ያገኘው ትምህርት ልቡን ስለነካው ስሜቱንም ስለቀሰቀሰውና የጉንዳኑን ትጋትም አይቶ ስለ ተደነቀ በራሱ ደካማነት ተጸጽቶ አለቀሰ ፡፡ ያሬድ በዚሁ አነስተኛ ፍጡር ጥረትና ተስፋ አለመቁረጥ ተደንቆ ራሱን እንዲመረምር ስሜቱን ስለሎረኮረው ፥ ወደ አክሱም ተመልሶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወሰነ ። የሰው አፈጣጠር ከዚህ አነስተኛ ፍጥረት እጅግ በጣም የላቀ መሆኑን ስለተገነዘበ ፡ ያጉቱን ምክርና ተግሣፅ ለሕይወቱ የሚጠቅም እንደሆነ በመረዳት ያለውንም ትምህርት በትጋት ቢማርና ቢያጠና የተሻለ ውጤት ሊያገኝ እንደሚችል በማመን ወደ አጉቱና ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ወደ አባ ጌዴዎን ተመልሶ በመምጣት አባቴ ሆይ ይቅር በለኝና እንደ ቀድሞ አስተምረኝ ብሎ አጉቱ እግር ላይ ወደቀ፡፡ መምህሩ አባ ጌዴዎንም ፈቅደውለት ዳዊቱን ያስተምሩት ጀመር ። ሕፃኑ ያሬድም ትምህርቱን እየተማረ ሁልጊዜ በጽሞና ወደ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲ ያን እየገባ "መሖሪ እግዚአብሔር ዐይነ ልቦናየን አብራልኝ" እያለ በየቀኑ በንጹሕ ልቦና ይጸልይ ነበር ። መሐሪውና የቅር ባዩ እግዚአብሔር ርም ልመናውን ሰምቶ ዐይነ ልቦናውን አበራለትና ትምህርቱ ተገለጸለት። ባጭር ጊዜ ውስጥ እንዲህ ዐይነት ከፍተኛና የማይታሰብ ለውጥ በማምጣቱ ጓደኞቹና መምህራኑ እጅግ በጣም ተደነቁ ፡፡ በዚህ ፈጣን የትምህርት መቀበል ችሎታ የብሉይ ኪዳንንና የአዲስ ኪዳንን ትርጓሜ መጻሕፍት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጨረሰ። ያሬድ ከፍተኛ የትምህርት ተሰጥዎ ያለው በመሆኑ ትምህርቱን በጣም አስደናቂ በሆነ መንገድ ፈጽሞ ዲያቆን ሆነ ፡፡ ከመምህሩ ከአባ ጌዴዎን በተማረው መሠረት የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋዎችን ደህና አድርጉ ያውቅ ነበር ይባላል ፡፡ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስና እንዲሁም በውጭ አገር ቋንቋዎች የአጉቱን የመምህር ጌዴዎንን ሙያ አጠናቆ ቻለ ፡፡ ያሬድ አጉቱ ሲሞት የዐሥራ አራት አመት ልጅ ቢሆንም የአጉቱን ሙያና የትምህርት ወንበር ተረክቦ ማስተማር ጀመረ። በግንቦት ፲፩ (11) ቀን ስንክሳር በተባለው የቅዱሳን የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ "ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶና ተነሣሥቶ የዜማ ድርሰቶቹን አዘጋጀ" ይላል። በዚሁ ስንክሳር እንደ ተጻፈው እግዚአብሔር በዚች ምድር እንዲመስገን በፈለገ ጊዜ ያሬድን በራሱ ቋንቋ ሰማያዊ ዜማ እንዲያስተምሩት በአእዋፍ አምሳል ሦስት መላእክትን ከገነት ላከለት ይላል ፥፡ እነሱም ያሬድ ካለበት ሥፍራ አንጻር ባለው አየር ላይ ረበው (አንዣብበው) ጣዕም ያለውና ልብን የሚመስጥ አዲስ ዜማ አሰሙት ፡፡ ያን ጊዜ ያሬድ በጣዕመ ዜማቸው ተመስጦ ቁሞ ሲያዳምጥ ወዲያውኑ ወፎቹ በግዕዝ ቋንቋ "ብጹዕ ወክቡር አንተ ያሬድ ብጽፅት ከርሥ አንተ ጾረተከ ውብጹዓት አጥባት አላ ሐአናከ" ብለው በአንድነት አመስግኑት። ትርጉሙ "የተመሰገንክና የተክበርክ ያሬድ ሆይ ፡ አንተን የተሸከመች ማኅፀን የተመስገነች ናት ፡፡ አንተን ያሳደጉ ጡቶችም የተመሰገኑ ናቸው" ብለው አመሰገኑት ፡፡ ከዚያም ሐያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዜማ ወደ ሚዘምሩበት ወጋ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም አሳረጉት ፡፡ ቅዱስ ያሬድም በመንበረ ጸባዖት ፊጓ ቁሞ ከሐያ አራቱ ካህናተ ሰማይ በፍጥነት የሰማው ማኀሌት ሁቦ በመንፈስ እግዚአብሔር ተገለጸለትና በልቦናው የተሣለበትን ጰዋትዜ ዜማ በቃሉ ያዜም ጀመር ፡፡ ከዚያም ወደ ቀድሞ ቦታው ወደ አክሱም በተመለሰ ጊዜ ክጥዋቱ በ፫ ሰዓት ወደ አክሱም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በታቦተ ጽዮን አንጻር ቆሞ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ፡ በከፍተኛ ድምፅ በአራራይ ዜማ ሃሌ ሉያ ለአብ ፡ ሃሌ ሉያ ለወልድ ፡ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቅዳሜሃ ለጽዮን ሰማየ ሳረረ ወዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘክመ ይገብር ግብራ ለደብተራ" ብሉ ሥነፍጥረቱንና ሰማያዊት ጽዮንን አሰመልክቶ ዘመረ ይህችንም ማኅሌት አርያም ብሎ ጠራት ዞ አርያምም ማለት ልዕልና ሰባተኛ ሰማይ መንበረ እግዚአብሔር ማለት ነው ፡፡ ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመርቶ መላእክት እንደ ከበሮ እንቢልታ፣ ጸናጽል ፣ ማሲንቆና በገና በመሳሰሉት የማኅሌት መሣሪያዎች እየዘመሩ አምላካቸውን እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ስለስማ እነዚህን መሣሪያዎች በሥራ ላይ እንዲውሉ አደረጋቸው ፡፡ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

☞= "ፍፁም ፍቅር" = ባልንጀራውን የሚወድ በባልንጀራው ላይ ክፉ ሥራ አይሠራም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።[ ሮሜ 13፥10] ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ☞"ይቅር ባይነት" በምትጸልዩበትም ጊዜ በሰማያት ያለው አባታችሁ በደላችሁን ይቅር እንዲላችሁ በወንድማችሁ ያለውን በደል ይቅር በሉ። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም በደላችሁን ይቅር አይላችሁም።" (ማር. 11፥25-26) ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ☞"በጎነት (ቸርነት)" ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚበድሉአችሁና ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ። ||ማቴ 5፥44|| ክፉ ላደረገባችሁ ክፉ አትመልሱ፤ የሰደባችሁንም አትስደቡ፤ጠላታችሁንም መርቁ፤ በረከትን ትወርሱ ዘንድ ለዚህ ተጠርታችኃልና።[ 1ኛ ጴጥ.3፥9] ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ☞"ትህትና" ለትዕቢተኞች ጥፋት ፈውስ የላትም፤ ክፉ ተክል በውስጣቸው ሥር ሰድዶአልና። (መ.ሲራክ 3፥26) ራሱን ከሁሉ ዝቅ የምያደርግ እርሱ ታላቅ ይሆናል።{ሉቃስ 9፥48} እግዚአብሔርን በመፍራት ለባልንጀራችሁ ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ።// ኤፌሶን 5፥21// ትህትናን በያዘ ልቡና ከራሳችሁ ይልቅ ባልንጀራችሁን አክብሩእንጅ አትታበዩ። ትዕቢትን የሚያደርግ በቤቴ መካከል አይኖርም፤ ዐመፃን የሚናገር በፊቴ አይጸናም። መዝ 100 ፥ 7 ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ኦሪትም ነቢያትም የሚያዝዙት ይህ ነውና። [[ማቴ7፥12]] ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ "ለራስህ የምትጠላውን ለማንም አታድርግ።" (መ.ጦቢት 4፥15) አቤቱ አባታችን ሆይ! ማስተዋሉን አድለን፤ እኛ ደካሞች ነንና አንተ አጋዥ ሁነን። ከሁሉ አስቀድመን እንለምንሃለንና ሁሉን እንወድ ዘንድ ንፁህ ልብን ስጠንን፤ የይቅርታ ልብንም ስጠን፤ ነፍሳችን ትህትናን ትላበስ ፤ በጎ ምግባርን ይዘን 30,60,100 ያማረ የሕይወት ፍሬ አፍርተን የመንግሥትህ ወራሾች እንድንሆን ፍቀድልን ሁሉ ይቻልሃልና። ክብር ምስጋና ለስምህ ይሁን አሜን። ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

የምስጋና ህይወት ለእግዚአብሔር ምስጋና ስናቀርብ ጊዜና ወቅት ጠብቀን በተለዬ ጊዜ ሳይሆን <<ሁልጊዜ>>መሆን አለበት። ምስጋናውም ደግሞ የማያቆርጥ እስከሆነ ድረስ መላ የህይወት ዘመንን ያጠቃልላል። መላ ህይወትን ከሚያጠቃልል የምስጋና ህይወት ጋር ተመሳሳይ የሆተ ትምህርት በመጀመሪያው ተሰሎንቄ ሰወች መልእክት ውስጥ እንዲ ተፅፍል (1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ምዕ. 5) ---------- 16፤ ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ 17-18፤👉 ሳታቋርጡ ጸልዩ፤👉 በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። ይህ ትምህርት የምስጋና ፀሎት ፀሎቶችን ሁሉ እንደሚመራ ያስሰዳል ። የሰርክ እንዲሁም ሁሉም የቤተክርስቲያን ስርአቶችና አገልግሎቶች የሚጀምሩበት በምስጋና ፀሎት ነው ። እግዚአብሔር ሁልጊዜ በማለዳው በቀትር እና በማታ እናመሰግነዋለን። እንደመዝሙረኛው ዳዊት <ስለቅን ፍርድህ ለምስጋና በሌሊት እነሳለሁ> እንላለን። ከአቡነ ሺኖዳ የምስጋና ህይወት ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ ይቀጥላል ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

፨ የእኔ ለምትለው ሰው የምትሠጠው ትልቁ ስጦታህ ጊዜህን፣ አትኩሮትህን ነው፡፡ ✅ ወዳጄ ሆይ!... እንደራስህ ለምትወደው ወዳጅህ ልትሠጠው የምትችለው ትልቁ ስጦታህ ጊዜህን፣ ፍቅርህንና አትኩሮትህን ከሆነ ለዚህ ሰው ያለህ አመለካከት መልካምና ቅንነት የተሞላው እንደሆነ ማወቅ ይቻላል፡፡ ምክንያቱም በዚህ ዘመን ጊዜ ወርቅ ነው፡፡ ለማትወደው ወይም ጥሩ አመለካከት ለሌለህ ሰው ውዱን ጊዜህን አታካፍለውም፡፡ ፍቅር ወረት በሆነበት ዘመን ፍቅርህን የምትቸረው ሰው በአንተ ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታ ላለው ሰው ነው፡፡ ፍቅር በዚህ ዘመን ውድ ከመሆኑ የተነሳ እንደከበሩ ማዕድናት ብርቅ ሆኗል፡፡ ✅ አትኩሮትህንም ቢሆን እንደው ለማንም ዝም ብለህ የምትለግሠው አይደለም፡፡ አትኩሮት ማለት የምታውጠነጥነው ሃሳብህ ነው፡፡ ስንት የሚያሳስብህና የምታሠላስልበት የኑሮ ጉዳይ እያለህ ሃሳብህን ሁሉ ሰብስበህ የምትሠጠው በልብህ ፅላት ውስጥ ላሠፈርከው ሠው ነው፡፡ አትኩሮት ለወዳጅነት፣ ለባለትዳርነት፣ ለተማሪ አስተማሪ ግንኙነት፣ ለአለቃና ለምንዝር እንዲሁም ለሌሎችም ነገሮች ወሳኝ ነገር ነውና፡፡ አትኩሮት አጥተው የተለያዩ ባልና ሚስቶች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ እሷ ለእኔ ግድ የላትም፡፡ እሱ ለእኔ ግድ የለውም እየተባባሉ ለዘመናት የገነቡትን ጓደኝነታቸውን፣ ጉርብትናቸውን ወይም ዝምድናቸውን የተዉ እልፍ ሠዎች ናቸው፡፡ አትኩሮት አጥቶ ትምህርቱ ላይ ስኬታማ ያልሆነ ተማሪ እንደአሸን ነው፡፡ አትኩሮት ለራስ፣ ለወዳጅ፣ ለቤተሠብ ወሳኝ ነገር ነውና፡፡ አትኩሮት መስጠት ማለት ለወዳጃችን ወይም ለቤተሠባችን ሃሳባችን ከሃሳቡ አስማምቶ፤ መንፈሳችንን ከመንፈሱ አዋህዶ፣ ልብ ለልብ ተገናኝቶ መኖር ማለት ነው፡፡ ✅ ወዳጆች ሆይ በወዳጅነት ስንኖር እነዚህን ሶስት ነገሮች ማለትም ጊዜን፣ ፍቅርንና አትኩሮትን ለወዳጃችን እንሠጠው ዘንድ ግድ ይለናል፡፡ አልያም የወዳጅነት ልኩ ሚዛን አይደፋም፡፡ ወዳጅ ላልነው ሰው ወዳጅነቱን ልናሥመሠክር የምንችለው ጊዜአችንን፣ ፍቅራችንን እና አትኩሮታችንን ሳንቆራርጥ፣ በወረት ሳንለወጥ በቋሚነት ስንሠጠው ብቻ ነው፡፡ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ራስን መሆን ልብ ያለው ያንብበው ፣ በአገር ውስጥ አንድ ሀብታም ባለጠጋ ሰው ይኖር ነበር ። ለጋብቻም የደረሰች ልጃገረድ የሆነች ሴት ልጅ ነበረችውና ልጅህን ዳርልን ጥያቄ በተደጋጋሚ ከብዙ ወንዶች ይቀርብለት ነበር ። ታድያ በዚህ የተማረረው አባት ልጁን ለማንም ለመዳር ፈቃደኛ አለመሆኑን ቢያሣውቅም የጠያቂዎችን ቁጥር በይበልጥ ጨመረው እንጂ ሊያስቆመው አልቻለም ። ፣ ታድያ በዚህ ግራ የተጋባው አባት እንደ ባህሉና ስርአቱ ወደ አገር ሽማግሌዎች በመሄድ እየሆነ ያለውን በሙሉ ያሥረዳል ። ሽማግሌዎችም ነገሩን በጥሞና ካዳመጡ በዋላ አንድ ምክር ይለግሡታል ፣ እንዲህም አሉት ፣ ለልጅህ በጣም ብዙ ኪስ ያለው ሱሪ ታሰፋና በእያንዳንዱ ኪስ ውስጥ ሳንቲሞችን ሙላበት ። ሳንቲሙን እስከ አፉ ድረስ ከሞላህ በዋላ ለጋብቻ ጥያቄ ያቀረቡትን በሙሉ ሠብሥበህ አንድ ትእዛዝ እዘዛቸው እንዲህም በላቸው ። ፣ ልጄን ከፊት ለፊታችሁ እንድትሮጥ አደርጋለው ። ከናንተም መካከል አሮጦ የያዘ ሰው እሱ ልጄን የሚያገባ ይሆናል ይላቸዋል ። በዚህም ግዜ ሰዎቹ ባባትየው ትእዛዝ ይስማማሉ ። ከዛም አባትየው ወደ ልጁም ይሄድና ልጄ እያባሩሽ ሳለ አንድ ሰው ሊይዝሽ ሲደርስብሽ ሳንቲሙን ከኪስሽ እያወጣሽ መሬቱ ላይ በትኚው ብሎ ይነግራታል ። ፣ ልጅቷም ያባቷን ትእዛዝ በመቀበል ሩጫው ይጀመራል ። ከዛም ከሩዋጮቹ መካከል አንዱ ሊይዛት ሲደርስባት ሳንቲሙን አውጥታ ትበትናለች ከዛም ሰውየው እሷን ትቶ ሳንቲሙን መልቀም ይጀምራል ። ሊይዟት የደረሡት ላይ በሙሉ ሳንቲሙን እያወጣች ስትበትን እሷን ትተው ሳንቲሙን መልቀሙን ተያያዙት ። ፣ ልጅቷም ሸክሙ እየቀለለላትና ፍጥነት እየጨመረች ሄደች ሊይዟትም የደረሱባት ሁሉ እሷን ትተው ከኪሷ የሚበተነውን ሳንቲም ወደ መልቀም ተቀየሩ ። አንድ ምስኪን ደሀ ሰው ግን ከኪሷ የሚበተነው ሣንቲም ሳያጓጓው እሷን ራስዋን አሳዶ በመያዝ ልጅቷን የራሱ አደረጋት ። ይህንንም የተመለከተ አባት ለልጁ ባል ሊሆን የሚችል ሰው በማግኘቱ ደስ አለው ። ልጁንም ዳረለት ። ፣ ብዙዎቻችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ለምንድነው የምንሄደው ? በረከትን ፣ ገንዘብን ፣ ትዳርን ፣ ቤት ፣ መኪና ፣ ትርኪ ምርከኪ ፍለጋ ፣ ወይስ እግዚአብሔርን ራሱን ፍለጋ ? ማናችንም እግዚአብሔርን አናታልለውም ። የእያንዳንዳችንን የተሰወረ የልብ መሻት ያውቃል ። እጁን ሳይሆን ልጁን ፍትፍቱን ሳይሆን ፊቱን ፈላጊ እንሁን ፡፡ ፣ ፌስቡክን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም ፡፡ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ፡፡ በምድር ላይ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና ፡፡ ፣ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

☞አንብበው ካልጨረሱት አይጀምሩት! ስለ # አዳምና_ሄዋን_ጥያቄ_ከነ_መልሱ 1/ እግዚአብሔር አዳምን ከፍጥረታት መጨረሻ ለምን ፈጠረው? 2/ እግዚአብሔር ሌሎችን ፍጥረታት አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳምን አቅንቶ ለምን ፈጠረው? 3/ እግዚአብሔር አዳምን ለሚቆም ፣የሚተኛ አድርጎ ለምን ፈጠረው? 4/ እግዚአብሔር ለአዳም ስንት ሀብታትን ሰጠው?ምንምን ናቸው? 5/ እግዚአብሔር ሄዋንን ከአዳም ከጎኑ አጥንት ለምን ፈጠራት ?ከግንባር ወይም ከ እግር ለምን አልፈጠራትም? 6/ በገነት ውስጥ ስንት አይነት ዛፎች ነበሩ? 7/አዳምና ሄዋን የእግዚአብሔርን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ቆዩ? 8/ አዳምና ሄዋንን በእባቢቱ ላይ አድሮ ያሳታቸው ሰይጣን ስም ማን ይባላል? 9/አዳምና ሄዋን ስንት ልጆች ነበራቸው ? 10/ አዳም በተፈጠረ በስንት አመቱ አረፈ? # አዳም ማለት ከመሬት የተፈጠረ ያማረ መልከ መልካም ማለት ሲሆን የተፈጠረው ከአራት ባህርያተ ስጋ ማለትም ከነፋስ፣ከእሳት ፣ከውሀ፣ከመሬት እንድሁም ከሶስቱ ባህርያተ ነፍስ ማለትም ከልብ ፣ከቃል፣ከእስትፋስ የስነ ፍጥረት መካተቻ በሆነች በእለተ አርብ በ3 ስዓተከህቱም ምድር ሚያዝያ 4 ቀን በምድር መካከል በምትገኘው <ኤልዳ> በተባለች ስፍራ የ30 አመት ጎልማሳ ሁኖ በእግዚአብሔር አርአያነት መልክ ተፈጠረ፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 1፣27 ፣ኩፉሌ 5፣6 # መልስ ፡- 1/አዳም ከፍጥረታት መጨረሻ ለምን ተፈጠረ? ☞መጨረሻ የተፈጠረበት ምክንያት እግዚአብሔር አምላካችን "በጎ አምላክ" ስለሆነ በጎ አባት ለልጁ አብሮት ከብት ያረባለታል ፣ጥማጅ ያጠምድለታል፣ የኑሮ ጓደኛ ያመጣለታል አስቀድሞየሚበላው፣የሚጠጣው፣የሚገዛውና የሚነዳውን ፈጥሮለት በመጨረሻም በሁሉ ላይ ሊያሰለጥነው አዳምን ፈጠረው፡፡ 2/ ሌሎችን ፍጥረታት አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳምን ለምን አቅንቶ ፈጠረው? ☞ እሱ ገዥ እናተ ተገዥ ናችሁ ሲል ነወ፣እንድሁም እናተ ፈርሳችሁ በሰብሳላችሁ ትቀራላችሁ እሱ ግን" ትንሳኤ ሙታን " አለው ሲል አቅንቶ ፈጠረው፡፡ 3/ አዳምን የሚቆም የሚተኛ አድርጎ ለምን ፈጠረው? ☞ መቆሙ- ሰማያዊ ፣ ☞መቀመጡ- ምድራዊ ነህ ሲለው ነው፣ ☞የሚተኛ ፣ የሚነሳ አድርጎ መፍጠሩ ደግሞ ☞መተኛቱ ሞቱን ☞መነሳቱ - ትንሳኤውን ሲነግረው ነው፡፡ 4/ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም ስንት ሀብታት ሰጠው?ምን ምን? ☞ሰባት ሀብታትን የሰጠው ሲሆን እነሱም፡- ➊ሀብተ መንግስት (የማስተዳደር ሀብት ➋ሀብተ ክህነት ( የመቀደስ፣የመባረክ፣መስዋዕት የማቅረብ ➌ ሀብተ ትንቢት (የመጣውን የመናገር ➍ሀብተ መዋኢ (የማሸነፍ ➎ሀብተ ሀይል (የጥንካሬ ➏ሀብተ ፈውስ ( የመዳን ፣የመፈወስ ➐ሀብተ ዝምሬ (የመዝሙር 5/ ሄዋን ከአዳም ከጎኑ አጥንት ወስዶ ለምን ተሰራች?ከግንባር ወይም ከእግር ለምን አልሰራትም? ☞ አዳም ለእንሰሳት፣ለሰማይ ወፎች ና ለምድር አራዊቶች ሁሉ ተባእትና እንስት ሁነው ሲመጡ ስም ያወጣላቸው ነበር፡፡ነገር ግን ለአዳም እንደ ራሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር ፡፡ "እግዚአብሔርም " ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረዳት ልፍጥርለት አለ ፡፡ኦዘፍ 2፣18 ከዚያም በአዳም ላይ እንቅልፍ አመጣበትና ፈፅሞ ሳይተኛ ፣ፈፅሞ ሳይነቃ ከጎኑ አጥንት አንስት አንስቶ ያችን ስጋ አልብሶ የ15 አመት ቆንጆ አድርጎ ፈጠራት ፣ኦዘፍ 2፣18 አዳምም ስሟንም "ሄዋን" አላት ፣ሄዋን ማለት "ሀይው" ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም" የህያዋን ሁሉ እናት "ማለት ነው፡፡ ፈፅሞ ሳይተኛ ፣ፈፅሞ ሳይነቃ ሄዋንን መፍጠሩ ☞ፈፅሞ ተኝቶ ቢሆን ኑሮ ምትሀት መስሎት ከየት መጣች ብሎ ይፈራታል ☞ፈፅሞ ነቅቶ ቢሆን ኑሮ ከአካሉ አጥንት ሲነሳለት ያመው ነበርና ይጠላት ነበር ፡፡ ☞ከፍ አድርጎ ከግባር ዝቅ አድርጎ ከእግር ያልሰራት ግባርና እግር በልብስ አይሸፈንም ጎኑ ግን በልብስ ይሸፈናልና ተሰውራ ወይም ተሸፍና መኖር ይገባታል ሲል ነው፡፡ በሌላ በኩል ግንባር የባለቤት እግር፣ የቤተሰብ ምሳሌ ነው ፡ እሷም ከባለቤቷ በስተታች ከቤተሰብ በላይ ሁና ትኑር ሲል ነው ፡፡1ኛ ቆሮ 12፣19-22 እንድህ አድርጎ አዳምና ሄዋንን እስከ 40 ቀን ድረስ በተፈጠሩበት በማዕለ ምድር በቀራንዮ አስናበታቸው ጌታችን አምላካችንና መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የሚሰቀልበት ቦታ ነውና ከዛም በ40ኛው ቀን አዳምን ብርሃን አልብሰው ፣ብርሀን አጎናፅፈው፣የብርሀን ዘውድ አቀናጅተው በብርሃን ሰረገላ አስቀምጠው ወደ ገነት አስገቡት፡፡ ሄዋንንም በ80 ቀኗ እንደ አዳም ባለ ክብር ወደ ገነት አስገቧት ፡፡ኩፉሌ ፈ 4፣12-15 አዳምና ሄዋን ከእግዚአብሔር የባህሪ ደግነት የተነሳ እርሱን ለማመስገንና ክብሩን ለመውረስ ተፈጠሩ፡፡ኩፋሌ 4 ፣3-5 እግዚአብሔር ለአዳም ረዳት የፈጠረለት ስለ ሶስት ነገሮች ሲል ነው፡፡ ➊ዘርን ለማብዛት ➋ ከዝሙት እንድፀዳና ➌ረዳት እንድትሆነው ነው 6/ በገነት ውስጥ 3 አይነት ዛፎች ነበሩ ➊ ዕፀ መብል -እንድበሉት የተፈቀደላቸው ምግብ ነው ➋ዕፀ በለስ-እንዳይበሉ የታዘዙት ነው ➌ዕፀ ህይወት - እንደ <እግዚአብሔር > ፈቃድ የሚመገቡት የዘለዓለም ህይወት የሚሰጥ ምግብ ነው፡፡ ህግን ጠብቀው በገነት ውስጥ 1000 አመት ከኖሩ ብኀላ እፀ ህይወት በልተው ከገነት ወደ ሰማያዊ እየሩሳሌም (መንግስተ ሰማይ ) እንድገቡ ለበለጠ ክብርና ፀጋ ሽልማት እንድሎናቸው ነበር፡፡ነገር ግን ያለ ጊዜው ሳቱ እንጅ 'እፀ በለስ ' እንዳይበሉ የታዘዙበት ህግ አዳም ፈጣሪ እንዳለው ፣ለፈጣሪው ያለውን ፍቅር የሚገልፅበትና ተገዥነቱን የሚያሳይበት ነው፡፡ 7/ አዳምና ሄዋን የእግዚአብሔርን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ቆዩ? ☞አዳምና ሄዋን ይህን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ለ7 አመት ከ 2ወር ከ 17 ቀን ኖሩ፡፡ 8/ አዳምና ሄዋንን በእባብ ላይ አድሮ ያሳታቸው ሰይጣን ስም ማን ይባላል ? ☞አዳም በሳጥናኤል ተተክቶ መቶኛ ሁኖ ከመላእክት ጋር ተቆጥሮ ነበር ሰይጣንም በእባብ አድሮ አሳቻቸው ጽድቃቸውም ተገፈፈ አዳምና ሄዋንን በእባብ ላይ አድሮ ያሳታቸው ሰይጣን ስም ' ጋርድኤል ይባላል፡፡ በመሆኑም አትብሉ የተባሉትን እፀ በለስ ህጉን አፈረሱ ከገነት ተባረሩ ፡ኦዘፍ 3፣1 ኦዘፍ 3 ፣22-24 9/ አዳምና ሄዋን ስንት ልጆች ነበሯቸው? ☞ ከገነት ከተባረሩ ብኀላ በደብረ ቅድስት ይኖሩ ነበር፡ አዳምና ሄዋን በሰሩት ሀጢያት በመፀፀታቸውና በንሰሀ በመመለሳቸው "እግዚአብሔር" መሀሪ ነውና 5 ቀን ተኩል ወይም 5500 ዘመን ሲፈፀም ሰው ሁኖ በመወለድ እንደሚያድናቸው ቃል ኪዳን ገባላቻው ፡፡ኦዘፍ 3፣15-22 አዳም ግን የራሱን ደም በስንደ ለውሶ ሲሰዋ ጌታችን በአንተ ደም አይደለም አለም የሚድነው በእኔ ነው ብሎ ተስፋ ሰጠው፡፡ አዳምና ሄዋንም በምድር ላይ ዘርን ተክተዋል ገብርኤል ፣ሚካኤል ፣ሩፋኤል ወርቅ ,እጣን,ከርቤ አምጥተው ለአዳም ሲሰጡት ወርቁን ማጫ ይሁንሽ ብሎ ሰጣት ከዛም አዳምና ሄዋን በ 30 ሩካቤ 60 ልጆችን ወልደዋል 10/ አዳም በተፈጠረ በስንት አመቱ አረፈ? ☞ አዳም በተፈጠረ በ930 አመቱ አረፋ ፡አዳም ለሄዋን የሰጣት ወርቅ ለሴት ሰጠችው ሴትም ለኖህ አስተላለፈው እጣኑንም ኖህ አፅመ አዳም እያጠነ ድኖበታል ፡፡ በአዳም ስም በሀገራችን የተሰሩ ቤተክርስቲያኖች ብዛታቸው 5 ናቸው በአዳም ስም የተቀረፀው ታቦት ከሶሪያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያመጣው ፃድቅ አባት 'መልከአ እግዚአብሔር ' ይባላል፡፡ እንድከበር ያደረገው ቅዱስና ሊቁ ያሬድ ማህሌት ነው፡፡ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስር

🌟🌟🌟 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን! በክርስቶስ ልዩ ፍቅር የምወድዳችሁ የክርስቶስ ቤተ ሰቦች! እንደምን ሰነበታችሁ? በጠባቂነቱ እየጠበቀን በመጋቢነቱም እየመገበን በቸርነቱ ይቅር ብሎ በአባታዊ ፍቅሩ የወደደን አባታችን፣ ፈጣሪአችን፣ አምላካችን፣ ጌታ እግዚአብሔር ስለ ሁም ነገር ለሁላችን ሞገስ የሆነው ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን! በዘመናችን ሁሉ ከአልማዝና ከእንቁ በላይ ውድ የሆነውን ሰላም እንሻለንና የሰላም አምላክ እርሱ ሰላሙን ለሁላችንም ያብዛልን። መችም ሁላችንም እንደ ምናውቀዉ በጠብመንጃ አፈ ሙዝ የተገኘ ሰላም አስተማማኝ ሰላም አይደለም። ስለዚህ እድሜ ልክ ጠብመንጃ ተሸክሞ መኖርን ይጠይቃል። ለዚህ ዓለም አስማተኞች አጎብድዶ በመገበር የሚገኝ ሰላምም ካለ እርሱ አስተማማኝ ሰላም ስላልሆነ እድሜ ልክ ለጠንቋዮች እየገበሩ መኖርን ይጠይቃል። ወደ እግዚአብሔር በሚደረግ ጸሎት የሚገኝ ሰላም ግን እርሱ አስተማማኝ ሰላም ነውና ያለ ስጋት የምንኖርበትን እውነተኛ ሰላም ለማግኘት ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ተግተን ልንጸልይ ይገባል! ምክንያቱም ለተኩስ ከሚመረተው የመትረየስ ጥይት በላይ፣ ለውርወራ ከተሰበሰበው ድንጋይ እንዲሁም ለመወጋጋት ከተዘጋጀው ጦርና ለመተራረድ ከተሳለው ገጀራ ይልቅ በንጹሕ ኅሊና የሚጸለየው አንድ አቡነ ዘበሰማያት ለሀገር አስተማማኝ የሆነ እውነተኛውን ሰላም መገንባት ይችላልና። ጥላቻ በየትኛውም ዓይነት የሂሳብ ስሌት ሰላም የሚባለውን ውጤት ማምጣት አንችልም። ጥላቻ የሚያፈራው እኮ ጥላቻን ብቻ ነው። ስለዚህ ከጥላቻ ሰላም እይለቀምም። ደግሞም እየተዋደዱ እንጂ እየተጣሉ መች ሰላም ይገኛል? ሀገራችን ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ደሀ የሆነችው እኮ ሌላ ምንም አጥታ ሳይሆን ሰላምን ማምረት ስላልቻለች ብቻ ነው። በኢኮኖሚ ከበለፀጉት አገሮች ተርታ እንዳንሰለፍ እንኳ የድሀነታችንን እድሜ እያራዘመብን ያለው ጥላቻ ነው። ስለዚህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ መቶ ሚልየን ሕዝብ ሆነን ጥላቻን መግደል ሲያቅተን ግን በጣም ያሳዝናል። እውነቱን ለመናገር በገዛ ሜዳችን ላይ ጥላቻ አንድ ለዜሮ እየመራን ነው። መችም ወንድምን መግደል ጀግንነት ነው ተብሎ ቅቤ አያስቀባም። ስለዚህ በእኔ አመለካከት ጀግንነት ማለት ጥላቻን መግደል እንጂ ወገንን መጨፍጨፍ አይደለም። ጀግንነት ማለት ጥላቻን ማሳደድ እንጅ ወገንን ማፈናቀል አይደለም። ጀግንነት ማለት ድህነትን ማጥፋት እንጂ ንብረትን ማውደም አይደለም። ለጥላቻ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ተሰጥቶት በሕይወት የመኖር መብቱ ከተጠበቀለት ግን በኢትዮጵያ ውስጥ የሰናፍጭ ቅንጣት የምታህል ሰላም ትኖራለች ብላችሁ አታስቡ! ዘረኝነቱ ይቀጥላል። መፈናቀሉ ይቀጥላል። መገዳደሉ ይቀጥላል። ለሕይወታችን አደጋና ስጋት የሚሆኑ ነገሮች ሁሉ ጉልበታቸውን እንደ ንስር እያደሱ ይበረቱብናል። ስለዚህ እኔ ጥላቻ በተገኘበት ሥፍራ ሁሉ ነፍሱ ጓዟን ጠቅልላ እስክትወጣ ድረስ ተይዞ ሊገደል ይገባል ባይ ነኝ። ምክንያቱም፦ ጥላቻ ካልሞተ ሰላማችን ሕይወት አይኖረውም፣ መለያየት ካልሞተ አንድነታችን ሕይወት አይኖረውም፣ መተነኳኮሱ ካልሞተ ፍቅራችን ሕይወት አይኖረውም፣ ዘረኝነት ካልሞተ ኢትዮጵያዊነታችን ሕይወት አይኖረውም፣ ስለዚህ እባካችሁ በዘር ደረጃም ቢሆን የአንዱ የአዳም ዘር መሆናችንን አምነን ማለፏ አይቀርምና ይህች ዓለም እስክታልፍ ድረስ ከእግዚአብሔር ለጋራ በተሰጠችን ኢትዮጵያ ውስጥ በፍቅርና በሰላም አብረን እንኑር! እኛ ጠባቦች ሆነን ሁሉን ነገር አጥብበን እያሰብነው እንጂ ሀገራችንማ እንኳንስ ለዜጎቿ ለሁሉም የምትበቃ ሰፊ ሀገር ነበረች። ስለዚህ፦ መወቃቀሱ ይቅር! መተነኳኮሱ ይቅር! መገፋፋቱ ይቅር! መቆሳሰሉ ይቅር! መገዳደሉ ይቅር! ምክንያቱም በዚህ ሁሉ ሰላምን ማምጣት አንችልምና። ይልቅስ ሰላምን ለማምጣት ጥላቻን መግደሉ ብቻ በቂ እንደ ሆነ እመኑ! ዳሩ ግን ጥላቻ በእጅጉ ያስፈልገናል የምንል ከሆነም እንኳ ጥላቻችን ጥላቻን በመጥላት ብቻ ሊገለጥ ይገባዋል። ከዚህ ውጪ ግን የጥላቻ ጉዳቱ እንጂ ጥቅሙ አይታየኝም። ደግሞም በfacebook እና በተለያዩ ሥፍራዎች ላይ የሚተከለው ጥላቻ በጥቂት ጊዜ ውስጥ እንደ እንቦጭ አረም ራሱን እያባዛና ሰማይ ምድሩን እያለበሰ ሕይወታችን የምትፈልገዉን የሰላም ውሃ እንዳያደርቅብን ዘሩን የማምከን ሥራ ልንሠራ ይገባል። ዛሬ ላይ ደርሳ ሀገራችን ኢትዮጵያ የጠበበችን እኮ ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው ጥላቻ መጥቶ በመካከላችን ስለገባ ነው። ጥላቻ ካለ ደግሞ ሀገራችን እንኳንስ ለመቶ ሚልየን ህዝብ ይቅርና ለሁለት ሰው እንኳ የማትበቃ ጠባብ ትሆናለች። ስለዚህ ዘመቻችን ሰፊዋ ሀገራችንን ኢትዮጵያን በሚያጠብብን በጥላቻ ላይ መሆን አለበት። የእድገታችንም ትልቁ ማነቆ ጥላቻ ነው። ግልፅ ለማድረግ ያህል ከየሥፍራው እየተፈናቀሉ ያሉ ወገኖቻችንን ተመልከቱ! ሀብት ንብረታቸው ስለወደመ የሚለብሱት፣ የሚበሉት፣ የሚጠጡትና የሚጠጉበት አጥተው በየቦታው ይንገላታሉ። ከዚህም የተነሣ ተፈናቃዮቹ ከችግራቸው እንዲያገግሙ በየጊዜው ከባድ መዋእለ ንዋይ ይወጣል። ኢትዮጵያ ወደፊት ከሁሉ አስቀድሞ ዜጎቿ ከቄያቸው እንዳይፈናቀሉ ከማድረግ ይልቅ ከተፈናቀሉ በኋላ ለተፈናቀሉት ዜጎች እያለች ኮሚቴ እያቋቋመች ብቻ በየጊዜው ብዙ መዋእለ ንዋይ የምታፈስ ከሆነ አሁን ካለችበት የኢኮኖሚ ደረጃ ዘቅጣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሕዝቦቿ ለልመና ይሰማራሉ። ለነዚህ ሁሉ ችግሮች ደግሞ ተጠያቂው ጥላቻ ነው። ስለዚህ ሳይቃጠል በቅጠል እንደ ሚባለው ዜጎች ከቄያቸው ከተፈናቀሉ በኋላ ላላስፈላጊ ወጪ ከመዳረግ ይልቅ ከሁሉ አስቀድሞ መንግሥት ጥላቻን ገድሎ በማንኛውም ሥፍራ የዜጎችን በነፃነት የመኖር መብት አስከብሮ ትኩረቱን ወደ ልማት አቅጣጫ ማዞር ይኖርበታል። ምክንያቱም ሁለት እርምጃ ወደ ፊት እየሔዱ ሦስት እርምጃ ወደ ኋላ መመለስ ሀገርን አያሳድግምና። እባካችሁ ከውስጥ ሆኖ እንደ በሶ የሚበጠብጠንን ጥላች ውጣ በሉት! ወደ ውስጥ የሚያስገባው ጠፍቶ ከውጭ የተቀመጠዉን ፍቅር ደግሞ ግባ በሉት! ምክንያቱም ፍቅር ሳይገባ ፍቅር የለምና። ሰላምም ወደ ውስጣችን ሠርጎ የሚገባው አስቀድሞ ጥላቻ ጓዙን ጠቅልሎ ከውስጣችን ነቅሎ ሲወጣ ነው። በድሮ ዘመን የሀገርን ክብር በማስጠበቅ ረገድ ከልዩነታችን ይልቅ አንድነታችን እንደ ተራራ ላይ መብራት ከሩቁ ጎልቶ ይታይ ነበር። ዛሬ ግን ከሚለያዩን ይልቅ አንድ የሚያደርጉን ነገሮች እንደ ሰማይ ከዋክብት በዙርያችን በዝተው ሳሉ አንድነታችን ደበዘዘ። መለያየታችን ሰፋ። ጥላቻችን ሥር ሰደደ። ሰላም ድንኳኗን ነቅላ ሸሸች። ከተራሮች ከፍታ በላይ የነበረው ፍቅራችን ተናደ። በዚህ ሁሉ ግን ተጠያቂው ጥላቻ ነው። ምክንያቱም፦ ጥላቻ ሰብአዊ ክብራችንን ተጋፍቶብናል። ጥላቻ ነፃነታችንን ገፍፎናል። ጥላቻ ምንም ዓይነት መተክያ የሌላትን የብዙ ዜጎችን ነፍስ በከንቱ አጥፍቷል። ጥላቻ የአንድነታችንን መሠረት ንዶብናል። ጥላቻ የፍቅራችንን ውበት አጥፍቶብናል። ጥላቻ ለኢኮኖሚ ውድቀት ዳርጎናል። ስለዚህ ሰላምን አጥብቃችሁ የምትሹ በክርስቶስ ልዩ ፍቅር የምወዳችሁ የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ጥላቻን ከልባችን ውስጥ ጀምሮ በfacebook ውስጥም ይሁን ባገኛችሁበት ሥፍራ ሁሉ ነፍሱ እስክትወጣ ድረስ ያለምንም ርኅራሔ አናት አናቱን እንደ እባብ ቀጥቅጣችሁ ግደሉት! ምክንያቱም ጥላቻን መግደል ያጸድቃል እንጂ አያስኮንንምና። ስለዚህ ምንጊዜም ቢሆን የጽድቅን ሥራ ለመሥራት አትታክቱ! 2ተሰ.3፥13 ✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠ