የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Відкрити в Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Показати більше4 374
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
4 374
☞ “…ለሊሁ እግዚአብሔር ዘበአማን ወወልደ እግዚአብሔር ዋሕድ ብርሃን
ዘእምብርሃን ወሕይወት ወኀይል ነሥአ ዘኢዚኣሁ…” (… አንድ የእግዚአብሔር ልጅ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ሕይወት ኀይል የሚኾን ርሱ እግዚአብሔር ባሕርዩ
ያልነበረ ሥጋን ተዋሐደ) (ቅዱስ ቄርሎስ)
☞ “ወነአምን ቦቱ ከመ ውእቱ እግዚአብሔር ቃል ዘበአማን ወለድንግልሂ ንጽሕት ወላዲተ አምላክ ንሰምያ እመ እግዚአብሔር” (በእውነት ርሱ እግዚአብሔር ቃል እንደኾነ እናምንበታለን፤ አምላክን የወለደች ንጽሕት ድንግልንም የእግዚአብሔር እናት እንላታለን) (ቅዱስ ቄርሎስ)
☞ “ምንት ውእቱ ተሳትፎ በእሉ ከመዝ ዘእንበለ ከዊኖቱ ከማነ በሥጋ ወደም እምድንግል ቅድስት ወላዲተ እግዚአብሔር ማርያም እንዘ ውእቱ አምላከ ጽድቅ…” (በሥጋ ሰዎችን መምሰሉ ምንድን ነው? የባሕርይ አምላክ ሲኾን እግዚአብሔርን ከወለደች ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው በነፍስ በሥጋ እንደ እኛ ሰው መኾኑ ነው እንጂ፤ ይኸውም ከአብ የተወለደ አካላዊ ቃል ነው፤ ለዘለዓለምም ከአብ ጋራ ትክክል ነው፤ በባሕርዩ ቀዳማዊ ነው፤ ልዕልና ባለው ጌትነት ርሱ ብቻውን ያበራል) (ቅዱስ ቄርሎስ)
☞ “ወከመዝ ንሕነ ነአምን ከመ ድንግል ቅድስት ኮነት ታኦዶኮስ (ቴኦቶኮስ)
ዘውእቱ ወላዲተ እግዚአብሔር ብሂል ወሶበ ወለደቶ ለነ መንክረ ለዋሕድ
ክርስቶስ በተሣትፎቱ ደመ ወሥጋ ከማነ” (እንደኛ ነፍስን ሥጋን በመዋሐዱ አንድ
ክርስቶስ ድንቅ በሚያሰኝ ልደት በወለደችው ጊዜም ንጽሕት ድንግል ታኦዶኮስ (ቴኦቶኮስ) (Θεοτόκος,) እንደኾነች እናምናለን፤ ይኸውም እግዚብሔርን የወለደች ማለት ነው) (ቅዱስ ቄርሎስ)
☞ “ወኮነ ሰማይ ዓለመ ወዓለምሂ ሰማየ ወኮነ እግዚአብሔር ሰብአ በታሕቱ
ወረሰዮ ለሰብእ ውስተ አርያም…” (ሰማይ ዓለም ኾነ፤ ዓለምም ሰማይን ኾነ፤
እግዚአብሔር ሰው ኾኖ በዚኽ ዓለም ተገኘ፤ ሰውንም በላይ በአርያም አደረገው፤ በሰማይ የሚቀርበው ምስጋና በዚኽ ዓለም ተደረገ፤ በአብ ዕሪና ያለ ርሱ
በማርያም ክንድ ተይዞ ታየ፤ እግዚአብሔር አብ በማይመረመር ምስጢር ያለ እናት የወለደውን ማርያም በማይመረመር ምስጢር ያለ ዘርዐ ብእሲ በሥጋ ወለደችው) (ቅዱስ ሳዊሮስ)
☞ “ወካዕበ ይቤ እስመ እግዚአብሔር አስተርአየ ለሰብእ በተወልዶ ወመጽአ ኀበ
ዕጓለ እመሕያው፤ ወዓዲ ይቤ ዝንቱ ውእቱ ቃለ እግዚአብሔር ዘኢይትገመር
ዘሀሎ እምቅድመ ኲሉ መዋዕል ዘአልቦቱ ሥጋ ነሥአ ሎቱ ሥጋ” (ዳግመኛ
እግዚአብሔር በመወለዱ ለሰው ተገለጠ፤ ወደ ሰውም መጣ አለ፤ ዳግመኛም የማይወሰን ከቀን ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እግዚአብሔር ቃል ይኽ ነው፤ ሥጋ ያልነበረው ሥጋን ነሣ) (ቅዱስ ሱኑትዩ)
☞ “በፈቃደ አቡሁ ወረደ ኀበ ማርያም ተአንገደ በድንግልናሃ ንጹሕ እግዚአብሔር ተወልደ” (በአባቱ ፈቃድ ወረደ በማርያም ዘንድ እንግዳ ሆነ
እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ) እንዲል ቅዱስ ዲዮስቆሮስ
በቅዳሴው
🙏[ከኹለት አካል አንድ አካል፤ ከኹለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የኾንኽ አምላካችን
ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፈጽመን እናመሰግንኻለን]🙏
[ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾✞ #የኢየሱስ_ክርስቶስ_እግዚአብሔርነት ✞🌾
❖ የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት ትንቢትን በተናገሩ በቀደምት ነቢያት ፈንታ፤ በዓለሙ ኹሉ እግዚአብሔርነቱን በግልጥ ያስተማሩ ሐዋርያት ተተኩ፤ ከዚያም ምስጢሩን የሚያመሰጥሩ ሊቃውንት በሐዋርያት እግር ተተክተው የአምላካቸው የክርስቶስን እግዚአብሔርነት አምልተው አስፍተው
አስተምረዋል፤ ይኽም ትምህርታቸው ጥልቅና ሰፊ ሲኾን በጥቂቱ ትምህርታቸው እነሆ፡-
☞ “ወአግሐዶ ዮሐንስ ወአጥመቆ በውስተ ዮርዳኖስ፤ ተመከረ በገዳም
ወተዐውቀ ከመ እግዚአብሔር ውእቱ” (ዮሐንስ ገለጠው፤ በዮርዳኖስም
አጠመቀው፤ በገዳም ተፈተነ፤ ርሱም እግዚአብሔር እንደኾነ ታወቀ) (ቅዱስ
ሄሬኔዎስ)
☞ “ተሰቅለ በሕማመ ሥጋ ወሐይወ በኀይለ እግዚአብሔር ዘውእቱ መለኮቱ፤
ወወረደ ውስተ መትሕተ ዕመቀ ምድር ወጼወወ ነፍሳተ ሰብእ” (ለሥጋ
በሚስማማ ሕማም ተሰቀለ፤ በእግዚአብሔርነቱ ኀይል ተነሣ፤ ይኸውም መለኮቱ ነው፤ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ማረከ) (ቅዱስ ሄሬኔዎስ)
☞ “እግዚአብሔር ቃል ስለ እኛ እንደታመመ እግዚአብሔር ለእኛ ቤዛ እንደሞተ ብትሰማ፤ እኛ መለኮትን ከትስብእት ጋራ አንድ አካል አንድ ባሕርይ አድርገን ለእግዚአብሔርነቱ በሚገባ በዚኽ ባንድ ስም እንደምንጠራው ዕወቅ… የእኛ አምላክ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ፈቃድ በግብረ መንፈስ ቅዱስም ከዳዊት ዘር ከእመቤታችን ማርያም ተፀነሰ” (ቅዱስ አግናጥዮስ)
☞ “ክርስቲያኖች በምድር ከሚኖሩ ሰዎች ኹሉ በልጠው እውነትን አገኙ፤
በመንፈስ ቅዱስም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ወልድን፤ የኹሉ ነገር
ፈጣሪንና ሠሪን እግዚአብሔርን አወቁ” (አርስቲደስ)
☞ “እናንተ ግሪኮች እግዚአብሔር ከሰው ልጅ እንደተወለደ ስናስገነዝብ ስንፍናና
እየተጫወትን ወይም ተርታ ነገር እየተናገርን አይደለም” (ቴሽያን ሶርያዊ)
☞ “የእግዚአብሔር ቃል ክርስቶስ ከአብ ጋር በህልውና ያለ፤ እኛንም ያስገኘ፤
አኹንም ይኸው ቃል ሰው ኾኖ ተገለጠ፤ ርሱ ብቻ እግዚአብሔርም ሰውም የኾነ
እና የበጎ ነገራት ኹሉ ምንጭ ነው… በተዋሐደው ሥጋ ሲያዩት የተናቀ ቢኾንም እንደ እውነቱ ግን እጅግ ያማረ የተወደደ የተፈቀረ ነው፤ ኢየሱስ መድኀኒታችንና ኀጢአታችንን ይቅር ያለ ፈውሳችን የኾነ መለኮታዊ ቃል ሙሉ በሙሉ በርግጠኛነት በእውነት እግዚአብሔር ነው” (ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ)
☞ “እግዚአብሔር ክርስቶስ የኹሉም ነገር አምላክ በመኾኑ ከሰው ዘር በመላ
ኀጢአትን ጠራርጎ ዐጥቦ አሮጌውን ሰው ዐዲስ አድርጎታል” (ቅዱስ ሂፖሊተስ
(አቡሊዲስ))
☞ “ክርስቶስ ዕሩቅ ብእሲ ቢኾንማ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የኾንኽ አንተን
የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይኽች የዘላለም ሕይወት ናት”
በማለት ያስቀመጠውን ሕግ ለምን እንድናምን አደረገ? (ዮሐ ፲፯፥፫)፤
እግዚአብሔር መኾኑን እንድረዳው ባይፈልግ ኖሮማ ለምን “የላክኸውንም
ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ” ብሎ ለምን አከለበት? ይኽም እንደ
እግዚአብሔርነቱ እንድንቀበለው ነው፤ ይኽ ባይኾን ኖሮማ “የላክኸውን ሰው
ኢየሱስ ክርስቶስን” ይለን ነበር፤ በርግጥ ግን ርሱ ይኽነን አላከለበትም፤ ወይም
ክርስቶስ ራሱን ፍጹም ሰው ብቻ እንደኾነ አድርጎ አላቀረበልንም፤ ኾኖም ግን
ርሱ ራሱ እግዚአብሔር እንደኾነ እንድንረዳው ፈልጎ ራሱን ከእግዚአብሔር አብ ጋር አስተካከለ እንጂ፤ በዚኽ መልኩ እንድረዳው ባይሻ ኖሮማ ራሱን በመነጠል ያቀርብ ነበር” (ኖቬሺያን)
☞ “ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደኾነ የካደ ሰው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ
(መቅደስ) ሊኾን አይችልም” (ቆጵርያኖስ (ሲፕርያን ዘካርቴጅ (ዘቅርጣግና))
☞ “የሕያው አካላዊ ቃል አባት አንድ እግዚአብሔር አለ፤ ርሱም ሕያው ጥበብ፣ ኀይልና ዘላለማዊ አካል ያለው፤ ፍጹም የኾነው ወልድን አካል ዘእምአካል
ባሕርይ ዘእምባሕርይ የወለደ የአንድያ ልጁ የባሕርይ አባት ነው፤ አንድ ጌታ
ከብቸኛው ከአብ የተገኘ ዋሕድ፤ ከእግዚአብሔር የተገኘ እግዚአብሔር፤ አባቱን በመልክ የሚመስለው በባሕርይ የሚተካከለው፤ ከሃሊው ቃል፤ የኹሉም ነገር መሠረትና ማጠቃለያ የኾነ ጥበብ ባለቤትና የፍጥረታት ኹሉ አስገኚያቸው፤
የእውነተኛው አብ እውነተኛ ልጅ ወልድ፤ ከማይታይ የተገኘ ኅቡእ፤ ኅልፈት
ውላጤ ከሌለበት የተገኘ ኅልፈት ውላጤ የሌለበት፤ ከማይሞት የተገኘ ሕያው፤
ከዘላለማዊ የተገኘ ዘላለማዊ … እናም ወልድ ፈጽሞ አብን ወደ መኾን
አይለወጥም፤ መንፈስ ቅዱስም ወልድን ወደ መኾን አይለወጥም፤ ግን ያለምንም ልዩነት እና ያለምንም ለውጥ በእግዚአብሔርነት የተካከሉት ሥላሴ
ለዘለዓለም ይኖራሉ” (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት)
☞ “እንግዲኽ የኾነ አንድ ቁጡ፤ የተናደደ እና የተደሰተ ሰው የእናንተ አምላክ
ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው? ብሎ ሊል ይችላል፤ በርግጥም ርሱ እግዚአብሔርና የተሰወሩት ኹሉ ኀይላት አምላካቸው ነው ብለን እንመልስለታለን” (አርኖቢዩስ)
☞ “ዝ ውእቱ ዘአጥፍኦ ለሞት ወሠዐሮ ለዲያብሎስ ዘምስሌሁ እዘዘ ሞት
በትንሣኤሁ ባሕቲቱ እግዚአብሔር ዘኮነ ሰብአ ወአስተርአያ በአርአያ ብእሲ” (ሞትን ያጠፋው ከሙታን ተለይቶ በመነሣቱ የሞት ሥልጣን የነበረው
ዲያብሎስን የሻረው ርሱ ነው፤ ሰው የኾነ በሰው ባሕርይ የተገለጠ እግዚአብሔር ነው) (ቅዱስ አትናቴዎስ)
☞ “ዝንቱ ዘበአማን እግዚአብሔር ወወልደ እግዚአብሔር ወውእቱ እግዚእ ቡሩክ ላዕለ ኲሉ…” (ርሱ በእውነት እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ ከኹሉም በላይ የሚኾን የባሕርይ ገዢ ነው…) (ቅዱስ አትናቴዎስ)
☞ “ወውእቱ እግዚአብሔር ዘቦቱ ልደት በሥጋ በሕማማት ዲበ ዕፀ መስቀል
ወመዊት ወትንሣኤ” (በሥጋ መወለድ በመስቀል መከራ መቀበል መሞት፣
መነሣት ገንዘቡ የኾነ ርሱ እግዚአብሔር ቃል ነው) (ቅዱስ ፊልክስ)
☞ “ተፈሥሒ ኦ ማርያም ምድር ቅድስት ዘበጽሐኪ እግዚአብሔር እንዘ ይጼዐን
ዲበ ደመና ብሩህ ወቦአ ውስቴትኪ፤ ተፈሥሒ ኦ ማርያም ዘአስተርአየ እምኔኪ
እግዚአብሔር ዘየዐርፍ በቅዱሳኒሁ፤ ተፈሥሒ ኦ ማርያም ዘሠምረ እግዚአብሔር ዘሀሎ እምቅድመ ዓለም ይትወለድ እምኔኪ ቃል ዘንሰግድ ሎቱ ምስለ አብ ወመንፈስ ቅዱስ” (እግዚአብሔር በብሩህ ደመና ኾኖ ወደ አንቺ የመጣ፤ በአንቺም ያደረ ምድር ቅድስት ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ በቅዱሳን ዐድሮ የሚኖር እግዚአብሔር ቃል ከአንቺ ተወልዶ የተገለጠ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የምንሰግድለት ቃል ከአንቺ ይወለድ ዘንድ ዓለም ሳይፈጠር የነበረ እግዚአብሔር አንቺን የወደደ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ) (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ)
4 374
🌾✞ #እናት_አለኝ ✞🌾
እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነምህረት ኪዳነምህረት
ኪዳነምህረት አንባ መጠጊያ ናት
ሔዋን ሰታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጓ እናቴ ቤተን አድምቀሻል
#አዝ---
ለዘላለም ንጽህይት በመሆኗ
ከኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሀዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
#አዝ---
ከጥፋቱ ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በህይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
#አዝ---
በእናትነት ህይወቴን ጎብኝታው
ልቤ አረፈ ተነቀወሎ በሽታው
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዮ በልጅሽ ጣፈጠ
#አዝ---
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
✞ #ኪዳነ_ምሕረት_የእረፍቴ_እናት ✞
ኪድነ ምሕረት የእረፍቴ እናት
ሠላም ሆነ በአንቺ አማላጅነት
ንጽሕት ድንኳን በዕምነት የአጌጥሁብሽ
ሠላም ሆነ በአማኑኤል ልጅሽ/፪/|//፪//
#አዝ---
የብርሐን ዝናር በአይኖረኝም
በንጉሥ ፊት ተሸልሜ ብቆም
በልጅሽ ነው ውበቴ ማማሩ
በምልጃሽ ነው ሥሜ መቀየሩ
በልቤ ላይ ተነበበ ልጅሽ
አዎ ሥሜ ተጠርቷል በልጅሽ
ከታች በምድር እስከ ሠማያት ድረስ
ድርሻዬ ነው ሥምሽን ማወደስ/፪/
#አዝ---
የከበረ ሆነሽ ንግግሬ
ቅኔ አነሳሁ ለክብርሽ ዘምሬ
እንደ ዝግባ ከፍ ብዬ ብታይ
ወጥቶልኝ ነው በሠማይ ጸሐይ
ሥለ ምልጃሽ ዘይቱ ፈሠሠ
አንቺን ይዤ ሙሽራው ደረሠ
ቀንዲሌ ነሽ ድንግል አዛኝቱ
በልጅሽ ነው የነፍሴ ጽናቱ/፪/
#አዝ---
ከኤልያብ ቢደምቅ ደም ግባቴ
ማን ሊመርጠኝ ያለ አንቺ እናቴ
ተዋብሁብሽ ነፍሴ በአንቺ አበራ
አንደበቴ ሥምሽን ሲጠራ
እንደ ሙሴ እንደ አሮን በትር
ማምለጫዬ ከፈርዖን ቀንበር
ከእንግዲኽማ እኔ እንዴት አዝናለሁ
አማላጄ አንቺን ይዤሻለሁ/፪/
#አዝ---
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾✞ #ኪዳነ_ምሕረት_እመቤት ✞🌾
ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት/፪/
ነይልን ነይልን ከአለንበት/፪/
#አዝ---
ከሠማያት በላይ ከአለው ከማደሪያሽ/፪/
ዝማሬ ከሞላው ከዘለዓለም ቤትሽ
የምድር ፍጥረታት ማርያም ማርያም ሲሉሽ /፪/
የቃል እናት እመቤቴ ነይ በሠረገላሽ /፪/
#አዝ---
ከጸጥታ ወደብ ከፍቅር አውድማ /፪/
ከሰላሙ መንደር ከእውነት ከተማ
ሰአሊ ለነ ቅድስት ውዳሴ ሲሠማ /፪/
ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር ነይልን ከራማ /፪/
#አዝ---
ዘርፋፋው ቀሚስሽ ይውረድ ከሠማያት/፪/
ዕንባችን ይታበስ በአንቺ አማላጅነት
በጽዮን ዝማሬ ተሞላ ነፍሳችን /፪/
ንዒ ንዒ ንዒ እንበል እንደ አባቶቻችን/፪/
#አዝ--
ፍጥረታት ሊድኑ በአማላጅነትሽ /፪/
የዘላለም ኪዳን አማኑኤል ሰጠሽ
ትውልድ ይኽን አምኖ ብጽዕት ይልሻል/፪/
እናቴ መመኪያዬ ምርኩዜ ሆነሻል /፪/
#አዝ---
የልብን ሲያዋዩሽ ሠምተሽ ዝም አትይም/፪/
ችግረኛን አይቶ ልብሽ አይጨክንም
ከዓይን ጥቅሻ ፈጥነሽ ትደርሽለታለሽ /፪/
ከሐዘን ከመከራ ታሳርፊዋለሽ /፪/
#አዝ---
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
#ድንግል_ሆይ_ስላንቺ
•••✞•••✞•••✞•••
ድንግል ሆይ ስላንቺ ነውና መሀሪ
አማልጅኝ ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ
ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ
ፊቱንም እንዳላይ ስራዬ አስቸገረኝ
#አዝ•••••••
ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ
ትዛዙን እንደሻርሁ ህጉን እንደጣስኩኝ
#አዝ•••••••
በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ
እለምንሃለሁ ከአሁኑ ይቅርታ
#አዝ•••••••
አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሳሪ
አማልደኝ ከጌታዬ ከፈጣሪ
#አዝ•••••••
ፃድቃን ሰማዕታት እናንተ ሁላችሁ
አማልዱኝ ከአምላኬ ከአምላካችሁ
#አዝ•••••••
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
ሀለዉ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ ወተቀበልዋ ኲሎሙ ነፍሳተ አበው እለ አዕረፉ እምአዳም እስከኔሁ ወሰገዱ ላቲ እንዘ ይብሉ ስብሐት ለእግዚአብሔር ዘፈጠረ ለነ ኪያኪ ሥጋ እምሥጋነ ወዐፅመ እምዐፅምነ” ይላል መላእክት አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉበትን የጻድቃን የማረፊያቸውን ቦታ ያሳዩዋት ዘንድ ወደ ገነት አሳረጓት፤ በዚያም ከአዳም ዠምሮ እስከዚያው ያረፉ ያባቶች ነፍሳት ተቀብለዋት “ከዐፅማችን አንቺን ዐጥንት ከሥጋችን አንቺን ሥጋ ለፈጠረልን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባው” እያሉ የአክብሮት ስግደት ሰግደውለታል፡፡
❖ ከዚያም መላእክት የጻድቅ ሰው ነፍስ ከሥጋው ሲለይ ያለውን ፍጹም ክብርና የሚወርሰውን የገነት ርስቱን መላእክት ካሳዩዋት በኋላ፤ ኃጥኣን ነፍሳቸው ከሥጋቸው ሲለይ ያላቸውን ጭንቅ ነፍሳቸው በሲኦል የምትቀበለውን ከፍተኛ መከራ አሳዩዋት፤ “ወሶበ ተስእኖሙ አምስጦ ይቤሉ እንዘ ይኬልሑ ኦ እግዝእትነ እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን ንዒ ኀቤነ ከመ ትፍትሕነ እማእሰሪሁ ለሰይጣን ወኢትኅድግነ” ይላል ለማምለጥ ባልተቻላቸውም ጊዜ “የመድኅን እናቱ የብርሃን መገኛ እመቤታችን ሆይ ከዚኽ ከዲያብሎስ ቊራኝነት ታላቅቂን ዘንድ ድረሺልን ቸል አትበዪ” እያሉ ምልጃዋን ሽተው በታላቅ ጩኸት ያለቅሱ ዠመር፡፡
❖ ያን ጊዜ ርኅርኅት የኾነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “ወይ ሎሙ ወአሌ ሎሙ መኑ እምዜነዎሙ ለውሉደ ሰብእ ኢይምጽኡ ዝየ” (ወዮላቸው ወዮታ አለባቸው ወደዚኽ እንዳይመጡ ለሰው ልጆች ኹሉ ማን በነገራቸው) እያለች ስታለቅስ፤ መላእክትም ለርሷ “ኢትፍርሂ ኦ ማርያም እስመ እግዚአብሔር ምስሌኪ ወምስለ እለ የአምኑ ብኪ” (እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ስለኾነና ባንቺ አማላጅነት ከአመኑት ኹሉ ጋር ስለ አለ አይዞሽ) በማለት ነገሯት፡፡
❖ ርሷም “እስእለከ እግዚኦ ወአስተበቊዐከ በእንተ ኲሉ ዘየአምን ብየ ረስዮ እግዚኦ ግዑዘ እምሲኦል ተዘኪረከ ረኃበ ወጽምዐ ወኲሎ መከራ ዘረከበኒ ኀቤከ ወምስሌከ” (አቤቱ በኔ ቃል ኪዳን ስላመነ ኹሉ እማልድኻለኊ እለምንኻለኊ፤ መራቤን መጠማቴንም ካንተ ጋር በምድረ ግብጽ ያገኘኝን ረኃብና ጥም ኹሉ አስበኽ አቤቱ ወደ ሲኦል ከመውረድ ነጻ አድርገው) በማለት ወደ ልጇ ፍጹም ልመናን አቀረበች።
❖ ጌታችን ተገልጾላት “ይኩን በከመ ትቤሊ እፌጽም ለኪ ኲሎ መፍቅደኪ አኮኑ ተሰባእኩ በእንተ ዝንቱ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ከመ ኢይሔሱ ኪዳንየ” (የለመሺዉን ኹሉ ይደረግልሽ፤ የምትፈቅጂውን ኹሉ እፈጽምልሻለኊ የለመንሺዉን ኹሉ ላደርግልሽ ሰው ኹኜአለኹና፤ መሐላዬን እንዳላፈርስ አማንየ በርእስየ ብዬ በራሴ ማልኹልሽ) ሲል ለእናቱ የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳንን ገብቶ ገብቶላታልና በዓሉ “ኪዳነ ምሕረት” በመባል ይታሰባል::
❖ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በዝማሬው ላይ ጌታ ለእናቱ ስለገባላት ቃል ኪዳን፡-
✍ “ይቤላ ለእ ማርያም እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተካየድኩ ምስሌኪ ኪዳነ ምሕረት ከመ አድኅን ዘተአመነኪ መሐልኩ ለኪ በርዕስየ ዘመሐልኩ አነ ለኖኅ ገብርየ ወለአብርሃም ፍቁርየ፤ ዘመሐልኩ አነ ለዳዊት ኅሩይየ ብእሲ ምእመን ዘከመ ልብየ መሐልኩ ለኪ በርዕስየ በቅዱስ ሥጋየ ወበክቡር ደምየ መሐልኩ ለኪ በርዕስየ ከመ ኢይሔሱ ማእኰትየ”
✍(ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ማርያምን እንዲኽ አላት በምልጃሽ ያመነብሽን አድን ዘንድ ካንቺ ጋራ የምሕረት ቃል ኪዳንን ተጋባኊ፤ ለአገልጋዬ ለኖኅና ለወዳጄ ለአብርሃም ቃል የገባኊ እኔ በራሴ ማልኹልሽ፤ እንደ ልቤ ለምለው ለታመነው ለዳዊት የማልኊ እኔ በራሴ ማልኹልሽ፤ በቅዱስ ሥጋዬና በክቡር ደሜ የማልኊ እኔ ምዬ እንደማልከዳ ማልኹልሽ) በማለት ጽፎታል፡፡
[በቀራንዮ ከፈጣሪያችን የተቀበልንሽ ስጦታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ልጅሽ ይቅርታውን ያድለን ዘንድ ለምኝልን]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
4 374
ኪዳነ ምሕረት
✍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ቃል ኪዳን” የሚለው ቃል 257 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፤ ኪዳን ማለት ቃል “ተካየደ” ከሚለው ከግእዝ ቃል የወጣ ሲኾን “ተዋዋለ፣ ተስማማ፣ ተማማለ” ማለትን ሲያሳይ እግዚአብሔር ሰውን ከማፍቀሩ የተነሣ ለሰው ልጅ እንደ ባልንጀራ አድርጎ መሐላን ይምላል፣ ቃል ኪዳንም ይገባል፡፡
❖ ክቡር ዳዊት በመዝ 88፡2-3 ላይ “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” እንዳለ ከኹሉም ቅዱሳን በላይ ኾና ሰማይ ምድር የማይወስኑትን አምላክ በማሕፀኗ ለመሸከም፣ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ የሚሸከሙትን ሰማያዊ መለኮትን በዠርባዋ ለማዘል፣ በክንዷ ለመታቀፍ፣ ሰማይ ምድር ከፊቱ የሚሸሹትን የባሕርይ አምላክን በከናፍሮቿ ለመሳም፣ ፍጥረታትን ኹሉ በዝናብ አብቅሎ በፀሓይ አብስሎ የሚመግበውን፤ ለቅዱሳን መላእክት ርሱ የገለጸላቸው ምስጋና ምግብ ኹኗቸው እንዲኖሩ ያደረገውን ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለውን እግዚአብሔር ወልድን የድንግልና ጡቶቿን ለማጥባት ከተመረጠች ከእናቱ ጋር የገባው ጽኑዕ የምሕረት ቃል ኪዳን እጅግ ልዩ እና ለኃጥኣን ኹሉ ተስፋ የሚኾን ነው፡፡
❖ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤልም በአምላክ እናት ፊት ቆሞ “ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝተሻልና አትፍሪ” በማለት ከፍጡራን ወገን ማንም ሊያገኘው የማይችለውን ይኸውም በልዑል እግዚአብሔር ዘንድ መወደድን በማግኘት ከባለሟልነት ኹሉ የላቀ ባለሟልነት ይኸውም የአምላክ እናት የመኾንን የማማለድ ልዩ ጸጋና ክብር እንደተሰጣት ነግሯታል፡፡
❖ መልአኩ በዚኽ ምስጋናው ላይ “ሞገስን አግኝተሻልና” አለ እንጂ “ወደ ፊት ታገኛለሽ” አለማለቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንቱኑ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የተጠበቀችና በልዑል የተመረጠች መኾኗን የሚያረጋግጥም ነበር፡፡ ከዚኽ ከተሰጣት ታላቅ ባለሟልነት የተነሣ ልጇን በማሳሳብ ውሃው ወደ ወይን እንዲለወጥ አስደርጋለች (ዮሐ 2፡1-10)፡፡
❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እንደምናነብበው በአምላካቸው ፊት ባለሟልነትን ያገኙ ብዙዎች ቅዱሳን ቢኖሩም ቅሉ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ግን ለነዚኽ ኹሉ ቅዱሳን ሰማያዊ ክብርን ቃል ኪዳንን የሰጠውን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና በመውለዷ “ወላዲተ አምላክ” የመባል ታላቅና ልዩ ባለሟልነት ተሰጥቷታልና የርሷ ክብር ከማንም ቅዱሳን ክብር ጋር ፈጽሞ የማይነጻጸር ነው፡፡
❖ ከ 432-447 ዓ.ም ሴሌኡሲያ ላይ ጳጳስ የነበረው ሊቁ ባስልዮስም እግዚአብሔር ለእናቱ የሰጣት ልዩ ባለሟልነትን ከቅዱሳን ጋር በማነጻጸር ሲጽፍ “What encomiums can we offer her as she deserves, when everything of this world is beneath her merits?...” (የሚመጥናትን ምን ዐይነት ልዩ ምስጋና እናቅርብላት? የዚኽ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና፤ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር “ዓለም አልተገባቸውም” (ዕብ ፲፩፥፴፰) ካላቸው፤ ለአምላክ እናትማ ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሓይ ለኾነችው ለርሷ ምን ልንል እንችል ይኾን? (ራእ ፲፪፥፩)... ምን ምስጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናንና አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነ አስተውል፤ ታዲያ የአምላክን እናት ታላቅነት ኹሉም ሰው እንደምን አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ላገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፤ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፤ ጴጥሮስ በጥላው ካደነ (የሐዋ ፭፥፲፭)፤ የጳውሎስ የልብሱ ጨርቅ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ (የሐዋ ፲፱፥፲፩)፤ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኀይል ተሰጥቷት ይኾን?
✔ ለቅዱሳኑ ይኽነን ያኽል ድንቅ እንዲያደርጉ ባለሟልነትን ከሰጣቸው ወልዳ ላሰደገችው እናቱማ ምን ያኽል ይሰጣት ይኾን? በምን ዐይነትስ ስጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ “ክርስቶስ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነኽ” ስላለው ብፁዕ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቊልፍ ከተሰጠው (ማቴ ፲፮፥፲፮-፲፱)፤ ርሷ ከኹሉም ይልቅ እንዴት የተባረከች (ብፅዕት) አትኾን? (ሉቃ ፩፥፵፭)፤ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ “ምርጥ ዕቃ” ከተባለ (የሐዋ ፱፥፲፭)፤ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች ርሷ ምን ዐይነት ልዩ ዕቃው ትኾን?
✔ ነገር ግን ስለርሷ ብዙ እናገራለኊ ብዬ ስለክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለኊ ስለዚኽ ካኹን ወዲኽ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጬአለኊ) በማለት በእግዚአብሔር ፊት የተሰጣት ባለሟልነት ፍጹም እንደኾነና ከቃላት በላይ እንደኾነ አስተምሯል፡፡
❖ ዳግመኛም ቅዱሳን መላእክትና ጻድቃን ካገኙት ሞገስ የተነሣ ወደ ፈጣሪያቸው እንዲያማልዱን ስንማጸናቸው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ግን የአምላክ እናት ናትና ካገኘችው ከዚኽ ታላቅ ባለሟልነት የተነሣ ወደተወደደው ልጇ እንድታማልደን እንማጸናታለን፤ ከዚኽም የተነሣ ነው ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬምም በእሑድ ውዳሴ ማርያም ላይ፦
✍ “ለኪ ይደሉ ዘእምኲሎሙ ቅዱሳን ትሰአሊ ለነ ኦ ምልእተ ጸጋ…” (ጸጋን የተመላሽ ሆይ ከቅዱሳን ኹሉ ይልቅ ትለምኚልን ዘንድ ላንቺ ይገባል፤ አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጪያለሽ፤ ከነቢያትም ከመምህራንም ትከብሪያለሽ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ፤ በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ) በማለት ያመሰገናት፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ካገኘችው ታላቅ ባለሟልነት የተነሣ ፭ሺሕከ፭፻ ዘመን ሲፈጸም ያለ ዘርዐ ብእሲ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በኅቱም ድንግልና የፀነሰች፤ ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመች፣ በኅቱም ድንግልና የወለደች፣ በክንዷ የታቀፈች፣ በጀርባዋ ያዘለች ርሷ ብቻ ናትና፤ በርሷ አማላጅነት የምናቀርበው ጸሎት ምን ያኽል ታላቅ እንደኾነ በሰዓታት መጽሐፉ ላይ፡-
✍“ወፈድፋደሰ በእንተ ማርያም እምከ እንተ ይእቲ ትምክህተ ዘመድነ …” (ይልቁንም የባሕርያችን መመኪያ ስለምትኾን ስለ እናትኽ ስለ ማርያም አንተን በመፅነስና አንተን በመውለድ ዕድፍ ጒድፍ ስላላገኘው ስለ አልተለወጠ ድንግልናዋና ስለ ተሸከመኽ ማሕፀኗ፤ ስለ ታቀፉኽ ስለ ክንዶቿና፣ ስለ ዳሰሱኽ ስለ እጆቿ፤ ስለ ሳሙኽ ስለ ከንፈሮቿ ስለ አሳደጉኽ ስለ ጡቶቿ፤ ከአንተ ጋር ስለ ተመላለሱ ስለ እግሮቿና፤ ስለ ዐዘለኽ ስለ ጀርባዋ፤ ብሩሃት ስለሚኾኑ ስለ ዐይኖቿ በጎ መዐዛ ስላላቸው አፍንጮቿ፤ ጸዐዶች ስለሚኾኑ ጥርሶቿ፤ በመልአኩ በገብርኤል ቃል ስለ ተበሠሩ (ብሥራትን ስለ ሰሙ) ስለ ጆሮቿ፤ ከርሷ ስለነሣኸው ሥሮችና ጸጒር፣ ደምና፣ ዐፅም ስለ ነፍስና ሥጋ፤ አባቶቻችን እንደ አስተማሩን ፈጽሞ ያለመለየትና ያለመለወጥ ከመለኮትነትኽ ጋራ አንድ ያደረግኸው) በማለት እንዳስተማረ፤ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ባለሟልነት እንዳገኘች በብርሃናዊዉ መልአክ የተመሰከረላት የአምላካችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን ከልጇ ታማልደን ዘንድ “ሰአሊ ለነ ቅድስት” (ቅድስት ሆይ ለምኝልን) እያልን እንማጸናታለን፡፡
❖ ይኸውም ታላቁ የነገረ ማርያም መጽሐፍ እንደሚያስረዳን ጌታችን ካረገ በኋላ እመቤታችን ጌታችን ወደ ተቀበረበት ጎልጎታ እየኼደች ትጸልይ ነበር፤ ከዕለታት ባንዳቸው በየካቲት ፲፮ ዕለት ስትጸልይ “አዕረግዋ ውስተ ሰማይ ከመ ያርእይዋ መካነ ዕረፍቶሙ ለጻድቃን ኀበ
4 374
✞✟ #መዳናችን_በማን_ነው?
#በክርስቶስ_ወይስ_በራ(የፀሐይ_አምላክ)
#ምልክታችን_ተ_ነው_ወይስ_ቶ? ✟✞
✅በዚህ ባለንበት የምናውቀውንና የምናምነውን በድርጊታችን መሌት የግድ ነው፡፡ ዘመኑ የእውቀት ዘመን ብቻ ሳይሆን የውዥንብርና የጥቅም ዘመን መሆኑ ማስተዋል ያሻል፡፡ መነሻቸውና መድረሻቸው ያልታወቀ ጽሑፎች መጻሕፍት ሃይማኖታዊ ቅባት ተቀብተው የቤተ ክርስቲያን የሚመስል ቅጥያ ስም ያላቸውና ደራሲያንና ፀሐፊዎች ከዚህ ውጭ የሆኑ መጻሕፍት እምነትንና ምርምርን ቀላቅለው መስቀልን ከተዛባ የአምልኮ ጣዖታት አርማዎች "ቶ" ጋር ተቆራኝቶ እንዲታይ ለማድረግ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዚህም በርካታ የአማርኛ ልብ ወለድና ታሪክ ሃይማኖት ቀመስ መጻሕፍት ተጽፈዋል፡፡ እነዚህ መጻሕፍት የክርስቲያኖች የሃይማኖትና የእምነት መጻሕፍት የሆኑትን የብሉያትናና የሐዲሳትን ዋጋ የሚሳጡ ሃሳቦችንና የጣዖታት ታሪክ ከያዙ የአርኪዮሎጂ የምርምር መጻሕፍት የተቀዱ ከ"ኢጅፕቶሎጂስት" ሥራዎችን የሚመነጩ ናቸው፡፡ እነዚህ የግብፅ ጣዖታት የእግዚአብሔር አገልጋይ በሆነው ነብዩ ሙሴ የተሸነፉ ናቸው፡፡ እነዚህ የ "ቶ" ታሪኮች የሚቀበል ክርስቲያን በኦሪት ዘፀአት ያሉት የእግዚአብሔር ኃያልነትና ነፃ አውጪነት፤ የወንጌል መንደርደሪያ የቤተ ክርስቲያን አጀማመር ፍንጮችን የማይሻር እውነትነት ሙሉ በሙሉ መካድ ነው፡፡
✅ከሁሉም በላይ ከእግዚአብሔር፤ በቀር በሥነ ፍጥረት ይሁን በእጅ በተሠራ
ማንኛውም ማምለኪያ እንዳናመልክና ምልክት እንዳይሆነን በሙሴ በኩል
ተምረናል፡፡ "ራ" ወደ ምሥራቅ ተዙሮ ሲወጣ ሦስቴ ይሰገድለታል፡፡ አማልክት
በሚያውቁት ስሙ ተጠርቶ ሲለመን በእጆቹ ጨረር "ቶ" ያድላል የህይወት
ጥበብ ኃይል ይሰጣል ማለት ነው፡፡ የጣዖታት ካህናት ይህን "ቶ" ይይዙታል፡፡ "ራ" "በአምላካዊ" ቁመና በፀሐይ ውስጥ ሆኖ በፀሐይነቱ "ቶ" ይይዛል፡፡
በሂሎግራፊያ ወይም በሱፊ የሚባሉ ጥንታውያን ጽሑፎችም ደግሞ ሆሄ ነው፡፡
✅ይህ "ቶ" በግብፆች "ቶ" የሚባል የ "ራ" የፀሐይ አምላክ አገልጋይ ከአማልክት ሁሉ አዋቂው ብልሃተኛው ጠቢቡ ከሁሉም በላይ ኃይለኛው ነው፡፡ የ "ራ" እውቀቱና ኃይሉ በመሆኑም ከ "ራ" አይለይም "ራ" ሁልጊዜ በቀኝ እጅ የማይዘው "ቶ" አገልጋዩን ነው፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችንስ ማን ነው የጌታችንና
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልስ "ቶት" ነው? በመስቀል ያገኘነውስ ምንድነው? እንደ ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ "ቶ" ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጋር ቀርቶ ከክርስትና ጋር ምንም ግንኑነት የሌለው ነው፡፡ በታሪክ ውስጥ በጥንታውያን ክርስቲያኖች በተለይ በግብፅ ክርስቲያኖች ዘንድ ጥቅም ላይ ውሎ የማያውቅና ያልዋለ በሙሴ የተሸፈነው የፈርኦኑ ጠንቋዮችና ካህናት እውቀትና ኃይል ነው፡፡ የ "ቶት" አርማ በዘመናችን ደግሞ የፆታ ምልክት ነው፡፡ በሌላ በኩልም የሰዶማውያን ማኅበር አስጎብኚ ስም ነው፡፡ ሌላም ይኖራል፡፡
✅እነዚህን የጣዖቱ የቶት ምልክት ባንገታቸው ያሰሩ ወጣቶች ክርስቲያኖች
በማወቅም ባለማወቅም ሊሆን እንደሚችል ስንገምት ይህ ግምታችን እነዚህን ጣዖቶች የሚሰሩ ባለሙያዎችም ሆነ በቤተ ክርስቲያኑ ደጀሰላም የሚሸጡ ነጋዴዎችም ጣዖት እየሸጡ መሆኑን ልብ ማለት አለባቸው፡፡ ይህ "ቶት" ከቤተክርስቲያን ጋር ምንም ግንኙነት ሳይኖረው የእጅ መስቀል ተሰርቶለት በአንዳንድ ያላወቁ ካህናት እጅ መግባቱም መታወቅ አለበት፡፡
✅በማተባችን የምናስረው መስቀል ግን በዘወትር ፀሎታችን የማናከብረውና
የምንሰግድለት በጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም የከበረ የተባረከና ድውያንን የሚፈውስ መስቀል ነው፡፡ ይህ መስቀል የክርስቲያኖች ክርስቲያናዊ ሕይወት ነው፡፡ የሥርዓተ አምልኮአችን ዋና አካል ነው፡፡ በልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ቤተ ክርስቲያን በካህናቶችዋ የምትገለገልበት
መስቀል የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ነው እንጂ
የጣዖት "ቶት" አይደለም፡፡
✅መስቀልን በተመለከተ ከቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ "መስቀሉን የካደ የሰይጣን ልጅ ነው" ሲል ሌሎች አባቶችም ለመስቀሉ ያላቸውን ፍቅር በልዩ ልዩ ጽሑፎች ገልጸዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድም ዜማ ደርሶለታል፡፡ ሊቃውንትም ቅኔ ይቀኙለታል ቤተ ክርስቲንም ለመስቀሉ በዓላት ሰርታለች ለመስቀሉ ለተደረገው ጦርነት እስካሁን የሕርቃልን ፆም ትፆማለች፡፡ መስቀሉ በልዩ ፍቅር በልዩ ልዩ ንዋያተ ቤተ ክርስቲያንና በእናቶች ቀሚስ በመስቀል በሃረግ እስካሁን ይሰራል፡፡
✅ለሁሉም ስለመስቀል ቅዱስ ጳውሎስ ከመስቀሉ ፍቅር የሚለየን ማን ነው ሞት
ነው? ረሃብ ነው? ወይስ ሥቃይ ብሎናል፡፡ አሁንስ ከመስቀሉ ወደ "ቶት" የቀየረን ምንድነው? እውቀት፣ ድንቁርና፣ ያልገባን አዲስ ምንነት እስቲ እናስተውል "ቶት" አንገት ላይ ማሰር ማለት ግን ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም አልተወለደም፣ አላስተማረም፣ አልተሰቀለም፣ አልተነሳም፣ አላዳነንም
ብሎ ማመን መሆኑ እንወቅ ከዚህ የዝምታ ክህደት ራሳችንን እንጠብቅ፡፡
🙏"ወስብሐት ለእግዚአብሔር"🙏
ከሰሎሞን ኃ/ማርያም (መ/ር)
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ጸሐፊ (Phd candidat)
Copyright © 2015 Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Patriarchate Head Office Sunday School Department. All Rights Reserved.
4 374
ጠራው፣ የሚያጸድቀው የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብ
ሔር መኾኑን በትክክል ካስረዳ በኋላ በመቀጠልም ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ ባባቱ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ መቀመጡን “የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው” በትክክል አስተማረ፤ ሞትን ድል አድርጎ ስለመነሣቱም ፊተኛው እና ኋለኛው ርሱ ስለመኾኑ ራሱ ጌታ “ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ” በማለት ይኽነን እውነት እንዲጽፍ ለዮሐንስ እንዳዘዘው ቅዱስ ጳውሎስም እውነቱን መሰከረ፡፡
ወንጌላዊ ማርቆስም ስለዚኽ ነገር “ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ” (ማር 16፡19) በማለት ባባቱ ዕሪና መቀመጡን እንደነገረን ቅዱስ ጳውሎስም በድጋሚ ይኽነን አስተማረ፡፡
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት አስቀድሞ፡- “እግዚአብሔር ጌታዬን፡- ጠላቶችኽን በእግርኽ መረገጫ እስካደርግልኽ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው” ብሎ እንደተነበየ /መዝ.፻፱ (፻፲)፡፩/ በአብ ቀኝ ተቀምጧል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ይኽ ትንቢት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንደተፈጸመ አስተምሯል /ዕብ.፲፡፲፪/፡፡
ዓምደ ሃይማኖት የተባለው ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ የሉቃስ ወንጌልን በተረጐመበት ፳፬ኛው ምዕራፍ ላይ ይኽን በተመለከተ ሲናገር እንዲኽ ይላል፡- “ደቀ መዛሙርቱን ከባረካቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በአባቱ ቀኝ (ዕሪናም) ተቀመጠ፡፡ የተቀመጠውም በባሕርየ መለኮቱ ብቻ አይደለም፤ በተዋሐደው ሰውነቱም ጭምር እንጂ፡፡ አካላዊ ቃል ባሕርያችንን ሲዋሐድ እኛን ወደዚኽ ክብር ለመመለስ ነበርና፡፡ … እግዚአብሔር ሲኾን ስለ እኛ ሰው ኾነ፡፡ በፍቃዱ መከራ መስቀልን በተዋሐደው ሰውነቱ ተቀበለ፡፡ በተዋሐደው ሰውነቱ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ በተዋሐደው ሰውነቱም ዐረገ፡፡ በሕያዋንና በሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድም ዳግመኛ በክበበ ትስብእት ይመጣል” /Commentary on Luke, Chap.24/፡፡
አኹን ለመለኮት የተገደበ የተወሰነ ቀኝ ግራ ፊት ኋላ አለው ማለትም አይደለም ቀኝ ማለት ኀይል ምልአትን በዕሪና መተካከልን የሚያመለክት ብቻ ነው ሊቁ “እስመ ብሂለ የማን ይመርሕ ኀበ ተዋሕዶቶሙ ወዕሪናሆሙ በክብር” (ቀኝ ማለት በክብር መተካከላቸውን ተዋሕዶቸውን ያመለክታል) እንዳለ፤ እንግዳን “ንበር” (ተቀመጥ)፤ ይሉታል እንጂ እንደ ባለቤት “ነበረ” (ተቀመጠ) እንዳይሉት ለዐይን ጥቅሻ እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስ ከክብሩ አልተለየምና “ነበረ” ይለዋል፤ ለዚኽ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ 1፡3 ላይ “በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” በማለት የጻፈው፡፡
እስኪ እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ ቀኝ የሚለውን ኅሊናን በመሰብሰብ እንየው፡፡
“እግዚአብሔር ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው እግዚአብሔር የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል በጠላቶችህም መካከል ግዛ” (መዝ 109፡1)
“እኔ ነኝ እኔ ፊተኛው ነኝ እኔም ኋለኛው ነኝ እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ (መዝ 48፡12-13)
እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል? ማቴ 22፡43-44
“አቤቱ፥ ቀኝህ በኃይል ከበረ” (ዘፀ 15፡6)
“አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? ቀኝህን ዘረጋህ፥ ምድርም ዋጠቻቸው” (ዘፀ 15፡11-12)
“የእልልታና የመድኃኒት ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች” መዝ 117፡15-16)
“ኢየሱስም፦ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ” ማር 14፡62 ይላል፡፡
በመኾኑም ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱሳን ሐዋርያቱን የጠራው የሚያጸድቀው የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ስለመኾኑና ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ በአብ ቀኝ (ዕሪና) እንዳለ ከገለጸ በኋላ በዕለተ ዐርብ ባደረገው የድኅነት ምስጢር ዓለምን አድኖ ዋጋችንን የሰጠን ዳግመኛም በታላቅ ጌትነት ለፍርድ ተመልሶ የሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና “ደግሞ ስለ እኛ የሚፈርደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” በማለት በትክክል ተናገረ እንጂ፤ ምክንያቱም ከላይ ዠምሮ የጥቅሱን ሐሳብ እንዳየነው ሙሉ ነገሩ የክርስቶስን እግዚአብሔርነት፣ መራጭነት፣ አጽዳቂነት፣ ኰናኝነት፣ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት፣ በአብ ዕሪና መቀመጥ ብቻ ነው፤ ታዲያ ራሱ ክርስቶስ ፍጹም እግዚአብሔር ከኾነና በአባቱ ዕሪና ከተቀመጠ በኋላ አንሶ ወደ ማን ሊማልድ ነው ይባላል? ወደ አብ ወደ መንፈስ ቅዱስ እንዳንል በአምላክነት፣ በፈጣሪነት፣ በቅድምና፣ በእግዚአብሔርነት፣ በዕበይ፣ በመንግሥት፣ በሥልጣን፣ በመመለክ፣ በመመስገን፣ በገናንነት፣ በክብር፣ በኀይል፣ በክሂል፣ በፈቃድ፣ በትእዛዝ አንድ ናቸው፡፡
ስለዚኽ ከጊዜ በኋላ እነዚኽ ቀሳጮች ምስጢረ ሥላሴን አፋልሰው የማይለየውን አንድነት ለመበታተን እንዲመቻቸው በማድረግ አስገብተውበታል እንጂ ክብር ይግባውና ጌታስ በዘመነ ሥጋዌዉ በዕለተ ዐርብ ባደረገው ተልእኮ ዓለምን ከራሱ፣ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀ ዳግመኛም ታረቀ ከዚያም የማስታረቅን ቃል ለሐዋርያት ሰጥቶ በክብሩ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድ በጌትነት ይመጣል እንጂ አኹንም እንደገና ያደነውን ዓለም እንደገና እንዳልዳነ አኹንም መልሶ ይማልዳል ማለት ሎቱ ስብሐት ጠላት ዲያብሎስ የዘራው መርዝ ኑፋቄ ክሕደት ነው፡፡
ለዚኽ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በ2ቆሮ 5፡18-20 “ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን” በማለት የማስታረቅ አገልግሎት ለቅዱሳን ሐዋርያት ለቤተ ክርስቲያን አበው የተሰጠ መኾኑን ትክክለኛውን ትምህርት ያስተማረው፡፡
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ሌሎችም በተጠራጣሪዎች የሚነሱ ጥቅሶችንም ወደፊት ተንትነን እናያለን፡፡
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
ነገረ ክርስቶስ ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የቀናውን እውነት የኾነውን የሐዋርያትን ትምህርት ሳትበርዝ ሳትከልስ ሳትቈራርጥ ያስተማረችውን በደምህ የመሠረትካትን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንን ጠብቅልን አሜን✞✞✞
🌻💐🌹 #Join us... 🌹💐🌻
🌻💐🌹 #Share it...🌹💐🌻
❀✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞❀
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @EOTC2921 👈
👉 @EOTC2921 👈
👉 @EOTC2921 👈 👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
4 374
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
#አንብበው #share⇩ ያድርጉ
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
【የመናፍቃን የሮሜ 8፡34 የማታለያ ጥቅስ ሲጋለጥ】
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር)
👉የኢየሱስን የባሕርይ አምላክነትና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ መኾኑን ለማመን የተቸገሩና ፈራጅነቱን የካዱ ተጠራጣሪዎች ከሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አንደኛው በሮሜ 8፡34 ላይ ያለው ኀይለ ቃል ነው፡፡ ይኽ “እስመ ለሊሁ ያጸድቅ መኑ ዘይኴንን ክርስቶስ ሞተ ወተንሥአ እሙታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር ወይትዋቀስ በእንቲኣነ” (ርሱ ሲያጸድቅ የሚፈርድ ማነው ክርስቶስ ሙቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል) የሚለው የጠራው የግእዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ኀይለ ቃል በተለየ መልኩ በዘመናት ኹሉ ለዚኽች ቤተ ክርስቲያን መቼም ቢኾን መልካም ዐስበው በማያውቁ ይልቁኑ ፈራርሳ ቢያይዋት ደስ በሚሰኙ የክርስቶስን ፈራጅነት በካዱ በባሕር ማዶ ቀሳጮች ብዙ ጊዜ ተሰርዞ (ይማልዳል) በሚል ተቀይሮ እናነብባለን፡፡
ለምስክርነት እስቲ እንይ፡-
👉በ1938 ዓ.ም ታትሞ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ “ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ፤ በአብ ቀኝ ተቀምጧል፤ ስለእኛም ይፈርዳል” ይላል
👉በ1975 ዓ.ም ታትሞ ከግእዙ ወደ ዐማርኛው የተመለሰው “ርሱ ሲያጸድቅ የሚፈርድ ማነው ክርስቶስ ሙቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል” ይላል፡፡
👉በ1980 ዓ.ም ግእዙን የሚያውቁ ዐይናማ ሊቃውንት ሳያዩት በጥቂቶች አስተባባሪነት የክርስቶስን ፈራጅነት በማያምኑ በምዕራባውያን የዶላር ድጋፍ የታተመው ደግሞ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” ይላል፡፡
ይኽ ዕትም ችግሩ ይኼ ብቻ ሳይኾን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ የተጻፈበትን የግሪክን ቋንቋ እና ቀደምት የተተረጎመትን የግእዝ፣ የሶርያ፣ የአርመን፣ የቅብጥ ቅጅ በተለይ በግሪክ የተጻፈውን የ1900 ዓመት እድሜ ያለውን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ከማየት ይልቅ እንግሊዞች እንዲመቻቸው አድርገው ቃላቱን በድፍረት እየጨመሩና እየቀነሱ በ1611 ዓ.ም ያሳተሙትን የ400 ዓመት ዕድሜ ያለውን የኪንግ ጀምስ ቅጂን ወደ ዐማርኛ ተርጒመው ለማቅረብ ሞክረዋል፤
በዚኹ በሮሜ 8፡27 ላይ “ወባሕቱ መንፈስ ለሊሁ ይትዋቀስ ለነ በእንተ ሕማምነ ወምንዳቤነ ወውእቱ የሐትቶ ለልብነ ወየአምር ዘይኄሊ መንፈስ ወይትዋቀስ በኀበ እግዚአብሔር በእንተ ቅዱሳን” (ርሱ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ይመልስልናል፤ ርሱ ልቡናችንን ይመረምረዋል፤ ልብ ያሰበውን ርሱ መንፈስ ቅዱስ ያውቃል፤ በእግዚአብሔር ዘንድም ለቅዱሳን ጸሎት መልስ ይሰጣል) የሚለውን ገጸ ንባብ ለውጦ በድፍረት “ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ ዐሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና” በሚል በድፍረት ቃሉን በመለወጥ መንፈስ ቀዱስንም አማላጅ አድርገው መንፈስ ቅዱስን በመናቅ አሳትመውት እናነብባለን፡፡
ይኽ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ የተጻፈውን ቅዱስ ቃል ሰዎች እንደገዛ ፈቃዳቸው አጣምመው ለማቅረብ የሚሞክሩ ቢኾንም እስቲ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 8፡33-34 ላይ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ …… ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” የሚለውን ኀይለ ቃል በዝርዝር ዐይተን ሰዎች በተለያየ ጊዜ የጨመሩበት በባዶ ቦታው ላይ ያለው በእውነት ስለምን እንደሚያስገነዝብ መረዳት እንችላለን እስቲ ከዚኽ በታች እንየው፡-
“እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?”
ቅዱስ ጳውሎስ በዚኽ ምዕራፉ ላይ በትክክል እንዳስቀመጠው እግዚአብሔር መራጭ እንደኾነ ነው፤ ከላይ በትክክል እንዳየነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደሰፈረው ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ በእውነት እግዚአብሔር እንደኾነ የታወቀ የታመነ የተረጋገጠ ነውና ስለዚኽ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” በማለት የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት አረጋግጦ ጻፈ፤ የመረጣቸውስ ማንን ነው ቢሉ “ንዑ ትልዉኒ” (ኑ ተከተሉኝ) ብሎ የጠራቸው ብሎ ሐዋርያትን፤ ዳግመኛም 72ቱ አርድዕትን፣ 36ቱ ቅዱሳት አንስትን ነው፤ ይኽነንም ወንጌላዊዉ ማቴዎስ “ዐሥራ ኹለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ርሱ ጠርቶ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ኹሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው” በማለት ፲፪ቱ ሐዋያትን እንደጠራና ሥልጣንን እንደሰጣቸው በትክክል አስቀመጠ፡፡
ራሱ ቅዱስ ጳውሎስም በዚኹ ምዕራፍ ቊ፴ ላይ “አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው” በማለት ሐዋርያት ሰብአ አርድዕት እያለ የሾማቸው ስምዖን የተባለውን ጴጥሮስ ልብድዮስ የተባለው ታዴዎስ፤ ዲዲሞስ የተባለውን ቶማስ እየለ የጠራ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መኾኑን መሰከረ፡፡
“የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው” በማለት የጠራቸውን የሐዋርያት ነገራቸው ወንጌልን በተአምራት እያስረዳ እያጸደቀ እውነት መኾኑን ሰዎች እንዲያውቁት ያደረገው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መኾኑን አስረዳ፡፡ ከዚያም “ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው” የጠራቸው ሐዋርያቱን በዚኽም ዓለም በተአምራት በወዲያኛውም ዓለም “እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ” (ማቴ 19፡28) በማለት ያከበረው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን በትክክል እንዳስተማረ በቊ 32 ላይ ላይም “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” በማለት ማንም ሊወቅሳቸው የማይችለውን ቅዱሳን ሐዋርያትን የመረጠው ፍጹም እግዚአብሔር የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን ገለጸ፡፡
የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?
ቅዱስ ጳውሎስ በትክክል በዚኽ ላይም ማጽደቅ እና መኰነን የሚችል ርሱ ልዑል እግዚአብሔር እንደኾነ በትክክል አስቀምጧል፤ እውነት ነው ዓለምን በታላቅ ግርማ አሳልፎ መላእክቱን አስከትሎ በዙፋኑ ተቀምጦ ለኹሉም እንደ የሥራው የሚከፍለው፤ ጻድቃንን በቀኙ አቁሞ “እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” ብሎ የሚያጸድቅ፤ በግራው የቆሙትን ኃጥኣንን ደግሞ “እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” በማለት የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም እግዚአብሔር መኾኑን በትክክል ገለጸ፡፡ ራሱ ጌታ “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል” በማለት እንዳስተማረን (ማቴ 25፡31-46)፡፡ ታዲያ ማጽደቅና እና መኰነን የፍርድ ሥራ እንጂ የማማለድ ሥራ ነውን በፍጹም አይደለም፡፡
“የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው”
ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያትን የ
4 374
🌿🌾✞ #ቅዱስ_ላሊበላ ✞🌾🌿
📖ሰኔ ፲፪
✅ቅዱስ ላሊበላ የተወለደው በላስታ ሮሃ ቤተመንግሥት በዋሻ እልፍኝት ውስጥ ታህሳስ ፳፱ በ፲፩፻ወ፩ ዓ/ም ሲሆን በዛሬው ዕለት ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ ያረፈበት ነው።
✅ይህ ቅዱስ ጌታችን የጠጣውን መራራ ሐሞት እያሰበ ዓርብ ዓርብ ኮሶ ይጠጣ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ ቅዱሳን መካናትን፤ ወደ ሰማይም ወስዶ የቤተ መቅደሶቹን አሠራር አሳይቶታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሚሠራበትን እግዚአብሔር እንዲገልጥለት ሱባኤ ቢገባ ቤተ ማርያም ከተፈለፈለችበት ቦታ የብርሃን ዐምድ ተተክሎ አይቷል።
✅ቅዱስ ላሊበላ ጎጃም በመሔድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን ተምሯል። ላሊበላ ከወንድሙ ቀጥሎ እንደሚነግሥ ትንቢት ተነግሮ ስለነበር ንጉሡ ሊገድለው ምክንያት ይፈልግበት ነበር፡፡ በእናትም በአባትም እኅት የምትሆነው፣ ለላሊበላ ግን በአባት ብቻ እኅት የሆነችው ላሊበላን ለመግደል አጋጣሚ ትጠብቅ ነበር፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ጌታችን መራራ ሐሞት መጠጣቱን እያሰበ ዓርብ ዓርብ ከጾመ በኋላ ኮሶ ይጠጣ ነበርና እኅቱ አጋጣሚውን በመጠቀም መርዝ ጨምራ ሰጠችው።
✅ለቅዱስ ላሊበላ መርዝ ጨምራ የሰጠችውን እርሱ ከመጠጣቱ በፊት ያገለግለው የነበረ ዲያቆን ሲቀምሰው ወዲያው ሞተ፡፡ ዲያቆኑ ያስመለሰውን የጠጣው ውሻም ወዲያው ሞተ፡፡ ቅዱስ ላሊበላም አገልጋዩ ለእሱ የተዘጋጀውን መርዝ ጠጥቶ እንደሞተ ባየ ጊዜ መርዙን ጠጣው፡፡ የጠጣው መርዝም ከሆዱ ውስጥ ሆኖ ያሰቃየው የነበረውን አውሬ አወጣለት። እሱም በተአምር ተረፈ።
✅በዚህ ምክንያት ቅዱስ ላሊበላ ለሦስት ቀናት አያይም አይሰማም ነበር። በዚህ ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ሰማይ ወስዶ ሰባቱን ሰማያት አሳየው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በመጀመሪያ አክሱም ከዚያም ኢየሩሳሌም ወስዶ በዚያ የነበሩትን ቅዱሳት መካናት አሳየው። ኢትዮጵያውያን ወደ ኢየሩሳሌም መንፈሳዊ ጉዞ ሲያደርጉ ይደርስባቸው የነበረውን መከራ እያሰበ ያዝን ነበርና በሮሐ ዐሥራ አንድ አብያተ ክርስቲያናትን ፈለፈለ።
✅ቅዱሱ አባት በሃይማኖት ብቻ ሳይሆን በድፕሎማሲም የተዋጣለት ስለነበር በቱርኮች ተይዞ የነበረውና በኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሡልጣን ገዳማችን እንዲመለስልን አድርጓል። ከውቅር አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ በርካታ ቤተ ክርስቲያኖችንም ሠርቷል፣ ንግሥናን ከክህነት፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አስተባብሮ የያዘው ቅዱስ ላሊበላ በዚች ሰኔ ፲፪ ቀን አርፏል።
የቅዱሱ አባት የቅዱስ ላሊበላ ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን!!
4 374
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
