cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል

ይኽ የፈረንሳይ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መካነ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ቻናል ነው። በዚኽ ቻናል በመንፈሳዊ ሕይወትዎ የሚበረቱባቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች ባሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ።

Більше
Рекламні дописи
1 016
Підписники
+124 години
Немає даних7 днів
-530 днів
Час активного постингу

Триває завантаження даних...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Аналітика публікацій
ДописиПерегляди
Поширення
Динаміка переглядів
01
እንዴትና ከምን እንጹም? - የጾም ሃይማኖታዊ ትርጉም ፈጣሪን መለመኛ ከኃጢአት ቁራኛ መላቀቂያ መሣሪያ ስለሆነ በጾም ወራት ለአምሮት ለቅንጦት የሚበሉ ወይም ለመንፈሳዊ ኋይል ተቃራኒ የሆኑ የአልኮል መጠጦች ሥጋና ቅቤ ወተትና እንቁላል ማራቅታዟል - ባልና ሚስትም ከአንድ ላይ አይተኙም 1ኛ ቆሮ 6፥5 - ሥጋዊ ጉልበትን በጾም የማድከም ቅብአት ካላቸው ምግቦች መከልከልም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለው ለምሳሌ ዳዊት በመዝሙር 108፥24  ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ ሥጋዮም ቅቤ በማጣት ከሳ ብሏላ ፣ ሠለስቱ ደቂቅና ነቢዩ ዳንኤልም የቤተ መንግሥቱን ሥጋና የጸሎት ምግብ ትተው በጥሬና በውኃ መቆየታቸው ተፅፎአል ት.ዳን 1፥8-21፣ት.ዳን10፥2 ዋናው ነገር ጾም እንጂ መብል ወደ እግዚአብሔር አያቀረበንም ብንበላም የምናተርፈው ባንበላም የሚጎዳን ነገር የለም 1ኛ ቆሮ8 ፥8 ከአዳም ጀምሮ መብል ሲጥል እንጂ ሲያነሣ አላየንምና ጾሙን ከኃጢአት  በመራቅ ለራስ ያስብነውን ለነዳያን በመስጠት፣ ጾም ከፀሎት ጋር ሲሆን ጸጋን እንደ ሐዋርያቱ  ያሠጣልና  በጸሎት በመትጋት በስግድት ወደ እግዚአብሔር በፍፁም ልብ በመመለስ ልንጾመው ይገባል፡፡ #ሼር https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw
400Loading...
02
Photo
901Loading...
03
††† እንኳን ለጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት አባ ድምያኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† አባ ድምያኖስ ††† ††† አባ ድምያኖስ ተወልደው ያደጉት ግብጽ ውስጥ ነው:: ቤተሰቦቻቸው ክርስቲያኖች በመሆናቸው ገና በልጅነት ዕድሜአቸው ቅዱሳት መጻሕፍትንና በጐ ምግባራትን ተምረዋል:: ዕድሜአቸው ወደ ወጣትነቱ ሲጠጋ ሥርዓተ መነኮሳትን ለማጥናት ወደ ገዳመ አባ ዮሐንስ ሔዱ:: በዘመኑ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ፈተና ሳያልፍ እንዲመነኩስ አይፈቀድለትም ነበር:: አንድ ሰው ሊመነኩስ ካሰበ በትክክል መናኝ መሆኑ ቢያንስ ለሦስት ቢበዛ ደግሞ ለአሥራ ሁለት ዓመታት እንዲፈተን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታዝዛለች:: ይኸውም "ሥርዓተ አመክሮ" ይባላል:: ከአሥራ ሁለት ዓመታት በላይ መቆየት ከፈለገ ግን ይፈቀድለታል:: በዚህም መሠረት አባ ድምያኖስ ለአሥራ ሰባት ዓመታት በአጭር ታጥቀው ገዳሙን አገልግለዋል:: ገዳሙም ይገባሃል በሚል ዲቁና እንዲሾሙ አድርጓል:: ከዚህ በኋላ ከአባቶች ተባርከው: ገዳሙንም ተሰናብተው ወጡ:: ነገር ግን የወጡት ወደ ዓለም ሳይሆን ራቅ ወዳለ ገዳም ነው:: የረድዕነት ዘመናቸውን ጨርሰዋልና አዲስ በሔዱበት ገዳም ወደ መደበኛው ገድል ተሸጋገሩ:: ያም ማለት በጾም: በጸሎት: በስግደት: በትሕርምት: በትሕትናና በፍቅር ሙሉ ጊዜአቸውን ማሳለፍ ጀመሩ:: በእንዲሕ ያለ ግብርም ዘመናት አለፉ:: የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ አባ ጴጥሮስ በእረኝነት ሥራ የሚያግዛቸው ሰው እንዲፈለግላቸው በጠየቁት መሠረት ትምሕርትም: ጽሕፈትም: በጐ ምግባራትም የተሟላለት ሰው እንደ አባ ድምያኖስ አልተገኘምና ያለፈቃዳቸው ወደ እስክንድርያ ተወስደው የፓትርያርኩ ረዳት ሆነው ተሾሙ:: በረዳትነት በቆዩበት ጊዜ በወንጌል አገልግሎትና በመንኖ ጥሪት ሕዝቡንና ሊቀ ጳጳሳቱን አስደስተዋል:: ልክ አባ ጴጥሮስ ሲያርፉ ሕዝቡና ሊቃውንቱ በአንድ ድምጽ አባ ድምያኖስን ለፓትርያርክነት መርጧቸዋል:: ጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት በዘመነ ፕትርክናቸው ከግል የቅድስና ሕይወታቸው ባለፈ እነዚህን ፈተናዎች በመወጣታቸው ይመሰገናሉ:: 1.ሕዝቡ ከሃይማኖታቸው እንዳይወጡና በምግባር እንዳይዝሉ ተግተው አስተምረዋል:: 2.በአካል ያልደረሱባቸውን በጦማር (በመልዕክት) አስተምረዋል:: 3.በዘመናቸው የተነሱትን መናፍቃን ተከራክረው : የተመለሰውን ተቀብለው : እንቢ ያሉትን አውግዘዋል:: 4.ከአንጾኪያ ፓትርያርክ የመጣውን የኑፋቄ ጦማር (መልዕክት) በይፋ ተቃውመው አውግዘዋል:: ለአርባ ሦስት ዓመታት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ሆነው ያገለገሉት አባ ድምያኖስ ከብዙ ትጋት በኋላ በመልካም ሽምግልና በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ከግብጽ አበው ሊቃነ ጳጳሳት ዝርዝር ውስጥም አርባ አምስተኛ ሆነው ተመዝግበዋል:: ††† ልመናቸው : ክብራቸው : ጸጋ ረድኤታቸው አይለየን:: ††† ሰኔ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አባ ድምያኖስ ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት 2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ 2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን) 3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ 4.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ ††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት : ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" ††† (ሐዋ. ፳፥፳፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/zikirekdusn
770Loading...
04
ጾመ ሐዋርያት ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው  ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡ ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘለዓለማዊ ዝምድና አለው፡፡ በብሉይ ኪዳን ጾም ከፍተኛ ቦታ ነበረው፡፡ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውኃ ለአፋቸው አይገባም ነበር፡፡ ዘዳ 34፥28 በኃጢአታቸው ብዛት የመጣባቸው መዓት የሚመልሰው ቁጣውም የሚበረደው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር፡፡ዮና 3፥5-10 በአዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሣይሆን ራሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው መጀመሪያ አድርጎ የሠራው ሕግ ነው፡፡ ማቴ 4፥21 ጌታችን በስስት በፍቅረ ንዋይና በትዕቢት የሚመጣበትን ጠላት ዲያቢሎስ በጾም ድል እንድምንነሣው አሳየን፡፡ ይህም ብቻ ሣይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር ጠላት ስይጣንን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል ማቴ 17፥21 በጾም የተዋረደና ለጸሎት የተጋ ሰውነት ለእግዚአብሔር ለመታዘዝ የተዘጋጀ በመሆኑ እግዚአብሔር ያዘናል እኛም እንታዘዝለታለን፡፡ ስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ቀሳውስት የሚሾሙትም በጾምና በጸሎት ነበር፡፡ የሐዋ13፥3፤4፥25 እነ ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ያላሰቡትን ክብር ያገኙት በጾማና በጸሎት ፈጣሪያቸው ማልደው ነው  የሐዋ 10፥20 ጾም እንኳን የጠበቅነውንና ያሰብነውን ቀርቶ ያላሰብነውንና ያልጠበቅነውን ፈጽሞም የማይገባንን ጸጋና ክብር የሚየሰጥ ነው፡፡ ከሐዋርያት ቤተክርስቲያን በዓልና ትውፊት መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመጀመሪያዎቹ አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ስለሆነች የጾም ሕግና ሥርዓት አላት  እነዚህም የፈቃድና የአዋጅ አጽዋማት ይባላሉ፡፡ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ የሐዋርያት (የሰኔ) ፆም ነው፡፡ ይህም ጾም በሕዝብ ዘንድ የወታደር ጾም ይባላል፡፡ ለስብከተ ወንጌል ዘመቻ የተዘጋጀ በጾሙት ተምሣሌት በድሮ ዘመን ወታደሮች ለዘመቻ ሲነሱ ወይም ከዘመቻ ሲመለሱ በተሳተ በተገጸፈ ይቅር በለን በማለት ይጾሙት ነበር፡፡ ይህም ጾም የሚፈሰክበትከሐምሌ 5 የማይለቅ ቢሆንም የሚጀመርበት ግን  የተወሰነ ቀን የለውም በዚህም ምክንያት የጾሙ ዕለት ቁጥር ከፍና ዝቅ ይላል አንዳንድ ጊዜ ከአርባ ይበልጣል አንዳንድ ጊዜ ከ30 ያንሣል ያሁኑም ጾም ሰኔ 17 ገብቶ  ለ 2 ሳምንት  ከ 3 ቀናት ይጾማል፡፡  ይቀጥላል https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw
1131Loading...
05
Photo
1030Loading...
06
✝ ስብሐት ብጡል (ከንቱ ውዳሴ) ✝ (ክፍል ፩) ✝ በስመ ሥሉስ ቅዱስ ✝ " ስብሐት ብጡል (ከንቱ ውዳሴ) " =>አበው ሊቃውንት የከንቱ ውዳሴ ሕመም 3 ደረጃ (ምልክት) እንዳለው ይናገራሉ:: "ደረጃ 1 (ሕመሙ ሲጀምር)" ¤አንድ አገልጋይ ከሰው ምስጋናን ሽቶ ባይሠራም ሲመሰገን ልቡን ደስ ደስ ይለዋል:: ይህን ጊዜ ማረም ከተቻለ እጅጉን ቀላል ነው:: "ደረጃ 2 (ሕመሙ ሲባባስ)" ¤አገልጋዩ "አመስግኑኝ" አይልም:: ግን የሚሠራው ሁሉ መመስገንን ሲሻ ነውና ተግባሩ ሁሉ የተርዕዮ (የእዩልኝ) ይሆናል:: ሠርቶ ካልተመሰገነም ይከፋዋል:: በዚህ ጊዜም በሽታውን ለመንቀል መትጋት ከተቻለ ሊድን ይችላል:: "ደረጃ 3 (ሕመሙ ሲጸና/ሲከፋ) ¤እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው አጋንንት ሙሉ በሙሉ ስለሚቆጣጠሩት ለመመስገን ሲል ከኑፋቄና ክህደት ሁሉ ሊደስርስ ይችላል:: የማያመሰግኑትን ሰዎች ከመጥላት አልፎ ለመጉዳትም የሚያስብ ሰው ይሆናል:: በቀላሉ ይህ ሰው ለእግዚአብሔር የሚገባውን ክብር የሚመኝ በመሆኑ ተግባሩ ሁሉ ሰይጣናዊ ይሆናል:: ✝ውዳሴ ከንቱ የሚሉት በሽታ እዚህ ደረጃ ላይ ከደረሰ የመዳን ተስፋው እጅግ የመነመነ ነው:: ነገር ግን ሕመምተኛው (ውዳሴ ከንቱ የጠለፈው አገልጋይ) ችግሩን አውቆ ንስሃ ከገባና ለትህትናዊ ሕይወት ከቆረጠ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ሊድን መቻሉ የሚጠረጠር አይደለም:: ✝ስለዚህም አበው ሲመክሩ "ከሚገስጽህ እንጂ ከሚያመሰግንህ ሰው ጋር አትዋል" ይላሉ:: <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> Re. Dn Yordanos ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
1140Loading...
07
Media files
1540Loading...
08
Photo
1850Loading...
09
✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞✝ ❖✝ እንኳን አደረሳችሁ ❖✝ ✞ ✞ ✝እንኩዋን ለሰማዕቱ #ቅዱስ_ሚናስ ዓመታዊ የቅዳሴ ቤት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ✞✝ +"+✝ #ቅዱስ_ሚናስ ምዕመን ሰማዕት +"+✝ =>ቅዱስ ሚናስ ( #ማር_ሚና ) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው:: ልክ በሃገራችን #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም:: +ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ ነው:: በተለይ ለታመመ: ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ: ባለ በጐ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው:: +ግብጽ ውስጥ ቅዱሱን የማያውቅ ሰው ካገኛችሁ እርሱ ኦርርቶዶክሳዊ አይደለም ማለት ነው ሲባልም ሰምተናል:: በነገራችን ላይ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር በመስጠት: ታሪካቸውን በመጻፍ: በማጥናት: በመጽሔት: በፊልምና በመሳሰሉት ለሕዝብ በማስተዋወቅ ግብጻውያኑ ከእኛ ብዙ ርቀት ሒደዋል:: ዛሬ እንኩዋ የምንጠቀምበትን ስንክሳር 80 ከመቶ እጁን ያዘጋጁት እነርሱ ናቸው:: +አባቶቻችንና እናቶቻችን #ኢትዮዽያውያን_ቅዱሳን ግን አብዛኞቹ ተረስተው ቀርተዋል:: መጽሐፈ ገድላቸውንም ብል በልቶታል:: ዛሬም የቤት ሥራው የእኛ ብቻ ነው:: +ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ሚናስ (ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው):- ¤በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ ¤በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ ¤በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ ¤ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ ¤በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት ሰማዕት ነው:: +እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል:: +የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ በዳ የበጐችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን አደረገ:: አንድ እረኛ በጐቹ ድውያን ሆኑበት:: በዚያ ሰሞን ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ:: +በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጐቹን አምጥቶ ነከራቸው:: እነርሱም ተፈወሱ:: ይህ ዜና በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ ገቡ:: ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ አልቻሉም:: +ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን ከሠራዊቱ ጋር ላካት:: ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና ፈውስን አጥታ ነበር:: መጥታ ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች:: +#ቅዱስ_ሚናስ በሌሊት ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች:: ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም " #መርዩጥ " ተባለ:: ጸበሉ የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ #ቤተ_ክርስቲያን ታንጾበት በዚህች ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል:: =>አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን:: =>ሰኔ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ) =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ 2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት) 3.ቅድስት እንባ መሪና 4.ቅድስት ክርስጢና =>+"+ ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይሕን እጽፍልሃለሁ:: ብዘገይ ግን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ:: ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው:: እግዚአብሔርንም የመምሠል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው:: +"+ (1ጢሞ. 3:14) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
1542Loading...
10
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን ✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11     ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥ ፆም ማለት ምንድ ነው ❓ ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥ እንኳን ለታላቁ ለሐዋርያት ጾወም በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን 📌 ፆም ❖ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ትምህርት መሰረት ጾም የማህበርና የግል ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡ ❓ ፆም ምንድ ነው ❖ ጾም ማለት ሰው ምግብ ወይም ሰውነት ከሚፈለጋቸው ነገሮች መካከል መወሰን ማለት ነው፡፡ ❖ ጾም በጥንተ ፍጥረት አትብላ ተበሎ የህግ መጠበቅም ሆኖ ለሰው ልጅ ከተሰጠው ትዕዛዝ ጾም ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ስርአት ስለሆነ ሃይማኖት በለበት ሁሉ አለ፡፡ ❖ ጾም ለተውሰነ ጊዜ ከእህልና ውሀ መከልከል ብቻ ሳይሆን ለሰውነት የሚምረውን ለማየት እና ለመፈጸም የሚያስጎመጀውን ነገር ሁሉ መፈጸም ነው፡፡ ❖ በተግባራዊ ትርጉም የተረዱና የተጠቀሙበት ሰዎች ጾምን ‹‹ለፀሎት እናቷ፣ ለእንባ መፍለቂያዋ ለበጎ ስራ ሁሉ መሰረት ›› በማለት ተርጉመውታል፡፡ 📌 የፆም አስፈላጊነት ❖ ሃይማኖት መሰረት ነው ነገር ግን ቤት በመስራት ብቻ የተሟላ እንደማይሆን ሃይማኖትንም ፍጹም የሚያደርጉት በእርሱ መሰረትነት ነው የመሚታነጹ ስነ ምግባራት ናቸው፤ ጾም፣ ጸሎት፣ ምጽዋትና ስግደትን የመሰሉት ምግባራት ሃይማኖትን እንዲሰራ ያደርጉታል፡፡ ❖ ጾም የስጋን ምኞትን እና ፈቃድን ለማስታገስ ይረዳል፡፡ 📖መዝ 34፥13፣ 📖ሮሜ 8፥12-14፣ 📖1ኛ ቆሮ 6፥12 ✍‹‹ ለሚጠፋ ምግብ አትስሩ ይልቅስ የሰው ልጅ ለሚሰጣቹህ የዘለዓለም ህይወት ለሚሆን ምግብ ስሩ›› 📖ዮሐ 6፥7 ❖ ጾም በአምሮት በምኞትና በስስት ጸባዮች ላይ የበላይነት ያስገኛል፡፡ 📌 በፆም የተጠቀሙ ሰዎች ⓵ በብሉይ ኪዳን ❖ የሰማርያው ንጉስ አክአብ 📖1ኛ ነገ 20፥27 ❖ የእስራኤል ሰዎች 📖2ኛ ዜና 20፥1-23 ❖ በጉዞ ላይ የነበሩ ሰዎች 📖ህዝ 8፥21 ❖ የነነዌ ሰዎች 📖ዮናስ 3፥3 ❖ ነብዩ ነሕምያ 📖ነህ 1፡2 ❖ ሃማ በተነሳ ጊዜ 📖አስቴር 3፡9 እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን ⓶ በሐዲስ ኪዳን ❖ በሐዲስ ኪዳን ጾም የጀመረው ክርስቶስ ነው፤ ክርስቶስ ከጾም በኋላ 3 ነገሮችን ድል ነስቷል፡፡ ❶ ስስት ❷ ትእቢት ❸ ፍቅረ ነዋይ ❖ መላእክትም ቀርበው አገልግለውታል፡፡ 📖መዝ 90፥11 ፣ 📖ማቴ 4፥1 ፣ 📖ሮሜ 14፥1-6 📌 የአዋጅና የግል ጾም ⓵ የአዋጅ ጾም ❖ በአባቶቻችን የተደነገጉ ሰባት አጽዋማት አሉ፡፡ ➘ ጾመ ነብያት ➘ ጾመ ገሃድ ➘ ጾመ ነነዌ ➘ ዓብይ ጾም ➘ ጾመ ድህነት ➘ ጾመ ሐዋርያት ➘ ጾመ ፍልሰት 📌 ጾመ ነብያት ❖ ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ይጠብቁ የነበሩ ነብያት የጾሙት ነው፤ ነብያት ስለ መሲህ መምጣት በናፍቆት ይጸልዩ ነበር፡፡ 📌 ጾመ ገሃድ ❖ ገሃድ ማለት ግልጥ ይፋ፣ በገሃድ የሚታይ ማለት ነው፡፡ ❖ መለኮት የተገለጠበት ጌታ ልዩ የሆነ የአንድነትና የሶስትነት ምሥጢር የተገለጠበት ስለሆነ ይህን ስያሜ አግኝቷል፡፡ 📖ማቴ 3፥16 📖ዮሐ 1፥29 📌 ጾመ ነነዌ ❖ ይህ የነነዌ ሰዎች የጾሙት ነው፤ የዚያች አገር ሰዎች የፈጸሙት በደል በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ሆኖ በመገኘቱ ቅጣት ታዝዞባቸው ነበር፤ የነነዌ ጾም ሰኞ፣ ማክሰኞና ዕረቡ ሶስት ቀን ነው፡፡ 📌 ዓብይ ጾም ❖ ሙሴ በሲና ተራራ ህጉን ከማቅረቡ በፊት 40 ቀን 40 ሌሊት ጾሟል፤ ጌታም ወንጌል ከመስበኩ በፊት በገዳመ ቆሮንጦስ 40 ቀን 40 ሌሊት ጾሟል፡፡ ❖ ይህ ጾም ዓብይ ወይም ሁዳዴ በመባል ይታወቃል፤ ዓብይ የሚሰኘው ዓብይ ነብያት የጾሙት በሐዲስ ኪዳንም ጌታም የኦሪተንና የነቢያትን ህግ ለመጠበቅና ለመፈጸም ሲል የጾመው በጾሙ ፍጻሜ ከሰይጣን የመጣውን ፈተና ድል የነሳበት በመሆኑ ነው፡፡ ❖ በዓብይ ጾም ሰባት ቅዳሜ ስምንት እሁድ ይገኛሉ፤ ይህም የጾሙን ጊዜ ስምንት ሳመንታት ያደርገዋል፡፡ ❖ የመጀመርያው ሳምንት ህርቃል ተብሎ ይታወቃል ወደ ጾሙ መግቢያ መለማመጃ ማለት ነው፤ የመጨረሻው ሳምንት ሕማማት ነው ክርስቶስ መከራ የተቀበለበት ቀን በመሆኑ ነው፡፡ 📌 ጾመ ሐዋርያት ❖ ጾመ ሐዋርያት ሀብተ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ወንጌልን ለሕዝብ ከማስተማራቸው አስቀድመው ጾመዋል፤ የሰኔ ጾም ይባላል፡፡ ❖ ይህ ጾም ከፍና ዝቅ ስለሚል የተወሰነ ቀን የለውም አንዳንድ ጊዜ ከአርባ ይበልጣል ሌላ ጊዜ ደግሞ ከሰላሳ ያንሳል፡፡ 📌 ጾመ ድህነት (የዕረቡና የአርብ) ❖"ከትንሳኤ በኋላ ከሚኖሩት 50 ቀኖች በቀር ዕረቡና አርብ ዓመቱን በሙሉ የጾም ቀኖች ናቸው፡፡ ❖ እንደጾሙአቸው የተደረገው አርብ እና ዕሮብ፤ ዕሮብ የተፈረደበት አርብ የተሰቀለበት ቀን መሆኑን አስመልክቶ ነው፡፡ 📌 ጾመ ፍልሰታ ❖ ጾመ ማርያም ይባላል፤ የእመቤታችን የዕረፍት፣ ትንሳኤና ዕርገት ምሥጢር ለሐዋርይት የተገለጠበት ታሪክ መታሰቢያ ጾም ነው። ❖ ሐዋርያት ከሐምሌ 1-14 ድረስ ጾመው ድንግል ማርያም ተገልጣላቸዋለች በ 16ኛው ቀን አርጋለች፡፡ ⓶ የግል ጾም ❖ በሕግ የታወቁ አጽዋማት በግልጥ በማህበር ይጾማሉ፤ የግል ጾም ግን ከዚህ የተለየ ነው። ❖ በሰዎች የግል ፍላጎትና የሕሊና ውሳኔ ሚጾም የፈቃድና የንስሐ ጾም ነው፡፡ 📖ማቴ 5፥6 📖ማቴ 6፥18 📖ዳን 6፥10 በአጠቃላይ ከላይ የተመለከትናቸው ከፍፁም ኃጢአትና ከበደል ተጠብቀን እንድንጾም አምላከ ቅዱሳና ይርዳን እንዲሁም የእናቱ የንፅህተ ንፅሀን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ጸሎት አይለየን ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 ✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ 🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ      ✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" 📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ                ወስብሐት ለእግዚአብሔር                               ይቆየን  ───────────                     Channel  🧲  https://telegram.me/Tewahedo12         FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ) 🧲  http://facebook.com/Tewahedo12           YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ) 🧲 https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw  ───────────
1452Loading...
11
#እንደ_ኃጢአት_አዋራጅ_የለም እንደ ኃጢአት አዋራጅ የለም፡፡ ኃጢአትን የሚያደርግ ሰው በሐፍረት ካባ ብቻ የሚከናነብ አይደለም፤ አስቀድሞ ከነበረው ማስተዋልና ማገናዘብም ይዋረዳል እንጂ፡፡ ይህንንም ለመረዳት የአዳም የቀድሞ ክብሩን ማሰብ እንቸችላለን፡፡ ዳግመኛም ኃጢአትን ከሠራ በኋላ ያገኘውን ውርደት እንመልከተው፡፡ “በሰርክ ጊዜ ጌታ በገነት ውስጥ ድምፀ ሰናኮ ብእሲ እያሰማ ወደነርሱ ሲመጣ በሰሙ ጊዜ አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር ፊት በገነት ዕንጨት መካስከል ተሰወሩ” (ዘፍ.3፥8)፡፡ በዚህስ አዳም እንደ ምን ባለ ውርደት እንደ ተያዘ ታስተውላላችሁን? ምሉእ በኩለሄ ከኾነው፣ ፍጥረታትን ካለ መኖር ወደ መኖር ካመጣው፤ የተሰወረውን ኹሉ ከሚያውቀው፤ የሰውን ልቡና የፈጠረና በኀልዮ የሠሩትን ዐውቆ ከሚፈርደው (መዝ.33፥15)፤ ልብ ያሰበውን ኩላሊት ያጤሰውን መርምሮ ከሚያውቀው (መዝ.7፥9)፤ ልቡናችን ያሰበውን ከሚያውቀው (መዝ.44፥21) ከእግዚአብሔር ሊሸሸግ መውደዱ ከማወቅ ወደ ድንቁርና ከክብር ወደ ኃሣር እንደ ኼደ ያመለክታልነ፡፡ እኛም ኃጢአት ስንሠራ እንደዚህ ነው፡፡ መሸሸግ ባንችል እንኳን መሰወርን እንሻለን፡፡ ይህን ማድረጋችንም በኃጢአታችን ምክንያት ክብራችን እንደ ምን እንዳጣን፤ ሐፍረታችንን መሸፈንም እንደ ምን እንዳቃተን ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ኃጢአትን የሠራ ሰው እንኳንስ በረኻ በኾነች በዚህች ምድር በገነት መካከልም መደበቅ አይችልም፡፡ ("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 81 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
1190Loading...
12
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ✞ ✞ እንኩዋን ለአራቱ ቅዱሳን አበው ሰማዕታት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ✞ => #4ቱ_ቅዱሳን አበው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ሲሆኑ ስማቸው #አባ_አክራ : #አባ_ዮሐንስ : #አባ_አብጥልማ እና #አባ_ፊልዾስ ይባላሉ:: ከመከራ ዘመን በፊት (ማለትም በቀደመ ሕይወታቸው) ካህናትና ሃብታሞች ነበሩ:: ሀብቱ ግን በሥራ ብቻ የተገኘ ነው:: +ታዲያ ቅዱሳኑ በያሉበት ሆነው በሀብታቸው እንግዳ እየተቀበሉ: ድሆችን እያበሉ: በክህነታቸው ደግሞ እያስተማሩና እየናዘዙ ትጉሃን ስለ ነበሩ በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ነበራቸው:: በእንዲህ ያለ ግብር ሳሉ ዘመነ ሰማዕታት አሐዱ አለ:: "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" እያሉ መኩዋንንቱና ነገሥታቱ ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሰቃዩ ገቡ:: +በዚህ ጊዜ 4ቱ ቅዱሳን አንድ ነገር መከሩ:: በየእሥር ቤቱ የተጣሉ ክርስቲያኖችን ለማገልገል ቆረጡ:: እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩ እሥረኞችን ያጽናኑ ገቡ:: የራበውን ያበላሉ: የተሰበረውን ይጠግናሉ: በቁስሉም ላይ መድኃኒትን ያደርጉ ነበር:: የመከራው ዘመን ግን እየረዘመ: ግፉም ከልክ እያለፈ መጣ:: +በዚህ ጊዜ 4ቱ ቅዱሳን ትልቁንና የመጨረሻውን ውሳኔ አስተላለፉ:: ከሰማዕታት ወገን ይቆጠሩ ዘንድ መርጠዋልና: ክርስቶስን በሞቱ ይመስሉት ዘንድ ሽተዋልና: የሩጫቸው መጨረሻ ሰማዕትነት እንዲሆን መረጡ:: +አራቱም ያላቸውን ንብረት ሁሉ ሰብስበው ለነዳያን አካፈሉ:: በትከሻቸው ካለች አጽፍ በቀር ስባሪ ገንዘብ ከሃብታቸው አላስቀሩም:: ከዚያ ጉዞ ወደ ምስክርነት አደባባይ (ዐውደ ስምዕ) አደረጉ:: +በዙፋኑ የተቀመጠው የመኮንኑ ግርማ: መሬት ላይ የፈሰሰው የወገኖቻቸው ደም: የሠራዊቱ ድንፋታ ቅዱሳኑን አላስፈራቸውም:: በይፋ "ክርስቲያን ነን" ሲሉ ተናገሩ:: በዘመኑ እንዲሕ ብሎ መናገር አንገት የሚያስቆርጥ ትልቅ ድፍረት ነበር:: +መኮንኑም ከበጐ ሃይማኖታቸው ይለያቸው ዘንድ በእሳት አቃጠላቸው:: እግዚአብሔር አዳናቸው:: በቀስትም: በስለትም: በብረትም ለቀናት አሰቃያቸው:: ቅዱሳኑ ግን አምላካቸውን አምነው ሁሉን በአኮቴት ተቀበሉ:: በመጨረሻ ግን በዚሕች ዕለት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ተገድለዋል:: ስለ ምጽዋታቸው: በጎ አገልግሎታቸውና ሰማዕትነታቸው ጻድቅ: ፈራጅ ከሆነ ፈጣሪ አክሊልን ተቀብለዋል:: =>የበረከት አምላክ ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን:: =>ሰኔ 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን አበው ሰማዕታት (አባ አክራ: አባ ዮሐንስ: አባ አብጥልማ: አባ ፊልዾስ) =>ወርሐዊ በዓላት 1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) 2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ 3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው) 5.አባ ስምዖን ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ 7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት =>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
1140Loading...
13
Photo
2460Loading...
14
††† እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ማር ገላውዴዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት ††† ††† ቅዱስ ገላውዴዎስ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘ በድሮው የሮም ግዛት በአንጾኪያ (አሁን ሶርያ ውስጥ) ነው:: አባቱ አብጥልዎስ የሮም ቄሣር የኑማርያኖስ ወንድም ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱ ያደገው በቤተ መንግሥት ውስጥ ነው:: ወቅቱ መልካምም ክፉም ነገሮች ነበሩት:: መልካሙ ነገር በቤተ መንግሥት አካባቢ ይኖሩ የነበሩት ልዑላኑ አብዛኞቹ በፍቅረ ክርስቶስ የታሠሩ ነበሩ:: ከእነዚህ መካካከል "ቅዱስ ፋሲለደስ: ቅዱሳኑ:- ፊቅጦር: ቴዎድሮስ: አባዲር: አውሳብዮስ: ዮስጦስ: አቦሊ: እስጢፋኖስ . . ." ነበሩ:: ቅዱሳቱ "ማርታ: ታውክልያ: ኢራኢ: ሶፍያ. . ." ነበሩ:: አስቸጋሪው ነገር ደግሞ ነጋ መሸ ኑሯቸው ጦርነት ነበር:: የዘመኑ የፋርስና የቁዝ መሪዎች ጦረኞች ነበሩና ዕለት ዕለት ፍልሚያ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ገላውዴዎስ የተመሠከረለት አርበኛና የተባረከ ንጹሕ ክርስቲያን ሆኖ አድጓል:: ከልጅነቱ ጀምሮ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማጥናቱ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት ታሽቷል:: እርሱ የነገሥታቱ ቤተሰብ ነው:: ማዕዱ በየዓይነቱ ሞልቶ ካልመሸ እህል አይቀምስም:: ጸሎቱ ስሙር: ስግደቱ ከምድር: አኗኗሩ በፍቅር ሆነ:: በዚያውም ላይ በድንግልናው የጸና ኃያል ነበር:: በጊዜው የቅዱስ ገላውዴዎስን ያህል መልኩ ያማረ (ደመ ግቡ) በአካባቢው አልነበረም:: ይህ ግን ሊያታልለው አልቻለም:: ሁሉ በእጁ ቢሆንም ለእርሱ ግን ብቸኛ ምርጫው ሃይማኖተ ክርስቶስ ነበር:: ቅዱስ ገላውዴዎስ ለጦርነት ወጥቶ ሲመለስ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ሃይማኖቱን ክዶ: ሕዝቡን ለጣዖት ሲያሰግድ: ክርስቲያኖችን ሲገድል ደረሰ:: ††† ቅዱሱ ኃያል የጦር ሰው ነውና ንጉሡን መግደል ሲችል ተወው:: በዚያ ሰሞንም ለገላውዴዎስ ሁለት ምርጫዎች ቀረቡለት:- 1.ክርስቶስን ክዶ የንጉሡ ተከታይ መሆን: 2.በክርስትናው ደሙን ማፍሰስ:: የቅዱሳኑ ምርጫቸው የታወቀ ነውና ታስሮ ወደ ግብጽ ተጋዘ:: በዚያ ከመኮንኑ ጋር ስለ ሃይማኖት ተከራክረው መኮንኑ ስለተበሳጨ ቅዱሱን በረዥም ጦር ጐኑን ወጋው:: ዘለፍ ብሎ ነፍሱን ሰጠ:: ሕዝበ ክርስቲያኑ በድብቅ መጥተው የቅዱሱን ሥጋ ሽቱ ቀብተው: ከዝማሬ ጋር ገነዙት:: የጓደኛው እናት ቅድስት ሶፍያ መጥታ ወደ ሶርያ ወስዳዋለች:: ††† ተወዳጅ: ኃያል: ቡሩክና መልካም ሰው ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት በሆነባት በዚሕች ዕለት በመላው ኦርቶዶክሳውያን ይከበራል:: ††† አምላካችን የቅዱሱን መንኖ ጥሪት: ትዕግስት: ጸጋና በረከት ያሳድርብን:: አሜን:: ††† ሰኔ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት (ሕይወቱ መላእክትን የመሰለ) 2.አንድ ሺ ሰማንያ ስምንት ሰማዕታት (የቅዱስ ገላውዴዎስ ማኅበር) 3.አባ ክርዳኑ ሊቀ ጳጳሳት 4.እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ክብራ ኢትዮጵያዊት (የአቡነ በጸሎተ ሚካኤል እህት) 5.የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዳሴ ቤቱ (ግብጽ) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ያሬድ ካህን 2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት 3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና 4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ ††† "የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ: ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ:: ሰባኪው:- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል::" ††† (መክ. ፲፪፥፩-፱) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/zikirekdus
2180Loading...
15
Photo
2650Loading...
16
+<< #ወይን_ለማይጠጣ_ሕይወቱ_ምንድን_ነው? >>+ "ምንትኑ ሕይወቱ ለዘኢይሰቲ ወይነ" (ሲራክ. 34:26) =>#ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን ወይንን (ጠላ: ቢራ . . .) ¤"አትጠጡ" ብላ አትከለክልም:: ¤ግን ደግሞ "ጠጡ" ብላም አታበረታታም:: ¤አልኮል መጠጦችን መጠቀም "ኃጢአት ነው" አትልም:: ¤ግን ደግሞ " . . . ካያያዝ ይቀደዳል" እንዲሉ አጠቃቀማችን ወደ ኃጢአት ሊወስደን ስለሚችል "ጥንቃቄን አድርጉ" ትለናለች:: +በዘመናችን ከመጠጥ ጋር በተያያዘ (በተለይ ለክርስቲያኖች) 2 ፈተናዎች ይታያሉ:: 1.አብዛኛው የቤተ ክርስቲያናችን ምዕመን (በተለይ ወጣቱና ጐልማሳው) አነሰም በዛም ጠጪ እየሆነ ነው:: (ልብ በሉልን "ይሰክራል" አላልኩም) 2.እጅግ በሚያስቀይም መንገድ ለመጠጣት ጥቅሶች ከቅዱስ መጽሐፍ ሲጠቀሱ እየሰማን ነው:: +በተለይ "#ወይን_ያስተፌስሕ_ልበ_ሰብእ" (መዝ. 103:15) ከእኛው አልፎ በዘፈንና በመገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያዎች ላይ ሲጠቀስ ስንሰማ አንጀታችን ካላረረ የቁም ሙት ሆነናል ማለት ነው:: +አሕዛብ ከመጽሐፋቸው አንዲት ዘለላ ብትነካ ሃገሪቱን በተቃውሞ እንደሚንጧት እናውቃለን:: ¤እኛ ግን #የሊቀ_ሰማዕታት ስም የቢራ ማሻሻጫ ሲሆን: #ቅዱስ_ቃሉ ለአልኮል መጠጥ ሲጠቀስ: #በአባቶቻችን_ካህናትና_ጻድቃን ላይ በፌዘኞች (ኮሜዲያን ነን ባዮች) ሲቀለድ: ማንም ባለጌ በተቀደሰች ሃይማኖታችን ላይ አፉን ሲከፍት ምንም አይመስለንም:: (አንቀላፍተናላ!!!) =>ወደ ጉዳዬ ልመለስና የወይንን ነገር እንጨዋወት:: "የትውልዱ ክፋቱ ኃጢአት መሥራቱ አይደለም:: ይልቁኑ ኃጢአቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስመሰሉ እንጂ" ብለውኛል የኔታ ክንፈ ገብርኤል:: (በቀኝ ያቁማቸውና!!!) +ዛሬ በሃገሪቱ የሚገኘውን ጠጪ (ካልጠጣ የሚሞት የሚመስለው) በመቶኛ/በ% ቢሰላ አብዛኛው (ምናልባት እስከ 90 % ) ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ባይ ነው:: +ታዲያ ይህ ጥራዝ ነጣቂ ትውልድ ለምን ስትሉት "ዳዊት እንዲህ አለ: ሐዋርያው ቅ/ዻውሎስ እንዲህ አከለ . . ." ይላል:: << ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱ ስለ ወይን መጠጣት የሚናገሩ ቃላት ትርጉም እንደሚባለው ነው?? #ለመሆኑ_ቅዱስ_መጽሐፍ_ጠጪነትን_ያበረታታል?? አምላካችን እግዚአብሔርስ ወደዚህች ምድር ያመጣን ለዚሁ ግብር ነው?? (ሎቱ ስብሐት!!!) >> +ቅዱስ ቃሉን ለገዛ ፈቃድ መተርጐም ፍጹም ኃጢአት ነው:: (2ዼጥ. 1:20) ስለዚህም "ወይን" የሚሉ ቃላት ምንድን ናቸው? ወደሚለው እንመለስ:: +በመጀመሪያ ግን #ብርሃነ_ዓለም: #ዓዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ) #ቅዱስ_ዻውሎስ ለደቀ መዝሙሩ #ቅ/ጢሞቴዎስ ስለ ምን "ውሃ ብቻ አትጠጣ:: ጥቂት ወይን ጨምር" አለው ቢሉ:- 1.ወይን በዘመኑ ለሆድ በሽተኞች ፍቱን መድኃኒት ስለ ነበር ነው:: (ቃሉም የሚለው ስለ ሆድህ ህመም ነው(1ጢሞ. 5:23)) ቅዱሱ ከገድል የተነሳ ሆዱ ፍጹም ሕመምተኛ ነበርና:: 2.ወይን መጠጣት በልኩ (ጥቂት) የሆነ እንደሆን አካልን ያለመልማል:: ልቡናን ያረጋጋል:: ግን በጊዜው: በቦታውና በመጠኑ ሲሆን ነው:: +#ቅዱስ_መጽሐፍ ላይ ግን "ወይን" ተደጋግሞ የተጠቀሰባቸው በርካታ መንፈሳዊ ምስጢራት አሉ:: እነዚህን መነሻ ርዕስ ባደረግነው: በቃለ ሲራክ ተመርኩዘን እንመልከታቸው:: =>ነቢዩ "#ወይን_ለማይጠጣ_ምን_ሕይወት_አለው?" ይላል:: 1.ወይን=(#ምስጢረ_ሥላሴ) ¤"ምስጢረ ሥላሴን ላላመነ ሰው ምን ሕይወት አለው?" ይለናል:: የእግዚአብሔርን አንድነት: ሦስትነት ሳያምኑ ዘለዓለማዊ ሕይወት የለምና:: (ዮሐ. 1:12, 3:17, ማቴ. 28:19) +ምስጢረ ሥላሴ በወይን መመሰሉን #አባ_ሕርያቆስ በቅዳሴው "አብ ጉንደ ወይን: ወልድ ጉንደ ወይን ወመንፈስ ቅዱስ ጉንደ ወይን . . ." ሲል ነግሮናል:: 2.ወይን=#ክርስቶስ (#ምሥጢረ ሥጋዌ) ¤በወልድ (ክርስቶስ) ያላመነ የዘለዓለም ሕይወት የለውም:: (ዮሐ. 3:36) ስለዚህ ነገር ጌታችን ራሱን የወይን ግንድ: አባቱን ተካይ አድርጐ ሲጠራ እንሰማዋለን:: "#አነ_ውእቱ_ጉንደ_ወይን=እኔ የወይን ግንድ ነኝ" እንዲል:: (ዮሐ. 15:1) +መዳን የሚቻለውም መድኅን ክርስቶስን "#አምላክ_ወልደ_አምላክ: #ወልደ_አብ_ወልደ_ማርያም: #ሥግው_ቃል" ብሎ ማመን ሲቻል ነው:: 3.ወይን=#ድንግል_ማርያም (#ነገረ_ማርያም) ¤ጌታን ወይን ካልን ድንግል ማርያምን #ሐረገ_ወይን: #አጸደ_ወይን ልንላት ግድ ይለናል:: (እሴብሕ ጸጋኪ ዘዘመነ ጽጌ) +መዳንን የሚሻ ሁሉ እመቤታችን ማርያምን #ወላዲተ_አምላክ መሆኗን: #ዘለዓለማዊ_ድንግልናዋን: ፍጹም ሞገስ ያላት #አማላጅ መሆኗን: #ቅድስናዋንና #ክብሯን ሊያምን ግድ ይለዋል:: (መዝ. 44:9, 86:5, ኢሳ. 1:9, 7:14, ሕዝ. 44:1) 4.ወይን=#ቅዱሳን (#ነገረ_ቅዱሳን) ¤መድኃኒታችን ክርስቶስ ራሱን የወይን ግንድ ብሎ አልቀረም:: ወዳጆቹን #ወአንትሙሂ_አዕጹቂሁ=እናንተ የወይኑ ቅርንጫፎች ናችሁ" ይላቸዋል:: (ዮሐ. 15:5) +ስለዚህም በቅዱሳን #ክብር: #አማላጅነት: #ፈራጅነትና #የጸጋ_አማልክትነት ልናምን ግድ ይለናል:: (ዘጸ. 7:1, መዝ. 81:1, ማቴ19:28) 5.ወይን=#ሥጋ_ወደሙ (#ምስጢረ_ቁርባን) ¤#እመቤታችን በቃና ዘገሊላ ቸር ልጇን የጠየቀችው ስለጊዜአዊው መጠጥ ቢመስልም ምስጢሩ ግን ለዘለዓለማዊው መጠጥ (ክቡር ደሙ) ነው:: (ዮሐ. 2:1) +ለዚያም "#ወይንኬ_አልቦሙ=ወይንኮ የላቸውም" ስትለው: "ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ=እናቴ ሆይ! በቀራንዮ አንባ ሥጋና ደሜን የምሰጥበት ጊዜየ ገና ነው" ሲል የመለሰላት:: +ወንጌል ደግሞ እንዲህ ይላል:: "የክርስቶስን ሥጋውን ካልበላችሁ: ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም::" (ዮሐ. 6:53) ¤የወይን ትርጉም ይቀጥላል . . . ለእኛ ግን እዚህ ላይ ይብቃን:: +ቅዱሱ #ነቢይ_ሲራክ "ወይን ለማይጠጣ ሰው ምን ሕይወት አለው?" ሲል በአንክሮ የጠየቀው ስለዚህ ነው:: ¤በወይን በተመሰሉ #በሥላሴ: #በምስጢረ_ሥጋዌ: #በነገረ_ማርያምና #ነገረ_ቅዱሳን ሳያምኑ: ከወይኑ ግንድ ክርስቶስ ጐን በፈሰሰ #ማየ_ገቦ ሳይጠመቁና #ከቁርባኑ ሳይሳተፉ ሕይወት የለምና:: =>ቸር አምላከ ቅዱሳን የምናስተውልበትን አዕምሮ አይንሳን:: << ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>
2422Loading...
17
††† እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ††† ††† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው : በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው:: ሊቁ የተወለደው መጋቢት 27 ቀን በ433 ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር:: አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት : ገና በ3 ዓመቱ : እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው:: ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ:: ሊቀ ዻዻሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው:: የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "አንሰ እፈርሕ ሠለስተ ግብራተ - እኔስ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ:: ††† ዻዻሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት:: እርሱም:- 1.ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ:: 2.ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ:: 3.ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው:: ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ዻዻሳቱ "እግዚአብሔር በዚሕ ሕጻን አድሮ ዘለፈን" እያሉ ለንስሃ በቅተዋል:: ቅዱስ ያዕቆብ 7 ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት:: በ5 ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ12 ዓመቱ ሊቅ ሆኗል:: በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን:: አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት:: እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው:: "እንግዲያውስ ትንቢተ ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል:: ፈጣሪንም አመስግነዋል:: ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በኋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን : ዕጸበ ገዳምን : ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል:: በድንግልናው ጸንቶ : ጾምና ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል:: በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ (በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት) ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል:: ††† በዘመኑም:- 1.የ451ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል:: 2.ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል:: 3.በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል:: 4.ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል:: በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በኋላ በተወለደ በ72 ዓመቱ በ505 ዓ/ም በዚሕች ቀን አርፏል:: አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ 27 ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ:: ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች:: ††† አምላከ ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ይክፈለን:: ††† ሰኔ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ 2.ቅዱስ : ቡሩክና አሸናፊ አባ አበስኪሮን (ታላቅ ሰማዕትና ባለ ብዙ ተአምራት ነው) 3."16,000" ሰማዕታት (በአንድ ቀን የተገደሉ) 4.የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን የተከፈተበት በዓል (ከ1ሺ ዓመታት በፊት ምስር (CAIRO) ውስጥ) ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) 2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ) 4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 5.አባ ባውላ ገዳማዊ 6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ) ††† "ይሕንን እዘዝና አስተምር :: በቃልና በኑሮ : በፍቅርም : በእምነትም : በንጽህናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው:: እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር : ለማስተማርም ተጠንቀቅ::" ††† (1ጢሞ. 4:11) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
1980Loading...
18
ዕርገት ‹ዕርገት› በግእዝ ቋንቋ ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት ማለት ሲኾን የጌታችን ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓልም ‹ዕርገት› ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፯፻፷)፡፡ በዓለ ዕርገት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለዐርባ ቀናት በግልጽም በስውርም ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳት አንስት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡ በዓለ ዕርገት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡ በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም ‹ዘመነ ዕርገት› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዘመነ ዕርገት ውስጥ በሚገኘው እሑድ (ሰንበት) ሌሊት ሊቃውንቱ የሚያደርሱት መዝሙርም ‹‹በሰንበት ዐርገ ሐመረ›› የሚል ሲኾን ይኸውም ጌታችን በሰንበት ወደ ታንኳ በመውጣት ባሕርንና ነፋሳትን እንደ ገሠፀ፤ ሐዋርያቱንም ‹‹ጥርጥር ወደ ልቡናችሁ አይግባ፤ አትጠራጠሩ›› እያለ በሃይማኖት ስለ መጽናት እንዳስተማራቸው፤ እንደዚሁም ወንጌልን ይሰብኩ፣ ያስተምሩ ዘንድ በመላው ዓለም እንደሚልካቸው፤ በሰማያዊ መንግሥቱ ይኖሩ ዘንድም ዳግመኛ መጥቶ እንደሚወስዳቸው የሚያስገነዝብ መልእክት አለው (ሉቃ.፰፥፳፪-፳፬፤ ዮሐ.፲፬፥፪፤ ፳፥፳፩)፡፡ በበዓለ ዕርገት ሊቃውንቱ ሌሊት በማኅሌት፣ በዝማሬ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ ሥርዓተ ማኅሌቱ እንዳበቃ የሚሰበከው የነግህ ምስባክም፡- ‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል›› የሚለው የዳዊት መዝሙር ሲኾን፣ ቀጥተኛ ትርጕሙ፡- ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል፤›› ማለት ነው (መዝ.፷፯፥፴፫)፡፡ ምሥጢራዊ ትርጕሙ ደግሞ ‹‹ነፍሳትን ይዞ ከሲኦል ወደ ገነት ለወጣ፤ አንድም በደብረ ዘይት በኩል ላረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ›› የሚል መልእክት አለው፡፡ እንደዚሁም ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን ‹የኀይል ቃል› የተባለ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት እንደ ላከላቸው፤ በተጨማሪም ጌታችን በሕያዋን እና በሙታን (በጻድቃን እና በኃጥአን) ላይ ለመፍረድ ዳግም እንደሚመጣ፤ እኛም ይህንን የጌታችንን የማዳን ሥራ እያደነቅን ለእርሱ ምስጋና፣ ዝማሬ ማቅረብ እንደሚገባን ያስረዳናል – ምስባኩ፡፡ በነግህ (ከቅዳሴ በፊት የሚነበበው) ወንጌል ደግሞ ሉቃስ ፳፬፥፵፭ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቃሉም ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት እንደሚወርድ፣ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ ወደ ሰማይ እንደሚያርግና ዳግም እንደሚመጣ በነቢያት የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን፤ ለዚህም ቅዱሳን ሐዋርያት ምስክሮች መኾናቸውን ማለትም በመላው ዓለም እየዞሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ እንዲሰብኩና በሰማዕትነት እንዲያልፉ፤ እንደዚሁም ሰማያዊ ሀብትንና ዕውቀትን እስኪያገኙ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ መታዘዛቸውን ያስረዳል፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው የሐዋርያትን ተልእኮ የሚመለከት ይኹን እንጂ ለፍጻሜው ግን ዅላችንም ቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩትን ቃል አብነት አድርገን የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና የማዳኑን ሥራ አምነን፣ ሌሎችንም በማሳመን በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር እንደሚገባን፤ እግዚአብሔር አምላካችን ኃይሉን፣ ጸጋውን፣ ረድኤቱን እንዲያሳድርብንም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መለየት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ መልእክት አለው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ዕብራውያን ፩፥፩ እስከ ፍጻሜው ድረስ፤ ከሌሎች መልእክታት ደግሞ ፩ኛ ጴጥሮስ ፫፥፲፰ እስከ ፍጻሜው፤ የሐዋርያት ሥራ ፩፥፩-፲፪ ሲኾኑ፣ ምስባኩም ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ›› የሚለው ነው፡፡ ትርጕሙም ‹‹በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ›› ማለት ነው (መዝ.፵፮፥፭-፮)፡፡ ወንጌሉ ደግሞ፣ ማርቆስ ፲፮፥፲፬ እስከ ፍጻሜ ድረስ ሲኾን ቃሉም በነግህ ከተነበበው የወንጌል ክፍል ቃል ተመሳሳይነት አለው፡፡ ቅዳሴውም ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን ይህ ቅዳሴ ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነውን የእግዚአብሔር ወልድን (የኢየሱስ ክርስቶስን) ዘለዓለማዊነት የሚያስረዳ፤ ሥጋዌዉን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና ዳግም ምጽአቱንም የሚናገር በመኾኑ በዘመነ ትንሣኤ፣ በዘመነ ዕርገትና በበዓለ ኀምሳ ሰሙን ይቀደሳል፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴዉ መጀመሪያ ላይ ሀልዎተ እግዚአብሔርንና ምሥጢረ ሥላሴን መሠረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ካቀረበ በኋላ፣ ቍጥር ፴፩ ላይ ‹‹… ወበ፵ ዕለት አመ የዐርግ ሰማየ አዘዞሙ እንዘ ይብል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ፤ … ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በዐርባኛው ቀን በብርሃን፣ በሥልጣን፣ በይባቤ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ ‹አብ የሚሰድላችሁ መንፈስ ቅዱስን እስክትቀበሉ ድረስ ከዚህ ቆዩ ብሎ አዘዛቸው›፤›› በማለት ቅዱስ ወንጌልን መሠረት ባደረገ ኃይለ ቃል ጌታችን ወደ ሰማይ ስለ ማረጉና ለሐዋርያት አምላካዊ ትእዛዝ ስለ መስጠቱ ይናገራል (ሉቃ.፳፬፥፵፱)፡፡ ይቆየን
1720Loading...
19
https://m.payquiz.icu/75237184342481291/
980Loading...
20
††† ✝እንኳን ለኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን እና ለእናታችን ቅድስት ማርታ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን። †††✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† አቡነ ተጠምቀ መድኅን ††† ††† ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ1610 ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው #ወልደ_ክርስቶስና #ወለተ_ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ 2 ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር 11 ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ #ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ #ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ #ጸጋ_እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ:: ሕጻን እያሉ #ቃለ_እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም:: ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን: ነብሩን: ተኩላውን ሰብስበው:- "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ: ከፍየሉ: ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን: ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ:: ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: 23 ዓመት ሲሞላቸው ወደ #መርጡለ_ማርያም ሔደው መንኩሰዋል:: ከዚሕ ጊዜ በሁዋላ ለ37 ዓመታት:- 1.በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል 2.ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል 3.ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል (ካህን ናቸውና) 4."7" ገዳማትንና "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል:: ††† ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ60 ዓመታቸው በ1670 ዓ/ም (በአፄ #ዮሐንስ_ጻድቁ ዘመን) ዐርፈዋል:: እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ #በጋሾላ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል:: ††† ቅድስት ማርታ ††† ††† እናታችን ቅድስት ማርታ በቀደመ ሕይወቷ እጅግ ኃጢአቷ የበዛ ሴት ነበረች:: እጅግ ቆንጆ መሆኗን ሰይጣን ለኃጢአት እንድትጠቀምበት አባበላት:: እርሷም ተቀበለችው:: በወጣትነት ዘመኗ በመልኩዋና በገላዋ በርካቶችን ወደ ኃጢአት ሳበች:: መጽሐፍ እንደሚል ለሁሉም ሰው የመዳን ቀን ጥሪ አለውና አንድ ቀን (በበዓለ ልደት) ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች:: ዘበኛው ግን ሲያያት ተጸይፏልና አትገቢም አላት:: ተከራከረችው: ለመነችው:: ግን አልተሳካላትም:: ሰዓቱ የቅዳሴ ቢሆንም እርሷ እሪ አለች:: ለቅዳሴ የቆሙ ሁሉ በመታወካቸው ዻዻሱ ወጥቶ ገሰጻት:: ያን ጊዜ ነበር ወደ ልቧ የተመለሰችው:: በጉልበቷ ተንበርክካ መራራ ለቅሶን አለቀሰች:: ዻዻሱንም ተማጸነችው:- "እጠፋ ዘንድ አትተወኝ:: ወደ ጌታየ አድርሰኝ" አለችው:: ወዲያውም ወደ ቤቷ ሔዳ የዝሙት እቃዋን አቃጠለች:: ጸጉሯን ተላጨች:: ንብረቷን ሁሉ ለነዳያን አካፈለች:: ዻዻሱም ንስሃ ሰጥቶ ወደ ገዳም አሰናበታት:: ወደ ገዳም ገብታ: በዓት ተቀብላ: ጾምና ጸሎትን ከእንባ ጋር አዘወተረች:: ለ25 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ከበዓቷ ሳትወጣ: አንድም ሰው ሳታይ ኖረች:: ከማረፏ በፊትም ብዙ ተአምራትን አድርጋለች:: ††† የቅዱሳን አምላክ ለእኛም እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሐ አይንሳን:: ከበረከታቸውም ያድለን:: ††† ††† ሰኔ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ማርታ ተሐራሚት 2.አቡነ ተጠምቀ መድኅን ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) 3.ቅዱስ ኢላርዮን ሰማዕት 4.ቅዱስ ኮርዮን ሰማዕት †††ወርኀዊ በዓላት 1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን) 4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ 5.አቡነ ዜና ማርቆስ 6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል ††† "አልሞትም: በሕይወት እኖራለሁ እንጂ:: የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ:: መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ:: ለሞት ግን አልሠጠኝም:: የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ:: ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ:: ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት:: ጻድቃን ወደ እርስዋ ይገባሉ:: ሰምተኸኛልና: መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ::" †††  (መዝ. 117:17-22) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
3260Loading...
21
††† እንኳን ለቅዱሳን ነቢያት ዮሐንስና ኤልሳዕ ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ††† †††የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ:- ¤በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ ¤በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ¤በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ ¤እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ ¤የጌታችንን መንገድ የጠረገ ¤ጌታውን ያጠመቀና ¤ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው:: ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን:- ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች:: ††† ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ ††† ††† ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ ኤልሳዕ:- ¤ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ ¤መናኔ ጥሪት የተባለ ¤በድንግልና ሕይወት የኖረ ¤የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት ¤እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ ¤አንዴ በሕይወቱ : አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው:: ቅዱሳት መጻሕፍት ሁለቱን ቅዱሳን በመልካቸውም ይገልጿቸዋል:: ቅዱስ ዮሐንስ ¤ቁመቱ ልከኛ ¤አካሉ በጸጉር የተሸፈነ ¤የራሱ ጸጉር በወገቡ ¤ጽሕሙ እስከ መታጠቃያው የወረደ ¤ግርማው የሚያስፈራ የ31 ዓመት ጎልማሳ ነበር:: ቅዱስ ኤልሳዕ ¤በጣም ረዥም ¤ራሱ ገባ ያለ (ራሰ በራ) ¤ቀጠን ያለ ¤ፊቱ ቅጭም ያለ (የማይስቅ) ሽማግሌ ነበር:: በዚሕች ቀን በ350 ዓ/ም አካባቢ የሁለቱም ቅዱሳን አጽም ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ ፈልሷል:: በወቅቱ ክፋተኛ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር:: ለዚሕ እንዲረዳው በ70 ዓ/ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም 3 ጊዜ ፈረሰበት:: ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ እሱን አውጥተህ አቃጥል" አሉት:: ሲቆፈር በመጀመሪያ የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው : ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል:: እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል:: በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል:: በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል:: ††† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅር ያድለን:: †††ሰኔ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ፍልሠቱ) 2.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ፍልሠቱ) 3.አባ ቀውስጦስ ኢትዮዽያዊ †††ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ 3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ 4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ) 5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ 6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ †††"ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ::" ††† (ማቴ. 11:7-15) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
2290Loading...
22
Photo
2483Loading...
23
"የጥበብ  መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው" ምሳሌ ፩÷፯ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ የተወደዳችሁ የሰንበት ት/ቤታችን አባላትና የመፅሐፍ ቅዱስ ንባብ ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ ፥ የከበረ መንፈሳዊ ሰላምታችን በያላችሁበት ይድረስ። 🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊 ከሰኔ 03/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከጥበብና የመዝሙር መፃሕፍት ውስጥ የሚመደበውን መፅሐፈ ምሳሌ ማንበብ እንደምንጀምር እናበስራለን። መጽሐፈ ምሳሌ 24 ምዕራፎች ሲኖሩት ሰዎች በተለይም በወጣትነት ዘመናቸው በአኗኗራቸው ጥበበኞች እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል መጽሐፍ ነው። 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 የመጽሐፈ ምሳሌ ዋነኛ ትኩረት – ሰው ጥበብ ፥ ማስተዋልና እውቀት እንዲያገኝ – ሰው ትክክለኛ፥ ፍትሐዊና፥ መልካም ነገርን እንዲያደርግ፥  – ሰው የተለያዩ ምሳሌዎችን፥ ምሳሌያዊ አነጋገሮችንና እንቆቅልሾችን እንዲረዳ፥  – ጥበበኞች በጥበባቸው ላይ ተጨማሪ ጥበብ እንዲያገኙ ለመርዳት፥  – ሰው ሥርዓት በተሞላበት ሕይወት እንዲኖር ለማስቻል፥  – ሰው የጥበብ መጀመሪያ የሆነውን «እግዚአብሔርን መፍራት» እንዲማር ለመርዳት የሚያችሉ ሀሳቦችን በውስጡ ይዟል። 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 ይህንን የጥበብ መፅሐፍ አንብበን ከጥበብ ገበታ ለመሳተፍ እየተዘጋጀን እንቆይ። ከ ሰኔ 03/2016 ጀምሮ  ⏳⏳⏳
2533Loading...
24
👍
10Loading...
25
Photo
2470Loading...
26
፨፨፨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚችም ዕለት የእናታችን የቅድስት ዜና ማርያም አመታዊ የበዓሏ መታሰቢያ ነው፨፨፨ ✝✞✝ ቅድስት ዜና ማርያም ✝✞✝ ፨ በ11መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት ግንቦት 30 ቀን በጎጃም ክፍለ ሀገር ተወለደች። የአባቷ ስም ገብረ ክርስቶስ የእናቷ ስም አመተ ማርያም ይባላሉ። እጅግ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፡ ቅዲስ ጋብቻቸውን በንጽሕና የሚጠብቁ፡ ለሰው የሚራሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ። እንዲህ ባለ መልካም ግብር ከኖሩ በኀላ በፈቃደ እግዚአብሔር 3 ወንዶች ልጆች እናት አንዲት ሴት ልጅ ወለዱ። ይህችም ሴት ልጅ ተወዳጇ እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ናት። ፨ ቅድስት ዜና ማርያም እናት እና አባቷን እያገለገለች፡ ፈርሐ እግዚአብሔን፡ በጎ ምግባርን ከወለጆቿ እየተማረች አደገች። ለአቅመ ሔዋንም በደረሰች ጊዜ ወላጆቿ ለአንድ ወጣት አጯት። ታላቅ ግብዣ ተደረጎ በተክሊል ተዳረች። በዚያው ወራት ግን የዜና ማርያም እናት አመተ ማርያም አምስተኛ ልጅ ወልዳ ተኝታ ሳለች በአካባቢው ሕማመ ብድብድ (ተላላፊ በሽታ) በመነሳቱ የዜና ማርያም እናት ታማ ነበር፡ በመጨረሻም ከዚህ ኃላፊ ዓለም አረፈች። ፨ ከዚህ በኋላ የታመመውን ወንድሟንና ሌሎቹንም በመያዝ ከተላላፊው በሽታ ለመትረፍ ሲሉ አካባቢውን ለቀው ወደ በረሃ ወጡ። በዚያም ሌሊት የዱር አራዊት መጥተው ከበቧቸው ሁሉንም ሊበሏቸው ሞከሩ እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ስመ እግዚአብሔርን ስትጠራ አራዊቱ ወደኋላ በመሸሽ ከአካባቢው ራቁ። እርሷም ከክፉ ሁሉ የጠበቃቸውን፡ ከአራዊት መበላት የሰወራቸውን እግዚአብሔርን አመሰገነች። በነጋም ጊዜ የታመመውን ወንድሟን እና ሌሎችን በመያዝ መንገድን ቀጠሉ አንዲት ባዶ ቤት አግኝተው ከእርሷ ተጠጉ። በፀሐዩ ንዳድና ታናሽ ወንድሟን በማዘል እጅግ ስለደከመች ከባድ እንቅልፍ ጣላት። ጠዋት ስትነሳ ግን የታመመው ወንድሟ ከአጠገቧ አላገኘችውም ሌሊት የዱር አራዊት በልተውታልና። አጅም አዘነች የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብላ አራሷን አፅናናች የወንድሟን ተረፈ ሥጋ አጠራቅሟ ቀበረች። በመቀጠልም በአካባቢው ካለ ገዳም ሔዳ ምንኩስናን ተቀበለች። ፨ ከዚህ በኋላ ባሏ አባቷን ሚስቴን አምጣ እያለ ስለጨቀጨቀው ከብዙ ልፋት እና ድካም ፈልጎ አገኛት ወደ ሀገሯም ወሰዳት። በዚያም ወደ ጉባኤ ቀርባ ለምን ወደ ገዳመ እንደሄደች እና ባሏን አንደከዳች ተጠየቀች። እርሷም እግዚአብሔር ከብዙ መከራ አድኖኛል እና እራሴን ለእግዚአብሔር ሰጥቻለሁ አለች። የጉባኤው ተሰብሳቢ በሏ ሀብቷን ወርሶ እንዲያሰናብታት ፈረዱ። እርሷም በዚህ ነገር በመስማማት የነበራትን ላም እና በሮች አስረከበች። ፨ ከዚህ በኋላ በአባቷ ቤት ለአንድ ዓመት ያህል በመቀመጥ የእናቷን ተዝካር አውጥታ ወደ ገዳሙ ተመለሰች በዛም ለጥቂት አመታት የተለያዩ ገድላትን ስትፈጽም ከቆየች በኋሏ ከነፍስ አባቷ ባሕታዊ አባ ገብረ መስቀል ጋር ወደ ጎንደር ሀገረ ስብከት ልዩ ስሙ እንፍራንዝ (ጣራ ገዳም) አካባቢ ዋሻ እንድርያስ በተባለው ለ25 ዓመት በብሕትውና ኖረች። አሁንም ድረስ በዚያ ዋሻ እናታችን ዜና ማርያም በፀሎት ጊዜዋ እንቅልፍ እንዳይጥላት ስትጠቀምበት የነበረ ዘንግ ፣ የምተቆምበት ዙሪያውን በገመድ የታሰረ የተቦረቦረ ግንድ አሁንም ድረስ ተአምር እየሰሩ ይገኛሉ። ከዚህም በመቀጠል ዛሬ ዜና ማርያም ተብሎ ወደ ሚጠራው ዋሻ ሔደች በዚያም በጾምና በጸሎት በልዩ ልዩ ተጋድሎ እስከ እለተ እረፍቷ ድረስ በዚያ ኖራለች። +++ የገድል ዓይነቶች +++ ፨ በየሰዓቱ ከ 100-300 ትሰግድ ነበር ፨ ሁለት ቀን እየፆመች በሶስተኛ ቀን ጥቂት ጥሬ ቀምሳ ሳምንቱን ታሳልፈው ነበር ፨ 150ን መዝሙረ ዳዊት እና ወንጌል በየቀኑ ትጸልይ ነበር ፨ በብሕትውና ወራት ማር፣ ቅቤን፣ ወተትን ፈጽሞ አትቀምስም ነበር ፨ የጌታችን መከራ መስቀል እና ስትየ ሐሞት በማሰብ በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብ ኮሶ የሚባል ቅጠል እየበጠበጠች ከቅል ውስጥ ከሚገኘው መራራ ፍሬ ጋር በማዋሐድ ትጠጣ ነበር ፨ ከጸሎት እና ከስግደት በምታርፍበት ጊዜ አትክልት በመትከል እና በመኮትኮት ጊዜዋን ታሳልፍ ነበር ፨ የጌታችንን ግርፋቱን በማሰብ 100 ጊዜ ጀርባዋን ስለምትገረፍ እና ደም ስለሚፈሳት ጀርባዋ ይቆስል እና ይተላ ነበር። +++ተአምራት+++ ፨ ዓይናቸውን በተለያየ በሽታ የታመሙ ሰውዎች ሁሉ ከህመማቸው ተፈውሰዋል ፨ የራስ በሽታ ( የራስ ፍልጠት፣ ጭንቀት፣ ማዞር) የታመሙ ጸበሉን በመቀባት ድነዋል፡፡ ፨ ጸበሉን በመጠመቅ፤ የጻድቋን ተአምር በማዘል፤ ስዕለት በመሳል መካኖች ወላድ ሆነዋል። ሌሎች በየቀኑ ብዙ ተአምራትን እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ታደርጋለች። +++ቃል ኪዳን+++ ቅድስት ዜና ማርያም ከዚህ ዓለም የምታርፍበት ጊዜ እንደደረሰ በመንፈስ ቅዱስ በአወቀች ጊዜ ከታላቅ ዛፍ ወጥታ ስትፀልይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክት ጋር፣ ከነቢያት፣ ከሐዋርያት፣ ከሰማዕታት፣ ከጻድቃን፣ ከደናግል መነኮሳት ጋር በመሆን ተገልጾ ከአረጋጋት በኋላ ቃል ኪዳንን ሰጧታል። ፨ በፀሎትሽ ያመነውን ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ ፨ በስምሽ የተራበውን ያበላ በመንግስተ ሰማያት ኅብስተ ሕይወት አበላዋለሁ፤ የተጠማውን ያጠጣ ጽዋዓ ሕይወትን አጠጣዋለሁ ፨ መጽሐፈ ገድልሽን የጻፈውን፡ ያጻፈውን፡ የሰማውን፡ ያሰማውን ስሙን በዓምደ ወርቅ እጽፈዋለሁ ፨ ከሕፃንነትሽ እስከ አሁን ድረስ ስለ እኔ ብለሽ ብዙ መከራ ተቀብለሻል፦ ደጅሽን የረገጠ የሦስት ጭነት ጤፍ ያህል ነፍሳትን እንደሚምርላት፡ እንዲሁም ከሲዖል ነፍሳትን እንደሚያወጣላት ጌታችን በማይታበል ቃሉ ቃልኪዳን ገብቶላታል። እንዲሁም ከሲዖል ነፍሳትን እንደሚያወጣላት፡፡ +++ ገዳሟ እና መገኛው+++ ፨ የቅድስት ዜና ማርያም መካነ መቃብሯ ( ጸበሏ) በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ከም ከም ወረዳ ይገኛል ቦታውም አዲስ ዘመን ከተማ 20 ኪ.ሜ ርቆ የሚገኝ ሲሆን ከከተማው በስተሰሜን በኩል "ደሪጣ" ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ይገኛል። "ደሪጣ" ሸክላ ማርያም ተብላ ትጠራ የነበረችው ቦታ ስያሜው ተቀይሮ ደሪጣ ዜና ማርያም ዋሻ (ገዳም) ተብሎ እስከ አሁን ድረስ እየተጠራ ይገኛል፡፡ ይህን ስያሜ ያገኘውም በቅድስት ዜና ማርያም ገድል ውስጥ " ወትሰቲ ሲካር (ኮሶ) ደሪፃ" የሚል ቃል ይገኛል። ይህም ማለት ኮሶ የተባለውን እንጨት (ቅጠል) ቀጥቅጣ (አልማ) ከቅል ውስጥ ከሚገኘው ፍሬ ጋር በማደባለቅ ትጠጣለች ማለት ነው። ስለዚህ ቦታው "ደሪፃ" ተብሎ ተሰየመ በማለት በአካባቢው የሚገኙ አባቶች ይናገራሉ። በመጨረሻም ተጋድሎዋን በመፈጸም በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ነሐሴ 30 ቀን ከዚህ አለም ድካም ዐርፋለች። የእናታችን የቅድስት ዜና ማርያም በረከቷ ቸርነቷ ይደርብን። አሜንን!! +++ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎታ፡፡ ወበረከታ ለቅድስት ዜና ማርያም የሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን!!! +++ https://t.me/zikirekdusn
2021Loading...
27
<<+>>✝✝   #የሰኔ_መዓልት <<+>>✝✝ =>ቀደምት #ኢትዮዽያውያን ሰው ወሬ ሲያበዛባቸው "#ምነው_የሰኔ_መዓልትን_ሆንክብኝ!" ሲሉ ይተርቡ ነበር:: "አሳጥርልኝ! ወሬህ ረዘመብኝ!" ለማለት ነው:: +ለዚህ መነሻ የሆነው ደግሞ ከ13ቱ ወራት መዓልቱ (ቀኑ) ቶሎ የማይመሽበት ወር ሰኔ መሆኑ ነው:: በእርግጥ ንግግራችን አጭርና ግልጽ ቢሆን ሁሌም መልካም ነው:: ሰው እስኪሰለቸን ድረስ ማውራቱ የሚገባ: የሚመችም አይደለምና:: +"ሺ ዓመት አላወራ! በናትህ (ሽ) ትንሽ ላውራ?" እያሉ መንዛዛቱም ቢሆን አይመከርም:: << እኔም ወደ ጉዳዬ ልግባ >> +ከዓመቱ 13 ወራት የሰኔ መዓልቱ ለምን ረዘመ ብንል:- መልሱ አጭር ነው:: "#ይህ_የእግዚአብሔር_ጥበብና_ሥራ_ነው::" ሳይንሱ ሺህ መንስኤን ሊደረድር ይችላል:: ለእኛ ግን አበው እንዳስተማሩን ሰኔ #የሥራና_የጾም ወር ነው:: +ትጋትን የሚወድ አምላክ ይህንን ወቅት ለጾም ለሥራና: ለበጐ ተግባር አርዝሞልናል:: በእርግጥ ጥቂት ሠርተን ብዙ ለምንተኛ ለዚህ ዘመን ሰዎች ይህ ሊጸንብን ይችል ይሆናል:: ግን ምንም እንኩዋ ሁሉ ወራት ለሥራ ቢሠሩም ወርሃ ሰኔ #ለገበሬና #ለክርስቲያን ትልቁን ሥራ የሚጀምሩበት ወቅት ነው:: +በሰኔ ያልተጋ #ገበሬ ዓመቱን ሙሉ መከረኛ ነው:: ከነ ተረቱም "#ሰነፍ_ገበሬ_ይሞታል_በሰኔ" ይባላል:: +#ክርስቲያንም ከበዓለ ሃምሳ ማግስት #በዓለ ዸራቅሊጦስን ተደግፎ ሰኔን ሊተጋባት ግድ ይላል:: በመከራ ዘመን የሚመሰል #ክረምት ሳይመጣ በወርሃ ሰኔ ሊተጋ ግድ ይለዋል:: ሽሽቱ በክረምትና በሰንበት እንዳይሆንም ይጸልያል:: (ማቴ.24:20) +#እግዚአብሔር ሁሉን በሁሉ የሠራ: ያዘጋጀና የፈጸመ ጌታ ነው:: ምንም እንዳይጐድልብንም አድርጐናል:: በተለይ #የኢ/ኦ/ተ_ቤተ_ክርረስቲያን ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነው:: ለሁም ነገር ትርጉምና ሸጋ የሆኑ ሐተታዎች አሏት:: +ስለዚህም የዘመን ቀመሯን መሠረት አድርጋ #ወርሃ_ሰኔ መዓልቱ 15: ሌሊቱ 9 ነው ትላለች:: ብርሃኑ ሲበዛም እንዲህ ትለናለች:: ¤ብርሃን #ጌታ_ነው:: (ዮሐ. 9:5) ¤ብርሃን #ድንግል_ማርያም_ናት:: (ራዕይ. 12:1) ¤ብርሃን #ቅዱሳን_ናቸው:: (ማቴ. 5:14) +ቀጥሎም መጽሐፍ እንዲህ ይለናል:- "#አምጣነ_ብክሙ_ብርሃን: #እመኑ_በብርሃን: #ከመ_ትኩኑ_ዉሉደ_ብርሃን: #ዘእንበለ_ይርከብክሙ_ጽልመት" (ጨለማ ሳያገኛችሁ: ብርሃንም ሳለላችሁ: የብርሃን ልጆች ትሆኑ ዘንድ: በብርሃን እመኑ) (ዮሐ. 12:36) =>አምላከ ብርሃን: ወላዴ ሕይወት አምላካችን: ቸር ብርሃኑን ይላክልን:: ተረፈ ዘመኑንም የሰላምና የበረከት ያድርግልን:: << ወስብሐት ለእግዚአብሔር >> " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ (re)  Dn  Yordanos Abebe 🔗https://t.me/zikirekdusn ▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
2782Loading...
28
Photo
3421Loading...
29
✝✝✝ በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን :: ✝✝✝ "✝" ግንቦት 26 "✝" +*" አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ "*+ =>እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው:: +እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ:: +አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር : የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል:: +ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው) ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ:: +አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት : የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ:: +አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ : ሲፈጩ : ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ:: +በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ : ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው:: +በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ (ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌል : በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ:: +ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:- +ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ:: +በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው:: +ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ:: +ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል:: +እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ : በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም:: "እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ:: መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል:: +ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::} << ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው !! >> =>+"+ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል:: +"+ (1ዼጥ. 5:3)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
3041Loading...
30
Media files
3051Loading...
31
አንድ አረጋዊ እንዲህ አሉ ፦”ልጆቼ ሆይ፦ ራሳችሁን መለወጥ ሳትችሉ የሌላን ሰው ነፍስ ማዳን ወይንም ሰወችን መርዳት አትችሉም፤ ነፍሳችሁ በልዩ ልዩ ምስቅልቅል ውስጥ ሆናም የሌላውን ሰው መንፈሳዊነት ስርአት ማስያዝ አይቻላችሁም፤ እናንተ ራሳችሁ የውስጥ ሰላም ከሌላችሁ ለሌሎች ሰላምን ማስገኘት አትችሉም ፤ ብዙውን ጊዜ የሰወችን በኛ ምክንያት ለበጎ ነገር መነሳሳትና ነፍሳቸውም ወደ እግዚአብሄር መቅረብ የምናየው ወደ በጎ ይቀርቡ ዘንድ በአፍ በምንነግራቸው ነገር ሳይሆን በእኛ ላይ በተግባር በሚገለጥ የመንፈስ ፀጋና ስጦታ ነው፡፡ ሌሎች ሰወችም ህይወታቸው ለበጎ ነገር እንዲነሳሳና እንዲለወጥ በእኛ ህይወት ሲማሩ እኛ እንኳን ላናየውና ላንረዳው እንችላለን፡፡"
3190Loading...
32
Media files
10Loading...
33
†✝️†🌷 እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችሁ †✝️†🌷 †✝️†🌷 ደብረ ምጥማቅ 🌷†✝️† =>የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች:: +ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ: +ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር:: +ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች:: +በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:- እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል:: +እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው:: +የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር:: +እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች:: ††† 🌷አባ መርትያኖስ 🌷††† =>አባ መርትያኖስ በበርሃ ከ68 ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ አባት ናቸው:: ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር:: +አንድ ቀን አንዷ ሽቶ አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን አጋንንትን አርቀዋል:: እሷንም በንስሃ መልሰው ለቅድስና አብቅተዋታል:: ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በ108 ሃገራት 108 በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው:: ††† ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን:: ††† =>ግንቦት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ) 2.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት) 3.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ 4.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ =>ወርኀዊ በዓላት 1.አበው ጎርጎርዮሳት 2.አቡነ ምዕመነ ድንግል 3.አቡነ አምደ ሥላሴ =>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ:: ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው:: ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው:: በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . . በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ:: በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ:: ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ. 44:12-17) ✝️✝️✝️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✝️✝️✝️
3210Loading...
34
በፎቶው ላይ የምታዩት አፄ ቅዱስ ካሌብ የመነነበት : አክሱም አካባቢ የሚገኝ የአባ ጰንጠሌዎን ገዳም ነው) የቅዱሱ ንጉሥ በረከቱ ይደርብን:: https://t.me/zikirekdusnt
3120Loading...
35
የወርሐ ግንቦት ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት መጽሔትን ያውርዱት ..........ያንብቡት..........ያጋሩት የመካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የመካነ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል
3 1707Loading...
እንዴትና ከምን እንጹም? - የጾም ሃይማኖታዊ ትርጉም ፈጣሪን መለመኛ ከኃጢአት ቁራኛ መላቀቂያ መሣሪያ ስለሆነ በጾም ወራት ለአምሮት ለቅንጦት የሚበሉ ወይም ለመንፈሳዊ ኋይል ተቃራኒ የሆኑ የአልኮል መጠጦች ሥጋና ቅቤ ወተትና እንቁላል ማራቅታዟል - ባልና ሚስትም ከአንድ ላይ አይተኙም 1ኛ ቆሮ 6፥5 - ሥጋዊ ጉልበትን በጾም የማድከም ቅብአት ካላቸው ምግቦች መከልከልም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለው ለምሳሌ ዳዊት በመዝሙር 108፥24  ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ ሥጋዮም ቅቤ በማጣት ከሳ ብሏላ ፣ ሠለስቱ ደቂቅና ነቢዩ ዳንኤልም የቤተ መንግሥቱን ሥጋና የጸሎት ምግብ ትተው በጥሬና በውኃ መቆየታቸው ተፅፎአል ት.ዳን 1፥8-21፣ት.ዳን10፥2 ዋናው ነገር ጾም እንጂ መብል ወደ እግዚአብሔር አያቀረበንም ብንበላም የምናተርፈው ባንበላም የሚጎዳን ነገር የለም 1ኛ ቆሮ8 ፥8 ከአዳም ጀምሮ መብል ሲጥል እንጂ ሲያነሣ አላየንምና ጾሙን ከኃጢአት  በመራቅ ለራስ ያስብነውን ለነዳያን በመስጠት፣ ጾም ከፀሎት ጋር ሲሆን ጸጋን እንደ ሐዋርያቱ  ያሠጣልና  በጸሎት በመትጋት በስግድት ወደ እግዚአብሔር በፍፁም ልብ በመመለስ ልንጾመው ይገባል፡፡ #ሼር https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw
Показати все...
††† እንኳን ለጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት አባ ድምያኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† አባ ድምያኖስ ††† ††† አባ ድምያኖስ ተወልደው ያደጉት ግብጽ ውስጥ ነው:: ቤተሰቦቻቸው ክርስቲያኖች በመሆናቸው ገና በልጅነት ዕድሜአቸው ቅዱሳት መጻሕፍትንና በጐ ምግባራትን ተምረዋል:: ዕድሜአቸው ወደ ወጣትነቱ ሲጠጋ ሥርዓተ መነኮሳትን ለማጥናት ወደ ገዳመ አባ ዮሐንስ ሔዱ:: በዘመኑ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ፈተና ሳያልፍ እንዲመነኩስ አይፈቀድለትም ነበር:: አንድ ሰው ሊመነኩስ ካሰበ በትክክል መናኝ መሆኑ ቢያንስ ለሦስት ቢበዛ ደግሞ ለአሥራ ሁለት ዓመታት እንዲፈተን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታዝዛለች:: ይኸውም "ሥርዓተ አመክሮ" ይባላል:: ከአሥራ ሁለት ዓመታት በላይ መቆየት ከፈለገ ግን ይፈቀድለታል:: በዚህም መሠረት አባ ድምያኖስ ለአሥራ ሰባት ዓመታት በአጭር ታጥቀው ገዳሙን አገልግለዋል:: ገዳሙም ይገባሃል በሚል ዲቁና እንዲሾሙ አድርጓል:: ከዚህ በኋላ ከአባቶች ተባርከው: ገዳሙንም ተሰናብተው ወጡ:: ነገር ግን የወጡት ወደ ዓለም ሳይሆን ራቅ ወዳለ ገዳም ነው:: የረድዕነት ዘመናቸውን ጨርሰዋልና አዲስ በሔዱበት ገዳም ወደ መደበኛው ገድል ተሸጋገሩ:: ያም ማለት በጾም: በጸሎት: በስግደት: በትሕርምት: በትሕትናና በፍቅር ሙሉ ጊዜአቸውን ማሳለፍ ጀመሩ:: በእንዲሕ ያለ ግብርም ዘመናት አለፉ:: የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ አባ ጴጥሮስ በእረኝነት ሥራ የሚያግዛቸው ሰው እንዲፈለግላቸው በጠየቁት መሠረት ትምሕርትም: ጽሕፈትም: በጐ ምግባራትም የተሟላለት ሰው እንደ አባ ድምያኖስ አልተገኘምና ያለፈቃዳቸው ወደ እስክንድርያ ተወስደው የፓትርያርኩ ረዳት ሆነው ተሾሙ:: በረዳትነት በቆዩበት ጊዜ በወንጌል አገልግሎትና በመንኖ ጥሪት ሕዝቡንና ሊቀ ጳጳሳቱን አስደስተዋል:: ልክ አባ ጴጥሮስ ሲያርፉ ሕዝቡና ሊቃውንቱ በአንድ ድምጽ አባ ድምያኖስን ለፓትርያርክነት መርጧቸዋል:: ጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት በዘመነ ፕትርክናቸው ከግል የቅድስና ሕይወታቸው ባለፈ እነዚህን ፈተናዎች በመወጣታቸው ይመሰገናሉ:: 1.ሕዝቡ ከሃይማኖታቸው እንዳይወጡና በምግባር እንዳይዝሉ ተግተው አስተምረዋል:: 2.በአካል ያልደረሱባቸውን በጦማር (በመልዕክት) አስተምረዋል:: 3.በዘመናቸው የተነሱትን መናፍቃን ተከራክረው : የተመለሰውን ተቀብለው : እንቢ ያሉትን አውግዘዋል:: 4.ከአንጾኪያ ፓትርያርክ የመጣውን የኑፋቄ ጦማር (መልዕክት) በይፋ ተቃውመው አውግዘዋል:: ለአርባ ሦስት ዓመታት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ሆነው ያገለገሉት አባ ድምያኖስ ከብዙ ትጋት በኋላ በመልካም ሽምግልና በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ከግብጽ አበው ሊቃነ ጳጳሳት ዝርዝር ውስጥም አርባ አምስተኛ ሆነው ተመዝግበዋል:: ††† ልመናቸው : ክብራቸው : ጸጋ ረድኤታቸው አይለየን:: ††† ሰኔ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አባ ድምያኖስ ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት 2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ 2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን) 3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ 4.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ ††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት : ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" ††† (ሐዋ. ፳፥፳፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/zikirekdusn
Показати все...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

ጾመ ሐዋርያት ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው  ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡ ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘለዓለማዊ ዝምድና አለው፡፡ በብሉይ ኪዳን ጾም ከፍተኛ ቦታ ነበረው፡፡ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውኃ ለአፋቸው አይገባም ነበር፡፡ ዘዳ 34፥28 በኃጢአታቸው ብዛት የመጣባቸው መዓት የሚመልሰው ቁጣውም የሚበረደው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር፡፡ዮና 3፥5-10 በአዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሣይሆን ራሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው መጀመሪያ አድርጎ የሠራው ሕግ ነው፡፡ ማቴ 4፥21 ጌታችን በስስት በፍቅረ ንዋይና በትዕቢት የሚመጣበትን ጠላት ዲያቢሎስ በጾም ድል እንድምንነሣው አሳየን፡፡ ይህም ብቻ ሣይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር ጠላት ስይጣንን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል ማቴ 17፥21 በጾም የተዋረደና ለጸሎት የተጋ ሰውነት ለእግዚአብሔር ለመታዘዝ የተዘጋጀ በመሆኑ እግዚአብሔር ያዘናል እኛም እንታዘዝለታለን፡፡ ስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ቀሳውስት የሚሾሙትም በጾምና በጸሎት ነበር፡፡ የሐዋ13፥3፤4፥25 እነ ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ያላሰቡትን ክብር ያገኙት በጾማና በጸሎት ፈጣሪያቸው ማልደው ነው  የሐዋ 10፥20 ጾም እንኳን የጠበቅነውንና ያሰብነውን ቀርቶ ያላሰብነውንና ያልጠበቅነውን ፈጽሞም የማይገባንን ጸጋና ክብር የሚየሰጥ ነው፡፡ ከሐዋርያት ቤተክርስቲያን በዓልና ትውፊት መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመጀመሪያዎቹ አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ስለሆነች የጾም ሕግና ሥርዓት አላት  እነዚህም የፈቃድና የአዋጅ አጽዋማት ይባላሉ፡፡ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ የሐዋርያት (የሰኔ) ፆም ነው፡፡ ይህም ጾም በሕዝብ ዘንድ የወታደር ጾም ይባላል፡፡ ለስብከተ ወንጌል ዘመቻ የተዘጋጀ በጾሙት ተምሣሌት በድሮ ዘመን ወታደሮች ለዘመቻ ሲነሱ ወይም ከዘመቻ ሲመለሱ በተሳተ በተገጸፈ ይቅር በለን በማለት ይጾሙት ነበር፡፡ ይህም ጾም የሚፈሰክበትከሐምሌ 5 የማይለቅ ቢሆንም የሚጀመርበት ግን  የተወሰነ ቀን የለውም በዚህም ምክንያት የጾሙ ዕለት ቁጥር ከፍና ዝቅ ይላል አንዳንድ ጊዜ ከአርባ ይበልጣል አንዳንድ ጊዜ ከ30 ያንሣል ያሁኑም ጾም ሰኔ 17 ገብቶ  ለ 2 ሳምንት  ከ 3 ቀናት ይጾማል፡፡  ይቀጥላል https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw
Показати все...
✝ ስብሐት ብጡል (ከንቱ ውዳሴ) ✝ (ክፍል ፩) ✝ በስመ ሥሉስ ቅዱስ ✝ " ስብሐት ብጡል (ከንቱ ውዳሴ) " =>አበው ሊቃውንት የከንቱ ውዳሴ ሕመም 3 ደረጃ (ምልክት) እንዳለው ይናገራሉ:: "ደረጃ 1 (ሕመሙ ሲጀምር)" ¤አንድ አገልጋይ ከሰው ምስጋናን ሽቶ ባይሠራም ሲመሰገን ልቡን ደስ ደስ ይለዋል:: ይህን ጊዜ ማረም ከተቻለ እጅጉን ቀላል ነው:: "ደረጃ 2 (ሕመሙ ሲባባስ)" ¤አገልጋዩ "አመስግኑኝ" አይልም:: ግን የሚሠራው ሁሉ መመስገንን ሲሻ ነውና ተግባሩ ሁሉ የተርዕዮ (የእዩልኝ) ይሆናል:: ሠርቶ ካልተመሰገነም ይከፋዋል:: በዚህ ጊዜም በሽታውን ለመንቀል መትጋት ከተቻለ ሊድን ይችላል:: "ደረጃ 3 (ሕመሙ ሲጸና/ሲከፋ) ¤እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው አጋንንት ሙሉ በሙሉ ስለሚቆጣጠሩት ለመመስገን ሲል ከኑፋቄና ክህደት ሁሉ ሊደስርስ ይችላል:: የማያመሰግኑትን ሰዎች ከመጥላት አልፎ ለመጉዳትም የሚያስብ ሰው ይሆናል:: በቀላሉ ይህ ሰው ለእግዚአብሔር የሚገባውን ክብር የሚመኝ በመሆኑ ተግባሩ ሁሉ ሰይጣናዊ ይሆናል:: ✝ውዳሴ ከንቱ የሚሉት በሽታ እዚህ ደረጃ ላይ ከደረሰ የመዳን ተስፋው እጅግ የመነመነ ነው:: ነገር ግን ሕመምተኛው (ውዳሴ ከንቱ የጠለፈው አገልጋይ) ችግሩን አውቆ ንስሃ ከገባና ለትህትናዊ ሕይወት ከቆረጠ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ሊድን መቻሉ የሚጠረጠር አይደለም:: ✝ስለዚህም አበው ሲመክሩ "ከሚገስጽህ እንጂ ከሚያመሰግንህ ሰው ጋር አትዋል" ይላሉ:: <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> Re. Dn Yordanos ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
Показати все...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞✝ ❖✝ እንኳን አደረሳችሁ ❖✝ ✞ ✞ ✝እንኩዋን ለሰማዕቱ #ቅዱስ_ሚናስ ዓመታዊ የቅዳሴ ቤት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ✞✝ +"+✝ #ቅዱስ_ሚናስ ምዕመን ሰማዕት +"+✝ =>ቅዱስ ሚናስ ( #ማር_ሚና ) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው:: ልክ በሃገራችን #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም:: +ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ ነው:: በተለይ ለታመመ: ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ: ባለ በጐ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው:: +ግብጽ ውስጥ ቅዱሱን የማያውቅ ሰው ካገኛችሁ እርሱ ኦርርቶዶክሳዊ አይደለም ማለት ነው ሲባልም ሰምተናል:: በነገራችን ላይ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር በመስጠት: ታሪካቸውን በመጻፍ: በማጥናት: በመጽሔት: በፊልምና በመሳሰሉት ለሕዝብ በማስተዋወቅ ግብጻውያኑ ከእኛ ብዙ ርቀት ሒደዋል:: ዛሬ እንኩዋ የምንጠቀምበትን ስንክሳር 80 ከመቶ እጁን ያዘጋጁት እነርሱ ናቸው:: +አባቶቻችንና እናቶቻችን #ኢትዮዽያውያን_ቅዱሳን ግን አብዛኞቹ ተረስተው ቀርተዋል:: መጽሐፈ ገድላቸውንም ብል በልቶታል:: ዛሬም የቤት ሥራው የእኛ ብቻ ነው:: +ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ሚናስ (ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው):- ¤በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ ¤በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ ¤በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ ¤ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ ¤በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት ሰማዕት ነው:: +እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል:: +የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ በዳ የበጐችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን አደረገ:: አንድ እረኛ በጐቹ ድውያን ሆኑበት:: በዚያ ሰሞን ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ:: +በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጐቹን አምጥቶ ነከራቸው:: እነርሱም ተፈወሱ:: ይህ ዜና በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ ገቡ:: ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ አልቻሉም:: +ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን ከሠራዊቱ ጋር ላካት:: ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና ፈውስን አጥታ ነበር:: መጥታ ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች:: +#ቅዱስ_ሚናስ በሌሊት ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች:: ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም " #መርዩጥ " ተባለ:: ጸበሉ የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ #ቤተ_ክርስቲያን ታንጾበት በዚህች ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል:: =>አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን:: =>ሰኔ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ) =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ 2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት) 3.ቅድስት እንባ መሪና 4.ቅድስት ክርስጢና =>+"+ ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይሕን እጽፍልሃለሁ:: ብዘገይ ግን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ:: ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው:: እግዚአብሔርንም የመምሠል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው:: +"+ (1ጢሞ. 3:14) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Показати все...
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን ✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11     ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥ ፆም ማለት ምንድ ነው ❓ ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥ እንኳን ለታላቁ ለሐዋርያት ጾወም በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን 📌 ፆም ❖ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ትምህርት መሰረት ጾም የማህበርና የግል ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡ ❓ ፆም ምንድ ነው ❖ ጾም ማለት ሰው ምግብ ወይም ሰውነት ከሚፈለጋቸው ነገሮች መካከል መወሰን ማለት ነው፡፡ ❖ ጾም በጥንተ ፍጥረት አትብላ ተበሎ የህግ መጠበቅም ሆኖ ለሰው ልጅ ከተሰጠው ትዕዛዝ ጾም ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ስርአት ስለሆነ ሃይማኖት በለበት ሁሉ አለ፡፡ ❖ ጾም ለተውሰነ ጊዜ ከእህልና ውሀ መከልከል ብቻ ሳይሆን ለሰውነት የሚምረውን ለማየት እና ለመፈጸም የሚያስጎመጀውን ነገር ሁሉ መፈጸም ነው፡፡ ❖ በተግባራዊ ትርጉም የተረዱና የተጠቀሙበት ሰዎች ጾምን ‹‹ለፀሎት እናቷ፣ ለእንባ መፍለቂያዋ ለበጎ ስራ ሁሉ መሰረት ›› በማለት ተርጉመውታል፡፡ 📌 የፆም አስፈላጊነት ❖ ሃይማኖት መሰረት ነው ነገር ግን ቤት በመስራት ብቻ የተሟላ እንደማይሆን ሃይማኖትንም ፍጹም የሚያደርጉት በእርሱ መሰረትነት ነው የመሚታነጹ ስነ ምግባራት ናቸው፤ ጾም፣ ጸሎት፣ ምጽዋትና ስግደትን የመሰሉት ምግባራት ሃይማኖትን እንዲሰራ ያደርጉታል፡፡ ❖ ጾም የስጋን ምኞትን እና ፈቃድን ለማስታገስ ይረዳል፡፡ 📖መዝ 34፥13፣ 📖ሮሜ 8፥12-14፣ 📖1ኛ ቆሮ 6፥12 ✍‹‹ ለሚጠፋ ምግብ አትስሩ ይልቅስ የሰው ልጅ ለሚሰጣቹህ የዘለዓለም ህይወት ለሚሆን ምግብ ስሩ›› 📖ዮሐ 6፥7 ❖ ጾም በአምሮት በምኞትና በስስት ጸባዮች ላይ የበላይነት ያስገኛል፡፡ 📌 በፆም የተጠቀሙ ሰዎች ⓵ በብሉይ ኪዳን ❖ የሰማርያው ንጉስ አክአብ 📖1ኛ ነገ 20፥27 ❖ የእስራኤል ሰዎች 📖2ኛ ዜና 20፥1-23 ❖ በጉዞ ላይ የነበሩ ሰዎች 📖ህዝ 8፥21 ❖ የነነዌ ሰዎች 📖ዮናስ 3፥3 ❖ ነብዩ ነሕምያ 📖ነህ 1፡2 ❖ ሃማ በተነሳ ጊዜ 📖አስቴር 3፡9 እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን ⓶ በሐዲስ ኪዳን ❖ በሐዲስ ኪዳን ጾም የጀመረው ክርስቶስ ነው፤ ክርስቶስ ከጾም በኋላ 3 ነገሮችን ድል ነስቷል፡፡ ❶ ስስት ❷ ትእቢት ❸ ፍቅረ ነዋይ ❖ መላእክትም ቀርበው አገልግለውታል፡፡ 📖መዝ 90፥11 ፣ 📖ማቴ 4፥1 ፣ 📖ሮሜ 14፥1-6 📌 የአዋጅና የግል ጾም ⓵ የአዋጅ ጾም ❖ በአባቶቻችን የተደነገጉ ሰባት አጽዋማት አሉ፡፡ ➘ ጾመ ነብያት ➘ ጾመ ገሃድ ➘ ጾመ ነነዌ ➘ ዓብይ ጾም ➘ ጾመ ድህነት ➘ ጾመ ሐዋርያት ➘ ጾመ ፍልሰት 📌 ጾመ ነብያት ❖ ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ይጠብቁ የነበሩ ነብያት የጾሙት ነው፤ ነብያት ስለ መሲህ መምጣት በናፍቆት ይጸልዩ ነበር፡፡ 📌 ጾመ ገሃድ ❖ ገሃድ ማለት ግልጥ ይፋ፣ በገሃድ የሚታይ ማለት ነው፡፡ ❖ መለኮት የተገለጠበት ጌታ ልዩ የሆነ የአንድነትና የሶስትነት ምሥጢር የተገለጠበት ስለሆነ ይህን ስያሜ አግኝቷል፡፡ 📖ማቴ 3፥16 📖ዮሐ 1፥29 📌 ጾመ ነነዌ ❖ ይህ የነነዌ ሰዎች የጾሙት ነው፤ የዚያች አገር ሰዎች የፈጸሙት በደል በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ሆኖ በመገኘቱ ቅጣት ታዝዞባቸው ነበር፤ የነነዌ ጾም ሰኞ፣ ማክሰኞና ዕረቡ ሶስት ቀን ነው፡፡ 📌 ዓብይ ጾም ❖ ሙሴ በሲና ተራራ ህጉን ከማቅረቡ በፊት 40 ቀን 40 ሌሊት ጾሟል፤ ጌታም ወንጌል ከመስበኩ በፊት በገዳመ ቆሮንጦስ 40 ቀን 40 ሌሊት ጾሟል፡፡ ❖ ይህ ጾም ዓብይ ወይም ሁዳዴ በመባል ይታወቃል፤ ዓብይ የሚሰኘው ዓብይ ነብያት የጾሙት በሐዲስ ኪዳንም ጌታም የኦሪተንና የነቢያትን ህግ ለመጠበቅና ለመፈጸም ሲል የጾመው በጾሙ ፍጻሜ ከሰይጣን የመጣውን ፈተና ድል የነሳበት በመሆኑ ነው፡፡ ❖ በዓብይ ጾም ሰባት ቅዳሜ ስምንት እሁድ ይገኛሉ፤ ይህም የጾሙን ጊዜ ስምንት ሳመንታት ያደርገዋል፡፡ ❖ የመጀመርያው ሳምንት ህርቃል ተብሎ ይታወቃል ወደ ጾሙ መግቢያ መለማመጃ ማለት ነው፤ የመጨረሻው ሳምንት ሕማማት ነው ክርስቶስ መከራ የተቀበለበት ቀን በመሆኑ ነው፡፡ 📌 ጾመ ሐዋርያት ❖ ጾመ ሐዋርያት ሀብተ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ወንጌልን ለሕዝብ ከማስተማራቸው አስቀድመው ጾመዋል፤ የሰኔ ጾም ይባላል፡፡ ❖ ይህ ጾም ከፍና ዝቅ ስለሚል የተወሰነ ቀን የለውም አንዳንድ ጊዜ ከአርባ ይበልጣል ሌላ ጊዜ ደግሞ ከሰላሳ ያንሳል፡፡ 📌 ጾመ ድህነት (የዕረቡና የአርብ) ❖"ከትንሳኤ በኋላ ከሚኖሩት 50 ቀኖች በቀር ዕረቡና አርብ ዓመቱን በሙሉ የጾም ቀኖች ናቸው፡፡ ❖ እንደጾሙአቸው የተደረገው አርብ እና ዕሮብ፤ ዕሮብ የተፈረደበት አርብ የተሰቀለበት ቀን መሆኑን አስመልክቶ ነው፡፡ 📌 ጾመ ፍልሰታ ❖ ጾመ ማርያም ይባላል፤ የእመቤታችን የዕረፍት፣ ትንሳኤና ዕርገት ምሥጢር ለሐዋርይት የተገለጠበት ታሪክ መታሰቢያ ጾም ነው። ❖ ሐዋርያት ከሐምሌ 1-14 ድረስ ጾመው ድንግል ማርያም ተገልጣላቸዋለች በ 16ኛው ቀን አርጋለች፡፡ ⓶ የግል ጾም ❖ በሕግ የታወቁ አጽዋማት በግልጥ በማህበር ይጾማሉ፤ የግል ጾም ግን ከዚህ የተለየ ነው። ❖ በሰዎች የግል ፍላጎትና የሕሊና ውሳኔ ሚጾም የፈቃድና የንስሐ ጾም ነው፡፡ 📖ማቴ 5፥6 📖ማቴ 6፥18 📖ዳን 6፥10 በአጠቃላይ ከላይ የተመለከትናቸው ከፍፁም ኃጢአትና ከበደል ተጠብቀን እንድንጾም አምላከ ቅዱሳና ይርዳን እንዲሁም የእናቱ የንፅህተ ንፅሀን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ጸሎት አይለየን ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 ✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ 🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ      ✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" 📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ                ወስብሐት ለእግዚአብሔር                               ይቆየን  ───────────                     Channel  🧲  https://telegram.me/Tewahedo12         FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ) 🧲  http://facebook.com/Tewahedo12           YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ) 🧲 https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw  ───────────
Показати все...
✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴

"ሥርዓትን እማር ዘንድ ያስጨነከኝ መልካም ሆነልኝ" መዝ 118 (119) ፥ 71 ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ ግሩፑ http://t.me/OrthodoxTewahedo12 ይህ Channel #ሐምሌ 26/2010 ዓ.ም አ/ጀመረ ለአስተያየት 📥 ➩ @Tewahedo12_bot

Авторизуйтеся та отримайте доступ до детальної інформації

Ми відкриємо вам ці скарби після авторизації. Обіцяємо, це швидко!