cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ውሉደ ጥምቀት ዘገዳመ ኢየሱስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት በገዳመ ኢየሱስ ቤተ-ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል መነሻ በማድረግ የተቋቋመ ማህበር ነው

Більше
Рекламні дописи
427
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
-930 днів
Час активного постингу

Триває завантаження даних...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Аналітика публікацій
ДописиПерегляди
Поширення
Динаміка переглядів
01
Media files
540Loading...
02
+++"እውነትም የመከር በዓል"+++ ጌታችን ከትንሣኤው በኋላ በጋራም በተናጠልም ለሐዋርያቱ እየታያቸው የትንሣኤውን አማናዊነትና ‹ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገር እየነገራቸው› አርባ ቀን ቆይቷል፡፡(ሐዋ 1:3) በአርባኛውም ቀን ሲያርግ ‹የሚያጸና፣ የሚያነጻ እና የሚያጽናና መንፈስ ቅዱስን› እንደሚልክላቸው ተስፋን ሰጣቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ኃይልን እስከሚቀበሉባት ቀን ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲቆዩ አዘዛቸው፡፡ (ሉቃ 24፡49-51) ሐዋርያቱም ከጌታ ዕርገት በኋላ በጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) ውስጥ በአንድ ልብ ሆነው በጸሎት ይተጉ ጀመር፡፡ ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት ቀን ማለት አይሁድ በዓመት ውስጥ ከሚያከብሯቸው ታላላቅ በዓላት መካከል አንዱ የሆነውን ‹በዓለ ሃምሳ› የሚውልበት ዕለት ነበር፡፡ ይህም በዓል አይሁድ ፋሲካቸውን ካከበሩ ከሰባት ሳምንታት በኋላ ባለው ሰንበት ማግስት (በእሁድ፣ በ50ኛው ቀን) ስለሚከበር ‹‹ጰንጠቆስጤ››/‹‹በዓለ ሃምሳ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዚህም ቀን እስራኤላውያን አርሰው ካመረቱት ላይ አዲሱን የእህል ቁርባን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡበትም ዕለት ስለሆነ በሌላ ስያሜ ‹የመከር በዓል› ተብሎ ይጠራል፡፡ በተጨማሪም የእስራኤል መስፍን የነበረው ሊቀ ነቢያት ሙሴ በሲና ተራራ ከአምላኩ ዘንድ ሕገ ኦሪት መቀበሉንም የሚያስቡበት ቀን ነው፡፡ በተለያዩ የዓለም ክፍላት የሚኖሩ አይሁድ ከያሉበት አገር ተጉዘው በመምጣት የፋሲካንና የመቅደስ መታደስ በዓላትን በኢየሩሳሌም ተሰብስበው ለማክበር ይቸገሩ ነበር፡፡ የችግሩም ምክንያት እነዚህ በዓላት በሚውሉበት ወቅት ያለው የአየር ጠባይ በጣም አስቸጋሪና ነፋሱም ማዕበል የሚቀሰቅስ በመሆኑ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚሁ ጊዜ ወደ ኢጣልያ ለመሄድ በመርከብ በተሳፈረ ጊዜ ስላጋጠመው እንግልትና ስቃይ በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፏል፡፡(ሐዋ 27፡9) እርሱ ራሱም በመንገዱ መካከል አብረውት ይጓዙ የነበሩትን ሰዎች ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ ይህ ጉዞ በጥፋትና በብዙ ጉዳት እንዲሆን አያለሁ፤ ጥፋቱም በገዛ ሕይወታችን ነው እንጂ በጭነቱና በመርከቡ ብቻ አይደለም›› ሲል ጉዞውን ለጥቂት ጊዜ እንዲያዘገዩት መክሯቸው ነበር፡፡ በዓለ ሃምሳ ግን የመጀመሪያዎቹ የፀደይና የመከር ወቅት ላይ ስለሚውል የአየሩ ሁኔታ ለመርከብ ጉዞ የተመቸ ነው፡፡ ስለዚህም የፋሲካና የመቅደስ መታደስ በዓላት ላይ በኢየሩሳሌም መገኘት ያልቻሉ አይሁድ ሁሉ በጉጉት የሚጠባበቁትና ወደ ቅድስቲቱ ከተማ በመግባት ተሰብስበው የሚያከብሩት ታላቅ በዓል ነው፡፡ "በዓለ ሃምሳ" የሚለው መጠሪያ አስቀድመን እንደ ተናገርነው በኦሪቱ ለሚከበረው በዓል መታወቂያነት የሚያገለግል ስያሜ ቢሆንም፣ የጌታ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በሃምሳኛው ቀን በመሆኑ ለሐዲስ ኪዳኑም ታላቅ በዓል መጠሪያነት ቢውል የሚያውክ አይሆንም፡፡ ይሁን እንጂ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ቀን ‹በዓለ ጰራቅሊጦስ› ስትል ለሐዋርያት በወረደው ቅዱስ መንፈስ ልዩ ስም ትጠራዋለች፡፡ ‹‹ጰራቅሊጦስ›› የሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን ‹‹መጽንዒ፣ መንጽሒ››/‹‹የሚያጸና፣ የሚያነጻ›› የሚል ትርጉም አለው፡፡ ወደ ቀደመ ነገራችን እንመስና ሐዋርያቱ በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሲጸልዩ ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ፣ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው፡፡(ሐዋ 2፡2) በዚህ ክፍል ይህን ታሪክ የሚጽፍልን ቅዱስ ሉቃስ የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ‹ድንገት› እንደ ሆነ ይነግረናል፡፡ ለመሆኑ ‹ድንገት› ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ጸሐፊው ቅዱስ ሉቃስ ‹ድንገት› የሚለውን ቃል የተጠቀመው ነገሩ በሰው ቀጠሮ ሳይሆን ‹በእግዚአብሔር ጊዜ› የተፈጸመ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ሐዋርያት አጽናኙ መንፈስ እንደሚላክላቸው ቢነገራቸውም በየትኛው ቀን ግን እንደሚወርድ የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህም ‹ድንገት› የሚለው ቃል ሐዋርያቱ ቀኑን ፈጽመው አለማወቃቸውን ያሳያል፡፡ ሁል ጊዜ ጸጋን የሚሰጠው እግዚአብሔር ስለሆነ የሚሰጥበት ቀነ ቀጠሮ በሰጪው እንጂ በተቀባዩ አይወሰንም፡፡ ስለዚህ የተቀባዩ ሰው ድርሻ ሳይዝል ተስፋም ሳይቆርጥ የአምላኩን የሥራ ቀን በትዕግሥት መጠባበቅ ነው፡፡ የዓውሎ ነፋሱም ድምፅ ልክ ኤልያስ የምድሩን መናወጥና እሳቱን ሲመለከት በመጎናጸፊያው ተሸፍኖ ከዋሻው በመውጣት እግዚአብሔርን ለማናገር ራሱን እንዳዘጋጀ፣ ሐዋርያቱም የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እንዲያስተውሉና ለዚያም ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የተሰማ የማንቂያ ድምፅ ነው፡፡(1ኛ ነገ 19፡12) በተጨማሪም ድምፅ ‹ኃይልን› ያመለክታል፡፡ ስለዚህ እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ የተሰማው ድምጽ ሐዋርያቱ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል መቀበላቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ እዚህ ላይ ጌታችን በዮርዳኖስ ወንዝ ከተጠመቀ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በእርሱ ላይ ሲያርፍ ያሰማው አንዳች ድምፅ አለመኖሩን ልብ ይሏል፡፡(ማቴ 3፡16) ይህም እርሱ ለደካሞች ጽንዕ የሚሆን እንጂ እንደ ፍጡር ኃይል የሚቀበል አለመሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ አስቀድሞ መድኃኒታችን ለኒቆዲሞስ ‹‹ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል›› ሲል እንዳስተማረው፣ በዚህች ቀን በነፋስ የተመሰለ መንፈስ ቅዱስ በወደዳቸው በሐዋርያት ሰውነት ያድር ዘንድ ወደ ጽርሐ ጽዮን ነፈሰ(መጣ፣ ወረደ)፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ መንፈስ ቅዱስን ከነፋሳትም መርጦ ከደቡብ አቅጣጫ በሚነፍሰው ነፋስ ይመስለዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ከሰሜኑ የሚነሣው ነፋስ ቀዝቃዛና ሰብል የሚያጠፋ በመሆኑ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖሩ ገበሬዎች ይፈሩታል፡፡ ከደቡብ አቅጣጫ የሚነፍሰው ነፋስ ግን ከምድር ወገብ የሚወጣውን ሞቃታማ አየር ይዞ ስለሚነፍስ የተዘራውን ሰብል ያበስለዋል፡፡ በዚህም ገበሬዎቹ ደስ ይሰኙበታል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ መንፈሳዊ ብስለትን የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ ልክ በደቡብ እንደሚነፍሰውና ሰብሎችን እንደሚያበስለው ያለ ተወዳጅ ነፋስ ነው ይላል፡፡ ቀጥሎም ለሐዋርያቱ እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፡፡ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ አስተውሉ በዚህ አንድ ታሪክ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በእሳትም በነፋስም ተመስሎ ሲቀርብ እናገኛለን፡፡ ታዲያ መንፈስ ቅዱስ የተመሰለባቸው ምሳሌዎች መብዛታቸው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንዳብራራው የመንፈስ ቅዱስ ባሕርይ በምልዓት የማይታወቅ መሆኑን ያመለክታል፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በእሳት መመሰል አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በዕብራውያን መልእክቱ ‹‹አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና›› ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡(ዕብ 12፡29) መንፈስ ቅዱስ በእሳት መመሰሉ፣ ከከርሰ ምድር መዓድናትን የሚያወጣ ባለሙያ ከመሬት ቆፍሮ ያወጣውን መዓድን ከትቢያው የሚለየው በእሳት እንደ ሆነ እንዲሁ፣ መንፈስ ቅዱስም ነፍሳችንን ትቢያ ከተባለ ኃጢአት ሁሉ ለይቶ ያነጻታልና በእሳት ተመሰለ፡፡ ይህንንም በተመለከተ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹የእስራኤልም ብርሃን እንደ እሳት፣ ቅዱሱም እንደ ነበልባል ይሆናል፡፡ እሾኹንና ኩርንችቱን በአንድ ቀን ያቃጥላል›› ሲል ይናገራል።(ኢሳ 10፡17) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በመጽሐፈ ምሥጢሩ ለሐዋርያቱ በሃምሳኛው ቀን በእሳት አምሳል የወረደው መንፈስ ቅዱስ ‹‹ሥጋቸውን ሳይሆን የኃጢአታቸውን እሾኽ አቃጠለ›› በማለት ይገልጻል፡፡
480Loading...
03
እነዚያ እንደ እሳት ላንቃ የተከፋፈሉት ልሳኖች ከመታየትም አልፈው በሐዋርያቱ ላይ መቀመጣቸው፣ ደቀ መዛሙርቱ የሚያዩት ነገር ሁሉ ቅዠት ወይም ምናባዊ ሳይሆን እውነተኛ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ መሆኑን እንዲገነዘቡ ነው፡፡ ከዚያም በኋላ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ልጅ በረገጡና አመጽ ወዳድ በነበሩት አይሁድ ቅንዓትና ቁጣ ሲሞላ፣ የሰላም ልጆች በነበሩት ሐዋርያት ግን መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ (በየአቅማቸው) እንደ ሰጣቸው በሌሎች ቋንቋዎች ይናገሩ ጀመር፡፡ እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ፣ ሐዋርያትም ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በየአገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መስበክ እንደማይችሉ ዐወቀ፡፡ ስለዚህም በሰናዖር ሜዳ የተበተኑትን የዓለምን ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ሰብስቦ ያኖር ዘንድ ቅዱስ መንፈሱን ላከ፡፡ የተላከውም መንፈስ ያለ አንድ ቋንቋ የማይናገረውን የሐዋርያቱን አንደበት በቅጽበት አሰለጠነው። በእውነት እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያለ አስማሪ ማን ነው?!በዚህችም እለት ሐዋርያቱ በዓለም ሁሉ ቋንቋዎች ተሞልተው ከእርሷ የወጡባት የጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) እንደ ምን ያለች ናት?! መንፈስ ቅዱስ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ታይታ የማትታወቅ ልዩ ትምህርት ቤት አደረጋት፡፡ ሐዋርያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተሟሙቀው በሰበኩት በመጀመሪያ ዕለት ስበከት ብዙዎችን አሳምነው አጠመቁ። በዚህ የመከር በዓል አይሁድ ከአዲሱ እህል ለእግዚአብሔር ቁርባን ሲያቀርቡ፣ ሐዋርያቱ ግን የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለሐዲሲቷ ቤተ ክርስቲያን ከእህል ቁርባን ይልቅ የሚወደዱ ምእመናንን ስጦታ አድርገው አቀረቡ። በአይሁድ የመከር በዓል ቀን በሐዋርያቱ በተሰጠ ትምህርት የእግዚአብሔር እርሻ የሆኑ ምዕመናን በዝተው አብበው ተገኙ። እውነትም የመከር በዓል!!! ዲያቆን አቤል ካሳሁን
530Loading...
04
የጸሎት ጥበብ -፪ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት ልንነጋገር እንደሚገባን እንወቅ፡፡ ጸሎት ማድረስ ያለብን እንዴት እንደ ኾነ እንረዳ፡፥ ይህን ለማወቅ ወዶ ቤተ መጻሕፍት መኼድ፤ ወይም ገንዘብ መክፈል፤ ወይም የንግግር ክህሎትን ለመማር ጊዜ መመደብ አያሻንም፡፡ የተገባ ጸሎትን ስማድረስ መሻት ብቻ በቂ ነው፤ ክህሎቱ በራሱ ይመጣልና፡፥ በዚህ [መንፈሳዊ] ችሎት ፊት የምትናገረውም ለራስህ ብቻ አይደለም! ለሌሎች ለብዙ ሰዎችም ጭምር ነው እንጂ፡፡ በጸሎት ውስጥ ሊኖር የሚገባው ክህሎትስ ምንድን ነው? የጸሎት ጥበብ፥ ይኸውም፦፡ የተዋረደ ልብና የተሰበረ መንፈስ መያዝ፤ በውሒዘ አንብዕ (በዕንባ ጅረት) መቅረብ፤ ከዚህ ዓለም የኾነውን ምንም ነገር አለመሻት፤ የወዲያኛው ዓለም የኾኑ ነገሮችን (ክብሮችን) መሻት፣ መንፈሳዊ ምግባራትን መለመን፤ እግዚአብሔር በጠላቶቻችን ላይ መዓት እንዲያዘንብ አለመለመን፤ ቂም በቀልን ማራቅ፤ [ሥጋዊ] ሁከትን ኹሉ ከነፍስ ማስወገድ፣፤ በተሰበረ ልብ መቅረብ፣ ትሑት መኾን፤ የውሃትን እጅግ መለማመድ፣ ስለ ሌሉች ሰዎች ስንናገር በጎ በጎውን መናገር፤ ከክፉዎች ኅብረት መለየት፣ የዓለም (የሰው) ኹሉ ጠላት ከኾነው ከዲያብሎስ ጋር ምንም ምን አንድነት አለማድረግ ነው፡፡ የዚህ ዓለም ሕጎች እንኳን ሳይቀሩ አንድ ሰው ስለ ንጉሥ ለሌሎች የሚናገር፤ በተለይም ከንጉሥ ጠላቶች ጋር የሚገናኝ ከኾነ ጽኑ ቅጣት ያገኘዋል፡፡ ስለዚህ አንተም ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ራስህና ስለ ሌሎች ስትነጋገር የሰዎች ኹሉ ጠላት ከኾነው ከዲያብሎስ ጋራ ምንም ምን አንድነት ሊኖርህ አይገባም፡፡ ስለዚህ የጸሎትን ጥበብ ገንዘብ አድርግ፡፡ ይህንን ጥበብም (ከቀራጩ) ከመጸብሐዊው ተማር፤ እርሱን መምህር አድርገህ ለመቀበልም አታወላውል፡፡ እርሱ ከአፍአ ሲመረመሩ እዚህ ግባ የማይባሉ ቃላትን በመናገር ማግኘት ያለበትን ኹሉ ለማግኘት የተገባ ኾኗልና (ሉቃ.18፥9-14)፡፡ ተመልከት! በጽርይት ሕሊና በንጽህት ልቡና ስለ ቀረበ አንዲቱ ቃሉ ብቻ ደጀ ሰማያትን ለመክፈት በቂ ነበረች፡፡ ይህችንስ እንዴት ነበር ያቀረባት? ➛ኃጢአቱን በማመን፤ ➛ ደረቱን በመድቃት፤ ➛ዓይኑን እንኳን ወደ ላይ ወደ ሰማይ ቀና ባለማድረግ! አንተም እንደዚህ ብትጸልይ ጸሎትህ ፈጥና ግዳጅ የምትፈጽም ትኾንልሃለች፡፡ ኃጥኡ እንደዚህ በመጸለዩ ጻድቅ ከኾነ፥ ጻድቅ ሰው እንደዚህ አድርጎ ጸሎት ማድረስን ቢያወቅ ደግሞ እንደ ምን ያማረ የተወደደ ሊኾን አንደሚችል ልብ ብለህ አስተውል፡፡ ("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 20-21 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
620Loading...
05
Media files
700Loading...
06
ከጻድቁ ከአቡነ አረጋዊ እና ከቅዱስ ገብረ ክርስቶስ በረከት ረድኤት ይክፈለን። “ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።”ማቴ:፲፥፵፩። ስለ ጻድቃን ሲነሣ “አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም፤”ሮሜ ፡፫፥፲።ተብሎ የለ እንዴ? የሚል ጥያቄ ይነሣል።አዎን ተብሏል።ነገር ግን የተባለው ለማን ነው? የሚለውንም አብሮ መመልከት ያስፈልጋል።እስኪ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ማን እንደ ተናገረው እዚያው ምዕራፍ ላይ አብረን እንመልከት። “እንግዲህ ምን እንላለን? እኛ ከእነርሱ እንበልጣለንን? ከቶ አይደለም፤አይሁዳዊንም፥ አረማዊንም እነሆ፥አስቀድመን ነቅፈናቸዋል፤ሁሉም ስተዋልና።መጽሐፍ እንዲህ እንዳለ ‘አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም፥አስተዋይም የለም፥እግዚአብሔርንም የሚሻው የለም።ሁሉም ተባብሮ በደለ፥በጎ ሥራንም የሚሠራ የለም፥አንድ ስንኳ ቢሆን የለም። ጉረሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው። በአንደበታቸውም ሸነገሉ፥ከከንፈሮቻቸውም በታች የእባብ መርዝ አለ፥አፋቸው መራራ ነው፥መርገምንም የተሞላ ነው።እግሮቻቸውም ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው።በመንገዳቸው ጥፋትና ጉስቁልና አለ።የሰላምን መንገድ አያውቋትም።በዐይኖቻቸውም ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።”ይላል።ሮሜ፡፫ ፥፱-፲፰፣መዝ፡፲፫፥፩-፫፣መዝ፡፶፪፥፩-፫፣መዝ፡፭፥፱፣መዝ፡፻፴፱፥፫፣መዝ፡፲፥፯፣ኢሳ፡፶፱፥፯።እንግዲህ “አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም፤”የተባለው ምንም እምነትና ምግባር ስለሌላቸው ሰዎች መሆኑን ማስተዋል ይገባል። ጻድቅ እግዚአብሔር ነው፥አዎን እግዚአብሔር ጻድቅ ነው።መዝ፡፲፥፯።በመሆኑም እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ሃይማኖት ይዘው፥ምግባር ፥ሠርተው፥ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው በማስገዛት ንጽሕናን እና ቅድስናን ገንዘብ አድርገው የተገኙ አገልጋዮቹ ጻድቃን ናቸው።”ልጆቼ ሆይ፥ማንም አያስታችሁ፥እርሱ (እግዚአብሐሔር) ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ጻድቅ ነው።”ይላል።፩ኛ፡ዮሐ፡፫፥፯።
680Loading...
07
ቃለ ሕይወት ዘደብረ ታቦር - ዘወርኃ ሰኔ • የወሩ ስም - ሰኔ • የግእዝ ሥርወ ቃለ - ሰነየ • ትርጉሙ - አማረ (አዝርዕቱ) • አበው ስለ ወሩ እንዲህ ይላሉ ፡- “በሰኔ ዝናቡን ወደ እኔ” የሰኔ መዓልት ቀደምት ኢትዮዽያውያን ሰው ወሬ ሲያበዛባቸው "ምነው የሰኔ መዓልትን ሆንክብኝ!" ሲሉ ይተርቡ ነበር ፡፡ "አሳጥርልኝ! ወሬህ ረዘመብኝ!" ለማለት ነው፡፡ ለዚህ መነሻ የሆነው ደግሞ ከ13ቱ ወራት መዓልቱ (ቀኑ) ቶሎ የማይመሽበት ወር ሰኔ መሆኑ ነው፡፡ ከዓመቱ 13 ወራት የሰኔ መዓልቱ ለምን ረዘመ ብንል:- መልሱ አጭር ነው ፡፡ "ይህ የእግዚብሔር ጥበብና ሥራ ነው::" ሳይንሱ ሺህ መንስኤን ሊደረድር ይችላል፡፡ ለእኛ ግን አበው እንዳስተማሩን ሰኔ የሥራና የጾም ወር ነው::ትጋትን የሚወድ አምላክ ይህንን ወቅት ለጾም ለሥራና: ለበጐ ተግባር አርዝሞልናል፡፡ በእርግጥ ጥቂት ሠርተን ብዙ ለምንተኛ ለዚህ ዘመን ሰዎች ይህ ሊጸናብን ይችል ይሆናል፡፡ግን ምንም እንኩዋን ሁሉ ወራት ለሥራ ቢሠሩም ወርሃ ሰኔ ለገበሬና ለክርስቲያን ትልቁን ሥራ የሚጀምሩበት ወቅት ነው፡፡ በሰኔ ያልተጋ ገበሬ ዓመቱን ሙሉ መከረኛ ነው፡፡ ከነ ተረቱም " ሰነፍ ገበሬ  ይሞታል በሰኔ" ይባላል፡፡ክርስቲያንም ከበዓለ ሃምሳ ማግስት በዓለ ጰራቅሊጦስን ተደግፎ ሰኔን ሊተጋባት ግድ ይላል፡፡ በመከራ ዘመን የሚመሰል ክረምት ሳይመጣ በወርሃ ሰኔ ሊተጋ ግድ ይለዋል፡፡ ሽሽቱ በክረምትና በሰንበት እንዳይሆንም ይጸልያል፡፡(ማቴ.24:20) በሰኔ ወር የሚከብሩ ዓበይት በዓላት ሰኔ ፩ - የያዕቆብ ልጅ የጻድቁ ዮሴፍና የሚስቱ የአሰኔት የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው ፡፡ ሰኔ ፪ - ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ፍልሰቱ ፣ ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ ፍልሰቱ ሰኔ ፰ - ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደረቅ ዓለት ላይ ውሀን ያፈለቀበት እለት ከ33ቱ ከእመቤታችን በዓል አንዱ ሰኔ ፱ - ነቢዩ ሳሙኤል ዕረፍቱ ሰኔ ፲፪ - ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት ፣ ቅዱስ ላሊበላ ሰኔ ፳ -ሕንጻተ ቤተክርስቲያን ሰኔ ፳፩ - ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእመቤታችንን ቤት ያነጸበት / እርሷም በጎልጎታ በጌታችን መቃብር የጸለየችበት ሰኔ ፳፫ - የንጉስ ሰሎሞን ዕረፍቱ ሰኔ ፳፬ - አባ ሙሴ ጸሊም ሰማዕት የሆነበት ዕለት ሰኔ ፳፭ - የክረምት መግቢያ ፤ የጸደይ መውጫ ሰኔ ፴ - ቅዱስ ዮሐንስ መጥመቀ መለኮት በዓለ ልደቱ
631Loading...
08
የጸሎት ጥበብ - ፩ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርን የተረዳ ያወቀ ሰው እግዚአብሔርን እንደሚገባ'ው አድርጎ ሲያነጋግረው ከዚያን ጊዜ አንሥቶ መልአክ ይኾናል፡፡ ነፍስ ከፈቃዳተ ሥጋ ሰንሰለት ነጻ የምትወጣው በዚህ መንገድ ነውና፤ ሕሊና ከፍ ከፍ የሚለው በዚህ መንገድ ነውና! ማደሪያችን ወደ ሰማይ የሚሻገረው በዚህ መንገድ ነውና፤ አንድ ሰው ግብረ ዓለምን የሚንቀው በዚህ መንገድ ነውና፤ አንድ ሰው የቱንም ያህል ነዳይ ወይም ባሪያ ወይም ተራ ወይም ዝቅ ያለ ቢኾንም እንኳን በንጉሥ ዙፋን ፊት የሚቆመው በዚህ መንገድ ነውና፡፡ እግዚአብሔር የሚመለከተው የንግግርን ውበት ወይም የቃልን ርቱዕነት ሳይኾን የመንፈስን ንጹህነት ነውና፡፡ በዚህ መንገድ መጥተን ወደ አእምሮአችን የመጣውን ብንናገርም እንኳን፥ ጸሎታችን ግዳጅ የሚፈጽም ኾኖናልን እንመለሳለን፡፡ እንግዲህ ይህን ማድረግ ምን ያህል ቀላል እንደ ኾነ ታስተውላለህን? በዚህ ዓለም ሰዎች ዘንድ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ለመለመን የንግግር ክህሎት (ብልሐት) ያሻዋል፡፡ የሚለመነው ሰው በቀላሉ የማይገኝ ከኾነ ደግሞ አጃቢዎቹን ማሳመን ይኖርበታል፡፡ ጥሮ ለፍቶ ካገኘው በኋላም ጉዳዩን በዝርዝር ማስረዳት ይጠበቅበታል፡፡ እግዚአብሔርን ለማናገር ግን የዚሁ ተቃራኒ ነው፡፡ ከተሰበረ ልብ በቀር ሌላ ምንም ምን አያስፈልግም፤ ወደ እርሱ ለመቅረብም የሚከለክል ማንም አይኖርም፡፡ “እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ ሩቅ አምላክ አይደለሁም” ይላልና (ኤር.23፥23)፤ የምንርቀው እኛ ነን እንጂ እርሱ ዘወትር ቅርብ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማነጋገር የንግግር ክህሎት (ብልሐት) አያስፈልገንም የምለውስ ለምንድን ነው? እንዲያውም ብዙ ጊዜ ድምፅም ቢኾን አያስፈልገንም፡፡ አንተ በልብህ ብትናገርና እግዚአብሔርን ማናገር እንዲገባ'ህ ብታናግረው እርሱ ጸሎትህን ለመስማት ዘንበል ይላል፡፡ ሙሴ ጸሎቱ የተሰማው በዚህ መንገድ ነውና፤ ሐና ጸሎትዋ የተሰማው በዚህ መንገድ ነውና፡፡ ወደ እግዚአብሔር እንዳይቀርቡ ብሎ ሕዝቡን ለማራቅ የሚቆም ወታደር የለም፤ አሁን ሰዓቱ አይደለም ብሎ የሚከለክል ዘበኛም የለም፡፡ እግዚአብሔርም፦ “አሁን ላነጋግርህ አልችልም፤ ሌላ ጊዜ ተመለስ” አይልም፡፡ ይልቅ ልታነጋግረው በመጣህበት ቅጽበት አንተን ለመስማት ይቆማል፡፦፥ የምሳ ሰዓትም ቢኾን፣ የአራት ሰዓትም ቢኾን፤ እጅግ አስቸጋሪ ጊዜም ቢኾን፣ በገበያ ቦታም ቢኾን፣ በመንገድ ላይም ቢኾን፤ በባሕር ውስጥም ቢኾን፣፤ በዳኛ ፊት በምትቆምበት በችሎት ፊትም ቢኾን፥ እግዚአብሔርን ብትጠራው መጥራት እንደሚገባህ አድርገህ እስከ ጠራኸው ድረስ ጸሎትህን እንዳይሰማ የሚከለክለው ግድግዳ የለም፡፡ ... ("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 18-19 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
740Loading...
09
                        †                           [ " ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች "  ] ▪ - [ በመከራ ውስጥ ያለ የሚጸልየው ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ፦ " በጠራሁህ ጊዜ ቅረበኝ ! " ] - [ በጠራሁህ ጊዜ በምህረትና በይቅርታ ቅረበኝ ! ] ------------------------------------------------ ❝ በሰማይም ሰልፍ ሆነ:: ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ:: ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ:: አልቻላቸውምም:: ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም:: ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ወደ ምድር ተጣለ:: ❞ † [ራዕ.፲፪፥፯] ❝ ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።❞ [ራእ.፲፰፥፩] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
1080Loading...
10
+ የተሠጠህን ቁጠር + ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው። የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም። ዕባብ ደግሞ የስይጣን አንደበት ነበረ። ሰይጣን እንዲህ አላት:- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። ልብ አድርጉ እግዚአብሔር "ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ" አላለም። የከለከለው አንዲት ዛፍ ነው:: ሰይጣን ግን ሁሉን ተከልክላችሁዋል? ብሎ እንዳላዋቂ ጠየቀ። ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግግሩን የከፈተው በውሸት ነበረ። ዓላማው ከሔዋን መረጃ ለማግኘት አልነበረም። ሔዋን እስከዛሬ ያላሰበችውን ማሳሰብ ነበር። ብሉ ተብሎ ከተሠጣቸው ብዙ ሺህ ዛፍ ይልቅ የተከለከሉትን አንዲት ዛፍ አሳይቷት ሔደ። ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስላልተሠጣት ማሰብ ጀምራ ደስታዋን አጣች። የተከለከለችውን በልታ የተሠጣትን ብዙ ሥጦታ ከነሠጪው አጣች። ወዳጄ የቀደመው እባብ ዛሬም መርዙን ይረጫል በሕይወታችን ከተሠጠን ብዙ ነገር ይልቅ ያልተሠጠንን ጥቂት ነገር እናስባለን። ገንዘብ እንደሌለህ እያሰብክ ጤና እንዳለህ ትረሳለህ። ጫማ እንደሌለህ እያሰብክ እግር እንዳለህ ትረሳለህ። አልጋ እንደሌለህ እያሰብክ እንቅልፍ እንዳለህ ትረሳለህ። ስለዚህ ውስጥህ ያለውን የዕባቡን ድምፅ  አትስማ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ይበልጣልና የተሠጠህን ቁጠር። (ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
1140Loading...
11
💒#መልካም ዕለተ ሰንበት💒 "' አቤቱ አምላኬ የሕይወቴ ጌታ ሆይ የስንፍናን መንፈስ፣ ተስፋ መቁረጥን፣ ስልጣን መሻትንና ከንቱ ወሬን ከእኔ አርቅልኝ ነገር ግን በምትኩ የንጽሕናን፣ የትሕትናን፣ የትዕግስትንና የፍቅርን መንፈስ ለእኔ ለባሪያህ አድለኝ አዎን፣ ጌታና ንጉሥ ሆይ የራሴን መተላለፍ እንድመለከት እንጂ በወንድሜ ላይ እንዳልፈርድ አድርገኝ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ምስጉን ነህና'' ✍#ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።" (ኦሪት ዘጸአት 20:8) ✝️መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ✝️
1131Loading...
12
Media files
1150Loading...
13
ጤና ይሰጥልኝ እንደምን አደራችሁ ዛሬ ወራዊ ፀሎታችን ነው በዚሁ አጋጣሚ የመለከት እና ነጋሪት አገልግሎት ስልጠና የምትፈልጉ ሰዎች ለምናደርገው የአገልግሎት ክፍተት እና ቅሬታ እንዳይፈጠር መጥታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን!!!
930Loading...
14
Media files
1011Loading...
15
Media files
1101Loading...
16
Media files
1060Loading...
17
Media files
960Loading...
18
Media files
1201Loading...
19
+ በዓለ ዕርገት + ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ ሞቶ ከተነሣ በኋላ ለ40 ቀናት ያህል ደቀ መዛሙርቱን ሲያስተምራቸው ቆይቷል ። "ደግሞ ዐርባ ቀን እየታያቸው ስለእግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው " ሲል ቅዱስ ሉቃስ እንደገለጸው ከትንሣኤው በኋላ በምድር ላይ የቆየው ለዐርባ ቀናት ብቻ ነው ። ከዐርባ ቀናት በኋላ በክብር በይባቤ ወደ ሰማይ ዐርጓል ። " ....ይኽን ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው" እንዲል ። (ሐዋ 1፥1-9 ) ጌታችን ያደረገውን /ዕርገቱንም/ ከደብረ ዘይት ተራራ ነው ። (ሉቃ 24-50-53) ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው ሲያስተምር "እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል ?" በማለት እንደገለጸው ዕርገቱ ፣ ክብሩ በሚገለጽበት በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ለመቀመጥ ነው ። (ዮሐ 6፥62) ይኽን ቅዱስ እስጢፍኖስ በዐይነ ሥጋው ለመመልክት መብቃቱን "እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ " በማለት ገልጾታል ። (ሐዋ 7፥57 ) ይኽን ጉዳይ አስመልክቶ ቅዱስ ጳውሎስ "እንግዲህ በሰማያት ስላለን ፣ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ " ብሎአል ። (ዕብ 4፥14 7፥26 ) ስለጌታችን አምላክነት ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ባስረዳበት አንቀጽ "......በሥጋ የተገለጠ ፣ በመንፈስ የጸደቀ ፣ ለመላእክት የታየ፣ በአሕዛብ የተሰበከ ፣ በዓለም የታመነ ፣ በክብር ያረገ "ሲል ገልጾታል ። (1ኛ ጢሞ 3፥16 )   ( "በዓላት" ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ገጽ 111-112)
1141Loading...
20
✞✝✞ እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝ +*" ዕርገተ እግዚእ "*+ =>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን 2 ጊዜ ታከብራለች:: አንዱ "ጥንተ በዓል": ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል:: ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል:: +የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ (በሕማሙ: በሞቱ) ዓለምን አድኖ: 40 ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል:: +በ40ኛው ቀን 120ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው: ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጉዋል:: +ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን እርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሳኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በ40ኛው ቀን ዐረገ:: +አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል:: <<ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ:: ወእግዚእነ በቃለ ቀርን:: ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ:: >> (መዝ. 46:6) =>ከበረከተ ዕርገቱ ይክፈለን:: +"+ እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ ሰማይም ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ:: +"+ (ሉቃ. 24:50-53) <<< ስብሐትለእግዚአብሔር >
1100Loading...
21
Media files
910Loading...
22
ወር በገባ በ4 ነባቤ መለኮት  ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። ጥበቃው አይለየን ወቶ ከመቅረት ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውረን።🙏❤
1532Loading...
23
Media files
1211Loading...
24
ከበዓታ ለማርያም በረከት ረድኤት ይክፈለን። ከቤተ መንግሥቱ ግቢ ውስጥ ያለሽ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም:-ለሀገራችን ቅን መሪ፥ለቤተ ክርስቲ ያናችን ቅን አገልጋይ አድዪን።በአማላጅነትሽ ኢትዮጵያ አገራችንን፥ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ከነደደ እሳት አውጪልን፥የመከራውን ዘመን አሳጥሪልን።
1281Loading...
25
"#እባክህን_ከእሳቱ_ላይ_አትውረድ"    አንድ ወንድም አባ ጴሜንን "ምከረኝ" ብሎ ጠየቀው። አባ ጴሜንም "ድስት በእሳት ላይ እያለ ምንም አይነት ተባይ ሊቀርበውና ሊያበላሸው አይችልም። ከእሳት ወጥቶ ሲቀዘቅዝ ግን ነፍሳት ሁሉ ለመግባትና ለማበላሸት ይቻላቸዋል። ክርስቲያንም ከመንፈሳዊ ተግባር ካልራቀ ጠላት የድቀት ምክንያት አያገኝበትም" አለው። ወዳጄ ሆይ ሕይወት ቀዝቅዛብሃለችን? ከእሳቱ ወደ መሬት ወርደህ በርደሃልን? የሕያውነትህ ሙቀት እሳት በማጣት ተንዘፍዝፏልን? ድስት የተባለ ሰውነትህ ክረምት የሚያህል ጉድን ተሸክሟልን? ዙሪያ ገባህ ፀሐይ እንደማትወጣበት ምእራብ ጨለማን የሚጠራ ሆኗልን? ማንነትህ እሳት እንዳጣ ምግብ ጥቃቅን ነፍሳት በተባሉ ኃጢአቶች (ቁጣ፣ ቸልተኛነት፣ ስስት፣ አልታዘዝ ባይነት፣ ጭንቀት፣ ሁሉን የመናቅ ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ...) ተወርሮ፣ መዓዛ ቅድስና ተለይቶት እጅ እጅ ብሏልን? ሞቅ የሚያደርገው አጥቶ በዓለማዊነት ሻግቷልን? የተባዮች መጫወቻ፣ የተውሳኮች መቀለጃ ሆኗልን? እንግዲያውስ በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡ ወዳጄ ሆይ ሃይማኖት በተባለችና ከሰማይ በወረደች ልዩ እሳት (ሉቃ.12፥49) ላይ ተቀምጠህ የድስትነትህን ሙቀት መልስ፡፡ እምነት፣ ተስፋና ፍቅር (1ቆሮ.13፥13) በተባሉ ሦስት ጉልቻዎች ላይ በምቾት ተጥደህ የሕይወትህን የኃጢአት ብርድ አስወግድ፡፡ ንስሐ በተባለች ነበልባል ውበትነት የክረምትህን ጽልመት በምስራቃዊ በጋነት ድል ንሳ፡፡ በሥጋ ወደሙ ፍምነት ድስት የተባለ ሰውነትህን በከዊነ እሳትነት ቀድስ፡፡ እባክህን በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡ ሃይማኖት የተባለ እሳትን ተባይ አይቀርበውም፡፡ እምነት ተስፋና ፍቅር የተሰኙ ጉልቻዎችን ተውሳኮች ሽቅብ አይወጡአቸውም፡፡ የነበልባለ ንስሐን ብርሃንና ሙቀት ነፍሳተ ጽልመት መቋቋም አይችሉም፡፡ ስለዚህ በእሳቱ ላይ እስካለህ ድረስ (በመንፈሳዊ ተግባራት እስከጠነከርክ ድረስ) አንተ ሁሌም ከተባይና ከነፍሳት ብልሽት (ከአጋንንት) የራቅክ ነህ፡፡ ወዳጄ እባክህን ከእሳቱ ላይ አትውረድ፡፡ እሳቱ በደንብ ይነድ ዘንድ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት የተባሉ እንጨቶችንና ምጽዋት የተባለ ጋዝን መጨመርህን እንዳትዘነጋ፡፡ እንዲህ ከሆነ ዘንዳ ድስትነት ሁሌም የሞቀ ይሆናል፡፡ እጅ እጅ ከማለት፣ ከመሻገትና የተባይ መጫወቻ ከመሆን ትድናለህ፡፡ ወዳጄ ሆይ እባክህን ከእሳቱ ላይ አይትውረድ፡፡ በኃጢአት "እጅ እጅ '' ከማለትና በበደል ከመሻገት እግዚአብሔር ይሠውረን! አሜን
1291Loading...
26
የንጉሥ ሥልጣን በሥጋ ላይ ነው፤ የካህን ሥልጣን ግን በነፍስ ላይ ነው፡፡ ንጉሥ ይቅር ቢል የገንዘብን ዕዳ ነው፤ ካህን ይቅር ሲል ግን የበደል የኃጢአት ዕዳን ነው፡፡ ንጉሥ ያዝዛል፤ ካህን ግን ያስተምራል ይዘክራል። ንጉሥ ያስገድዳል፤ ካህን ግን ነጻ ፈቃድን ያያል፡፡ ንጉሥ ቁሳዊ የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፤ ካህን ግን ረቂቅ (መንፈሳዊ) የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፡፡ ንጉሥ የጦር ዕቃ መሣሪያውን ቢሰብቅ አንገዛም ብለው ባመፁት (እንዲሁም ከወራሪዎች፣ ሥጋውያን ደማውያን) ላይ ነው፤ ካህን ግን ውጊያው ከጨለማ አበጋዞች ከአጋንንት ጋር ነው፡፡ ስለዚህ ሥልጣነ ክህነት ከሥልጣነ መንግሥት ይበልጣል፡፡ እንዲህም በመኾኑ ንጉሥ አንገቱን ለካህናት እጅ ያጎነብሳል፡፡ (#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ፣ ትንቢተ ኢሳይያስ፣ ድርሳን ፬ በተረጎመበት ድርሳኑ)
1050Loading...
27
“እገድልኻለሁ ያልከኝ እውነትም ገደልከኝ’’ በአንድ ወቅት ከቤ/ክን አገልጋይ ከነበረ ሰባኪ ሲመሰከር ከሰማሁት እውነተኛ ታሪክ ላካፍላችሁ። አንድ እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚያገለግል ዲያቆን ነበር። የዚህ ዲያቆን ጎረቤት የሆነ ሰውም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ይኽን ዲያቆን በጣም ጠምዶ ይዞት ነበር። በመንገድ ላይ ባገኘው ቁጥር በጣም አስፀያፊ ስድብ ከመስደብ ጀምሮ ቆሻሻ ውኃ በላዩ ላይ እስከመድፋት እንዲሁም ካልደበደብኩት እያለ በገላጋይ ነበር የሚለመነው ዲያቆኑ ግን ይኽ ኹሉ ሲሆን "እግዚአብሔር ይባርክህ ያስብኽ" ከማለት ውጪ ምንም የክፋት ቃል ከአንደበቱ አይወጣም ነበር። ከእዕታት በአንዱ ቀን ግን ዲያቆኑ ምርር ብሎት ሰውየውን “እገድልኻለሁ’’ ብሎት ይሔዳል። ሰውየውም ይኽ ዲያቆን እገድልኻለሁ ያለኝ ምን ገዝቶ ነው ቦንብ ነው ?  ሽጉጥ ነው? ዱርየ ነው ? በማለት መጨናነቅ ይጀምራል። ታዲያ ከዕለታት በአንዱ ቀን ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ ዲያቆኑ ከቅዳሴ ወጥቶ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲሔድ መንገድ ላይ ሕዝብ ተሰብስቦ ያያል። ጠጋ ብሎ ምን እንደተፈጠረ ይጠይቃል። ሰዎቹም አንድ ተሽከርካሪ አንድ ሕጻን ልጅ ገጭቶ እንዳመለጠ ይነግሩታል። ጠጋ ብሎ ሲያይም የተገጨው የዚያ እርሱን የሚሰድበውና የሚያዋርደው ሰው ልጅ መኾኑን ይረዳል። በኋላም ልጁን ከነደሙ ይሸከምና ኮንትራት ታክሲ ጠርቶ ልጁን ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ይወስድና ያሳክመዋል። የልጁ አባትም ሥራ ቦታ ነበርና ልጁ ተገጭቶ ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል መወሰዱ ተደውሎ ይነገረዋል። ሰውየውም ዘውዲቱ ሆስፒታል ሔዶ ልጁ የተኛበት ክፍል ሲገባ ልጁ ጉሉኮስ ተሰክቶበት ተኝቶ አጠገቡ ደግሞ ያ አልወደውም ጠላቴ እያለ የሚሰድበው ዲያቆን ሲያስታምመው ያያል። በአካባቢው የነበሩ ጎረቤቶቹም ልጁ በመኪና እንደተገጨና ያ ጠላቴ የሚለው ዲያቆን አምጥቶ እያሳከመው እንደሆነና እሱ ባያሳክመው ልጁ ሊሞት ይችል እንደነበር ነገሩት። ሰውየውም ዲያቆኑን ጠርቶ  “እገድልኻለሁ ያልከኝ እውነትም ገደልከኝ’’ ። አሁን ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለኽ ? " ሲለው ዲያቆኑም "እኔ ምንም አልፈልግም ከነ ቤተሰቦችህ ንስሐ ግባ ሥጋ ወደሙ ተቀበል። እኔ የምመኝልህ ይኽን ብቻ ነው።" ብሎ አለው። በኋላም ዲያቆኑን የሚያውቁት ሰዎች "ለመሆኑ ሰውየዉን እገድልኻለሁ ያልከው ለምንድን ነው? " ብለው ሲጠይቁት ዲያቆኑም "እኔ እኮ እገድልኻለሁ ያልኩት ሰውየውን አይደለም እኔ እገድልኻለሁ ያልኩት በሰውየው ላይ አድሮ የሚረብሸኝን ዲያብሎስን ነው። እግዚአብሔርም ዲያብሎስን መግደያ ምክንያትና ጥበብ እንዲሰጠኝ ስጸልይ ነበር። ልጁ የተገጨውም እግዚአብሔር ለእኔ ዲያብሎስን መግደያ ምክንያት ሊሰጠኝ ነው። እኔም የሰጠኝን ምክንያት ተጠቀምኩና እንደዛትኩት ዲያብሎስን ገደልኩት።" ብሎ አላቸው። ግሩምና በጣም ጣፋጭ ትምህርት ነው። እኔ እራሴን ታዘብኩት እናንተስ? ከዲያቆኑ ምን ተማራችሁ? በእውነት የዲያቆኑ ጥበብና የቀናች የሃይማኖቱ ትሩፋት ትደርብን አሜን ።
1081Loading...
28
Media files
1320Loading...
29
Media files
1360Loading...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
+++"እውነትም የመከር በዓል"+++ ጌታችን ከትንሣኤው በኋላ በጋራም በተናጠልም ለሐዋርያቱ እየታያቸው የትንሣኤውን አማናዊነትና ‹ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገር እየነገራቸው› አርባ ቀን ቆይቷል፡፡(ሐዋ 1:3) በአርባኛውም ቀን ሲያርግ ‹የሚያጸና፣ የሚያነጻ እና የሚያጽናና መንፈስ ቅዱስን› እንደሚልክላቸው ተስፋን ሰጣቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ኃይልን እስከሚቀበሉባት ቀን ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲቆዩ አዘዛቸው፡፡ (ሉቃ 24፡49-51) ሐዋርያቱም ከጌታ ዕርገት በኋላ በጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) ውስጥ በአንድ ልብ ሆነው በጸሎት ይተጉ ጀመር፡፡ ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት ቀን ማለት አይሁድ በዓመት ውስጥ ከሚያከብሯቸው ታላላቅ በዓላት መካከል አንዱ የሆነውን ‹በዓለ ሃምሳ› የሚውልበት ዕለት ነበር፡፡ ይህም በዓል አይሁድ ፋሲካቸውን ካከበሩ ከሰባት ሳምንታት በኋላ ባለው ሰንበት ማግስት (በእሁድ፣ በ50ኛው ቀን) ስለሚከበር ‹‹ጰንጠቆስጤ››/‹‹በዓለ ሃምሳ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዚህም ቀን እስራኤላውያን አርሰው ካመረቱት ላይ አዲሱን የእህል ቁርባን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡበትም ዕለት ስለሆነ በሌላ ስያሜ ‹የመከር በዓል› ተብሎ ይጠራል፡፡ በተጨማሪም የእስራኤል መስፍን የነበረው ሊቀ ነቢያት ሙሴ በሲና ተራራ ከአምላኩ ዘንድ ሕገ ኦሪት መቀበሉንም የሚያስቡበት ቀን ነው፡፡ በተለያዩ የዓለም ክፍላት የሚኖሩ አይሁድ ከያሉበት አገር ተጉዘው በመምጣት የፋሲካንና የመቅደስ መታደስ በዓላትን በኢየሩሳሌም ተሰብስበው ለማክበር ይቸገሩ ነበር፡፡ የችግሩም ምክንያት እነዚህ በዓላት በሚውሉበት ወቅት ያለው የአየር ጠባይ በጣም አስቸጋሪና ነፋሱም ማዕበል የሚቀሰቅስ በመሆኑ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚሁ ጊዜ ወደ ኢጣልያ ለመሄድ በመርከብ በተሳፈረ ጊዜ ስላጋጠመው እንግልትና ስቃይ በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፏል፡፡(ሐዋ 27፡9) እርሱ ራሱም በመንገዱ መካከል አብረውት ይጓዙ የነበሩትን ሰዎች ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ ይህ ጉዞ በጥፋትና በብዙ ጉዳት እንዲሆን አያለሁ፤ ጥፋቱም በገዛ ሕይወታችን ነው እንጂ በጭነቱና በመርከቡ ብቻ አይደለም›› ሲል ጉዞውን ለጥቂት ጊዜ እንዲያዘገዩት መክሯቸው ነበር፡፡ በዓለ ሃምሳ ግን የመጀመሪያዎቹ የፀደይና የመከር ወቅት ላይ ስለሚውል የአየሩ ሁኔታ ለመርከብ ጉዞ የተመቸ ነው፡፡ ስለዚህም የፋሲካና የመቅደስ መታደስ በዓላት ላይ በኢየሩሳሌም መገኘት ያልቻሉ አይሁድ ሁሉ በጉጉት የሚጠባበቁትና ወደ ቅድስቲቱ ከተማ በመግባት ተሰብስበው የሚያከብሩት ታላቅ በዓል ነው፡፡ "በዓለ ሃምሳ" የሚለው መጠሪያ አስቀድመን እንደ ተናገርነው በኦሪቱ ለሚከበረው በዓል መታወቂያነት የሚያገለግል ስያሜ ቢሆንም፣ የጌታ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በሃምሳኛው ቀን በመሆኑ ለሐዲስ ኪዳኑም ታላቅ በዓል መጠሪያነት ቢውል የሚያውክ አይሆንም፡፡ ይሁን እንጂ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ቀን ‹በዓለ ጰራቅሊጦስ› ስትል ለሐዋርያት በወረደው ቅዱስ መንፈስ ልዩ ስም ትጠራዋለች፡፡ ‹‹ጰራቅሊጦስ›› የሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን ‹‹መጽንዒ፣ መንጽሒ››/‹‹የሚያጸና፣ የሚያነጻ›› የሚል ትርጉም አለው፡፡ ወደ ቀደመ ነገራችን እንመስና ሐዋርያቱ በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሲጸልዩ ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ፣ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው፡፡(ሐዋ 2፡2) በዚህ ክፍል ይህን ታሪክ የሚጽፍልን ቅዱስ ሉቃስ የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ‹ድንገት› እንደ ሆነ ይነግረናል፡፡ ለመሆኑ ‹ድንገት› ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ጸሐፊው ቅዱስ ሉቃስ ‹ድንገት› የሚለውን ቃል የተጠቀመው ነገሩ በሰው ቀጠሮ ሳይሆን ‹በእግዚአብሔር ጊዜ› የተፈጸመ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ሐዋርያት አጽናኙ መንፈስ እንደሚላክላቸው ቢነገራቸውም በየትኛው ቀን ግን እንደሚወርድ የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህም ‹ድንገት› የሚለው ቃል ሐዋርያቱ ቀኑን ፈጽመው አለማወቃቸውን ያሳያል፡፡ ሁል ጊዜ ጸጋን የሚሰጠው እግዚአብሔር ስለሆነ የሚሰጥበት ቀነ ቀጠሮ በሰጪው እንጂ በተቀባዩ አይወሰንም፡፡ ስለዚህ የተቀባዩ ሰው ድርሻ ሳይዝል ተስፋም ሳይቆርጥ የአምላኩን የሥራ ቀን በትዕግሥት መጠባበቅ ነው፡፡ የዓውሎ ነፋሱም ድምፅ ልክ ኤልያስ የምድሩን መናወጥና እሳቱን ሲመለከት በመጎናጸፊያው ተሸፍኖ ከዋሻው በመውጣት እግዚአብሔርን ለማናገር ራሱን እንዳዘጋጀ፣ ሐዋርያቱም የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እንዲያስተውሉና ለዚያም ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የተሰማ የማንቂያ ድምፅ ነው፡፡(1ኛ ነገ 19፡12) በተጨማሪም ድምፅ ‹ኃይልን› ያመለክታል፡፡ ስለዚህ እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ የተሰማው ድምጽ ሐዋርያቱ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል መቀበላቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ እዚህ ላይ ጌታችን በዮርዳኖስ ወንዝ ከተጠመቀ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በእርሱ ላይ ሲያርፍ ያሰማው አንዳች ድምፅ አለመኖሩን ልብ ይሏል፡፡(ማቴ 3፡16) ይህም እርሱ ለደካሞች ጽንዕ የሚሆን እንጂ እንደ ፍጡር ኃይል የሚቀበል አለመሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ አስቀድሞ መድኃኒታችን ለኒቆዲሞስ ‹‹ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል›› ሲል እንዳስተማረው፣ በዚህች ቀን በነፋስ የተመሰለ መንፈስ ቅዱስ በወደዳቸው በሐዋርያት ሰውነት ያድር ዘንድ ወደ ጽርሐ ጽዮን ነፈሰ(መጣ፣ ወረደ)፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ መንፈስ ቅዱስን ከነፋሳትም መርጦ ከደቡብ አቅጣጫ በሚነፍሰው ነፋስ ይመስለዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ከሰሜኑ የሚነሣው ነፋስ ቀዝቃዛና ሰብል የሚያጠፋ በመሆኑ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖሩ ገበሬዎች ይፈሩታል፡፡ ከደቡብ አቅጣጫ የሚነፍሰው ነፋስ ግን ከምድር ወገብ የሚወጣውን ሞቃታማ አየር ይዞ ስለሚነፍስ የተዘራውን ሰብል ያበስለዋል፡፡ በዚህም ገበሬዎቹ ደስ ይሰኙበታል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ መንፈሳዊ ብስለትን የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ ልክ በደቡብ እንደሚነፍሰውና ሰብሎችን እንደሚያበስለው ያለ ተወዳጅ ነፋስ ነው ይላል፡፡ ቀጥሎም ለሐዋርያቱ እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፡፡ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ አስተውሉ በዚህ አንድ ታሪክ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በእሳትም በነፋስም ተመስሎ ሲቀርብ እናገኛለን፡፡ ታዲያ መንፈስ ቅዱስ የተመሰለባቸው ምሳሌዎች መብዛታቸው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንዳብራራው የመንፈስ ቅዱስ ባሕርይ በምልዓት የማይታወቅ መሆኑን ያመለክታል፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በእሳት መመሰል አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በዕብራውያን መልእክቱ ‹‹አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና›› ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡(ዕብ 12፡29) መንፈስ ቅዱስ በእሳት መመሰሉ፣ ከከርሰ ምድር መዓድናትን የሚያወጣ ባለሙያ ከመሬት ቆፍሮ ያወጣውን መዓድን ከትቢያው የሚለየው በእሳት እንደ ሆነ እንዲሁ፣ መንፈስ ቅዱስም ነፍሳችንን ትቢያ ከተባለ ኃጢአት ሁሉ ለይቶ ያነጻታልና በእሳት ተመሰለ፡፡ ይህንንም በተመለከተ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹የእስራኤልም ብርሃን እንደ እሳት፣ ቅዱሱም እንደ ነበልባል ይሆናል፡፡ እሾኹንና ኩርንችቱን በአንድ ቀን ያቃጥላል›› ሲል ይናገራል።(ኢሳ 10፡17) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በመጽሐፈ ምሥጢሩ ለሐዋርያቱ በሃምሳኛው ቀን በእሳት አምሳል የወረደው መንፈስ ቅዱስ ‹‹ሥጋቸውን ሳይሆን የኃጢአታቸውን እሾኽ አቃጠለ›› በማለት ይገልጻል፡፡
Показати все...
እነዚያ እንደ እሳት ላንቃ የተከፋፈሉት ልሳኖች ከመታየትም አልፈው በሐዋርያቱ ላይ መቀመጣቸው፣ ደቀ መዛሙርቱ የሚያዩት ነገር ሁሉ ቅዠት ወይም ምናባዊ ሳይሆን እውነተኛ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ መሆኑን እንዲገነዘቡ ነው፡፡ ከዚያም በኋላ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ልጅ በረገጡና አመጽ ወዳድ በነበሩት አይሁድ ቅንዓትና ቁጣ ሲሞላ፣ የሰላም ልጆች በነበሩት ሐዋርያት ግን መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ (በየአቅማቸው) እንደ ሰጣቸው በሌሎች ቋንቋዎች ይናገሩ ጀመር፡፡ እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ፣ ሐዋርያትም ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በየአገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መስበክ እንደማይችሉ ዐወቀ፡፡ ስለዚህም በሰናዖር ሜዳ የተበተኑትን የዓለምን ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ሰብስቦ ያኖር ዘንድ ቅዱስ መንፈሱን ላከ፡፡ የተላከውም መንፈስ ያለ አንድ ቋንቋ የማይናገረውን የሐዋርያቱን አንደበት በቅጽበት አሰለጠነው። በእውነት እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያለ አስማሪ ማን ነው?!በዚህችም እለት ሐዋርያቱ በዓለም ሁሉ ቋንቋዎች ተሞልተው ከእርሷ የወጡባት የጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) እንደ ምን ያለች ናት?! መንፈስ ቅዱስ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ታይታ የማትታወቅ ልዩ ትምህርት ቤት አደረጋት፡፡ ሐዋርያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተሟሙቀው በሰበኩት በመጀመሪያ ዕለት ስበከት ብዙዎችን አሳምነው አጠመቁ። በዚህ የመከር በዓል አይሁድ ከአዲሱ እህል ለእግዚአብሔር ቁርባን ሲያቀርቡ፣ ሐዋርያቱ ግን የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለሐዲሲቷ ቤተ ክርስቲያን ከእህል ቁርባን ይልቅ የሚወደዱ ምእመናንን ስጦታ አድርገው አቀረቡ። በአይሁድ የመከር በዓል ቀን በሐዋርያቱ በተሰጠ ትምህርት የእግዚአብሔር እርሻ የሆኑ ምዕመናን በዝተው አብበው ተገኙ። እውነትም የመከር በዓል!!! ዲያቆን አቤል ካሳሁን
Показати все...
የጸሎት ጥበብ -፪ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት ልንነጋገር እንደሚገባን እንወቅ፡፡ ጸሎት ማድረስ ያለብን እንዴት እንደ ኾነ እንረዳ፡፥ ይህን ለማወቅ ወዶ ቤተ መጻሕፍት መኼድ፤ ወይም ገንዘብ መክፈል፤ ወይም የንግግር ክህሎትን ለመማር ጊዜ መመደብ አያሻንም፡፡ የተገባ ጸሎትን ስማድረስ መሻት ብቻ በቂ ነው፤ ክህሎቱ በራሱ ይመጣልና፡፥ በዚህ [መንፈሳዊ] ችሎት ፊት የምትናገረውም ለራስህ ብቻ አይደለም! ለሌሎች ለብዙ ሰዎችም ጭምር ነው እንጂ፡፡ በጸሎት ውስጥ ሊኖር የሚገባው ክህሎትስ ምንድን ነው? የጸሎት ጥበብ፥ ይኸውም፦፡ የተዋረደ ልብና የተሰበረ መንፈስ መያዝ፤ በውሒዘ አንብዕ (በዕንባ ጅረት) መቅረብ፤ ከዚህ ዓለም የኾነውን ምንም ነገር አለመሻት፤ የወዲያኛው ዓለም የኾኑ ነገሮችን (ክብሮችን) መሻት፣ መንፈሳዊ ምግባራትን መለመን፤ እግዚአብሔር በጠላቶቻችን ላይ መዓት እንዲያዘንብ አለመለመን፤ ቂም በቀልን ማራቅ፤ [ሥጋዊ] ሁከትን ኹሉ ከነፍስ ማስወገድ፣፤ በተሰበረ ልብ መቅረብ፣ ትሑት መኾን፤ የውሃትን እጅግ መለማመድ፣ ስለ ሌሉች ሰዎች ስንናገር በጎ በጎውን መናገር፤ ከክፉዎች ኅብረት መለየት፣ የዓለም (የሰው) ኹሉ ጠላት ከኾነው ከዲያብሎስ ጋር ምንም ምን አንድነት አለማድረግ ነው፡፡ የዚህ ዓለም ሕጎች እንኳን ሳይቀሩ አንድ ሰው ስለ ንጉሥ ለሌሎች የሚናገር፤ በተለይም ከንጉሥ ጠላቶች ጋር የሚገናኝ ከኾነ ጽኑ ቅጣት ያገኘዋል፡፡ ስለዚህ አንተም ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ራስህና ስለ ሌሎች ስትነጋገር የሰዎች ኹሉ ጠላት ከኾነው ከዲያብሎስ ጋራ ምንም ምን አንድነት ሊኖርህ አይገባም፡፡ ስለዚህ የጸሎትን ጥበብ ገንዘብ አድርግ፡፡ ይህንን ጥበብም (ከቀራጩ) ከመጸብሐዊው ተማር፤ እርሱን መምህር አድርገህ ለመቀበልም አታወላውል፡፡ እርሱ ከአፍአ ሲመረመሩ እዚህ ግባ የማይባሉ ቃላትን በመናገር ማግኘት ያለበትን ኹሉ ለማግኘት የተገባ ኾኗልና (ሉቃ.18፥9-14)፡፡ ተመልከት! በጽርይት ሕሊና በንጽህት ልቡና ስለ ቀረበ አንዲቱ ቃሉ ብቻ ደጀ ሰማያትን ለመክፈት በቂ ነበረች፡፡ ይህችንስ እንዴት ነበር ያቀረባት? ➛ኃጢአቱን በማመን፤ ➛ ደረቱን በመድቃት፤ ➛ዓይኑን እንኳን ወደ ላይ ወደ ሰማይ ቀና ባለማድረግ! አንተም እንደዚህ ብትጸልይ ጸሎትህ ፈጥና ግዳጅ የምትፈጽም ትኾንልሃለች፡፡ ኃጥኡ እንደዚህ በመጸለዩ ጻድቅ ከኾነ፥ ጻድቅ ሰው እንደዚህ አድርጎ ጸሎት ማድረስን ቢያወቅ ደግሞ እንደ ምን ያማረ የተወደደ ሊኾን አንደሚችል ልብ ብለህ አስተውል፡፡ ("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 20-21 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
Показати все...
👍 1
ከጻድቁ ከአቡነ አረጋዊ እና ከቅዱስ ገብረ ክርስቶስ በረከት ረድኤት ይክፈለን። “ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።”ማቴ:፲፥፵፩። ስለ ጻድቃን ሲነሣ “አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም፤”ሮሜ ፡፫፥፲።ተብሎ የለ እንዴ? የሚል ጥያቄ ይነሣል።አዎን ተብሏል።ነገር ግን የተባለው ለማን ነው? የሚለውንም አብሮ መመልከት ያስፈልጋል።እስኪ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ማን እንደ ተናገረው እዚያው ምዕራፍ ላይ አብረን እንመልከት። “እንግዲህ ምን እንላለን? እኛ ከእነርሱ እንበልጣለንን? ከቶ አይደለም፤አይሁዳዊንም፥ አረማዊንም እነሆ፥አስቀድመን ነቅፈናቸዋል፤ሁሉም ስተዋልና።መጽሐፍ እንዲህ እንዳለ ‘አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም፥አስተዋይም የለም፥እግዚአብሔርንም የሚሻው የለም።ሁሉም ተባብሮ በደለ፥በጎ ሥራንም የሚሠራ የለም፥አንድ ስንኳ ቢሆን የለም። ጉረሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው። በአንደበታቸውም ሸነገሉ፥ከከንፈሮቻቸውም በታች የእባብ መርዝ አለ፥አፋቸው መራራ ነው፥መርገምንም የተሞላ ነው።እግሮቻቸውም ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው።በመንገዳቸው ጥፋትና ጉስቁልና አለ።የሰላምን መንገድ አያውቋትም።በዐይኖቻቸውም ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።”ይላል።ሮሜ፡፫ ፥፱-፲፰፣መዝ፡፲፫፥፩-፫፣መዝ፡፶፪፥፩-፫፣መዝ፡፭፥፱፣መዝ፡፻፴፱፥፫፣መዝ፡፲፥፯፣ኢሳ፡፶፱፥፯።እንግዲህ “አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም፤”የተባለው ምንም እምነትና ምግባር ስለሌላቸው ሰዎች መሆኑን ማስተዋል ይገባል። ጻድቅ እግዚአብሔር ነው፥አዎን እግዚአብሔር ጻድቅ ነው።መዝ፡፲፥፯።በመሆኑም እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ሃይማኖት ይዘው፥ምግባር ፥ሠርተው፥ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው በማስገዛት ንጽሕናን እና ቅድስናን ገንዘብ አድርገው የተገኙ አገልጋዮቹ ጻድቃን ናቸው።”ልጆቼ ሆይ፥ማንም አያስታችሁ፥እርሱ (እግዚአብሐሔር) ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ጻድቅ ነው።”ይላል።፩ኛ፡ዮሐ፡፫፥፯።
Показати все...
ቃለ ሕይወት ዘደብረ ታቦር - ዘወርኃ ሰኔ • የወሩ ስም - ሰኔ • የግእዝ ሥርወ ቃለ - ሰነየ • ትርጉሙ - አማረ (አዝርዕቱ) • አበው ስለ ወሩ እንዲህ ይላሉ ፡- “በሰኔ ዝናቡን ወደ እኔ” የሰኔ መዓልት ቀደምት ኢትዮዽያውያን ሰው ወሬ ሲያበዛባቸው "ምነው የሰኔ መዓልትን ሆንክብኝ!" ሲሉ ይተርቡ ነበር ፡፡ "አሳጥርልኝ! ወሬህ ረዘመብኝ!" ለማለት ነው፡፡ ለዚህ መነሻ የሆነው ደግሞ ከ13ቱ ወራት መዓልቱ (ቀኑ) ቶሎ የማይመሽበት ወር ሰኔ መሆኑ ነው፡፡ ከዓመቱ 13 ወራት የሰኔ መዓልቱ ለምን ረዘመ ብንል:- መልሱ አጭር ነው ፡፡ "ይህ የእግዚብሔር ጥበብና ሥራ ነው::" ሳይንሱ ሺህ መንስኤን ሊደረድር ይችላል፡፡ ለእኛ ግን አበው እንዳስተማሩን ሰኔ የሥራና የጾም ወር ነው::ትጋትን የሚወድ አምላክ ይህንን ወቅት ለጾም ለሥራና: ለበጐ ተግባር አርዝሞልናል፡፡ በእርግጥ ጥቂት ሠርተን ብዙ ለምንተኛ ለዚህ ዘመን ሰዎች ይህ ሊጸናብን ይችል ይሆናል፡፡ግን ምንም እንኩዋን ሁሉ ወራት ለሥራ ቢሠሩም ወርሃ ሰኔ ለገበሬና ለክርስቲያን ትልቁን ሥራ የሚጀምሩበት ወቅት ነው፡፡ በሰኔ ያልተጋ ገበሬ ዓመቱን ሙሉ መከረኛ ነው፡፡ ከነ ተረቱም " ሰነፍ ገበሬ  ይሞታል በሰኔ" ይባላል፡፡ክርስቲያንም ከበዓለ ሃምሳ ማግስት በዓለ ጰራቅሊጦስን ተደግፎ ሰኔን ሊተጋባት ግድ ይላል፡፡ በመከራ ዘመን የሚመሰል ክረምት ሳይመጣ በወርሃ ሰኔ ሊተጋ ግድ ይለዋል፡፡ ሽሽቱ በክረምትና በሰንበት እንዳይሆንም ይጸልያል፡፡(ማቴ.24:20) በሰኔ ወር የሚከብሩ ዓበይት በዓላት ሰኔ ፩ - የያዕቆብ ልጅ የጻድቁ ዮሴፍና የሚስቱ የአሰኔት የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው ፡፡ ሰኔ ፪ - ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ፍልሰቱ ፣ ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ ፍልሰቱ ሰኔ ፰ - ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደረቅ ዓለት ላይ ውሀን ያፈለቀበት እለት ከ33ቱ ከእመቤታችን በዓል አንዱ ሰኔ ፱ - ነቢዩ ሳሙኤል ዕረፍቱ ሰኔ ፲፪ - ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት ፣ ቅዱስ ላሊበላ ሰኔ ፳ -ሕንጻተ ቤተክርስቲያን ሰኔ ፳፩ - ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእመቤታችንን ቤት ያነጸበት / እርሷም በጎልጎታ በጌታችን መቃብር የጸለየችበት ሰኔ ፳፫ - የንጉስ ሰሎሞን ዕረፍቱ ሰኔ ፳፬ - አባ ሙሴ ጸሊም ሰማዕት የሆነበት ዕለት ሰኔ ፳፭ - የክረምት መግቢያ ፤ የጸደይ መውጫ ሰኔ ፴ - ቅዱስ ዮሐንስ መጥመቀ መለኮት በዓለ ልደቱ
Показати все...
👍 2
የጸሎት ጥበብ - ፩ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርን የተረዳ ያወቀ ሰው እግዚአብሔርን እንደሚገባ'ው አድርጎ ሲያነጋግረው ከዚያን ጊዜ አንሥቶ መልአክ ይኾናል፡፡ ነፍስ ከፈቃዳተ ሥጋ ሰንሰለት ነጻ የምትወጣው በዚህ መንገድ ነውና፤ ሕሊና ከፍ ከፍ የሚለው በዚህ መንገድ ነውና! ማደሪያችን ወደ ሰማይ የሚሻገረው በዚህ መንገድ ነውና፤ አንድ ሰው ግብረ ዓለምን የሚንቀው በዚህ መንገድ ነውና፤ አንድ ሰው የቱንም ያህል ነዳይ ወይም ባሪያ ወይም ተራ ወይም ዝቅ ያለ ቢኾንም እንኳን በንጉሥ ዙፋን ፊት የሚቆመው በዚህ መንገድ ነውና፡፡ እግዚአብሔር የሚመለከተው የንግግርን ውበት ወይም የቃልን ርቱዕነት ሳይኾን የመንፈስን ንጹህነት ነውና፡፡ በዚህ መንገድ መጥተን ወደ አእምሮአችን የመጣውን ብንናገርም እንኳን፥ ጸሎታችን ግዳጅ የሚፈጽም ኾኖናልን እንመለሳለን፡፡ እንግዲህ ይህን ማድረግ ምን ያህል ቀላል እንደ ኾነ ታስተውላለህን? በዚህ ዓለም ሰዎች ዘንድ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ለመለመን የንግግር ክህሎት (ብልሐት) ያሻዋል፡፡ የሚለመነው ሰው በቀላሉ የማይገኝ ከኾነ ደግሞ አጃቢዎቹን ማሳመን ይኖርበታል፡፡ ጥሮ ለፍቶ ካገኘው በኋላም ጉዳዩን በዝርዝር ማስረዳት ይጠበቅበታል፡፡ እግዚአብሔርን ለማናገር ግን የዚሁ ተቃራኒ ነው፡፡ ከተሰበረ ልብ በቀር ሌላ ምንም ምን አያስፈልግም፤ ወደ እርሱ ለመቅረብም የሚከለክል ማንም አይኖርም፡፡ “እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ ሩቅ አምላክ አይደለሁም” ይላልና (ኤር.23፥23)፤ የምንርቀው እኛ ነን እንጂ እርሱ ዘወትር ቅርብ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማነጋገር የንግግር ክህሎት (ብልሐት) አያስፈልገንም የምለውስ ለምንድን ነው? እንዲያውም ብዙ ጊዜ ድምፅም ቢኾን አያስፈልገንም፡፡ አንተ በልብህ ብትናገርና እግዚአብሔርን ማናገር እንዲገባ'ህ ብታናግረው እርሱ ጸሎትህን ለመስማት ዘንበል ይላል፡፡ ሙሴ ጸሎቱ የተሰማው በዚህ መንገድ ነውና፤ ሐና ጸሎትዋ የተሰማው በዚህ መንገድ ነውና፡፡ ወደ እግዚአብሔር እንዳይቀርቡ ብሎ ሕዝቡን ለማራቅ የሚቆም ወታደር የለም፤ አሁን ሰዓቱ አይደለም ብሎ የሚከለክል ዘበኛም የለም፡፡ እግዚአብሔርም፦ “አሁን ላነጋግርህ አልችልም፤ ሌላ ጊዜ ተመለስ” አይልም፡፡ ይልቅ ልታነጋግረው በመጣህበት ቅጽበት አንተን ለመስማት ይቆማል፡፦፥ የምሳ ሰዓትም ቢኾን፣ የአራት ሰዓትም ቢኾን፤ እጅግ አስቸጋሪ ጊዜም ቢኾን፣ በገበያ ቦታም ቢኾን፣ በመንገድ ላይም ቢኾን፤ በባሕር ውስጥም ቢኾን፣፤ በዳኛ ፊት በምትቆምበት በችሎት ፊትም ቢኾን፥ እግዚአብሔርን ብትጠራው መጥራት እንደሚገባህ አድርገህ እስከ ጠራኸው ድረስ ጸሎትህን እንዳይሰማ የሚከለክለው ግድግዳ የለም፡፡ ... ("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 18-19 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
                        †                           [ " ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች "  ] ▪ - [ በመከራ ውስጥ ያለ የሚጸልየው ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ፦ " በጠራሁህ ጊዜ ቅረበኝ ! " ] - [ በጠራሁህ ጊዜ በምህረትና በይቅርታ ቅረበኝ ! ] ------------------------------------------------ ❝ በሰማይም ሰልፍ ሆነ:: ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ:: ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ:: አልቻላቸውምም:: ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም:: ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ወደ ምድር ተጣለ:: ❞ † [ራዕ.፲፪፥፯] ❝ ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።❞ [ራእ.፲፰፥፩] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
Показати все...
+ የተሠጠህን ቁጠር + ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው። የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም። ዕባብ ደግሞ የስይጣን አንደበት ነበረ። ሰይጣን እንዲህ አላት:- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። ልብ አድርጉ እግዚአብሔር "ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ" አላለም። የከለከለው አንዲት ዛፍ ነው:: ሰይጣን ግን ሁሉን ተከልክላችሁዋል? ብሎ እንዳላዋቂ ጠየቀ። ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግግሩን የከፈተው በውሸት ነበረ። ዓላማው ከሔዋን መረጃ ለማግኘት አልነበረም። ሔዋን እስከዛሬ ያላሰበችውን ማሳሰብ ነበር። ብሉ ተብሎ ከተሠጣቸው ብዙ ሺህ ዛፍ ይልቅ የተከለከሉትን አንዲት ዛፍ አሳይቷት ሔደ። ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስላልተሠጣት ማሰብ ጀምራ ደስታዋን አጣች። የተከለከለችውን በልታ የተሠጣትን ብዙ ሥጦታ ከነሠጪው አጣች። ወዳጄ የቀደመው እባብ ዛሬም መርዙን ይረጫል በሕይወታችን ከተሠጠን ብዙ ነገር ይልቅ ያልተሠጠንን ጥቂት ነገር እናስባለን። ገንዘብ እንደሌለህ እያሰብክ ጤና እንዳለህ ትረሳለህ። ጫማ እንደሌለህ እያሰብክ እግር እንዳለህ ትረሳለህ። አልጋ እንደሌለህ እያሰብክ እንቅልፍ እንዳለህ ትረሳለህ። ስለዚህ ውስጥህ ያለውን የዕባቡን ድምፅ  አትስማ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ይበልጣልና የተሠጠህን ቁጠር። (ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
Показати все...
👍 1
Авторизуйтеся та отримайте доступ до детальної інформації

Ми відкриємо вам ці скарби після авторизації. Обіцяємо, це швидко!